Tuesday, May 29, 2018

አሁን በመከላከል ላይ ነን ፥ ወደ ማጥቃት መግባታችን ግን አይቀሬ ነው (ደብረጽዮን) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አሁን በመከላከል ላይ ነን ወደ ማጥቃት መግባታችን ግን አይቀሬ ነው (ደብረጽዮን)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ይህ ርዕስ በሚቀጥለው ሰሞን የሚቀርብ ነው። ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታት አንድ ልበል። እንደታዘብነው አገሪቷ በስሜት የሚነጉዱ ብዙ የዋህ ዜጎች አፍራተለች። በስሜት የሚከንፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ለፖለቲካ ጮሌዎች እና ፋሺስቶች ዛሬም ለሚቀጥለውም በቀላሉ የመሰለብ ዕድሉ ክፍት ነው።  ከነዚህ ስሜተኞች ውስጥ አንደ ምሳሌ የምንጠቅሳቸው የግንቦት 7 አባሎች እና አባላች ባይሆኑም በስሜት ተውጠው በየአዳራሹ ባስገራሚ ትዕይንት ‘እምባ የሚያቀርሩ” የዋህ ዜጎችን ማየት ይቻላል። እነዚህ የዋሾች ሰለባ በመሆናቸው ይድናሉ ብሎ ማለት የማይቻል ነው።  አንዴ የተሰለበ ሕሊና ደግሞ በአመክንዮ ኣያምንም። ዋሾችን እንደ ኣምላክ ማምለክ ይቀጥላሉ። ሰይጣንም ተከታዮች አሉትና።

ስለሆነም ኤርትራ ውስጥ ሆኖ ከኤርትራዊትዋ “ሰሚራ” ጋር ፍቅር ይዞት በየዓረብ አገሮች እና በየዱባዩ እቃ ሲያመላልስላት የነበረው ኤርትራ ውስጥ እያለ ለኢሳያስ አፈወርቂ እሽከርና በገሃድ የቆመውና ለበርካታ ዜጎቻችን “ድብደባና የህይወት መጥፋት” የሚከሰሰው አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታቱ ቅር ባንሰኝም፤ ኤርትራ ውስጥ እያለ በነበረው ስልጣን የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረቡለትን ዜጎች ለኤርትራ የምርመራ ገራፊ ቡድን  ተላልፈው እንዲደበደቡ እና እንዲረሸኑ ማድረጉ ከድብደባውና ከእስራት አምልጠው የመጡ የሰጡት ቃል እና በጻፉዋቸው የድርጅቱ የቀድሞ አባላት ለማወቅ ችለናል። 

ባለጊዜዎች ናቸው እና ዋና ተጠያቂ የምናደርገው አንዳርጋቸውን ሳይሆን በራሱ ስም የሚያሽቃብጡ የዜና ማሰራጨያዎች እና ተከታዮቹ ናቸው። ይህንን ወንጀሉን የሚከላከሉለት ደግሞ በዋናነት “ስለ ሰብኣዊ መብት፤ስለ ዜጎች መብት ቆመናል ብለው ሌት ተቀን በየሚዲያቸው ቁጢጥ ብለው የሚያሽቃብጡ ውጭ አገር በስደት የሚገኙ ‘ሀፍረተ ቢስ’ ጋዜጠኞች ናቸው።” እነዚህ ጋዜጠኞች የሚያተኩሩት የዜጎች መብት የሚመለከተው ‘ወያኔ’ በፈጸመው ወንጀል እንጂ ‘ግንቦት7’ የፈጸመው ሰብኣዊ ወንጀል እንደ ወንጀል ኣይቆጥሩትም”። ለዚህ ደግሞ ግልጽ ነው። አባሎች ናቸው፤ ወይንም ግንቦት 7 ከሚያገኘው የውጭ አገር ዕርዳታ እየተቀበለ በሺዎች ዶላሮች የሚከፈላቸው ደሞዝተኞቹ ናቸው። ደሞዝተኛ ደግሞ ደሞዝ የሚፍለው አለቃው አውራ የተባለውን ብቻ ነው የሚያወራው እንጂ የቀጣሪውን ገበና ማጋለጥ ኣይችልም። ኢሳት የተባለው አስገራሚ ሚዲያ ያሉት “ጋዜጠኞች/ሃያስያን” ባንድ ልብ ፤ባንድ ትርታ፤ ባንድ ሳምባ እንደተንፈሱ የተሰሩ ሰዎች ናቸው። ይህ እኔ የማነሳው ትልቁ የሰው ልጆች መብት ጥሰት አንስተው እርስ በርስ አይነታረኩም/አለቃቸውን ወጥረው አይጠይቁም፤ ተጠቃን የሙሉ ከሳሾችም ጠርተው እንዲያነጋግርዋቸው ኣይፈልጉም። እንዲህ ካደረጉ ደሞዝ ከፋዩ ወይንም አባል ነን ብለው የሚደግፉት ግንቦት 7ን ማጋለጥ ስለሚሆንባቸው ‘ሊነኩት’ እየፈልጉም። ይህ ቡድን የ “ኢ ቲ  ቪ” ግልባጭ ነው።

