Tuesday, April 14, 2015

ከ “አዳነች” ወደ “አድሓነት” ……አስመራ ውስጥ ዘኢትነገር የት ነው? (ክፍል 2) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)


ከ “አዳነች” ወደ “አድሓነት
……አስመራ ውስጥ ዘኢትነገር የት ነው? (ክፍል 2)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)
Getachew Reda Editor Ethiopian Semay

እንኳን ለበዓለ ትንሳኤው አደረሳችሁ!! ባለፈው ክፍል 1 ፋሲል የኔ አለም እና መሳይ መኮንን የተባሉ የግንቦት 7 የኢሳት ጋዜጠኞች የኢሳያስ አፈወርቂ የግል ንብረት ወደ ሆነቺው “ምድሪ መረብ ምላሸ” ድረስ ሄደው ለግንቦት 7 ደጋፊዎቻቸው እና እንዲሁም ግንቦት 7 አዲስ አበባ ድረስ ይዞን ይሄዳል፣ነፃነት ያመጣልናል ብለው በስሜት ለሚያንጨበጭቡ፤የዋሃን ኢትዮጵያዊያንን ገንዘብ እያስከፈሉ፤ ስለ ኢሳያስ ተክለሰውነትና የጦር መኰንኖቹ “ድርሳነ ውዳሴ” ያነበነቡትን፤ እንዲሁም በስርአቱ ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉትን አሰቃቂ ግፎችን አንስቼ አብረን ለማየት ሞክረናል። ዛሬ ደግሞ የምንመለከተው የኢሳያስ አፈቀላጤ የሆኑ አበበ ቦጋለ (የግንቦት 7 አመራር /ከኦሮሞ ጎሳ) እና መሐመድ ሓሰን (አምባሳደር ሆኖ የወያኔ አገልጋይ የነበረ፤ ለብዙ አመት ወደ ኢሳያስ መንደር ብቅ ጥልቅ የሚል/ለድምህት እንግሊዝኛ አስተርጓሚ) በጐሳው ኢትዮጵያዊ ሶማል)ለ እነኚህ  ሁለት ኢትዮጵያዊያን ባንዳዎች በግንቦት የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያ ‘ኢሳት’ ላይ ቀርበው ኢሳያስ አማርኛ የማይችል መሆኑን “በማያውቁት” ጉዳይ ሲቀባጥሩና ሲከላከሉለት በሚያሸማቅቅ አሳፋሪ ጥብቅና ሲለፈልፉ አድምጣችሗቸው እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ።

አስገራሚ ሚያደርገው የነዚህ “ፈትፋች” ግለሰቦች ደግሞ “ኢሳያስ አማርኛን መናገር ያልፈለገበት ምክንያት አማርኛን/አማራን ጠልቶ ሳይሆን፤ ስለማይችል ነው፤ እያሉ፤ ይህንን ውሸታቸውን ለማሳመን ደግሞ በተለይ መሓመድ ሓሰን የተባለው እሩቅ በመጓዝ የኢሳያስ ማንነት በማያውቀው ሲፈተፍት አድምጬው ገርሞኛል።

ኢሳያስን ለምናውቅ ትግሬዎች እና ከቋንቋ ጥላቻ ነፃ የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት የመረብ ምላሽ ምሁራን ስለ ኢሳያስ አማርኛ የመናገር፤የመረዳትና የመጻፍ ችሎታው በሚገባ እናውቃለን። ኢሳያስ የስድስተኛ ክፍልም ሆነ የ8ኛ ክፍል ፤የጀነራል ፈተና ለማለፍ አማርኛ ማለፍ አለበት። ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባትም ማትሪክ ማለፍ አለበት። ማትሪክ አማርኛ አለበት። ሰዋሰው፤ አንብቦ መረዳት፤ ሰም እና ወርቅ ወዘተ..ወዘተ..የመሳሰሉ ውስብስብ ሐረጎችን፤ አረፍተ ነገሮችን ተንትኖ ማወቅ እና ፈተናውን ማለፍ ይጠይቃል። ስላለፈም አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ገብቶ ተምሯል። ይህንን በመረጃ ከማቅረቤ በፊት፤ ቅርብ ወዳጄ የሆነው ፕሮፌሰር ዶ/ር ተስፋጽዮን መድሃንየ “ይኼ ሰውየ እነኚህ የመሃል ሰዎች ጅሎችን አማርኛ አልችልም ሲል ሲላገጥባቸውና፤ ጅሎቹ በበኩላቸው “ስለ ማይችል እንጂ አማርኛ ጥላቻ ስላለበት አይደለም እያሉ ሲዘባርቁ ሰማህ? ብዬ በስልክ ስጠይቀው፤ ጌታቸው አንተ  ታውቀዋለህ፤ ኢሳየስ የማይፈጥረው ሃሰት ምን አለ ብለህ ነው! እኔ ኢሳት ላይ ቀርቤ በአማርኛ ቃለ መጠይቅ ሲደረግልኝ ‘አማርኛ በመናገሬ’ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ‘አማርኛውን በደምብ ያስኬዱታል’ ብለው አድናቆታቸው ሲገልጹልኝ፤ እኔም “ በእኔ ዕድሜ ክልል ያለ ኤርትራዊ ‘አማርኛ’ የማይችል ሊኖር አይችልም፤ (በተለይ አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የገባ) ብየ መልስ መስጠቴ አስታውሳለሁ ስለዚህ ኢሳያስ አማርኛ መናገር ማይችልበት ምክንያት ምንም የለም?” ሲል አጫውቶኛል።

ከዚህ በመነሳት አማርኛ ቋንቋ አልችልም፤ የሚለን ሃሰተኛው እና የሃሰተኛው ወናፍ የሆኑት ከበሮ ደላቂዎቹ ውሸታቸውን ለማጋለጥ የዛሬ አያድርገው እና (ወደ ፈረንጂና ዘመን አቆጣጠር ሳይለወጡ) ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የኢሳያስ አፈወርቂ የ1962 (ያውም ዓ/ም እና ቀኑ በግእዝ ፊደል የተጻፈ)፤የጀብሃ ታጋይ በነበረበት ወቅት፤ ከጀብሃን የተቀላቀለበት ዘመን/ቀን፤ ስሙ፤የቤትሰቡ ስም፤ የትምህርት ደረጃው፤ እና የሚችላቸው ቋንቋዎችን ጀብሃ በሰጠው መታወቂያ ደብተሩ ውስጥ አማርኛ እንደሚችል እራሱ በሰጠው መረጃ በግልጽ ተጽፎ ታነብባላችሁ። የሚቀጥለው መረጃ ካሁን በፊት ከሌሎቹ መታወቂያዎቹ ጭምር የሚቀጥለው መረጃ ካልረሳችሁት አቅርቤላችሁ እንደነበር ታስታውሱ ይሆናል።

አንድ ፎከታም የግንቦት 7 ጀሌ ለውሸታሞቹ አለቆቹ ጥብቅና ቆሞ፤ ‘ፓል ቶክ ክፍል ውስጥ’ ስለ እኔ ያለ ማስረጃ የግንቦት 7 ውሸታሞችና ኢሳያስን መውቀሴን ሲላፋደድ የሰሙት ወዳጆች ድምፁን ቀድተው ልከውልኛል። ጌታቸው ረዳ ያለ መረጃ አልጽፍም። መረጃየም ከዚህ ቀጥሎ ይኼው! 
The University ID below reads mother's name Adanch. The above Tigringa ELF ID reads mother's name as Adhanet.            

ኢሳያስ አማርኛ ይችላል። አማራ እና አማርኛን ይጠላል።ስለሆነም አማርኛ መናገር የማይፈልግበት ምክንያት ከጥላቻ የመነጨ ነው። መረጃውም ከላይ የምታዩት ፎቶ ከፒ አማርኛ እንደሚችል ያረጋግጣል።መታወቅያው ዩንጉሡ ወይንም የደርግ ሳይሆን፤ የጀብሃ (የተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ) መታወቂያ ነው።
 መረጃው የሚለው ፦
የመጀመሪያ አመት ዩኒቨርሲቲ  ያጠናቀቀ፤ ሥራ “ታጋይ”፤ ጀብሃን የተቀላቀለበት ቀን እና አመት፤ ወታደራዊ ስልጠና የተከታተለባቸው ቦታዎች (ቻይና)፤  መናገር የሚችለው የቋንቋ ችሎታ “ትግርኛ፤እንግሊዝኛ፤ዓረብኛ፤አማርኛ እና ትግረ” 5 ቋንቋዎች ይችላል ይላል፤ ከጀብሃ መታወቂያ ደብተሩ ላይ ያስመዘገበው። እዚህ ላይ ውሸታሙ ማነው? ፍርዱን ለናንተው።
እነኚህ ከሰሜን አካባቢ የራቁ ኢትዮጵያዊያን ስለ ሰሜን ሰዎች (ትግሬዎችና መረብ ምላሽ)፤ በተለይ የመሪዎችን ተንኰልና ታሪክ እንዲሁም ባሕሪ ሳያውቁ “ዘልለው” ለነሱ ጥብቅና ቆመው ሲፈተፍቱ ማየት ሁሌም የሚገርመኝ ነው። ግንቦት 7 ውስጥ ለኢሳያስ ጥብቅና ቆመው የሚከራከሩ ጋዜጠኖቻቸው እና መሪዎቻቸው (አንዳርጋቸው፤ኤፍሬም ማዴቦ ወዘተ…ወዘተ…የመሳሰሉ) እና ዛሬ ለወያኔ ቆመው ጥብቅና የሚያሳዩ ከተለያዩ ጎሳዎች የተወጣጡ ‘ባንዳዎች’ አንድ የሚያደርጋቸው ይህ የሰሜን መሪዎችን ባሕሪ ያለማወቃቸውን ነው።

በመታወቂያው ላይ በጣም የሚገርመው ይህን አስገራሚ የኢሳያስን የማንነት ቀውስ በመታወቂያው ደብተሩ ላይ በግልጽ ሲያምታታ ምን እንደሚል ላሳያችሁ። ይኼውም የናቱን ስም ከአማርኛ ወደ ትግርኛ መለወጡ ነው። እናቱ ወ/ሮ አዳነች ይባላሉ የወ/ሮ መደህን ልጅ ናቸው። እሱ ግን ለአመርኛ ቋንቋ እና የአማራ ጥላቻ ስላለው፤ ከ “አዳነች” ወደ “ኣድሓነት” ለውጦ አስመዝግቦታል። የወንድሙ ስም “አማረ” ነው። አማርኛ ስለሆነበት “አምዓረ” ብሎ ተጽፎ ከላይ ተመዝግቦ የምታዩት ነው። “ዓ” የሚለው አማራዎች የሚያነብቡት እንደ “አ” ነው። ትግርኛ ተናጋሪዎች ግን “ዓ” ን የምናነብበው በላንቃና በጉሮሮ ውስጥ የሚድቦለቦል ልዩ ድምፅ ያለው  ነው። “ዓ” ውሃ ጉሮሮህ ውስጥ አሽከርክርህ አንደምታጉረመርመው  ደምፅ  አለው።  “ዓ” አማርኛ ከሚያነብበው ‘አ’ ፊደል እና ደምፅ ይለያል። ስለሆነም ኢሳያስ የወንድሞቹን ስም ሲያስመዘግብ የታላቅ ወንድሙን ስም “አማረ” የሚለው “አምዓረ” ብሎ ሲያስመዘግብ፤ ‘አማረ’ የሚለው ስም አማርኛ ስለሆነበት ( “የአማራ ስም”) ስለሆነበት “አምዓረ” ብሎ አስመዝግቦታል። “አምዓረ”  በኔው የትግርኛ አተረጓጎም ትርጉም “የማር ለዛ ያለው”  አንደማለት ይደመጣል። ሆኖም  “የማር ለዛ” ብለህ ብትተረጉመውም፤ ‘አማረ’ የሚለው “አማረበት፤ተሽሞነሞነ፤ መጎስ ግርማ ለበሰ” ከሚለው ቀጥተኛ የአማርኛው ትርጉም ጋር አይገናኝም። ስለሆነም ኢሳያስ አፈወርቂ የእናቱን ሰም ብቻ ሳይሆን የለወጠው ፤የታላቅ ወንድሙንም ስም ከአማርኛ ወደ እራሱ ፈጠራ የሆነ ትግርኛ ፈጠራ ለውጦ “ኣምዓረ” ብሎ አስመዝግቦታል።

