ዋናው ጠላት ትግሬው እራሱ ወይስ አፈወርቅ
ገብረ ኢየሱስ?
ጌታቸው ረዳ
POSTED AT ETHIO SEMAY
12/24/2021
የትግራይ ሰው የሆነው በሙያው “አርቺቴክተር” የሆነው ወጣት ኤርሚያስ አማረ በሚያዘጋጀው ፌስቡክ የትግራይ ሕዝብ “የወያኔ አስተዳደር” በቃኝ ማለት እንዳለበት\ በጻፈው ትችት ላይ “ኣፅብሃ ኣፅብሃ ሃጎስ” የተባለ አንድ የወያኔ “ቆዛሚ” “የጥላቻ መመህር የነበረው ፋሺስቱ “መምህር ገብረኪዳን ደስታ” የጻፈውን መጽሐፍ በመጥቀስ አንዱን ኢትዮጵያዊ አያቶችህ እኛን ትግሬዎች ከማጥፋት አይቦዝኑም ነበር በማለት ፤ ለቄሳራዊው ጣሊያን ያደሩት የድንቅ መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት “ጦቢያ” እና “የዳግማዊ አጤ ምኒለክ” መጽሐፍ ደራሲ ዶ/ር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ
”ስለ ትግሬ አንስተው በጻፉት “ምኒልክ መቸ ይነግሡልን እና ይኼ አምበጣ ትግሬ በጠፋልን እያለ የማይመኝ በኢትዮጵያ አልነበረም።” ብለው የጻፉትን በኤርሚያስ አማረ ፌስቡክ ላይ ‘አፅብሃ አፅብሃ ሃጎስ’ የተባለ ወያኔ ለቁመዘማው እንዲመቸው ጠቅሶት ስላየሁት “ዋናው ጠላት ትግሬው እራሱ ወይስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ? በሚል ርዕስ የወያኔ ጀሌዎች ማወቅ ያለባቸውን እውነታ በራሳቸው በትግሬ ሰዎች እንደ ወዳጄ ገብረመድህን አርአያ
(በነገራችን ላይ ገብረመድህን እኔ ጋር መገናኘት ካቆመ ቆይቷል፤ በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጽሑፍ እንዲያየውና እንዲደውል አውስትራሊያ ያለችሁ ወዳጆቹ ጋዜጠኞች አቀብሉት)
እንዲሁም ሌለው የትግራይ ሰው የሆነው “ትግሬዎች በትግሬዎች
ላይ እንዴት እንደሚጨክኑ” የትግሬዎች እርስ በርስ መጠፋፋት ወንጀል ተጨማሪ ማስረጃ በሃውዜን ጭፍጨፋ የተደረገው የወያኔዎች
ወንጀል አብርሃ ደስታ ያቀረበው ማሕደር ለማስታወሻችሁ ከሚለው ወርሃዊ አምዴ እነሆ መዘከሩ አስፈላጊ ስለሆነ አንባቢዎቼ እነሆ
ለታሪክ መዝግቡልኝ። መልካም ንባብ፦
Sunday, June 22nd, 2014
ሰኔ 15 የሰማታት ቀን ነው!