እንኳን ፈልገው አፈላልገው፤ አነጋግሩን ብለው ተጠቂዎቹ የጻፉላቸው ደብዳቤ እንኳ ዋጋ አልሰጡትም።ባጭር አገላለጽ “የግንቦት 7 ምልምል አጋፋሪዎች ናቸው”። ከነሱ ይልቅ በነሱ ፈንታ ሳየው አፈርኩላቸው! የሰው ልጆች ስሞታ እና ቤቱታ ብታፍነውም እንደገና በሌላ ጊዜ መውጣቱ ኣይቀርም። ሚዲያዎች ከወያኔ ሰለባ አቤቱታ አቅራቢዎቸ እንዴት መማር እንዳልቻሉ ግራ የሚገባ ነገር ነው።

አንዳርጋቸው ያለ ምንም ጥርጥር “አንዳርጋቸው ማለት አድርባይ፤ ባንዳ፤ በወንጀል የጨቀየ ፤ተንኮለኛ ፤ ደም የጠማው የሰው ልጆች መብት የሚጻረር ክፉ ሰው ነው”። ይህንን በማስረጃ የተነገረ የራሱ ሰለባዎች “እርይ!” እያሉ የነገሩን ነው። ይህንን በሚመለከት ከግንቦት 7 እና የሻዕቢያ አፈናና ግድያ በመከራ አምልጠው ከወጡት የህዝባዊ ኃይል አመራሮች አባስ/ ማስረሻ (የስልጠና ከፍል ኃላፊ) አና ኮስሞስ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) ቴዎድሮስ ስዩም (ምኒሊክ) (የምልመላ ክፍል ላፊ) ሽታው (አስተዳደር እና ፈይናንስ ሃላፊ)፤ ዳኒኤል፤ አንተነህ፤ ወዘተ ወዘተ… የመሳሰሉ ታጋዮች አንዳረጋቸው ጽጌ ከሻዕቢያ ጋር በጠበቀ ሴራ እየተመሳጠረ፤ ጨካኝነት እና ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ ሰብአዊነት ስብእናውን ያዩትን “በእኛ ይብቃ” በሚል ጽፈው ያሰራጩትን መግለጫ፤ ሕሊና ላለን ሰዎች ያስደመመንን ሰነድ አስነብበውናል።
የአንዳርጋቸው ሰለባዎች ከሆኑት አንዱ ሽታው ሺፈራው በቃለ መጠይቁ መሃል እምባ እየተተናነቀው-እንዲህ-ይላል፤
Heart breaking Tears!!!!!! Agony!!!!    - Victim of Andargachew Tisge Ginbot 7 fighter in Eritrea explains his ordeal of torture in Tears.
“ሽታው ሽፈራው ለሦስት ወር ከዛፍ ጋር ታሰሬ ከጥዋት እሰከ ምሽት ለ 12 ሰዓታት አንድ ጊዜ ብቻ ውሃ እንድጎነጭ እየተደረግሁ ሄሎኮፕተር/ወፌ ላላ/ በተባለ የግርፊያ ዓይነት ቁልቁል ዘቅዝቀው ገርፈውኛል። እባካችሁ በወንድ አምላክ ማሩኝ፤ ልታገል ነው የመጣሁት፤ጥፋቴን ንገሩኝ ምንድነው? ብላቸው መግረፍ ብቻ ነው! “ ሲል እየተገረፈ ያሳለፈው መከራ በዝርዝር እንባ እየተናነቀው በቪዲዩ እና በድምጽ ገልልናል።

