ኢትዮጵያ ሠራዊት ወይንስ የአብይ ወታደር?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
7/3/2021
ባለፈው ክፍል 1 ጽሑፌ “አመድ ልሳ እንደተነሳችው እንደ “ፎኒክስዋ ወፍችሁ ‘ዳግም ልደታችሁ” ለማየት በማዕቀብ ፈተና እንዲፈትናችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ እጠይቃለሁ!” የሚል እንደተነጋገርን በክፍል ሁለት እንደሚቀጥል ነበር ያቆምነው። ክፍል 2 በሰፊው በሚቀጥሉት ቀናቶች እንመለከተዋለን ላሁኑ ግን ኢትዮጵያ ሠራዊት ወይንስ የአብይ ወታደር የሚለው እንመለከታለን።
ለሁላችሁም ግልጽ እንዲሆንላችሁ ‘በወያኔ ቀያሺነት የተመራው የትግራዋይነት
የነገድ ፖለቲካና መረን የለቀቀ የነገድ ፍቅር” ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ተብለው ሲሞገሱ የነበሩ እንደ እነ ቴድሮስ ጸጋየ ሳይቀር
እጅግ በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያን ጦር “የአብይ አሕመድ ጦር” እያለ ሲጠራ ወያኔ ጦር የሚያይበት ትንታኔ ግን “የትግራይ መከላከያ
ጦር” በሚል ስም “የትግራይ ሕዝብ ጦር” ሲል ያሞካሻቸዋል። በኔ በኩል ወያኔዎች የሚመሩት ጦር የትግራይ ሕዝብ ከሆነም ችግር የለኝም።
ምክንያቱም ወያኔ ማለት የትግራይ ሕዝብ ነው። እኔ እና ርዕዮት ሚዲያ ልዩነታችን የኢትዮጵያን ጦር የሚጠራው “የአብይ ወታደር”
በሚል በንቀት ሲሆን እኔ ግን ኢትዮጵያ ወታደር ነው እላለሁ። ያውም ቴድሮስ “ወራሪ” ነው የሚለው።
ወራሪ ጦር ማለት “ኮሎናይዘር” ቅኝ ገዢ ማለት ነው። እኔ ልክ እንደ ቴድሮስ ጸጋየ አብይን እቃወማለሁ። ግን አብይ የትግራይን ሕዝብ ሂዱና አጥፉት፤ ዝረፉት ሴቶችን ድፈሩ ብሎ እንደ ናዚ ወታደር ትዕዛዝ አስተላልፎ ሴቶችን አስደፍሯል፤ ለዚህ ደግሞ ትግራይን ስለሚጠላ የሚለው እውነታ ቢኖሮውም። ይበልጥኑ አብይ ከትግሬ ይልቅ አማራን ይጠላል ብትሉኝ እቀበላለሁ። ማስረጃወም ብዙ ብዙ ቢሆንም ፡ “ነፍጠኛ” እያለ እንደ አለቆቹ ወያኔዎች የሚገልጽበት ‘አውድዮ’ አለ። አማራ ጦር እንዳያደራጅ የሰራው ብዙ ነገር አለ። የወሎ ንግግሩን አንዱ ማስረጃ ያዙልኝ። ከዚያም አሳምነውን እንዴት እንዳጠፋው ሌላው የአማራው ጥላቻው ነው። ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል።
