Friday, July 19, 2019

ከትግሬዎች ወደ ኦሮሞዎች የተዘዋወረው የዋሺንግተኑ ኤምባሲ እና ለጀኔራል አሳምነው ጽጌ ልጆች ሊውል የታሰበው የ "ጐ ፋንድ ሚ" እገዳ ጉዳይ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ከትግሬዎች ወደ ኦሮሞዎች የተዘዋወረው የዋሺንግተኑ ኤምባሲ እና ለጀኔራል አሳምነው ጽጌ  ልጆች ሊውል የታሰበው የ "ጐ ፋንድ ሚ" እገዳ ጉዳይ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
Abey Ahmed the OLF insider
እንደምን አላችሁ? እንደትወያዩባቸው ሁለት ርዕሶች ይዤላችሁ መጥቻለሁ።

(1)- ለ27 አመት በትግሬ ወያኔዎች ቁጥጥር ሥር የነበረው የዋሽንግተን ኤምባሲ ትናንት የ ኦሆዴድኦነግ ኦሮሞዎች የተተኩበትን ትዕይንት እንመለከታለን።

(2)- በቅርቡ ባሕር ዳር ውስጥ “በአዴፓ” (ብኣዴን) ባለሥልጣናት የተከሰተው የመገዳደል ቅንቆቅልሽ ምክንያት ከዚህ ዓለም ለተለዩት ለጀኔራል አሳምነው ጽጌ ታዳጊ ልጆቻቸው ሊውል ታስቦ የተዘጋጀ ነበር የተባለው “የ ጐ ፋንድ ሚ” ዕርዳታ “በኢትዮጵያ ስም የሚጠራው” ዋሺንግተን ውስጥ የሚገኘው ኦሮሞዎች የተቆጣጠሩት አምባሲ በ(ኢሕአዴግ ኤምባሲ) ውትወታ (ኮመፕለይንት/ክስ) ምክንያት ስለመታገዱ ጉዳይ እንመለከታለን።

በተራቁጥር 1 የተጠቀሰው ርዕስ እንጀምር።

ትናንትና በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር በሐምሌ 18/2019 በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሐምሌ 11/2011 ኢትዮጵያ ኤምባሲ ተብሎ በሚጠራው በአፓርታይድ ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች ስርዓት የሚተዳዳር አምባሲ ህንጻ ፊት ለፊት ባለ አደራ ተብሎ በሚጠራው “የሲቪክ ማሕበር” እና ሌሎች ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የተቀላቀሉበት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር።

በአንጻሩ ደግሞ ‘ሰላማዊውን ሰልፍ የተቃወሙት’ በቁጥር ከ10 (አስር) የማይሞሉ እጅግ ጥቂት የሆኑ የ “ኦ ኤል ኤፍ/ኦፒዲኦ” ጀሌዎች ነበሩ። አስገራሚ የሚያደርገው የቁጥራቸው መጠን ማነስ ሳይሆን ለ27 አመት ትግሬዎች ልክ እንደ የግል ቤታቸው አድርገው በመቁጠር ሲቆሙበት በነበረው በኤምባሲ ደጃፍ ላይ ዛሬ በምትካቸው ቦታቸውን የወሰዱት ኦሮሞወቹ ከአምባሲው በር ላይ ቆመው የኢትዮጵያን ሕብር የያዘ ሰንደቃላማ ቀዳድደው ከስሩ የኦነግ ባንዴራ አያይዘውበት አንዲት ወጣት በሰንደቃለማው ቀዳዳ ክፍል እራስዋን አስገብታ “ፖለቲካዊ ምስጢር” ያለበት ትዕይንት ስታሳይ ደጋግሞ የታየ ቪዲዮ እጅግ የሚገርም አሳፋሪ ትዕይነት ነበር።

በኦነጉ ጀሌ የሚመራው አምባሰደር ተብየው “አምባሳደር ፍጹም አረጋ” ኤምባሲ ጽ/ቤት ደጃፉ በር ላይ ቆመው ኦነጎቹ ይህንን አሳፋሪ ትዕይንት ሲያሳዩ ‘ቆሜለታለሁ ብሎ ለሚዋሸው የአገሪቱ ሰነደቅ’ ክብር እንደሌለው ያየንበት ታሪክ ነበር። ይህ ደግሞ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩዋት ማሳያ ነው።

እጅግ የገረመኝ ግን ታስታውሱ እንደሆነ ለ27 አመት ትግሬዎች ሲቆሙባት በነበረችበት ኤምባሲ በር ላይ ቆመው “ማሃል ጣታቸውን” እያሳዩ ተቃዋሚውን በብልግና ሲሳደቡባት በነበረቺበት በር ላይ ቆመው ዛሬ በተራቸው ኦሮሞዎቹ ኤምባሲው ያለምንም ይሉኝታ የነሱ መሆኑን በኩራት እየጮኹ መፈክር ሲያስተጋቡ ማየት የአፓርታይድ መንግሥት  ክፉ ባሕሪ ምንኛ ክፉ እንደሆነ ከመገረም አልፌ የብስጭት መገረም አሳድሮብኛል።

መለስ ዜናዊን የተካው አዲሱ ባንዳው አብይ አሕመድ ኦሮሞ ጀሌዎቹን አምባሳደር እያደረገ፤ ቁጫጭ ጀሌዎቹም በኤምባሲው ደጃፍ ላይ ቆመው በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ የተገዛው ኤምባሲ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ለሚቀዳድዱ ዋልጌ ኦሮሞ ጀሌዎቹ መፈንጪያ ማድረጉ ለ27 አመት የታየው የትግሬዎች አፓርታይድ ስርዓት የኦሮሞ ሄጂመኒ “አፓርታይድ” ስርዓቱን በመተካት ታሪክ እራሱን እንደደገመ ማየት ትችላላችሁ።