አንዳርጋቸው ጽጌን ‘የኔ አንበሳ” እያለ የሚሸልም ለታማኝ በየነ እነዚህ ልጆች ሲያለቅሱ ብሶታቸውን ለማስሰማት ታፍነው ግራ ቀኝ ሲዋከቡ፤ለታማኝ በየነ እንዲህ ብየ በ5/25/14 ጽፌ ነበር ፡” Ethiopian activist TamaNn Beyene is known for his cry and protest to expose or confronting abusers on behalf any citize’s abuse. Unfortunately, in this situation, he is intentionally silent from talking about those abused victims by Ginbot 7. Not even mentioning an iota of word about the crime of his friends Dr.Berhanu Negga and Andargachhew Tsige who committed crime against humanity.  How bias can one is than this open pick and chose defense of humanity? This guy is been talking about Humanity ever since 1991, you mean to tell me, he can't understand the tears and agony of the Ginbot 7 victims'?! በማለት ውጭ አገር ያሉት የስሜተኞች ልብ ሁሌም የሚያምልለው ታማኝ በየነን ጠይቄው ነበር በ 5/25/14። ይህ ለታሪክ የሚቀር ሁሌም ታማኝን ወጥሬ የምጠይቀው ጥያቄ እርሱ ይመልሰው አይመልሰው በበርካታ አንባቢዎቼ ልብ ግን ለታሪክ ተቀርጾ የሚያልፍ ትዝብት ነው።

በማከልም እንዲህ ብየ ነበር።
 
“…The opposition is romanticizing such myth to itself without any strong spine of its own. Many do not understand what torture mean, unless one is tortured by someone or perhaps “Unless one has been subjected to torture oneself, it is impossible to get an accurate sense of what it must be like to be subjected to it, which is why one can dismiss out of hand the excuses given by torture apologists that it is little more than fraternity hazing, although that is bad enough.”  Mano Singham.Yes, torture is evil and those who committed it, provided the authorization for it, and gave the orders for it should all be prosecuted.

I still ask the Diaspora opposition groups (leaders/supporters/media) to challenge them now and for the future asking them “why going to Ethiopia to accuse another criminal (TPLF…) when there are similar criminals inside the Diaspora opposition who are not better than the TPLF criminal? Are these not victims of Ginbot 7 of Andargachew? Are these not Ethiopians/ human beings? Certainly, the opposition media and their activists do not believe these victims are human or Ethiopians in their eyes. But, if they argue these are humanbeings/Ethiopian citizens, why then is the opposition media and some claimed “activists” like Tamng Beyene do not want to talk about it? 

How can I trust and march with these as real opposition and their media who do not want to bother for Human Rights or did not eve moved and bother by tears flowing from the eye of these victims of Ginbot 7? Where is Ethiopia again heading? To a circle of another period of torture with these criminals controlling the political stage all over again? I need your answer.” ብየ ጠይቄ ነበር። እየተጓዝንበት ያለውም የሰው ልጆች መብት የጣሱ በድብደባ በግድያ የተሳተፉትን ሁሉ ተለቅቀው በመጪው አዲስ ስርዓት ላይ የፖለቲካ ስልጣን ተሰጥቶአቸው የለመዱትን ድብዳበ እና ግድያ ይቀጥሉበታል። 

