Sunday, August 25, 2024

ለወረቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በእጄ ልጨብጣቸው አልፈልግም! ሞት የነጠቀን ትንታጉ የሕግ ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ) 8/25/24

 

ለወቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በእጄ ልጨብጣቸው አልፈልግም!

ሞት የነጠቀን ትንታጉ የሕግ ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ

ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ)

8/25/24

ደረጀ ዘለቀ (ዶ/ር) ምክንያቱ ባልተገለተጸ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መሰናበቱ ስሰማ እጅግ አዘንኩ።

ዶክተር ደረጀ ሲያቀርባቸው የነበሩ አንዳንድ ሃሳቦቹ ስላልተስማሙኝ ሁለት ወይንም ሦስት ጊዜ የተቸሁት መሰለኝ። አንዳንዴም ያንዳንድ ሰዎች ንግግሮች በማጣመም ያላሉትን አሉ የሚላቸው ለምሳሌ አንድ ካሕን “ እነኚህ ሰዎች “ወያኔ” ከሚገዙኝ ሰይጣን ቢገዛኝ ይሻለኛል” ያሉትን ንግግራቸው “የትግራይ ሕዝብ ከሚገዛኝ ሰይጣን ቢገዛኝ ይሻለኛል” ብሏል በማለት ሲተረጉማቸው የነበሩትን እና የመሳሰሉት አይጥሙኝም ነበር። ያም ሆኖ ከነ አንዳንድ ድክመቶቹ እንዲያ የመሰለ ብሩህ ምጡቅና ሞጋች ኢትዮጵያ ማጣትዋ ከባድ ጉዳት ነው።

የዶ/ር ደረጀ እና የአቶ አሰፋ ጫቦ ሕልፈት ሳስበው አንጀት ይበላል።የዶ/ር ደረጀ ድክመቶቹ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ቃላቶቹ ሳስባቸው አይበገሬነቱ ማሳየት የሚችል ብቃት ያለው የሚሞግታቸው ግለሰቦችና ድርጅተቶችን አንደበት የሚዘጋ  የሚያርበደብድባቸው የንግግር አንደበቱ ከውስጤ ስወድለት ነበር።

ይሉኛል የማይል አንደበተ ርቱዕ፤ የተሰማውን የሚዘረገፍ ግሳንግስ ምሁራኖችንና “የአማራ ናሺናሊስቶች የሚላቸውን በደም በአጥንት ጉልጥምጥሚት እየተበጠረ ብቻ አማራ ይሰለፍ እያሉ (ዛሬ እንደምናያቸው ዘመነ ካሴ እራሱ እና እዚህ ውጭ አገር የሚኖሩ የዘመነ ካሴ የሁሉም አማራ የድሮ ብአዴን ተዋጊና ካድሬ የነበረው የኖርዲኮች ጥራት ዓይነት የሚሰብክ አጥንት ሲሸነሽን ማን አማራ ማን ትግሬ እንደሆነ ሲቆጥር የሚውል የእስክንድር ባለቤት “ትግሬ ነች እያለ ዘር ሲቆጥር በየሚዲያው የምንሰማው “ሳሙኤል አበራ (“ሳሚ” ይሉታል በቁልምጫ ሲጠሩት)” ፤ እንዲሁም አኪላ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው “ኤልያስ” የተባለ የ “ዋን አማራ” የኢንተርኔት ድርጀት መሪ እና ወጣት ፋሺሰት የመሳሰሉትን ጠባቦችን ዶ/ር ደረጀ “ባለ ሁለት እግር አሳማዎች” እና “ገጣጣ ዘረኞች” ይላቸዋል። እኔ እንደምጠየፋቸው ሁሉ እርሱም ይንቃቸዋል።

ስለሚሰነዝራቸው ቃላቶችና ንግግሮች ሁሉ በሙሉ ሐላፊነት የሚወስድ ደፋር፤እጅግ መራራ ተናጋሪ በመሆኑ አድማጮቹን እንዲህ ይገልጻቸዋል፡

“ የሰው ሙገሳ አይሞቀኝም፤ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ውግዝ ከመአርዮስ ቢለም I don’t give a dumb!!” ግድ አይሰጠኝም” ሲል የሚሰማውን በገሩ የሚቆጭ ሳይሆን በሙሉ ልቦና የሚደሰት አስገራሚ ልዩ ኢትዮጵያዊ ነበር።

ከላይ የገለጸው አነጋገር ዶ/ር ደረጀ እኔን ወክሎ የተናገረልኝ መስሎ ይሰማኝ ነበር። እኔና ደረጀ ተመሳሳይ ባሕሪ ያለን ይመስለኛል። ሰዎች ይሉኛል ሳይል የተሰማውን ያፈነዳዋል፡ በራሱ ቃላት “mushroom cloud” ይለዋል (“የፍንዳታ ቁልል” ይመስለኛል በአማርኛ ስተረጉመው)።

ትንታጉ ሊቀሊቃውንቱ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ “የአማራ ናሺናሊሰቶችን” ብቻ ሳይሆን፤ የኦሮማ ናሺናሊሰቶችን ኢሕአፓዎችን አሁን ያለው የኦሮሙማው ሕጻን የሚመራው መንግሥት ኦሆዴዱ አብይ አሕመድን በፖለቲካ የጉማሬ ኮርማጅ እስኪበቃቸው ድረስ ይለበልባቸዋል። እነዚህ መርገምቶች እና Idiotic ብሎ ከሚጠራቸው ይልቅ ደርግ የሰራው መጥፎ ነገሩ እንዳለ ሆኖ በጎ ጥረቱን ያደንቃል። ለትግራይ ሕዝብ ያለው ሙገሳ፤ ፍቅር እና ከበሬታ ከፍተኛ ሲሆን፤ አክሎ የሚከተለውን ምክር ይለግሳቸዋል፡

“የማከብውን ቅዱስ የሆነው ከዚያች ቅድስት መሬት የተፈጠረው የትግራይ ሕዝብ ልው ምፈልገው “እንደ ወያኔ ያለ ከማሕጸናቸው ድጋሚ እንዳይወለድብን ብለው መጸለይ አለባቸው” ሲል ሃሳቡን ያጋራል። የወያኔ ፈለግ ተከትለው እንደ አዲስ የተወለዱ ወያኔዎች (እኔ “የወያኔ ዕንቁላሎች” የምላቸውን እነ ባይቶና፤ ሳልሳይ ወያኔ ወዘተ…የሚባሉትን እዚህ ግቡ ያማይባሉ “የወያኔ ስባሪዎች” ይላቸዋል።

መርገምቶች እና Idiotic ኮች እንዲሁም “ባለ ሁለት እግር አሳማዎች” እና “ገጣጣ ዘረኞች” ፤ለወቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በዚህ በኢትየጵያዊው ገናናው የሕግ መምሕር ሞት ሲደሰቱ ለኛ ግን መራራ ሐዘን ነው።

ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ጽናቱን ይስጣችሁ እያልኩ፡ነብስሕን አምላክ በገነት ያኑረልን።

ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ)