Friday, December 31, 2021

የአማራ ሰቆቃና የአማራ ምሁራን ቸልተኛነት ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 12/31/2021

 

የአማራ ሰቆቃና የአማራ ምሁራን ቸልተኛነት

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY 12/31/2021

መጀመሪያ ይህንን ካርቱን ላዘጋጀው ሰው አመሰግአለሁ።

ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ የተባሉ የአማራ ተወላጅ ስለ ወያኔ የሚያቀርቡት ሙግታቸው ሁሉ የረቀቀ የበሰለ ነው። ይመቹኝ ነበር። ሆኖም ምሁር ዋለልኝ መኮንን ፍልስፍና “ዛሬም” በማመጎሳቸው አጭር የፎቶ ተቃውሞ የለጠፈ አንድ ፌስቡክ ስመለከት፤ የአማራ ሰቆቃ ጉልህ ሆኖ ዓይናቸው ላይ ተገትሮ እያዩት ባሉበት ወቅትም “ብዙዎቹ የአማራ ምሁራን” ለምን እንዲገባቸው እንዳልቻለ እንቆቅልሽ ነው።ዋለልኝ መኮንን “በንጉሡ ዘመን ስራ ፈላጊ ሕዝብ የአማራ ስም ካልያዘ ሥራ አንደማይሰጠው” ዋሽቷል።

ነፍጠኛ እያለ የሚጠራው አማራን  “በምግብ፤ በሻማ አስለባሽነት፤ አማርኛ ሙዚቃ አስፋፊነት”  እያለ አማራን በማይገባ ወንጀሏል። ሌላም ሌላም።

ያ ጦስ ያቀጣጠለው እስካሁን ድረስ አማራው “ተጠቂ” ሆኗል። የ27 አመት ጥቃት በዝምታ አልፈውት ስንጮህባቸው ዛሬ ይነሱ ይሆን ብለን ስንመለከት፤ ይባስ ብሎ ጸረ አማራ የሆነውን “አብይ አሕመድን” መሪየ እየሉ አንዳንዶቹ በአማካሪነት አንዳንዶቹ በጀሌነት ሲያሞግሱት እያየሁ ለመገረሜ ገለጻ ቃላት አጥሮኛል።

ካሁን በፊት አማራዎች በጉምዝ ሰዎች ተገድለው ሥጋቸው ተቀቅሎ እየተበላ ነው ብለን ዜናውን ስናስተጋባ “አማራ” ነን የሚሉ አንዳንድ የኢሕአፓ አባላት “እኔን እና አቶ ተክሌ የሻውን” የጉምዝ ሕዝባችን እና ኢትዮጵያ እንዲም የአፍሪካ ሕዝብ ስም በፈረንጅ እና በዓለም ፊት ስማችንን ለማጥፋት ያደረጋችሁት ሴራ ነው፤ በማለት ቃላት እስኪያጡ ድረስ የራቸው ስደብ ሳይቀረ ሙልጭ አድርገውናል።

ታስታወሱ እንደሆነ “የአመቱ ባለጌ ሰው” በሚል የተቸሁት አለምነው መኮንን የተባለ

አማራው ተጠቃ ስንል “አማራ ተናጋሪ” እንጂ ኣማራ የሚባልየብእዴኑ ምክትል ሓላፊ የነበረ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ አማራውን “አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ በስንፋጭ ትምክሕት የታጀለ መርዝ ንግግሩን እስካሁን ድረስ ማቆም ያልቻለ፤ትምክህት እየተመገበ ያደገ፤……” እያለ አማረውን መሳደፉ ታስታውሳላችሁ።

ሌላም ላስታውሳችሁ “አማራ የሚባል ማሕበረሰብ የለም” የሚሉ እራሳቸው “አማራ” የሆኑት ፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም “አማራ የሚባል የለም” እያሉ ሲከራከሩን ያንን ሳያምኑበት ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። በትንተና አንጻር ስንመለከት እውነታ ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። ማለትም ኢትዮጵያዊያን በደም የመሰበጣጠራችን ውሁድነት አንጻር ማለቴ ነው።  አሁን እየታየ ባለበት አማራዎች ተለይተው በሚጠቁበት ወቅት ግን ክርክራቸው መሰረተ ቢስ ነበር።

ከላይ የጠቀስኳቸው ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ የተባሉት ምን  ዋለልኝ እያሞገሱ ስለ አማራ ምን እንዳሉ በዝርዝር ባላገኝም ይህ  “አማራ የለም የሚለው ያላስተዋለ ክርክር እና ግራ ዘመም ፖለቲከኞ ዋለልኝ የአማራ እና ኢትዬጵያዊ ቤዛ ነው” የሚል ችግር ያለበት ፖለቲካዊ ክርክር፤ ያውም አክራሪ ነገዶች የሚጠቀሙበት ችግር ላንዴና ለመጨረሻ መቆም እንዳለበት ይታየኛል።

አማራ ምሁራን ዛሬም ከዚያ እንዝህላልነት ያልወጡ ስላሉ ዛሬም ጉዳዩ ማንሳት ያስፈልጋል።

የካሁን በፊት አማራ ምሁራን ችግር አንዱ እንደምሳሌ የፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ታሪክ ላስታውሳችሁና  ሎቻችሁ አማራ ምሁራን ከዚህ እንድትማሩ ስንከራከርበት የነበረው የፕሮፌሰሩ አቋም መማርያ እንዲሆን እነሆ፤

 ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም፦

«ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ 2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120 ላይ እንዲህ ብለዋል። 

ኅዳር 1951 ዓም ከአጼ ኃይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ባለሥልጣኖች ባሰራጨሁት የጥናት ጽሑፍ ስለኦጋዴን የሚከተለውን ብየ ነበር። «በጠቅላላው የአማሮቹና የሱማሌዎቹ ግንኙነት ላስተዋለው፣ አማራዎቹ የሚያሳዩት የበላይነት መንፈስና በሱማሌዎቹ ላይ ያላቸው ንቀት፤ ሱማሌዎቹ በበኩላቸው ያላቸው ኩራት በአማራዎቹ ንቀት እየተነካባቸው የሚሰማቸው ስሜት በአንዴ ይታወቃል። ``ቆሻሻ ሱማሌ``በያለበት የሚሰማ ነው። በዕድሜም ሆነ በክብር ከፍ ያሉትን ሱማሌዎች እርሰዎ እያለ የሚያነጋግራቸው በቁጥር ነው።---እንደዚህ ዓይነቱ የሌለውንየአማራ የበላይነትና የሱማሌ የበታችነት በግልጽም በድብቅም የሚያሳይ መንፈስ የሱማሌዎቹን ልብ በጣም እንደሚያሞክረው የሚያጠራጥር አይደለም። ሱማሌዎቹ ልክ እንደአማራዎቹ መሆናቸውን ሁሉ የተገነዘቡት አይመስሉም፤ ሱማሌዎቹም ሁሉ የሚውቁት አይደለም።……”

( መስፍን /ማርያም «ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ 2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120)

መጽሐፉ ካላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

በወቅቱ እኔም ሆንኩኝ “የምጽአተ ዐማራ መጽሐፍ ደራሲ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው” በወቅቱ ይህንን ተቃውመን ለየግላችን ፕሮፌሰሩን ተችተናቸዋል። በወቅቱ እኔ ያልኩት

