Thursday, May 5, 2016

በኢትዮጵያ ሰማይ ድረ-ገጽ አዘጋጅ የተመረጡ የዓመቱ የፋሲካ ምርጥ ኢትዮጵያውያን! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)



 በኢትዮጵያ ሰማይ ድረ-ገጽ አዘጋጅ የተመረጡ የዓመቱ የፋሲካ ምርጥ ኢትዮጵያውያን!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
ለዐውዳመት በዓል “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት የአባት በመሆኑ ለዚህ ለ2008ዓ.ም የኢየሱስ ክርቶስ የትንሣዔ በዓል እንኳን አደረሳችሁ የምላችሁ በዚህርዓት ግፍ ምክንያት በሞት የተለዩንን ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምርልን፣ በሕይወት ያለነውም አብረንሞትን ያህል እንቆጠራለንና እኛም ትንሣዔያችንን እየተጠባበቅን ስለሆነ እንዲያፋጥንልን በመመኘት ነው። ለነፃነት ዘመን እንዲያበቃን ወደ ኢትዮጵያ ሰማይ ጸሎቴን አቀርባለሁ።


የተመረጡት 10 ድንቅ ኢትዮጵያውያን እነሆከዚህ በታች ያሉት ናቸው፡- (My apology for those whom I can't find their photo)
በፎቶግራፋቸው ቅደም ተከተል መሠረት -
(1)-የሐረር ወርቅ ጋሻው
(2)-ዶ/ር አበባ ፈቃደ
(3)-ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ
(4)-ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ (ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል)
(5)- ዶ/ር ማንከልክሎት ኃይለ ሥላሤ
(6)- ክቡር አቶ ተክሌ የሻው 
(7) አቶ ግርማ በቀለ
(8)-ዶ/ር ተስፋዬ ደምመላሽ
(9)- አቶ ተድላ አስፋው (የኒውዮርኩ ኗሪ)

(10) “ይነጋል በላቸው” (ስለ ይነጋል ከታች በሰፊው ተገልጿል)

ይነጋል በላቸው በአብዛኛው በዘሃበሻ፣ኢትዮላዮን፣ ደብተራው፣ ኢትዮ-ሚ ዲያና መሰል ድረገፆች ዘወትር የሚጽፍ ማራኪ ጸሐፊና አንዱ የሀገራችን የክፉ ቀን አለኝታ ነው። ይነጋል በላቸው፤ ገና ወያኔዎችና ሻዕቢያዎች ትከሻ ለትከሻ እየተሻሹ ኢትዮጵያን ሲያንበረክኩና ሲገዙ፤ በታዋቂው መጽሔት “ጦቢያ” ላይ ትችቱና ሰፊ የታሪክ ትንተና እና የሲአይኤ እና የውስጥ  ተቀጣሪ አርበኞቹ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ሲያደርሱት የነበረውን ጉዳት በመግለጽ ሰፊ ትንተና በመስጠት ነበር የታዋቂ ብዕሩን ትሩፋት ያካፈለን።  ወዳጄ ይነጋል፤ ፎቶግራፉን ማስተዋወቅ ከደኅንነት አንጻር አሁን አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘሁት፤ ከመቃብር ተነስተን ትንሣዔያችንን ስናረጋግጥ ማንነቱ ያኔ እራሱ ያስተዋውቀናል። እስከዚያው ድረስ ከዚህ በታች የሚ ገኘው ን የራሴን ዕይታ ከገለጽኩኝ በኋላ ይነጋል በላቸው ስለ ወያኔ ትግራይ ምንነትና ስለ እኔ የጻፈውንና ይሁንታው ን ሰጥቶኝ በመጽሐፌ ሽፋን ውስጥ  ማሳረግያ ሆኖ እንዲታተም ያረግሁትን ጽሑፍ አስነብባችኋለሁ።
  

እነዚህ ምሁራን የላቀ ትኩረት ያደረግሁባቸው ምክንያት፤ አማራው ኅብረተሰብ በኦነግ፤ በወያኔና በመሳሰሉ ጸረ አማራ  ኃይላት ለ25 ዓመት ተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስበት፤ በትውልድ አማራ የሆኑ፣ ነገር ግን የአማራን ኅብረተሰብ ስቃይ ሊሰሙ የማይፈልጉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪው ዓለም የሚኖሩ ‹አማራ ነን የሚሉ›  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አሉ። አሳዛኝና አስገራሚ ሆኖ ያገኘሁት ጉዳይ ደግሞ አማራውን ከጥቃት ለመከላከልና ስለ አማራ እሪታችውን ለማሰማት በሚሞክሩ ጥቂት ምሁራን ላይ ከፍተኛ ዘለፋ ሲያስጋቡባቸው፤ እነዚህ ምርጥ ዜጎች ከየአቅጣጫው የሚሰነዘርባቸውን ዘለፋና ውርደት እየተጋፈጡ የአማራን ሰቆቃና መከራ ለዓለምና ለሕዘባችን ሲያስተምሩ ቆይተዋል፤ ለዚህ ታሪካዊ ተግባራቸውም የግል አድናቆትና ምስጋናየን አቀርብላቸዋለሁ። በታሪክ ሥፍራም ስማቸው የሚነሳ ግዙፍ ምሁራን ናቸውና እናንተ ሃቀኛ ዜጎችና ውድ የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አንባቢዎች አብራችሁ አክብሮታችሁን አንድትለግሱዋቸው በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው ነገር የአማራው ጉዳይ በጥቂት ታጋዮች ብርታት አሁን አሁን “ቀልብ” (ትኩረት) እየሳበ ቢመጣም ተገቢውን ሽፋን ዛሬም ሊያገኝ እንዳልቻለ መረዳ ይገባል። እንደሚታወቀው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር አዳባባዮች ስለ ጋምቤላ ማኅበረሰብ መጨፍጨፍ፣ ስለ ኢትዮጵያውያን በሊቢያ አክራሪዎች መታረድ፣ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ዐመፅ፣ በኦጋዴን ማኅበረሰብ ላይ ስለደረሰ ጥቃት … ወዘተ. የሻማ መብራትረሃብ ዐድማ፣ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የኮንግረስ አቤቱታ፣ ወዘተ..ወዘተ… ያለ ማቋረጥ በስፋት ሲደረግና ችግሩ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ በዓለም ሚዲያ ሲስተጋባ “የአማራው ስቃይ” ግን አሁንም ተገቢውን ሽፋን ባለማግኘቱ ጥቃቱ ሊቆም ቀርቶ በረድ ሊል እንኳን አልቻለም። ስለዚህም ከመቼውም በበለጠ የወልቃይት (የጎንደር)፣ የወሎ፣ የጎጃም፣ የሸዋና በሌላው ክፍለ ሀገር ነዋሪ የሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠር በየእሥር ቤቱ ታጉሮ ድብደባ፣ ስድብና እንግልት እየደረሰበት ያለው የአማራ ማኅበረሰብ  ዛሬም ድምጹን እንድናሰማለት የአቤቱታ ጥሪውን እያቀረበ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ የሲቪክ ድርጅት የሆነውን የሞረሽ ወጣትና አዛውንት መሪዎችንና ደጋፊ አባሎችን ጨምሮ ሌሎች ቅን ዜጎች ለምታደርጉት ትግል ብርታቱን እንዲሰጣችሁና ትግላችሁ ፍሬ እንዲያፈራ ፈጣሪን እለምናለሁ።

