Thursday, October 16, 2014

ትችት በገብሩ አስራት መጽሐፍ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) ክፍል 2

ትችት በገብሩ

ራት መጽሐፍ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

ክፍል 2


Source YeweYane Gebena Mahder book cover - Meles and gebru
ይህ ባለፈው ሰሞን በገብሩ አስራት ያቀረብኩት የመጀመሪያው ትችት፤ አሁንም የቀጠለ ነው። ይህ ክፍል 2 ነው። ገብሩን ስተች፤ የለፋበት፤ እረፍት አጥቶ፤ አንቅልፍ ሳይተኛ ላመታት ያዘጋጀው አዲስ መጽሐፉ መመስገን ያለበት ለሌሎቹም መልካም አርአያ መሆኑን ገልጫለሁ። በገብሩ መጽሐፍ ትችቴ ወደ ሁለተኛው ክፍል ከመግባታችን በፊት በፊት ግን አቶ ይልማ በቀለ በተባለው ጸሐፊ መጠነኛ ትችት አቅርቤ ወደ ዋናው አንገባለን። አቶ ይልማ በቀለ በገበሩ ላይ “The honorable Ato Gebru Asrat and his politics በማለት በየድረገጹ የተቸው ትችት የማልስማማበት መሆኑን ትንሽ ልበል።
በገብሩ ላይ ለብዙ አመታት ከይልማ ይልቅ የበረታ ትችት ሳቀርብ የነበርኩ እኔ ነኝ። አሁንም የሰላ ትችቴን እየቀጠልኩበት ነው። ሆኖም ይህ አዲስ መጽሓፍ ሲጽፍ በአግባቡ ምስጋና መስጠት ተገቢ ነው። መስመር የጣሰ፤ መረጃ የጎደለው የይልማ በግበሩ ላይ ትችት ግን አልቀበለውም። ወደ እኛ ተቀላቀሉ፡ የምታውቁት ምስጢር ንገሩን አንላለን። ሲነግሩን ደግሞ “ልብ ወለድ” ትሉታላችሁ። ልብ ወለድነቱን ደግሞ ማሳየት ተገቢ ሆኖ በደፈና ማጣጣል ግን ተገቢ አይደለም። ተስፋዬ ገብረአብን ሲያደንቁ የነበሩ ቱለቱላዎች አሁን የገብሩን መጽሐፍ ልበወለድ ሲሉት ይገርመኛል።

ይልማ የማውቀው ለሻዕቢያን/ኤርትራኖችን ወግኖ ማልቀሱ የተለመደ ነው። ገብሩ አስራት የሉዓላዊነትቻንን ጉዳይ ችግሮች እና መፍተሔዎቻቸው ከነታሪኩ የቻለውን ያህል አፍረጥርጦ በመግለጹ አቶ ይልማ በቀለ “ዋር ሞንጀር” (ጦርነት ናፋቂ) በማለት የሰነዘረው አግባብ ያልሆነ ዘለፋውን መወገዝ አለበት።

ባይገርማችሁ እንዳውም ገብሩ የኤርትራ ጉዳይም ሆነ ወደቦቻችንን ለማስመለስ በሚመለከት ሁለት መፍተሔዎችን ጠቁሟል። አንደኛው ‘በሕግ ከስሰን/ሞግተን’ ሁለተኛው ደግሞ ‘በፌደረሺን/ኮንፌደረሺን..’ ችግሩ መቋጨት ነው ኢላል። ገብሩ ጦርነት አይደግፍም። የምደገፈው እኔ ነኝ ። በጉልበት ነጠቅነዋል ያሉትን ወደቦቻችን እና ሉዓላዊነታችነን “በጉልበት” መመለስ አለበት እላለሁ። አለ ጉልበት ወደ ጠረጴዛ የሚመጣ ኤርትራዊ የለም ወይንም ወያኔ ቡድን የለም። ልክ አሁን ወያኔ አሻፈረኝ ብሎን አንዳለው ማለት።) ሓቅ በዚህ ዓለም ውስጥ ቦታ የለውም። ገንዘብ እና ጉልበት ወሳኝ ናቸው። በእንሰሳ ኣለምም ጉልበተኛው ብቻ ይኖራል። ይልማ በቀለ ከገብሩ የሚለየው፤ ይልማ “ኤርትራኖች አገራቸውን አንዲሁ ካልተዋጉ በዋዛ አይሰጡምን፤” (ይልማ ‘አገራቸው’ ሲል የነሱ አገር አንጂ የኛ አገር አንደሆነም እምነት የለውም) ስለዚህም  “ጦርነት ከማድረግ ከመጪው “የሰለጠነ” ኤርታራዊ መንግሥት ሲመጣ በጠረጴዛ ይፈታል” በማለት የሚቃዠው የቀን ሕልመኞች መፍትሔውን በምንም መልኩ ከገብሩ መፍትሔ ያልተለየ መሆኑን እያወቀ “ድምበራቸው አንንካ” የሚለውን ጅላጅል ቅዠቱን አንደ መፍትሔ ቆጥሮ  “በጦርነት ሳይሆን በሕግ” እንጠይቅ የሚለውን የገብሩ ምኞት እና የይልማ ቅዠታዊ መፍትሔ አንድ ሆኖ እያለ፤ ገብሩን “ዋር ሞንጀር” (ጦርነት ናፋቂ) ብሎ ከሻዕቢያ የተዋሰውን “የሻዕቢያዎች መፈክር” ገብሩን መዝለፉ የቆየ የይልማ ለሻዕቢያ ሙሾ ማውረድ አላስገረመኝም። በነገራችን ላይ ይልማ ለሻዕቢያኖች መሽኮርመሙ አዲስ አይደለም።

ሌላው አስገራሚው ይልማ የግበሩ መጽሐፉን ማጣጣል ደግሞ አንዲህ ይላል።Like all books written by Woyane officials present or past this book is also fiction trying to pass as a serious work.” 

ወንድምቻን ይልማ “ልብወለድ መጽሐፍ” ብሎ የሚተቸውን መጽሐፍ ልብ ወለድነቱ አላሳያንም። የሰው ልጆች እንዴት አረመኔ ጨካኞች ነን? ይገርማል!


ይህ ማስተዋቂያ ደግሞ እዩልኝ “One would think anyone that wants his book to be read by many would approach ESAT. From what I know he has chosen VOA and the Tigrean speaking radio programs to talk to the rest of us. He is still preaching to his own Kilil” እንዴ! ትግርኛ የሚባል ራዲዮንም ይዘጋ እና የግንቦት ሰባት ሳተላይቱ ራዲዮ ጣቢያ “ኢሳት” ይያዘው ነው? ገብሩ የ ቪ ኦ ኤውን ትግርኛ ብቻ አይደለም ተጋብዞ የተናገረው “አማርኛውንም ክፍል ነው”። እንዴት ነው?!  የአዳነች ፍስሃየ እና የገብሩ አማርኛ አይሰማኝም ለማለት ከሆነ ሌላ ነገር ነው፤ ግን ትግርኛ ብቻ ተጠቅሞ ለትግርኛ ተናጋሪው ሕዝብ ስለ መጽሐፉ ይዘት ተጠይቆ መልስ መስጠቱን ጠባብነት ነው ማለት በኢሳት ፍቅር ታውሮ ለኢሳት ማስተወቂያ መሰራት ነው። ፈረንጆች እንደዚህ ዓይነት ማስታወቂያ ሲያገኙ Here we go again! ይላሉ::

ይልማ በቀለ ሻዕቢያዊው ግንቦት 7 የሚቆጣጠረው (ገንዘቡ ምንጭ የምታውቁት ነው) ኢሳት ሳተላይት የተባለው ጣቢያ በገብሩ አማካይነት ማስታወቂያ ለመስራት ሲያምረው “ቪ ኦ ኤን” በማጥላላት ኢሳትን ሲያወደስ ያስገርማል። ኢሳት እና ቪ ኦ ኤ አንድ ለማድረግ መሞከሩ እኔን “ፈገግ” ከማሰኘቱ በላይ ሰውዬው የ ቪ ኦ ኤን ረዢም የሚያስመሰግን ስራቸውን ከንቱ ማድረጉ የሰውየው ጭንቅላት ወገናዊነትን ያሳያል። ቪኦኤ ያልሰራው ስሕተት ኢሳት ያልሰራው ወገንተኛነት ምን አለ? ቪኦኤ ትንሽ ስሕተት/ወገንተኛነት ሲሰራ መጮህ፡ “ኢሳት የተባለው የሻዕቢያ ቱልትላ እና ወገንተኛ ጣቢያ” አንደቡቹላ ነጋ ጠባ ለሻዕቢያና ለጠላቶቻችን ወግኖ ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ግን “”ኢሳት ነፃ ሚዲያ እና የሕዝብ አፍ እና ጆሮ ፤ለማንም ያልወገነ” ኢትዮጵያዊ ሚዲያ ብሎ ማጨብጨብና ራስን ከማስገመትና ማታለል አልፎ  በግንቦት 7 ጋዜጠኞች የተሞላው እና በነ ንአምን ዘለቀ የግንቦት 7 መሪዎች የሚመራው ኢሳት አታውቁትም እያለ እያሺፈብን ነው ልዩ አስገራሚነቱ። ወይ ቱጉዱ!!!! 