አብይ “ዓጋሜ፤ ወይንም “ቅማላም ትግሬ” ሲል ሰምቼው አላውቅም። እንደ ዕድል/ አጋጣሚ/
ለወደፊቱ አብይ ነገ ትግሬ ሴት ቢያገባ “አማቻችን” ብለው እንደ ጎንደሬዎቹ ይመርጡታል።
ወደ ሗላ ልውሰዳችሁ።መለስ ለኤርትራ የነበረው ፍቅር አብይ ለትግራይ ተመሳሳይ ፍቅር አለው። በጦርነት ግን በጥቃት ምክንያት መለስ ከሻዕቢያ ጋር አብይ ከወያኔ ጋር ተጋጭተዋል። አብይ ከመጀመሪያውኑ የወያኔ መሪዎችን ፋታ ሳትሰጥ ይዘህ ለፍርድ አቅርብ ፤ሗላ ሰበብ ያመጣሉ ስንለው ለእነ ስዩም መስፍንን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትርነትህን ልስጥህ እያለ ሲተሻሽ “ፍቅሩ ስላልጨረሰ “አክሱም እና መቀሌ” ድረስ እየሄደ ሲሽኮረመምና ሲያሽቀብጥ ፤ሰራዊታችን ለጥቃት አጋልጦ ሰጣቸው።” እውነታው ይህ ነው።
ቴድሮስ ጸጋዬ “ይህንን ምስኪን
ሰራዊት “እምሽክ ብሎ ደቅቆ ተዋርዶ እስኪበቃው “መቀጥቀጡ” እጅግ ደስ ብሎኛል! ረክቻለሁ! እፎይታ ነው! ይላል ማይክሮፎኑ እስኪንቀጠቀጥ።
የቴድሮስ ጸጋየ ንግግር ካመጥኩ በሗላ፤ ኒው ዮርክ ታይምስ በቪዲዮ የዘገበው ዘገባ ማየት አንጀት ያቃጥላል። ኒው ዮርክ ታይምስ
የተባለ የዜና ማሰራጫ በሺዎች የሚቆጠሩ የተማረኩ ወታደሮች ወያኔ መቀሌ ከተማ ፒያሳ ላይ ሻዕቢያ በ1983 አስመራ ከተማ እንዳደረገው
በኩታራ ታጣቂ ወያኔዎች ግራና ቀኝ ታጅበው ሕዝቡና ህጻናት ሳይቀሩ እየተገረሙ “እያንጨበጨኑ እያሾፉባቸው” ማየት አንጀት ያቃጥላል።
አማራ ወታደሮች እያለ ሻዕቢያ በ1983 ዓ.ም አስመራ ኮምቢሽታቶ ሲያዞራቸው የነበው ወታደሮቻችን ዛሬ በድጋሚ ትግራኤኢ መቀሌ ውስጥ
በሚገርም ጣሊያናዊ ትዕይንት በትግሬዎች ተደገመ። (ያው የተረከሉት ሃውልታቸው ሳንረሳ መለቴ ነው)
ይህ ብቻ አይደለም አሳዛኙ
ትርኢት። ቁስለኞች በወታደሮቹ ወሳንሳ /ቃሬዛ/ ተሸክመዋቸው በፕያሳ
እንዲዞሩ መደረጉ ጣሊያን ያላደረገው በትግሬዎች መደረጉ የሚገርም ነው። ሙርከኛ ምን አለበት ቤት ወይንም ት/ቤት/ክሊኒክ/ካልተቻለ
ጥላ ስር፤ ህንጻ እንዲያርፉ እና ስቃያቸው እንዲችሉ ቢደረግ ምናለበት? ቁስለኛን በቃሬዛ ሕዝብ እንዲያያቸው እና ህጻናት ፒያሳ
ላይ እንዲሳለቁባቸው ማድረግ? ለምን? ያውም “ቁስለኛ” ስቃይ ውስጥ ያለን ሰው በቃሬዛ ለትዕይነት? ጣሊያን በየት መጣ ያሰኛል?
የሙርከኛ አያያዝ የሚመጻደቅበት ወያኔ ስቃይ ላይ ያለው ቁስለኛ ምን እየሆነ እንዳለ እያየ ይሆን?