የአማራው ጉዳይ እጅግ እጅግ አንጀቴን ይበላኛል። ለምን? የሚል ጠያቂ ሊኖር ይችላል። አንድ አብነት ልስጥ። አማራ ናቸው የሚባልላቸው፣ ከእዛው ማኅበረሰብና ክ/ሀገር የተገኙ እንደ እነ ታማኝ በየነ የመሳሰሉ ታዋቂ ወገኖቻችን ስለ አማራ ኅብረተሰብ ሰቆቃ ግንዛቤያቸው አነስተኛ መሆኑን በአንድ ምሣሌ ላሳያችሁ። በወልቃይት አማራዎች ላይ ወያኔ በረሃ ከወጣበት ዘመን ጅምሮ በአማራ ላይ ሲደርስ የነበረው የዘር ማጽዳትና ስቃይ ወያኔን በንቃት ስንከታተል የነበርን ዜጎች በተቻለ መጠን ከወልቃይት ተወላጆች መረጃዎች እየሰበስብን ጉዳዩን ስንከታተል እንደነበር ቀደም ብዬ ገልጫለሁ፡፡ እንደነ ታማኝ በየነ የመሳሰሉ ለአካባቢው ቅርብ የሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ግን ስለ ወልቃይት ሕዝብ ስቃይ፣ሞት፣መፈናቀል፣ መሰደድ፣ ዐመጽና ውርደት የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያለ አንዳች ሀፍረት ሲናገሩ እንሰማለን፡፡ ”ታማኝ” አውስትራሊያ አገር “ለኢሳት” (?) ጉዳይ በሄደበት ወቅት ሰዎች ከወልቃይት አባቶች ጋር አገናኝተውት መሰለኝ/ወይንም ሰዎቹ እራሳቸው ፈልገው አነጋግረውት/ “ቃለ መጠይቅ ሲያደርግላቸው” በውይይቱ ውስጥ “እኔ እስካሁን ድረስ ወልቃይቶች እንዲህ ያለ ግፍ እንደተፈጸመባችሁ አላወቅሁም ነበር” ብሎ ሲናገር ማመን አቅቶኝ ክው! ብየ ነበር የቀረሁት።

 የአማራ ኅብረተሰብ ማሕጸን እንዲህ ያለ የመድረክ ታዋቂ ሰው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያበረክት፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያገለግል የተበረከተ ይህ  ሁለገብ ችሎታ ያለው “ፈጣን አርቲስት”፣ ተመልሶ የወለደውን ማሕጸን “እሪታ” ሳያዳምጥ መቆየቱን ስንሰማ መገረማችን አይቀርም፡፡ ይህ የወልቃይቶች የዘመናት ሰቆቃ እንደባዕድ ነገር “አዲስ ዜና” ሆኖበት ሲገረም ላደመጣችሁ አድማጮች ምን ያህል ስሜት አንደሚፈጥርባችሁ ሳልገምት አልቀረሁም (እንደኔ ከተሰማችሁ ማለቴ ነው)። 
ይህን ክስተት እንደምሣሌ ልገልጽላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት፣ አማራው በራሱ ልጆች ምን ያህል እንደተረሳ ለማስታወስ ነው። በየፖለቲካ ፓርቲው ድርጅት እየመሩ ሻማ የሚያበሩ ስብሰባ የሚጠሩ መሪዎችና ተከታዮች አብዛኛዎቹ አማራ ናቸው። የገዛ ማኅበረሰባቸውን ግን ዞር ብለው ስቃዩን ሊያስተጋቡለትና ሊያነሳሱት አልቻሉም። አስገራሚው ደግሞ ስለ አማራ መጮህ ሲነሳ ወይንም ሲጻፍ “ስለ አማራ ነገድ ሰቆቃ መናገር፣ መደራጀት… ማለት ወያኔን መሆን ነው” እያሉ ጩኸቱ እንዳይሰማ የሚያግዱና ግምባር ቀደም ሆነው እንቅፋት የሚሆኑ፣ እንደዚሁም የአደራጆችንና የጯኺዎችን ስም እያጎድፉ የሚገኙት እራሳቸው ከአማራ ማኅበረሰብ ተገኘን የሚሉን ወገኖች መሆናቸው አማራውን ከተጣለበት ወያኔያዊ የጥፋት ውርጅብኝ ለማዳን የሚደረገውን ትግል እጅግ የከበደና ውስብስብ አድርጎታል። የኢሳት ጋዜጠኛው ፋሲል የኔአለም የተባለ በተለይ አማራውን በሚመለከት እጅግ የወረደ ግንዛቤ ያለው ግለሰብና እሱን መሰል የሚዲያ ሰዎች ለአማራ ያላቸውን ሸካራ አመለካከት ሳልገልጽ ማለፍ አልፈልግም።
ስለ አማራ በመጮኼ ወዳጄ የሆነች አንዲት የአማራ ነገድ ማኅበረሰብ አባል “አንተ ማን ወክሎህ ነው ስለ አማራ የምትጮኸው!?” ያለቺኝ ምንጊዜም አይረሳኝም። ጥልቅ ሁኔታው ስላልገባት አልተቀየምኳትም፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፤ ለጊዜው አይጠቅመንም እንጂ ይህን የሚመስሉ በርከት ያሉ አጋጣሚዎችን ማስታወስ እችላለሁ። ብርቱካን ሚደቅሳ ከብርሃኑ ጋር ስትዞር ትግሬዎች ወደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ስብሰባዎች የማይመጡበትን ምክንያት ስትገልጽ “የተከፉ መሆናቸውን ሰምቻለሁ”  “ስለሆነም በራሴና በድርጅቴ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ስትል ትግሬዎች ከኢትዮጵያዊነት ስብሰባ የማይገኙበት ምክንያት (ትግሬዎች “አኼባ አምሓሩ/የአማራዎች ስብሰባ ወይንም የተሸነፉ የደርጎች ስብሰባ የሚሉት ማለት ነው) በራሳቸው ጠባብ እምነት ሣይሆን ራሳቸውን የሚያገልሉት “እኛ ስላስቀየምናቸው ነው” የሚል በማወቅ ይሁን ባለማወቅ የውሸትና የተዛባ ትምህርት ሲነሰነስ ነበር። ይህ ሁሉ ሲጠቃለል በዳዩ እንደ ተበዳይ፣ ተበዳዩ እንደ በዳይ እየተደረገ የሎሌነት አጸያፊ ተግባር በስፋት በመካሄዱም ጭምር ኅብረተሰቡ ስለ አማራ መጠቃት በቂ ግንዛቤ አንዳይኖረው ከባድ ጫና ተፈጥሯል።

