Thursday, April 2, 2009

ስለ የኢትዮጵያ ታጣቂ ድርጅቶች ሁኔታ ከአስመራ የተገኘዉ ምንጭ

ስለ የኢትዮጵያ ታጣቂ ድርጅቶች ሁኔታ ከአስመራ የተገኘዉ ምንጭ
ጌታቸዉ ረዳ
ወገኖቼ ፣መቸስ ዜና ሲባል ዕዉነቱም ሃሰቱም ሁሉም አግበስብሶ የሚያዳምጥ ህሊና አስካለን ድረስ የመለየቱ ጉዳይ በሗላ የሚመጣ ቢሆንም መቀበሉ ግን ዜና ነዉና የግድ ነዉ። ለስድት ወር ያህል ኢሳያስ አፈወርቂ በወታደሮቹ እና በሹማንቶቹ እንዳልተመቸዉ ከወደዚያዉ የሚመነጩ ዜናዎች ሲሰራጩ እንደነበርና አስካሁን ድረስም እየተዘገቡ ናቸዉ አላባሩም። የራሱ ትላልቅ የጦር አለቆችና በርጌስ ባለስልጣኖች እየተገደሉ አልባሌ ቦታ ላይ ተጥለዉ እየተገኙ እንደሆነ ዜናዎቹ ይጠቁማሉ። ግድያዎቹ የሚፈጸሙት በራሱ የደህንነት ክፍሎችና በተቃዋሚ ክፈሎች በኩል እንደሆኑ ይነገራል። ከፍተኛ ወታደራዊ ባለማረጎች እና ሚኒስትሮች/ የሻዕቢያ ዲፕሎማቶች ተገድለዉ ተጥለዉ የሚገኙት በራሱ/በ ኢሳያስ ትዕዛዝ እንደተገደሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች ካሁን በፊት በፊዉ ዘግቤላችሁ እንደነበር ይታወሳል። ስለሆነም አዳዲስ ክስተቶች አብረዉ እየመነጩ ነዉ። ከዚህ ጋር የተያያዘ አሰና.ካም በተባለዉ የሻዕብያ ተቃዋሚ ራዲዮ ጣብያ ሮብዕ መጋቢት 23 ቀን 2001 ዓ.ም (ባለፈዉ ሮብዕ ማለት ነዉ) በፈረንጅ March 24/2009 ባስተላለፈዉ የዜና ዘገባዉ ላይ ኤርትራ ዉስጥ ወታደራዊ ስልጠና በማግኘት እየተደራጁ መለስ ዜናዊን ለመጣል የሚጥሩ ኢትዮጵያዉን ድርጅቶች ለኢሳያስ አፈወርቂ እና ለኤርትራ ደህንነት መቆም እንዳለባቸዉ ከኢሳያስ አፈወርቅ ልዩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸዉ አንድ ስሙን እንዲጠቀስለት ያልፈለገ እዛዉ ኤርትራ ዉስጥ ከሚንቀሳቀሱ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች መሪ “አሰና” ለተባለዉ ዉጭ አገር ለሚገኘዉ የኤርትራዉያን ተቃዋሚዎች ራድዮ ጣቢያ ለምንጮቹ እንደገለጸላቸዉ አስታወቋል። ራዲዮዉ በዜና ርዕሱ ላይ “ኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያዉያን ተቃዋሚ ድርጅት ታጣቂ ሠራዊቶች ተቀዳሚ ዓላማዉ የፕረዚዳንት ኢሳያስን ሥልጣን እና ደህንነት መጠበቅ እንደሆነ ተገለጸ” በማለት ዝርዝር ሀተታዉ እንደሚከተለዉ አቅርቦታል። ኤርትራ ዉስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሠራዊቶች ያቀፈና አሁንም ብዙ ሠራዊቶችን እየተቀበለ በማሰልጠን በዕድገት ላይ የሚገኘዉ የኢትዮጵያዊያን የተቃዋሚ ድርጅቶች ሠራዊቶች፣ ባሁኑ ሰዓት ዋነኛ ዓላማቸዉና የዕለት ተለት ተግባራቸዉ ከዉስጥ አገር ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅን በመቃወም የሚሰነዘር ጥቃት ቢኖር ተቃዉሞዉን ለመጨፍለቅ ፕረዚዳንቱን ለመከላከል አጋር ሆኖ በተጠንቀቅ መቆም