ስለ ዲሞክራሲ ትቶ ስለ ወደብ ማጣት ዋነኛው ያገሪቱ ችግር ነው ብሎ አንደ ዓይነተኛ ችግር ማውራቱ “ፌዝ” ነው ብሎ ግበሩን መተቸቱ፤ የይልማ በቀለ ሌላው ቅዠቱ ነው። ዲሞክራሲ ኖሮህ ሶማል እና ጁቡቲ ቢዘጉብህና ኤርትራኖችህ እና ሶማሌዎች በግብፆችና በዓረቦች እየታገዙ ጦርነት ቢለኩሱብን ምን ልታደርግ ነው? ዲሞክራሲ ወደብ ሊሆንልህ ነው?መሳሪያው፤ሸቀጡስ፤ንግዱስ በየት ነው የምታስገባው? ስለላውስ አንዴት ልትቆጣጠረው ነው? አገርና ኢትዮጵያዊ መንግሥት ሳይጨብጡ ስለ “ዲሞክራሲ” መፏከት ምን እሚሉት ሱሰኛ እከክ አንደሆነ ይገርመኛል። ደግሞ ገብሩም እኮ ስለ ዲሞክራሲ ከወያኔ ሪቪሊሺናሪ ዲሞክራሲ እያወዳደረ በሰፊው ገልጾልናል። ምን ትፈልጋለህ? ይልማ! ከዚህ ወዲያ ትንተና ያንተን ትንተና አሳየንና እንመልከተው። ገብሩን አስታከህ ቪኦን መዝለፍ እና ስለ ኢሳት ማስታወቂያ መስራትህ ግን ጎበዝ አራዳ ነህ።
አንዳውም ይልማ በቀለ የቱ ይቀደም ካልክስ “ባሁኑ ጊዜ፤ በዚችው ሰዓት አማራው ሕብረተሰብ አንተው አንደደላህ “ስለ ዲሞክራሲ” ነው የሚጨነቀው ወይስ “ስለ ህልውናው” ? አገር ማጣት ዲሞክራሲን አያስናፍቅም። ዲሞክራሲ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ አስተዳደር ነው። መጀመሪያ አገር ማቅናት ነው።ኢትዮጵያዊ የሆነ መንግሥት አጥተናል! ባሁኑ ሰዓት ወታደራዊ መፈንቅል አድርጎ ኢትዮጵያዊነትን መጀመሪያ የሚያስከብር ‘ወታደር’ ቢመጣ ስለ ዲመክራሲ የምጨነቀው ከዚያ በሗላ ነው። ዲሞክራሲ ፈዛዛዎች የሚቃዡት ቅዠት ነው! በዲሞክራሲ ሰበብ እጦት አይደለም ይህ ሁሉ ጋዜጠኛ ይህ ሁሉ አማራ እየጠፋ እየታሰረ ያለው። አገራችን በጠላት በመያዟ ነው! ጋዜጠኛ ማሰር ፤የዜጎች የመናገር መብት “ማገድ” የዲክቶሮች ጸባይ ነው ። ማሊ ወደ ዲሞክራሲ የተሸጋገረቺው መጀመሪያ ያገሪቱን ሰሜናዊ እና መላው ሉዓላዊነቷ ሕልውና ካረጋገጠች በሗላ ነው ወደ ምርጫ እና ዲሞክራሲ የተራመደቺው። ማሰር፤መግደል፤ማፈን ምን ጊዜም የሚኖር የዲክታቶር ሥርዓት ጸባይ ነው። ሕዝብ የሚፈጅ፤ አማራውን የሚጨፈጭፍ ዲክታቶር ሳይሆን ግን ጠላት ስለሆነ መጀመሪያ መቀመጫህን ማስከበር እና አንዲተኰርበት ማድረግ ነው! የቡርዣ ዲሞክራሲ ቅዠታችሁን ወደ ጓዳ አቆዩት! የሰለጠነ ኤርትራዊ መንግሥት ይመጣል እና የሉዓላዊነት ችግራችንም ሆነ ሰላማችንን፤ልማታችነን በጠረጴዛ አንፈታዋለን የምትለው የወያኔ መሰል ፕሮፓጋንዳችሁን አንተ እና መሰሎችህ አቁሙ! አሁን ወደ ገበሩ እናምራ።    

በድጋሚ አሁንም መጽሐፉ በጣም ዋጋ ያለው ለተመራማሪዎች ጠቃሚ መጽሐፍ ነው። በተደጋጋሚ ስተቸው ድካሙንም ሆነ ሞራሉም ወይንም መጽሐፉን ዋጋ ለማሳጣት ሳይሆን መገለጽ የነበረበት እሱ በማወቅ ወይንም ባለማወቅ ወይንም በሆነ ምክንያት ሊዳስሳቸው ያልፈለጋቸው ጉዳዮች ከመጽሐፉ አብሮ መካተት የነበረባቸው ጉዳዮች መዘለላቸውን ለመጠቆም ወይንም ቀጣይ ዓለማ ካለው በሚቀጥለው መጽሐፉ በራሱ ዕይታ አንዲዳስሳቸው እና መልስ አንዲሰጥባቸው ለመጠቆም ነው። መጽሐፉ በተለይ ቀንደኛ የጠላት የቅጥረኞቹ ቁንጮች መለስ ዜናዊ እና ስበሓት ነጋን እና ሥዩም መስፍን ማንነት በማጋለጡ እጅግ አንጀቴን ያራሰበት የመጽሐፉ ከአስኳሎቹ አንዱ ክፍል ነው። ‘ከፈረሱ አፍ’ የሚሉትም ይኽ ነው። ኢሓፓዎች ቢያንስ የነ ጸጋዬ ደብተራው ሁኔታ አንዲያውቁ አድርጓል። ቅሬታ ካላቸውም ጋብዘው መወጠር እና እውነቱን ማፈላለግ የኢሕአፓዎች የሚዲያ ፈንታ ነው።

 በተለይ አስገራሚው ነገር የመለስ ዜናዊ አባት ወደ መቀሌ ሲመጡ የሚያርፉት እና የሚዝናኑት ከኤርትታኖች/ኰንስላ ሓለፊዎች ጋር መኖሩን እና ከነሱ ጋር ተመሳጥረው ወደ ኤርትራ ኮንትሮባንድ እየነገዱ ሳለ ተይዘው መቀጣታቸው፤ ከሁለት አህያ ባለቤትነት ተነስተው በርካታ ሃብት ማከማቸታቸውና የመለስ ዜናውን ልጅ ውድ ት/ቤት ለማስገባት የተትረፈረፈ ገንዘብ ማከማቸተቸውን እና የዝርፊአው መጠን  የገለጸውን እና እሳቸውም ከኤርትራኖች ጋር ወግነው በገብሩ ላይ ማሴራቸው እና እነ ስብሓት፤መለስ እና የመሳሰሉትንም በኤርትራን ኮንሰላሮቹ እየተመሩ “በኤርትራኖች” ወጥመድ ተከብቦ ያሰለፈው ንትርክ ስመለከት የሕሊና ጭንቀቱ መገመት አያስችግርም። (የሱን የተባባሪነት ድርሻው አንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው)።
ያም ሆኖ እሱ በነበረበት አስተዳዳር አንመልከት። ይህ አስረዳደራዊ ችግሮቹ በዲሞክራሲያዊ እጦት እንጂ ሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን አልዳሰሳቸውም።አንዲያውም አንዳንዴ በሕዝቡ የተደረገ ጥናት “አስተዳዳር በደል” አለን ያሉ ጥቂቶች አንደነበሩ መግለጹ አብዛኛው ሕዝብ ፍትሓዊ የሆነ አስተዳዳር ነበረው ለማለት የሚቃጣው ይመስላል።

አቶ ገብሩ በመጽሐፉ ያነሳቸው አገራዊ ጉዳዮች ሲወሰኑ ወደ ኋላ ዞር ብዬ ስመለከተው “ስሕተት” ነበር የሚለውን ስመለከተው፤ ከጓዶቹ ጋር ሆኖ መንግሥታዊ ውሳኔዎች እና የመሳሰሉ የፖሊሲ እና የሉዓላዊነት ጉዳዮችን በሰፊው ሲያብራራ፤በራሱ አስተዳዳር ስር የተፈጸሙ የሕዝብ በደሎች ግን በጥልቀት አልዳሰሳቸውም።የተደረገው ክርክር “ትግራይ ኢዲሞክራት በሆነ አስተዳደር እየተመራች ነው” የሚለው ከበስተጀርባ ሆኖ መለስ የሚመራው የመለስ ቡድን በገብሩ ላይ ያነጠጠረ ንትርክ አንብበናል። በስፋትም አመንጪው እና ከምን የተነሳ ተንኮል እና ውንጀላ መሆኑን ለመግለጽ ሞክሯል። እኔም መለስ እና ኤርትራኖች የዚያ ሴራ አጠንጣኖችና መሪ ተዋናዮች መሆናቸወን አልጠራጠርም።

አቶ ገብሩ አስራት ከ1983 እስከ 1993 ዓ.ም የህወሓት የአመራረ አባል እና የትግራይ ፕረዚዳንት በመሆን ሰርቷል። በነዚህ ዓመታት ትግራይን ባስተዳደረበት ከሕዝቡ ሲሰሙ የነበሩ በርከታ ቅሬታዎች ነበሩ። ለምሳሌ አንደኛው ቅሬታ ገበሩ አስራት የደርግ የዕድገት በሕብረት ዘመቻውን ጥሪ አቋርጦ ወደ መቀሌ ሲመጣ ሸሽገው እቤታቸው ወስጥ አቆይተው ወደ በረሃ  የሸኙት የስፖርት መምህር ስለ ነበሩት ሰው ጉዳይ እናነሳለን።
እኝህ ሰው ዛሬ የመቀሌ ከተማ ኗሪ ናቸው (በሕይወት ይኑሩ፤ ይታመሙ አላውቅም)። እነ ገብሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የደርግ “ተራ” የኮሚኒሰት የፓርቲ አባል ነበርክ በሚል ሰበብ በላባቸው የሠሩት መኖሪያ ቤታቸው ነጠቅዋቸዋል። ዛሬ በወር $400.00 (አራት መቶ ብር) የጥሮታ ደሞዝ እያገኙ ከ6 ለጆቻቸው ጋር ቤት መኖሪያ አጥተው በመንከራተት ላይ ይገኛሉ። አሁን በተነጠቀው በቤታቸው እየኖሩ ያሉ ጉልበተኞች የተሰራው የድሮ ህነፃ አፍርሰው ፎቅ ሰርተውበታል።

ገብሩ  ከጫካ ሥልጣን ወደ መንግሥታዊ ሥልጣን ተሸጋግሮ የትግራይ ክፍለሃገር አስተዳዳሪ ሆኖ  ሲሰራ በነበረበት ጊዜ በወየኔዎች አስተዳደር የተነጠቀው የመቀሌ ከተማ መኖሪያ ቤታቸው በማን አለብኝነት የተወሰደባቸው በመሆኑ ይህ ኢፍትሓዊ ውሳኔ አንዲቀለብስላቸው እና ቤታቸው አንዲመለስላቸው ለአቶ ገብሩ “ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያያሰሙም” ገብሩን ለማነጋጋር አልሰማም በማለት ወደ ጽሕፈት ቤቱ ውስጥ ለመግባት ችግር ገጥሟቸው እንደነበር ከብዙ አመታት በፊት ባንድ ሚዲያ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው በነበረበት ወቅት ገልጸዋል።

እሱን የሚያውቁ በርካታ ሰዎች ወደ ገብሩ በመላክ አንዲያነጋግራቸው መልክተኛ ቢልኩም አቶ ገብሩ አላነጋግርም ብሎ ካሰለቻቸው በላ በስንት መከራ አግኝተውት ባነጋገራቸው ወቅት “ጉዳዮን አልሰማም”፤ “አላውቅም ብሎ አሰናበተኝ” ብለው እሮራቸውን ገልጸዋል። ገብሩን አግኝተው ኢፍትሓዊነቱን ለማስረዳት ሞክረው ፤ ለቤታቸው መነጠቅም “ምክንያቱን” አንዲገለጽላቸውና በሕግ ፊት ቀርበው መከራከሪያ ነጥባቸውን አንዲያቀርቡ  ትዕዛዝ “አስተላልፍልኝ” ብየ ብለው አምቢ አለኝ። ሕዝቡም መኖሪያ ቤቱን መነጠቁ አግባብነት የለውም፤ ይህ ሰው ምንም የበደለው ነገር የለም፤ እያለ ለባለሠልጣናቱ ባጋጣሚው ስብሰባ እንደምሳሌ የኔን እና የመሰል ሰዎች አቤቱታ ቢገልጽም፤ አቶ ገብሩ ግን  “የምረዳህ ነገር የለኝም በማለት አሰናበተኝ። በማለት “ፍረድ ቤት ቀርበው ሳይከሰሱ ንብረታቸው በማጣታቸው መብታቸውን ለማስከበር አንዲሞግቱ ዕድል ሳይሰጣቸው” ንብረታቸው ተነጥቆ  በፍትሕ ተቋም ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ተነጥቀው ከ6 ልጆቻው ጋር ሜዳ ላይ ተጥለው በስቃይ ኑሮ አንደሚኖሩ ገልጸዋል።

 አቶ ገብሩ ጋር ለመነጋገር ስሄድም ዕድሉን አጣሁ።በስንት መከራ ዕድሉን አግኝ ሳነጋግረው አላውቅም ያለኝን ገብሩ፤ “ከሥልጠኑ ሲወድቅ” (የሳቸው ቃል ነው) መንገድ ላይ አግኝቼው ስለ ጉዳዩ አነጋግሬው “በጣም ተሳስቻለሁ” በማለት መሳሳቱን ገለጸልኝ። እኔም ሥልጣን ላይ እያለ እንደ እየሱስ ክርስቶስ እሱን ለማግኘት ችግር ሆኖብኝ ‘ተራ ጠብቄ’ በስንት መከራ እሱን ለማነጋገር የቸገረኝን፤ አሁን ከሥልጣን  ማማው “ሲወድቅ” እመንገድ ላይ አጋጣሚ አግኝቼ አነጋግሬው፤ሥልጣን ላይ እያለ ለማነጋገር የነፈገኝ ሰው መሳሰቱን ሲገልጽልኝ ከማዘን ሌላ ምን ማለት እችላለሁ? ሲሉ ቁጭታቸውን እና ምሬታቸውን ገልጸዋል። ይህ እና የመሳሰሉ ለምሳሌ አንደ እነ ወ’ሮ ኤልሳ ካህሳይ የመሳሰሉ ሰዎች ንብረታቸው ፤ንግድ ቤታቸው፤መኪና መኖርያ ቤታቸው ያለ ምንም ፍረድ ቤት ክስ እና ሙግት ፤ያለ ምንም ወንጀል ጥፋት ለበረካታ አመታት ታስረው በነፃ የተለቀቁ አሁን ቤት አጥተው እየተንከራተቱ ያለ በውቅቱ ገበሩ ሲያስተዳድርበት በነበረበት ክ/ሀገር የፍትሕ ችግር ታይቷል። ገብሩ አስራት ባገሪቱ የታየው ኢፍትሓዊ የሆነ የጠላት ስርዓት መለስ በግምባር  ሃለፊነት ተጠያቂ አንዳደረገው ሁሉ ገብሩ ይህነን እንዴት ይመለከተዋል?
 
“የ.ህ.ወ.ሐ.ት.  ታጋዮች  በሰባት  ጥይት  ደብድበው  ጫካ ወስደው ጣሉኝ”  በማለት ህወሓትን በጭካኔአቸው የሚኰንን፤ ነብሰገዳይ የተጠራቀመበት ድርጅት መሆኑን ኢትኦጵ ቅፅ 2 ቁጥር 016 መስከረም 1993 ዓ.ም.  ቀርቦ ቃለ መጠይቅ የደረሰበትን ግፍ የገለጸ ወጣት ጉዳይ አንዳስሳለን (የወያኔ ገበና ማሕደር በሚለው መጽሐፌም ተጠቀሰ ታሪክ ነው።) ወጣቱ በወቅቱ የድቁና ትምህርት ያጠናቀቀ ነው። የትግራይ አስተዳዳሪዎች የነበሩት አቶ ግበሩ አስራት እና ወ/ሮ አረጋሽን ይከሳል።

ሰሚ አጥተው በየቤቱ በጸጥታ የተዋጡ የሚጮህላቸው ያጡ ዜጎች እሮሮአቸው  ፍትሕ አጥቶ ለዓመታት የደም ዕምባ ያፈሰሱት የወያኔ ሰለባዎች የሆኑት የትግራይ ቀሳውስትና ዲያቆናት አንዲሁም ሌሎች የትግራይ ኗሪዎች፤ በወቅቱ የትግራይ ክፍለሀገር (የትግራይ ከልል መንግሥት ይሉታል በዛሬው በወያኔዎች አጠራር) በወቅቱ ወንድሜ ገብሩ አስራት ፕረዚዳንት በነበረበት ወቅት “በረሃ እያለን ለፈጸምነው ወንጀል አንጠየቅበትም” ብሎናል የሚል ክስ ቀርቦበታል።  ከሳሾቹ ልክ ከሆኑ በወያኔ የተጠቁ ፍትሕ ፈላጊዎች በሥልጣን ማን ያህለኝነት ያሰናበታቸው አቶ ገብሩ አስራት እና የእርሱ ረዳት የነበረቺው ወ/ሮ አረጋሽ አዳነም በዚህ ታሪክ የተጠቀሱበትን ሁኔታ እንመልከት።

ብርሃኔ ገ/ሕይወት ይባላል። ወደ ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ትግል ውስጥ እንዲቀላቀል የቀረበለትን ጥሪ ባለመቀበሉና በመቃወሙ፤ በተደጋጋሚ መታሰሩንና በመጨረሻም በአሰቃቂ ሁኔታ በሰባት ጥይት መደብደቡን ይነግረናል። ይህ ወጣት ቤተክርስቲያን በማገልገሉም ሳቢያ፤ ከፍተኛ ተጽዕኖ ተደርጎበት የዲቁና መታወቂያውንም የሕወሐት ታጋዮች ቀደውታል። የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በሀገር ውስጥ ሕክምና የማይድን መሆኑንም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሰኔ 20 ቀን 1986 አረጋግጧል። ይህንንም ማረጋገጫ የሰጡት ከፍተኛ ሕክምና እንደሚያስፈልገው ያረጋገጡት ዶ/ር ተመስገን ፍጡር (ቀዳጅ ሐኪም)፤ ዶ/ር ዘሩ ገ/ማርያም (ሜዲካል ዳይሬክተር) ፕሮፌሰር W.Mcquillan (የቀዶ ሕክምና አማካሪ) ናቸው።

ይህ የ35 ዓመት ወጣት ከዚህ በላ ከደረሰበት ጉዳት ለመዳን እርዳታ ያደርጉለት ዘንድ የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን አነጋግሯል። "ዳውተር ኦፍ ቻሪቲ" ከተሰኘ ግበረ-ሰናይ ድርጅት ጥሩ ምላሽ በማግኘት ከውጭ ሀገር ገንዘብ ቢሰበሰብለትም ገንዘቡ በድርጅቱ ሐላፊዎች መበላቱንና በኋላም እሱ ሜዳ ላይ መጣሉን ይናገራል። ወጣቱ በዚህ ጉዳይ ኬንያ ድረስ ሄዷል፤ ወደ ትግራይ ብቅ ብሎም የትግራይ ክልል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነን አነጋግሯል። እዚያም አንደር-ግራውንድ (ከመሬት በታች) አስገብተው ለረዢም ሰዓት በጥያቄ እንዳፋጠጡት ይናገራል ። ይህ ወጣት ሰውነቱ ላይ ያለው ቁስል እያመረቀዘ እንዳስቸገረው ለማየት ችለናል። … ይህን ቁስሉን ለማዳንና ከበሽታው ለመፈወስ 6 ሚሊዮን 200 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ (103 ሺህ ዶላር) እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ጆን.ኢ.ኤ የተባሉ በኬኒያ የሚገኙ ሐኪም ያረጋገጡበትንና እ/ኤ/አ ዲሴምበር 21/98 የተፃፈ ወረቀትም ይዟል።

ዋና ዋና አንኳሩን ለማስጨበጥ አሳጥሬ ጉዳዩን ለማሳየት የቀረበ እንጂ ሙሉ ታሪኩን አይደለም።

ስምህ ማን ይባላል?

ብርሃነ፦
ብርሃነ ገ/ሕይወት።

ትውልድና ዕድገትህ

ብርሃነ፦
ትውልዴ ዓድዋ አውራጃ ሲሆን፤ ቀበሌው ጣቢያ ኮረም መንደሩ እንዳ መትከል ስብሃቱ ይባላል።

ዓድዋ አውራጃ እያለህ የደረሰብህ በደል ምንድ ነው?-

ብርሃነ፦
ቤተክህነት ተማሪ እያለሁ በ1975 ዓ.ም. ከአክሱም ጽዮን ዲቁና ተቀብየ ስሄድ በውድቅት ሌሊት የማላውቃቸው ሰዎች ኢሳ ወደ ሚባል ወረዳ አስረው ወሰዱኝ። "በአሁኑ ወቅት ያለው ጳጳስ ከደርግ ጋር ሰው እንዲገደል ያወጀ ስለሆነ ቅስናንም ሆነ ዲቁናን ሊባርክ አይችልም።" የሚል ምክንያትም ስጡኝ።

ጳጳሱ ማን ነበሩ?

ብርሃነ፦
ስማቸውን ዘንግቼዋለሁ፤ በዚያ ሰዓት ስማቸው መታወቂያየ ላይ ነበረ።

የትግራይ ተወላጅ ናቸው?

ብርሀነ፡-
እኔ እንጃ … አማርኛ ነበር የሚናገሩት።

በተያዝክበት ወቅት ማለትም በ1975 ዓ.ም. አካባቢውን የሚያስተዳድረው ደርግ አልነበረም እንዴ?

ብርሃነ፦ ከተማው ደርግ ነው፡ በገጠር ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩት ወያኔዎች ነበሩ።

ከገጠር ነበር የያዙህ?

ብርሃነ፦
አዎ! ከገጠር ነው የያዙኝ። እኔ ስለ እናንተ ዓላማ አላውቅም፡ ከዚህ በፊትም አላውቃችሁም። እኚህ ጳጳስ ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ መሪ መሆናቸውን ብቻ ነው የማውቀው እንጂ፤ ጦርነት ያውጁ አያውጁ እኔ የማውቀው ነገር የለኝም ስላቸው በቅጣት 10 ቀን አስረው መታወቂያየን ቀዳደዱት። በኋላም ደርግ ካለበት አካባቢ እንዳልደርስ አስጠንቅቀው በዋስ ለቀቁኝ። ሌሎችም
ቅስና እና ዲቁና የተቀበሉ ከ50 በላይ የሆኑ ሰዎች ታስረው ነበር። እነሱም ከእስራትና ከቅጣት በኋላ መታወቂያቸውን ተቀምተዋል።
የተቀሙት የዲቁና መታወቂያቸውን ነው?