ለምን የሚለው ጥያቄ፤ መልሱ ሁለት ነው። አንደኛው መልስ “አማርኛ እና አማራን” ስለሚጠላ የአማርኛ ስም ከናቱ ጀምሮ እስከ ወንድሙ ድረስ ያለው ስም ወደ ትግርኛ ቀይሮታል።

ሁለተኛው መልስ፤ ይህ የማንነት ቀውስ ኢሳያስን በደምብ እንዳጠቃው መገንዘብ ትችላላችሁ። የኢሳያስ አፈወርቂ ወላጆች ከአፄ ዮሐንስ ደም እና አጥንት የተወለዱ ታላላቅ የትግራይ ባላባቶች እና ባለስልጣኖች የተወለዱ እናቱም አባቱም ትግሬዎች ናቸው። ይህ ደግሞ ካሁን በፊት ዝርዝሩን በራሴው በ Ethiopian Semay ድረገጽ ላይ ከጥቂት አመታት በፊት የለጠፍኩት የዘር ሓረግ አለ፤ እሱን ተመልከቱ። ስለሆነም ዓጋሜ/ትግሬ ነው እንዳይሉት ሆን ብሎ ያደረገው የማንንት ቀውስ የፈጠረው መሆኑኑንም በሌላ በኩል ትገነዘባለችሁ።

ይህ የትልቅ ሰው ዘር፤ ጀብሃን ሲቀላቀል፤ እራሱን ደብቆ ብቻ ሳይሆን ለአማርኛ ጥላቻውም ወሰን እንዳልነበረው ያሳያል። ያቺው ጥላቻውም እስካሁን ድረስ መሪ ሆኖ እያለም ቀጥሎበታል። “ኣዳነችን” ወደ “ኣድሓነት”፤ “አማረን” ወደ “ኣምዓረ” የሰየመ ባሕሪ ‘እውነት’ ይናገራል ብለው ለኢሳያስ ጥብቅና የቆሙ ሰዎች/ ባንዳዎች፤ መጀመሪያ የቆሙለትን ቀጣሪያቸው ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ፤ማጥናት ይጠበቅባቸዋል። ካልሆነ መሳቂያና ማፈሪያዎች ሆናችሁ እኔ የምለጋችሁ “ኳሶቼ” ሆናችሁ እስከመቸ ድረስ አንደምትዘልቁ ለኔም ገርሞኛልና፤ እባካችሁ በማታወቁት ገብታችሁ አትፈትፍቱ። ከ “አዳነች” ወደ “ኣድሓነት” ከ “አማረ” ወደ “ኣምዓረ” አስመራ ውስጥ ዘኢትነገር የት ነው? ክፍል 3 ይቀጥላል። አመሰግናለሁ! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ።getachre@aol.com