Wednesday, March 2, 2016

ትግሬዎች “እኔም ወልቃይቴ ነኝ!” እያሉ የወያኔ ወረራ በማውገዝ ለታሪክ ያስመዝግቡ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)ትግሬዎች “እኔም ወልቃይቴ ነኝ!” እያሉ የወያኔ ወረራ በማውገዝ ለታሪክ ያስመዝግቡ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
Prince Mengesha Seyum Ethiopian Semay weblog
በርዕሱ የተመለከተ ማሳሰቢያ ግልጽ ላድርግ። በቁጥር 8 የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ባለፈው ወር “እኔ ኦሮሞ ነኝ” የሚል በፌርማቸው ያረጋገጡት ለኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ድጋፍ መለጋሰቸው ይታወሳል። ድጋፍ መለገሳቸው እንዳልተቃወምኩ፤ ነገር ግን አማራ ሲጠቃ ተመሳሳይ ‘ፌርማን ያሰባሰበ’ ድጋፍ ባለመስጠታቸው ‘ቅሬታ መግለጼ’ ባለፉት ጽሑፎቼ ያነበባችሁት ነው። ሰሞኑን በወልቃይት አማራ ላይ የትግሬ የበላይነት የተረጋገጠበት አሰራር ትክክል እንዳልሆነ በልዑል ራስ መንገሻ አማካኝነት የተሰጠው ምስክርነት ይፋ በመሆኑ፤‘እኔም ኦሮሞ ነኝ” ብለው የነገሩን ትግሬዎች ፤ ዛሬ ‘በስማቸው’ በአማራ ወልቃይት እና በመሳሰሉት አማራዎች’ እየተፈጸመ ስላለው የትግራይ ፋሺስቶች የበላይነት እርምጃ ማውገዝ ስለሚገባቸው “እኔም ወልቃይቴ ነኝ ብለው ድጋፋቸው ይስጡ” የምለው ምክንያት ለዚህ ነው። ማሳሰቢያው ለነዚህ ወንድሞችና እህት ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለማላው የትግሬ ተወላጅ የሚመለከት ጥሪ ነው።

ይህንን ግልጽ ካደረግኩኝ በሗላ፤ “የትግራይ ፋሺዝም እና የትግራይ የበላይነት’ በተንሰራፋባት ሃገረ ኢትዮጵያ ደህና መሆን የለምና፤ብቻ ለነገሩ “አማን ሰነበታችሁ? ብዬ ሐተታየን ልጀምር።

ሰሞኑን የራስ ሥዩም መንገሻ ልጅ የሆኑ፤ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም “ፋሺዝሞ ወያነ ትግራይ” ጠመንጃ ደግኖ የወልቃይቴዎች መሬት ነጥቆ ለሥልጣን ያበቃኝ የትግሬ ሕዝብ ነው ለሚለው ለትግሬዎች የሰጠው የወልቃይት መሬት እሳቸው እስከሚያውቁት ድረስ “ወልቃይት የጎንደር እንጂ በትግሬ መስተዳድር ሥር ሆኖ አያውቅም” በማለት ሰሞኑን በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ ክ/ጊዜ ከጋዜጠኛው “መለስካቸው አማሃ” ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቃላቸውን ሰጥተዋል። የወያኔ ተከታዮች “ወልቃይት የጎንደር እንጂ በትግሬ መስተዳድር ሥር ሆኖ አያውቅም” ማለት ወደ ጎንደር ተዛውሮ በጎንደር መስተዳድር ነበር ማለት እንጂ ድሮ የትግሬ መሬት አልነበረም ማለታቸው አይደለም” ሲሉ ምስክርነቱን ለማጣጣል ሞክረዋል። “ወልቃይት በጎንደር እንጂ በትግሬ መስተዳድር ሥር ሆኖ አያውቅም” ማለት “ወልቃይት በጎንደር ሥር እንጂ የትግሬ ሆኖ አያውቅም” ማለት ነው!  ይህ ደግሞ፤ ልዑሉ እስከሚያውቁት የታሪክም ሆነ እሳቸው ባስተዳደሩበት ወቅት ወልቃይት ከቶውንም የትግሬ መሬት ሆኖ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ማለት ነው። አይገባችሁም አማርኛው?  

በኔ በኩል እንደትግሬነቴ የምለው ነገር ካለ ፤ አምናም፤ ታች አምናም ዛሬም፤ ነገም ወልቃይት ለትግሬዎች የመሰጠቱ ጉዳይ ሕጋዊነት እንደሌለው ደጋግሜ ጽፌአለሁ።ታስተውሱ እንደሆነ ኦሮሞዎችና ትግሬዎች በጉልበት፤ በሴራ፤ ሰፋፊ ለም መሬቶችና አካባቢዎች ወደ ክልላቸው በማጠቃለላቸው “የኦሮሞ እና የትግሬ ሄጂመኒ” ብየ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መጻፌ ታስታውሳላችሁ።
በጣም እኮ ግልጽ ነው! የትግሬዎች ኖሮ ቢሆንስ፤ በጠመንጃ አስገድደህ በአመጽ ሕዝብንና መሬትን በጉዳዩ ላይ ሳያማክር ትግሬነህ እና ወደ ትግሬ ትቀላቅላለህ ብለህ ማስገደድ እንዴት ይሆናል? ወያኔ ይህ አመጽ የቀየሰው ጫካ ሆኖ ነው። ሥልጣን ሲይዝ ትግባራዊ አደረገው። ይህ ምን ማለት ነው? ኦነጎችም ጫካ ላይ ሆነው የቀየሱት “የአፓርታይድ ፕሮግራም” ወያኔን አስፈቅደውና ወያኔን አጋር አድርገው ተግባራዊ አድርገው ይኼው አገሪቱ ለብጥብጥና ለጥላቻ አበቋት።

