Friday, January 24, 2014

የግርማይ ገብሩ ‘መቐለ’ እና ‘መቀሌ’ ቡሩ ሃ!….ሃ! ጩኸት (ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)የግርማይ ገብሩ ‘መቐለ’ እና ‘መቀሌ’ ቡሩ ሃ!….ሃ! ጩኸት
ጌታቸው ረዳ  (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (ጥር 2006 ዓ.ም)
Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)
በቅርቡ የኢትዮጵያ መርከብ ድርጅት ብሎ  ራሱን የሰየመ ወያኔዎች የሚያዙት ድርጅት ለትግራይ ክ/ሃገር ጠቀሜታ የሚውል ብሎ አዲስ በተረከበው መርከብ ላይመቀሌብሎ መፃፉ የትግሬዎች የማንንት ጥያቄ የሚጻረር ስለሆነ ‘መቀሌ’ የሚለው የአማራዎች አጠራር/አጻጻፍ ወደ ‘መቐለ’ መለወጥ አለበት በማለት ሁለት የታወቁ የትግራይ ጠባብ ብሔረተኞች ማለትም ግርማይ ገብሩ (ትግራይ/መቀሌ ውስጥ መሰረቱ ያደረገ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የትግርኛ ቃል አቀባይ) እና በጸረ አማራ እና በጸረ ምንሊክ የታወቀው ጐጠኛው መምህር ገብረኪዳን ደስታ የተቃውሞ ፌርማ በማሰባሰብ አዲስ ጩኸት በማስተጋባት ላይ አንደሆኑ አብርሃ ደስታ የተባለ ወጣት በፌስ ቡኩ ገልጾልናል (በነገራችን ላይ አንዳንድ የአብርሃ ደስታ ፖለቲካዎች ባይስማሙኝም በዚህ ጉዳይ ግን አብርሃ ደስታ በሚያስመሰግን ሁኔታ እነኚህ ሁለት ጐጠኞችና ወያኔ አወዳሾችን አግባብነት አንደሌለው ተቃውሞአቸዋል)፡፡ለዚህም በመቐለና መቀሌ ስሞች የትርጉም ልዩነት የለም  በማለት አብርሃ ደስታ ተቃውሞውን ገልጿል።

አብርሃ ልክ ነው። በመሰረቱ መቐለ ትግርኛ አጠራር ቢሆንም ‘መቀሌ’ የሚለው አጻጻፍ ደግሞ አማርኛ ነው። መርከቧ የትግራይ ብትሆንም ንብረትነትዋ መንግስታዊ እና መሰረት የጣለችውም ባዕድ አገር ‘ጅቡቲ’ ውስጥ ከሆነ የመንግሥት ንብረቶች ሁሉ በላያቸው ላይ በብሔራዊ ቋንቋ የአጠቃቀም ዘይቤ ቢጻፉባቸው ምንም ስህተትነት የለውም። ነገር ግን “መንግሥት ማለት ሁሉንም በጁ ሁሉም በደጁ ባለቤቱ ወያኔ አይደለም ወይ ባትሉኝ ማለቴ ነው።
የገብረኪዳን ደስታ መፍትሄ ብሎ የሰጠው አስቂኝ መፍትሄ ላስነብባችሁ።  ዞር አሉ አልሸሹም አንደሚባለው፤ መቐለ ተብሎ መጻፍ አለበት ሲል ቆይቶ  መቐለ’ ማለት የማይቻል ከሆነ ‘መቀለ’ ተብሎ መጻፍ ይቻላል።   ‹‹መቐለ ተብሎ ነው መፃፍ ያለበት፤  እንደው ‹‹ ‹‹›› ለመፃፍ> ይከብደኛል አይሆንልኝም የሚል ሰው <መቀለ> ብሎ ይጽፍ ይሆናል እንጂ <መቀሌ> የሚልበት ምክንያት የለም፡፡››

አልገረማችሁም? “መቀለ” ተብሎ መጻፍ ይቻላል ካለን ‘መቀለ’ ተብሎ መጻፍ ከተቻለ እና ገብረኪዳን አስታራቂ ብሎ የሰጠው ‘መቀለ’ የሚለው ስያሜ በምንኛ ቋንቋ አባባል ነው? መቀሌ ማለት አማራዎች የሚጽፉት ወይንም የሚሉት አባባል ነው፡ ‘መቀለ’ ግን ‘መቀሌ’ን ተክቶ ለመጻፍ ተቀባይነት የሚኖሮው ወያኔዎች ‘ሌ’ን ወደ ‘ለ’ የመቀየር ሥልጣን መብት ማን ነው የሰጣችሁ?  ከመቀሌ ይልቅ ‘መቀለ’ በየትኛው የአማርኛ ‘ልሳን’ መመዘኛው ነው አርኪ ሊሆን የሚችለው? ወይስ እንዲሁ ‘ድመት ላመሏ….’ የአማርኛ ጥላቻችሁ እንደ አዲስ ‘ሃ’ ብላችሁ እንደገና ‘ለማስተጋባት’? አስቀድሜ በጻፍኩት መጽሐፌ ላይ “ትግሬዎች አማራዎችን “አምሓሩ” እያሉ ሲጠሩ አግባብነት የሚኖረው አማራዎች ግን ትግሬዎችን “ትግሬ” ብለው መጥራታቸው፡ የሚያብከነክናቸው በምን መመዘኛ ነው” ብየ ነበር። አሁንም መቐለ ማለት ካልቻሉ መቀሌ ከማለት ይልቅ ‘መቀለ’ በሉት ይላቸዋል፡፤መቀለ ብሎ የሚጽፍ አዲስ የአማራ ነገድ አጻጻፍ ገብረኪዳን ሊፈጥርልን መጣሩ ያስገርማል።

ግርማይ ገብሩ የተባለው ሌላው የትግራይ ብሔረተኛ ደግሞ ‘ትግራይ ኦን ላይን’ ተብሎ በሚጠራው ድረገጽ በሚለቀቀው ‘ስኒት’ (ስምምነት/አንድነት) ብሎ ራሱን የሚጠራ በወያኔው ኢንተርኔት ራዲዮ ላይ ከዘላበዳቸው መካካል ውስጥ “ኣብ ሃገረይ ኰሪዔ እንብር ኣለኹ!” ( በአገሬ ምድር ላይ ኰርቼ እኖራለሁ!) በማለት አገሩ ውስጥ ተንደላቆ ኮርቶ እንዲኖር እያቀላመጡት በሚገኙት ወያኔዎች ምክንያት ከሚወዷት አገራቸው እና ቤተሰቦቻቸው ተለይተው አገራቸው ለቀው “በተሰደዱት ተቃዋሚዎችን” እየተኩራራ ‘በመቀሌ’ እና ‘በመቐለ’ ያለው ልዩነት ‘የማንነት ጥያቄ  የህለውና ጉዳይ’ እንደሆነ አንዲህ ይላል።

‹‹ [በመርከቡ] ላይ የሠፈረውመቐለሳይሆንመቀሌየሚል መሆኑ፤ ለዚህ ቃል ሆነ ለሌሎች (ሽሬ፣ ትግሬ፣ ወዘተ) የተዛቡ የአፃፃፍ/አጠራር ልማዶች የትግራዋይ ማንንት የሚጻረሩ እና “የህልውና ጥያቄ” ስለሆነ እንቃወመዋለን።…” ይላል ግርማይ ገብሩ ከእነ ገብረኪዳን ደስታ እና መሰሎቹ በመስማማት።

መቐለን በመቀሌ ተጻፈ ተብሎ እንደ አህያ ሜዳ መሬት አንደተናጋ “ቡሩ ሃሃ”  ሕብረተሰቡን በጩኸት ከማወክ ይልቅ ስለ ማንነት እና የህልውና ጥያቄ የሚያሳስበው ትግሬ ብሄረተኛ ሁሉ የወያኔ ትግሬዎች በወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው አንዲሁም ልጆቻቸው ላይ ግዕዛዊው እና አክሱማዊው ብሔራዊ ቋንቋ የሆነው ‘አማርኛ”ን በማስወገድ ከአፀደ ህጻናት (መዋዕለ ህፃናት) የትምህርት ደረጃ ጀምሮ እንግሊዝኛ አንዲማሩ በሕግ ትግራይ ውስጥ በመደንገግ የትግራይ አዲስ ትውልድ አማርኛን በማስወገድ በምትኩ የባዕድ ቋንቋ በሆነው እንግሊዝኛ አንዲማሩ ለ21 አመት የተደረገው ማንነትን የማስካድ እና  በባዕድ የመተካት የወያኔ ዘመቻ ሲካሄድ ምነዋ ግርማይ ገብሩ የተቃውሞ ፌርማ አሰባስቦ አሁን በ ‘ቐ’ እና በ ‘ሌ’ የፈደል ጦርነት እያሰባሰበ እንዳለው ተቃውሞውን በፌርማ አላሰባሰበም? አማርኛ በእንግሊዝኛ ሲተካ ፤ ትግራይ ውስጥ ያልነበረ ባህል በማስተዋወቅ ጫት አከፋፋዮች ተፈቅዶላቸው ወጣቶች በጫት መርቅነው ሲበላሹ፤ባለትዳሮች የሞቀ ጋብቻቸውን በሱስ ተጠምደው ሲያፈርሱ  እና ሲናጋበቸው፤የእንደርታ፤ የዓጋመ (አጋሜ)፤የራያ፤የተምቤን ገበሬዎች ፤ ከተማ ኗሪዎችና ወጣቶች “ልሳናቸው” በኤርትርኛ እና በ ‘አሽዓ’ ልሳን ሲወረሩ፤ የ‘ድምፂ ወያነ ትግራይ’ ጋዜጠኞች አብረው የኤርትርኛው የልሳን ለውጥ ዘመቻ ተዋናዮች ሲሆኑ፤ የትግራይ ኪነት ስዕለ-ድምፅ ተዋናያን  እና ሙዚቀኞች በወረርሺኙ ለሃያ ሁለት አመት ‘ሲለከፉ’ የትግራይ ወጣቶች “ባጊ/ሳጊ/አቅማዳ ሱሪ” እና በ‘ራፕ’ ሙዚቃ ህሊናቸውና ባህላቸው ሲበረዝ፤ በቲቪ እና በራዲዮናቸው ሲያስተዋዉቁላቸው፤ ገጣሚ፤ጋዜጠኛ እና ደራሲ ‘ግርማይ ገብሩ’ የማንነት እና የህልውና ጥያቄ ብሎ የሚለው እከላከልለታለሁ፤ቆሜለታለሁ ለሚለው በትግራይ ሕብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለው የባህል፤ የቋንቋ፤ የልሳንና የባሕሪ ለውጥና በስርአተ ትምህርት ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥልቅ የጥቃት ዘመቻ ያልተሰማው አድዋዊ በመሆኑ? ወይስ የለውጡ ተባባሪ? ወይንስ አማርኛ ቋንቋ ላይ ሲደርስ የአማራ ጥላቻ ስላለው ያንን የገብረኪዳን ደስታ የጥላቻ ጭፈራ አብሮ ለማጫፈር?    