ለዚህ ነበር ደግሜ ደጋግሜ ለበርካታ አመታት ኦሮሞዎች አፓርታይድ ስርዓቱን ከወያኔ ትግሬዎች ተረክበው በከፋ መልኩ ሊተኩት ነው እያልኩኝ ሳስጠነቅቅ የነበረው። ሰሚ ግን አልነበረም ። ምክንያቱም አሽቃባጭ ምሁር በማይሆን ስራ ተጠምዶ ስለነበር።
ዛሬም ምሁሩ ከማሽቃበጥ ባሕሪው አልተላቀቀም። እንዳውም ብሶበታል።

 ነባሮቹ በአዳዲስ አጫፋሪ ምሁራን ተተክተው ለኦነጎቹ ስርዓት ማጎብደድ ጀምረዋል። ከነዚህ መሃል የፈረንጆች “ጀሮ ጠቢ/ተቀጣሪ አባል” ነው ተብሎ የሚታማው ወያኔ አባርሮት የነበረው አብይ ደሞዘዙን ከፍሎ እንደገና ወደ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ መምህርነቱ የተመለሰው አሳፋሪው ቡሃቃው ወሎየው “ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ” ልክ እንደ እህቱ ገነት (ጉዲት) እና እንደ የገዛ ውንድሙ የወያኔው ዋና አሽቃባጭ የነበረው “ገናናው አሰፋ” ዳኛቸውም እነሱን ተክቶ ለባንዳው አብይ አሕመድ ሲያሽቃብጥ መስማት የሚገርም ታሪከኛ ጊዜ ነው። በዚህ ሰፋ ባለ ሁኔታ እምለስበታለሁ።
ወደ 2ኛው ርዕስ ወደ ጀኔራሉ አሳምነው ጽጌ ጎ ፋንድ ሚ እገዳ ልግባ።
የእርዳታው ማሰባሰብ ያቀደው ሄኖክ የሺ ጥላ መሆኑን ከዚህ በታች ያለውን በእንግሊዝኛ የተጻፈ የእገዳው ተቃውሞ ፌርማ ማሰባሰቢያ ደብዳቤ (ፔቲሽን) ያሰረዳል። አንዲህ ይላል።

am writing this letter asking you to sign the  petition form  in response  to the current compliant by the EPRD/TPLF regime on my Go Fund me fund raiser, which was insolently reported by the government affiliated human right violation gangs.

The goal is to enable my Go Fund me again.  I will then attach the petion sign form to the Go Fund me to justify my claim.
Thanks,
Henoke Yeshetlla

ይላል። ይህንን ስመለከት ለእገዳው ዋናው አቤቱታ አቅራቢ ሆኖ የቀረበው የአብይ መንግሥት መሆኑን ይገልጻል። እዚህ ላይ ልትቃወሙም ልትደግፉም የዜጎች መብት ነው። ጥያቀው ግን ‘መንግሥት ተብየው በያንዳንዳችን ዜጎች ኪስ ውስጥ ገብቶ ለምናደርገው እርዳታ የመቆጣጠር ሥልጣን ማን ሰጠው? ማን ለማን ፤ምን ለምን መስጥተ እንዳለብን ሥልጣኑ ማን ሰጠው? የሚገርም ነው!!!!!

ይህ እርዳታ ደግሞ አባታቸው ድንገት ላጡ ለጀኔራሉ ህጻናት ታዳጊ ወጠቶች የሚውል እርዳታ ነው ይላል። እንዴት አንድ መንግሥት ነኝ የሚል በአንድ አመት ውስጥ ወደ ባሰ አራዊታዊ አፓርታይድ ስርዓት ተለውጦ የአብይ አሕመድ መንግሥት ለህጻናት መረዳጃ የሚውል የገንዘብ ዕርዳታ እንዳይሰባሰብ እጁን አስገብቶ በጣም ወደ የወረደ አሳፋሪ ስራ መግባት ቻለ? ስራ የለውም?

ባንዳው አብይ አሕመድ እንደ ባንዳው መለስ ዜናዊ ዛሬ “ቢቀነጠስ” በበጎ ተነሳሽነት ተነስተው ለልጆቹ መርጃ የሚሆን እርዳታ ገንዘብ ቢጠየቅ አብይን የሚተካ ስርዓት መጥቶ “ፔቲሽኑን” ቢቃወም የአብይ ልጆችም ሆኑ ባለቤቱ ምን ይሰማቸዋል? እንዴት መንግሥት የሚያክል ትልቅ ድርጅት በዜጎች ኪስ ብርባራ እና ቊጥጥር ውስጥ መግባት ቻለ?

ይህ አሳፋሪ የባንዳዎች ስብስብ ስርዓት በእጅጉ ወደ ዝቅጠት እየወረደ መምጣቱ ባያስገርመኝም፤ ወደ እንዲህ ያለ በጣም የወረደ “ስራ ፈት ወደ ሆነ መንግሥት” ይለወጣል ተብሎ ግን የሚገመት አልነበረም። ለማንኛውም አፓርታይዱ የኦሮሞዎቹ ስርዓት ከዜጎች ኪስ ብርበራና እና ቁጥጥር እጁን ያንሳ እንላለን! አያገባውም!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)