ኦሮሞዎችም በተቀበሉት “የአፓርታይድ አስተዳደር” ሰበብ ለሞትና ለብጥብጥ ተዳርገዋል። ብሔራዊ አማርኛ ቋንቋ ጠልተው አማርኛ ላለመናገር “ኦሮምኛ በላቲን ፊደል” እየጻፉ፤ ከተቀረው ሕዝብ ጋር መነጋጋር ስላልቻሉ “መገበያቱና አብሮ ተዘዋውሮ ባገሪቱ መሬት ሥራ መስራቱ “ከፍተኛ ጋሬጣ ሆኖባቸዋል” ለወደፊቱም ከፍተኛ ችግር ከፊት ለፊታቸው ተደቅኗል። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያ የወያኔና የኦነግ አፓርታይድ ፖሊሲ ሰለባ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ችግር ውስጥ ይገባል።

ትግሬዎች “በሄጂመኒ ጉልበት” ወልቃይቴዎችን አስገብረው ብቻ ሳይሆን አምጸዋቸዋል።ትግሬዎች ወደ ሥፍራው እየሄዱ ለሸቅልና ለም መሬት ፍለጋ፤ እንዲሁም በጋብቻ ምክንያት ከኗሪው ተደበላልቀው የኖሩበት እንጂ ‘ወልቃይት’ እንኳን በዘመናችን ቀርቶ፤ በዘመነ አክሱም እንኳ “ሃዳኒ ዳኒኤል” የተባለው አክሱማዊ ገዢ ‘ወልቃይቴዎች’ አልገዛም ብለውት ልክ እንደ ‘ቤጃዎች’ ያስቸግሩት ስለነበር እራሱ ወደ ዘመቻው ሄዶ ተካፍሎ አልሆን ብሎት ብዙ ጊዜ የወረራ ሙከራ ማድረጉ ሩስያዊው Yuri M.Kobishchanov (AXUM) በሚለው መጽሐፉ አስቀምጦታል። ይህ መጽሐፍ በጣም የቆየ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ ክለሳ ተደርጎለት ታትሟል። እሱን አላነበብኩትም፤ ደራሲው ምናልባት ወያኔ እጁን አስገብቶበት ያልሆነ ‘የብረዛ ታሪክ’ አሳስቶት ሊሆን ሰለሚችል፤የቆየውን እትም አንብቡት።

 ይህ ጉዳይ በየመድረኩ የሰሞኑ ትኩስ ዜና ሆኖ እየተመዘገበ፤ እያነጋገረ ነው። አሜን! ለወዲ ላሕምና ብያለሁ። ‘ወዲ ላሕምና’ ደግሞ ምንድነው እንዳትሉ፤ከወዲሁ ትርጉሙን ልግለጽ። “ወዲ” ማለት “የእገሌ ልጅ” ማለት ሲሆን “ላሕምና” ማለት ደግሞ “ላሜ ቦራ” ማለት ነው። ካልተሳሳትኩ ስተረጉም፤ ላሜቦራ ማለት የሁሉም በሬዎችና ላሞች አንጋፋ ‘እናት ላም’ ማለት ይመስለኛል። ልዑሉ የተገኙት ከራሥ ሥዩም እና ከዚያም ከዮሓንስ ዘር ስለሆኑ የትግራይ ሕዝብ የሚያያቸው እንደ ‘ላሜ ቦራ’ ልጅነታቸው በመሆኑ “ወዲ ላሕምና” ተብለው በቁልምጫ ይጠራሉ።  

ካሁን በፊት ልዑሉ በወያኔ ደጋፊ ‘ፓልቶክ’ ክፍሎች ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ‘“የትግራይ ጋንግስተር ፋሺስት ወያኔዎችን” የማሽሞንሞን ባሕሪ እየታዘብኩባቸው መሄዴን አስቀይመውኝ እንደነበር ሁሉ (ይህ በእሳቸው የተወሰነ ሳይሆን ብዙዎቹ የጃንሆይ የልጅ ልጆች ሁሉ በሚያሳፍር ባሕሪ ከወያኔ ጋር ሲሽኾረመሙ ማየታችን አዲስ አልነበረም። ቢሆንም ጥንታዊ ፊውዳሊዝም እና ዘመናዊ የትግሬዎች መስፍናዊ ግዛት አብሮ ስለሚሄዱ ጉዳይ አያስገርምም) ሰሞኑን ግን ልዑሉ “የወያኔዎችን ዘረኛ ምላስ እንዲንጣጣ” ምክንያት መሆናቸው አስደስተውኛል።

