የፋኖዎቹ ትግል “በፕሮቪንስያሊስቶች” ተጠልፎ ወድቋል!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 12/22/24
እስክንድር ላይ የግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻው ተጧጥፏል። ትግሉ የመጠለፉን (ሃይጃክድ የመደረጉ) ምልክት ነው። ትግሉ “በፕሮቪንሺያሊስቶች” እየተመራ ነው። በተለምዶ አውራጃዊነት ወይንም በእንግሊዝኛው ቃል “ፕሮቪንሺያሊዝም” (Provincialism) አሁን ወሎ ጎጃምና ጎንደር ክ/ሃገር ውስጥ በአምሐራነት መሪነት ሳይሆን <<በአውራጃ ልጆች መሪነት>> የሚቀኝ (በጫካም በውጭ አገርም) እየታየ ያለው የትግል መርህ ነው።
ቃሉ ለሀገራዊ ወይም ለሀገራዊ አንድነት ኪሳራ የቆመ ለራስ አካባቢ መሪዎች ወይም “ክልል” የመቆርቆር አባዜ የተጠናወተው ማለት ነው። በተለይ ይህ በወሎ ጎንደርና በጎጃም ፋኖ ውስጥ እየታየ ያለው “የአውራጃ ልጆችነት በሽታ” የሚታየው በፋሺስት ቡድኖች የሚታይ ባሕሪ ነው። ይህ ባሕሪ ለትግሉም ለሀገርም ከፍተኛ አደጋ አለው። ያው ያየነው የ27+5 አመት የዜሮ ድምር ክስተት አዙሪት ነው።
በዚህ ትንታኔ ወሎ ጎጃምና ጎንደር አውራጃዎች ሲጠቀሱ፤ መልካምና ቅን እሳቤ ያላቸው ከጠባብ “አውራጃ ልጅነት” ነጻ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የወሎ ፤ የጎጃምና የጎንደር ፋኖ (አንዳንድ) መሪዎችና ደጋፊዎቻቸውን አይመለከትም።
የዚህ ብዕር ባውዛ የሚያበራው በዘመነ ካሴና በወሎ “ምሬ ወዳጆ” በተባለ (ማይሙ) እንዲሁም ጎንደር ውስጥ ባሉት አንዳንድ የፋኖ መሪዎች እና እንዲሁም ትግራይ ጠልና እስላም ጠል የፋኖ መሪዎችን እና ደጋፊዎቻቸውን ላይ ነው።
የዚህ ቡድን አደገኛነት ነገሩ የቆየ ነው። ዜጎችን ፤ ሽማግሌንና እናቶችን አፍኖ እምብርክ እስከ ማስኬድ ከማሰር፤ ከማሸበርና ከመሰወር እስከ መገድል ጀምሮ የቆየ ትግሉን የጀመረበት ባሕሪ ነው። ዛሬ እስክንድር ነጋ ላይ የመግደል ዛቻ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ዛቻው የቆየ ቢሆንም።
“የአውራጃ ልጆች አንድነት“ (በሩዋንዳዊያን Kinyarwanda ተብሎ በሚጠራው ሀገራዊ ቋንቋ “ኢንተርሃሙዌ” የሚባለው ፤ለአንድ የጥፋት ግብና አብሮነት በጋራ ተቀናጅቶ የሠራ መዋቅር አሁን በወሎ፤ በጎጃም እና በጎንደር ፋኖ በእስክንድር ላይ የግድያና የሥም ማጠልሸት ዘመቻ እየተካሄደ ያለው አጀማማር ሩዋንዳ ውስጥ “ኢንተርሃሙዌ” የተባለው ቅንጅት ሲጀምር ያሳየው አጀማማር ይመስላል።
እስክንድርን እስከ መግደል የዛተው የዛቻው ጀማሪው የጎጃም አውራጃ ልጆች ነፃ አውጪ ዘመነ ካሴ የተባለ ካፍንጫው ርቆ ማሰብ የማይችል መንደርተኛ የጎበዝ አለቃ ነው። ከዚያ ተከትሎ የራሱ አሽከሮችና የጎጃምና የጎንደር እንዲሁም የወሎ አውራጃ ልጆች ቃሉን በመከተል ይኼው እስክንድር ላይ የማያባራ የግድያና የሥም ማጠልሸት ዛቻ እያካሄዱበት ነው። ለዚህ ክፉ ሥራ የተመደቡም አሉ። አንዳንድ ሰዎች እነዚህን <<የአውራጃ ልጆች>> “የብአዴን ልጆች” ይልዋቸዋል።