ደጋግሜ ለብዙ ዓመታት ከነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ምርጥ ምሁራን ጋር ሆኜ እንደገለጽኩት አማራው ኅብረተሰብ እጅግ ቻይና ወንድማማችነትን በፅኑ የሚያከብር፣  በትዕግስት ረዢም ርቀት የሚጓዝ ኅብረተሰብ በመሆኑ ትዕግስቱና ፍቅር ፈላጊነቱ እጅግ ሲያስጠቃው በማየቴ “አማራው” በተማሩ ልጆቹ የተከዳ ማሕበረሰብ ነው” በሚል ሰፊ ትንተና እየጻፍኩ መቆየቴ ይታወቃል፡፡ (አስገራሚው ነገር እስካሁን ድረስ አማራ ዘፋኞች ስለ ኤርትራዊያን ናፍቆታቸውንና ወንድማማችነታቸውን ደጋግመው በስፋት ሲገልጹ አማራ ምሁራንም “ኢሣያስ ለአማራ ኅብረተስበ ወዳጅና አሳቢ ነው” እያሉ ባደባባይ ሽንጣቸውን ገትረው መሞገታቸውን ስታደምጡ፣ አማራው ምሁር ምን ያህል እንደተጃጃለ ይገባችኋል፡፡ የአማራውን ገበሬና ማኅበረስብ በዝምታው ላይ ተጨማሪ የዝምታ የሚያሰፍን ትምህርት እየሰጡ፣ “ጅቦች” ሚዳቋን/የሜዳ ፍየልን ከብበው በአሰቃቂ ሁኔታ ቦጫጭቀው ሰውነቷን ሲገነጣጥሏት “ጩኸት እንደማታሰማ” ሁሉ፣ አማራውም ሲጠቃ በባሕሪያዊው ቻይነቱ ላይ ተጨማሪ “ሰው ሰራሽ ዝምታ” ስለጫኑበት፣ እየተጠቃም ቢሆን አጥቂዎቹን እንዴት አንደሚፈርጃቸው ጨንቆት ግራ እንዲጋባ አድርገውታል።

አማርኛ የሚናገሩና አማራ የሚመስሉ ግን አማራ ያልሆኑ የግንቦት 7 አባላት እንደነ ደ/ር ፈቃደ ሽዋቀና (በራሱ አንደበት ኃይሉ ሻውልን እንዲዘልፍ ተፈቅዶለት ኢሳት ውስጥ ከሲሳይ አጌና ጋር ውይይት ሲያደርግ “ብዙ ሰው አማራ እየመሰለው አማራ ነው ይለኛል፤ ግን አይደለሁም….” ሲል የተናገረውን ልብ ይሏል፤ ለነገሩ በአማራነት መፈረጅ ያን ያህል ሆድ የሚያስብስ መሆን አልነበረበትም)፡፡ “ወያኔ ጠላት አይደለም” የሚሉትን እንደነ ፈቃደና እንደነ ብርሃኑ ነጋ የመሳሰሉ ግራ የገባቸው “ዋዣቂ” ምሁራን (በቪኦኤ ላይ የተናገረውን በጊዜው አስደምጫችኋለሁ) አማራው አጥቂውን በወዳጅነት ዓይን እንዲመለከት ብዙ ተጽዕኖ አድርገውበታል። ስለሆነም ነው አጥቂዎቹን በ‹ወንድምነት› እንዲመለከታቸው ዛሬም ‹ወንድማማቾች ነን› የሚል ዘፈን እየተዘፈነ እስኪሰለች ድረስ እያስተማሩት የሚገኙት። ሁሉም መጠን አለው፤ መድሓኒትም ማርም ሲበዛ ጥሩ አይደለም - እስከመግደልም ሊደርስ ይችላል፤ ይመርራል!ይጎመዝዛል!ያስጠላል! ያንገሸግሻል፡፡ ለዚህም ነው በብሂላችን “ማርም ሲበዛ ይመራል” የሚባለው፡፡

የምሁራን መዋዠቅና ቅዠት ማቆሚያው የት ነው? አማራው ገበሬ ከነቤተሰቡ ለምንድነው ከቻይነቱ ላይ ተጨማሪ ብትር እንዲወርድብት የተፈረደበት? ለምንድነው ነው አማራው እንዲህ እስኪሆን፣ የሚወርድበትንም ግፍና በደልም አይተን እንዳላየን እንድንሆን “ዝም በሉ” የምንባለው? ከምሥራቅ ወለጋ ባንድ ፀሐይ/ጀምበር 12 ሺህ አማራ ከየመንደሩ በጠመንጃ እየተገፋ ተባሯል! በሣምንቱ ሬሳ በሬሳ እየተሸጋገሩ አጥቂዎቹ እንደገና በሁለተኛው ዙር 6 ሺ አማራዎች እየተለቀሙ ከየገጠሩ እንዲባረሩ ተደረገ። የሞተ የቆሰለው ብዛት ማንም ሊቆጥረውና ሊቀብረውም እንዳልሞከረ በወቅቱ የደረሱት ዜናዎች ያብራራሉ።
ይህ እንግዲህ “ሀ” ብሎ ጥቃቱ ሲጀምር ከላይ የሚታየው ፎቶግራፍ ነበር በዓይናችን እንድናይ የተደረገው። ከዚያ በኋላ የተከተለው’ የሩዋንዳን ታሪክ ያስንቃል። ቤተ ክርስቲያናትና ገዳማት ሲቃጠሉ፣ “የአማራ ቤተ ጸሎት የአማርኛ ቋንቋ ማዳበሪያና የአማራዎች መሸሸጊያ ነው” በሚል ነው ሲወድሙ የነበሩት። እስላሞች መስጊዶቻቸው ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ለትንኮሳ ሲሉ ደጀ ሰላም/በሩ ፊት ላይ ነበር ሲያንጹ የነበረው። ይህ ሁሉ በአማራው ላይ ያነጣጠረ ነበር።
ይህ ሁሉ በደል ሲፈጸምበት የትግሬ ብሔረተኞች በደስታ ሰክረው “በቁስሉ ላይ ጨው ነሰነሱበት”።፡ ስለሆነም ነው ልጆቹ ከድተውት ዐይቼ ከዛው ቁጭቴ የተነሳ “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” የሚል ጸረ-አማራ ለሆነው የታወቀው ፋሺስት፣ ትምክሕተኛና ዘረኛ ለሆነው ለወያኔው ደቀ መዝሙር ለ“መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ” መልስ የጻፍኩት።
 ያን መጽሐፍ ለመጻፍ የተነሳሁበትና ያጠናቀቅኩበት ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ነበር። መጽሐፉን እንዳነበው የተሰጠኝ ከወዳጄ ከእንጂኔር አበበ ኃይሉ (ሳንሆዜ ኢትዮጵያ ራዲዩ ዳይሬክተር) ነበር። መጽሐፉን ሳነብበው እጅግ ነበር ሰላም የነሳኝ። በዚያች ሌሊት እንቅልፍ አልመጣ ብሎኝ ሳስብ ስጨነቅ ነበር ያደርኩት። ለንደቴ መነሻ የሆነኝ “ገብረ ኪዳን ደስታ” የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሤራ ከትናንት እስከ ዛሬ” የሚለውን ጸረ አማራ መጽሐፍ ሲጽፍ፤ አማራ ነን የሚሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምሁራን እና ሊቃውንት ምላሽ ሳይሰጡ መቅረታቸው ነበር እጅግ አበሳጭቶኝ “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” የሚለውን መጽሐፌን ለመጻፍ የተነሳሁት። ያ ሁሉ ሲሆን  እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ምርጥ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እና እዚህ ያልጠቀስኳቸው በጣም ጥቂት የሆኑ ሰብአዊያን ብቻ ስለ አማራው ስቃይ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል። ልዩ የሚያደርገውም ይህ ጥቂትነትና በጣም ፈታኝ የሆነ ቁርጠኝነታቸው በመሆኑ ነው ትኩረቴን ሊስበው የቻለው። ስለዚም ፋሲካው የደስታና የሰላም እንዲሆንላቸው ከነቤተሰቦቻቸው በድጋሚ እመኝላችኋለሁ።
ወደ ይነጋል ትንተና ይዣችሁ ከመሄዴ በፊት አንድ ነገር ልበል። ስለ አማራው በተበታተነ ዘርፍ የበኩላቸውን የሚያደርጉ ዜጎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እነሱን አልረሳሁም፤ ግን በቂ አይደለም ነው የኔ አጣቃላይ እሮሮ። ስለሆነም ለተረሳውና አላግባባብ በደል ለደረሰበት ጠበቃም ላጣው አማራ ወገናችን ካልቆምን ይህ ማኅበረሰብ ተቆጥቶ በሚያደርሰው ያልተገራ አጸፋ አገሪቷ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ምሁራን ካሁኑ ዓይናቸሁን ወደ እዚህ ማኅበረሰብ ብታተኩሩ ከጥፋት እንድናለን። ልብ አድርጉ! “ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ” ይባላልና መጠንቀቅ ከወዲሁ ነው፡፡ የፈሰሰ አይታፈስም፡፡ እንዲህ የምልበት ምክንያት አለኝ፡