ዘርኡ ሓጎስ እያለ እራሱን የሚጠራው “የወያኔው ዓይጋ ድረገጽ” ስለ ሉዑሉ እንዲህ ሲል ጽፏል፦” I could not fathom why leul chose to speak on this issue this time! What good outcome was he expecting from his witnessing?” ይላል።
  “ገንዘብ ናብ ዋናኡ፤
አንጭዋ ኣብ ኳናኡ”

 እንላለን እኛ ትግሬዎች፦ ትርጉም
  “አይጡ ወደ አጥሩ፤
  ንብረቱ ወደ ባለቤቱ”
እንደ ማለት ነው። በቋንቋ፤በትውልድ፤ በነገድ፤ በአጥንት ከልሎ ማስተዳዳርን “እንደ ወንጀል” የማያዩት የወያኔ ናዚ አስተዳደር ተከታዮች፤ የሰሞኑን የልዑሉ ጥልቀት ያለው ምስክርነት ለምን እንዳንጣጣቸው ግልጽ ነው። በትግሬዎች ነገድ የበላይነት/Tigrayan racial supremacy” መሬቱ የተነጠቀው የወልቃይት ሕዝብ፤ መሬቱ በትግሬዎች መነጠቁ ብቻ አይደለም አሳሳቢነቱ ፤ በወልቃይት አማራ እና በውስጡ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ነገዶች በወያኔ Biological State (የዘር መንግሥት)  የተደረገው የracial hygieyene የዘር/ማጥራት ወንጀል በላያቸው ላይ እየተፈጸመ እያለ መሆኑን በጥሞና ስንመረምረው ፤ ወደ ሗላ ትውስታ የሚወስደን የጀርመን ናዚዎችን ታሪክ ነው።

የወልቃይት አማራ ወንዶች እየተገደሉ፤እየታፈኑ የወልቃይት ሴቶች “በትግሬ ወንዶች” እየታመጹ አዲስ የትግሬ ትውልድ በወልቃይት መሬት እንዲባዛ እንደተደረገ ወልቃይቴዎች እራሳቸው በተደጋጋሚ በሕዝብ መገናኛ መስመሮች እየተጋበዙ በሚያደርጓቸው ቃለ መጠይቆችና የጽሑፍ ማስረጃዎች የተገለጸ ነገር ነው። ለምሳሌ ይህንን መረጃ ይመልከቱ፤-

Government carries out secret mass sterilization among Amhara women https://youtu.be/2iRwEudb3NM

ያ ብቻ ሳይሆን ‘ወልቃይት አማራ ሴቶች “እንዳይወልዱ ማሕጸናቸው የሚያደርቅ መድሃኒት” ይሰጡ እንደነበር ለአማራ ሕልውና የቆሙ ሰብአዊ ነክ ጠበቃዎች/ሲቪክ ማሕበሮችና ከወልቃይት የተወለዱ ግለሰቦች በመረጃ አቅርበውታል። ይህ ደግሞ ከላይ የቀረበው በጎጃም አማራ ሴት እህቶቻችን መርዛማ መርፌ እየተወጉ እንዳይወልዱ እንደተፈጸመ የሚያሳይ በቪዲዮ ያየነው ታሪክ በወልቃይት አመራዎችም ተፈጽሟል።

ሰሞኑን ልዑሉ የወልቃይት መሬት አስተዳዳሩ በጎንደር እንጂ በትግሬ ሆኖ አያውቅም ማለታቸው ብቻ ሳይሆን፤ በአካባቢው ሲኖሩ የነበሩ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ትግሬዎች ለሸቅል/ለእርሻ የሄዱ ናቸው ማለታቸው እኛም የምናውቀው ታሪክ ነው። አንዳንዱ ሑመራ ውስጥ ሄዶ  የናጠጠ ሃብት አካብቶ በሺዎቹ የሚቆጠር የሰሊጥ እርሻ ሰራተኛ ይቀጥር ነበር (ለምሳሌ “ተስፋይ ዓድዋ” የተባሉት ዓድዋ ሰው) በጣም የሚገርመው ደግሞ በአካባቢው ሲኖሩ የነበሩ ትግሬዎች ብዛት ስንት እንደነበር በአካባቢው አስተዳዳሪ እና አካባቢው አስተዳዳሪና ተወላጅ የሆኑት ቢትወደድ አዳነ እና በልዑሉ ራስ መንገሻ ሥዩም መካከል የተደረገው ንግግር ስንት ትግሬ እንደነበር ጠቅሰዋል። ይህ ሃቅ የወልቃይት አማራ ተወላጆች የትግሬዎች እንዳልሆኑ ይጠቁማል።