እንደሆነ ስሜን በምስጢር ይያዝልኝ ያለዉ አሥምራ ዉስጥ ከሚገኙት አንድ የኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ድርጅቶች የአመራር አባል መሪ ለምንጮቻችን አስታወቀ። ይህ ስሙን በምስጢር እንዲያዝለት የጠየቀዉ አስመራ ዉስጥ የሚገኝ የኢትዮጵያዊን ተቃዋሚዎች የአመራር አባል በመቀጠልም “በታሕሳስ ወር 2008 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ኤርትራ ዉስጥ ያሉት የእነኚህ የተለያዩ ድርጅቶች የአመራር አባላት በተናጠል በመሰብሰብ በኤርትራ የጦር መኮንነኖች እና ባለስልጣኖች የነበረዉ እምንት እየመነመነ እንደሄደ እና አብዛኛዎቹ የዉጭ አገር ተገዢ ቅጥረኞች እንደሆኑ እና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የራስን በራስ የመወሰን መብት የሚቃወሙ መሆናቸዉንና ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ኤርትራ ዉስጥ መመስረታቸዉ እንደሚቃወሙት ከገጸላቸዉ በሗላ በኤርወትራዊያን የጦር አበጋዞች ላይ ዕምነት እንደሌላዉ የኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ድርጅቶቹ በማንኛዉም ረገድ በተጠንቀቅ ቆመዉ ከእርሱ ጋር የጠነከረ መረዳዳት እንዲገነቡና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ለዕርዳታ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸዉ አስገንዝቦአቸዉ እንደነበረ ከገለጸ በሗላ- ከዛ በመነሳት “ሻባይ” በተባለዉ በአፍዓበት አካባቢ በሚገኝ መንደር እና በአዉጋሮ አካባቢ የሚገኝ የእነኚህ የኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ድርጅቶች ሰራዊቶች በዛዉ ወር ማለትም ከስብሰባዉ በሗላ በታሕሳስ 2008 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ልዩ የተጠንቀቅ መልክት ተላልፎላቸዉ እንደነበርና ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከነታንክ ጭምር ታድሏቸዉ/ተሰጥቶአቸዉ እንደነበር፤ ዕቅዱም “ዜሮ ሰዓት” (የመጨረሻ የሞት የሽረት አስጊ ሁኔታ ሲደርስ) በሚሆንበት ሰዓት ሻባይ መንደር ያለዉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የሽምቅ ተዋጊ ጦር “ከሻባይ መንደር በመነሳት ሰሜናዊ ባሕር ሰንጥቆ በሰሜን አሥመራ በኩል ወደ አሥመራ በመግባት”፣ - “አዉጋሮ” የሚገኘዉ የእነኚህ ክፍሎች ሰራዊትም “ከአዉጋሮ ተነስቶ መንሱራን ሰንጥቆ ወደ ሕምብርቲ በመዝለቅ የአይሮፕላን ማረፍያ ነጥቦችን በመቀጣጠር ማንኛዉም ዉስጣዊ ተቃዉሞ ለመጨፍለቅ ዝግጁ እንዲሆኑ” በምስጢር ተነግሮአቸዉ እንደነበር ባለስልጣኑ ለምንጮቻችን ምስጢሩን አጋለጠ። ይህ የፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መግለጫ እጅግ በጣም ምስጢራዊ ከመሆኑ የተነሳ ለእነዚህ የ ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች አስተባባሪና ተጠሪ ለሆነዉ ኤርትራዊዉ ኮሎኔል ማና አርአያ እንኳ ሳይቀር ምስጢሩ ድብቅ እንደነበር አመልክቷል። ባለስልጣኑ ምስጢሩን በዝርዝር በመቀጠል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሰራዊታችን ዓላማዉን ስቶ የ ኢሳያስ ጥቅም ለማስጠበቅ ታጋቾች (ሆሰቴጅ) ሆነዉ እንደሚገኙና፣ የራሳቸዉን ንድፍ በመቀየስ ኢትዮጵያዊ ተልኮአቸዉን ከመንደፍ ይልቅ የኢሳያስ/የኤርትራ ሠራዊትን በመሰለል ሥራ ተጠምዶ ይገኛል።የስለላ ስራ ለማከናወን “አምቼ” በመበል የኤርትራ ዜግነትና የዉሸት መታወቅያ እየተሰጣቸዉ በኤርትራ ሠራዊት ዉስጥ በመቀላለቀል ጸጥታን በመከታተልና በስለላ ተግባሮች ተሰማርተዉ የኤርትራን ሠራዊት ለአመጽ እንዳይነሳሳ በመቀላለቀል ሁኔታዉን ከዉስጥ እንዲከታተሉ ተመድበዋል። በተለይም የጦር ዉግያ ስልት ለመማር ከብርጌድ ሃይሎች ወይንም ክፍለ-ሠራዊት አዛዦች ጋር ተመድበዉ አመራር እንዲማሩ የተመደቡ ሰዎች የብርጌድ አዛዦች ወይንም የሰራዊት አዛዦች የዕለት ተግባርና እንቅስቃሴ ከነ ሁኔታዉ በየዕለቱ ምስጢራዊ ራፖር/ዘገባ ምስጢሩን እንዲረከቡ ለተመደቡ ክፍሎች እንዲያስተላልፉ ይገደዳሉ። ይህ የኢትዮጵያዊያን የተቃዋሚ ድርጅት ያመራር አባል ከፕረዚዳንት ኢሳያስ ጋር ባለዉ ቅርብ የሥራ ግንኙነት ምክንያት ምን ዓይነት ሰዉ መሀኖኑ ሲገልጽ፦ እናነተን ለማቋቋም በግሌ ባደረግሁት ጥረት እንጂ አሁን በምታዩዋቸዉ የኤርትራ ባለስልጣኖች ፈቃድ እንዳልሆነ ዕወቁት በማለት ይገልጻል። በተለይም ባለስልጠኖቹን እጅግ አድርጎ ያንኳስሳቸዋል። የምታዩዋቸዉ ባለስልጣኖች ብብቴ ሥር ተወሽቀዉ ከበረሃ ወደ ከተማ የገቡ ለመኖር የሚስገበገቡ ለሆዳቸዉ ያደሩ ናቸዉ እያለ ሲያሳንሳቸዉ ይደመጣል። በማለት ለምንጮቻችን ሚስጥሩን አካፍሏል።” በማለት ዜናዉን ሲደመድም በሚከተለዉ ያጠቃልለዋል። የኢሳስ አፈወርቅ ማንነት ለሚያዉቅ ሰዉ የባዕድ ጦር ከጎኑ ማስሰለፍንና መወዳጀት አዲስ ነገር አይደለም። በትግሉ ወቅት የ “ኤርትራ ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ”ን ለመምታት “ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ’ን ከጎኑ በማስሰለፍና በማሰልጠን የማይረሳ ቅራኔ ትቶ አልፏል። ዛሬም እንዚህ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጀቶች ወያኔን ለመምታት ሳይሆን የሚያሰለጥናቸዉ ኢሳያስን ለመምታት የሚነሳ ሃይል ሁሉ የተዳፈነ የባዕድ እሳት ከጓሮ ዉስጥ ወሽቆ በማቆየት አስፈላጊ ሲሆን የዉስጥ ተቃዉሞን በባዕዳን ሃይል ለማኮላሸት እየተጠቀመባቸዉ እያለ እንደሆነ የፖቲካ ታዛቢዎች ሁኔታዉን ይገልጹታል።” www.Ethiopiansemay.blogspot.com ኢትዮጵያ ለዘላም ትኑር!