በምሳሌ ላስረዳ። ይነጋል በላቸው እንዲህ ይላል፡
አህያ በመሠረቱ ጅብን አያሸንፍም ተብሎ ነው የሚታሰበው፤ ትምክህታዊ አስተሳሰብ ሊሆን ይችል ይሆናል እንደአካሄድ፡፡ የሆነ ሆኖ አሸንፎ የማያውቅ ማሸነፉ ያለ ነውጠንቁ ግን ከባድ ነው፡፡ አህያ ጅብን ማንቁርቱን ይዞ ገደለው እንበልትናንትና ማታ። ዛሬ ጧት ላይ ሰዎች ደርሰው አህያውን ከጅቡ ሬሣ እናላቅቃለን ቢሉ በጭራሽ አይሆንም። ልዩ ዘዴን መጠቀም አለባቸው፡፡ አህያው መግደሉን አያምንም፤ብለቀው ተነስቶ ይቆረጣጥመኛልብሎ ነው እሚያምን፡፡ ስለዚህ ብልህ ሰዎች በዘዴ አህያውን በገመድ ያሥራሉበቀላል ከማይነቀል ግንድ ወይም ወደመሬት በተቀበቀበ እንጨት ላይ። ከዚያ በጋለ ብረት አፉን ይለመጥጡታል ወይም እንደምንም መንጋጭላውን በእንጨት ይፈለቅቁታል፡፡ ያኔ ሩጫውን ያቀልጠዋል፤ ካልታሠረ መቆም የለምገደል ገብቶ ነው እሚሞት፡፡ ለዚህም ነው ታዲያን በገመድ ወይ በጠፍር ከግንዲላ ጋር መታሠር ያለበት፡፡ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ማሸነፉን ከማያውቅ ገገማ አሸናፊ ይሠውራችሁ፡፡ ጥሩ አሸናፊ ያሸነፈውን ሰው በወዳጅነት ቀረቤታ ይይዝና ግጭትን አስወግዶ ለመልካም ነገር ይበረታል፤ ተሸናፊውም እንደተሸነፈ ባለመቁጠር በይቅርታና በሰላማዊ መወቃቀስም ቂሙን ከልቡ አውጥቶ ጥሎ ከአሸናፊው ጋር ለጋራ ብልፅግና በጋራ ይሠለፋሉ፡፡ ይሄ ዓይነቱ ጤናማ መሸናነፍ ውብ ነው፡፡ ሁለቱም አግኝተውበታልና።” ይላል። 

 ይነጋል በዚህ አላቆመም ከታች መደምደሚያውን አንድታነቡት እጠቁማችኋለሁ።

እስከ ዚያው የኔን ታሪክ ላውጋችሁ። በአማራው ላይ ያነጣጠረው ባለ ብዙ ዘርፍ ጥቃት ትኩረት አግኝቶ ልብ አልተባለለትም። ከሩዋንዳ በላይ ዕልቂት ተፈጽሞበታል ባልኩኝ ቁጥር ትግሬዎች እና አማራዎች እንዲሁም ኦሮሞች በኔ ላይ ሲያውርዱት የነበረው የስድብ ማዕበል አስገርሞኝ “የዳመናው አገር” (ደም መና) የሚለው ግጥም መግጠሜን ታስታውሳላችሁ። መጽሐፌ ላይ ታትሟል። ተቃዋሚዎችም ሆነ ወያኔዎች በኔ ላይ ያልዘመቱት የዘመቻ ዓይነት  አልነበረም። አይጋፎረም የተባለው ወያኔን አገልጋይ ድረገጽ   በቅንጅት ወቅት እንዲህ ያለ ዘረኛ ማስታወቂያ በካርቱን መልክ
አውጥቶብኝ ነበር፤

 ወዳጄ ይነጋል በላቸውም እንዲህ ሲል ገልጾታል። በመጽሐፌ የጀርባ ሽፋን ላይም ይህን ጽሑፍ አትሜዋለሁ። እንዲህ ሲል ይጀምራል፦
“ሰው ከመሬት ተነስቶትግሬ ነኝሲል ትሰማለህየምታውቀው አማራ ወይም ኦሮሞ፡፡ ነገሩ ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ዓይነት መሆኑ ነው፡፡
 
በሃይማኖቱም ይሄው ነው፡፡ አማራ ከሆንክ የሚያስቀርብህ የለም፤ ብትቀርብም በከፍተኛ የስለላ መረብ ውስጥ ትገባና እስትንፋስህ ሁሉ በየቀኑ ትለካለች።”