ትግሬዎች እንዳልሆኑ በዚህ መረጃ ተመልከቱ፡

Wolqait and Tigray expansion https://youtu.be/i2iKJSHKDEM

እዚህ ቪዲዮ ላይ በግልጽ እንደምትሰሙት፤ “ወድደን ሳይሆን ሳንፈቅድ ‘በግድ ተገድደን’ ትግሬዎች እንድንሆን ወደ ትግሬ አስተዳዳር ተጨምረን፤ቋንቋችን ባሕላችን ትግሬና ትግርኛ እንዲሆን ተደርገናል።’ ነው የሚሉት። እዚህ ላይ የምንረዳው ነገር፤ አስር ጊዜ በየጽሑፎቼ የምጠቅሰው ‘ፋሺዝም’ ኢትዮጵያን “እያሰተዳዳረ ነው!” ስላችሁ የነበረው፤ በዚህ ቪዲዮ በግልጽ መረጃው ማየት ትችላላችሁ። “የትግሬ ሄጀመኒ” ስላችሁ የነበረው፤ ‘አፍሪካም ሌላ ዓለምም ‘ፋሺስቶችና ኮሎኒያሊስቶች’ የሌላ ሕዝብ እና የሌላ ማሕበረሰብ ስነ ልቦና እና መኖሪያ በጉልበት ነጥቀው ለራሱ ነገድ/ዘር/አካባቢ መጠቀሚያ እንዲውል ሲያደርጉት የነበረውን እጅግ ዘግናኝ አረሙኔአዊ ባሕሪ ማለት ይኼ ነው። እንዲህ ያለ አስነዋሪ “ባርባሪዝም/አረመኔነት” በትግሬዎች የበላይነት ሲፈጸም፤ ትግሬነቴን እንደዛሬ ያስጠላኝ ነገር የለም የምላችሁም በዚህ በወያኔዎች ፋሺስታዊ ስነ ምግባር ምከንያት ነው።

ይህ በጣም ሰፊ የሆነ የወልቃይቶች ‘ለም’ መሬት ዛሬ ለትግሬዎች እና ለወያኔ ታጋዮች ሕይወት ግንባታ እንዲውል ለምን እንደታቀደ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው። ይህ መሬት ብቻ ሳይሆን “ዓሰብ ወደብም” የወያኔ አመራሮች ባዘጋጁት ካርታ ላይ፤  ግን ቆይተው በሗላ የሸሸጉት ‘አዲስ ካርታ’ ተቀርፆ ታትሞ እንደነበር ይታወቃል። ለምን እንዲህ እንደሆነ በውስጡ የነበሩ ታጋዮች ምስክርነታቸው ሲሰጡ፤

“የትግራይ ሪፓብሊክ’ ለመመስረት ያመቻቸው ዘንድ ሦስት መሰረታዊ ነገሮችን ያስፈልጋቸው ነበር፦ ‘በወያኔ ስነ ልቦና የታነጸ ሕዝብ፤ የለማ መሬት እና የባሕር ወደብ”። ከሞላ ጎደል ሁለቱን ሲያጠናቅቁ፤ ሦስተኛው ግብ ግን፤ በችኮላ ወደ ኢትዮጵያ ቢጨምሩት፤ ድንገት ሥልጣናቸው ጥያቄ ውስጥ ቢገባ፤ ተገንጥለው ለመሄድ ሲያስቡ “ዓሰብ” ኢትዮጵያ ሆኖ እንዳይቀር፤ ስላሳሰባቸው፤ በወቅቱ ከኤርትራኖች በነበራቸው ምስጢራዊና ይፋዊ ግንኙነት “ትግራይ ትግርኚ” ምስረታ ዓላማ ሲከናወን የባሕር ወደብ ችግር ስለማይኖር፤ ዓሰብ በኤርትራ ሥር ቢቆይ ይሻላል ብለው ‘ዓሰብን ያካተተው አዲሱን ካርታ” በይደር እንዳቆዩት ይታመናል።ለዚህ ነው ኤርትራን ለማስቀየም/ለመውጋት/ለመጋፈጥ የማይፈቅዱት።ለዚህ ነው ኢሳያስ ትገሬዎነችን በተደጋጋሚ እያፈነ ወደ ‘ድምህት’ እና ወደ እርሻ ሥራ በባርነት ሲያሸቅላቸው፤ አንደልቡ እንዲጨፍር እየፈቀዱለት የምናየው። ለዚህ ነው ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንድትቀላቀል ፍላጎት የማያሳዩት። “ሪዘርቭ ሃውስ” ፤ተጠባባቂ መኖርያ፤ ማለት ነው “መሸሸሸጊያ/ማምለጫ”!

ዘርኡ ሓጎስ እያለ በብዕር ስም እራሱን የሚጠራ፤ ‘በኦባንግ ሜቶ ጥቁርነት እና በኦባማ ‘ኔገር’ አስተዳዳር’ ብሎ በድረገጹ ያሾፈ፤ በዘረኛነት ባሕሪው የሚጠቀሰው የዓይጋው ድረገጽ ባለቤት Short commentary on VOA Amharic and Leul Mengesha Seyoum በሚለው የሳምነቱ ርዕሰ አንቀጹ ላይ 

Many people think VOA Amharic is on a mission to tarnish EPRDF government.  I could not agree more! How else do you explain VOA Amahric selective news coverage of issues? Did they cover the Qimant issue in Amhara Kilil like they covered the Tsegede/Wolqayit issue?” 