ብርሃነ፦
የዲቁና እና የቅስና መታወቂያቸው ነበር የተቀሙት። ከዚያ እዚያው ቆይተን በ1981 ዓ.ም. በግድ ወደ ግንባር ዝመቱ አሉን።

በ1975 ዓ.ም. እንደተያዛችሁ እንድትዘምቱ አልጠየቅዋችሁም?

ብርሃነ፦
ይጠይቁን ነበር፤ ነገር ግን ግዴታ አልነበረብንም። በዘፈን ይቀሰቅሱን ነበር። በስብሰባ ያስቸግሩናል። ይቆጡናል እንጂ የጠነከረ ግዴታ አልነበረም። በ1981 ዓ.ም. ግን ውጥረቱ ሲበረታባቸው ነው መሰል ግዴታ ታገሉ አሉን።
እኛ "አንታገልም፤ እናንተ ታገሉ፡ እኛ ድሆች ነን፡ ገና ዳቦ አንኳን አልጠገብንም" ስንላቸው "ማን አጥንቱን ከስክሶ ሊያኖርህ ፈለግክ?" በማለት በተለይም "ቢሄን/ቢሆን" የተባለ ታጋይ አፈር በእጁ ከመሬት ቆንጥሮ በማፈስ ወዳፍንጫችን አስጠግቶ እንድናሸተው በማስገደድ አስፈራራን። በአገራችን መኖር ካልቻልን ተሰድደን እንሄዳለን፡ ይለፍ ብቻ ስጡን ስንል ስትፈልጉ በሰማይ ሂዱ እንጂ አይሰጣችሁም፤ እያሉ ያፌዙብን ነበር።
"ታዲያ የት እንድረስ?" ስንላቸው "የራሳችሁ ጉዳይ! ከፈለጋችሁ አገራችሁን ነፃ አውጡ። ነፃ አናወጣም የምትሉ ከሆነ ግን የትግራይ ምድር አትረግጡም። አሉን። "ከማን ነው ነፃ የምናወጣት?" ደርግም ኢትዮጵያዊ ነው፤ እናንተም ኢትዮጵያውያን ናችሁ።" ስንል <ከበስተጀርባችሁ የሆነ ነገር አላችሁ!> በማለት ማሰር እና መቅጣት ጀመሩን።
ስንት ትሆናላችሁ?

ብርሃነ;-
1500 እንሆናለን።

ከዚያ ምን ተከተለ?

ብርሃነ;-
ወላጆቻችን ታሰሩ። የእርሻ ማስታዎሻችንም ተወረሰ። ቀንደኛ አድመኞች ናችሁ በተባልን በተወሰንን ሰዎች ላይ ከባድ ቅጣት ተፈጸመብን። ከ6 ወር እስከ ዓመት በእስራትና በግርፋት ተቀጥተናል። ክንዶቹ ለረዥም ጊዜ በቀጭን ጅማት ነገር በመታሰራቸው ምክንያት ጣቶቹ ደም እስከ ማንጠብጠብ የደረሰ ጓደኛችንም ነበረ።

በጅማት ታስሮ እጁ ደም ያንጠባጠበውን ጓደኛህን ስም
ታስታውሰዋለህ?

ብርሃነ፦
የአንዱ ስም አላስታውሰውም። ሰሎዳ የሚባል ቀበሌ ነዋሪ ነው። ሌላው በግርፋት አንድ እጁ እና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ጓደኛየ ሃለቃ ሓዲሽ የባላል። ቢዚያን ወቅት <ሙሹሮችና ካህናት> ሳይቀሩ <በህማማት ጊዜ ከቤተክርስቲያን> ተወስደው ከሽማግሌዎች በቀር ሁሉም ታፈሶ ተወሰደ። ለመሸሽ የሞከረውን እንደጅግራ እያሯሯጡ በጥይት ያሳድዱት ነበር።

ይህ ሁሉ የተፈጸመው መቼ ነው?

ብርሃነ፦
የካቲት ወር 1981 ዓ.ም. ጀምሮ ማለት ነው።

ትግራይ ነፃ ከወጣች በኋላ ማለት ነው?

ብርሃነ፦
አዎ:: ከዚያ… ሰው እንደ አውሬ በአካባቢው እየተበተነ በአካባቢው በቀን ሰው የሚባል አይታይም ነበር። እነሱም እንደ ጅግራ እያደኑ ይውላሉ፣ መሬታችንም ለታጋይ ቤተስብ ታድሎ የምንቀምሰው የምንልሰው አልነበረም። ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚያስተላልፉ የነሱ ካድሬዎች ካዩን ጥይት ይተኩሱብናል፣ የተኰሱብን ጥይት አልመታንም እንጂ ቁጥር የለውም። ከዚያ በኋላ እየተንከራተትንና እየተራብን ቆይተን ህዳር 21/1983 ዓ.ም. ገረዳ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ የገበሬ ማኅበር ለአቶ በርሄ እህል ስንሸከምላቸው ውለን፣ ቤት ገብተን ገበታው ቀርቦ እህል ልንበላ ስንል ቤቱ ተከበበ። የማይታወቁ ታጣቂዎች ናቸው። ከተሰበሰበው ሰው እኔን ጠሩኝና ውጣ አሉኝ። መጀመሪያ እህል ይብላ እና ውሰዱት ብለው የቤቱ ባለቤት ቢጠይቁም "አስቸኳይ መልዕክት ስላለን ነው እንጂ አሁን ይመለሳል" ብለው ወሰዱኝ። ሌሎችም ከያቅጣቻው ተሰበሰቡ። ወደ 5 እንሆናለን። ሁላችንም በስብሰባ ላይ የምንከራከራቸው ነበርን።"እነዚህ ካልጠፉ ወጣቱ አይታገልም በታኞች ናቸው ከደርግ ለይተን አናያቸውም" በማለት ከዚያ በፊት እንዳጠፏቸው ወጣቶች እኛንም ለማጥፋት ተዘጋችተው እየወሰዱን ሳለ እርስ በርሳችን እንነጋገር ነበር። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ይሆናል።

የት ነበር የሚወስዷችሁ?

ብርሃነ፦
ጫካ ነው፤ እኛ አናውቀውም። ኢሳ የሚባል በረሃ ነው። ምን ይሻላል? ለመሞት ለመሞት እዚሁ እንሙት እየተባባልን እንደገና ጉዞ ጀመርን። አልፎ አልፎ ነው እንጂ እኛን ባንድ ላይ አይወስዱንም ነበር። አንድ እዚህ፤ አንድ ደግሞ ራቅ አድርገው ሊወስዱን ከፊት ያለውን ገፍቼ ሸሸሁ። ቁጥር የሌለው ጥይት እላየ ላይ ዘነበ። ፀጉሬ ላይ ትንሽ ነካኝ እንጂ አልመታኝም። አምልጬ ሕግ ያለ መስሎኝ ወደ ዋናው አለቃ ሄጀ <የማይታወቁ ታጣቂዎች ሌሊት መጥተው በደል አደረሱብኝበነዚህ ሰዎች ላይ ክትትል ይደረግልኝከየት እንደመጡ ማን እንደላካቸው ይጣራልኝ> ብየ አቤቱታ ሳቀርብ፡ "እኛ እናጣራዋለንእንከታተላቸዋለን" የሚል መልስ ሰጡኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ጥር 23 ቀን 1981 ዓ.ም. ሥራ አድሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወደቤቴ ስሄድ……..

ምንድነው ሥራህ?

