Monday, November 26, 2012

አዲስ መጽሐፍ-ደቂቀ ተወልደመድኅን

አዲስ መጽሐፍ
ደቂቀ ተወልደመድኅን
ደራሲ
ጌታቸው ረዳ
(ህዳር 2004 ዓ.ም)
ዋጋ $20.00
P.O.Box 2219
San Jose, CA
95109
(408) 561-4836
ስለ መጽሐፉ ለማንበብ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ጽሑፍ ይመልከቱ።
 
ይህ ታሪክ በአገር ውስጥ ደራሲ ሲታተም የመጀመሪያ መጽሐፍ ነው። ያልተጻፉ ብዙዎቹ ታሪኮቻችንን አፈላልገን አሁን ላለው ሕዝብ እና ለተተኪው ትውልድ በሃሰት ሳይሆን ታሪኩን በእውነት ዘግቦ ታሪኩን እንዲገነዘብ ማድረግ አገራቸውን በሚያፈቅሩ ዜጎች መከናወን ያለበት ከባድ የሕሊና ግዴታ እና ሸክም ነው።
ታሪክ ማለት በአመዛኝ መልኩ በሁለት ጎራዎች በተከፈሉ ተቃራኒ እይታዎች የተከናወኑ የማሕበረሰቡ ህይወት የሚያትት ዘገባ ነው።ደቂቀ ተወልደመድኅን ብየ የሰየምኩት ይህ መጽሐፍ የሚያትተው፤በጥንቱ ዘመን ትግራይ ውስጥ በዓድዋው ተወላጅ በአለቃ ተወልደመድኅን ገብሩ እና በአክሱም ተወላጅ በአለቃ ጐበዜ ጐሹ የተመራው የኢቫንጀሊካል(ፕሮተስታንት/ከኒሻ)ሃይማኖት እንቅስቃሴ ከአካባቢው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሪዎች፤ አማኞችና የአካባቢው ተወላጅ በነበሩት አስተዳዳሪዎች መሃል የታየው የእምነት “ፍጭት” በጥልቅ የሚያትት ነው። በፍጭቱ ሂደት የተወሰዱ የጭካኔ እርምጃዎች ዘግናኝ የሆኑ የከፉ እርምጃዎች (ኤክስትሪም ሜዠር) ተወስደዋል።
የተጠቀሱት ሁለቱ መሪዎች ወደ ፕሮተስታንት እምነት ከመከነሻቸው በፊት ወላጆቻችውም ሆኑ እራሳቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አማኞች እና በተዋህዶ ትምህርት የመጠቁ የተከበሩ ሊቃውንት ነበሩ። በአዲሱ እምነታቸው ምክንያት የገጠማቸው ተቃውሞ ላለመሸነፍ እስከመጨረሻ ተጋትረው በጽናት በመቆም በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ እየተከራከሩ በርካታ ተከታዮች በማፍራታቸው አስተዳዳሪዎች፤ የሃይማኖት መሪዎችና መነኰሳት ከየገዳማቱ የተሰባሰበ ብርቱ ተቃውሞ ደርሶባቸው ለእስራት፤ለእርዛት፤ ለግርፋት፤ ለቤት እጦት፤ከማሕበረሰብ መገለል እና በመጨረሻም ለስደት ተዳርገዋል።