         እዚህ ላይ ወያኔ ሳይሆኑ እንደኛው በተለያዩ ሥጋዊና መንፈሳዊ ችግሮች ውስጥ እያለፉ ያሉት ትግራዉያን ወገኖቻችን እኛ ትግሬ ባለመሆናችንና ኢትዮጵያዊነት ይሻለናል በማለታችን ምክንያት በገዛ ሀገራችን የምንሳደደውን ወገኖቻቸውን በመንፈስም ይሁን በተጨባጭ የትግል አጋርነት መቀላቀላቸው የግዴታ ግዴታቸው እንጂ የውዴታ ግዴታቸው እንዳልሆነ በበኩሌ ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ አንድ ትግርኛ ተናጋሪ ለምሳሌ እንደ ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጲያንሰማይ ድረገፅ አዘጋጅ) ዓይነቱ ለኢትዮጵያዊነቱ ፍጹም ሟችና የድርሻውን እየተወጣ ያለ ዜጋ ለኔ ለይነጋል በላቸው ብሎ ሳይሆን ለገዛ የጋራ እናቱ ብሎ የሚታገል መሆኑን በሙሉ ልቤ አምናለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነትን በደስታ ጊዜ የሚይዙት በመከራ ጊዜ ደግሞ የሚለቁት የትርፍ ሰዓት መዘናጊያ እንዳልሆነና ለኢትዮጵያዊነት የመታገልን ተፈጥሮኣዊ ግን በኩራት የማያንጠባርር ዕጣ ፋንታ ሰጪና ተቀባይ የለም እያልኩ ነው ባጭሩ፡፡ የአሁኑን ከንቱ ዘመን አያድርገውና ትግራይ እኮ ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዊት ነበረች፡፡ እስከማስታውሰው ድረስ ከማንም ሌላ ኢትዮጵያዊ ሕዝብ በተለዬ፣ አስከሬን በኢትዮጵያ ባንዴራ ተሸፍኖና መጽሐፍ ቅዱስ ራስጌው ላይ ተቀምጦ ወደ መቃብር የሚሄድባት ክፍለ ሀገር ትግራይ ብቻ ነበረች፤ የአሁኑን ግን አታስዋሹኝ አላውቅም - ደግሞም ሳለ ወያኔ ለውጥ መኖሩ አይቀርም ባይ ነኝ፡፡
 
ዛሬ ታዲያ ምን ገባብንና ልዩነት ተፈጠረ? አሁንማ የዲያቢሎስ ምሣር የሆነው ወያኔ ተሰነቀረብንና እንዲህ ሆንን፡- አዲስ አበባ ላይ ባይኔ በብረቱ እያየሁት ያለሁትን ስለሆነ የምናገረው አይዘግንናችሁ - በተለይ ትግርኛ ተናጋሪ የሆናችሁ በውጪ ሀገራት የምትኖሩ ወገኖቼ ትግስታችሁን ተንበርክኬ እለምናለሁ፡፡

ወደ መከላከያ ሚኒስቴር የትኛውም ሥፍር ሂዱና ውስጠኛው ክፍል ድረስ ዝለቁ፤ ካለ ትግሬ አታዩም፡፡ የትኛውም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሂዱ እዚያም ያው ነው፤ መሽቆጥቆጣቸው አንጀታችሁን የሚበላው የሌሎች ዘውጎች ሰዎች ቅስማቸው ስብር ብሎ እዚያና እዚህ ተጨብጠው ከምታገኗቸው ሌላ በአንደኛ ዜጋነት ትልቅ የመኮፈስ ስሜት ሲንጎራደዱና ሲፈልጡ ሲቆርጡ የምታዩዋቸው ወያኔ ትግሬዎች ናቸው፡፡ ሌላ ወንበር ያለውም ቢሆን እንኳ በራሱ አይወስንም- ትግሬ አለቃውን ማማከር አለበት፡፡ በነገራችን ላይ ቀደም ሲል በአንድ የጨዋታ ማዕድ ላይ የተቋደስኩትን ዝነኛ ወያኔያዊ ጀብድ ልንገራችሁ፡፡
 
ሲግናል ውስጥ አንዲት የአንድ መኮንን ሚስት አለች፡፡ ሌሎች ሴቶች በትግርኛ ያናግሯታል፡፡ ትግርኛ እንደማታውቅ ትገልጻለች፡፡ ትግርኛ ባለመቻሏ በሳቅ ያስካኩባታል፤ በጣምም ይገረማሉ፡፡ እንዴት በዚያ ግቢ ልትገኝ እንደቻለችም በመደነቅ ይጠይቋታል፡፡ በባሏ ምክንያት እንደሆነ ትነግራቸዋለች፡፡ ይህን ስል ከሌላው ዘውግ የጦር መኮንን የሆነ አይኖርም ከሚል አይደለም፡፡ ይኖራል፡፡ ነገር ግን መኖር አትበሉት፡፡ በየጊዜው በሚደረግበት ስለላና ቁጥጥር ሰውነቱ እያለቀና ሙዳ ሙዳ ሥጋ እየቀነሰ ነው እሚኖርመኖር ተብሎ፤ ሌላ ሥራ የለማ! በሌላም መሥሪያ ቤቶች ሁኔታው ከዚህ ቢብስ እንጂ ያው ነው፡፡ ለይስሙላ ከሌሎች ዘውጎች ሆዳቸውን ብቻ የሚወዱ ሰዎች በአነስተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ይቀመጣሉበትልቅም ሊሆን ይችላል፤ አይሠሩበትም እንጂ፡፡ ለታይታዊው የጎሣ ተዋፅዖ ፍጆታ ነውለድራማ ብቻ፡፡ ከላዩ ወይም ከጎኑ ግን ትግሬ በግድ መኖር አለበት፡፡ ትግሬ ስል ወያኔም ማለቴ ነው፡፡ ወያኔ ስል ደግሞ የተጋቦትም ስላለ ስሜቴን በተሟላ ሁኔታ አይገልጽልኝም፡፡ እንጂ የጎንደርን፣ የጎጃምን፣ የወሎንና የሸዋን ሜዳና ተራራዎች አቋርጠው አዲስ አበባ የገቡት በትግሬው(የኤርትራ ትግሬ) በረከት የሚመራው በጀንፈሉ ኢህዲንና በየዋሁ ሕዝብ አጋዥነት አይደለምን? ኢትዮጵያ እኮ ትንግርተኛ ሀገር ናት፡፡ በሬ ካራጁ እንዲሉ ወያኔን ከትግራይ አዝሎ ወደመሃል ሸዋ ያመጣት በስድብና በሥውር የዘር ማጥፊያ ዘዴ ዕልቂቱ በወያኔ የተቀነባበረለት አማራው ራሱ መቼስ ቢሆንዘነጋ ይችላልን? ቢያንስ ቢያንስ ከመጥፋት ራሱን እዬተከላከለ ግን ለራሱ ጥፋትና ውድመት ከሼረኞች ጋር መተባበሩን ቢተው ኖሮ እኮ አማራውም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ አሁን ተያይዞ ከማለቅ ይድን ነበር፡፡ ግን ዕውቀት እሚገኝ በሃምሳ ገንዘብ እሚገኝ በሠላሣ እንደሚባለው ሆነና ሁሉም ፀፀቱን ብቻ ታቅፎ ቀረ፡፡ ለበጎ ነው ይሁን ግዴለም፡፡ ለወደፊቱ ብዙ እንማርበታለንለዚያውምወደፊትየሚባል ነገር ካለን፡፡

