Friday, June 26, 2020

መቀሌ ውስጥ የገዳ ስርዓት የኦሮሙማው የመደመር ብልጽግና ፓርቲ ሹም ሆኖ የተሰየመው በምኒሊክ ሸዋ ጥላቻ የሰከረው ትግራዋዩ የሃተታ 70 እንደርታ መጽሐፍ ደራሲ ነብዩ ስሑል ሚካኤልን ላስቃኛችሁ! (ጌታቸው ረዳ) (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)


መቀሌ ውስጥ የገዳ ስርዓት የኦሮሙማው የመደመር ብልጽግና ፓርቲ ሹም ሆኖ የተሰየመው  በምኒሊክ ሸዋ ጥላቻ የሰከረው ትግራዋዩ  የሃተታ 70 እንደርታ መጽሐፍ ደራሲ ነብዩ ስሑል ሚካኤልን ላስቃኛችሁ!
(ጌታቸው ረዳ)
(Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)

በፎቶ ላይ የሚታየው ደራሲው ነብዩ ስሑል መጽሐፉን ሲያስመርቅ የተሰጠው የካባ ሽልማት ለብሶ ምርቃቱ ሲከናወን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ነው። 

እንደምን ሰነበታችሁ!  
ባለፈው ሰሞን የመጀመርያው ወያኔ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ረዳ ልጅ የሆነው ‘ካሳ ሃይለማርያም’ አክራሪ የሸዋ ጥላቻው ምን እንደሚመስል በመጠኑ ለማሳየት ሞክሬአለሁ። በጣም በበርካታ አንባቢዎች ተነቧል። የምጽፋቸው ሰነዶች ለኢትዮጵያ ወገኖቼ ለሕዝብ እንዲዳረሱ ላደረጋችሁ ወገኖች ሁሉ አመሰግናለሁ።

ዛሬ ደግሞ አዲስ አባባን “ፍንፍኔ” እያለ በመጽሐፉ የሚጠቅሰው የብልጽግና ፓርቲ የነብዩ ስሑል ማንነት ላጫውታችሁ ነው። በቂ ጊዜ ባላገኝም በማገኛት ክፍት ደቂቃም ቢሆን ‘አረፈ እያልኩ’ ማንበብ የጀመርኩት የዚህ ልጅ መጽሐፍ የታዘብኩት ነገር መጽሐፉ በእንደርታ ታላቅነት እና በወያኔዎች የ“አሽዓ” ጥንታዊ የንግሥና  የበላይነት “ፉክክር” ያነሳሳው ውስጣዊ ቁጣ ይመስላል። 


ያም ካልሆነም የታላቅዋ እንደርታነት የንግሥና መሰረት ነን ባይነት ያመነጨው እልክነት በተለይ እንደርታዎች በወያኔ አሽዓዎች (አክሱም  ዓድዋ ሽሬዎች- በተለይ  በዓድዋዎች የመተዳደሩ እንቆቁልሽ የሚያበሳጭ እውነታ እንዳለው ቢገባኝም) ባጭሩ “ዓድዋዎች እጃችሁን ከእንደርታ አንሱ” - ራሳችን በራሳችን እንተዳደር የሚለው ድብቅ ሕጋዊ መልእከቱ እንዳለ ብቀበለከውም ጥያቀው አስታኮ የሄደበት እጅግ አክራሪ ጸረ ሸዋነቱ ለማንበብ ይጎመዝዛል። ዓድዋዎች ወይንም እንደርታን ትግርኛ የሚያንኳስሱ መሰል አውራጃ የወያኔ ትምክሕተኞች እቅጩን ሲነግራቸው (1ኛ) ትግርኛ ቋንቋ የተመሰረተው “እንደርታ ውስጥ መሆኑን” በመጽሐፉ በገጽ 22 ይናገራል። ሆኖም ነብዩ ይህን ሲል- እንደርታ ውስጥ ትግርኛ ሲፈጠር በስንተኛው ክ/ዘመን መሆኑንም አይገልጽም፡ የሚገልጸው ፣ማስረጃ “እዛው ለመጀመሪያ ጊዜ ትግርኛ መነገሩንም “እንደሆነ ይታመናል” ከማለት ውጭ ማስረጃ አልጠቀሰም። አማርኛም ቢሆን ከተለያዩ ነገዶች የተወጣጡ  ላስታ ውስጥ የነበሩ የንጉሥ ወታደሮች እንደተፈጠረ እንጂ እንሌሎቹ ማሕበረሰቦች “አማራ የተባለ ማሕበረሰብ” ራሱ ችሎ የተከሰተ ማሕበረሰብ እንዳልነበረ እነ ‘ ዶ/ር ላጲሶ ደሊቦን’ የጻፉትን እንደ ማስረጃ ይጠቅሳል።ወቅቱም ወሎ ላስታ ውስጥ አማርኛ በተፈጠረበት ወቅት ትግርኛም እንደርታ ውስጥ ባንድ ወቅት መፈጠሩን ይገልጻል።ያንን እንዲህ እንዳለ፤ ልጁ በአጼ ምንሊክና በሸዋ ላይ ያለው ጥላቻ ከወያኔ ጸሐፍቶች እና ፖለቲከኞች ያልተሻለ እንደውም ንጉሡ በከፋ መልኩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ክፉ የሆነ ውስጣዊ የጠለቀ ጥላቻ እንዳላቸው ይገልጻቸዋል። “የእንደርታ ታዳጊ ወጣቶች የወያኔ የቂም እና ጥላቻ ትምህርት እንዳይበቃቸው ዛሬ ደግሞ እንደ አዲስ ወያኔን ይቃወማሉ ተብሎ የተነገረላቸው ወጣቶቹ እነ ነብዩ ስሑል የጥላቻ ማስተማርያ መጽሐፍ ተጨምሮበት ሌላ የ29 አመት ንትርክና ቂም ብቻ ሳይሆን የሺ መጪው ዘመን ጥላቻ እየተከለ የመሄዱን እድሳት ስመለከት ማቆሚያው የት ይሆን? እላለሁ።ለውግዘቱ መነሻ ነው ብሎ የሚጠቅሰው ማስረጃ “ንጉሡ ጎረምሳ የሆነውን “የእንደርታን ወንድ” እየለዩ እንዲሰለብ በማድረግ የእንደርታ ልጃገረዶች እና ሴቶች የሚያገባቸው ወንድ አጥተው ቁም ቀር ሆነው “የትግርኛ  ግጥም” ተገጥሞ በእንደርታ ሕዝብ ላይ “የዲሞግራፊክ መናግት (እራሱ የተጠቀመበት ቃል ነው) “የተዋልዶ መናጋት” ሆን ተብሎ  የተደረገ በእንደርታ (ትግራይ) የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ ምኒልክ ፈጽመዋል እያለ ይከሳቸዋል።


ለዚህም እንደማስረጃ የሚጠቅሰው ደብተራ ፍስሃ አብየዝጊ የተባሉ በጣሊያን ጊዜ የራስ ስብሓት ተከታይ ሆነው ራስ መኮንን ከጣሊያን አገር ኖርው በኤርትራ በኩል ወደ ትግራይ ሲሻገሩ ምኒሊክ መቀሌ ከተማ ሲገቡ ራስ መኮንን *ን) አጅበው ወደ መቀሌ ከተማ የገቡ የትግራይ ሰው ናቸው። 


ሰውየው በጣሊያን ጊዜ ኤርትራ ውስጥ የኖሩ የጣሊያን ሃይማኖታዊነት/ ዘመናዊነት/ንክኪ የነበራቸው፤ እጅግ አድርገው ሸዋን የሚጠሉ፤ ጎንደር አማራ እና የሸዋ አማራ እየለዩ (በባድሜ ጦርነት ወቅት ልክ አቶ አብርሃም ያየህ መቀሌ ውስጥ የመቀሌ ህጻናት የጨፈጨፈው ኤርትራዊ ፓይለት ሳይሆን የሸዋ ሰው የሆነ እንጂ ጎንደሬ ቢሆን እንዲህ አያደርግም ብለው በሕዝብ ፊት እንደተናገሩት ማለት ነው። በሗላ ግን ኤርትራዊው ፓይለት ጅቡቲ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቆ እንደገባ በወቅቱ እኔም መዘገቤ ትዝ ይለኛል) ፡ ሰውየው (ደብተራ ፍስሐ አብየዝጊ)  ጎንደሬው የዋህ እና የትግሬዎች ወዳጅ “ሸዌው” ግን የትግሬ ጠላት እያደረጉ በማነጻጻር አማራን ከሌላው አማራ በባህሪ እንደሚለያዩ እያነጻጸሩ የሚገልጹ እጅግ አክራሪ የትግራይ ብሔረተኛ የነበሩ መጨረሻ የጣሊያን አገር ሆነው በእጅ ጽሑፍ በትግርኛ የጻፉትን መጽፍ ነው የጠቀሰው።


እኔ የገረመኝ ግን ነብዩ ምኒልክን ያለ አግባብ ንጉሡ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ አድርጎ በመዋሸት ፡ “የእንደርታ ወንድ እንዲሰለብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል እያለ ንጉሡን በውሸት ይከሳቸዋል። ደብተራ አብየዝጊ ግን የምኒሊክ ወታደሮች ናቸው የፈጸሙት እያሉ ነበር በታጣቂ ወታደሮች ላይ ብዕራቸው የጻፉት እንጂ ነብዩ እና መሰሎቹ እንደሚሉት እንደርታን/የትግሬ ወንድን እየለያችሁ ስለቡት ብለው ምኒሊክ ትዕዛዝ አላስተላለፉም።  ያውም ደብተራ ፍስሓ የጻፉት  “ምኒሊክ የዋህ ነበሩ ሰውን አትስለቡ ሲሉ ነበሩ፤ ተራራ ላይ መሽገው እየወጉን ያሉትን የመድፍ ጥይት አትተኩሱባቸው ተው! ሲሉ ነበር” ብለው ጽፈዋል። ነብዩ ግን ምኒልክን ከግራኝ አህመድ የባሰ አረመኔ ነው ይላቸዋል።አርግጥ ደብተራ ፍስሓ አክራሪ ብሔረተኛ ትግራይ ትግርኚ ነበሩ። ‘አማራዎች በትግራይ ደጋማ ለምለምነት ይደነቁ ነበር፡ ሆኖም የትግርኛን ቋንቋ ሲሰሙ ትግርኛን እጅግ የሚጠሉ ነበሩ ይላሉ። ዘማቾቹ በሙሉ አማርኛ በመናገራቸው አማራዎች አድርገው ስለዋቸዋል።  እንዲህ ይላሉ፡ አክራሪነታቸውን ተመልከቱልኝ፡ “ትግራይ ለምና ያመጣቻቸው ይመስል ይንገጫገጫሉ፤ ፡ እንኳን እነሱ አብረው የመጡት አጥንታቸው የወጡ የከሱ ከብቶቻቸው ሳይቀር አይተውት የማያውቁት “የትግራይ ለም ግጦሽ መሬት” እየጋጡ ሰውነታቸው ደልቶአቸው ነበር”።  እያሉ የሚጽፉ ከትግራይ ወዲያ ያለው መሬት ደረቃማ ምድረበዳ ለከብት እንደማይመች አስመሰልው በሚገርም ሁኔታ የሚገልጹ አሰገራሚ ሰው ነበሩ።


እንደውም “ትግሬ ሲጠግብ እስክስታ ያምረዋል ፤አማራ ሲጠግብ ጦር አውርድ የሚል ሕዝብ ነው” ይላሉ። በዚህ ጦር አውርድ ብለው  እግዚሓርን ሲለምኑትና መሬት እየደበደቡ ሲጸልዩ፤ አህመድ ግራኝን ላከላቸውና ከቀያቸው ፈረጠጡ’፡ ብለው የጻፉ  የፋሺስቶቹ የወያኔዎቹ የነ መምህር ገበርኪዳን ደስታ የጥላቻ የጡት አባት ነበሩ።  ዛሬም የነ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የጡት አባት ሆነው ‘ምኒልክን” የትግራይ ሴት ወንድ እንዳትወልድ “ወንድ እንዲሰለብ አድርገው፤ ሴቶች እንዲበዙ አደረጉ” እያለ መጽሐፍ ጽፎ በትግራይ መቀሌ ውስጥ የአብይ አሕመድ የብልጽግና ወኪል ሹም “ወጣት ነብዩ ስሑል ምኒልክን ይከሳል”።


ምኒሊክ ይላል ነብዩ ‘ ከግራይ አህመድ የከፋ ጭፍጨፋ በትግራይ/እንደርታ ሕዝብ ላይ የፈጸመ ንጉሥ ነው” “..፣ “የትግራይ የፖለቲካ ማዕከል ሆና በቆየቺው ‘በታላቅዋ’ እንደርታ ውስጥ ወንድ የተባለ እየለየ በመግደል ትግራይን ለማዳከም እንዲህ ያለ የጭፍጨፋ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ንጉሥ (ምኒሊክ) ‘ክርስትያን ወይንም ኢትዮጵያዊ ነው’ ለማለት አያስደፍርም”


በማለት የነብዩ ስሑል አያቶች ከጣሊያን መገዛት ነጻ ያወጣቸውን እምየ ምኒልክን ክፉኛ  በሆነ ቃላት በመጠቀም “የትግራይ ዘር አጥፊ እያለ” ያወግዛቸዋል።


በዚያ ሳይወሰን ጣሊያን ተምቤን ላይ መሽገው የነበሩት የትግራይ ተዋጊዎች ከብቦ እንዲወጋቸው ተመሳጥሮ ነበር እያለ ምኒሊክን ይከሳቸዋል። እኔ ደግሞ ምን አለበት እኛ ትግሬዎች ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር ሆነን የጣሊያን እግር አጣቢ እንድንሆን ለምን አልፈቀዱልንም ነበር እላለሁ?  አዎ! ምክንያቴን አድምጡኝ፡  “ምኒልክ ወደ ትግራይ ለምን እንደሄዱ እወቅሳቸዋለሁ” የሐርር ፤ የጎንደር፤ የሸዋ፤ የወሎ፤ የወላይታ… እምቡጥ  ወጣት አበቦች - ትግሬን ነፃ ለማውጣት “መቀሌ እንዳየሱስ ተራራ” እና  “ዓድዋ ሰሎዳ ተራራ” ረግፈው ሲቀሩ እንዲያ ነፃ ባወጡት ሕዝብ “ሲዘለፉና ክብራቸው ስደፈር መስማት እጅግ ያመኛል”። ትግራይ ያፈራቻቸው የ28 አመት የወያኔ ፍሬዎች እንዲህ ይመስላሉ። ነጻ አውጪውን ምኒሊክን ሲከስሱ መስማት ይዘገንናል።