‘ቋንቋየ፤ባህሌ ማንንቴ በአማራዎች ስለተረገጠ ይህንን ለመቃወም እና ማንነታችን ለማስመለስ ነው ወደ ጫካ ገብቼ ወያኔ ሆኜ የታገልኩት የሚለን “የቪ ኦ ኤው” ጋዜጠኛው ትግራዊው ብሄረተኛው ግርማይ ገብሩ ‘በወያኔዎቹ  የትግራይ ኦን ላይን  ለስኒት ራዲዮ አዘጋጁ ሃብቶም ተኽሌ በቃለ መጠይቁ መሰረት እንዲህ ይላል፡- ‘የተነጠቅነውን ማንነታችን ለማስመለስ መቀሌ የሚለውን ወደ መቐለ ለመለወጥ ትግሉ ቀጥሏል፤ ‘ፐትሽን አዘጋጅተናል’ አንደምናሸንፍ ደግሞ አንጠራጠርም……..” ይላል። ግርማይ ገብሩ። ይህ ሁለ ሰማይ የተገለበጠ የሚያስመስለው “ቡሩ ሃ!ሃ!” የግርማይ ገብሩ እና መሰሎቹ ጩኸት አማራዎች ሆን ብለው በትግርኛ ቃላት ላይ አማራዎች  ጉዳት ለማድረስ እንዳደረጉት የሚከሱት የተዛባ ክስ እስኪ በጥሞና ረጋ ብለን እንመርምረው።

በመላ አለም የታወቁ የቋንቋ ሊቅ የሆኑ መምህሬ በዚህ ጉዳይ ጠይቄአቸው የእነ በገብረኪዳን አና የእነ ግርማይ ገብሩ ጩኸት በተሳሳተ አመለካከት የህልውና ጥያቄ  አንዴት ለማገናኘት እንደተፈለገ አንብበውት በጣም ነው የገረማቸው። ለምሳሌ አሉኝ፤ ‘አንግሊዝኛ እንደተናጋሪዎቹ ልሳን ለመናገር አንደነሱ ልሳን መናገር ነው ያለብህ አይደል?’ አሉኝ። አዎ። አልኳቸው። ‘When you pronounce English words, you would like to pronounce them exactly like an English speaker.’ ልክ እንደ እንግሊዞቹ ለመናገር። ምኞትህ ያ ነው።  ‘That is your wish, you “the speaker.” ግን  ቋንቋህ ስላልሆነ፤ ወደ አልፈለግከው የአጠቃቀም ዘይቤ ይወስድሃል። ‘But your language takes you to where you do not wish to go.’ ስለሆነም እንግሊዝኛውን የምትናገረው ልሳን ቋንቋህ በሚኖረው ተጽዕኖ ላይ ይሆናል ማለት ነው።  So you pronounce the English words as your language dictates.’ ለምሳሌ ግዕዝን ተመልከት “ብዕራይ” የሚለው የግዕዝ ቃል Look, for example, in Ge’ez “cow” is “bi’iray.”  በአማርኛ ሲጻፍ ወይንም ሲነገር “በሬ” ነው። In Amharic it is “bere.” ተመልከት “ራይ” የሚሉ ፊደሎች ወደ ‘ሬ’ እንዴት አንደተወሰደ።  Look how ay is changed to e. Amharic speakers do not hate Ge’ez. ራይ የሚለው ወደ ሬ ሲለወጥ አማርኛ ተናጋሪዎቹ አንድያ ሲጠቀሙበት ለግዕዝ ጥላቻ ስላላቸው አይደለም። ለግዕዝ ጥላቻ የላቸውም። ቋንቋቸው ስለሚጫናቸው ነው። But their language takes control. በግዕዝ ላይም አንዲሁ ‘ትግራይ’ የሚል ታገኛለህ። Similarly, in Ge’ez you find Tigray.  ልክ እንደ ላይኛው “ራይ” የሚለው ወደ “ሬ” በማስተጋባት “ትግሬ” ብለውታል/ይላሉ። አማራዎቹ የትግራይ ሕዝብ ስለጠሉ አይደለም። ቋንቋቸው ተጽእኖ ስለሚያደርገባቸው ነው።These Amharic speakers do not hate people from Tigray. But their language takes over and changes the ay to e. There is no malice at all. ስለሆነም ሆነ ተብሎ የተደረገ ጥላቻ ወይንም የትግራይን ህልውና ወይንም ባህል ለመጻረር ሆን ተብሎ የተፈጸመ ሴራ አይደለም።’ በማለት በኢመይል ገልጸውልኛል። ወደ አማርኛ ስተረጉም ስህተት ካለ የኔው እንጂ የማንም አይደለም።  

እነ ግርማይ ገብሩ ግን አማርኛን በማስወገድ በየገጠሩ አንግሊዝኛ ተክቶ ትግራይ ውስጥ በስርዓተ ትምህርት ሁለተኛ የትግራይ ሕጋዊ የገበያና የመግባቢያ ቋንቋ (ምናልባትም ለወደፊቱ ትግርኛን ለመተካት፤ ይህን በመረጃ የቀረብከትን  ይመልከቱ Tigrayan Modern Elites and their bizarre Love for Colonial Language. Getatchew Reda) ሆኖ እያለ ‘የህልውና ጉዳይ’ የሚሉት ሳያስባቸው በመቀሌና በመቐለ የቃላት ስንጠቃ ገብተው ቡራ ከረዩ (ቡሩ ሃ!ሃ!) በየማሕበራዊ የመገናኛ መስመሮች ሲጮሁ ማድመጥ በጣም አስቀያሚ ብሄረተኛነት በመፋፋም ላይ መሆኑ የሚያመላክት ነው። አንደውም ሕብረተሰቡ በባእድ ቋንቋ አንዲማር እና አማርኛ እንዲጠፋ በመደረጉ ‘ፋሺስዝም’ በትግራይ እየተስፋፋ መሆኑ አያጠራጥርም።

ምክንያቱም አንድ የውጭ ጸሐፊ አንዲህ ይላል “fascist exploiters select a weak community.  fascists socially and culturally uproot the victimized community by imposing a foreign language and culture on them. Because the local people cannot easily express their individual and collective feelings and sentiments in a foreign language, they develop a defeatist psychology and inferiority complex with respect to the exploiters. This defeatist psychology destroys the natural spiritedness and will to fight of the local people, and the fascists skillfully utilize this golden…” ስተረጉም እንዳላዛባው እንዳለ አንደተረዳችሁት ተስፋ አለኝ። ፋሺዝም/አፓርታይድ ትግራይ ውስጥ  መስፈኑ የማታምኑ ካላችሁ

የመቀሌው  ገረብ  ቡቡ  የ “አፓርታይድ” መንደር ( በጋዜጠኛ በዮናስ በላይ አበበ (መቀሌ)  የተጻፈው  አንዲህ ይላል፦

“የከተማዋ ነዋሪዎችን ባገለለ መለኩ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ጥቂት ኢንቨስተሮች (በድምሩ 40 ሰዎች ናቸው) ከመቀሌ ከተማ ነዋሪ የተለየ መንደር ራሱን የቻለ የገበያ ማዕከል፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት፣ የመዝናኛ ማዕከል እና የመሳሰሉትን ተቋማት ያቀፈ፤ በግልባጩ ሌሎች የመቀሌ ሰዎች ድርሻ እንዲሉ የማይፈቀድበት መንደር እየተመሰረተ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በዛን ወቅት ማንም ሰው እነዛ ታጋዮች ከ60ሺ በላይ የትግራይ ሰዎች በሞቱለት ድል ተጠቅመው.. በአፓርታይድ ስርዓት የሚተዳደር መንደር ይመስረታሉ ብሎ አልጠረጠረም፡፡ የሆነው ግን ያልጠረጠረ……..” እያለ ይዘረዝረዋል። ሙሉውን ለማንበብ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/9028

ታዲያ እነ ገብረኪዳን ደስታ እና እነ ግርማይ ገብሩ በታገሉለት የወየነ ትግራይ ድርጅት ዋና ዋና ሰዎች “አፓርታይድ በመቀሌ” ሲያስፋፉ  እያዩ የ ‘ቐ’ ፤ የ ‘ቀ’ እና የ ‘ሌ’ ፊደላት ለውጥ ሲያሳብዳቸው ማየት “ ትገርምኒ!” የሚያስብል ነው።አማራዎች “ታስገርምኚአለሽ/ትገርሚኝያለሽ” ለማት ነው ትግርኛውን በደም ሲጠቀሙበት እዛው ትግራይ የኖሩ አማራዎች ለዛ ባለው ልሳናቸው “ትገርምኒ” ይላሉ ።

እስኪ አሁን ደግሞ ወያኔ ትግራይ ከበረሃ መጥቶ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መዝገቦች፤አንቀፆችም ሆነ በትግራይ ክልል ‘መንግሥት’ ብሎ በሚጠራው  የራሱ ሕጋዊ ጋዜጣ እና ድረገጽ አንዲሁም በየትምህርት ቤቱም ሆነ በመንግሥት መሥርያቤቶች ድረገጾች እና ‘ድምፂ ወያነ ትግራይ’ ራዲዮ ድረገፅ ምን አይነት የባዕድ ቃላቶች ተቀባይነት አግኝተው እየተጠቀሙባቸው አንዳሉ ለናሙና አንመለክት።

ዞንሊስ፤ “ዝለዓለ መዓቀኒ ሞዴል” (የላቀ የሞዴል መለኪያ) ፤ኣብያተ ትምህርቲ ብተመጋጋብነት ክንፍታት ሰራዊትን ፎረም” ማሕበረሰብ ትምህርትን ተጠናኺሩ ብዝፍጠር መሰረታዊ ለውጢ ክነዕውቶ ኢና! http://www.tiggovpr.org/ ሓሙስ 16, ጥሪ 2014 የተገኘ መንግሥታዊ የወያኔ መግለጫ ሰነድ