የሚገርመው ደግሞ የፋኖ ትግል አስቀድሞ ሁሉም እንደገመተው አምሐራን ነፃ ያወጣሉ የተባለው ግምት ተኮላሽቶ አምሐራን ነፃ ለማውጣት ሳይሆን የገዛ ወገናቸ አምሐራ የሆነው ኢትዮጵያዊው እስክንድርና ብዙ አምሐራዎችን በመግደልና ለመግደል በመዛበት አሁን እያየነው ያለው የጫካው ትግል “በፕሮቪንስያሊስቶች” ተጠልፎ የመውደቁ ክስተት ስናይ ከመገረም ያለፈ ተግርመናል።
አሁን በሦስቱ ፕሮቪንስያሊስቶች ፤ (የአውራጃ ልጆች) በኢትዮጵያዊው እስክነድር ነጋ ላይ የዛቱትና እየደረጉት ያሉት ሴራ ስንመለከት ካሁን በፊት ከገጠሙት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት በከፋ መልኩ በግድያ ቀለበት ገብቶ እንዲጠፋ በየሚዲያው ሲያውጁ መስማት የትጥቅ ትግል በሚያካሂዱት ፕሮቪንስያሊስቶች ላይ ከፍተኛ የምርምር ጥናት ማካሔድ ያስፈልጋል። ባሮ ቱምሳ የተባለው የኦነግ መሪ በኦነጎቹ (ባጃራ) የመገደሉ ዕጣ ፈንታ ስናይ እስክንድር ላይ ይህንን እንዳይከሰት ያሰጋል
ብዙዎቹ የወሎ የጎንደርና የጎጃም ፋኖ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው እስክንድር ላይ እስከ ግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻ የሄዱበት ምክንያት በደምብ መፈተሽ የሚኖርበት ነው። በተለይም በጎንደርና በጎጃም ፋኖ ኢንተርሃሙዌው መዋቅር።
ስለሆነም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ይህ “የአውራጃ ልጆች” አደገኛ በሕሪ በቸልተኝነት ከተተወ ለእስክንድር ብቻ ሳይሆን አደጋው ለሀገራችን ኢትዮጵያም (ለአምሐራው በዋናነት) ጭምር ነውና መመከት አለብን።
ትግራይ ውስጥ ወያኔ የጀመረው የእርስበርስ “የአውራጃ ልጆች ዘመቻና ጥፋት” ታስታውሳላችሁ፤ አሁን ያ ግርሻ ከስንት አመት በሗላ ትግራይ ውስጥ በሰብዓ እንደርታ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ። ይህ በአውራጃ ልጆች መቀናጀት ሰበብ በሚፈለጉት ላይ ‘ገዳይና ሥም አጥፊ’ “የኢንትርሀሙዌ ቡድን በማዋቀር” ብዙ ቀና ሰዎች ተገድለው ጠፍተዋል። እዚህ ፋኖ ላይም ችግኙ አቆጥቁጦ ያለው ያንኑ ነው።
በየሚዲያው የምታዘባቸው ብዙዎቹ ምሁራን ከጎንደር፤ ከወሎና ከጎጃም የተገኙ “የአውራጃ ልጆች” በሚያስፈራ ፍጥነት ጠባብ ጎሰኞች ሆነው አይቻቸዋለሁ። አንዳንዶቹ እስከ 7 ትውልድ ያልተደባለቀ የአምሐራ ትውልድ ያለው “የጠራ ደም” ያላቸው መሪዎች ፋኖን መምራት እንዳለባቸው የሚሰብኩ “የናዚ አቀንቃኞች” አሉዋቸው።
እነዚህ በኢትዮጵያዊያን በተለይ ቀና በሚባሉ አምሐራ ምሁራን እነዚህን የናዚ አቀንቃኞች ከኦነግም ከወያነ ትግራይም ተለይተው አይታዩምና ዘመቻቸው እንደዋዛ መታየት የለበትም። ጀርመን የጀመረው የደም ጥራትና ያስከተለው ጥፋት ይህ መፈክር ነው።
ይህንን እስክንድር ላይ እየሰማን ያለነው የግድያም፤ እስክንድር አምሐራ አይደለም እና <<ትግሬዋ ባለቤቱ እስክንድር ነጋ ከሕዝብ የሰበሰበው ገንዘብ እየኖረችበት ነው>> የሚል <<የሲፍረዘኒኩ ዘመድኩን በቀለ>> የሥም ማጥፋት ዘመቻ (ወንጀል) ይህ ወንጀል በመረጃ ቲቪ ተላልፎ ከሆነ ጣቢያው ስም በማጥፋት መከሰስ ነበረበት) እና የነ ዘመነ ካሴ ደጋፊዎች እነ “አቶ ተክሌ የሻው” የመሰሉ <<የደም ጥራት አደገኛ ሰባኪዎች>> ለአውራጃ ልጆች ኢንተርሃሙውዌው ቡድን ጭንቅላት ቀራጺዎች ናቸውና መልዕክታቸው መጠናት አለበት ።
ትናንት አንድ ወዳጄ ሥልክ ደውሎ “ትንግርቱ” የተባለው እስክንድርን ሲቃወም ሰምቼው ገረመኝ እንዴት ታየዋለሁ ብሎ ጠየቀኝ።
እኔም እንዲህ አልኩት ፤ ምን እንዳለ ባልሰማውም “ረ/ፕሮፌሰር ተበየው” ትንግርቱ ገ/ጻድቅ እንኳን ባንድ ግለሰብ እስክንድር ነጋ ቀርቶ <<የትግራይ ሕዝብ ጠፍቶ እንደገና መሠራት>> እንዳለበት የሰበከ ወጣት ፋሺሰት ስለሆነ ልጁ በግለሰብ ላይ መዝመቱ አያስገርምም አልኩት።
ረዳት ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገ/ጻዲቅ ለአምሐራ ሕዝብ የሰበከው ሰበካ፦
<<ሺሕ አመት አስበህ ይህንን ትውልድ (የትግራይ ሕዝብ) ኒውትረላይዝድ (ካላጠፋህ/ካላሟሟኸው) ካለደረግኸው ፤ ትግራይ የሚለው መጠርያ እራሱ “ወንጀል” ማለት ስለሆነ ቃሉ በሕግ ታግዶ መጥፋት አለበት። ትግራይ የሚለው ቃል ይህንን ስም ይዘን እያሽሞነሞንን የምንቀጥልበት ሁኔታ መኖር የለበትም። ትግራይ የሚባለው ክልል ወደ አራት አምስት ክልል ከፋፍሎ ይህንን ትግራይ የሚባል የወንጀል ስምና አካባቢ መከፋፈልና በቋሚነት ከነስያሜው “ሪ-ቪዚት” (መከለስ) አለበት እላለሁ።>>
የሚል የናዚና የፋሺስቶች መርሃ ትምሕርት ያሰከረው የዘመነ ካሴ ደጋፊ <<የኢንተርሃሙዌው ቡድን አባል ነው>>። ሰለዚህም ረ/ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገ/ፃድቅ በእስክንድር ነጋ ላይ መዝመቱ አትገረም፤ አልኩት። ወዳጄም፤ ይህንን ስነግረው አልሰማሁትም ነበር አለኝ። ቪዲዮውም ላኩለት። አየውና ደውሎ “ደነገጥኩኝ” አለኝ።
የፋኖ ትግል በኢንተርሃሙዌው<<የአውራጃ ልጆች>> ከተጠለፈ ቆይቷል የምልበትም ከላይ በስም የተጠቀሱት ታዋቂ ሰዎች እና እንደ ትንግርቱ ያሉ በጣም ዘረኞች የሆኑ ሰዎች የተካተቱበት የዘመነ ካሴ ደጋፊዎች በሚያራግቡት አደፍራሽ “መናፍህ” ምክንያት ነው።
ፋኖን በሚመለከት የኔን ጽሑፍ ስትከታተሉ የነበራችሁ ተከታታዮቼ እንደምታስታውሱት የፋኖ ትግል ከተጠለፈ ቆይቷል ነበር ያልኩት (ገና ሲጀመር ዘመነ ካሴ ጠልፎ አኮላሽቶታል)።
እንደምታውቁት አውራጃዊነት ትግራይ ውስጥ ስር የሰደደ አደገኛ መልሕቅ ነበር። አሁን ፋኖ ውስጥ ጎንደር፤ ጎጃምና ወሎ ላይ ተንሰራፍቷል። ይህ ፕሮቪንስሊዝም ርዕዮት እየተከተለ ያለው ቡድን እጅግ በጣም በታጠረ እይታ ውስጥ እየዳከረ የራሴ የሚለው “ክልል” “አውራጃ” “ክፍለ-ሃገርና ከዚያ አውራጃ የተወለዱ መሪዎችን” ባጠቃላይ ተወልጄበታለሁ በሚለው የማሕበረሰብ ማንነትን ከጫፍ ከፍታ ላይ በመስቀል የኔ የማይላቸውን ቁልቁል የሚመለከት የራሱን ማሕበረሰብ በደረቱ ላይ ለጥፎ ፍቅሩን እና ፍቺውን ለራሱና ላካባቢው የሚያጎላ፣ ብዙ ጊዜ ወደ አግላይ ድርጊቶች በማትኮር፣ ግጭት በመጥመቅ ላይ ነው። በእውነቱ ይህንን ወቀሳ ሳቀርብ ጠላት እንዳይመቸውም እየቀፈፈኝ ነው። ሆኖም መገለጽ ያለበት ጉዳይ ነው።
ይህ በአውራጃ ተወላጆች መሪዎች እምነት ጥሎ እስከ ወዲያኛው የመመራት ፍላጎትና መሪዎቹን የማጉላት ክስተት ከፍተኛ ችግር አለበት። ችግሩም “እኛ እና እሱ” በሚል አግላይ መርሆ እስክንድር ላይ ግልጽ የግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻ በመካሄድ ትግሉ እንዲቃጠል አድርገውታል። ባጭሩ ትግሉ ጥናት የሚያስፈልገው ባልታወቀ ብክለት ተበክሏል። አውራጃዊ መሪ ለአምሐራ ችግር መፍቻ አድርጎ የሚጓዝ የሽምቅ ነፃ አውጪ የፖለቲካ ምጥቀት ያጠረው የብቃት ቁርቆዛ ነው።
አውነት ነው፡ “ፕሮቪንስቶቹ” ስካር ውስጥ ናቸው። የጎሪላ የሽምቅ ተዋጊ ሕግና ጥንቃቄ አይከተሉም። በዘፈቀደ እየተጓዘ ወታደር ሲማርኩ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው ባንዴ ይሰክራሉ። ይህ ደግሞ አደጋ አለው። ከውስጥ አንድነትን የሚሸረሽር የግድያና የስም ማጥፋት ዘመቻ እያጧጧፉ በወታደራዊ ድል መስከር ረዢሙን ጉዞ ባጭር ማስቀረት ነው። በሽምቅ ተዋጊዎች ሕግ በጊዜዊ ድል የሚሰክር ቡድን ሕጻን እና የኳስ ጨዋታ ደጋፊ ብቻ ነው። ድል ሲያገኝ ይቦርቃል ሳይታሰብ ግብ ሲገባበት የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ይጨልምበታል። በኒዚህ የአውራጃ ልጆች እያየን ያለው ይህንኑ ችኮላ ነው። እስክንድርን መተናኮል ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም በሗላ ትግሉን እጅግ ዋጋ ያስከፍለዋል። እመኑኝ ፖለቲካው ውስጥ ቆይቻለሁ።
እስክንድር ላይ እየወረደበት ያለው የግድያ ዛቻ፤ ጥላቻና የሥም የማጠልሸት ዘመቻ በትግል ዕድሜየ ውስጥ ያላየሁት እጅግ አሳፋሪ ዕብደት እያየሁ ነው። ታላቁ እስክንድር በኦሮሙማው መንግሥት እና ወገኖቼ ብሎ ባመናቸው የመንገሥ ሕልሜ “በ ዲ ኤን ኤ” የተላለፈልኝ የነጋሽና የአንጋሽ ዘር ልጅ ነኝ’’ የሚሉ እንደ ዘመነ ካሴ” ዓይነቱ <<የፋሺሰት ክሊክ>> ግሰለቦችና ደጋፊዎቹ በኩል የግድያ ዛቻ የተሰነዘረበት አጅግ አሳዛኝ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ማየቴ እስክንድርን ሳይ በምስጋና ቢስ ሕዝቦች የተገለሉ ያጎረሳቸውና የታገለላቸው እጅ በሚነክሱ ሰዎች የተገለሉና የተገደሉ የብዙ የዓለምና የአፍሪካ ነፃ አውጪ መሪዎች ታሪክ ያስታውሰኛል።
እስክንደር 10 ጊዜ ሲታሰር ሲደበደብና ሲፈታ “ለዝናውና ለስለላ አለመሆኑን መፈተሽ አለበት” እያለ የሚለፍልፍ “የጀርመኑ ሲፍሮዘኒክ (ዘመድኩን በቀለ) ሰምቼው የፋኖ ችግር በነዚህ ዓይነቱ ሰዎች መዳፍ ውስጥ መውደቁ” ያሰዝናል።
እስክንድርን መተናኮል ትግሉን እጅግ ዋጋ ያስከፍለዋል የምልበት ምክንያት አንዱ ትግሉ “በፕሮቪንስያሊስቶች” <<ሃይጃክድ>> ሆኖ መጠለፉ ነው። በዚያው ላይ የማይሙ ብዛትና አጃቢ የት የሌለ ነው።
ሰላሙን ለናንተ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay