Saturday, May 24, 2014

The EPLF General Sebhat


የሻዕቢያዉ ጀነራል ስብሓት ኤፍሬም “ከሃይለሥላሴ እና ከደርግ ሠራዊት ሲንጻጸር የወያኔዉ ጦር እጅግ ደካማ ነዉ” አለዉ። ከጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ- ካሊፎረንያ ሐምሌ 2000 ዓ/ም “ወዲ ኤፍሬም” በመባል የሚታወቀዉ በጀኔራልነት እና በመከላከያ ሚኒስትርነት ማዕረግ የሚጠራዉ የሻዕቢያዉ ባለስልጣን “ታዓጠቕ” (ታጠቅ) ተብሎ በተሰየመዉ አሥመራ ዉስጥ የታተመዉ አዲስ የሻዕቢያ የትግርኛ መጽሄት፤ ሰሞኑን(በፈረንጅ በሐምሌ/ጁላይ ወር 2008 ቁጥር 14) (በኛዉ አቆጣጠር ሐምሌ/2000 )ባወጣዉ ልዩ እትሙ ላይ ለቃለ መጠይቅ ቀርቦ የሰጠዉ 64 ገጽ ሙሉዉን ባላቀርበዉም አለፍ አለፍ ብየ ጠቃሚ ጉዳዮችን ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላንባቢያን አቀርባለሁ። << ….የኤርትራ ትልቁ ስጋታችን ነዉ ብልን የምንሰጋዉ ‘ኢትዮጵያ ለወደፊቱ የኢርትራ ትለቁ ሸክም አንዳትሆንብን ነዉ የምንሰጋዉ። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በቀጣይ የዉስጥ ሽኩቻና ቀዉስ ከመወጠርዋ በላይ፤ አገሪቷ ድሃ በመሆኗ ያለ የዉጭ ዕርዳታ መኖር ይቸግራታል ፤አትችልም።ተያይዞም ጦርነት እንደ ዓላማ ስለያዙት በድህነትና በረሃብ በቀጣይ ይሰቃያሉ። በረሃብና በድህነት የሚሰቃይ ጎረቤት ደግሞ መጨረሻዉ ሸክሙ ለጎረቤት ነዉ። ይህ ሁኔታ አሁን ባሉበት የዉስጥ የፖለቲካ ፍትግያና ድህነት አንዲሁም መራቡን ከቀጠሉበት፤ ሸክማቸዉ ሊከብደን ነዉ።…….>> በማለት ኤርትራ ዳቦ ቅርጫት የወ ያኔ ኢትዮጵአ ደግሞ ኤርትራ ተመጸዋች እነደምትሆን ስጋቱን የገለጸበት ረዥሙ ቃለ-መጠይቅ አንብቡ አነሆ። ወያኔን እንዴት ትመለከተዋለህ ለሚለዉ ኣጠቃላይ ጥያቄ ስብሓት ኤፍሬም ሲመልስ <<አንደሚታወቀዉ አሁን እያየነዉ ያለዉን አዲሱ የዓለማችን ስርዓት ሲታይ ወያኔ በዚህ መነጽር ዉስጥ እስገብተህ የአሜሪካኖች አገልጋይ መሆኑን ነዉ ምትደመድመዉ ።…….>> ወታደራዊ ሚዛኑ-ወያኔ’ና የደርግ እንዲሁም ከሱ በፊት የነበረዉ ጦር ስታነጻጽራቸዉ ወያኔ በየትኛዉ መመዘኛ ታስቀምጠዋለህ? ለሚለዉ ጥያቄ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥቶበታል። << የወያነ ጦር ከዚህም ከዛም የተጠረቃቀመ ጦር ከመሆኑ ባሻገር፤ ተዋጊዉና አዋጊዎቹ ካለፉት ማለትም የደርግና ከሱ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ሰራዊቶች ሲታዩ ወያኔ ደካማ ነዉ።…>> ኢትዮጵያና ኤርትራ ስታወዳድራቸዉ አሁን ሁለቱም አገሮች በምን ላይ ታስቀምጣቸዋለህ ? ለተባለዉም አንዲሁ አስገራሚ በሆነ መልስ መልሶታል። << ኤርትራና ኢትዮጵያ ስታነጻጽራቸዉ፤ - ኤርትራ ከጥዋቱ 5፡00 ሰዓት በንጋት ላይ ስትገኝ፤-ኢትዮጵያ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ሆና የጭለማዉ ጉዞ መጛዙን የጀመረችዉ አሁን ነዉ።ንጋት ላይ ለመድረስ ረዥሙ የጨለማዉ ጉዞ መጛዝ ሊኖርባት ነዉ። >> ፈረንጆቹ ከንጋቱ 5 ሰዓት ሲሉ ጠዋት11 ሰዓት ማለት ነዉ። በአንድ ወቅት ድሮ ከረን/ናቅፋን ለማስለቀቅ 6 ወር የፈጀ እልክ አስጨራሽ ዉግያዎች ተካሂደዉ አንተ በተካፈልክበት በ3ኛዉ ባታልዮን (607 እና 301- ባታልዮን) ስንመለከት፤ አንዴት አንድ ስፍራ ለማስለቀቅ ያን ያህል ረዥም ዉግያ ለካሄድ ቻለ? << ሁለት ነገር እናያለን። እዛ የነበረዉ የጠላት ጦር በጣም በጣም ሃይለኛ ነበር። እኛ የደረስነዉ ከተዳከመ በጣም ከደከመ በሗላ ነዉ። እዛ የገጠመን የጠላት ጦር ብርቱ ነበር ለማለት ምትደፍርበት ምክንያት ብዙ ነዉ። አንደኛ ለ6 ወር ሙሉ ያለ ምንም ረዳት ተከበህ ሌሊት ሌሊት ጦርነት ገጥመህ ቦታህን ሳትለቅ መጋተሩ በጣም አስገራሚ የሆነ አዋጊና ተዋጊ ጦር መኖሩን ታያለህ።በጣም ካባድ ነዉ።ቀላል አይደለም። የጠላት ጦር ያሳየዉ ቁመናም ይሄንን ነበር። የ607 እና 301 ባታልዮን ሰራዊት በጠላት ላይ ያደረገዉ ከበባ እና ቦታን የማስለቀቅ ዉግያ፤ በጣም ፈታኝ ነበር። ለ6 ወር ያክል ዙርያዉ በከበባ ገብቶ ሲዋጋ እሱን ለመርዳት በሄልኮፕተር የመጡት አየር- ወለዶች በፓራሹት ሲወርዱ ህዋ ላይ እንዳሉ ብዙዎቹ ተጎድተዋል።ሁለታችንም ረዥም ዉግያ አካሂደናል። እዛ የነበረዉ የጠላት ጦር ኮማንዶ፤ ምርጥ ከሚባሉት አንዱ ነበር። እንደነዚያ አይነቶቹ ምርጥ የጠላት ተዋጊዎች ከኛ ባታልዮን ጋር በተለያዩ የዉግያ አዉድማዎች ላይ፤ሁለት ሦስቴ ያክል ገጥሞናል። በተለይም “ሃብረንጋቓ’ የነበሩ የጠላት የክብር ዘበኛ ተዋጊ ሃይሎች አስደናቂ የመዋጋት ብቃት ነበራቸዉ። እንደነዚህ ዓኢነቶቹ ብርቱ የጠላት ሃይል ለማዳከም በተለይም ዙርያዉ ፈንጅ በታጠረ ምሽግ በኛ በኩል መከፈል የነበረበት እዳም ያን ያህል መሆኑ አትዘንጋ። በጣም ፈታኝ ነበር።……… ……..እንደሚታወቀዉ የናቅፋ ተራሮች እርስ በርስ በትይዩ የቆሙ ናቸዉ። ያንን በፈንጅ የታጠረዉ ወረዳ ጥሶ ለመግባት በጣም ክፉ ነዉ። እዛ የነበረዉ ጠላት አዋጊ “ማሞ” ይሉታል፡- “ማሞ” ብርቱ የጦር አዋጊ ነበር። የቦታ አያያዝና የጦሩ አስገራሚ አሰላለፍ ሞያተኛ ነበር።>> <….ለረዥም ጊዜ ተከቦ ተዋግቷል። በሄሊኮፕተር አየር ወለዶች ሊረዱት ሞከሩ፤ግን ለረዥም ጊዜ ተከቦ ስለተዋጋ መጨረሻተዳከመ። እኛም የማጥቃት ስልታችን ከሌሊት ወደ ቀን አዙረን በቀን ይዋጉናል የሚል ጥርጣሬ ስላልነበራቸዉና አድርገነዉም ስላማናዉቅ፤ ጦሩ ጥበቃዉን አላልቶ ፤ተዝናንቶ በነበረበት ሰዓት ገብተን ዉግያ ከፍተን መጨረሻ ሊደመሰስ በቃ…..።>> <<ስለዚህ ወያኔ በዚህ እኩል ልታየዉ አትችልም። መሰተረታዊ ባህሪዉ የአዲስ ዓለም ስርዓት አገልጋይ ነዉና። ወ ያነ ማለት “በግ” ማለት ነዉ። በግ ትንሽ ሳር ከጣልክለት፤ሳሯን ተደፍቶ ሲጎራርድ፤ ከሗላዉ ምን እየተዘረፈ እና እየተደረገ እንዳለም አያዉቅም። ለወያነ ግን ትንሽ-ሲጥሉለት ይጠቅመዋል። ወያነ የሕዝቡን ንብረት ሲነጥቅ፤ እየጣሉለት ያሉት ጌቶቹ ደግሞ አገሪቷን ያራቁታሉ። ለሱ ብሔራዊ ጥቅም/ልማት ..የሚለዉ የዘረፋዉ መንገድ ነዉ። የስነ-አእምሮ ዉግያ እያካሄድኩ ነዉ ሚለዉም ቢሆን የአዲሱ ዓለም ስርዓት አገልጋይነቱ ለመግለጽ ነዉ። አጼ ሃይለስላሴ የመገነኛ ብዙሃን ፤ራዲዮ አላስፈለጋቸዉም ነበር፤ ምክንያቱም ስራዉ የሚከናወነዉ በቤተ-ክህነቱ በኩል ነበርና። አንደዚያ ዓይነት የቅስቃሳ ክንዋኔ ለወያኔ የሚያካሂዱለት ደግሞ አሜሪካኖች ናቸዉ። ምክንያቱም፤የአዲሱ ዓለም ስርዓት የማገልገል ስራ በአንጻሩ ለወያኔ ስለተሰጠዉ። ስራዉ ያን ተልእኮ ማገልገል ነዉ። ይህ አዲስ ስርዓት እየተባለ ያለዉ የዓለም ህዝብ ተቃዉሞታል። ያሜሪካን ሕዝብ ሳይቀር ተቃዉሞታል። ወያኔ ብቻ ነዉ ባገልጋይነት የቆመዉ።የስነ-ኣእምሮ ትግል የማካሄዱ ስራ በደረግ ጊዜም የነበረ ነዉ። ወያኔ አሁን እየደገመዉ ያለዉ ያንኑ ነዉ። “ዉግያ” እያለ የሚጠራዉ ያነን ነዉ። <<…..በወታደራዊ መልኩ ግን የደረግ ሰራዊትና የወያነ ይለያያል። የደረግ ሰራዊት በወታደራዊ ስነምግባረና በሙያዉ የተለየ ነዉ።ሌላ ስራዉን ትተህ፤በጣም እልከኛ ተዋጊ ሰራዊት ነበር። የደረግ የጦር አለቆች በሰራዊቶቻቸዉ አድናቆትንና ተወዳጅነት ያተረፉ ነበሩ።አዋጊዎቹን ስትመለከት፤በጣም ጎበዞች ፤ሃይለኞች ነበሩ።እነ ረጋሳ ጅማ እነ ታሪኩ ላይኔ….ወዘተ.ወዘተ..የሚባሉ አዋጊዎቻቸዉን ስትመለከት ከፍተኛና ልዩ ችሎታ ያላቸዉ አዋጊዎች ነበሩ። በጣም ልዩ ነበሩ። እልከኞች ነበሩ።የኛ ሰራዊት ከእነደዚያ ዓይነቱ ምርጥ አዋጊና ተዋጊ ጦር መግጠማችን ያኮራናል። የጠላት አዋጊዎችም በኛ ሰራዊት አድናቆትን አትርፎላቸዋል። በእንደዚህ ዓይነት ሃየለኛ ሰራዊት እና አዋጊዎች ባየነበት ዓይናችን የወያኔን ጦር ስንመለከት አንደነዚያ ዓይነት አዋጊዎችና ባለሞያተኞች የሉትም። ለሽታ ፈልገህ አታገኝባቸዉም……….። << ….ወያኔን ከአዲሱ የዓለማችን ስርዓት ጋር አያይዘህ ነዉ ማየት ያለብህ። አዲሱ የ ዓለማችን ስርዓት ዓለምን በ ኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አንቆ ሊይዝህ የሚፈልግ ነዉ።ከዚም ከዚህም እየዘረፈ ወደ ሌላ መጓዝ። ያለንበት ዓለም በዚህ እየተመራ ስላለ በዓለም ዉስጥ ያሉት የብዙሃን የመገናኛ ጋዜጦች ሁሉ ተቆጣጥሮ ሁሉም ጋዜጦች በአንድ ርዕስ አንዲዘጋጁ ያደረግጋል።ከሚተነተነዉ ርዕስም አብሮ ትንሽ ወታደራዊ ነክ ጉራ ይጨመርበታል። ከሚተነተነዉ የስነ ዓእምሮ ትነተና ዉስጥ የወያኔ ሃይል ትነሽ ነጥብ ነች።የወያኔ ጦርነት የስነ-ዓእምሮ ጦርነት ነዉ። ሌላዉ ነገር ዉስጡ ባዶ ነዉ። ያ የስነ ዓእመሮ ጦርነት ነጥለህ ብትለየዉ የወያኔ አቅም ኢሚንት ነዉ። ምን ዉግያ አለዉ?የለዉም! ወታደራዊ ስልቱ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የሰዉ ሃይል ሰብሰቦ መዋጋት ብቻ ነዉ። ትንሽ ቦታ ለማግኘት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሰው ሕይወት ያስፈጃል። ኤርትራ 19,000 ሺህ ሰዉ ሲሰዋባት ዉያኔ 170,000 ሺህ ሰዉ ነዉ ያስፈጀዉ። የከፈለዉ ሕይወት በጣም ብዙ ነዉ። ታሞ በህመም የሞተ ሳይጨምር ማለት ነዉ። የደርግ ሰራዊት እኮ ልክ አንደፊተኛዉ ሰራዊት በስለቱም በጥንካሬዉም እያደገ የመጣ ሰራዊት ነበር። የወያኔ ሰራዊት ጥርቃሞ ነዉ። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሞ ያቆመዉ ነዉ። ከወያኔ በፊት የነበረዉ ጦር በፍጹም ታወዳዳሪ አይገኝላቸዉም። ወያኔ አቅሙን መጥኖ ስለመያዉቅ፡ አቅምም ስለሌለዉ፤ የኢኮኖሚ ረዳት የሌላትን ኤርትራን በኢኮኖኖሚ እናንቃታልን እያለ ነዉ የስነ እምሮ ዉግያዉን እየነዛ ያለዉ። <<……..የዓእምሮዉ ጦርነቱን አብረዉ የሚያጫፈሩት አንዳንድ ኤርትራዊያን አቅጥረኞቹን ድሮ የተረሱ ፤የበሰበሱ ፤የሞቱ በድን ድርጅቶችን አፈላልጎ እያስባሰባቸዉ ነዉ። አነዘሂም በነገርኩህ በዛዉ በስነ ዓእምሮዊ ዉግያዉ ዉስጥ እንደ ፓኬጅ ጨምራቸዉና ገምግመዉ። ግልጽ ነዉ! ዉግያዉ ከዚያ አያልፍም። ወያኔ ሊያደረጋት የሚችላት አቅሙ ያች ብቻ ነች። በዚህ መለኪያ ስትመዝነዉ የወያኔ አቅም ለመገመት የሚያሳስት ነገር አይደለም።>> የወያኔ ሰራዊት ገፍቶ ወደ ዉስጥ ኤርትራ በመዝለቁ እንደ ዋታደራዊ የበላይነት ተደርጎ ይታያል።የሄንን እንዴት ትመለከተዋለህ? << ወያኔ በወታደራዊ ሃይል የበላይነት ለማግኘት ሦስት ጊዜ=ሞከረ።መጀመሪያ፤ሁለተኛ፤…..ሦስተኛ ጊዜ የባሰ መጣበት። ከዚያ ወዲያ መቀጠል ስላልቻለ አቅም ስላልነበረዉ ወደ አልጀሪስ ለመሄድ ተገደደ። እዛም በሽንፈት ተከናንቦ የውርደት ዉርደቱን አገኘ።በሽንፈት ላይ ሽንፈት ኪሳራ ደረሰበት። ያካሄደዉ ዉግያ የስነ ዓእምሮ ዉግያ ነበር፡ በሺዎቹ የሰዉ ሕይወት ታስፈጅና በምትኩ፤ ትንሽ ቦታ ይዘህ ከየአቅጣጫዉ ጋዜጠኞችን ሰብስበህ “ኑ እዩልኝ፤ዘግቡልኝ” ይላል። የኛ ጦር በ ኤርትራ ምድር በየአቅጣጫዉ በስፋት ስለዘረጋነዉ፤ ወያኔ በሺዎቹ የሰዉ ሃይል ሰባስቦ በአንድ አቅጣጫ መጣ። ያ ዕድል ነበር ለወያነ የሰጠነዉ። እኛ በአቅማችን እንተማመናለን።ይሄ የሚያስጨንቀን አይደለም።የዉግያ ሙያ የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ቀስ እያልን እንደምንጠርገዉ ያዉቅ ነበር። ለዚያም ነበር ያቆመዉ። አስኪ እንደዉ በእወነቱ ወያነ ከጸሮና ዉግያ ወዲያ ዉግያ መቀጠልና ማሰብ ነበረበት? ያ የታየዉ የሬሳ ክምር፤የዉትድርና ብቃት ምለክት አይደለም። በዓለም ጋዜጦች የተዘረጋዉ በቲቪ የታየዉ የሬሳ ክምር እኮ ሙሉዉን አልታየም። በዓይን ስታየዉ እኮ የክምሩ ብዛት በእዉነቱ “በፍሊት” መርዝ የተፈጁ ነበር የሚመስሉት። በፍሊት የተገደሉም እንደዚያ ዓይነት የሰዉ ሬሳ “ክምር፤ በክምር ላይ ተደራርቦ” ማየት ያስቸግራል። 170.000 ሰራዊት አስፈጅቶ አንዴት ድል በድል ሆንን ይላል? አቅም ኖሮት ወያኔ ቢችል ኖሮ ነበር 10 ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደ ዉሸትና መለማመጥ የመረጠዉ? ያ ሊያደርገዉ የሚችለዉ አቅሙ ያኔ አብቅቷል። ጊዜዉ አልቋል። አሁን የቀረዉ ፕሮፖጋንዳ የስነ ዓእምሮ ፤ጉራና መዋሸት ብቻ ነዉ። ወያነ ደካማ መሆኑን የምታዉቀዉ ባደረጋቸዉ ሥስት ሙከራዎች ላይ ነዉ። የወያኔ የድሮ ተዋጊዎች አብዛኛዎቹ በዉግያዉ ተፈጅተዋል። ትግራይ ዉስጥ የመወያያ ርዕስ ሆኖ የሚነገረዉም ይህነኑ ነዉ። ድል አመጣሁ እያለ ወያነ የሚለፍፈዉ፤-ድሉ ከየት መጣ ቢባል- የስነ ዓእምሮ የፖለቲካ ወግያና የዲፕሎማሲ ዉግያዉ ነዉ። ያነን የስነ እምሮዉ ዉግያዉ ብትለየዉ ወታደራዊ አቅሙ 20% አይበልጥም። …ወያነ ኤርትራን ቢቆጣጠር ነብሰጡሮች ቁጥቋጦ ስር ነበር የሚወለዱት። ተመልከት ለአማራ ህዝብ እያደረጉት ያሉትን ግፍ። መልከመልካም ሚስቶቻቸዉን እየነጠቁ ያማግጧቸዋል። ልጆቻቸዉም አንደዚሁ። ባኦጋዴን፤ በሶማሊ እየፈጸመ ያለዉን ድርጊት በአልጀዚራ በቲቪ ያየነዉ ነው።>> ወያነ የያዛቸዉን ሉአላዊ መሬታችን አልሰጥም ብሏል በዚህ የምትለዉ ነገር ካለ አስተያየትህ? <<ወያነ ከግዛታችን ካስነሳልን በጀ! ለሱም ይበጀዋል። ካላነሳም ማስነሳቱን የሚከብድ አይደለም።የድምበር ክርክር ጉዳይ ያበቃለት የሞተ ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያን ስንመለከት አርግዛለች።ምን እንደምትወልድ ግን ሕዝቡ እየተጠባበቀ ነዉ። በእወነቱ ኢትዮጵያ ማርገዝ በተገባት ነበር? አያስፈልጋትም።ሕዝቡ ከወያኔ ማነቆ ተገላግሎ ወደ ሌላ ሽግግር እያመራ መሆኑን እያታዘብን ነዉ። ይህ ከድምበር ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ሌላ ጉዳይ ነዉ። በኛ በኩል ፤የድምበር ጉዳይ አልቆለታል። የተባበሩት መንግሥታት ከዚህ ተባሯል። የቀረ ነገር ካለ፤ “ተመድ” ስሙን አንዴት ያስመልስ/ያ’ሳድስ ነዉ። ስሙን በእንዴት መልክ ማሳመር እንዳለበት የራሱ የግሉ ጉዳይ ነዉ። ለራሱ ችግር ሲል። የ ኤርትራ ጉዳይ አንደሆነ ያለቀለት ነዉ። የኛ የተሰጠዉ መሬት በፈለግንበት ሰዓት መልስን መዉሰዳችን የማይቀር ነዉ። ዓለምም ብትሆን ወዳ ሳትሆን በግዷ የኛዉን ትቀበላለች። ኤርትራንም እኮ ወዶ የሰጠን ሃይል የለም። ተመድ እኮ በ 50 ዎቹ ወደ ኤርትራ መጥቶ ነገር አበላሽቶ ሄደ። ነጻ ስናወጣት ተመልሶ መጣ። አሁንም መሬታችን ካስመለስን በሗላ፤ ያ ሲሆን- ተመልሶ እንደገና ይመጣል። ይሄ እኮ ነዉ ተመድ ማለት። ሌላ ተመድ የለም። የማናዉቀዉ ሌላ ተመድ የለም። ሄልኮፕተራችሁ ከዚህ አስነሱ፤ ልቀቁ ብለን ስናስነሳቸዉ አዉቀዉታል፡ ያኔ ያለቀ መሆኑን ያቃሉ።>> …….ኤርትራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ህጋዊም ሆነ ወታደራዊ መብት አላት።ተመድ ኖረ አልኖረ፤ተመድ ሄደ አልሄደ ጦርነት ሊያስቆም አይችልም።ለዚህ ነዉ ኤርትራ ዉስጥ ሲነጋ በነሱ ምሽት ሆኖ ጨለማዉ ገና መያያዝ የጀመሩት። ገና አልነጋላቸዉም። ኢትዮጵያ ሰላም አንድታገኝ ብልን ድሃ ስለሆነች በዉስጣዊ ዉጥረት ስለተወጠረች ሰላም እንድታገኝ ብለን፤ ለኛም ሸክሙ አንዲቀለን፤ ሸክማቸዉ የኛ እንዳይሆን፤ብለን እጃችን አስገብተናል።ኤርትራ አንደ መዓከላዊ ስበት ሆና መታየትዋ የማይቀር ነዉ። ……እሳቱ እየነደደ ነዉ።እኛ ከእሳቱ አጠገብ ነን፡ ያለነዉ።አሳቱ ነዶ ወደ አመድ ለመለወጥ ሊቀረዉ በቁጥር ስንት ያክል የማገዶ እንጨቶች እንደቀሩ የሚያዉቀዉ ከእሳቱ አጠገብ ላይ ያለዉ ሰዉ ነዉ የሚያዉቀዉ።ከእሳቱ አጠገቡ ላይ ያለነዉ ደግሞ እኛ ነን።……>>
በማለት “ተዓጠቕ”/ታጠቅ ከተባለዉ ወታደራዊ መጽሄት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ አንኳር አንኳር ነጥቦች እነዚህ ነበሩ።.ኢትዮጵያ ለዘላም ትኑር!!!!-

አናካሹ ኢትዩጵያዊው እስላም ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር)

አናካሹ ኢትዩጵያዊው እስላም ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር) ወነገረነ አዲ በእንተ ምፅአተ እስላም ወይቤለነ ናሁ ይበጽሕ ጊዜሁ ከመ ኩሉ ዘይቀትለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመስዋዕተ ያበውእ ለእግዚአብሔር።>> “ዳግመኛም ስለ እስልምና መምጣት ነግሮናል፡ እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዳቀረበ የሚመስልበት ጊዜ ይደርሳል፤ብሎናል።” ይህን የወንጌል ቃል ጠቅሰው ስለ እስላም እንደተናገረ ያስረዱት አባ እንባቆም መጀመሪያ በአስላም ሃይማኖት የነበሩ ሰው ናቸው። አባ እምባቆምም በትውልድ የመናዊ ሲሆኑ ቁርዓንን ሲመረምሩ ከቆዩ በኋላ በቁርዓን ስለክርስቶስ የተነገረውን ይዘው አብዝተው በመጸለይና እውነቱን ግለጽልኝ በማለት ሱባኤ ሲገቡ ጌታችን እውነቱን ገልፆላቸው ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም ወደ ክርስትና ሲመለሱ እንደተለመደው ሁሉ አክራሪ እስላሞች ሊገድሏቸው ተነሡ። በእርሳቸው ክርስትያን መሆን ምክንያትም ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ያቃጥሉ፤ክርስትያኖችንም ያሳድዱ ጀመር። አባ እንባቆምም ከአክራሪዎቹ እየሸሹ ነገር ግን ከዚያው ከቁርዓን እየጠቀሱ ክርክራቸውን በጽሑፍ ይልኩላቸው ጀመር። በዚህ ወቅት እርሳቸውን አሳድዶ ለመየዝ የተላከ አንድ የአክራሪ እስላም ጦር አዝማች እሰኪ የምትለውን በደንምብ አስረዳኝ፤ከዚህ በኋላ እኔ ቤተክርስትያንም አላቃጥልም ክርስትያኖችንም አልገድልም ሲላቸው ለእርሱ አንድ መጽሐፍ አዘጋጅተው ላኩለት “አንቀጸ አሚን” (ሐመር ጥር 2001 ዓ.ም ወቅታዊ ጉዳዩች (ደ-/ን ብርሃኑ አድማስ - ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ ማቴ.26፤52) (ገጽ 19)። በአንቀጸ ብርሃን የተጠቀሰው የአባ እንባቆ ታሪክ ለአንባቢዎቼ ልጠቅስላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት ከላይ በርዕስ የተጠቀሰ “ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ ወይንም “አቡ ሐይደር” በመባል የሚታወቅ የእስልምና ሃይማኖት ሰባኪ በእለተ እሁድ በዶቸበሌ ራዲዩ የተላለፈው የሃይማኖት ችግሮችና መፍትሄው በኢትዩጵያ በሚል ርዕስ ከወያኔ መንግሥት የሃይማኖት ጉዳዩች፤ እንዲሁም ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው በቅርበት ያውቁ ይሆናል ብለው የገመቷቸው ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተጠሩ እንግዶች አነጋግሮ ነበር። እስልምናን ወክሎ በማብራራት ከእንግዶቹ አንዱ የነበረው “አቡ ሓይደር” ነበር። አቡ ሓይደር ሃይማኖቱ የት እንደተማረ እና እንዳጠናቀቀ ባለውቅም የሃይማኖት መምህር ነው ብለው ደግ ሰው መስሏቸው ሰው አግኘን ብለው እንደዛ አይነቱ አናካሽና ውዥምብራም በእንግዳነት ማቅረባቸው ባልወቅሳቸውም በመንግሥት ደረጃ ተወክለው የተገኙት የወያኔ መንግሥት ተወካዮች ተብየዎች ግን እውን አንዳንድ ተቃዋሚዎች “ወያኔ ነው ከበስተጀርባ እያሳበበ የሚያቆራቁሰው/የሚያጋድለው” እያሉ የሚከሱት ዓይነት ክስ ልክ ሆኖ ካልሆነ በስተቀር እውን “የመንግሥት” ተወካዩች ከሆኑ ኣቡሃይደርን ጥላቻና ቅራኔ በሚያናፍስበት“Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice,” በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ማሕበራዊ የድረ ገጽ ራዲዩ መነጋገሪያ Pal Talk (ፓል ቶክ) መድረክ የሚዘለብደው የጥላቻና የጭካኔ ንግግሩን ተከታትለው አቡሐይደርን ወደ ሚመለከተው ዓለም አቀፍ የደህንነት ተቋማት በማስተላለፍ ወይንም እራሱ ወደ ሕግ (ወያኔ እውን ሕግ የሚያከብርና ግጭት የለም እያለ የሚያስተባብለው ውሸት የማያራግብ ስርዓት ባይሆን ኖሮ) አቅርቦ ተገቢውን ምርመራ እንዲካሄድበትን የፍትሕ ተቋማት (እውን ካሉ ፡ አንዳንድ የፍትሕ ሰዎች ላይታጡ ይችሉ ይሆናል የሚል እምነት አለኝና) በዚህ ሰው ላይ አንዲዳኙ ማድረግ ነበረባቸው።

ለምንድ ነው እንደዚህ ልል የቻልኩት? ከላይ የተጠቀሰው “Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice” የተባለው ፓል ቶክ አቡ ሃይደርና አንዳንድ እሱን መሳይ ጽንፈኞች በመሰባሰብ እስልምና በኢትዩጵያ ዋና አትኩሮታቸው በማድረግ በክርስትና አማኞች ጥቃት እንዲደርስ በግልጽ ሲሰብኩ የተቀዳ መረጃ አለ። ለምሳሌ አንድ የክርስትና እምነት ተከታይ በተጠቀሰው መድረክ “አቡሐይደርን (ሳዲቅ መሐመድን)“ እስልምና ሃይማኖት ጥለው ወደ ክርስትና ሃይማኖት የገቡ እስላሞች ላይ ምን ትላለህ ብሎ ሲጠይቀው መልሱ “አንገቱ ይቆረጣል! አንገቱ ያጣል፤ግድያ ነው!” በማለት በማያወላዳ መልሱ ሰጠቷል። ይህንን ቃል በቃሉ እንደወረደ ልጥቀስ፡ <<አንድ ሰው ከእስልምና ወደ ከክርስትና ወዶ በፈቃዱ አልተስማማኝም ብሎ መመለስ ይችላል ወይ? ቢመለስስ ለምንድ ነው ሞት እሚፈረድበት? መጽሐፋችሁ ለምን ሞት ይፈርድበታል? የኼን እንድታብራራልኝ እፈልጋለሁ። ፋክቱ/fact አሁን ላለው ዓለም የሚያንጸባርቅ ነው ወይ? እንግዲህ የመጀመሪያውን ጥያቄየ አትርሳ “አንድ ሰው ሃይማኖቱን ከተወ ይገደላል ሲል ከራሳችሁ ሰምቻለሁ፡ ይህንን ብታብራራል
"የ“ሸኽ ሳዲቅ መሐመድ(አቡሓይደር) መልስ እነሆ "ሃይማኖቱን የለወጠ ይገደል! ወይንም እምቢ ቢል ይገደል! እዚህ ጋር የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እኮ ነው አሁን።… እምነቱ ለቆ የወጣ ሰውስ? እምነቱን ለቆ የወጣ ሰው፤- በመጀመሪያ “አላህን” መካድ “ወንጀል” ነው። ከወንጀሎች ሁሉ የመጨረሻው ጣራ የነካው አንዱንና እውነተኛውን አምላክ “አላህን” ክዶ መገኘት ነው። ሰው በፈጣሪ ላይ ለመወንጀል መብት አልተሰጠውም፡ ይሄ መብት አይደለም። ሃይማኖቱን ለቆ የወጣ ሰው በመጀመሪያ የሦስት ቀን ዕድል ይሰጠዋል፡ “ምንድ ነው ሰበቡ? ነው።” ይሄ ሰው ሰበቡ ምክንያቱ ምንድነው፡ አንደኛ የኢኮኖሚ ችግር ደርሶበት ባኮኖሚ ምክንያት ችግር ደርሶበት ከሆነ ያ ነገር ይመለስለታል፤(ይብራራለታል)።ያ ካልሆነ ደግሞ በሃይማኖቱ ላይ “ሹባሃት” ወይንም አስመሳዮች ገብተውበት ጥርጣሬ አድሮበት ከሆነ በሊቃውንቶች ይፈታለታል። እነዚህ ትቶ አልፈልግም ብሎ የሚወጣ ሰው ግን “ምን ይሆናል?” ጋሬጣ ይሆናል! ሌሎች ወደ እምነቱ እንዳይገቡ እኔም አውቀው ነበር እያለ ዕንቅፋት ይሆናል። ዕንቅፋትን ማስወገድ ደግሞ “በሸሪአችን” ግዳጅ ነው።ስለዚህ አላህን መካድ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከሆነ ቅጣቱ “ግድያ” ነው! ቅጣቱ ግድያ ነው! የሃይማኖት ነፃነት ሌላ ግድያ ሌላ'
 ምንጭ http://www.youtube.com/watch?v=A6rHwMBeNyU
ፋሺስቶች፤ኮሚዩኒስቶችና ደርግ እንዲሁም የነጻነት ግምባሮች ሲያደርጉት እንደነበረው ማለት ነው። {ምንላባትም የፖለቲካ ድርጀቶች ይሻሉ ይሆናል} አንድ የፖለቲካ አባል ድርጅቱን ከድቶ የወጣ ከሆነ ይገደል እንደነበረው ማለት ነው። እንግዲህ ይህ ሰዎች የሚደነግጉት ድንቁርና ነው። ካለይ ያነበባችሁት የአቡ አይደር ግን የአላህ/የእስልምና ትዕዛዝ ነው፡ሲል ነው ሰውን መግደል ወንጀል ሳይሆን “ሕጋዊ” መሆኑን ነው እየገለጸልን ያለው። እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ለምሳሌ አንድ እስልምና ዕምነት አማኝ የነበረ ኢትዩጵያዊ ዜጋ በፈለገው ሁኔታ ወይንም በፈለገው ፍላጎታዊ ምክንያት ይኑረው እስልምናን ለቆ መውጣት እንደማይፈቀድለትና ሁሉንም ተሞክሮ አሁንም አማኙ ከእንግዲህ ወዲህ የፈለጋችሁ አሳማኝ ክርክርም ይሁን የኢኮኖሚ ድጎማ ብታደርጉልኝም ‘አልፈልግም’ ‘አልከተልም’ ማለት እንደማይችልና ሁሉንም ምክንያት ተሞክሮ አሁንም “አይሆንም” እስልምናን አልከተለም “በቃኝ” ካለ ሳድቅ መሐመድ (አቡ ሐይደር) እንዳለው ቅጣቱ “ግዲያ” እንደሆነ፤ አንገቱ እንደሚያጣ ‘በእስልምና ሃይማኖት ቀልድ’ እንደሌለና ቁርአናቸው ወይንም ሸሪኣቸው ሰውን የመግደል መብት እንደሰጣቸው፤ ይህ የመግደል መብትም ሕጋዊ እንደሆነ ነው ሳያመነታ በጠራ አገላለጽ ነበር መልሱን ያስቀመጠልን። ይህ ጭካኔ፤ይህ ጉድ፤ይህ ወንጀል በሃይማኖት የተደገፈ “ሕጋዊ” ሃይማኖታዊ ግድያ ከሆነ፤ በዚህ መሠረት በሺዎቹ የሚቆጠሩ የኢትዩጵያ እስላሞች የነበሩበት እምነት ለቀው ወደ ክርስትና እምነት በመቀላቀላቸው በየዓመቱና ባለፈው ወር የታየው በነዚያ አዲስ የክርስትና እምነት ተከታዩች ላይ በእስላም ሽብርተኞች ጥቃት ደርሶባቸው ስንመለከት “አቡሐይደር” የሃይማኖቱ መምሕራቸው ግድያ ይገባቸዋል እያለ በይፋ ሲሰብክ በነዚህ ንጹሃን ዜጎች ላይ ሰይፍ ሲመዘዝባቸውና ለወደፊቱም ማንም እሰላም ሃይማኖቱን ከለወጠ “እስልምናን መካድ ወንጀል” ነውና ቤቱን ንብረቱን እየተቃጠለ ፤አብረውት ወደ ሌላ ሃይማኖት የሄዱት ቤተሰቡና ዘር ማንዘሩ እንደሚጨፈጨፍ እያስተማረ ያለው ሰባኪ (ሸክ ሳዲቅ መሐመድ/አቡ ሓይደር) መንግሥት ተብየው ምን እየጠበቀ ነው? በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህ ኋላ ቀር ሰው በግድያ ሰበካ ዜጎችን የሕሊና ጭንቀት እንዲያደርባቸው እያስፈራራና እስልምና የተወ ሰው ይገደል እያለ ሲሰብክ ለታየው ብጥብጥም እንዲህ ዓይነት ሰበካ በነፃ ሲለቀቅ ለሽብር ጥቃት በቀላሉ መስፋፋት ብር የሚከፍት ምክንያት ሆኖ እያለ “እስላሞች በአክሱም፤እስላሞች በኢትዩጵያ መብታቸው አልተከበረም እያለ በባዶ ጭንቅላቱ ሲጠይቅ “የመብት” ትርጉም የሚጻረረው “ሰው መግደልን” የመሰለ አረመኔነትና የፍጡራን “መብት” የሚጻረር ከሁሉም ወንጀሎች የበላይነት የያዘ ከባዱን ወንጀል “ሕጋዊ” ነው ሲል በጥላቻ ስብከት ሕሊናው የዞረበት ይህ አደገኛ ሰው እንዴት ልቅ እንደተተወ እንቆቅልሽ ትዕይንት ነው። እሱ በሚያስተምረው አረመኔነት የሚገደሉ ዜጎች መብት የላቸውም ሲል ይህ ሰው የሚኖረው በጫካ ሕግ The law of the jungle” ዘመን የሚኖር ወይስ በ21ኛው ክፍለ ዘመን? ለመሆኑ ሼኩ “መብት” ማለት ምን እንደሆነ ስለ የሰው ልጅ ክቡርነትና “መብት’ ትምህርት ቤት ውስጥ ተምሮ ያውቃል? ‘ዜጎች እስልምናን ከለቀቁ አንገታቸው ይቆረጥ ብሎ የሚያዘው የእርሱ ቁርአንም/ሸሪአም ይሁን የክርስትና ወይንም የማንም ሃይማኖት ይሁን የሰው ልጅ በሆስቴጅ/እገታ/ወደ ሌላ ቦታ /እምነት/ፍቅረኛ/ትዳር/ሥራ/ጓደኛ/ የመምረጥ መብቱን አግዶ “ባርያ” አድርጎ የሚይዝ ሃይማኖት፤ስለ ሰው ልጅ ቤተሰብነትና የሰው ልጆች ህይወት ክቡርነትና መብት ‘ምን እያለ ሊሰብክ ይሆን’? እግዚአብሔር/አላህ ማለት “ፍቅር” መሰሎኝ? አላህ ግድያ ውስጥ እንዴት ገባ? እኔ አይመስለኝም እራሳቸው ሰዎች ያጣመሙት ካልሆነ እንዲህ አይነት የራሱን ፍጡር የመመራመር ሃይል ሰጥቶ የሚያግድ ያውም እሱን ፍለጋ እውነታውን ለማግኘት ሩቅ መጓዙን እንዴት ይቃወመዋል? ሱኒው ውሃቢው ሺዓቱን እና ሌላውን ሲገዳደል የምናየው በዛው ሕግ ይሆን? መሰንበት ደጉ ማለት እኮ ጥሩ ነው። እንኳን እስላም አልሆንኩ። በዚህ የሰው ልጆች መብት ይከበር ምላሴ እስልምናውን ብተው ወይም ብወቅስ “አንገቴን ይቁኝ ነበር ማለት እኮ ነው” ጉድ! አቡ ሐይደርን ሳዳምጥ ተመስገን አምላኬ አንኳን ክርስትያን ሆንኩ አሰኘኝ አሁንስ።እንዴት ሰው በባርነት ተይዞ አትመራመር፤ ከተመራመርክ እንዴት ትገደላልህ ይባላል? እኔ የምገምተው ሼኮቹ የሚጠመዝዙት ሕግ እንዳይሆን? አቡ ሓይደርን ሳዳምጥ “ቶራ ቦራ” ሆኖ የሚያስብ የአፍጋን የሃይማኖት ጦረኛ ይመስለኛል፡ ንግግሩ ሁሉ ሳዳምጠው፡በጣም የጠበበ፤ አናካሽና ጉረኛ ትዕቢትም የወጠረው ባዶ ሰው እንደሆነ ይሰማኛል። ዘመኑ 21ኛ ክፈለዘመን ነን ያለነው፡ ሰውየው የሚዘባርቀው የሰው ግድያ ወንጀል “ህጋዊነት” እንዳለው የሚሰብከው የመቸ የዘመነ ጭካኔ ሕግ እንደሆነ ባይገባኝም፤ በዚህ ዘመን በዚህ በሰለጠነው ዓለም “ነውር፤ጥሩና በጎ” ተለይቶ በሚታወቅበት የሰው ልጅ ክቡርነት መብት ይብዛም ይነስ በሚከበርበት ዓለም እየኖረ፤“እስልምናን የተወ ሁሉ ይገደል” ብሎ በመላው ዓለም የተበተኑ ኢትዩጵያዉያን እስላሞችን በተጠቀሰው ፓል ቶክ በየጊዜው እየመጣ ሲሰብክ፤ አቡሓይደር በሚጠቅሰው የእስለሞች የመግደል መብትና ሕግ ተሞርኩዞ ብዙ ዜጎች ለጥቃት መጋለጣቸውና ለወደፊቱም የሚጋለጡ ከሆኑ የሰው ልጆች መብት ጠበቃዎችና መንግሥት ተብየው የወያኔው መንግሥት ይህንን ተከታትሎ እርምጃ ካልወሰደ የሱ መንግሥትንት ምን ሊረባ ነው? ይህ ትምክህት እየተዘረጋ እያዳመጠ እንኚህን ባዶ መንፈሶች በህግ ካልያዛቸው መንግሥት የማን ጐፈሬ ሊያበጥር ነው መንግሥት ሊሆን የሚችለው? ደግሞ እኔን የገረመኝ የዶቼቤላ ራዲዩ አዘጋጆች ይህ ቢከፍቱት ተልባ የሆነ በቶራ ቦራ ጭንቅላት የሚጓዝ ሰው አገኘን ብለው ለውይይት ማቅረባቸው በጣሙን ይገርማል። ሰውየው ባዶ መሆኑን እና ዋሾ መሆኑን የምትታዘቡት ደግሞ በአንድ የሰበካው አወድዩ ቪዲዩ ያስተላለፈው ንግግር በሌላኛው መርሐግብር/ፐሮግራሙ ያስተላለፈው ንግግር እርስ በርሱ ሲምታታበት ታዳምጣላችሁ።እየተደናገጠ ይሁን ወይንም ችሎታ አንሶት ወይንም ሆን ብሎ የመዋሸት ልምድ ኖሮት ብቻ አሁን ያለው ነገ ሲክደው ታዳምጣላችሁ። ያንን ቆየት ብየ አቀርብላችሗለሁ። የአቡ ሓይደር “የግደል ግደል” ሰበካ በሸሪዓ ከተደገፈ በየራሳቸው ምክንያት ብዙ ዜጎቻችን እስልምናን እየጣሉ ወደ ክርስትና ሲገቡ እየተከታተሉ ንበረታቸውን የሚያቃጥሉላቸውና አንገታቸውን በገጀራና በሰይፍ እየተቀሉ ያሉት ዜጎቻችን እያጠቋቸው ያሉ ቡድኖች ሃይማኖታቸው “አወስልምናን የተወ መግደል” ስለሚፈቅድላቸው “የእስልምና አክራሪ/ጽንፈኞች” ብለን ነው የምንጠራቸው ወይስ ምን ተብለው ነው የሚጠሩት? (ጉድ ዘመን እኮ ነው የገባነው!) እስኪ በሌላ መልኩ እንደገና ልጠይቅ፦<<ነብሰገዳዩችና ወንጀለኞች’ ሽብርተኞችና አክራሪ እስላሞች>> ብለን እንጥራቸው ወይስ <<ሕጋዊ ነብሰገዳዩች&፤ 'ሰላም አስፋኞች?>> ምን እንበላቸው? አሸባሪ እንዳንላቸው “አቡሓይደር” ሰውን መግደል “ሕጋዊ ነው” ሲል በይፋ እየሰበከ ነው። ለዚህም መጽሐፉ እንደሚደግፈው ይጠቅሳል። ይሄ ከሆነ በዚህ ሰበብ የሚገደሉ፤ንብረታቸው የሚወድምባቸው ሰዎች፤ በሽብር ኑሮአቸው በፈርሃት ኑሮአቸው የሚበጠበጥ ዜጎቻችን” ፤ “እንዲሞቱ፤ አንገታቸው በሰይፍ፤በገጀራ እንዲቀላ፤በድንጋይ ተወግረው እንዲሞቱ፤የትም ዞረው በነፃ የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ተነፍገው ሕይወታቸው ለጥቃት የሚጋለጡ ዜጎቻችን “ቁርኣኑ/ሸሪአው መብታቸው ከገፈፈባቸው እና ገዳዩቹም ሰው ለመግደል ንብረት ለማቃጠል ተፈቀዶላቸዋልና ዜጎች እንዴት ከ“ጽንፈኞች አትበሉን” “ሕጋዊ ነብሰ ገዳዮች” መከላከል ይቻላል? ለመግደል/ነፃ እርምጃ ለመውሰድ በአላህ የተሰጠን መብት ነው ሊሉን ሽብርተኞች/አክራሪዎች ብለን ብንጠራቸው ፍረድ ቤት ቢወስዱን “ሕጋዊ” ነብሰገዳዩች (የአላህ የግደል፤ የአርዕድ፤አሸብር ትዕዛዝ አስፈጻሚዎች) ነን አንጂ ሽብርተኞች አይደሉም ልንባል ይሆን? እንዲህ ከሆነ ምን እንበላቸው? ወይስ ምን ቃል እንስጣቸው? መንግሥት ተብየውና የዓለም የደህንንትና የሰው ልጆች መብት ጠበቃዎች በዚህ ከፍተኛ ትኩረት አድርገውበት እውን ቁርኑ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪና ኢሰብአዊ የግድያ ወንጀል ውስጥ ግቡ የሚል መጽሐፍ ከሆነና ዜጎች እንዳይገደሉ ንብረታቸውና ቤተሰቦቻቸው በሰይፍ እንዳያልቁ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የመከላከል መብታቸው እንዴት ይከበር የሚለው ጥያቄ ሕብረተሰቡና መንግሥት መነጋገር ይኖርበታል። ሰው መግደል መብት የላቸውም የሚል ሕግ ካለም ፤ በይፋ የግድያ ስብከት የሚሰብኩት እንደ እነ አቡሐይኢደር አስከመቸ ቸል ተብለው ሊታለፉ ነው? ጽንፈኛው አቡሐይደር ቁርአኔ/ሸሪአው ይፈቅድልኛልና እስልምና ለቀው የሚሄዱ ሰዎች ተከታትየ እገድላቸዋለሁ ቁርአን/ሸሪዓ ፈቅዶልኛል እያለን ነው። ታዲያ ምን ይበጃል? በዚህ የተነሳ ሃይማኖታቸውን እየለቀቁ ወደ ሌላ ሃይማኖት የገቡ እና የመመራመር መብታቸው ተነፍጎ እየተገደሉ እንደሆነ ሁላችን የምናውቀው እውነታ ነው። የማያምን ካለ አብሮ ከዚህ ጋር በድምፅ የተቀዳ ቃለ መጠይቅ ለማስረጃ አቀርብላችኋለሁ። እንዲህ ከሆነ “አቡሐይደርም” ይሁን ሌሎች የኢትዩጵያ እስላሞች ኢትዩጵያ መብታችን አላስከበረችልንም፤ አክሱሞች የእስላሞች መብት አላስከበርም ብለዋል እያሉ የመብት ጥያቄ ሲያቀርቡ በሌላ በኩል የሰው ልጅ በሕይወት የመኖርና ደስ ያለው እምነት የመከተል መብት እንዳይኖረው “በግድያና ቤቱና ቤተሰቡ በእሳት ማጋየት፤ አንገቱን እንደ “በግ’ እነደ “በሬ” በቢላዋ እንዲታረድ በሰይፍ አንዲቀላ በድንጋይ ተወግሮ “እንዲሞት” ሕጋዊ ነው ብሎ መሰበክ “የአማኞች መብት መጣስ” ብቻ ሳይሆን “ወንጀል፤ጭካኔ አራዊትነት፤ነብሰ ገዳይነት፤ጥፋት፤እልቂት፤ብጥብጥ” እንዲነሳና እንዲስፋፋ ምክንያት ስለሚሆን ይህ እስካላቆሙና ካላወገዙ የእስላሞች መብት በአክሱምና በምድር የሚጠየቀው የመብት ጥያቄ የራስን ጭንቅላትን መጀመሪያ መወጠርና በሰብአዊ አስተሳሰብ በደግናትና በርህሩህነት አርቆ አሳቢነት ማነጽና ማጽዳትን ይጠይቃል። ሃሳዌ መሲሕ ማለት እንደዚህ ያለው ሰባኪ “ግድያን ህጋዊ” የሚያደርግ ስብከት ነው። ያፈለገው ይሁን ሃይማኖት ሃይማኖቱን ስለ ጣለ “ይገደል” የሚል በጣም አረመኔ፤ግራ ቀኝ ያለተመለከተ የሰው ልጅ ክቡርንት ሚጥል ስለሆነ ሁሉም ማውገዝ አለበት። ትልቁ የመብት ትርጉም ከዚህ ላይ ይጀምራል። ሰውን በካራ እያረዱ በሰይፍ በገጀራ እየቀሉ “መብቴን አክብሩልኝ” የሚል በጣም አስቂኝ ነው። ታራ ወንጀለኛና አሸባሪነትም ነው። እኔ እንደ ሚገባኝ ሃይማኖት ፍቅርን እንጂ ግድያን ላላንበት ዘመን የሚሄድ አይደለም። የቅድሙን ልጨምርላችሁለ- እስልምና ትተው ወደ ክርስትና የገቡት በተባለው የግድያ ሕጋዊነት እንደኔው የገረማቸው አባ ዕንባቆም እንዲህ ሲሉ ለቀድሞው ኢማማቸው ጽፈው እንደነበር መጽሐፋቸው ይመሰክራል፡


"ኦ እማም እምይእዜሰ አወስአከ በቃለ ትሕትና በከመ አዘዘኒ መጽሐፈ እምነትየ" ኢማም ሆይ ከእንግዲህ ወዲህ የምመልስልህ የሃይማኖቴ መጽሐፍ እንዳዘዘኝ በቃላት ትህትና ነው"

 ክርስትና እንኳንስ የኖሩበትን የተለወጡትም ሰይፍ ከማንሳትና በሰይፍ ከማጥቃት ሕሊና መልሶ እንዴት ሰላማዊ እንደሚያደርግ ለማሳየት ነው። “አባ ዕንባቆም ከሃገራቸው ከየመን ሸሽተው ወደ ኢትዩጵያ ገብተው በተለያዩ ገዳማት ተዟዙረው የቤተክርስትያኒቱን ትምህርት ልቅም አድርገው የተማሩና በምንኩስና የኖሩ በመጨረሻም በደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔትነት /እጨጌነት/ የተመረጡ የበቁ ሰው ነበሩ። እስካሁን የሚታወቁት እጨጌ እንባቆም በመባል ነው። ( እንደላይኛው)።

ዛሬ አቡሐይደር ባለው ትኩስ ምላስ ቢያገኛቸው ምን ይላቸው ኖሯል? ያውም እኮ በጣም ከሚገርመው ነገር እሱ በሚያስተምርብት ፓል ቶክ ውስጥ የሚነገረው ጸረ ክርስትና እና ጸረ ኢትዩጵያዊነት፤ እንዲሁም አፍጋኒስታንና ዓለምን በሽብር የሚቆሏዋት የታሊባንና የአልቃይዳ ሽብርተኞችን እንደግፋለን በማለት በፓልቶኩ በይፋ ሲናገሩ እንዲሁም የኢትዩጵያ አብያተ ክርስትያናት በእሳት አቃጥሏቸው እያሉ የሽብር አዋጅ የሚነዙ በዛው አቡ ሓይደር በሚሰብክበት “Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice,” በተባለው ፓል ቶክ የሚናገሩትን በዩቱብ የተዘረጋውን ብታደምጡ ምን ትሉ ይሆን?

 ከዚህ በታች ሊንኮቹን/ መሰኮቱን/ቁልፎቹን እየከፈታችሁ አድምጡ። ሳዲቅ መሐመድ (አቡ ሓይደር) ለአላህ የሚውል ጥቅም ከሆነ ውሸት ዋሽቶ መስበክ በቁርአን ይፈቀዳል በማለት ውሸት እንደ እውነት ተደርጎ እስላሞች እንዲዋሹ የሰበከትንና እስልምናን ጥሎ የሄደ ሰው ግደሉት እያለ የሚሰብክበትን የሽብር መድረክ ምን እንደሚል እነሆ ከዚህ ቀጥሎ ያድምጡ። ይህነን ሲያደምጡ አምላክ ትዕግስቱን ይስጠዎት እላለሁ። የተዘገቡ 8ንት መዝገቦችን በቲ-ዩብ “ስዕለ ድምፅ” የተዘገቡትን ያድምጡ እነሆ፦

Please open the attached files to hear some of the audios. IF YOU CAN'T JUST COPY THE GIVEN URL ADRESS AND PASTE IT ON YOU TUBE. BUT, MAKE SURE CLICK ONLY WHAT I GAVE YOU TO HEAR SO YOU WILL NOT MISS ANY OF THEM. Audio evidences instigating Crime:-

1. The picture and teaching of Sheik Sadik Mohammed on killing X-Muslims : http://www.youtube.com/watch?v=A6rHwMBeNyU 2.Crime instigators lead by Sheik Sadik Mohammed : http://www.youtube.com/watch?v=k6PYrgrxtpE 3.Crime instigators lead by Sheik Sadik Mohammed video2: http://www.youtube.com/watch?v=cNwRPU-N2JQ 4.Instigators lead by Sheik Sadik Mohammed to burn Saint marry church in Ethiopia: http://www.youtube.com/watch?v=zskKK4X1smM&feature=related 5. Instigators lead by Sheik Sadik Mohammed declaring war : http://www.youtube.com/watch?v=v5wsqz7R4Vk&feature=player_embedded 6.A witness telling the damage of the violence in Jimma area and Muslims rejoicing: http://www.youtube.com/watch?v=sAdPBZD65zQ 7.A witness telling the reason for the violence was Muslims being converted to Christianity: http://www.youtube.com/watch?v=W4nIq7F8c3c 8.Crimes in jimma: http://www.youtube.com/watch?v=yTL3Yhlxb7Y Posted by Getachew Reda www.ethiopiansemay.blogspot.com Inquiry for any of my books please do call 408 561 4836