ሲል ልዑሉ የሰጡት ምስክርነት ብቻ ሳይሆን ፤ ቪኦኤንም ጭምር ለመውቀስ ሞክሯል።

‘ቪ ኦ ኤ’ የቅማንት ማሕበረሰብ በአማራዎች ላይ መጨቆኑ ለምን አልወረፈም ሲል “አማራ የሚባል ዛሬም እንደ ዘርኡ ሓጎስ የመሳሰሉ “ዘረኞች” በአማራ ላይ ያላባራ ጥላቻቸው በግልጽ መረዳት እንችላለን። ቪ ኦ ኤን “Are the VOA-Amharic journalist ignorant?” ሲል “ጋዜጣዊ ግብዝነታቸውን ለመክሰስ ሲዳዳው፤ የራሱ ግብዝነት ሊገባው አልቻለም እንጂ ፤ አመራዎችም ሆኑ ቅማንቶች የሚሉትን ይህ ማሕደር ቢያደምጠው ቢረዳው ፤ የቅማንት ሕዝብ ማንን እየከሰሰ እንዳለ ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ይመልከት እና በዘረኝነት የተበላሸው ሕሊናው ይህ ተገንዝቦ ሁኔታው ቢገባው ይህነን ልጋብዘው

kimant - woyane braking bridge between people. https://youtu.be/rt9ZNRtYZQM

ይህ የቅማንት ማሕበረሰብ በወያኔ አማራ ክልል ባለሥልጣኖች ላይ ምን እያለ ነው? ከላይ የምታዩት ተናጋሪ የቅማንት ነገድ “ከወያኔ ሹማምንት ፊት ለፊት ቆሞ የተናገረውን ልጥቀስ፦

“እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች አማራና ቅማንት ተጋብቶ ተዋልዶ ነው ያለው።ከማንኛው ብሔር ብሔረሰብ ተዋልደናል። ነገር ግን እንድንኖር የአማራ ክልል መንግሥት አይፈልግም። የፌደራል መንግሥት በሚችለው አግባብ በተሎ ፈጥኖ ይመልስልን።ሥረተን እንብላ፤ ልጆቻችን እናስድግ፤ የታሰሩትም ይፈቱልን!”

ይላል አንዱ ተናጋሪ፤

ሌላው ተናጋሪ ደግሞ ጠመንጃውን በማሳየት “

በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን ጠምንጃ የምንይዝበት ዘመን አልነበረም፤ ሆኖም አለመታደል ሆኖ… ቅማንት እየተገዛ ያለው እኮ በኢትዮጵያ መሬት “ይሓዴግ” እየመራ ያለው ሃያ ምናምን አመት ነው። …..፤ የአንዱን እየነጠቀ ለሌላው እየሰጠ፤  ሲያጋድል የቆየ ቡድን አለ፤ “የአማራ መንግሥት! (የሚባል)። የአማራ መንግሥት ጣልቃ ሳይገባ እናንተ ልዑካን ሕዝብ የሚለውን አስፈጽሙልን”

ሲሉ ነገድ ለነገድ ለማበጣበጥ ወያኔ የሾማቸው አሽከሮቹ ላይ እንዲህ ያለ ስሞታ ያስተጋባሉ።

 ቅማንቶች “በናዚ ቅኝት” ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ‘የወያኔ ትግራይ ስርዓት እና ወኪሎቹን” እንዲህ እየከሰሱትና እየተቃወሙት እንዳለ እየታወቀ፤ የዓይጋው ድረገጽ ‘ዘርኡ ሓጎስ’- ‘ቪ ኦ ኤን’ ኢግኖራንት በማለት ጋዜጠኛነታቸውን በማሳነስ ‘የወልቃይት አማራዎች እሮሮ ከሚያስደምጠን ይልቅ በቅማንት እና በአማራ መካካል የተከሰተው ሁኔታ መናገር በቀለለው ነበር ሲል፤ በቪ ኦ ኤ ላይ የተሰማው ስሞታ አስነብቦናል።

ይህን ልጨምርለትና ወደ ሌላ እናምራ።

Ethiopia; Wolkit Tegede is Gonder not Tigri https://youtu.be/1ov5s4PziPo

ምስኪኑ ዘርኡ ሓጎስቪኦኤን’ ሲቃወም፤ የጎንደር ሕዝብ ስለ አንድነቱ ሃይመኖቱ እና ስለ  ሰንደቃላማውስ በፋሺስት ወያኔ ላይ እያቀረበው ያለውን እሮሮና ብልሹነት ምን እያሉት እንደሆነ እስኪ ዘርኡ ሓጎስን ይህንን ልጋብዘው