“ እንግዲህ ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ይህ ግፍ ሲፈጸም በመጽሐፍዎ የዘገቡት በመረጃ ያልተረጋገጠ አማራውን የመወንጀል ዘመቻዎ በአገራችን የነበረው የተለመደ ዕርስ በርስ የመሰዳደብ ልምድ አማራውን ብቻ እንደሚናገረውና እንደሚሳድበብ አአድርገው  ነጥለው “ለአማራ መስጠትዎ” ያሳዩን/ ወይንም እርስዎ ያደረጉት የተደገፈ ጥናት የለም። ባልሰሩት ጥናት በዘፈቀደ ተነስተው አማራው በሶማሊ ተወላጆች ላይ ዘለፋ ያደርግ ነበር ማለትዎ ካንድ ምሁር የሚጠበቅ ጽሑፍ አልነበረም።

ያስ እንደ እምነትዎ እንቀበለው፡ ሆኖም በ1951 ዓ.ም አማራ የሚባል ማሕበረሰብ እንደነበር ለመጥፎ ነገር ሲጠቀሙበት በቅርቡ ግን “አማራ የሚባል ማሕበረሰብ” የለም ሲሉ “ነበር” ያሉት አማራ ፡ዛሬ ወይም ከ1951 ዓ.ም በላ ወዴት ተሰወረ? ምን በላው?

ይህንን ተንተርሰው ሰበቡ የአካባቢው የአካባቢው አክራሪ እስላሞች በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ የተቀነባባረ ጥቃት ልክ አንደ እነ “የወያኔው ም/ጠ/ሚኒስትር “ታምራት ላይኔ” ንግግር ለዛሬው ግፍ የእርስዎ ምስክርነት ተጨማሪ ብትር አላቀበልኩም ሊሉ ይችላሉ?” ብየ ጽፌ ነበር። 

የሆነውንም ለማሳየት አንድ ምሳሌ አቅርቤ ነበር። በሕይወት የሌለው ዋለልኝ ስለ አማራው እንዲህ አጣምሞ ተማሪውን ሲቀሰቅስ፤ በሕይወት የሚገኙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሶማሌ “ክልል” ውስጥ አማራዎች እንጂ ትግሬዎች ጠላታችን አይደሉም እያሉ የክልሉ አስተዳዳሪዎች በግልጽ ለመናገር የበቁት ፕሮፌሰሩ አስተዋጽኦ የለበትም ማለት ይቻላል?  ብየ ነበር።

በዚህ የተነሳ፡ይህንን አንብቡ

በአገራችን  አቆጣጠርበ2006 (በፈረንጅ 2014) በጅግጅጋ (ጅጅጋ) የሚኖሩ አማራዎች ወደ ኢሳት ቲ/ቪ እና ራዲዮ ጣቢያ የተላከው ደብዳቤ እና የስልክ ጥሪ መልዕክት ላስታውሳችሁ፡ እንዲህ ይላል፤

 “ ቤታችን እየተነጠቅን ለጎዳና ተዳዳሪነት ተጋልጠናል። እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ የነበሩት የአማራዎች ዋና ዋና የንግድ ተቋማትን እየተነጠቁ ለሶማሌ ተወላጆች እያስረከቡ ስለተደረገ አብዛኛዎቻችን ከተማውን እየለቀቅን ወደ መሃል አገር ሄደናል። ተወልደን ያደግንበትን አገራችን አንለቅም ያሉትንም ፌደራላዊ ጫናዎች እየተደረጉ ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ በደብዳቤና በቃል ትዕዛዝ ተነግሯቸዋል።

የአንድ ቤሔር የበላይነት በሰፈነበት መልኩ “አማራ ወይንም ሐበሻ” የሚል መጠሪያ ተደርጎልን፤ እነሆ ከህጻናት እስከ ትልቅ በመንገድ በቢሮም እየተሰደብን መኖራችነን ሳያንስ፤ አሁን ደግሞ ያለምንም ልዋጭ ቤቶቻችን ተቀምተን ሜዳ ላይ ተጥለን እንገኛለን። የኛ ልጆች አንደልብ መንገድ ላይ መሄድ አይችሉም፤ ሱሩ የለበሰች ሴት ‘አማራ ነች’ እየተባለ በፖሊስ በዱላ ትደበደባለች። ማንፖሊስ ማን ሃላፊ እንደሆነ በማናውቀው ሁኔታ የ “ሸሪዓ ፍርድ ቤት” ተቋቁሞ ቤቶቻችን እንድንለቅ እየተደረገ ነው። ተወልድን ባደግንበት አገር አንደ ሁለተኛ ዜጋ እንደ ቆሻሻ እየታየን ነው” ብለዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማዋ ኗሪ በከተማዋ የመኖር ስሜታቸው እየተሟጠጠ መሄዱ ደግሞ በስልክ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።

“በዚህ አካባቢ የመኖር ስሜታችን ተሟጥዋል። ያፈራነውን ያለንን ነገር ለቀቅቀን ለመውጣት እየተዘጋጀን ነው። ሰላሳ እና አርባ አመት እና ከዚያም አመታት በላይ የኖርክብትን ቦታ ለቅቀህ ስትሄድ ዝም ብለህ ወፍ አይደለህ፤ በርረህ አትሄድም። አንዳንድ ያፈራሃቸው

ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ልጆች ይኖራሉ..አንዳንድ ንብረቶች ይኖሩሃል… እነሱን ጥለህ አትሄድም፤ አጋጣሚና ዕድል ይገኝ እንደሆነ ብለን፤ አንዳንዶቻችን ያንን እንደምንም ብለን እያስተካከልን ብለን ነው እስካሁን እየተንገዳገድን ያለነው። የወደፊት በዚህ ከታማ የመኖሩ ተስፋ እንኳን እንጃ!..እንጃ!” 

ሲሉ አማራዎች እንደ ሶማሌ እስላም “ሸሪዓ ፍርድ ቤት” ቀርበው ንብረታቸው እያስረከቡ ወደ አገራችሁ ሂዱ እየተባሉ እንዲባረሩ ሲወሰንባቸው; ልጃገረዶች ልጆቻቸውም “ሱሪ” ታጥቃ ስትሄድ

አንደ ሳውዲ አረቢያ “ሰፋጢን” ተብለው በሚጠሩ የሃይማኖት ፖሊሶች “አማራ/ሐበሻ” እየተባሉ በዱላ ይደበደቡ እንደነበር አማራዎች በጅጅጋ የደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ሲፈጸም ዛሬም ብዙዎቹ አማራ ምሁራን እና “የኪነት/አክቲቪስት/” የሆኑ አማራዎች ከዚያ ጥቃት ሳይማሩ ዛሬም ያንን ጥቃት በሰፊው እየተካሄደ ባለበት ወቅት “ ይህንን ጥቃት ማቆም ያልፈለገው “በአብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ መንግሥት” ደጋፊዎች ሆነው ማየት እጅግ ፤ እጅግ ከፍተኛ በሽታ ነው።

በዚህ አጋጣሚ በርትተው አልበገርም ብለው ለሕዝባቸው የቆሙ “አማራ” ምሁራን ምስጋና ይገባቸዋል። እንደዚህ ስል ግን ቅጥ ባራ ስሜት ገንፍለው ፋሺሰትንት ለመከተል ያማራቸው ዘፋኞች፤ገጣሚዎች  እና ‘የፌስ ቡክ አርበኞች’ ወደ አክራሪ አማራነት እየተበራከቱ ስለመጡ አማራን ልክ እንደ ትግሬ ማሕበረሰብ ከማድረጋቸው በፊት ትኩረት ይደረግ እላለሁ።

እኔ ያለኝን ኢትዮጵያዊ ድርሻየ አድርጌአለሁ፤ ጽሑፉን ማሰራጨት ግን የናንተ ተራ ነው።

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

እስኪ በዩ ቱብ ስዕለ ድምፁን በዓይናችሁ እና በጆሮአችሁ እነሆ

አድምጡ።

TPLF puppet Somali president secret video exposed TPLFs hate against Amhara May 8 2013

https://youtu.be/Kj2sNJ5B2j0