ፖሊስን ስትራቴጅን፤ ኤጀንሲ ልምዓት፤ፕሮጀክትታት ልምዓት፤ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል፤ፖርታል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ፤መንግስታዊ ሊንክታትአድቨርታይዝመንት (ድ ወ ት) (ማስታወቅያ የሚለው አማርኛ ላለመንካት ነው) አንዳንዴ “ሻዕብያ የፈጠረላቸው “ምልክታ” የሚል ይጠቀማሉ” ፤አርካይቭ ክልላላዊ መንግሥቲ ትግራይ ፤ ፈነወ ፕሮግራም… ዓሚል….  ሚሊየነም፤ ኢንቨስትመንት፤ ሊዝ መሬት፤ በጀት አንዳባጃጀትካ (በጀት እያዋቀርክ ለማለት ነው)፤መንህስታዊ ‘ኰታ’፤ ዞን፤ መርሃ ጉጅለ፤ ሙጉጅጃል፤ዓወት ንሓፋሽ፤ መኽዘን/ ጎተራ ላለማለት ነው፡(መኽዘን በማለት ኤርትርኛ/ዓረብኛ የሚጠቀሙት)፤ አርቲስት… ወዘተ ወዘተ…….. እጅግ ለመቁጠር የሚያዳግቱ በርካታ የባዕድ ቋንቋዎች እና የሽምቅ ተዋጊዎች፤ አራባዊ ቋንቋዎች ትግራይ ውስጥ ሕጋዊነት አግኝተው ያለ ምንም ተቃውሞ ገበሬዎች አንዲነጋገሩባቸው እየተሰራባቸው ነው። ወያኔዎች ከበረሃ ከገቡ በሗላ ታሪካዊ ገጠሮች፤ተራራዎች፤መንደሮች፤ወንዝ/ፈለጎች፤ከተማዎች፤የጥንት ነገሥታት የዋሉባቸው ጦርነት ታሪካዊ ስሞች ፤ “የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወታደራዊ የስልጠና ማዕከሎች” ልክ የግል ይዞታቸው አድርገው በመቁጠር፤በማን አለኝነት በታጋዮቻቸው ስም እንዲሰየሙ ታለቅ ወንጀል እና ሴራ የፈጸሙትን እዚህ አልጠቀስኩም። እነ ግርማይ ገብሩ የድርጅቱ ታጋዮች ናቸው ይህ ሴራ እና የሥልጣን ብልግና ባህላዊ ረገጣ አላሳሰባቸውም።

እዚህ ላይ በእግረ መንገዴ ትዝ ያለኝ ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛ ቪ ኦ ኤ ቃለ መጠይቁ ያለውን ትዝ ይለኛል። እንዲህ ይላል፦ “ቋንቋችን ድሮ የተረገጠ እንዳይበቃው አሁን በወጣት ዘፋኞች ሲደገም እያደመጥን ነው።” ለምሳሌ ይል እና “ለምሳሌ  ብርሃነ ሃይለ እና ዳዊት ነጋ የተባሉት ዘፋኞች ብንወስድ፤ ብርሃነ ሃይለ “ዝዓበኹላ መረበተይ” በማለት (ያደግኩብሽ መንደር) ትከክለኛውን ትግርኛ ሲጠቀም እንደርታዊ የሆነው ዳዊት ነጋ ግን “መንደረይ” እያለ ያዜማል።” አስቂኝ ነው!” ሲል በእንደርታዊው ዘፋኝ ለምን መንደር የሚል ቃል ተጠቀመ ሲል ተሳልቆበታል። ገብረኪዳን ደስታ እየደገፈ ያለው የቅርብ አውራጃ ጎረቤቱ የሆነው አክሱማዊው ብርሃነ ሃይለን ነው። አማርኛ እና ትግርኛ አንዲሁም ግዕዝ እና አገው ቀላቅለው የሚናገሩት አንደርታዎች፤ራያ፤አጋሜ ተምቤን የመሳሰሉት በገብረኪዳን ደስታ ዘረኛ ሕግ “አነኚህ ትግሬዎች አይደሉም” ማለት ነው። ‘ሰዎች’ እና ‘ንቦች’ ሁለቱም አንድ ናቸው። ‘ሰዎች እና ቋንቋዎቻቸው’፡ ‘ንቦች እና አበባዎች’ ከየትም እየቀራመቱ በመስጠት እና በመቀበል ተፈጥሮአዊ ሕግ የሚጓዙ መሆናቸውን በእነ ገብረ ኪዳን እና በእነ ግርማይ ገብሩ አይታወቅም።  በቋንቋ ስለሚተዳደሩ፤ በደም እና በአጥንት ቆጠራ ስለሚጋቡና ስለሚነጋገሩ  ‘ክልላዊ የጥራት ፍልስፍናቸው’  ስለሚጻረር የጠቀስኩት ተፈጥሮአዊ ሕግጋት በወያኔዎች ላይ አይታወቅም።

ቋንቋዎች “ግብረ ፆታዊ” ግንኙነት አይፈጽሙም እንጂ ፊደሎች/ልሳኖች/ቃላቶች ግበረፆታዊ ግንኙነት በሚመስል ተፈጥሮአዊ የልውውጥ ሕግ በመጠቀም ‘ቋንቋ’ የሚባል አዲስ ልጅ/ውልድ ይወልዳሉ ማለት ነው። ሁሉም ቋንቋዎች በወጥ የተፈጠሩ ሳይሆኑ ግብረፆታዊ በሚመስል ግንኙነት እየተሰበጣጠሩ ጽንስ በመመስረት የተለያዩ አቋንቋዎችን ይወልዳሉ። ይሕ ሕግ በፋሺስቶች ሕሊና በጥራት ስለሚሰክሩ ተቀባይነት የለውም። አንድ ወጥ የሆነ ልሳን እና አጠቃም/አጻጻፍ አንዲኖሮውም እንዲሆንም አዋጅ ያውጃሉ።

