Wednesday, October 9, 2024

የሁለቱ ቴድሮሶች ቃለ አጋንኖች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ 10/9/24

 

የሁለቱ ቴድሮሶች ቃለ አጋንኖች

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay አዘጋጅ

10/9/24

የእስክንድር ነጋን ቃለ መጠይቅ በስፋት ሳይዘረጋና በብዙ ሚዲያዎች አርካይቭድ (ሳይቀመጥ) አየር ላይ ተንጠልጥሎ ደብዛው የቀረው ኢትዮ 360 ያስተላለፈው ቃለ መጠይቅ ፈልጌ ለማግኘት ጥሬ አስቸጋሪ የሆነበት ምክንያቱን ባላውቀውም ፡ ያገኘሁት ዘግየት ብየ ስለነበር፤ በስንት መከራ አፈላልጌ ፤ አንድ ወዳጄ “ሊንኩን” አጥቶት ይመስለኛል የቀዳውን MP3 አውድዮውን ብቻ በስልክ ላከልኝ እና ለማድመጥና አስቁሞ ለመመለስና ለመጻፍ አስቸጋሪ ነበርና በቴ/ፎን የተላከልኝን እንደምንም አደመጥኩት።

ቃለ መጠይቁ ለማድመጥ ጉጉት ያሳደረብኝ ዋናው መነሻ የቃለ መጠይቁ ነቃፊዎች ትችት ከሰማሁ በኋላ ነው። ቃለ መጠይቁ ያስተላለፈውና ያከናወነው በEthio 360 በእውቁ ትንታጉ ሃያሲ ሃብታሙ አያሌው ነው። ጊዜ ባለመመቸቱ (ይመስለኛል) በይደር ለመተላለፍ ተይዞ የነበረው የታላቁ እስክንድር ነጋ 2ኛው ክፍል ቃለ መጠይቅ የዘመነ ካሴ ደጋፊዎች (እነ ግርማ ካሳ- ብዙ ግርማ ካሳዎች አሉ የትኛው እንደሆነ አላውቅም፤ ግን የሚቀባጥር ጽሑፉውን አንብቤዋለሁ) እንዲሁም ከሁሉም ወገን የለንበትም የሚሉ “ኒውትራል” ነን የሚሉ ሚዲያዎች እንደ እነ ሁለቱ ቴዎድሮሶች ያቀረቡትን የርዕዮት ሚዲያ ተንታኞች ተመልክቻለሁ።

 የእስክንድርን ቃለ መጠይቅ አላስፈላጊ ሲሉት፤ ቴዎድሮስ ፀጋዬ እና አብሮት የሚሰራው ቴዎድሮስ አስፋው ስለ ቃለ መጠይቁን የተቹበትን ከ70 ሺሕ አድማጭ ያደመጠው መርሃ (ፕሮግራም) ላመድመጥ ለሚፈልግ ይህንን

“ፋኖን ልክ እናስገባዋለን” የእስክንድርና ዘመነ ግርሻ የጌታቸው ህወሀት ሰነዶች የሻእቢያ ቁጣ 10/2/24 በሚል ርዕስ የሄዱበትን ትችት አድምጡት።

ለምን አሁን ቀረበ? ለሚሉት ለኔ አስፈላጊ ጥያቄ አላልኩትም። ቃለ መጠይቁ የተከናወነው ምክንያት ብዙዎቹ ከኢትዮ 360 ተከታታዮች እስክንድርን ጠይቁልን ብለው ለየጠየቅዋቸው ተጨምቀው የተጠየቁ ተከታታይ ናቸውና ተቺዎቹ ምን እንዳቁነጠናቸው ባላወቅም ለማንኛውም