እስኪ አንድ ልጨምርላችሁና ልጨርስ፦

 መቀሌ እንዳየሱስ ተራራ ላይ የመሸገው የጣሊያን ሰላቶ በውሃ ጥም ተይዞ እጁ እንዲሰጥ የመጀመሪያው ምክር ለጋሽ የሆነው የፊተውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም ወንድም የሆነው “የሸዋው  አርበኛ ዋጊ ወጣት የአብዩን” ምክር ፡ ደብቆ እንዲህ ያለውን ዘዴ ያመጡት “ራስ አሉላ ናቸው ለጣይቱ አማክሮአቸው ነው ጣሊያኖች በውሃ ጥም እንዲከበቡ ያደረጉት”፡ እያለ በጀሮአቸው የሰሙ የዓይን ምስክር የነበሩ እራሳቸው የጦርነቱ ተካፋይ የነበሩት ሎጋ (ወጣት ዘማች) ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት እያሉ ፈረንጅ የጻፈውን ማስረጃ በማቅረብ አቶ ነበዩ ስሑል ብልሃቱን የፈጠሩት የትግሬው ራስ አሉላ ናቸው እያለ መጽሐፉ ላይ ጽፎ ለታሪክ ማስተላለፍ  ስመለከት፤ የኔ ዘመዶች ብዙ እንደሚቀራቸው ግልጽ ነው።አብዩ ይንን ሓሳብ በማቅረቡ ከራስ መኮንን የስብሰባ ምሽግ ተሰብስቦ ከስብሰባው የጉርስም ጦር ዘማች ዋና አዛዥ በነበሩት በቀኛዝማች በሻህ ቁጣ ከስብሰባው እንዴት እንዲወጣ እንደተደረገ ፊታውራሪ የጻፉትን በሗላ “አብዩ” በዚህ እልክ ወደ ጣሊያን ምሽጉ ገብቶ ተዋግቶ እንዴት እንደሞተ አሳዛኝ ታሪክ በገጽ 61 በወንድማቸው በፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም የተጻፈ “የሕይወቴ ታሪክ” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ  “ወደ ትግራይ ዘመትን” በሚል ንኡስ ምዕራፍ በገጽ 61 ሲያነቡ እንባዎ ይተናነቀዎታል።
                          
                ማጠቃለያ-

    አዲስ አበባን በምጸሐፍ ውስጥ በገጽ 146 “ፍንፍኔ እያለ በመጥራት ለታሪክ ትቶ   የሚያልፈው የኦሮሞዎቹ የመደመር  ፖለቲካ “ነገረ ፈጂ”  ሆኖ የተሾመው ትግራይ የብልጽግና ወኪል “እንደርታዊው ወጣት ነብዩ ስሑል” አብይ አሕመድን ደግፎ አንድ ያደረጋቸው ርዕዮት “የምንሊክ ጥላቻ እና ኦሮሙማ ፖለቲካ እምነታቸው የሚመሳሰል እንደሆነ በግልጽ ማየት የቻላል”። “ሓየሎም” ምናምን እያሉ ምጽዋ ወደብ ሄደው የኢትዮጵን ወታደር የጨፈጨፉና ያስጨፈጨፉ፤ ያዋረዱና ያስገነጠሉ’ የወያኔ ጀኔራሎች/ታጋዮች/ አድናቂዎች ሁላ “ወያኔን እቃወማለሁ እያለ” በዩቱብ ሲንጫጫ ማድመጥ ዛሬም የሚገርም ነው።  ትግራይ ከወ ኔ እስቴች እና ስተሳሰቦች ነፃ ለመውጣት አዲስ አስተሳሰብ ይዞ ለመውጣት አዲስ ትውልድ (ጀኔረሽን) መጠበቅ አለብን። ይህ በሳብቨርሺን የተጠናቀቀ ሳይንሳዊ የሳብቨርዢን ሕግጋት ነው። በመጽሐፌ የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው” በሚለው መጽሐፌ  የጠቀስኩት “ሳብቨርዢን ምንድነው?” በሚለው ርዕስ ውስጥ ይመልከቱ።
       አመሰግናለሁ።  
       ጌታቸው ረዳ  (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)