 Gondar Protest With real Ethiopian flag https://youtu.be/G2pgk1FcdK0

በዚህ ቪዲዮ የምታዩት “የጠመንጃ ታጣቂ ብዛት” Gondar set to respond to repeated TPLF massacre in the region https://youtu.be/LkqR7fsAVrs 

ይለያል! ይለያል! ይለያል ዘንድሮ!” የሚለው የጎንደሬዎች እምቢተኛነት በዚህ ቪዲዮ ማንን እየከሰሱ እንደሆነ ‘ዘርኡ’ ማወቅ ይገበዋል።

ይህ ሁሉ “ወያኔዎች እንደሚሉት’ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው? መብት የሚጠይቅ ሁሉ ትርጉመ ቢስ የሆነ የኮሚኒሰት ቃላት የትም ቦታ እየሰነጠሩ “ኪራይ ሰብሳቢ” እያሉ ‘የሚያቅለሸልሹ’ ኮሚኒስታዊ ቃላት እየተጠቀሙ መስማት እውነት የእነዚህ ፋሺስቶች የትምህርት ብቃት ዛሬም በጫካ ዘመን በነበሩበት ሕሊናቸው እዛው ላይ እንደሆኑ ያሳያል።

እጅግ የሚገርመው ደግሞ አማራ እንጂ ትግሬዎች አይደለንም ብለው መብታቸው የጠየቁ አማራ ወልቃይቴዎችን ለመቃወም እንዲያመቸው ፋሽስታዊው ወያነ ትግራይ “ትግሬዎች እንጂ አማራዎች” አይደለንም ብላችሁ ተከራከሩ ብሎ የሰበሰባቸው “ቄሱ፤ተማሪው፤ሴቱ” ሁሉ፤ አብዛኛዎቹ ወልቃይት ላይ ያሰፈራቸው የድሮ ታጋዮች ሲሆኑ፤ ተቃዋሚዎቻቸውን ለማውገዝ ሲጠቀሙባቸው የነበሩት ቃላቶች ከወያኔ አመራር የተላለፈለቻው “ኪራይ ሰብሳቢ” የሚለው ቃል እና “የማያዳግም አርምጃ” እያለ ሲደገምና ሲደጋግም መስማት “ኮሚኒስታዊ የጫካ መፈክር” ዛሬም ያለ ሐፍረት ያንኑ ኮሚኒስታዊ መፈክር መከተላቸው እጅግ ይደንቃል። 

 ‘ዓባይ ወልዱ’ የተባለው ፋሺስታዊ ተልዕኮ እንዲያከናውን ‘በመለስ ዜናዊ’ የተመረጠ ግለሰብ (ድሮ ገና ወጣት ተማሪ እያለ ባንድ ከተማ ስናድግ ስለማውቀው የትግሬ ሕዝብ በእነዚህ ግለሰቦች ሥር ሲተዳደር እጅግ ያሳዝናል) የተመራው የወያኔዎች የዘር ጽዳት ዘመቻ (racial hygieyene) በወልቃይትና አካባቢው የሰፈሩት በሺዎቹ የሚቆጠሩ የትግሬ ወያኔ ታጋዮችን ሰብስቦ በአማራ ወልቃይቶች የስደብና የህይወት ማስፈራራት ዛቻ እና መፈክር ሲደመጥ፤ በሌላ በኩል “መሬታቻው እና ማንነታቸው የተነጠቁት የወልቃይት አማራዎች እንዲህ ይላሉ፤-

 “አማርኛ የምንናገረው እኮ፤ እንደ ‘ሲም ካርድ’ እየሞላን አይደለም አማርኛ የምንናገረው፤በውስጣችን በሥጋችን፤ በደማችን፤ በዘራችን ሁሉ የመጣ ቋንቋ፤የመጣ ስነልቦና፤ የመጣ ህይወትና ኑሯችን ነው። ይኼ አይደለም የሚለን የሚሞግተን አካል ካለ፤ አስገድዶን ያጎረሰን እንጀራ ነውና ያስታውከናል!”   

በማለት የማንነታቸው ሁኔታ በጉልበት ተነጥቆ “የትግሬ ማንነት” እንዲይዙ መደረጉ ፋሺስታዊ መሆኑን በግልጽ ተቃውመውታል። ይህንን እሮሮ በሚያስሰሙት ወልቃይቶች ላይ የማያዳግም ፋሺስታዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ታጋዮቹን ሰብስቦ “በእጅ ብልጫ/mob rule/ እጃቸው እያነሱ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
 ይህ ዘገባ ደግሞ “አገርህ የት ነው? ብለው ቢጠይቁህ “ትግሬ” ነው ብለህ ንገራቸው” የሚለው “ሻዕቢያዎች አገርህ የት ነው? ብለው ቢጠይቁህ “ኤርትራ” ነው ብለህ ንገራቸው” ብለው ሲዘፍኑት የነበረው “ቅዠታዊ ማንነት”፤ወያኔዎች ያንን ትክክለኛ ቅጅ ቀድተው ‘አገርህ የት ነው ቢሉህ ‘ትግሬ’ ነው፤ ብለህ ንገራቸው፤ የሚል “የወያኔ ሱፕረማሲያዊ የማንነት ቅዠት” የሚያስተጋባ ዘፈን እያሳጀቡ ነበር አውድዮው እና ቪዲዮውን ለሕዝብ ያስተላለፉት።   

