Wednesday, July 14, 2021

ይድረስ ደብዳቤዬ ለባሕርዳር ከተማ ባለሥልጣኖች እና ፖሊስ ኮሚሽነር ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/14/2021 ወንድሜን ስላሰራችሁት ጉዳይ

 

ይድረስ ደብዳቤዬ ለባሕርዳር ከተማ ባለሥልጣኖች እና ፖሊስ ኮሚሽነር

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/14/2021

ወንድሜን ስላሰራችሁት ጉዳይ

ታናሽ ወንድሜ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ በሰላምና በፍርሓት ከሚኖርበት መኖርያ ቤቱ ትናንት ማታ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አፍናችሁ ሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ አስራችሁታል። ከማንኛችሁ በላይ ወንድሜን አውቀዋለሁ። ትግሬ በመሆኑ ብቻ አስራችሁ እያሰቃያችሁት ነው።

 ቤተሰቦቼ ደውለው እንደነገሩኝ ወደ ሌላ ማጎርያ ሥፍራ እንዳይወስዱት ሰግተናል እና የምውቃቸው ባለሥልጣኖች ካሉ አነጋግርልን ስላሉኝ፡ እኔ እናንተን የማወቅበት መንገድ የለኝም። እናንተን የማውቀው እኔ ወያኔን ስታገ እናንተ ግን ወያኔን ስታገለግሉ እና አማራን ስታሰቃዩ በሞኖራችሁ ተቃዋሚያችሁ መሆኔን ነው የማውቀው።

ወንድሜን ስላፈናችሁት፤ በንዴት ወደ ወያኔ ካምፕ እንደማልገባ ግን ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። ከወራት በፊት ትግራይ ውስጥ በተደረገው ጦርነት የታላቅ እህቴን ልጅ በአይሮፕላን ተደብድሞ ሲሞት “አቋሜን ለውጨ” ብንዴት ሌሎቹ እንዳደረጉት ወደ ወያኔ ካምፕ አልተቀላቀልኩም።  ስለዚህም ምንም የሌለበትን ወንድሜን አሁኑኑ ፍቱት!!!

የማውቃቸው ሰዎች በመደወል ባለሥልጣናቱን እንድያነጋግሩልኝ በመጠየቅ ላይ ነኝ። ተከታዮቼም ትብብራችሁ እጠይቃለሁ።

የአማራ ክልል ባለሥልጣናት እና የደህንንት ሰራተኞች ን ትግሬዎች ወደ ወያኔ ካምፕ እንዲገቡ የምታደርጉት ግፊት አሁኑኑ አቁሙት!! የዘር አፈናው ለናንተም ለኛም አይጠቅምም። የጎስታፖ ሥራችሁን አቁሙ!! የጠላትን ጎራ እንዲጠናከር አታድርጉ!! ባለሥልጣኖችን የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ እርደታችሁን እንጠይቃለን። ጌታቸው ረዳ በታገለላት አገር ቤተሰቦቼን ማሰር አንጀቴን ተፈታትኖታል። ግን በናንተ ዘረኝነት እኔ ወደ ወያኔ ካምፕ አልሄድም። መልእክቴ እንዲዳረስ እባካችሁን “ሼር” በማድረግ ተባበሩን።

ድል ለኢትዮጵያ

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ። Ethiopian Semay