Monday, October 4, 2021

ራስጌና እግርጌ መለየት የማይችል ወጣቶች ንጉሳቸው ዛሬ ዘውድ ሊደፋ ነው! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethiopian Semay 10/3/2021

 

ራስጌና እግርጌ መለየት የማይችል ወጣቶች ንጉሳቸው ዛሬ ዘውድ ሊደፋ ነው!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 

Ethiopian Semay 10/3/2021



ይህ መንጋ ጎረምሳ በሰጠው ድጋፍ ተዉት እና ጎረምሳን መደብደብ’ ሴትና ደካማ እናቶችን በጎስታፖ ፖሊሶች የሚያስቀጠቅጥ፤ የድሃ ቤት የሚያፈርስ፤ አማሮችን የሚያፈናቅል እና የሚጨፈጭፍ ንጉሳቸው አብይ አሕመድ ዛሬ  የኦሮሙማ ንጉሠ ነገሥትነት “ዘውድ” ሊደፋ ነው።  ማሃይም ወጣት እናቶቻቸው ቢደበደቡም  ብጥብጥ ያስነሳል ማለት ቅዠት ነው። ውርንጭላ ውርንጭላነትዋን ያስጣላት እና ወደ አህያነት ያስለወጣት “ዱላ” ነው። የፋሺስቶችን ቅስቀሳ እየተመገበ ያደገ ወጣት ፋሺስቶችን ሲደግፍ ማየት 30 አመት ያየነው እውነታ ነው።

የጣሊያን ፋሺስቶም ሆኑ የጀርመን ናዚዎች የመጀመሪያ ትኩረታቸው የወጣቱን ሕሊና መበረዝ ነበር። “ኦፔራ ናዚዮናለ ባሊላ” የተባለው የመጀመሪያው የጣሊያን ፋሺሰቶች ወጣት ብቅል ነበር። በአገራችን የመጀመሪያው የፋሺስቶች አገር በቀል ወጣት ብቅል (ጥንስሱ) የተመሰረተው ትግራይ ውስጥ ትግራይ ‘ደደቢት’ እና ኦሮሞ “ባሌ” ውስጥ ነበር።

ከዚያም ፋሺሰት ድርጅቶቹ አድገው ቀስ በቀስ ወደ መንግሥትነት ሲሸጋገሩ የ27 አመት የፋሺዝም መንግሥታዊ ትምህርት በየትምህርት ተቋማት እና አብያተ ጸለቶች በማስፈራረትም፤ በገንዘብም ይሁን በቅስቀሳም ሁሉ ወጠቱን በመበረዝ “ሳብቨርዢን” ተብሎ በሚታወቀው የሕብረተሰብ የብከላ መረብ አስጠምደው አሁን ላለንብት የፋሺስቶች የሥልጣን ሽግግር ውስጥ ወጣቱ በፋሺዝም ርዕዮት ተጠምቆ አገር ከሚያፈርስ አብይ አሕመድ የተባለው ከ27 አመቶቹ ባሊላ ፋሺስቶች የተገኘ ሌላ የፋሺስቶቹ አሸጋጋሪ ግለሰብ ወደ መደገፍ ደርሰዋል።

በ28 አመት ውስጥ በፋሺዝም ትምህርት የተበከሉ ወጣቶች ጉዳቸው የሚከተለው ነው። ‘ወጣት ልጃገረዶችን ከየትምህርት ተቋማቶች አፍኖ ከመጥለፍ እስከ የሴቶች ጡት ቆረጣ እና ሰው ዘቅዝቆ በአደባባይ መስቀል፤እንዲሁም አማራ ተማሪዎችን እየለዩ ከየትምህርት ገበታቸው ከፎቅ እየገፈተሩ መግደል፤ቤተ ጸሎት ማቃጠል የሰው አንገት አርዶ ሬሳን በመኪና መጎተት ተሸጋግረዋል።

ወጣት ይንገስ፤ አዛውንት ይወገድ ሰትሉ የነበራችሁ ግራ ተጋቢዎች ይኼው ዛሬ ወጣት ነግሶ ዛሬ ይኼው ለ30 አመት በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው ዜጎች ሲያሰቃዩና ሲገድሉ ሲሰውሩ የነበሩት ወጣቶች እስከ ጠ/ሚኒስቴርነት ድረስ ወደ ሥልጣን በመውጣት ለነሱ አጨብጫቢ የሆኑ የፋሺሰት “ባሊላ“ ወጠቶችን በየከተማው በማሰማራት “ወያነ ትግራይ” ሲሰራው የነበረው ወንጀል እንደገና በመፈጸም “ሌላ 30 አመት” ተጨማሪ ብሔራዊ ወንጀል እንዲፈጽሙ “ይንገሡልን” በማለት “በዓረብ አገር በዱባይ” እና “በኢትዮጵያም በናዝሬት” ያሉ  በዚህ ፎቶግራፉ ላይ የምታይዋቸው የተበከሉ የፋሺሰት “ባሊላዎች” ለሁለተኛ ዙር የፋሽስቶች ሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ድጋፋቸው እየሰጡ የሚያሳይ ለታሪክ የተዘገበ ፎቶግራፍ-ነው።