ለይምሰል በሚኒስትርነት ቦታ ላይ የምታገኙትን ትግሬ ያልሆነ ሰውሂድና ሌላህን ብላበሉት፤ ውሸት ነው፡፡ ዘበኛና ጽዳት የሆኑት ትግሬ ወያኔዎች ጎይታይ እምበይተይ ብሎ አስኪሰግድ ያስደገድጉታልበግልጽ፡፡አማሮችን እንዳያንሠራሩ አድርገን አርቀን ቀብረናቸዋልየሚል ኢትዮጵያኤታማዦር በሚገኝባት ጉደኛ ሀገር ውስጥ ትግሬ ዘበኛ አማራ ሚኒስትርን ቢያንቆራጥጥ ከላይ ከአናት ጀምሮ አይዞህ ባይ እስካለው ድረስ ይሾም ይሸለማል እንጂ ሌሎችን ማሽቆጥቆጡን እንዲተው ሃይ የሚለው የለም፡፡ ትግሬ ወታደር ትግሬ ያልሆነ ዜጋ ቢገድል ቦታ ይቀየርለታል እንጂ ዝምቡን እሽ የሚለው እንደማይኖር ከውስጥ ዐዋቂዎች ስትሰማ ሰው ሆነህ መፈጠርህ ራሱ ያስጠላሃል፤ ቋንቋን ጨምሮ በብዙ ነገር በሚመሳሰሉ ነገደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህን መሳይ ዘግናኝ ክስተት መፈጸሙን ስታውቅ ምነው ዜግነቴ የሌላ ሀገር በሆነ ብለህ ትመኛለህ፡፡ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እሚያስገኙ የሀገሪቱ ዋና ዋና መሥሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በትግራዉያን ቁጥጥር ሥር ናቸው፤ ከሁለተኛ ዜጎች ውስጥ የመንግሥታዊ /ቤቶች የቦርድ ሊቃነ መናብርትና አባላት ሆነው የምታገኘው በቁጥር ነውበዚህኛው ወይም በዚያኛው መንገድ ንክኪ የሆኑ፡፡ ፀረ ሙስና የተባለውን ጨምሮ ብዙ /ቤቶች ቁጭ በሉ ናቸው፡፡
 
ወያኔዎች የሚፈልጉትን ለመጥቀምና የማይፈልጉትን ለመጉዳት በአንድ አዳር ሳይቀር የሚኒስቴር /ቤት ፈጥረው ሊያድሩ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ልብ አድርጉየምድር ጦሩ፣ የሰማይ ጦሩ፣ የአየር ጦሩ፣ ፖሊሱ፣ ደኅንነቱ፣ ታጣቂ ሲቪሉ፣ ቤተ መንግሥት ዘቡ፣ የአየር መንገድ ጠባቂው፣ሁሉም በአንድ የትግራይ ዘውግ ተጠፍንጎ በተያዘበት ሁኔታ መለስ ማንን ሊፈራ ይችላል? እውነት ነው ማንንም ሊፈራ አይችልም! ግን የሁሉም ትብታብ መፍረሻ ስላለው ያንን ነው መፍራት፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ደግሞ ጊዜ ሳይመጣና እንደነሊቢያ ጉድ ሳይሠራን ከአሁኑ በተባበረ ክንድ የደም ጎርፉን ወደ ልማት ጎርፍነት እንለውጠው ነው፡፡ አይነጋምን ትተሸ ይነጋልን ባሰብሽ ነው ነገሩ፡፡ ይህንን ሀገራዊ አሳዛኝ እውነት እያወቁ አለመናገር ጥፋት ይመስለኛል፡፡ ቁስላችን ይፍረጥረጥና መድሐኒቱ ይፈለግለት፡፡ ብዙ የሚገማ ቁስል በመካከላችን ይገኛል፤ አሁን አሁን ሽታውና ግማቱ አላስቆም አላስቀምጥ ብሎን እምንሠራውን አሳጥቶናል፡፡

ከዚህ ሥርዓት ታዲያ አንድም ቢሆን የአማራ ከፍተኛ መኮንን እንዲገኝ ትጠብቃላችሁ? እንዴት ብሎ? ይሙት በቃ ተፈርዶበት? በየጊዜው የወያኔ መቀለጃና ማሽሟጠጫ ሊሆን? በነጄኔራል ተፈራና በሌሎቹ አማሮች የደረሰውን እኔን ያየህ ተቀጣ ዓይነት ኢሰብኣዊ የሥቃይ ውርጅብኝና የሚዘገንን ውርደት እያዬ? የሚሠራውን ቲያትር እየተመለከተ በተለይ በወታደርነት ከወያኔ ጋር የተሠለፈ ሰው ተራው እስኪደርስ ይቆይ እንደሆነ እንጂ ተዋርዶ ነው የሚቀር - ደግሞስ ከመነሻው አማራን  ወደሥልጣንና ወደ ትልቅ ማዕረግ ማን አስጠግቶት፡፡ እንደምንም ዕድል ገጥሞት የተጠጋ ሆዳም ቢኖር እርግጥ ነው የተቻለውን ቦጭቆ ዘወር ሊል ይችላል፤ ሊያውም በክትትል ሥር ሆኖ፡፡ ካለ ትግሬ አንድም ሌላ ዜጋ የማይገባባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መኖራቸውንስ ስንቶቻችን እንሆን እምናውቅ? ለምሣሌ ኢንሳ አንዱ ነውነጻ ሚዲያን እሚያፍነው:: (INSA)

ንግዱንና ፖለቲካውን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያሰደፍር ሁኔታ የተቆጣጠሩት ትግሬዎች ናቸውየሥርዓቱ ተጠቃሚ ትግሬዎች፡፡ ተጠቃሚ ያልሆናችሁ ትግሬዎች እንደኔው ኩሩ፤ ዋጋችሁ በነገይቷ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ዕጥፍ ድርብ ነው፡፡ ነገን ልናያት ባይቻለን እንኳን ከቆሸሸ ኀሊና ይልቅ ንጹሕ ኅሊናን ይዞ ወደማይቀርበቱ መሄድ የገዛ ትውልድን ከማሳፈር ይታደጋል፡፡ የነአፄ ኃይለ ሥላሤና የነመንግሥቱ ኃጢያትና ወንጀል ከነመለስ ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ የሰማይንና የምድርን ያህላል፡፡ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ በመንግሥት ሠራተኝነት ከዱሮ ሥርዓቶች ባንደኛው ስቀጠር አለቃየ ባጋጣሚ ትግሬ ነበር፤ ወደሌላ ቦታ ስዛወርም አለቃየ እንዲሁ ባጋጣሚ ትግሬ ሆነ፡፡ የሚገርመው ነገር እኔ ምን እንደሆንኩ አላውቅም፤ የአለቆቼ ትግሬነትም አላስኮራኝም ወይም አላሳፈረኝም፤ የዘውግ ዕውቀቱም ሆነ ግንዛቤው እንዳሁኑ ስላልነበር፡፡ አሁን ግን አለቆች ትግሬዎች መሆናቸው ፀሓይ የሞቀው ሃቅ ከመሆኑም በተጨማሪ አንተ ትግሬ ካልሆንክ በሥነ ልቦናህ ተጨማድደህና ተኮማትረህ አንገትህን ደፍተህ ዕጆችህን የኋሊት አጣምረህ ነው አለቃህን እምታነጋግር፡፡ የትግሬው ወያኔ ኩራትና ትዕቢት ደግሞ ቅስምህን ይሰብራል፡፡ ከዚህም ታዲያ ስደትን ሲያንስም ለምኖ መብላትን ልትመኝ ትችላለህ፡፡ እውነት ነው! ፍርድ ቤቶች የተሞሉት፣ ሀኪም ቤቶች የተሞሉት፣ በከተሞች የሚታዩ ትላልቅ ሕንጻዎች የተያዙት፣ ምን አለፋችሁ ሁሉም በትግሬዎች ለትግሬዎች ነው፡፡ ቁርጥህን ዕወቅ ወዳጄ በአሁኑ ወቅት ሀገር የለህም፡፡ ሆድህን ከሞላህ በሌላው እንደእኩዮችህ ሌሎች እንስሳት በድብቅ እንደአህያ እያናፋህ ወይ እንደአንበሣ እያገሣህ ወይ እንደውሻ እየጮህክ መኖር ነው፡፡

አዲስ አበባም ሆነ ሌላ ቦታ የትም ሂድ፡፡ ቡና ቤትም ግባ፡፡ ትላልቅ ሆቴሎችም በድንገት ዘው በል፡፡ ብሔራዊ ቋንቋ ትግርኛ እስኪመስልህ ልትደነግጥ ትችላለህ፤ የምለው ግልጽ ይሁንልኝ፤ የመደንገጥህ መንስኤ ትግርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆኑ አይደለም አያስከፋም፤ አያስደነግጥምም፡፡ ችግሩ ሌላውን ሕዝብ ምን ዋጠው? ነው ሌላውና ብዙውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚወክል የሚነገርለት ወገንስ አይዝናናም? አይበላም? አይጠጣም?

 በትምህርት ቤቶች ግቡና የነማን ልጆች በጥሩ ትምህርት ቤቶች እንደሚማሩ እዩ፡፡ በዩኒቨርስቲዎችም ግቡ፡፡ ያለማጋነን 80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የውድ ክፍያ /ቤቶች ተማሪዎች የትግሬ ልጆች ናቸው፡፡ ጥያቄው ለምን ተማሩ አይደለም፡፡ ይማሩ ወገኖቼ ናቸው፡፡ ግን ሌላውስ? ሌሎች ደንቁረው እንዲቀሩና በረንዳ እንዲያሞቁ ሤራ የሚሸረበው ለምንድነው? የንግድ ተቋማትን ስናይ ሌላው ወገን በግብርና በቀረጥ፣ በጉልበትና በዘዴ ወደውጪ እየተገፋ ሳለ፣ ትግሬነቱን እስከጥግ ሊጠቀምበት የሚፈልግ ትግሬ ዜጋ በህግ ሽፋን እዬተደገፈ ካለግብርና ቀረጥ አዬር ባየር እየነገደ በአንድ ሌሊት ይከብራልይሄ ጭንቅላት ብሎ ነገር ጭራሽ ያልፈጠረበት የወያኔ ጀሌ በወገኑ ላይ የሚሠራው ደባና ወንጀል ገደብ አጥቷል፡፡ ይሄ የደም ዋጋ 20 ዓመት እንኳን ተከፍሎ አያልቅም እንዴ? ለትውልድ እየተላለፈስ ሕዝብን ማሰቃየት አለበት እንዴ? ትግሬ አለመሆን በወንጀል የሚያስቀጣ ያህል ሆንዋል እኮ በሀገራችን፡፡ ምን ይብቃን እንግዲህ?

 እናቴ ስትወልደኝ መቼ አማከረችኝ…› የሚለው ዘፈን የማን ነበር? አዎ፣ እናቶቻችን ሲወልዱን ቀድመው አማክረውን ቢሆኑ ኖሮ ማን ጎንደርና ጎጃም ወይም ወለጋና ኢሉባቦር ይወለድ ነበርእዚያችው አድዋና ሽሬ እንተፋፈጋት ነበር እንጂ! ብቻብዙ ችግር፣ በጣም ብዙ ችግር፤ እጅግ በጣም ብዙ ችግር አለብን ወገኖቼ፡፡ በምን ታጥበን ከዚህ ሀገራችንን ካጨቀያት ወረርሽኝ እንደምንጸዳ እንጃልን፡፡
    ቀበሌ ብትሄዱ ከመዝናኛው አቅም ከሞላ ጎደል በትግሬዎች ነው የተያዘው፡፡ በየትኛውም የመስተዳድር ቢሮ ስማቸው የኦሮሞ ወይም የአማራ ሊሆን ይችላል እንጂ የሚያዙት የሚናዙት እነሱው ናቸው - ወያኔዎቹ፡፡ ሠራተኞች (ዕድሮችና ሌሎች ሕዝባዊ ማኅበራት ጭምር) እንኳን ለመሥሪያ ቤታቸው ጥያቄ ለማቅረብ ቢፈልጉ ተጠሪ አድርገው የሚመርጡት ትግሬዎችን ነውጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝና  በፍጥነት መልስ እንዲሰጥበት፡፡ አለበለዚያ ችግርን በሰላማዊ መንገድ ማቅረቡ ራሱ በነፍጠኝነት ወይም በኦነግነት አስጠርጥሮ ዘብጥያ ሊያስወርድ ይችላል፡፡
 
ቡና ቤቶች ባቅማቸው ቤታቸው እንዲከበር የትግርኛ ዘፈን ነው የሚከፍቱት፡፡ በትግሬዎች ተፅዕኖ ምክንያት ትግሬ ሳይሆን ትግሬ የሆነ አስመሳይ ወይም ርጅድትግሬ ከተሞቻችንን አጥለቅልቆታልያሳፍራል፡፡ ሰው ከመሬት ተነስቶትግሬ ነኝሲል ትሰማለህየምታውቀው አማራ ወይም ኦሮሞ፡፡ ነገሩ ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ዓይነት መሆኑ ነው፡፡
 
በሃይማኖቱም ይሄው ነው፡፡ አማራ ከሆንክ የሚያስቀርብህ የለም፤ ብትቀርብም በከፍተኛ የስለላ መረብ ውስጥ ትገባና እስትንፋስህ ሁሉ በየቀኑ ትለካለች፡፡ የደብር አለቃ ለመሆን ከዐድዋ መምጣት ወይም የብፁዕ አባታችንን እግር መላስ ሳይኖርብህ አይቀርም፤ ብዙ መማርህ አይጠቅምህም ብቻ ሳይሆን ይጎዳሃል፡፡ እግዚአብሔር ተረስቶ ሥጋዊ ፍላጎትና ምኞት እውን የሚደረግባት ሆናለች ቤተ ክርስቲያን፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን ይዞታዎች ስትሄድ እዚያም ብሔራዊ ቋንቋችን ትግርኛ የሆነ ያህል ይሰማሃል፡፡  
እንዲህ እያልኩ ያለሁት ስለእውነት ብዬ እንጂ ማንንም ለመጉዳት ወይም ለመጥቀም አይደለም፡፡ ይልቁንም ራሴን እያሰቃየሁ ነውመናገር የማይገባኝንና በሽፍን መያዝ የነበረብኝን የወንድምና የእህቶቼን ነውር እኔም በበኩሌ ለማውጣት በመድፈሬ አዝናለሁ፤ ግን በሌላ አቅጣጫ ሳየው የሚያደርጉትን ያሳጣቸው ራሳቸው ልበ-ዕውራኑ ያላፈሩ እኔን ምን ያሳፍረኛል? ብዬ እጽናናለሁ፡፡ እዚህ አካባቢ አንድ ጥያቄ በአእምሮህ ሊያጭር ይችላል፤ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታ በትግሬ ወያኔ ለመሙላት ዝግጅቱ መቼ ይሆን የጀመረው›? መልሱን ደግሞ በቀላሉ ታገኘዋለህ፡፡የሥልጣን ቦታዎቹ በታማኝ ትግሬዎች ይሞሉ እንጂ የባለሥልጣኖቹ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ በጭራሽ አስፈላጊ አይደለምየሚለው የዝግጅቱን አላስፈላጊነት ያሳይሃል፡፡ አንድ የሥራ ሂደት ባለቤት ደረቱን ነፍቶ ለሚናገረው ነገር አስቀያሚነት ወይም ትክክለኝነት ሳይጨነቅ እንደ ልቡ ካነጋገረህ ሰው የትግሬ ወያኔ መሆኑን ለመረዳት ተጨማሪ ማረጋገጫ አያስፈልግህም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ እንደዚህ ዘመን አፍሬ የማላውቅ መሆኔን የምገልጽላችሁ የሀፍረቴን ጥቁር ሸማ አንድዬ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አውልቆ እንዲጥልልኝና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወገኔ በሀገሩ የጋራ ባለቤትነት ኮርቶ በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር እንዲኖረው በጽኑ በመመኘትና በመጸለይም ጭምር ነው፡፡ ይህችን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ሳላይ በእናቴ ማሕፀን ውስጥ ያኔ ወላጅ እናቴ ቅሪት እንዳለች ውኃ ሆኜ ብቀር ኖሮ ምንኛ በታደልኩ ነበር? የማወቅ መጥፎነት እዚህ ላይ ነው፡፡ አንዳንዴ አለማወቅን የመሰለ ፀጋ የለም፡፡ በውጪ ያላችሁ ታድላችሁ! ቢያንስ እንደዚህ ዓይነት አድልዖዎችንና ሸውራራ የትግሬው መንግሥት አሠራሮችን እየተመለከታችሁ በየዕለቱ ኅሊናችሁ አያለቅስም፡፡ እኛስ ዕንባም ባቅሙ እዬተጓደደብን(እየኮራብን) በደረቁ ለማልቀስ ተገድደናል፡፡

እንደማጠቃለያበዚህ አያያዝ በወያኔ ትግሬ በወለድ አገድነት የተጠረነፈች ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ምን ማድረግ ያስፈልጋል? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ሁላችንንም ከዳር እዳር ሊያነጋግረን ይገባልይሄን እዚያ ማዶና እዚህ ማዶ ሆኖ በከንቱና ለትዝብት ዓምድ የሚዲያ ፍጆታ በሚውል መልኩ መነታረኩን ትተን ቁም ነገር እንሥራ፡፡ ለዚህ ጥያቄ በተለይ ከትግርኛ ተናጋሪ ጤነኛ ኢትዮጵያውያን ሁነኛ ምላሸ ብንጠብቅ ሞኝነት አይመስለኝም፡፡ ሌላው ሕዝብ በሀፍረትና በኑሮ ውድነት አንገቱን ደፍቶ እየኖረ ነውመኖር ተብሎ፤ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብም እንደዚሁ በተወሰነ ደረጃ አንዳንዶች ባልተገባ መንገድ ሊጠቀሙበት ከሚፈልጉት የሥነ ልቦና እርካታ ውጪ ይህ ነው የሚባል የረባ ጠቀሜታ ያገኙ አይመስለኝምና ብዙዎቻችን በአንድ የሥቃይ ቅርጫት ውስጥ የምንገኝ መሆናችንን አምናለሁ፡፡ መላው የኢትዮጵያ የተረገጠ ሕዝብ አንገቱን ቀና የሚያደርግበት ጊዜ መምጣቱ ግን በፍጹም የማይቀር ነው፡፡ እሾህን በእሾህ መንቀል የነበረና ያለ በመሆኑ የትግራይ ሕዝብ ከአንጀቱ ካለቀሰ የወያኔ ዕድሜ አጭር ነው፡፡ ወያኔ ከትግራዉያን ያለው ድጋፍ ቀላል እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ ዓሣውን ለመያዝ ባሕሩም የበኩልን አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይጠበቅበታል፡፡ ያኔ የትግሉ ዘመንና የመስዋዕትነቱ መጠንም ይቀንሳል፡፡ ለፀረ-ዳግማዊ ወያኔ የነጻነት ትግል የትግራይ ሕዝብ ያለው ድርሻ በመጥፎና ማፈሪያ የጋራ ልጆቻችን የጠየመውን የዚህችን የኢትዮጵያዊነት እምብርት ታላቅ ክፍለ ሀገር የቅርብ ጊዜ ታሪክ እስከማደስ የሚደርስ ታላቅ አወንታዊ ድርሻ አለው፡፡ ብዙ ማለት እችል ነበር - ግን ለጊዜው ይብቃኝ፡፡ እየሆነ ከሚታየው አንጻር ምንም አልተናገርኩም ማለት እችላለሁ፡፡ ሌሎችም አግዙኝና እውነቱን ዐውቀን ለወደፊቱ የሚበጀንን መምረጥ እንዲያስችሉን በግልጥ የሚታዩና በሥውር የሚካሄዱ ወያኔያዊ የግፍ አሠራሮችን እያጋለጥን በታሪክ ስንክሳር እናስመዝግባቸው፡፡ ዛሬ ያልፋል፤ ነገም ሌላ ቀን ነውእንደሚባለውና እንደውነቱም፡፡

በመጨረሻየ መጨረሻ ጥሩዎቹን የትግራይ ተወላጆች ደግሜ ይቅርታ እንድል ይፈቀድልኝ፡፡ ከላይ የጠቀስኩት አበሳና በኢትዮጵያ ላይ እየወረደ ያለው መቅሰፍት በሁሉም የትግራይ ሕዝብ ምክንያት ሳይሆን አጋጣሚዎችን ተጠቅመው ሕዝባዊውን ድል ወደቤተሰባዊና ቡድናዊ የዘውግ አደረጃጀት በለወጡ የእርግማን ፍሬዎች አማካይነት ነው፡፡ ስለዚህ የእነሱን ገመና ለመናገር ያደረግሁት በጣም ኢምንት ጥረት ደጋጎቹን እንዳያስቀይምብኝ አደራ እላለሁ፡፡ በበኩሌ በሁለት አጣብቂኞች መካከል ላላችሁ ወገኖቼ ያለኝ አዘኔታ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ነገረ ሥራችን ላም እሳት ወለደች ዓይነት ነው፡፡ ፈጣሪ የሚያፈቃቅር ደግ ዘመን ያምጣልን።” ይላል ወዳጄ ይነጋል በላቸው።

የኢትዮጵያ አኩሪ ታሪኳ፣ መልክአ ምድሯ፣ ባሕር ወደቦቿ፣ እንደክርስቶስ ተሰቅላ የሞተችው አገራችን ትንሣዔዋ እስኪበሰር ድረስ መልካሙን እመኝላችኋለሁ፤

ሁላችንም በያለንበት መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ! አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ አሜሪካ ሳንሆዜ ከተማ) (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com