ብርሃነ ፦
የቤት ሥራ፤ ቤት በደቦ ስንሰራ ደክሞኝ እዚያ አድሬ ነበር። አባቴ ሞቷል..እናቴ አለች፤ የእናቴ ትንሽ መሬት ነበረችን፡ ቤቴ እንደደረስኩ በረቱን ከፍቼ ለበሬዎቹ ድርቆሽ ልሰጣቸው ስል….የማላውቃቸው ሰወች ብትንትን ብለው ተኝተው አገኘኋቸው። ቤቱ ተከቦ ነው ያደረው። እናንተ እነማን ናችሁ? ስላቸው አንዱ እያናገረኝ ሌላኛው በሰባት ጥይት መታኝ። በሆዴ እና በአንጀቴ ላይ ደሙ እየተንዠቀዠቀ ሲፈስ እናቴ እንዳታይና እንዳትጮህ ውስጥ ግቢ አሏት። ከዚያ በላ <እግሬና እጄን አንጠልጥለው ጎትተው ጫካ ውስጥ ጣሉኝ>። አንጀቴ ተበጥሷል። እንጀቴ ይታያል፡ቅጠላቅጠል አልብሰውኝ ተሰወሩ። ይህ ሁሉ ሲሆን ከሩቅ ይከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ሰዎች እነማን እነደሆኑ አይተዋል።

ስንት ነበሩ?
ብርሃነ፦
ወደ 10 ይሆናሉ። ሕዝቡ ተከትሏቸው፤ "እነማን ናችሁ? ቁሙ! ነፍስ አጥፍታችሁ አትሄዱም" ሲላቸው "እየሳቁ" ሄዱ ። በመጨረሻ ከወደቅኩበት አንስተው በሰልፍ ተሸክመውኝ ዓድዋ አውራጃ አሰተዳደር ወሰዱኝ። "የዛሬ ብርሃነ ዕድል ነገ ለኛ ነው። ይሄ ልጅ ምን አጠፍቶ ነው በወጣትነቱ የተቀጠፈው?" ብሎ ሕዝቡ አቤቱታ አቀረበ። በዚህ ወቅት ሕዝቡ መቷል ብሎ ስላመነ ጉድጓዴ ሳይቀር ተቆፍሮ ነበር። ጫካ ወስደው እንደጣሉኝ የተነገረኝም በኋላ ነው። ሕዝቡ አሰከረኔን ተሸክሞ "ደርግን ግፈኛ ትላላችሁ እንጂ ይኼውና የናንተም ግፍ!" ሲሏቸው 15 ወጣቶች በሲሚንቶ የተሰራ የጣሊያን ጉድጓድ ውስጥ አስገብተው አሰሯቸው። በአጠቃላይ ሕዝቡ 500 (አምስት መቶ) ይሆን ነበር። ወጣቶቹን ካሰሩ በኋላ ሕዝቡን በዱላ በታተኑት። እኔንም የሚያውቁኝ ሰዎች ወደ አክሱም አመጡኝ በአጋጣሚ ነጮች ነበሩ ኦፕራሲዮን አደረጉልኝ።

የት ነው ኦፕራሲዮን ያደረጉልህ?
ብርሃነ፦
አክሱም ሆስፒታል። ሁለት ሰዎች ደም ሰጡኝ። ደም ጨርሼ ነበር። ይሄን ሲነግሩኝ እንጂ እኔ አላውቅም። ለ3 ወር ያህል ሕይወቴን አላውቅም ነበር። የተኛሁበት የጀርባየ ጠባሳ አሁንም አለ። ሕይወቴ መቆጣጠር ስላልቻልኩ መቀሌ ታከምኩ። እዚያም ስላልቻሉ አዲስ አበባ ጥቁር አምበሳ መጣሁ።

ጥቁር አምበሳ የመጣኸው መቸ ነው?

ብርሃነ፦
1984 ዓ.ም. ሚያዚያ 4 ቀን አዲስ አበባ መጣሁኝ። ጥቁር አምበሳ ሆስፒታልም እስከ መጨረሻ ጥረት አደረጉልኝ። ሕይወቴን ለማዳን በህክምና ብቻ ሳይሆን በተለያየ መልኩ ሲረዱኝ ቆይቶ መጨረሻ ሲያቅተው በ1986 ሰኔ 16 ውጪ ድረስ ሄጄ እንድታከም ወስኖ አሰናበተኝ። ከዚያ በኋላ አማራጭ አጣሁኝ። ቀኑ ጨለመብኝ።
ከጥቁር አምበሳ ስትወጣ ወዴት ሄድክ?
አዲስ አበባ
ቤተሰብ አለህ?
ብርሃነ፦
የለኝም።
ታዲያ የት አረፍክ?

ብርሃነ፦
እዚሁ ሆስፒታል ኮሪደር ላይ ነበር የምተኛው ።
ከተሰናበትክ በኋላ?

ብርሃነ፦
አዎ። ከዚያ ወደ ትግራይ ሄድኩ ። የማላውቃቸው ሰዎች አዋጥተው ቲኬት ቆረጡልኝ ። ትግራይ ከሄድኩ በኋላ ከብዙ ደጅ ጥናት በኋላ የክልሉ መንግሥት ጸሐፊት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነን አነጋገርኳት።
ምን ሆንክ? አለችኝ።
በጥይት ተመትቼ
ማን መታህ?
የህወሃት ታጋዮች
እንዴ! ምን ብለው ይመቱኋል? ክሰሳቸው። 
ምን ብየ እከሳቸዋለሁ? ታውቁት የለም እንዴ ራሳችሁ። እንደ ብርሃነ አንዳትሆኑ እያላችሁ መድረክ ላይ ስበሰባ ላይ ትናገሩ አልነበረም አንዴ? ከ500 ሕዝብ በላይ አቤቱታ ለማቅረብ ሲቀርብ በዱላ አላባበረራችሁትም?  ወንጀለኛ ከሆንኩኝ ግደሉኝ፤ ካልሆንኩ ግን አሳክሙኝ። አናውቅም የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ ስንብት ወረቀት ስጡኝና የትም ሀገር አቤት ልበል ስላት፡የለም ምንግሥት አይመታህም አለችኝ።
መንግሥቱ ይለማርያም አሰቃይቶ የገደለው ሰው የለም። የእርሱ ወታደሮች ግን ሰው ገድለዋል። የህወሐት ወታደሮችም እንደቅጠል ነው የቀጠፉን፤ የገረፉን። ዕድሜ ልካችንን ሲያሰቃዩን ነው የከረሙት። ስለዚህ ለውጥ የለውም። ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ነበረ አሁንም አለ። ያለው ፍርድ ቤት (መንግሥታዊ) ነው እንጂ ማኅበራዊ (ነፃ) ፍርድ ቤት አይደለም። የመሰላችሁ ፍትሕ ስጡኝ ስላት፡

ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠይቅ አለችኝ። 
ከ300 በላይ ግብረሰናይ ድርጅቶችን አነጋግሬ "መንግሥት ማንንም ሰው በግለሰብ ደረጃ እንዳትረዱ የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጥቶናል" ብለውኛል፡ አኔ ከ60 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ስለማልበልጥ ብጠይቃቸውም መልስ አጥቻለሁ። ስላት

ይህንን ነገር እንዴት ልታወቅ ቻልክ?

ይሄማ ግልጽ የሆነ እኮ ነው፡ ስላት

ይኼማ የፓለቲካ አዝማሚያ ነው ብላ ወዲ ሻምበል የሚባለውን የፖሊስ አዛዥ ጠራች ። አሱም መጣ። ሌሎችም ተከተሉ። ድምፅ እንኳ ወደማይሰማበት "አንደር-ግራውንድ" አስገቡኝ።
አንደርግራውንዱ አዚያው ምክር ቤት ውስጥ አካባቢ ነው ያለው?

ብርሃነ፦
አዎ። ከ8፡00-1130 ድረስ ጎሮሮየ ደርቆ መናገር አስኪያቅተኝ ድረሰ በጥያቄ አፋጠጡቡኝ።
የሚጠይቁህ ምን ነበረ?