ኢትዮጵያውያን ደብዳቢዎቻቸው፤እጨካኞች እና ጨፍጫፊዎችን አንዲወዱ ለዘመናት በሕሊናቸው የተቀረጸባቸው ፕሮፓጋንዳ የሚጠፋ ኣይመስልም። አንዳንዶቹን ወንጀለኞች ‘በነፃ አውጪነት፤ በአምበሳነት እና በጀግንነት” እየተጠሩ ያው ወደ ቀጣዩ ዙር እየገቡ ነው።
እኔ ማለት የምችለው ‘ከሚቀጥለው እልቂት ይሰውረን”። ለምን እንዲህ አልክ አትበሉኝ; ማስረጀ ስላለኝ ነው። መለስ ዜናዊ ይብቃኝ ልረፍ ሲለን “አይሆንም ቀጥል” ብለን አስቀጠልነው።ሃይለማርያም ደሳለኝ ልቀጥል ሲል “ውጣ’ ብለን ያስወጣነው እኛ ነን” (ደብረጽዮን ገብረሚካኤል- የህወሓት ሊቀመንበር)። በተስፋም በአደጋም ላይ ተወጥረን እንገኛለን፡ ህወሓት ምን እየተበቀች ነው? (ጠያቂ) ፤ ልክ ነው በተስፋም በአደጋም መካከል ነን። በእርግጠኛነት የምነግራችሁ ግን ‘አሁን በመከላከል ላይ ነን፡ ወደ ማጥቃት መሸጋገራችን ግን አይቀሬ ነው” (ደብረጽዮን ገብረሚካኤል)  ይህንን በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያ ጠብቁኝ።

ከዚህ ርዕስ ቀጥሎ ደግሞ  “አሞናል በለው!!” የተባለው አየነው አረጋ” በተባለው ዘፋኝ የተዘፈነ በዘ-ሐበሻ  “ሄኖክ አለማየሁ ደገፉ” ዳይረክተርነት  የተዘጋጀ ጸረ ትግራይ ህዝብ የሆነ እውቁ  የኢትዮጵያ ንጉሰነገሥት አጼ ዮሐንስን እና አፍሪካዊው ጀኔራል የተባለለት ጣሊያንን ድባቅ የመታው እውቁ ትግሬው ራዕሲ ኣሉላ  እንዲሁም ሃይለስላሴን (እሳቸውም ትግሬነት አላቸው ስለተባሉ ይሆናል)ሆን ተብሎ ውጭ አገር ባሉ አክራሪ ወገንተኞች እና ለብጥብጥ በር የሚከፍቱ ሃይላት ‘የኛ ናቸው’ ከሚልዋቸው ከነ ቴዎድሮስ እና ከነ ምንልክ እና የራሳቸው ባንዴራ ከሰቀሉት ከነ መረራ ጉዲና (እባካችሁ እንዳትስቁ) ነጥለው በህዝባችን ሕሊና ውስጥ  በክብር እንዳይኖሩ ከታሪክ ማህደር ለመሰረዝ ‘ሆን ተብሎ’ ዘረኛ የሆነ የሙዚቃ ቪዲዮ Ayenew Arega (Shalon) - Yamenal Belew | ያመናል በለው - New Ethiopian Music 2018 ) https://youtu.be/Fp32rpZsFqo
 
እየተባለ “ዘረኞች የሚጨፍሩበት” ሆኖ ስለታዘብኩኝ ይህንን በሚመለከት ሌላ ዝግጅት አስነብባችለሁ። ጹሐፉ በትግርኛ ኢትዮ-ሚዲያ ላይ፤ በአማርኛ ደግሞ በምለጥፍባቸው ድረገፆች አቀርበዋለሁ።