ይህ መጽሐፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ምክንያት ህወሓት/ወያኔዎች ለአማራ እና ለአማርኛ ቋንቋ መረን የለቀቀ የጎሳ ጥላቻቸው በጐሰኝነት ጥማት የታመመው ልቦናቸውን ለማርካት ሲሉ፤በ14ኛው ክፍለዘመን የነገሠው የቤተክህነት ሊቅ በነበረው በገናናው ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ ላይ የጥላቻ መርዛቸውን በንጉሡ ታሪክ ላይ በመርጨት፤ የውሸት መጽሐፍ በመጻፍ፤ በእዛው ዘመን በነበሩት በታወቁት የትግራይ መነኩሴው በአባ እስጢፋኖስ እና ተከታዮቻቸው (ደቂቀ እስቲፋኖስ በመባል ይታወቃሉ) የተመራው ለየት ባለ ባልተለመደ መልኩ የተከሰተው የሃይማኖት ክርክር (እንቅስቃሴ) ምክንያት፤የትግራይ አበምኔቶች ተቃውሞአቸውን በጋለ ቁጣ በማሳየት ክርክሩ እየጦፈ ከቁጥጥር በላይ እየሆነ በመሄዱ በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ሕግን ያልተከተለ የሃይል እርምጃ መውሰድ እንደጀመሩ ታሪኩን ከክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ይሌ የተጻፈውን “ደቂቀ እስጢፋኖስ” መጽሐፍ ያነበባችሁ ዜጎች የምታስታውሱት ታሪክ ነው። በዚህ መልኩ ነገሩ እየጋለ ሲሄድ የትግራይ አበምኔቶቹ ለክርክሩ እልባት ለማስገኘት ይመቻቸው ዘንድ ጉዳዩን ወደ ቤተክህነቱ ሊቅ ወደ ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ ሥልጣን በላይ ንጉሡ ወደሚኖርበት ወደ ድብረብርሃን (ሸዋ) ድረስ በመውሰድ ክርከሩን አስቀጠሉት።
በክርክሩ ወቅት በንጉሡ እና በአባ እስጢፋኖስ መሃል መግባባት የነበረ ቢሆንም፤ ተቃዋሚዎቻቸው ንጉሡን ለማሳመን ብዙ ክሶች ደርድረው ለማሳበቅ በመጣር ባንዳንድ ጎዳዮች ላይ ያለመግባባት ተከስቶ፤ንጉሡ ከረር ያለ ቅጣት በመኖኩሴው በአባ እስጢፋኖስ ላይ በይኖ ቅጣቱ ተግባራዊ እንደሆነም የሚታወስ ነው። ያ ብይን በማስታወስ ነው ዛሬ ወያኔዎች በ14ኛው ክፍለዘመን የተፈጸመው ሃይማኖታዊ የአስተዳዳር ውሳኔ በጎሳ ፖለቲካ ተርጉሞው “አማራ” እያሉ የሚጠሩት ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ የትግሬ ጥላቻ ስለነበረው እንደ እነ አባ እስጢፋኖስ እና ተከታዮቻቸው የመሳሰሉ የትግራይ የሃይማኖት ፈላስፎች አብበው እንዳይወጡ በማሰብ በእንጭጩ እንዲቀጩ አድርጓል፡ በማለት ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብን በጸረ ትግሬነት ከስሰውታል።