ከላይ በቪዲዮ እንድታደምጡት የሰጠሁዋችሁ ‘እሮሮዎች’ ወልቃይቴዎች የመናገር ነፃነታቸው “በፋሺስታዊ የትግሬ ዘር የበላይነት/Tigrayan racial supremacy” እንዴት ታፍኖ እንዳለ እንድተረዱት በሚል ነው። ቪዲዮዎች አጫጭሮች ስለሆኑ እጅግ ጠቃሚ መረጃዎች ይዘዋልና ጊዜ ወስዳችሁ አድመጧቸው።-
አጅግ የሚገርመኝ ግን፤ ወያኔዎች በምንም መልኩ ወልቃይት የሚባል አካባቢ በየተኛውንም ዘመን እኛ ኢትዮጵያዊያን የምናውቃቸው በውጭም አገር ውስጥም የተሰሩ ካርታዎች “ወልቃይት” ትግሬን ያካተተ ካርታ ጭራሽ አይገኝም። በአህመድ ግራኝም ሆነ በጣሊያን፤ እና በመሳሰሉት ‘የመከራ ዘመናት’ ሁሉ፤ አከባቢው ሲያስተዳድሩ የነበሩ መኳንንት፤ታላላቅ አርበኞች ሁሉ ትግሬዎች ሳይሆኑ አማርኛ ተናጋሪ አማራ ወልቃይቶች ናቸው። 

ከወልቃይት ተነስቶ ጣሊያንም ሆነ ማንም ወራሪ ሃይል ለመመከት፤ ወልቃይት/አርማጨሆ መሰረት ያደረገ የትግሬ አርበኛ በታሪክ አንብቤ አለውቅም። እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በጋብቻ ተሳስሮ ሲኖር የነበረ ትግሬ ሊኖሩ ካልሆነ በቀር፤ ‘ወልቃይት መሰረቱ አድርጎ ‘ስመ ጥር’ የሆነ የትግሬ ሽፍታ፤አርበኛ፤መስፍን፤መኮንን’ ከቶ ተፈልጎ አይገኝም።

 ወያኔዎች ኢትዮጵያን ከተቆጣጠሩ በሗላ “ሰነድ እየበረዙ ፤እየደለዙ፤እየቀደዱ፤የወንዝ ስም፤አርበኛ ስም፤የተራራ ስም፤የከተማ ስም…” እየለወጡ ካልሆነ በቀር፤ በታሪክ የሚገኝ ወልቃይትን ወደ ትግሬ ያካተተ ካርታ የለም። አንዳንዱ ተሟጋች ወልቃይት ውስጥ የትግረኛ ስም አለበትና የትግሬዎች ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ለዚያ የተለየ ሌላ ምክንያት ቢኖሮውም፤ በስም እማ ከሆነ ‘አብደልራፊ’ የሚለው መሬት የሱዳን ነው ልንል ነው ማለት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ እስላሞች “ሰላም አሊኩም” ብለው ስለሚሉ ዓረቦች ናቸው ማለት አይደለም። 

(እነ ታጋይ ታማኝ በየነ  “ሰላም አሊኩም” እያሉ እያጠናከሩላቸው አስቸጋሪ ሆኖ እየመጣ አስቸገረ እንጂ፤ እንዲያ ያለ ለሐበሻ አይመችምና ያ ተለምዶ እስላም ወንድሞቻችን ቢያስቡበት ግን ደስ ባለኝ ነበር።ከእኛው ጋር አይሄድም፤ አያምርም፤ ቋንቋ፡ባልታጣበት አገርና ኩሩ ዘር! )

 ወልቃይት ያሉት ኗሪዎችም “ዓረብኛ፤ትግርኛ እና አማርኛ” ይናገራሉ። ዓረብኛው የሚናገሩት ወደ ሱዳን ብዙ ጊዜ ለገበያ፤ለሸቀጥ ስለሚመላለሱ፤ መናገሩን ችለውበታል። ሁለቱም ቋንቋዎች ለመገበያያ ሲጠቀሙባቸው፤ አማርኛ ግን የኗሪው ዋነኛ መሰረታዊ ቋንቋ እንደሆነ እራሳቸው ናሪዎቹ ይነግሩናል።
አንዳንድ ትግሬዎች በፓልቶክ ሲናገሩ የዓጋሜው ራስ ሱሑል ሚካኤል ጎንደርን ያስተዳድሩ ነበርና ወልቃይትም የትግሬ ነው የሚሉ ገራገር ‘ትግሬዎች’ አድምጫለሁ። ዮሐንስም ‘ሸዋን፤ጎንደርን ጎጃምን ወሎን….መላዋ ኢትዮጵያ እራሰቸውም ሆነ በወኪሎቻቸው ሲየስተዳድሩዋቸው የነበሩት ግዛቶች ሁሉ “የትግሬ መሬት” ነውና መላዋ ኢትዮጵያ “ትግሬ” መባል አለባት ሊሉን ከሆነ፤ ያው ምን አለፋቸው! ዛሬ ትገሬዎች መላዋ ኢትዮጵያ ተቆጣጥረዋታል አይደል? “የነገድ ፉደራል መሳፍንቶቻቸው” በየክልሉ ግዛታቸው እየሾሙ አስቀምጠዋል አይደል/!!!  እንዲያ ከሆነ እማ፤ ራስ ውቤም ትግሬን ያስተዳድሩ ነበርና ‘የዛሬቷ ትግራይ’ ተጠቃልላ ወደ ጎንደር ወይንም ወደ አገው አስተዳደር ትሂዳ! እንዴት ነው ነገሩ?! 
 የሆኖ ሆኖ፤
“ኣይንደልን ጓና
 ናዓየ ወዲ ላሕምና’