 መከራችን ብዙ ነው። በዚህ ስንታገላቸው በሌላ በቀዳዳ እየሾለኩ በመምጣት ሕዝብን በሚለያዩ እና በሚያስቆጡ ስራዎች እየዘረጉ ትግሉ ፈር ልይዝ አልቻለም። ከጊዜ በላም እንዲህ ያለ ሴራ ህዝቡ፤ በተለይ በምሁራን ካልታገሉት/ካለወገዙዋቸው (ዝም ብሎ እየተቀበለ የሚጨፍርበት ከሆነ)እኔንም የምታጡኝ ይመስለኛል። የቀረችሁ ትግሬ እኔ ብቻ ነኝ መሰለኝ በየሚዲያው የምታዩኝ። ጌታ ሆይ ከነዚህ ሴረኞች መአትና ከእልቂቱ ጠብቀን። እስከዛው ጠብቁኝ። እናንተ እውጭ አገር ተቀምጣችሁ በተመቸ አልጋ ተኝታችሁ ምስኪኑን ሕዝባችን ልታለያዩ እና ልታባሉ የምትጎነጉኑት ሴራ የህግ አዋቂዎች ቢኖሩ ኖሮ ለብጥብጡ ተጨማሪ እየሆናችሁ ናችሁና የህግ ተቃውሞ ሊደርስባችሁ በተገባ ነበር። ግን የሕግ ምሁራንም ከስሜታዊው ማሕበረሰብ የባሱ ስሜተኞች ናቸውና አንድም ወንጀለኛ እስካሁን ከስሰው ማስቀጣት አልቻሉም።

በመጨረሻ- ለአንዳርጋቸው በምጠይቀው ጥያቄ ልሰናበት።

 ከእስር ተለቅቀሃል።ከእስር ስትለቀቅ ደግሞ ያለምንም የእስረኞች ልውውጥ ሳይደረግ ነው ወያኔ (አብይ) የፈታህ።  ጥያቄ፡- አንተን ለመግደል ወደ ኤርትራ ተልኮ ያልከው በአባስ አማካኝነት ለራስህ የተነገረህ ምስጢር ግን ሰውየው ያንን ተልእኮው ላለማሳካት ወስኖ ከግንቦት 7 ጋር ለመቀላቀል እንደወሰነ ሲነገርህ “ሰላይ” ያዝን ብለህ  ነው ለኤርትራኖች አሳልፈህ ሰጥተህ ያስገደልከው።  ወይንም አስሮትም ከሆነ በህይወት ካለ ወያኔ ሻምበል ዳዊትንም ይሁን አንዳርጋቸውን ለመግደል የላኩትን ሰላይ አሳልፈህ ሰጥተኸዋል እና እንድንፈታህ ከፈለግህ ሰላያችንንም ጭምር ግንቦት 7 እንዲያስፈታው አስረክበን ብለው ለግንቦት7 ሳይጠይቁ (ከትግራይ የታፈሱ ወርቅ ለቃሚዎችም ጭምር) ሳይጠይቅ አንተን መፍታቱ እመሃል ተጠቂው አንተ ወይንም ወያኔ ሳይሆን ምስኪን ተራ ዜጎች ናቸው። ሁሌም ተጠቂ የሚሆነው ዞሮ ዞሮ ‘ጠበቃ የሌለው’ ተራ ዜጋ ሆኖ ዛሬም መቀጠሉ ያሳዝናል

እድለኛ ነህ እና ያለ ምንም የእስረኞች መለዋወጥ ተፈትተሃል። እውነት ሰብኣዊ መብት አሳድረህ በተግባርህ ተጸጽተህ ከሆነ ኤርትራ ሄደህ የታሰሩትን እና ከትግሉ ለመሰናበት ፈልገን ታግለናል እያሉ ያሉት ዜጎቻችን እንድታስፈታቸው ሌላው ፈታኝ ጥያቄ እንጠይቅሃለን። መጥፎ ነገር ዶርሶብህ ኣይተሃል። ያሁ ሉ ካየህ በላ ኑዛዜ ማድረግ ይገባሃል።፡ኑዛዜ የሰው ልጆች መልካም ስነ ምግባር ነው። ለወቀሳ አትፍራ። የሰራኸው በደል አለ፤ እሱን ከሕዝብ ፊት ደምስሰው።ካልሆነ፤ እንደ ዱሮው ከስሜተኞች ጋር ማሽቃበጡን እጥልበታለሁ ካልክ፤ ስሜተኞች ሊያሽቃብጡ ይችላሉ፤ እኛም የአሽቃባጮቹ ማንቋለጥ ማጋለጣችን ይቀጥላል።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)