የማይበገር ድንቁርና፡
ጌታቸው ረዳ
ETHIO SEMAY
1/1/2022
ሊቃውንት የተለያዩ ድንቁርናዎች እንዳሉ ይናገራሉ። የትውልድ አገርዋ “ኤርትራ” ድረስ ሄዳ መሪዋን ከልብ የምትወደውን “ኢሳያስ አፈወርቂን” ጎብኝታ “ፓስፖርትዋን እና የማንነት ወረቀትዋን ልክ እንደ ሟቹ “ተስፋየ ገብረአብ” በምስጢር “ሁሉም ወደ እሚያላግጥባትና የሚግጣት” ኢትዮጵያ ወደ ወሎ የተመለሰቺዋ “መነን ሃይለ” ስለ እማነሳው ድንቁርና “ዳፍንት ድንቁርና” የሚለውን ነው።
“የዓይን ሳይሆን የሕሊና ዳፍንት” አደገኛ ድንቁርና ነው። ዳፍንት የተለያዩ ቀለሞችን በዓይን የማየት ችሎታን ያሳጣል። “ዳፍንት ድንቁርና” ግን ከዓይን ዳፍንትነት የተለየ ነው።
ስለ እዚች ሰላይ የማነሰው ድንቁርና “ተራው ድንቁርና” አይደለም ማለትም “ተራው” ድንቁርና “ብሩህ ድንቁርና” ሲሆን ባለማወቅህ ለማወቅ የእውቀት ፍላጎትህን ያነሳሳል።
የዚች ልጅ ድንቁርና ግን “የማይበገር ድንቁርና” ነው። የዚህ
ዓይነት ድንቁርና ስታንጸባርቅ የታዘብኳት ይህች ልጅ “በኢትዮጵያችን የባሕል፤የታሪክ፤የሕግ፤የሰንደቃላማ አክብሮት፤ ጥንቃቄ የሚሹ ባሕሬዎችን ጥሳለች። በአካባቢ ኗሪዎች ነውር የሆኑ የተወገዙና የማይደረጉ የንግግር ነውሮችን በሙሉ ያለምንም የሞራል ጥያቄ “በድፍርት” ፈጽማለች።
ይህ እንድትፈጽም የሚገፋፋት ብዙ ምክንያቶች መዘርዘር ቢቻልም በጥቅሉ “የሞራል ውድቀት ነው” (Moral Depression) ምልክት ነው።
ይህች ልጅ ለበርካታ ወቅቶች ዩቱብ ቲ/ቪ በሚሰጠው የነፃ ኦምድ በመጠቀም “ወሎ” ውስጥ ሆና ስታስተላለፍቻው የነበረ እጅግ አደገኛና ዘረኛ ቃላቶች ያለ ምንም የሞራል ስጋት ስታስተላልፍ ቅሬታም
ስጋትም አይታየባትም። ለ6 ሚሊዮን የያዘ አካባቢ ሕዝብ ያላት ጥላችም ሆነ ንቀት በዘለፋ ስአስተላልፍ እንደ “አማራ” ሆና ነው። በአማራ ስም “ኤርትራዊያኖችን እስካስደሰተቻቸው ድረስ” አዛውንቶች ሕጻናት እናቶች አባቶች ጉዳይ አይሰጣትም።
“የተስፈዬ ገብረአብ እና የመነን ሃይለ” ተልዕኮ አንድ ሲሆን በድፍረቷ ግን ትምሕርት ስለሌላት እንጂ ከተስፋየ ገብረአብ የከፋች እጅግ የሚያስደነግጥ ድፍረት አላት።
አንዳንዶቹ ኤርትራኖች እንደሚሉት ከሆነ “ወ/ት መነን ሃይለ” ኤርትራ ውስጥ ሄዳ በሕግደፍ አፍቃሪነትዋ በዋለጆችዋ የጥንት ርስት “ሳትመራ” አንዳልቀረች የሚናገሩ አሉ።
ልጅቷ አሁን ያለው ኦሮሙማ መንግሥት ደጋፊ ካድሬ እና
የነ ኮ/ል አለበል አማረ ጥብቅ ግንኙነት እንዳላት ይነገራል። ኮ/ል አለበል አማረ ማለት አርበኛው አሳምነው ጽጌን “ካሀዲ” ብሎ የዘለፈ “ወላዋይ” የሆነ ማፈሪያ ነው።
ልጅቷ ከዚህ ኮ/ል ጋር የሚታማ ግንኙነት እንዳላትም በየፌስቡኩ ሲወራባት የነበረች ልጅ ነች። ያ እንዲያ የሆነው ምናልባት ልክ እንደተስፋዬ የስለላ መረብዋን ለመዘርጋት ከዚህ ኮ/ል ጋር ያደረገቺው ተልዕኮ ይሆን? ማን ያውቃል? ጠርጥር!
ይህች ልጅ ልዩ የሚያደርጋት ደግሞ “የኔ መሪ ብላ የምታደንቀው “አረመኔው” የኢሳያስ አፈወርቂን ፎቶግራፍ “በቤትዋ ግድግዳ” ውስጥ ለጥፋ ወደ ሚዲያ ስትቀርብ የኢሳያስን ፎቶ በጀርባዋ አስተካክላ በመደገን “ዩቱብ” ላይ እዩልኝ የምትል “ዳፍንታማዊ ደንቆሮ” ነች።
የመጨረሻ ምክሬን ለማስተላለፍ የምፈልገው፡ አብይ አሕመድ ኢትዮጵያ በኤርትራ ሰላዮች እንድትዋጥ አድርጓል። የናንተ “የአማራዎች” ፈንታ ማድረግ ያለባችሁ እንዲህ ያሉ አደገኛ ሰላዮች በጥንቃቄ መከታተል ይኖርባችሗል። በተለይ በማሕበራዊ (ኮሚኒቲ) እና ወታደራዊ ቦታዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጥንቃቄ መከታተል አለባችሁ።
ሁሉም አማራ ነኝ ስላለ አማራዊ ስነምግባር ይከተላል ማለት አይደለም። እንኳን ሰላዮቹ አማራ የሆኑትንም ጸረ አማራ እየሆኑ እያየን ነው። ትምሕርት የጎደላቸው ካድሬዎች ከሆኑ በቀላሉ ሰላዮች መሆናቸው የምታውቁት “ለኤርትራ ባንዴራ” እና ”ለኢሳያስ” ከሚያሳዩት እጅግ መረን የለቀቀ ፍቅርና ቅስቀሳ ማወቅ ትችላላችሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
ETHIO SEMAY 1/1/2022