ተብሎ በእንደርታዎች የተዘፈነላቸው ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም፤ ወያኔዎች ባልጠበቁት ወቅት የወልቃይት ግዛት ማንነት እና እንዲሁም ብዛት እና እዛው የነበሩ ‘ትግሬዎች’ ወልቃይት እና ሑመራ ድረስ ‘ምን ሊያደርጉ’ እዛ ድረስ ይሄዱ እንደነበር ግልፅ አድርገውታል። ስለሆነም ነው ከላይ የተመለከታችሁት ዓይጋው ድረገጽ “I could not fathom why leul chose to speak on this issue this time! What good outcome was he expecting from his witnessing?” በማለት ልዑሉ እውነቱን መናገራቸው “ወያኔዎችን እንደ ምጥሚጣ” እያወራጫቸው ያለው።

በነገራችን ላይ
“ኣይንደልን ጓና፤
ናዓየ ወዲ ላሕምና
ማለት “የላሜ ቦራ ልጅ ሆይ፤ ባዕድ ገዢ እንዲያስተዳድረን አንፈልግምና ተሎ ና አስተዳድረን” ማለት ነው። በወቅቱ ልዑል መንገሻ ከደርግ አስተዳዳር አምልጠው ወደ ውጭ በመሄዳቸው፤ የትግራይ ሕዝብ፤ በተለይ የእንደርታ ሕዝብ አጅግ አዝኖ ስለነበር፤ በወቅቱ ለእሳቸው የተቀኘላቸው ዘፈን ነበር። በወቅቱ እኔም በአካባቢው ስለነበርኩ ይህ ዘፍን በጣም ገናና ዘፈን ሆኖ በየሰርግ ቤቱ እና የቤት ሰራተኞች፤ ሸቃዮች፤ገበሬዎች እና አሸንዳ የሚጫወቱ ልጃገረዶችና ለልብስ አጣባ ወንዝ የወረዱ ልጃገረዶች ሁሉ፤  ከአፋቸው የማይለይ ‘ቀዳሚ’ ዘፈናቸው እንደነበር አስታውሳለሁ። ይህንን በሚመለከት “ሓይካማ” በሚለው የትግርኛ መጽሐፌ በሰፊው ጠቅሸዋለሁ።

ለማንኛውም ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም፤ ዛሬ እውነቱን በመናገራቸው ‘ታሪክ ሰርተዋል እና አመሰግናቸዋለሁ”። ይህንን ሃሳባቸው ለማስቀየር ‘ወያኔዎች’ “በጥምዘዛ ቴክኒካቸው” በወያኔዎች ሚዲያ ቀርበው ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ በማድረግ ‘ያልሆነ ሃሳብ’ ውስጥ እንዲገቡ አድርገው ፤ የተናገሩትን እንዲቀይሩ አንደሚሞክሩ አውቃለሁ። “በሌለ አናጋገር ምን ማለትዎ ነው?’ እያሉ እየጠማዘዙ የሰጡትን ሃሳብ ለማስቀየር “ሃራስ” እያደረጉ /እያስጨነቁ/ “አንደሚወተውቷቸው ‘ጌታቸው ረዳ’ ምን አለ በሉኝ።ወያኔ ለበርካታ አመታት ብቻ ሳይሆን የማውቀው፤ ትግሬ እንደመሆኔ መጠን የትግሬ “ሳይክ” እና “እልክ” ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዝ ስለማውቅ፤ ልዑሉንም በቃለ መጠይቅ በሄዱበት ቦታ እየሄዱ ሃሳባቸውን ለማስቀየር እንደሚወተውቷቸው አውቃለሁ።ለማንኛውም አክብሮቴ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽላቸው አፈልጋለሁ።

ያዘጋጀሁትን  ‘ሳምንታዊው የኢትዮጵያ ሰማይ ሐተታ’ ስላነበባችሁልኝ እጅግ አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያ ከትግሬዎች ፋሺስታዊ የበላይነትና ከወያኔ Biological State (የዘር መንግሥት) ቀንበር አምላክ ነፃ ያወጣት!። ደህና እንሰንብት። Getachew Reda getachre@aol.com (Editor Ethiopian Semay)