ታዲያ እኔ የገረመኝ እንደዚህ የመሳሰሉ በፋሺስቶች ርዕዮት የተበከሉ ወጣቶች ተይዞ ነው የሰው ልጆች መብት ቢረገጥ አንቀጥቅጥ ብጥብጥ አስነስቶ ፋሺስቶችን ያስወግዳሉ የሚባልላቸው?

ለመሆኑ ይህንን አብይ አሕመድ የተባለው የስለላ መረብ በመዘርጋትና በመቆጣጠር የአገር ምስጢሮችን ለኦነግና ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት የታወቀው በብዙ ብሔራዊ ወንጀል ተጨማለቀው (እራሱም ወንጀል መፈጸሙ ፓርላማ ውስጥ ያመነ) የሥልጣን ጥም ያሰከረው “ጂሃዳዊ ወንጀለኛ” ሰው ከያዘው ኢሕጋዊ-ሥልጣን ማስነሳትና እሱንም ማሰር የሚያስችል ብዙ ብሔራዊ ወንጀሎች ተፈጽሞ ባለበት “አሁን! አሁን! አሁን ዛሬ!” እንኳ ሕዝቡ መነሳት ያልቻለ፤ (ያውም ብዙዎቹ ደግሞ “አግዚአብሔር ሃይላችን ነው” እያለ በአቡነ ዘበሰማያት መዘዝ የተጠመደ “ማተቡ እየተበጠሰ ቆሞ የሚያስበጥስ ፤ ጥፊ እና መንገላታት እራቱ ያደረገ” ማሕበረሰብ ተይዞ) ለወደፊቱስ ቢሆን ይህንን “ጂሃዳዊ የሥልጣን ጥመኛ” ሰው የሚያስወግድ ሰላማዊም ሆነ የብርት ትግልና ብጥብጥ ይነሳል ብለው የሚቃዡ እና ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ሳደምጥ እጅግ ይገርሙኛል። እስካሁን ድረስ የተፈጸመው ግፍ ይበዛል ወይስ ስለ የትንቢት በብጥብጥ ተስፋ አብይን ማስወገድ? የትኛው ግፍ ይበረታል?


ፍራሽ አዳሽ የሚባለው ቀልድ የሚጫወተው ትምህርት ሰጪው ቀልድ ሰሪው “ተስፋሁን ከበደ” እንዲህ ብሎ ነበር፡


“አያ ጅቦ አንድ ቀን ባለቤቱ አርፋበት አህዮች መርዶውን ሰምተው “አይ ምንም ጠላት ብንሆን ‘ሓዘን ነውና’ ብለው ሰብሰብ ብለው ለቅሶ ጋ ይሄዳሉ ። አንድ ሞሾ አውራጅም ፊት ለፊቱ ቆማ “ሙሾዋን መውረድ ጀመረች”፡ አህዮቹ ልክ ዱንኳኑ በር ሲደርሱ

“ምንም እሩቅ ቢሆኑም ይሰማል ድምጸዎ

አስገራሚ ነው ግርማ ሞገስዎ

እንደምነሽ ምን ነካ አበዎ..”=

እያለች ሙሾ ስታወርድ

አያ ጅቦም ወደ ድንኳኑ እንዲገቡ እየጋበዛቸው ‘ግቡ ግቡ’ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ እንዲህ ሲል ለሙሾ አውራጅዋን መለሰላት፡

“እውነት ተናግረሻል እውነትም ብለሻል

ይህ ሁሉ ሐዘንተኛ ምን ይብላ ብለሻል!”

 አላት ይባላል።

እንዲህ ያለ ወደ ጅቦች ድንኳን የሚንጋጋ የጅቦች ሙሾ አውራጅ ባለበት የወጣት መንጋ ፋሺሰቶችን ስርዓት ይጥላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ውሃ መዝገን ነው። አሳዛኙ ክስተት ግን ሁሌም ራስጌና እግርጌ መለየት የማይችል ወጣት በማጎብደድ ይጀምርና በመጨረሻ እራሱን ማንገላቻ እስርቤት ውስጥ ገብቶ ራስጌም እግርጌም በማይለይበት ማሰርያ ቤት ተኝቶ የገዛ እራሱን ያገኘዋል። (ሰው ይማርበት ሼር አድርጉ)

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)