በጣም የሚገርመው “የሸዋ አማራዎች” የትግሬ ጥላቻቸውን የጀመሩት በዛው በ14ኘው ክ/ዘመን ጀምሮ ነው በማለት አማራው እና ትግሬው በጠላትነት እንዲተያይ መርዛቸውን በመርጨት የጻፉትን የሃሰት መጽሐፋቸውን ከሸፈቱበት “ከደደቢት” ያመነጩት የፈጠራ “አተላ ታሪክ” መሆኑን የማሳይበት በመረጃ የምከራከርበት ሌላው መጽሐፌ ነው። እኔ በዚህ መጽሀፍ ያቀረብኩት የታሪክ ሰነድ ”ትግራይ ውስጥ” በ19ኛው ክ/ዘ መግቢያ ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ሰዎች የተመራው ተመሳሳይ የሃይማኖት እንቅስቃሴ ተነስቶ በነበረበት ወቅት በወቅቱ የነበሩ የአካባቢው ተወላጅ የመንግሥት ባለሥልጣኖች አዲሱን የሃይማኖት ክርክር ባስነሱትና በመሩት በዓድዋው ተወላጅ በአለቃ ተወልደመድኅን ገብሩ፤በአክሱማዊው በአለቃ ጐበዜ ጐሹ እና ተከታዮቻቸው ላይ የተፈጸመው የ19 ክ/ዘመን ኢፍትሃዊ እና የግፍ ድርጊት በትግሬ ተወላጆች አስተዳዳሪዎችና ውሳኔ አስፈጻሚዎች የተከናወነ የእርስ በርስ ድርጊት ስለነበር፤“የትግሬዎች የውስጥ ገመና” ላለማጋለጠጥ ሲሉ፤ወያኔዎች ይህንን ታሪክ አውቀው በመደበቅ ‘እንደ ጥዋት ውሃ የነጡ ወርቆቹ የትግሬ ነገሥታት እና አስተዳዳሪዎች በሙሉ’ “የፍትሕ ሰዎች፤መብት አስከባሪዎች፤አገር ወዳዶች” የደቂቀ ምኒሊክ እና ደቂቀ ዛርአ ያዕቆብ አማራዎች ግን “አገር ሻጮች፤ከዳተኞች፤የዜጎች መብት ተጋፊዎች፤ ፍትሕ አልባዎች፤የትግራይ የጀግንነት እና ፍትሕ ታሪክ ዘራፊዎች…”  እያሉ አጉል ስለሚመጻደቁ ያንን ውስጥ ገበናቸውን ላለማስወጣት ሲሉ  እፊታቸው ላይ ተገትሮ እያዩት ያለውን በየቤታቸው የተደበቀው የቅርብ ጓዳቸውን ትተው በ14ኛው ክ/ዘመን ተፈጸመው በሺሕ ኪሎሜትር ርቀት ወደ እሚገኘው ደብረብርሃን / ወደ ሸዋ ክ/ሃገር/ አሻግረው በመመልከት የራሳቸውን የቅርብ ዘመን ጉድፍ እንዳላዩት ሆነው ሆን ብለው “ዓይናቸወን በጥቁር ጨርቅ ሸፍነው” የ19ኘውን ክ/ዘ ትልቁን የትግራይ የግፍ ተራራ አይተውት እንዳላዩት አጎንብሰው በጐሰኝነት ስሜት፤ዘልለውት በማለፍ  ወደ 14ኛው ክፍለዘመን ጉብ ብለው በወቅቱ የተፈጸመው ሃይማኖታዊ እና አስተዳዳራዊ ብይን ወደ ጐሳ ፖለቲካ የተረጐሙትን የወያኔዎችን ማለቂያ የሌለው የታሪክ ብረዛ እውነቱን ለሕሊና ፍርድ እንዲቀርብና የገዛ መልካቸውን በዚህ መጽሐፍ እንዲያዩበት ይረዳቸው ዘንድ የጻፍኩት የመጽሐፍ መስተዋታቸው ነው።
ለእናንተ የኢትዮጵያ እውነተኛ አገር ወዳዶች የሆናችሁ ሁሉ የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር ‘መጽሐፉን በመግዛት’ ወያኔዎች የትግራይን አዲስ ትውልድ ለመመረዝ በብዛት እያሳታሙ የሚያሰራጯቸው በውሸት የታጀቡ ጎሰኛ መጽሕቶቻቸውን መቋቋም የሚቻለው ከወገንተኛነት የጸዱ ሚዛናዊ መጽሐፍቶችን እየገዛችሁ መጪው ትውልድ እንዳይሞኝ መከላከያ ሰነዶች እንዲኖረው ማድረግ ነው። ይህ ጐጠኛ ባሕሪያቸው ለመመርመር ይህ መጽሐፍ ስጽፍ የታዘብኩት ነገር ካለ፤ “በ 14ኛው ክ/ዘመን