የወያኔ ሰራዊት ትግራይን ተቆጣጥሮ፤ ዘረፋ፤ የሴቶች አመጽ፤ ግድያ… ሳይታይ
፤ ትግራይን በእፎይታ ተኝታለች ወደ እሚል ቅዠት እያንጸባረቀ ያለው ቴዲ በስቃይ የሚያቃስቱ ወታደሮቭ በቃሬዛ መቀሌ ፒያሳ ሲያዞርዋቸው
ቢያይ ኖሮ ምን ይል ነበር ይሆን? በጥይት የተመታ ደም እያፈሰሰ ስቃይ ላይ ያለን ሙርከኛ? በስመ አብ!!
የወያኔ ጭካኔ ለከት የለውም።
ወያኔ የሰሜን ዕዝ ጦር ወታደሮች ከነ ህጻናት ልጆቻቸው ማርኮ በየበረሃው ሲያንከራትታቸው ነበር ፎቶውንም ስዕለ ድምጹንም ከመነሻው
ማስረጃ ለጥፌዋለሁ። ይህን ተመልከቱ ንባቡን ስትጨርሱ።
የመኖር ተስፋን የቀጠለው ህፃን
- በሰሜን እዝ
https://youtu.be/vUU8yIyPePo
ትንሽ እየተበሳጨሁ ስለሆነ
ቻሉኝ። ወደ ርዕሱ ልመልሳችሁ። ቴድሮስ ይህንን ልጅ ብያይ ምን ይሰማው ይሆን?
አሁን ከዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሁኔታ
ቴድሮስ እሰየው አረፍን! ብሎ እያለ ያለው፤ ወያኔ ወደ መቀሌ ሲገባ እነዚያ እየታፈኑ ያሉት የአሲምበባ እና አውራጃ ከተሞችና ገጠሮች፤
የግጀት እስላሞች፤ ንብረታቸው የተዘረፈ፤እየተቃጠለ፤ በወያኔ አፋኝ
ቡድን እየተገደሉ ያሉ ሰለማዊ ሰዎች፤ ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ታፍነው ያሉ ተማሪዎች፤ ግን ለቴድሮስ የተሰማው እፎይታው ይህ ይመስለኛል።
በሚገርም አባባሉ ዛሬ የሰማሁት “ትግራይ ውስጥ እጅግ ሰላማዊ ኑሮ እንዳለ ተነግሮኛል ይላል።
በሌሎች ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት የራሴ የታላቅዋ እህታችን ልጅ “ተምቤን “ወርቅ
ኣመባ ውስጥ” በአይሮፕላን/ድሮን መገደሉን ገልጫለሁ። ሌሎቹ ዘመዶቼም በጣም ቆላ በሚባል አስቸጋሪ የጦርነት ቦታዎች ስለሚኖሩ ይሙቱ
ይኑሩ አላውቅም። ስለዚህ “የሰላማዊ ትግሬዎች በደል አይሰማህም የሚሉኝ እና እነሱ ብቸኛ ትግሬዎች ሆነው የሚዘላብዱት ርቀት ዛሬም
እየገረመኝ ነው።
አንዳንዳንድ ስድ የወያኔ ባለጌዎች እማ ከነሱ በፊት የተወለድኩባት እትብቴን
የተቀበረባት፤ያደግኩባት የወላጆቼ አፈር እና መሬት ገጠርና መንደር እየሄዱ ከራያ ገስግሰው እነ ጌታቸው ረዳ የሚሸሸጉበት አውራጃ
እና መንደር የማን መንደር መሆኑን ሳያውቁ “ወያኔን ስለተቃወምኩኝ “አንተ አማራ” ነህ “ትግሬ አይደለህም” እያሉ የነገድ ምስክር
ወረቀት ሰጪዎች ሆነው ሳያቸው እስቃለሁ። ስልክ ቢኖረኝ ገጠር ያሉ ዘመዶቼን ደውዬ፤ ወያኔዎች ሸሽተው መጠለያ ሲጠይቅዋችሁና ቁራሽ
እንጀራ ሲለምንዋችሁ’ “እናንተ ማን ትባላለችሁ?” ብላችሁ ጠይቁልኝ እላቸው ነበር። የወያኔ ጀሌዎች ድፍረት ይገርመኛል!
ግፍ ተፈጸመ የሚባለው እስኪ
ይጣራ። በፕሮፖጋንዳ መንጫጫት ጋብ አድርገን ሰከን እንበል፤፡ ግን ደረሰ የተባለው ግፍ “ለምን?” እንዴት?” ማን?” የሚለው ለወደፊቱ
መጣራት ያለበት ነገር ነው። የተገደሉ የትግራይ ንጹሃን ሰዎች የተደፈሩ ሴቶች በሰራዊቱ ከተፈጸመ ወይንም በዱሩየዎች ወይንም በወያኔ
ተዋጊዎች “የፈጸሙት ሰዎች” በሕግ መጠየቅ አለባቸው። በዚህ ምንም ልዩነት የለንም።
ከዚህ ውጭ እንግዲህ ይህ ቀጥቅጦ
አዋርዶ አስወጣው እያለ ደስታውን እየገለጸ ያለው ቴድሮስ ጸጋዬ ደስታውን የሚገልጽላቸው የሽምቅ ተዋጊ መሪዎች ግን እነማን ናቸው?
ለምንስ የነሱ ሓጢያት ሊገልጸው አልቻለም? የሚል ነው እኔ የምጠይቀው። እስካሁን ድረስ ለ7 ወር ያህል ፕሮግራሙ የወያኔን ወንጀል
ገሸሽ እያለ የአብይ ጦር የሚለውን ወታደር ጉንጩ እስኪደክም ድረስ በየቀኑ የሚቀጠቅጠው ወታደሩን ብቻ ነው። ስድቡ በኩንታል ነው። ለምን?
አሁን በዳቦ ስም እየተጠሩ
እየተሞካሹ ያሉት መሪዎቹ ቴድሮስም ሆነ እኛ የምናውቃቸው “የሰሜን ታሊባኖቹ” በወንጀል የተጨማለቁ ፤ የወያኔ መሪዎች ናቸው ወይስ
ሌሎች ፍጡራን? አደለም እንዴ? የነሱ ወንጀል እንዴት እንዳልፈጸሙ እንዴት በዝምታ ይታለፋል? የአገር መከላከያ የሚያክል ሚሳይሎች
ሁሉ ሲነጥቁና እንቅልፍ ተኝተው “በግሪደርና በጭነት መኪና” በላያቸው ላይ የተካሄደባቸው የአገሪቷ ምስኪን ወታደሮች ማን ነው የፈጸመባቸው?
የትግራይ መከላከያ ጦር ተብሎ በማሞካሸት የተጠራው “የወያኔ ጦር” ነው ወይስ የማናውቀው ጦር አለ?
የ 6 አመት ህጻን ልጅ የያዘ ወታደር አስገድደው ከነ ልጁ ወደ በረሃ ማርከው
ሲያሰቃዩት አላየንም? ማን ነው ይህንን ጭካኔ የፈጸመው? ወያኔ ወይስ ““ሰራዊት ምልክኻል ትግራይ”? ለመሆኑ ይህ ስም በማን ዕዝ
የሚታዘዝ ጦር ነው? ንገረን እሰኪ? በወያኔ ነው። አደለም እንዴ?
ይህ ጦር ለትገራይ ምን ግፍ
እንደ ሰራ እንዴት ተዘነጋ? አምበጣ ሲከላከል እና ከደሞዙ ቀንጭቦ ትምህርትና ሕክምና ሲገነባላቸው፤ እርሻ ሲኮተኩትን የትግራይ
ገበሬን ሲያግዝ “የአብይ ወታደር” ተብሎ ሲጠራ ነበር ወይስ “የኢትዮጵያ ጦር”? የነ አስመላሽ ዘሞ (አባዲ ዘሞ) እግር ሲያጥብ’
ውሃ ሲያጣቸው አላየንም? እንዴት ነው ነገሩ። ደጉን በደግነቱ ወንጀለኛንም ለይተን በወንጀሉ እንናገር እንጂ? በሓሽሽ ጭስ ሱስ
ጦዞ “ከንፈሩ” የደረቀ ውሃ የጠማው የወያኔ ታጣቂ ወጣት “ተዋጊ” ውሃ ሲያጠጡት አላየንም? አብይ ለጦር መሪነት ብቁ እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ጦሩ ግን ለምን የግለ ሰብ
ጦር ተብሎ ይጠራል?