ለዚህም ነው ፤ ዘመን ሲፈጠር ጀምሮ በተጠቃሚዎቹ ተቀባይነት አግኝቶ በግብር የሚገለገሉበት ስብጥር ቋንቋ እና ልሳን በፋሺስት ወያኔዎች ሕሊና ተቀባይነት እንደሌለው በመገናኛ ዘዴዎች ቀርበው ባለ ማፈር በግልጽ የእንደርታ፤የተምቤን፤የራያ፤ የአጋሜ/ዓጋመ ትግርኛ ተናጋሪ ሕዝብን የሚዘልፉት። ስለሆነም ነው በጋዜጦቻው እና በወያኔ ደምጽ ራድዖኖቻቸው የ “አሽዓ” ወይንም  የ “ኤርትርኛ” ትግርኛ በሰፊው በመጻፍ እና በማስተላላፍ እየተጠቀሙ ሕዝቡ ከነበረው ባሕላዊ ልሳን ቀስ በቀስ በማስወጣት በማንነቱ ላይ (በምላሱ/ልሳኑ አጠቃቀም) እየተሸማቀቀ የበታች ስሜት አንዲሰማው በማድረግ አብዛኛው የዛው የተጠቀሱት አካባቢ ኗሪ ትግሬዎች ዓድውኛ ወይንም ኤርትርኛ በመጠቀም ማንንቱን በመጋፋት ዘመቻ እያካሄዱበት የሚገኙት። የተጠቀሱት አካባቢ ተናጋሪዎች በራድዮንም ሆነ በፓል ቶክ ስታዳምጧቸው በጣም ታዝናላችሁ። ከተዘበራራቀ ኤርትርኛ ትግርኛ አጠቃቀማቸው ስታዳምጡ እንደተምታታባቸው በግልጽ ከሚጠቀሙት ቃላቶች እና ልሳኖች ማየት ይቻላል። አሳዛኝ የማንንት ጥቃት ሲፈጸም አንደርታዎችም ሆኑ ራያዎቹ እና ተምቤኖቹ ተቃውሞ ማሳየት ነበረባቸው። ነገር ግን ፋሽስት ፖለቲካ በፍራንኮ/ስፐይን/ በሙሶሎኒ/ ጣሊያን በህወሓት/ወያኔ “አንድ ወጥ” ፖቲካ እና ልሳን ለማራመድ እንደሞከሩ ታሪክ ዘግቦታል። ወየኔዎች በህዝቦች

 ቋንቋ እና መስተጋብር አያምኑም። ትግርኛ አንድ አይደለም። እስክስታውም ሳይቀር  (ተምቤኖች ትግሬዎች ናቸው፤ እስክስታቸው ግን ጭራሽ ከትግርኛው እስክስታ አይገናኝም) አንድ አይደለም፤ የከበሮ አመታትም እንዲሁ።

በነገራችን ላይ ከወያኔዎች በፊትም አፄ ዮሃንስም አንድ ሃይሞኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ፕሮተስታንት ወይንም እስላም የተባለ ወደ ኦርቶዶክስ ካልተጠመቀ ከትግራይ ግዛቴ ለቃችሁ ወደ ሌላ አገር ሂዱ ብለው አውጀዋል። (ካሁን በፊት መረጃወን አቅርቤአለሁ)። ከእዛ በሗላም “ቀዳማይ ወያነ/የመጀመርያ ወያኔ የሚባለው የትግራይ ገበሬዎች አንቅስቃሴም በጉልተኞች ተነጥቆ ሲመራ ቀይ ጨርቅ እያውለበለቡ አንዲህ በማለት አዋጅ ብለው ካወጡት ባጭሩ ላቅርብ። እንዲህ ይላል።

“…ስምዑ፤ስምዑ!

አዋጅ ሃይለማርያም አዋጅ ገረብ እዩ

ገዛኢና እየሱስ ክርስቶስ፤

ሓላዊና ሃይለማርያም፤

ዳኝነትና ናይ ዓሰርተ ክልተ ገረብ፤

ባንዴራና ባንዴራ ኢትዮጵያ፤

ሃይማኖትና ናይ ሃፀይ ዮውሃንስ

ህዝቢ ትግራይ ወያነ ተኸተል፤

ገረብ መንግሥቲ ተቐበል።”


ዋናውን ነጥብ ቆርጬ ልተርጉመው፤- አንዲህ ይላል “ባንዴራችን የኢትዮጵያ፤ ሃይማኖታችን የአፄ ዮሐንስ፤ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ተከተል፤ የገረብ መንግሥትን ተቀበል፡…” እያሉ አዋጅ አወጁ። የመቀሌ ከተማ ሕዝብም በመሰብሰብ ደስታውን በእልልታ ገለጸ። ይላል። አዋጁ ላይ የሚነበበው “ንጉሳችን ሃይለማርያም ረዳ”  “ገዢያችን እየሱስ ክርስቶስ” እና “ሃይማኖታችን የአፄ ዮሐንስ” የሚለው ስትመለከቱት። እስላሙን እና ሃይመኖት የሌለው ወይንም የመሳሰሉት አማኞችን የሚጻረር እና ኦርቶዶክሳዊ ሃይሞኖት በሌሎች ላይ በመጫን በአዋጅ አግላይ አዋጅ አውጀዋል። በግጥሙ መሰረት “ ሃይለማርያም ንኡስየ፤ ሎሚ ሽፍታ ልዓመታ ንጉስየ” (ጎልማሳው ሃይለማርያም ዛሬ ሽፍታ ቢሆንም፤ ለከርሞ ግን ንጉሳችን ነው)። በዚህ መሰረት ኦርቶዶክሳዊው ሃይለማርያም ረዳ ንጉሥ ሲሆኑ “ገዢያችን እየሱስ ክርስቶስ” እና “ሃይማኖታችን የአፄ ዮሐንስ” የሚለው በቀዳማይ ወያኔ አዋጅ መሰረት የትግራይ ሕዝብ ሃይማኖት (ምናልባትም ከቻሉ የኢትዮጵያ) ክርስትያናዊ ሃይማኖት የሚከተለው የቀዳማይ ወያነ ቡድን የትግራይ ሕዝብ ሃይማኖት እንዲሆን ታውጆ ነበር። ለዚህም ወያኔንን ተከተል ብለውታል። ይህ ጉድ እየሸፈኑ ሃይለስላሴ ወይንም ምንሊክ ወይንም ደርግ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ አገር፤ አንድ  ቋንቋ …….ወዘተ እያሉ ሲጨቁኑን ነበር እያለ የሚዋሹት ውሸት “የእኛ የትግሬዎችንም ጉዳችንን አንድታዩት ብየ ነው ይህንን ማስረጃ” ያቀረብኩላችሁ።   


እነ ግርማይ ገበሩ እና ገብረኪዳን አነዚህ እንግዝኛ/ዐረባዊ hybride/ዲቃላ ቋንቋዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ሆን ተብሎ በወያኔ ሕገ መንግሥት ሲደነገግ ሳያሳስባቸው በግዕዝ ጸሐፊዎች እና አማርኛ ተናጋሪዎች ሲጻፉ የነበሩትን የአካባቢም ሆነ የኗሪ ሕዝብ ስሞች ሆን ተብሎ የተፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው እያሉቅራኔን ማስተጋባት ተናካሽ ብሔረተኛነት እያስፋፉ ነው።  ለምሳሌ ሽረ ትግራይ በሽሬ በትግሬ መጻፍ የለባቸወም እያሉ ይቃዣሉ። የጥላቻ አስተማሪዎቻቸው እና ተማሪዎቻቸው ያልተረዱት ነገር የቃላት እና የቦታ ስም መለዋወጥ አሁን አልተጀመረም። አክሱም እኮ ከአኽሱም በፊት “አከሰመ” ተብሎ ነው በጥንት አክሱማዊያን ጸሐፍት በድንጋይ ቀርጸው ጽፈው የተውልን። እንዴ! አንዴት ነው ነገሩ? የአማርኛ ቃላቶች “የትግራይን ህልውና “ ጥያቄ ውስጥ  አስገብተውታል የምንል ከሆነ “በሕግ ተደንግጐ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ድረስ እንግሊዝኛ አንጂ አማርኛ አንዳይማሩ ተማሪዎችን ያገደ” ጸረ አገራዊ ቋንቋ የሆነው የወያኔው ቡድን ሲያውጅ አንዴት ነው የህልውና ጉዳይ ሊሆን የማይችለው?  ትግርኛ ውስጥ  ተሰግስገው የሚገኙ እአላፍ ዓረብኛ እና እብራይስጥ አንዲሁም ግሪክ እና አገው ቃላቶች እንዲሁም ምንጫቸው እና ትርጉማቸው የማይታወቁ የትግራይ የገጠር ስሞች በሙሉ የመቀየር ዘመቻ ልንገባ ነው ማለት ነው። 90% የሆነው የትግራይ ተወላጅ የጥንትም ሆነ የዛሬ የትግራይ ሕብረተሰብ ስሙ አማርኛ፤አይሁዳዊ/ሃይማኖታዊ ነው። የእነ መምህር ገብረኪዳን ደስታ “የዛና” ገጠር ኗሪ ወላጆቻቸው “ደስታ” የሚለው የአማርኛ ትርጉም ስም ገጠር ውስጥ ለምን “ደስታ” ብለው ሊጠሯቸው እንደመረጡ ገብረኪዳን ባያወውቀውም የገብረኪዳን ወላጅ አባት አያታቸው ያውቁታል። የቃላት ዘመቻ ጥራት  ከተጀመረ ወያኔ የጀመረው እና የደከመበት የደም  እና የአጥንት ቆጠራ ዘመቻውም ወደ እላይ ከወጣ ከእነ ማን ጋር ሲደርስ መጨረሻ አንደማይኖረው የታወቀ ነው።

ባሻይ ደበስ የተባሉ በአብዛኛው የእንደርታ/የመቀሌ ኗሪ ሕዝብ የታወቁ ‘ቀልደኛ ተጫዋች” ነበሩ። ከሰውየው ጋር በጣም ቅርብ እውቅና አለኝ። እኔ እና እሳቸው እንዲሁም አንድ “አያ ታፈረ’  የሚባል ዘመዴ የቅርብ ወዳጃቸው ቀኑ የቅዱስ ዮሐንስ የዘመን መለወጫ በዓል ነበርና፤ ቆመን፤ አንጋሬ ለመሸጥ ከሳቸው ጋር እንነጋገራለን። ባሻይ ደበስ አንጋሬዎቹን ገዝተው ለአንድ ሸቃይ ወጣት ጐረምሳ ጠርተው “ወዛደር! ወዛደር!” በማለት ከፍ ብሎው በመጮህ አንዱን ሸቃይ ይጠሩታል። እሱም “አቤት ባሻይ!” በማለት ሮጦ ወደሳቸው በመጠጋት “ምን ልላከዎት/ልታዘዘዎት?” ሲል ይጠይቃቸዋል። እሳቸውም “አነኚህ አንጋሬዎች እቤቴ ድረስ አድርስልኝ” ይሉታል። አሱም “በሚገባ እሺ” በማለት ትዕዛዙን ተቀበለ እና፤ “ለመሆኑ ስንት ነው የምታስከፍለኝ?” ይሉታል። እሱም “ሜንዞ/ሱሙኒ” ይላቸዋል። (ሜንዞ/ሞዞ እንደርታዎች ሲጠቀሙበት፤አሽዓዎች ደግሞ “ሕርካም” እንለዋለን)። ባሻይ ቀበል አርገው “ስንት?” ሜንዞ/ሞዞ” (ሱሙኒ) ይላቸዋል። እሳቸውም በመገረም “ወይከ ሕልፍ ፤ሹምካ ቀይርካ እምበይ!” (ስምህ ቀየርክ እንጂ፤ከዛች ከሱሙኒ ድህነትህ ወይ ፍንክች!” ብለው ሱሙኒውን ሰጥተውት አንጋሬውን አደረሰላቸው። እኛም በንግራቸው ተሳስቀን ተለያየን። ባሻይ ቀልደኛ ስለነበሩ ደርግን ሲጻረሩ እያሳሳቁ በቀለድ ነበር ነገራቸውን ጣል የሚያሰደርጉ።

 ስምህ ቀየርክ አንጂ እያሉ ያሉት ድሮ “ሸቃይ ሸቃይ” ይባል ነበር በደርግ ጊዜ ግን“ወዛደር” የሚል መጠርያ ስለተሰጠው ነው። ለዚህ ነው “ወይከ ሕልፍ ፤ሹምካ ቀይርካ እምበይ!” (ስምህ ቀየርክ እንጂ፤ከዛች ድህነትህ ወይ ፍንክች!”) በማለት የተሳለቁበት። አሁንም ወያኔዎች ከ ‘ቀ’ ወደ ‘ቐ’ ከ ‘ሌ’ ወደ ‘ለ’ ካልተቀየረ ሕልውናችን አደጋ ላይ ነው በማለት ቅዠት ውስጥ ቢገቡ እና ሕበረተሰቡን ለማጃጃል የባህል አስከባሪዎች መስለው ለመታየት ቢሞክሩም ፤ባሻይ ደበስ አንዳሉት አውነታው ውጫዊ ለውጥ እንጂ ነባራዊው እውነታው የስም ለውጥ መቀየር እድገት አያሳይም።  አመጣሁላችሁ ከሚላቸው ዘመቻው ይልቅ ከዛው በባሰ የባዕድ ወረርሺኝ ዘመቻ በትግራይ እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ሆን ብሎ እንዲስፋፋ ከውጭ አገር ሳብቨርሲቭ/ አጥቂዎች እየተመካካረ አገሪቷን ወለል አድርጎ ለቅኝ ግዛት አስፋፊዎች በመክፈት በታሪካችን ታይቶ የማያውቅ የባህል ውርደትና የማንንት ረገጣ እንዲደርስብን ያደረገ የውጭ አገር ወኪል ቀንደኛ ተላላኪ ተዋናይ እነ ግርማይ ገብሩ እና ገብረኪዳን የታገሉለት ደርጅት “ወያኔ” እንደሆነ ማንም ሊሸሽገው የማይችል ገበነኛ ስርዓት ነው። በወያኔ ዘመን የባህል እና የባሕሪ ወረርሺኝ አንዴት እንዲስፋፋ እንዳደረገ የወያኔ ጉደኛ እድገት ለማወቅ ከፈለጋችሁ ይህንን የግብረሰዶም የባሕል ወረርሺኝ በወያኔ ጊዜ የተከሰተው የባህል ጥቃት ተመልከቱት፤-  Homosexuality in Ethiopia- Exposed ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት http://youtu.be/R7uqyXQp35Y

የወያኔ ማንንት በይበልጥ ለማወቅ የጻፍኳቸውን መጽሐፍቶች  (1) ሓይካማ (ትግርኛ) (2) ጠበቕ ማይ ኮሖ (ትግርኛ፤- የቆየ መጽሐፍ) (3) ይድረስ ለጐጠኛው መምህር (4) የወያኔ ገበና ማህደር (5) ደቂቀ ተወልደ መድህን፤-… እና በመሰራት ላይ ያሉ ሁለት መጽሐፍቶች ማንበብ ይጠቅማል። getachre@aol.com 408- 561-4836 ከዚህ በጠጨማሪ የትግራይ ሊህቃን እንግሊዝኛ የአገሪቱ መነጋገርያ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን እነ ዶከተር  አለመስገድ አባይ እና ለእነ ፈስሃ አፈተጽዮን የመሳሰሉት ለጻፉት ዘመቻቻው የጻፍኩት/የመልስ ምት ጠቃሚ ሰነድ እነሆ ያንብቡ፡ Tigrayan Modern Elites and their bizarre Love for Colonial Language. Getatchew-Reda http://www.ethiolion.com/Pdf/07142013Tigrayan_Modern_Elites_and_their_bizarre_Love_for_Colonial_Language.pdf

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ
www.ethiopiansemay.blogspot.com