የተፈጸመውን ግፍ፤ በ19ኛው ክ/ዘመን የኖሩ አስተዳዳሪዎች እና ማሕበረሰቦች ሲደግሙት፤በ20ኛው ክ/ዘመን እየኖሩ ያሉት ወያኔዎች በ14ኛው እና በ19ኛው ክ/ዘመን  የተፈጸመውን ግፍ ሳይማሩበት ያንኑን ድርጊት እነሱም እንደገና ሲደግሙት ስመለከት፤ ከ14ኛው ክ/ዘመን ሕሊና መውጣት ያቃታቸው እነዚህ ትውልዶች በ14ኛው ክ/ዘመን የተፈጸመው ግፍና ስሕተት አንስተው የ14ኛው እና የ19ኛው ክ/ዘመን የነበሩትን መሪዎች ሊከስሱ እና ሊወቅሱ የሚችሉበት ሞራል ከየት እንዳገኙት ሳስበው “ድፍረታቸው” በጣም ይገርመኛል።”
ስለ መጽሐፍ ማንሳት ላልቀረ አንድ ነገር ልበል። ካሁን በፊት ያሳተምኳቸው መጽሐፍቶች ከወያኔ በላይ መጽሓፍቶቼ እንዳይሰራጩና ለሕዝብ እንዳይዳረሱ ብዙ ሴራዎች የጐነጐኑ ቀናተኛ ግለሰቦች እና በተቃዋሚነት የቆሙ የፖለቲካ መጻጉእ የድርጅት አባሎችና ድረገጾቻቸው እንደነበሩ ካሁን በፊት አስታውሼአችሁ እንደነበር የሚታወስ ነው። ሆኖም በጠንካራ አርቆ አሳቢ አገር ወዳድ ግለሰቦች ብርታት እና ትብብር መጽሐፍቶቼ ከሞላ ጎደል ተሰራጭተው ለትውልድ እንዲተላለፉ ያደረጉ ወጣቶች፤ ግለሰቦች እና ደምበኞች እጅግ የከበረ ኢትዮጵያዊ አክብሮት እና ምሳጋናዬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ። ዛሬም በቁጥር እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ ቅጆች ያሰተምኩት ይህ መጽሐፍ ለትውልድ እንድታስተላልፉለት እንደገና በድጋሜ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
“አንዲት ኢትዮጵያ” እንደቀድሞዋ ህያው ሆና የተነጠቁባትን ዳር ድንበሯን፤ሰንደቃላማዋን እና ክብሯን ከዋየኔ በፊት ለዘመናት ታፍራ እንደነበረቺው ለማስመለስ የወያኔ የውሸት ሰነዶች ከታሪክ መድረክ አሳፍረን የምናስወግደው በእውነት የተመረኰዘ ሰነድን በማቅረብ ትውልድን ማስተማር ስንችል ብቻ ነው። ከዚህ ወዲያ ለትውልድ የምናወርሰው የተከበረ ገድል ሊኖር አይችልም።
እኔ ጐሳዬ ትግሬ ነኝ። ለብዙ ጊዜ የነሱን ውሸት ለመጋራት ብዙ የማታለያ የምቾት መማለጃ ምልጃዎች አቅርበውልኛል።ጠንካራ ኢትዮጵያዊነቴ መበገር ስላልቻሉ፤ ተስፋ ብቆርጥ ብለው በዚህ ይደናገጥና ይተወን ይሆናል በማለት ትግሬነቴን ለመንጠቅ አጉል የሆኑ ብዙ የውሸትና ጐሰኛ ሙከራዎች እና ስድቦች ለብዙ አመታት በወያኔ ጀሌዎች ተሰንዝረውብኛል።የግብዝነታቸው ክምር መጠኑ ሲበዛ አንዳንዴ በጣም እያሳቀኝ መዝናኛ አደርጋቸዋለሁ።ውሸት እና የዘረኛ ዓላመውን ስላልተከተልክ ማንነትክን ለመንጠቅ ከሚሞክር ግለሰብ ወይንም ድርጅት የከፋ አራዊት በምድር ውስጥ ሊኖር አይችልም።በአራዊት ባሕሪያቸው ማንነቴን ለመጋፋት በተጋፉኝ ቁጥር እየቀያየሩ የሚለብሷቸው  የናዚዎችና የፋሺስት ካባቸው እራሳቸው በጫሩት እሳት ሳቃጥልላቸው እጅግ እረካለሁ።መዝናኛም አደርጋቸዋለሁ።ደስታየ ግላዊ ሳይሆን ሕዝባዊ ደስታ ነው። በነዚህ የታሪክ አተላዎች ምክንያት፤ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቆሽቱ  ያረረውን ያሀል አዲስ መጽሐፍ አሳትሜ ፋሺስታዊ ካባቸው ባቃጠልኩላቸው ቁጥር ዜጎች በጣም ሲደሰቱ ስመለከታቸው “ድካሜ እንደ ጉም ይበንናል” ደስታየ ወሰን የለውም። ወያኔን በታሪክ መድረክ መጋፈጥ ጠንካራ መንፈስ እና ቆራጥነት የሚጠይቅ ቢሆንም ‘የሕሊና እርካታ እና እፎይታ/ፕለዠር/ ነው’ የምለውም ለዚህ ነው።
እነኚህ አውሬዎች የሰው ሥጋ የለበሱ የአዳም እና የሄዋን ቋንቋ የሚናገሩ “ያልተገሩ አራዊቶች” ትግሬነቴን ለመንጠቅ በሚያደርጉት የአራዊት ባሕሪያቸው ምክንያት ጓዳቸው እያስፈተሹ መሆናቸውን መገንዘብ አቅቷቸዋል። ዛሬ ወያኔም ሆነ ማንኛውንም ጎሰኛ በፈጣሪ ሥልጣን ውስጥ ገብቶ የዘር የደምና የአጥንት ጥራትና ቆጠራ ውስጥ የሚፈተፍት መስፍናዊ አውሬ ካለ የትግሬን ጎሳ አመሰራረት ታሪክ ወይንም የኢትዮጵያን ህብረተሰብ የደም ትስስር አያውቅም ማለት ነው።ሌላ ቀርቶ ከአውሬነት ሕሊና መውጣት አቅቶት አገርን ያክል ለባዕዳኖች ሲያስረክብ ከነበረው  ‘ከመለስ ዜናዊ’ አስገራሚ የህይወት ቅስፈትና የፈጣሪ ቁጣ እንኳ መማር አቅቷቸው የባንዳ እና የፋሺስት ታሪክ ትቶላቸው የሄደውን መመሪያውን እንቀጥልበታለን ብለው ሲግማሙ ሳስተውላቸው “አራዊቶቹ” ዛሬም ከዛው ተብትቦ አስሮ ከወጠራቸው አራዊት ሕሊናቸው ሰብረው መቸ መውጣት እንደሚችሉ ሳስበው ለነሱ እሳቀቃለሁ። እራሳቸውን ነፃ ማውጥ ካልቻሉ ከአውሬ ሕሊና መውጣት ያቃታቸው እነኚህ የሰው አውሬዎች የሚያሰራጯቸውን የውሸት መጽሐፍቶቻቸው መጪው ትውልድ እንዲታገላቸው ያመቸው ዘንድ የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት መጽሕፈቶች ጽፌአለሁ። ከናንተ የሚጠበቀው ግዴታ ደግሞ ይህ ታሪካዊ አዲስ መጽሐፍ በማሰራጨትና “የእውነት ብርሃን” ላለማየት ዓይናቸው ጨፍነው፤ የውሸት እንቅልፍ ተኝተው፤ እያንኰራፉ ያሉትን አብዛኛዎቹ የትግሬ ምሁራን ከተኙበት ቀስቅሳችሁ እንዲያነቡት ይህ የብርሃን መጽሐፍ ዓይናቸው ላይ እንዲበራ ማድረግ ይጠበቅባችሗል።
በጣም አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
P.O.Box 2219
San Jose, CA
95109
(408) 561-4836