ብርሃነ፦
የደረሰብህ ነገር ተንትነህ በሙሉ ንገረን ያየኸው ነገር ሁሉ ተናገርሙሉ መብት ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ የቤተክህነት ተማሪ ነበርኩ። ወላጆቼ ቤተክርስቲያንን እንድታገለግል ለቤተክርስቲያን ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክህነት ተማሪ ነበርኩ። ዲቁናየ ስቀበል ደግሞ ታጋይ ሐጎስ የሚባል የወረዳ አስተዳዳር "የዲቁና የምስክር ወረቀቴን ቀደደው"። ቀጥለው ታገል ተባልኩ። እኔ አልታገልም ሰርቼ ነው የምበላው ስላቸው፡ "የለም መታገል አለብህ" አሉኝ። መጨረሻ “ወጣቱን በታኝ ነህ! አሳዳሚ ነህ!” አሉኝ። የበተንኩት ሰው የለም። ብርሃነ እንዳትታገል ብሎኛል የሚል ሰው ካለ አምጡት አልኳቸው።

መጨረሻም ወጣቱን ማፈን ጀመሩ። እንደ አራዊት ማባረርና ማፈን ሲጀምሩን እኛም የምንገባበት ቦታ አጣን። ተረበሽን፤ የት እንሂድ? ገሚሶቹ ወጣቶች ወላጆቼ በእኔ ሰበብ ከሚሰቃዩ አኔ ልሙት እያለ ወደ ትግል ግምበር ሄዶ ሞቷል። እላዩ ላይ ሳር በቅሎበታል። የተቀረንም ሰውነታችን በጥይት ተበሳስቷል። እሳት ጨብጦ ፈንጅ ረግጦ ለሥልጣን ያደረሳችሁ ወጣት በየፌርማታው ወድቋል፡ ግማሶቻችንም ጠፍተናል።
ለምሳሌ ያህል
ይግዛው ጣሰው - ከማይጓጓ
ፍቱሕ ገ/ሕይወት - ከማይዳዕሮ
አለቃ ሐጎስ- ከማይደዕሮ
ገ/እግዚአብሔር-ከደዕሮ ሸዊቶ
ዓለምሰገድ ይግዛው-ከዳዕሮሸዊቶ
አረፋይኔ -ከገረዓ
አበበ ገብረአብ - ከገረዓ
ሲጠቀሱ ከነዚሁ አንዱ አኔ ነኝ።

እነዚህ የተገደሉ ናቸው?

ብርሃነ፦
ታፈነው ተወስደው የጠፉ፤ አድራሻቸው የጠፋ ናቸው። ስላቸው
አሁንም የት አንዳሉ አይታወቅም? አሉኝ የሉም! በቃ!....ለአብነት ያህል ከነዚህ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። ጊዜ ከሰጣችሁኝ በመቶ ሚቆጠሩ ሰዎች አውቃለሁ አልኳቸው። በመጨረሻ መሬት ተወስዶብኛል ብለሃል ማን ነው የወሰደው? አሉኝ። አኔ እዚህ ሆኜ መሬቴ ተወስዷልመሬት የለኝም። የሚል መልስ ሰጠኋቸው።
በምን ትደዳራለህ አሉኝ፤ ለምኜ ዕድሜ ለሕዝቤ፤  የሚል መልስ ሰጠኋቸው።

በል አሁን የምትፈልገው ምንድነው? ደረሰብኝ የምትለው በደልስ ምንድነው? አሉኝ "እኛ የትግራይ ተወላጆች በሦስት ፓርቲ ብዙ ችግር ደርሶብናል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የትግራይ ሕዝብ በደርግ በሻዕቢያ በሕወሓት ተበድሏል። እንደዚህ ሆኖ እያለ የደርግ ባለሥልጣኖች ለፈጸሙት ግፍ በፍረድ ቤት ሲጠየቁ እኛስ ለምን መፍትሔ ለምን አይሰጡንም? ለምሳሌ ለደርግ ባለሥልጣናት በጀት መድባችሁ ጠበቃ አቁማችሁ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ አድርጋችኋል። በህወሐት እና በሻዕቢያ በኩል በደል የደረሰብን ሰዎችስ ምን እንሁን?እኛም እኮ ሰዎች ነን። ቅጠል አይደለንም። መፍትሔ ለምን አይሰጠንም? "ብየ መልስ ሰጠኋቸው። አንዲያውም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት "በትግላችን ወቅት ያጋጠሙን አንዳንድ ችግሮች በአሁኑ ሰዓት ሊያስጠይቁን አይችሉም።" የሚል መልስ በመድረክ ላይ ተናገረ።

በስብሰባ ላይ ነው?

ብርሃነ፦
በስብሰባ ላይ የተናገረውና በቴሌቪዥን የቀረበ ነው ፤ መልስ የሰጠው። እኔ የተናገርኩት እና ሌሎችም ቤተሰቦቻችን አምጡልን፡ሞተውም እንደሆነ ንገሩን ብለው አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።

ከእነ ወዲ ሻምበል ጋር በእንዴት ተለያያችሁ?

ብርሃነ፦
መጨረሻ ላይ አሁን የት ነው ምትኖረው አሉኝ?
እኔም አቅጣጫ ቀይሬ አዚህ ቦታ ነው የምኖረው አልኳቸው። ተከትለው ሊይዙኝ ነው የፈለጉት።
እዚያው ትግራይ ውስጥ ነው ያልከው?

ብርሃነ፦
አዎ። መቀሌ ውስጥ የሐሰት አድራሻ ነግሬያቸው ከከተማ ወጥቼ ቲኬት አስቆርጨ አ/አበባ መጣሁ። አ/አበባ እንደመጣሁ ድርጅቶች ውጭ ልከው አንዲያሳክሙኝ ጠየቅኩ። ……. በማለት አሰዛኙ ታሪክ በሰፊው ገልጿል( ሙሉውን ለማንበብ የመጽሔቱ እትም ያንብቡ ወይነምየወያኔ ገበና ማሕደርውስጥየትግራይ ድያቆናት እና የቀሳወስት ዕንባበሚል ርዐሰስ በተካተተው  መጽሐፌን ያንብቡ፤ ከሌለዎት አንድ ሦስት የቀሩ እትሞች ይኖሩኝ ይሆናል ገዝተው ማንበብ ይችላሉ)

አንግዲህ ከላይ ባጭሩ ከቃለ መጠይቁ ያቀረብኩበት ጉዳይ ስለ ጉዳዩ ቁንጽል ሃሳብ አንዳይኖራችሁ በማሌት ነው ዋና ዋና ፍሬ ነገሩን ላስጨብጣችሁ የፈለግኩት። አሁን በቃለ መጠይቁ መሰረት የተመለከተው  ወደ አቶ ግበሩ አስራት ጉዳይ እንመልከት።
ይችን የዲያቆን የብርሀነ /ሕይወት ክስ እና ንገግር እንደገና እናምጣት

 “ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የትግራይ ሕዝብ በደርግ በሻዕቢያ በሕወሓት ተበድሏል። እንደዚህ ሆኖ እያለ የደርግ ባለሥልጣኖች ለፈጸሙት ግፍ በፍረድ ቤት ሲጠየቁ እኛስ ለምን መፍትሔ ለምን አይሰጡንም? ለምሳሌ ለደርግ ባለሥልጣናት በጀት መድባችሁ ጠበቃ አቁማችሁ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ አድርጋችኋል። በህወሐት እና በሻዕቢያ በኩል በደል የደረሰብን ሰዎችስ ምን እንሁን?እኛም እኮ ሰዎች ነን። ቅጠል አይደለንም። መፍትሔ ለምን አይሰጠንም? "ብየ መልስ ሰጠኋቸው። አንዲያውም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት "በትግላችን ወቅት ያጋጠሙን አንዳንድ ችግሮች በአሁኑ ሰዓት ሊያስጠይቁን አይችሉም።" የሚል መልስ በመድረክ ላይ ተናገረ።

በስብሰባ ላይ ነው?

ብርሃነ፦
 በስብሰባ ላይ የተናገረውና በቴሌቪዥን የቀረበ ነው ፤ መልስ የሰጠው። እኔ የተናገርኩት እና ሌሎችም ቤተሰቦቻችን አምጡልን፡ሞተውም እንደሆነ ንገሩን ብለው አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።”
ይላል።

አቶ ገብሩ ይህነን ጉዳይ በምን መልክ ይመልሰዋል? ልዩ ፍርድ ቤት መስርተው፤ባጀት ጠይቆ (መድቦ) ለሥራ አስፈጻሚው አካል አነጋግሮ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ያልደፈረበት ምክንያት እና “"በትግላችን ወቅት ያጋጠሙን አንዳንድ ችግሮች በአሁኑ ሰዓት ሊያስጠይቁን አይችሉም።" ሲል የአቶ ገብሩ ሞራላዊ ፤ሰብአዊም ሆነ ስለ እራስ መተማመን ምንን ያመላክታል? አቶ ገብሩ እንዲህ ሲል ራሱን መከላከሉ ነው ወይስ ሌሎቹን ጓዶቹ በሕግ ፊት ላለመቀጣት ፍራቸ/ስጋት ስላደረበት? አቅርቦስ ከሆነ እንዲህ ያሉ በጣም ወሳኝ የሆኑ የሞራል፤የሕግ እና የሰብአዊ ጉዳይ ነክ ክሶች መቅረባቸው እና ጓዶቹን አነጋግሮ ከነበረ የተወሰነውስ ውሳኔ ለምን በመጽሐፉ አላካተተውም?

አሁን የአረና አመራር አባል የሆነች / አረጋሽ አዳነ በገብሩ አስተዳደር ስር ሆና የፈጸመቺው ኢሰብአዊ የምርምራ ትዕዛዝ አርግጥ በገብሩ ትዕዛዝ እንዳልተደፈጸመ ብንረዳም፤ በአስተዳዳር ጉዳይ ማንኛውንም ከሕግ ውጭ ሲፈጸምአስታደሩሃላፊነት ይወስዳል የሚል ሕግ ባንዳንድ አገሮች ያለ ነው (በወያኔ ሕገ ደምብ ይኑር አይኑር ባላውቅም፤ ቢኖርም ተግባራዊ  አንደማይሆን ብዙ ማስረዳት ይቻላል፡ ግበሩም ነግሮናል።) ሆኖም አረጋሽ ይህንን እንደፈጸመቺው አላወቅኩም የሚል ከሆነም፤ በመላ አገሪቱ የተዘረጋ መጽሔት ስለ ገብሩ እና ስለ አረጋሽ የቀረበ በጣም ዘግናኝ ክስ አላነበብኩም ፤አላወቅኩም ማለት አይችልም። በወቅቱ ገብሩ ሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን ያሳስቡን ነበር የሚል ከሆነምክትሉአንዲህ ያለ ክስ ሲደርባት (የሱንም ክስ ከላይ አንደተጠበቀ ሆኖ) ጠርቶ ወይንም በውይይት ስለ ጉዳዩ ምንነት አንድታብራራለት አነጋግሯት ነበር? ለዚህ መልሱ ምን ይሆን?

ይህ የሰብአዊ ነክ ጉዳይ በሰባት ጥይት ደብድበው የድቁና ወረቀቱ ነጥቀው ትግሬነቱን ነጥቀው ከትግሬ ምድር አንዲወጣ የመሳሰሉት ግፎችና ንግግሮች የተፈጸመበት ያ ወጣት ባሁን ሰዓት በሕይወት ይኑር ይሙት አላውቅም። ሆኖም ስለ እሱ የመናገር መብት አለን እና “ላደረግኩት ስሕተት ሃላፊነት እወስዳለሁ” በማለት አቶ ግበሩ ከገለጸልን ዘንዳ “ሃላፊነት” መውሰድ ማለት በመንግስት ሕግ ቆሞ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ ገብረመድህን አርአያ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ካይሮፕላን ሲወርድ ወደ መሬት ተደፍቶ መሬቷን እየተሳለመ ሕዝብ እያየው “ኢትዮጵያ አገሬ ይቅር በይኝ!” ብሎ በሗላ በዝርዝር የራሱ ሃለፊነትም ሆነ የድርጅቱ ወንጀል በግልጽ አስቀምጦ በሰላም እና በክብር እየኖረ አንዳለበት ሁሉ አቶ ግበሩ አስራትም አንዲህ እና እነዚህ የመሳሰሉትን በግልጽ ቢያስቀምጥልን ለሌሎቹ መሰል ጓዶቹ ጠቃሚ አስተምህሮ ሊሆን ይችላል እላለሁ።ይህ ስል ግን የመለስ ቡድን ደጋፊዎች አንዲደሰቱበት በር ለመክፈት ሳይሆን እነሱም ከባድ ሃላፊነት አንዳላቸው እና ገብሩ አነዚያ ቡድኖች እና ተከታዮች ሃላፊነት መውሰድ (እርግጥ የተቻለውን ሃላፊነት ተሸክሞ አስመስጋኝ መጽሐፍ ጽፏል) ምን ማለት አንደሆነ እና ከባድ ሸክም መሆኑን ለማስመር ነው። አንድ ነገር ለማት የምፈልገው “ሃላፊነት ወስዶ” በግልጽ “እራሱን የሚጋፈጥ” ሰው በጣም የተወሰኑ ናቸው። ማንም ቢሆን እራሱን ወደ መቃብር ወይንም እራሱን የሚወነጅለ ሰው አንደሌላ የሰው ልጆች ባሕ መሆኑ ቢገባኝም፤ ለሚመጣው እርቅ እና ሰላም መንገድ የሚጠርገው ሰዎች በተለይ ሃለፊዎች የተደረጉ ምስጢሮች ለሕዝቡ በመንገር እና ይቅርታ መጠየቅ ዓይነተኛ የመተማመኛ መንገድ በመሆኑ ነው “እራሳቸውን ላለማጋለጥ ቢቸግራቸውም፤  ጥራሳቸውን ነክሰው የቻሉትን በር መክፈት አስተማሪነት አለው ለማት ነው።

ለምሳሌ ግንቦት 7 አመራሮች  ወደ ኤርትራ ለስልጠና የላኩዋቸው ወጣቶች በአመራሩ አምባገነንነት ብዙ ስቃይ አንደደረሰባቸው እያለቀሱ ለሕዝብ የታነገሩትን አቤቱታ ሰምተናል። ጉዳዩ አጣርቶ ለሕዝብ እና ከታጋዮቹም ፊት ለፊት ሚዲያው ላይ ቀርበው ከመነጋገር ይልቅ እነሱን ተመልሰው  “ወያኔዎች ናቸው” እያሉ መልስ ላለመስጠት እና ድፈን ድፈን ማለቱ “ለጊዜው ይደበቅ” ይሆናል አንጂ ለወደፊቱ “ጥያቄው አንደገና ብቅ ብሎ ውጥረቱ እየተጋጋለ ሃላፊነት መውሰድ የሚገባቸው ሰዎች ተመልሰው ይህንን ጥያቄ አንዲመልሱ በህግም ሆነ በሚዲያ ይወጠራሉ” ከሓላፊነት መሸሽ የባሰውኑ ጉዳዩ እየተከተለ ኰቴህ ላይ ፤ በምታረመድበት አደባባይም ሆነ መንደር ወይንም ሚዲያ ሁሌም የሚወጥር ጉዳይ መሆኑን “የፖለቲካ መሪዎች” መረዳት ይኖርባቸዋል። በመጨረሻ በም{ሀፉ ተጠቀሰ የኢሳያስ አፈወርቂ አምነት መደምደሚያ ልስጥ እና ቅለቧት “እኛ ማንቆጣጠረው ድርጅት ማስታጠቅ አንፈልግም” ኢሳያስ አፈወርቂ!!!!!!

ክፍል 3 ትችት ሰፊ እና ምናልባትም በገብሩ የ1977ቱ ድርቅ ትንተና እና በሓውዜን ጉዳይ እሱ ከሰጠው በተጻራሪ ትችት ይቀርባል። በገብሩ ትንታኔ ስለ አማራ የሚመለከት ትንሽ ጠንክር ያለ ትችት ይቀርባል። በክፍል ……እየለ ይቀርባል ተከታተሉ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) getachre@aol.com    (Ethiopian Semay)