በቴዎድሮስ አስፋው ቃለ አጋኖ- እንጀምር፡

 ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ፀጋዬ እንዲህ ይላል

“የአቶ እስክንድር ነጋ መግለጫ አልወደድኩትም” ብሎ ሲጀምር ቴዎድሮስ ፀጋዬ ደግሞ ደስ ብሎት “የተገንጣይ ትግሬ መንጋ ታጣቂ “ተጋዳላይ ትግራይ ቦሎ ነዚ ዓሻ ኣምሐራይ” እያለ እየጨፈረ አማራውን ሲዘርፉና ሴቶች ሲደፍር የነበረው የትግሬ ዱርየ ታጣቂ በፋኖ ተመትቶ ወደ ቦታው በመመለሱ ምክንያት አንጀቱ የተቃጠለው ቴድሮስ ፀጋዬ በወቅቱ እስክንድር ከእስር ሲፈታ ለመጀመሪያ ጊዜ ፋኖዎችን ለማመስገን ወደ አማራ አካባቢ ሄዶ የተናገረው ንግግር  ስላላስደሰተው ከዚያ ወቅት ጀምሮ ቴድሮስ ለእስክንድር ያለው አንጀት ለስላሳ አልነበረምና የቴዎድሮስ አስፋው “የአቶ እስክንድር ነጋ መግለጫ አልወደድኩትም”  የሚለው ንግግሩ ሲጀምር ለቴድሮስ ፀጋዬ የውስጡን አበሰረለት መሰለኝ እሰየው በሚል ድምፅ አልባ ድጋፍ በመስጠት የሚያምሩ ጥርሶቹን ሙሉ በሙሉ ብልጭ በማድረግ በፈገግታ ተባበረው።

ይቀጥልና ቴዎድሮስ አስፋው አንዲህ ይላል

<<ጊዜው አልፎበታል፤አንደኛ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡ በወቅቱ ብዙ የተባለለት ነገር ነው።እንደገና ደግሞ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ የዚያን ወቅት አንጂ አሁን ለምንድ ነው የሚያስፈልገው? እንደውም ስጋት አለኝ “ቴዲ” ይሄ የእስክንድር ንግግር ወይንም መግለጫ ራሱን ሌላ አደጋ ውስጥ ሊጨምረው ሊጥለው ይመስለኛል። ምክንያቱም አሁን አማራ ውስጥ ያለው አጀንዳ ይሄ አይደለማ! እንደውም አንድ መሆን የሚጠበቅበት ወቅት ላይ ትላንት የተለያዩበትን አጅንዳ ዛሬ ላይ አምጥቶ መሞከር ፤ ለዚሁም እሱ እንደሚለው ስሙን የሚያጠፉትን አሁንም ስሜን ለማጥፋት የሚፈልጉ አሉ እያለ ከሆነ ደግሞ “ወጥመድ ውስጥ እንደመግባት ነው” ሊቆጠር የሚችለው። ወቅቱ አይደለም! በጊዜው ተናገር ተብሎ ነበር በዚህ ጉዳይ። እሱ ሌላ እሳቤ ውስጥ ስለበረ አልተናገረም።ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ አማራ ክልል ባለበት አሁናዊ ሁኔታ ይህንን እንዴት እንለፈው ብሎ መመካከር አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ትላንት የተለያዩበትን አጀንዳ ብድግ አድርጎ እገሌ ነበር ጥፋተኛው እኛ ትክክል ነበርን ማለት ….. “ሁሉም ጊዜና ቦታ አለው” እያለ እስክንድር የመጻሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ሁሌም ይጠቅሳል፤ ታዲያ አሁን ወቅቱ ሳይሆን ትርጉም ያጣል።ትርጉም የለውም፤ ትርጉም እንስጠው ከተባለም እውነት ለመናገር እሱን የሚጎዳ ነው።…>> ይላል።

ወደ ቴድሮስ ፀጋዬ ከመሄዴ በፊት በቴድሮስ አስፋው ከላይ የተተቸውን እንመለከት፤-

<<ጊዜ አልፎበታል፤አንደኛ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡ በወቅቱ ብዙ የተባለለት ነገር ነው።እንደገና ደግሞ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ የዚያን ወቅት እንጂ አሁን ለምንድ ነው የሚያስፈልገው?>> ስለሚለው እንመልከት፤

የዚያን ወቅት ያልተላለፈበት ምክንያት ቴድሮስ ጠፍቶት አልመሰለኝም። ቃለ መጠይቁ የሚደረገው በጣም አስቸጋሪ በሆነ የመገናኛ ስልክ ያለመጠለፍ ጥንቃቄና አመቺ ቦታና ወቅት የሚጠይቅ እንደሆነ መገመት ያስፈልጋል። እስክንድር ያለው ጦርነት ውስጥ በረሃ እንጂ ዋሺንግቶን ውስጥ አይደለም።

አደስ ነገር የለውም ለሚለውም ፤ አዎ አዲስ ነገር አለው እንጂ!! እስክንድር በመጀመሪያው ቃለ መጠይቁ የተናገረው ለአንባቢዎቼ ላስታውስ (እስክንድር ያለውን ላስታውሳችሁ)፤ አንዲህ ብሎ ነበር

 “ዋናውና ወሳኙ መሰረታዊ ጥያቄ አለ እሱም በቀጣይ ጊዜ  ለተጠየቅኩት ጥያቄ ጊዜው በፈቀደው በመጠኑም ቢሆን እንዳብራራ እፈልጋለሁ ያንን ዕድል ከሰጣችሁኝ አብራራለሁ …>> ነበር ያለው (በሜታፎሪክ/ሲጠቃለል)።

 ጠያቂው ስለ ምርጫው ሂደትን ጭቅጭቅ በንጥልጥል አቆይቶት የቀረን ቃለ መጠይቅ ዛሬ እንዲያብራራለት ሲጠይቀው (በዚሁ ሁለተኛው ቃለ መጠይቅ ማለት ነው) እስክንድር ያለው እንዲህ ነው፤

“ደረጃ በደረጃ ሙሉውን ስዕል የሚወጣበት ሂደት የሚጠይቅ ስለሆነ ፡ ሙሉውን ስዕል ከጊዜና ቦታ አኳያ ሙሉ ስዕሉን አቀርባለሁ ብየ አልደፍርም ፤ ሆኖም-ግን ጅማሮ ይሆናል ብየ የምለውን ለማስቀመጥ እችላለሁ። እኔ ትቼ ያለፍኩዋቸውን ክፍተቶች ጓዶቼ ይሙለበታል ብየ በሚል ተስፋ ነው እምናገረው ማለት ነው……>> ይላል፡-

በዚያ ምክንያት (አንድ ሰው ለመስማት ፍላጎት የለኝም ካላለ ወይንም ከማቃለል ፍላጎት የተነሳ ካልሆነ በቀር) ድርጅት እንዴት እንደሚመሰረት እና ተበታተነው የፋኖ እንቅስቃሴና ዕድገት ከዚያም የተበታተነው 7 የፋኖን ቡድን አንቅስቃሴ በአንድ ማዕቀፍ (ዕዝ/ ኮማንድ) ለማማጣት 14 ሰዎች ከ7ቱ ፋኖዎች እኩል 2 ሁለት ተወጣጥተው (14) የአንድነት አመቻች ኮሚቴዎች ተደራጅተው ለድርጅቱ እንደ መነሻ ሊሆነን ተብሎ መተዳደሪያ ሰነድ 8 ምዕራፎችና 43 አንቀፆች መፈጠሩንና ሁሉም መስማማታቸውና ማጽደቃቸው እስክንድር ሰምተነውን የማናወቅ ዜና ነግሮናል። እነ ዘመነ ካሴ የዋሹንን ስታስታውሱ <<የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት” የሚለውን ስም ሰምተነውም አይተነውም አናውቅም ሲል የነበረው ከላይ በተጠቀሰው የመተዳደሪያቸው ደምብ የድርጅቱ ስምና አርማ ተጠቅሶ በመሪዎቹ የመጀመሪያ ውሳኔ ሙሉ ድምፅ አልፎ ተስማምተው (በ8 ምዕራፎችና 43 አንቀፆች) ያስቀመጡት እንደሆነ እስክንደር መጥቀሱ ሰምተነው የማናውቀውን ምስጢር ነውና ለጆራችን አዲስ ነው።

ይህ ደግሞ ሲያብራራው

 <<በምዕራፍ 1 እና ምዕራፍ 2 የድርጅቱ ስያሜና መዝሙር እንዲሁም አርማ ምን መሆን እንዳለበት በሙሉ ድምጽ በሚገርም ስምምነትና መደማመጥ መንፈስ እንደፀደቀ…>> እስክንድር በዚሁ ቃለ መጠይቅ ነግሮናል። አዲሰ ነገር የለውም የሚሉን ተቺዎቹ ይህን ለምን አዲስ ነገር አልሆነላቸውም? ይገርማል!!!

 

አፈንጋጩ ቡድን- በወቅቱ በደምፅ መሸነፉን ፍንጭ ሲያገኝ አፍንግጦ የወጣው ሥልጣን አነፍናፊው ያልሰለጠነው የጫካው ጎረምሳ “ዘመነ ካሴ”፡ እና አሽከሮቹ” ባብላጫ ደምፅ  ከግማሽ በላይ ድምጽ ማግኘት እንዳልቻለና መሸነፉን መሸነፉን ሊያውቅ አስመራጩ የዘመነ ካሴ ሎሌ “ማርሸት ፀሃዬ” በመሃሉ አፈንግጦ “ሥልኩን ዘግቶ እንደጠፋ ይፋ መሆኑን እናስታውሳለን። ለዚህ እስክንደር ስለሁኔታው ሲያስታውስ <<ሁላችንም ደነገጥን”>>  ይላል እስክንድር።

በመቀጠል እንዲህ ይላል፦

<<በተደጋጋሚ ሁላችንም ተገናኝተን በሁኔታው ተገርመንና ተደናግጠን ምን ሆነው ይሆን ብለን “ቢደወልላቸው” አርበኛ ዘመነ ካሴና አስመረጩ ስልካቸውን ጭራሽኑ ተዘጋ። ያኔ ወዲያውኑ ትዝ ያለኝ ምርጫ 97 ነበር፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚውን አሽንፋለሁ ብሎ ምርጫ ውስጥ ገብቶ በቆጠራው ጊዜ የሚያመላክተው ነገር ሲመለከት ቆጠራውን አስቁሞ ወደ ኮሮጆ ግልብጣ ገባ። አሁን ደግሞ እዚህ እኛው ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ተደግሞ የምርጫው ሂደት እንዲቋረጥ ተደረገ።

ያኔ ኢሕአዴግ ውጤቱን ተቀብሎ ቢቀመጥ እራሳቸውን ከጥፋት አድነው ፤ሰላም ሆኖ ዛሬ ኢትዮጵያ ሰለማዊ ሽግግር ተደርጎ በፈጣን ምጣኔ ሃብት ውስጥ ትገባ ነበር። አሁንም ወንድሞቻችን ያንን እየደገሙት በማየቴ አዝኛለሁ።>>

 ይላል እስክንድር፤ አጭበርባሪው አስመራጭ ስልኩን ዘግቶ ሲሸሽ ስለ ሂደቱ ሲያብራራ።

ዘመነ ካሴ ያልገባው ነገር ከሰከነና ልምድ ካለው ከምጡቅ ፖለቲከኛ ሰው ጋር መግጠሙ ሳያውቅ ግበቶበት ያላቅሙ ለመገዳደር ሲወራጭ ያልበሰለ ጩጬ ጭቅላነቱን እራሱ ከፍቶ አሳየን። ቆየት ብሎም በሃሳብ የሚቃወሙትንና ለምን እኔን አልመረጥክም ብሎ ሰውን ማፈንና ማስፈራራት፤ ስም ማጠልሸት፤ መዛትና መዝለፍ ጀመረ። እጅግ ኢየሚገርም ዲገላነት ያየንበት አጋጣሚ ነበር።

 የእስክንድርን ሌላው አዲስ ምስጢር የነገርንን አቀልየ   ላቅርብላችሁ’-

  እንዲህ ይላል፤

<<….ሕግ ደምብ ተቀርፆ በጓዳዊ ስምምነት ሰላማዊ ሂደት ተከናውና ለድርጅቱ መሪ ምርጫ ወደ ደምጽ ሲኬድ የነበረው አስገራሚ ሰለማዊ መናበብና የመደማመጥ  መንፈስ ተለወጠ። (ሥልኩን ዘግተው ሲጠፉ) ያም ሆኖ በቀጣይነት የተቋረጠው ምርጫ መቀጠል እሚገባው የነበረ ቢሆንም፤ የተሸነፉት ወንድሞቻችንን ለማስታመም ብለን ከምርህ ውጪ ከሕግ ውጪ ምርቻው እንደ አዲስ እንዲከናወን ፈቅደንላቸዋል።በዚህኛውም ዙር ዳግም ሊሳተፉበት አልፈለጉም (ተሸንፈዋል?)። በዚህኛውም በፈጣሪ ስም፤ በሕዝብና በድርጅቱ ስም ቃል የገቡለትን የማሓላ ኪዳን ረግጠው ወጥተዋል።ለድርጅት ተገዥ መሆን ማለት ለብዙሃኑ ድምፅ ምርጫ ተገዢ መሆን ማለት ነው። እኔ ከዚህ አልፌ እኔ እከሌ ይህ አለ፤ እከሌ ይህን አደረገ እያልኩ ጣት መቀሰር አልፈልግም፤ ትልቁ ነገር የምርጫ ድምጽ መቀበልና መሪም መቀየር ግዴታና መብት ነው። መብት ግን ከግዴታ ተነጥሎ አይቆምም። በዓለም የመሪነት አመራረጥ መሪ ሲመረጥ ሙሉ በሙሉ ድምፅ አግኝቶ የሚደገፍ መሪ የለም፤ ጥያቄው ግን በብዙሃኑ ይደገፋል ወይስ አይደገፍም የሚለው ነው። የምርጫ ሸንፈቱን መቀበል ትልቁ የመሪነት ክሕለት ነው።……..>>

ያለውን ልብ ስትሉ እኔ ካልተመረጥኩ ብሎ አኩርፎ ያፈነገጠው ወጠጤ ቡድንም ደስ እንዲለውና አንድነታችን እንዳይበላሽ ብለን “ምርጫው እንደገና እንዲካሄድ ፈቃደኝነታችን ብንግልጽም፤ ሊቀበሉን አልቻሉም” ያለውን ይህ አዲስ ያልሰማነውና እጅግ የሰለጠነ እጅ የመዘርጋት ሰናይነት ከዚህ ወዲያ ማሳያ የት ይገኛል። ይህ ደም ካላፈሰስኩ ከሚለው የቃሎ አጋኖ ሰዎች አባባል ፍፁም የሚገጥም አይደለም።

እስክንድር የተሰማው ሐዘኔታ ሲገልጽም፡

<<ስሜን ለማጥፋት ብዙ ተሞክሯል፡ ሰው ነኝና ሮቦት አይደለሁምና ሰሜን ሲያጠፉኝና ስሰደብ ይሰማኛል፤ እኔን በአካል ለማጥፋት ሰዎች ተረባርበዋል፤ ቤተሰቤም ባለቤቴም ልጄም ስድብ ደርሶባቸዋል፡ እነሱንም ለትግሉ ሲባል እዚህ ውስጥ መካተታቸው  እንደ ሰው ተሰምቶኛል፤ ባጣም አዝናለሁ።  ባጠቃላይ ቤተሶቼም እኔም ለትግሉ ስንል ዋጋ ከፍለናል። አብረው ከኔ ጋር ከሁለት ዓመት በፊት አርበኛ መከታው ነው ወደ ጫካ ይዞኝ የገባው። እባብ ብቻ የበዘበት እልም ባሉ ጫካዎችና የዓፋር በረሃማ ስፍራዎች አብረውን ፋኖ ከገቡት ከ80ዎቹ ጓዶቻችን 16 መስዋዕት ሆነዋል፤ እነሱን ማስታወስ አለብኝና ትግሉ ላይ በማትኮር ትዕግስትን መርጫለሁ።

ሰዎች በኔ ላይ ያተኮሩበት ምክንያት ግን ይገባኛል። በመሰዳደብ ሰም በማጥፋት ማንም አያተርፍም (ያ ሁሉ ሲፈጸምብን ምንም መልስ አልሰጠሁም)። ከዚያም በላይ ‘ዛሬ የተሳሳተ ነገ በሂደት ይስተካከላል በሚል ተስፋ ስለምናደርግ በዚህ እኛ ሸናፊ ሆነን እንድንኩራራ፤ ሌላኛው ተሸናፊ ሆኖ ሲሸማቀቅ ማየት አንፈልግም፤ የኛ ልባዊ ጉጉት ሁላችንም አሸናፊ ሆነን ስንገኝ ነው።ለዚህም ሁሌም በሩን ክፍት አድርገን እንጠብቃለን።>>

ሲል ያልሰማናቸው አዳዲስ ነገሮች ነግሮናል። እንግዲህ እስክንድር ወዴትና ከማን ጋር ወደ ጫካ እንደገባ ያልተነገረውን ያለወቅነውን ምስጢር ነግሮናል። ለኛ አዲስ ነገር ነው። ዋሾቹ እንደሚሉን እስክንደር ጎጃም ሄዶ ለመወሸቅ ፍልጎ የሚያስጠጋው አጥቶ ምናምን እያሉ ሲዘባርቁ ሰምተን የነበረውን አሁን እውነታው ግልጽ ሆኗል። አሜን! አሜን! አሜን! 

የቴድሮስ አስፋው ቃለ አጋኖ ልጥቃስና ወደ ሌላው ቃለ አጋኖ ልለፍ። ፦

<<ይሄ የእስክንድር ንግግር ወይንም መግለጫ ራሱን ሌላ አደጋ ውስጥ ሊጨምረው ሊጥለው ይመስለኛል። ምክንያቱም አሁን አማራ ውስጥ ያለው አጀንዳ ይሄ አይደለማ! እንደውም አንድ መሆን የሚጠበቅበት ውቅት ላይ ትላንት የተለያዩበትን አጅነዳ ዛሬ ላይ አምጥቶ መሞከር ፤ ለዚሁም እሱ እንደሚለው ስሙን የሚያጠፉትን አሁንም ስሜን ለማጥፋት የሚፈልጉ አሉ እያለ ከሆነ ደግሞ “ወጥመድ ውስጥ እንደመግባት ነው” ሊቆጠር የሚችለው>>

ይላል ቴድሮስ አስፋው በቃለ አጋኖ ምላሱ።

“ራሱን ሌላ አደጋ ውስጥ ሊጨምረው ይችላል” የምትለው ምን  ዓይነት አደጋ ነው ሊጨምረው የሚችለው? ሃቁን በመናገሩ ነው? ከራሱ አልፎ ቤተሰቡ ድረስ ከስድብ ታልፎ የግድያ ዛቻ  (እኔ በጀሮየ ያደመጥኩት ዛቻ ነው) ዛቻ ደርሶበታል አደለም እንዴ? ሌላ ተጨማሪ አደጋና ወጥመድ የምትለው ከዚህ ሌላ ምን ይመጣበታል ወጣት ጋዜጠኛ አቶ ቴድሮስ አስፋው? የትላንት አጀንዳ ለዛሬው ጋሬጣ እየሆነ እንደሆነ እንዴት አንተ አንደ ጋዜጠኛ ይህን ማወቅ ተሳነህ?

ለመሆኑ የዛሬ አጀንዳ እኮ እስክንድር በሚገባ ወቅታዊ አጀንዳ ምን መሆን እንዳለበት  ስላወቀ ፦ “የጎጃሙ ዲገላ” የመጓጓዣ እንቅስቃሴ በመላ አማራ እንዲቆም ሲያውጅ እስክንድርና ጓዶቹ ድጋፍ በመስጠት የትብብር አዋጅ ሲያወጡ “የጎጃሙ ዲገላ” ስለ መልካሙ ትብብራችሁ እናመሰግናለን ወይንም እናደንቃለን ብሎ መልስ እንዳልሰጠ አንተ ታውቃለህ (ዘመነ መልስ ባለመስጠቱ ተችተህበታልም- ለዚያ ምስጋና ይድረስህ)።

ከዚህ አልፎ ፤ አሁንም በዚህ ቃለ መጠይቁ ለሰላምና ለውይይት በሩን ከፍተን ዛሬም እየጠበቅናቸው ነው፤ በራችን ክፍት ነው ብሎ ተናግራል። የወቅቱ አጀንዳ ከዚህ ወዲያ ምን ይኖር ይሆን? ጠላትን ስለመዋጋት ከሆነም የወቅቱ አጀንዳ የእስክንድር የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሚሊየነም አደራሽ ገብቶ እስክስታ እየጨፈረ ሳይሆን ከጠላት ጋር ጎሮሮ ለጉሮረ እየተናነቀ እየተዋደቀ ነው፡ ጫካ ውስጥ ነው ያለው። በራችን ክፍት ነው እንተባበር ብሎ ጥሪ አቅርቦ መልስ ያላገኘ የወቅቱ ጥሪ ከዚህ ሌላ ምን አጀንዳ አለ? እስኪ ንገረኝ አቶ ቴዎድሮስ አስፋው!

በመጨረሻም ወደ ሌላው ቃለ አጋኖ ወደ ቴዎድሮስ ፀጋየ ባጭሩ  ልተችና ልጨርስ፡

ቴድሮስ ፀጋዬ እንዲህ ይላል ስለ እስክንድር 2ኛው ቃለ መጠይቅ አስመልክቶ ሲተች፡

<< እሰክንድር ጋር የማየው ሃይለኛ የኢንታይትልመንት ነገር ነው (ቴድሮስ የተጠቀመበት አንግሊዝኛው ሹመቱ/ሥልጣኑ የኔ ነው የሚለው ነው፤ አምባ ገነን ነው ማለቱ ነው) ።

  ቴድሮስ ፀጋዬ በመቀጠል፤

<< (እስክንድር) ምን ይላል፤_ በፋኖ መዋቅር በዲሞክራሲ የመጣውን ውጤት ለመጠበቅ ትግል ማድረግ አለብኝ። ትግሉን “ዲፋይን” ሲያደረገው ከውስጥና ከውጭ ካሉት ሃይላት ጋር ነው። ሁለቱም የሕልውና ትግሎች ናቸው፤ በእሰክንድር ብየና መሰረት በአማራ ውስጥ ከእርሱ ጋር አብረው ያልሰሩ አባላት የብልጽግና ያህል ጠላት ናቸው፡ የሚል ድምዳሜ ደርሷል። እንዴ!!! በመጀመሪያ ደረጃ በዲሞክራሲ ዉጤት የተገኘ ውጤትና መዋቅር እንከላከላለን ማለት ‘ስልጣኔን በማንኛውንም ዋጋ (at any cost) እከላከላለሁ ማለት ነው። እንዴ! ምንድነው ይሄ? እንኳን በፋኖ መዋቅር ኮንቴስትድ በሆነ ቻለንጅ በበዛበት ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው የፋኖ አመራር አባላት ያልተቀበሉት ሂደት ነው፤ የተቀበሉት አሉ ያልተቀበሉት አሉ። ሲጀመር የሕዝብ ምርጫስ ቢሆን ይህን ያህል <<ደም ካላፈሰስኩኝ> ማለት አለ እንዴ!?! አንድ በሕዝብ ምርጫ የተመረጠ መንግሥት ቢኖር ሃይለኛ የሕዝብ ተቃውሞ ቢደርስበት ምርጫን ካላከበራችሁ “እፍጃችሗለሁ ሊል ነው እንዴ?”>>

 እያለ የቃለ አጋኖው ሊቅ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ታላቁን እስክንድር ነጋን የጨፍጫፊ ባሕሪና ፍላጎት እንዳለው በተካነበት የቃሎ አጋኖ ስለት ሊስለው ሞክሯል።

እስከንድር ያለው ካለማድመጥ የዘለልኩት ነገር ከሌላ በቀር

<<የወስጥና የውጭ ሴራዎች አሉ፤ እነሱም መበጣጠስ ያስፈልጋል>> <<የሕልውናው ትግል ከውስጥም ከውጭም ነው>> ብሏል እስክንድር።   የፋኖ ትግል ጠላትና ወዳጅ ስላለ የሕልውናው ትግል ህያው እንዲሆን በውጭም ትግሉ ከመሳሪያ መለስ ያለው ትግል ሁሉ ስለ የአምሐራው ሕልውና ትግል ሲቀጣጠል ያንን ለማክሸፍ በውስጥም በውጭም ሰርገው ገብተው ትግሉን ለማኮላሽት የተሰለፉ ሃይላት እንደሚኖሩ የሽምቅ ተዋጊ ታሪኮች ይመሰክራሉ።

ውጫዊ ስንል  ባሕር ማዶ ማለት ከሆነም አይሁዶች ከናዚ ጭፍጫፋ ወዲህ ስለ ሕልውናቸው ሲሉ በውጭም በውስጥም ስላደረጉት ትግል ለስኬት ዳርጓቸዋል። ከምድረ ገጽና ከምድረ ኢትዮጵያ ሰንደቃላማው ፤ቋንቋው፤ ትውልዱ እንዲጠፋ በተለያዩ መጥፊያ መንገዶች የታወጀበት አምሐራ ማሕበረሰብ በውጭም በውስጥም ትግል ማድረጉ ተገቢና መደረግም ያለበት የሕልውናው ዋነው ክፍል ነው።

ለሕልውናው ሲል አደለም ቲ ዲ ኤፍ የተባለው አማራ ጠሊታ ጋጠወጥ ታጣቂን ውጭ አገር ሆኖ ሲደግፍ የነበረው? አምሐራ ጋር ሲደርስ ለምን አይሆንም?

 ቃለ አጋኖው ሲቀጥል፡-

<<ሲጀመር የሕዝብ ምርጫስ ቢሆን ይህን ያህል <<ደም ካላፈሰስኩኝ> ማለት አለ እንዴ!!? አንድ በሕዝብ ምርጫ የተመረጠ መንግሥት ቢኖር ሃይለኛ የሕዝብ ተቃውሞ ቢደርስበት ምርጫን ካላከበራችሁ “እፍጃችሗለሁ ሊል ነው እንዴ?”>> የሚለው “ደም ካላፈሰስኩ” “እፈጃችኋለሁ” ቴዎድሮስ ፀጋዬ ያለበትን ቃል አገኝቶት ነው ምኑን ከምኑ ጋር ሊያገናኝ የከጀለው?

“ናበይ ኢሂ?” (ወዴት ነሽ?) አለ ትግሬ ይሉናል አምሐራዎች አንዲህ ነገር ሰገጥማቸው።

ሰላም ለሁላችሁ!

ጌታቸው ረዳ