ABRAHA DESTA
POSTED AT ETHIO SEMAY ጌታቸው ረዳ
ሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ነው። ሰኔ 15, 1980 ዓም በሐውዜን ከ2500 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአንድ ፀሓይ የተጨፈጨፉበት ቀን ነው። ጭፍጨፋው የህወሓት እጅ እንደነበረበት ይነገራል። ይህ ማለት ቦምቡ የጣሉት ጀቶች የህወሓት ነበሩ ማለት አይደለም። ህወሓት በግዜው በሓውዜን ከተማ ጉባኤ እንደሚያደርግ ሆን ብሎ (የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት) ለደርግ የሐሰት መረጃ አስተላልፏል። ብዙዎቹ የደርግ ጀነራሎችና መርማሪዎች የህወሓት “ስርዒት” ነበሩ። የአብዛኞቹ የደርግ ባለልስጣናት ፀሓፊዎች የህወሓት ስርዒት (ሰላዮች) ነበሩ። (አግአዚ ኦፕሬሽን ፊልም ይመልከቱ)። ለህወሓት የሚሰሩ ወታደራዊ መኮነኖችና ፓይለቶች ነበሩ።
የሐውዜን ደብዳብ የታቀደ ድራማ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ደርግም ሐላፊነት ይወስዳል። ደርግ መንግስት እስከነበረ ድረስ ህዝብን ማዳን ነበረበት፤ መረጃው ማስተካከል ነበረበት። ሲጨፈጨፍ የነበረው ሰለማዊ ሰው እንጂ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ ይታወቅ ነበር። ስለዚህ ሁለቱም ሐላፊነት ይወስዳሉ።
ህወሓት መጥፎ ተግባሩ እንዳይታወቅ በመስጋት ድራማውን የሚያውቁ ታጋዮች እንዲረሸኑ ተደርጓል። ከድር የተባለ ታጋይ “ምን ስንል ነበር? አሁን ምን እያደረግን ነው?” ብሎ በመጠየቁ ተገድሏል። ዳዊት የተባለም “በሐውዜን የተደረገው ነገር ስህተት ነበር” ብሎ በመከራከሩ ምክንያት ተረሽኗል። ከዛ ጦፍ ተልኳል ተብሏል።
አሁንም ይሄ ጉዳይ አለ። በሐውዜን ጉዳይ ጥናት ያደረገ የሐውዜን ተወላጅ የሆነ ጋዜጠኛ አፈወርቂ አርአያ የሐውዜን ጉድ በማጋለጡ ምክንያት ታስሮ ነበር፤ አሁን ደብዙ ጠፍቷል። ሚስጥር ያጋልጣል በሚል ስጋት እንዲጠፋ ተደርጓል (የት እንዳለ የምታውቁ ንገሩኝ)። ሌላ ገብረአነንያ ገብረስላሴ የተባለ የሐውዜን ተወላጅ “ሓመድ ሓውዜን፡ መን ንመን?” በሚል ርእስ ብዙ ሚስጢሮች በማጋለጡ ምክንያት በሰበብ አስባቡ በመቐለ ከተማ ዓዲሓቂ ፖሊስ ጣብያ ያለ ምንም ፍርድ ለሦስት ወራት ታስረዋል፤ አሁንም እዛው በእስር ይገኛል።
ህወሓት ከደሙ ንፁህ ከሆነ ስለጉዳዩ የሚናገሩ ሰዎችን ማሳሰርና እንዲጠፋ ማድረግ ለምን ፈለገ? የሐውዜን ጉዳይ አልፏል። ማስታወስ አንፈልግም፤ ይሰማናልና። ለፖለቲካ ፍጆታ መዋልም የለበትም። ግን የእስርና እንግልት ምንጭ ደግሞ መሆን የለበትም። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሰዎች መታሰር የለባቸውም።
የሆነ ሁኖ አልፏል። የኛ ያሁኑ ጉዳይ የሐውዜኑ ዓይነት ጨፍጫፍ በሰዎች ላይ እንዳይደገም መከላከል ነው። ዳግም ደም መፍሰስ የለበትም። ስለዚህ ህወሓትም ይፈፅመው ደርግ መደርጉ ስህተት ነው። ስሀተት በስህተትነቱ እናወግዘዋለን። ያሁኑ ጉዳይ ማነው የፈፀመው አይደለም። ያሁኑ ጉዳይ መፈፀም የለበትም፣ አልነበረበትም ነው።
ክብር ለሰማእታት! It is so!!!
በማለት አብርሃ ደስታ ስለ ሓወዜን ጭፍጨፋ በሚገርም ዘገባ ነግሮናል።
አብርሃ የተጠቀመው “ጦፍ” የሚለው የተጋዮች ቃል “መልዕክት” (መልዕክት
ለማድረስ/ ተልዕኮ/ ሚሽን) ማለት ነው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
ETHIO SEMAY