ዛሬ ግን የቴድሮስ ጸጋዬ “ሠራዊት ምክልኻል ትግራይ” ቁስለኛ እና ሬሳ ሲያዞሩ ጣሊያን
የማረኩ ይመስል፡ ወታደሮችን ለትርዒት መቀሌ ከተማ ላይ አንደከብት እየነዱ ሲኩራሩ እያሳዩ ጥላቻን ሲያጎለብቱ አይተናል ። ጊዜ እንጂ ሰው አሸናፊ እንዳልሆነ ዛሬም አልተማሩም (ፋሺሰት በአሸናፊነትና
ተሸናፊነት ስለሚያምንወ መማር አያወቅም)። አሁን በቃ! የት እንደምትሄዱ አይተናል። እኔ ከ45 በፊት አካሄዳችሁ አውቃዋለሁ፤ ሌሎቹ
ኣላወቁዋችሁም። ለዚህ ነው እየተጃጃሉ እስከዚህ ድረስ የፈረሱት!
ለመሆኑ አብይ ወታደር የምትላቸው
‘ነገ አብይ ከሥልጣን ሲሰናበት’ ወደቤቱ ይዟቸው ይሄዳል ወይስ የቴድሮስ ጸጋየ “ታሊባን መሳዮቹ የወያነ ታጁሮች የሚገዙት ሊሆን
ነው? እየተስተዋለ እንጂ!! ትግሬ የሚኖሮው ለማንም አይደለም ለኢትዮጵያ ሲልም አይደለም” ለራሱ ሲል ነው። ይሻለኛል ካለ ይሂድ፤
ግን ልክ እንደ ኤርትራኖቹ ትግራይ ለግላችን ኢትዮጵያ የግላችን የሚለው የ27 ኢትዮጵያን ጡት እየጠቡ እየመጠጡ ሊፈቀድ አይቻልም።በቃ!
በጣም፤በጣም በዛ!! ወያኔ ኢትዮጵያዊ ሆኖም ፤ ኖሮም ፤አድርጎትም፤ አያውቅም። ስለዚህ ማስፈራራታችሁ ይቁም! ማንም ለማንም ጥቅም
ሲል አይደለም አብሮነት የመረጠው፤ ለራሱ ሲል ነው!
አንተ ቴድሮስ ጸጋየ የተናገርከው
አነጋገር የሰማሁህ ግን የሚገርም ነው። “ትግራይ ብትገነጠል፤ መስጊዱ ክርሰትናው፤ ሃይማኖቱ ሁሉ አብሮ ወደ ትግራይ እንደሚሄድ
እና አገራችን ያለ ትግሬ ሃይማኖት አልባ እና ታሪክ አልባና ፤ቅርስ አልባ” ሆና እንደምትቀር የምትደሰኩረው “ትዕቢት” ማዕቀብ
ያስፈልገዋል። ትግሬ እንደማንኛውም አስተዋጽኦ አድርጓል፡ አክሱም የትግሬ ብቻ ነው ያለህ ማን ነው? በየትኛው ታሪክ? ትግሬ ሲጠቃ
ሌሎቹ ስለ ትግሬ ደማቸው ሰጥተው ሞተዋል። እንዴት ነው ይህ ትዕቢት!? ይብቃኝ መሰለኝ፤ እጅግ ተቆጣሁ!
ሼር አድርጉት~!!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