Monday, August 4, 2014

የዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ናዚ ኔት ዎርኰች በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያስተጋቡት ዛቻየዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ናዚ ኔት ዎርኰች በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያስተጋቡት ዛቻ     

 (ጽሑፍ  ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
ዛሬ የምንመለከተው ጉዳይ Ethiopian Current Affirs Discussion Forum (ECADF) (የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ) እና Ethiopian Free Discussion Forum Voice Room  በተባሉት ሁለት የኢትዮጵያዊያን የናዚ ኔት ዎርክ የፓል ቶክ ክፍሎችን አንመለከታለን። ሁለቱም የግንቦት 7 እና የኢሳት ቴ/ቪ  “ሃርድ ኰር” ተለጣፊ ደጋፊዎች ናቸው።

ወይዘሪት (?) ሥርጉተ ሥላሴ ፤ የካረንት አፌይርስ ፓል ቶክ (ECADF) ቦርድ አባል እና የዘሓበሻ ድረገጽ ቋሚ ጸሐፊት።
ዓሊ ሊበን (የEthiopian Free Discussion For
um Voice Room ቦርድ ዋና ባለቤት እና ሰብሳቢ) የፓል ቶክ ስሙ “መተማ” አደገኛ ጸረ ትግሬ ግለሰብ።
እንደልቡ (ትከክለኛ ስሙ “ዳግም” (ዳግማዊ?)Ethiopian Current Affirs Discussion Forum (ECADF) (የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ) ዋና የቦርድ ሰብሳቢ። በስሜት የሚጋልብ እውነትም “እንደልቡ” አደገኛ ጸረ ትግሬ። የግንቦት7 እና የኢሳት ዋልታ እና ማገር።----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ታዬ ሙሉጌታ የቃሌ ፓል ቶክ ክፍል ዋና ተጠሪ። ድሮ የከረንት አፈይረስ ሩም ቦርድ አባል። የግንቦት 7 ደጋፊ እና ስለ አንዳርጋቸው ወንጀል ወይንም ሂስ መጻፍ በክፍሉ በጥብቅ የተከለከለ። ለመጻፍ የሞከረ “በቀይ ልጓም” (የተቃዋሚዎች ዲሞክራሲ) ይከረቸማል (ሬስተረይን ይሉታል)። 
የኤርትራ ሕዝብ ከዬት ወዴት (መለስ ዜናዊ) የአማራ ሕዝብ ከዬት ወዴት (ኦሮሞው አንዳርጋቸው ጽጌ) የኦሮሞ ሕዝብ ከየት ወዴት (ኤርትራዊው አባ ዱላ ገመዳ)። የአለቃቸውን ኰቴ እየተከተሉ አርእስቱን አንዴት አንደቀዱት ታሪክም ገርሞት ይሆናል።
የመለስ ዜናዊ ሞት ከተሰማ በሗላ በቀጥታ የጎበኘሁት የትግራይ ናዚ ኔት ዎርክ ፓልቶክ ክፍል ገዛ ተጋሩ የሚባለውን ነበር በቀጥታ የጎበኘሁት።  “”የጎጃም እና የጎንደር አማራ ሕብረተሰብን  “ሪታርድ፤ ኢድየት” እያለች በመጮህ የምትታወቀዋ እና “ከጉራ ፈርዳ የመባረር እጣ ፈንታቸው የሆነውን አማራዎች ሲባረሩ “ለምን ይባረራሉ? ዘረኝነት ነው? ተብሎ ሲጠየቅ “ቢ ኢት! ሶ ዋት!?” በማለት በአማራዎች ስቃይ በመሳለቅ የታወቀቺው ጐሰኛዋ የገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ባለቤት “ወ/ሮ ሕድያት” የተባለች (ዛሬ ገዛ ተጋሩ ፓል ቶክ ከምድረ ገጽ የተሰወረ ይመስላል። ምክንያቱን እየተከታተልን ነው።) ይህች የራያ/የመኾኒ/ጨርጨር ትግራይ የገበሬ ልጅ ነኝ የምትል ጐሰኛ “በመለስ ሞት የተሰማት ሓዘን እንዴት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ እንደነበረች” እና ሌላው የትግራይ ተወላጅ የሆነ ለትምህርት ተልኰ ለማስትሬት ዲግሪ ስልጠና እየሄድኩኝ ነኝ በማለት ራሱን ያስተዋወቀ የትግራይ ወጣት ለሁለተኛ ቀኑ ምግብ አንዳልበላ እና ለተከታታይ ቀንም ምግብ አንደማይበላ እያለቀሰ ክፍሉን በአሰልቺ ረዢም ንግግር እና በልቅሶ እየጮኸ ክፍሉን ሲንጠው፤ ኤርትራኖችም አንዲሁ ወደ ገዛ ተጋሩ በመጉረፍ ‘በወንድማችን በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ መሞት የተሰማንን ሃዘን የትግሬ ወንድሞቻችን “ጽናት ይሐብኩም” (ጥናቱን ይስጣችሁ) እያሉ እየተላቀሱ ያደመጥኩት ጉደኛ ትርኢት ሳስታውስ፤ ዛሬ  የግምቦት 7 ምክትል መሪ የነበረው  “አንዳርጋቸው ጽጌ”  በየመን ታግቶ ለወያኔዎች ተላለፈ በተባለበት ሰሞን ከአንድ ፓልቶክ ሩም (ደብተራ ሊክ) በስተቀር በጐበኘሗቸው  የፓልቶክ ክፍሎች “ከገዛ ተጋሩ ፓልቶኮች” ባልተናነሰ አንዳንዱ በባሰ መልኩ “ሲያለቅሱ፤ሲጮኹ”፤ አንዳንዱም “ትግሬ” የተባለ ሁሉ መገደል እንዳለበት አዋጅ ሲያውጁ አደምጬ ተገረምኩ።

አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ መውደቁን ከተሰማ በሗላ በእነዚህ እላይ የጠቀስኳቸው የተቃዋሚ ፓልቶክ ክፍሎች ሲሰተጋባ የነበረው እና አሁንም እየቀጠለ ያለው ደግሞ የሰማሁት አስደንጋጭ ባሕሪ እንመለከታለን።  አንዳርጋቸው ጽጌ፤ኤርትራ በረሃ እያለ በእራሱ አባሎች ላይ “ግርፋት እና እስራት” አንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከሰለባዎቹ አንደበት በማስረጃ እየተነገራቸውም ቢሆን ፤ ለሰው ልጅ መብት እንቆማለን የሚሉ የፓልቶክ ክፍሎች፤ የገዛ ተጋሩ ጉደኛ የሐዘን ቤት  ልቅሶ የሚያስታውስ፤ “ገራፊዎችን” ወደ ጀግናነት እና ሰብአዊ ተሟጋችነት የመለወጥ ባሕሪ ተደምጧል። አንዳርጋቸው “የራሱን ታጋዬች በድበድባ “በቶርቸር” አንዲሰቃዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሳተፍ ተጠያቂ አንደሆነ ያለ ጥርጥር መረጃዎች አሉ። ኢሳትም ሆኑ እውጭ ያሉ የተቃዋሚ ሚዲያዎች አንዳርጋቸው ከኤርትራኖች ጋር ተባብሮ አሰቃይቶናል እና በደላችንን ለሕዝቡ አንድናሳውቅ በዜና ማሰራጫ መስመሮቻችሁ ቀርብን አንድንናገር ፍቀዱልን ብላው ቢለምኗቸውም “አንፈቅድም” በማለት የአንዳርጋቸው ወንጀል አንዳይጋለጥ ተባባሪዎች ሆነዋል (ባዘብዛኛዎቹ- ማለትም ኢትዮ-ሚዲያ፤ ዘሓበሻ፤ ኢሳት፤ ወዘተ…..ወዘተ….። አይ አንዳርጋቸው “ይህ ወንጀል አልፈጸመም” የሚሉ ደጋፊዎቹ እና ሚዲያዎች ካሉም ሕዝብ ፊት ቀርብን እውነቱ አንዲገለጥ ወደ ሚዲያችሁ ጋብዙን እና ወንጀሉን ለሕዝብ እናብራራ ፤ እናንተም ለምን አምቢ አንደምትሉ እንከራከራችሁ ብለው ደብዳቤ ጽፈው ቢጮኹም  ሚዲያዎች ሕዝቡ አንዳያዳምጣቸው/አንዳይቀበላቸው ደምፃቸውን አፍነውታል። እስከዚችኛዋ ደቂቃ ድረስ!

ምናልባት Ethiolion.com እና Assimba.org እና የክንፉ አሰፋ EFM የሰለባዎችን ደምፅ በመጠኑም ቢሆን ከኔም ሆነ ከ ያሬድ ሃይለማርያም የተላለፈው የሰብአዊ ጉዳይ ስሞታ ወደ ሕዝቡ ለማስተላለፍ ሞክረዋል።እና እነሱን ከነዚህ ወገንተኛ ሚዲያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ አትጨምሯቸው። መመስገን ይገባቸዋል።አንዳርጋቸውን የሚከሱት ሰለባዎቹም በሚዲያዎቹ ስለተበሳጩ መሰለኝ፤ በራሳቸው በግንቦት 7 ዲ (Ginbot 7 D) ድረገጽ ብቻ ናቸው ሃሳበቸወን እየሰነዘሩ የሚገኙት።

አክቲቪስት ነን፤ ለሰው ልጆች መብት መከበር ቆመናል የሚሉ ሌት ተቀን በየሚዲያዎች የሚያስመስሉ አክቲቪስቶች ነን የሚሉን እነ ተድላ አስፋውም ሆኑ እነ ታማኝ በየነ፤ የእነዚህ የአንዳርጋቸው ሰለባዎች  ጩኸት እና ክስ ግን ከሙያ ሳይቆጥሩ በየአደባባዩ ለአንዳርጋቸው መብት መከበር ሲጮኹ መስማት ምንኛ ዘግናኝ እና “ፒክ ኤንድ ቹዝ” አድላዊ ፤ወገንተኛ የሰብአዊ ጥብቅና ሥራ አንደሆነ አንባቢዎቼ አንድትገነዘቡት። ይህ አድላዊ እና ወገንተኛ “አክቲቪዝም” የመሪያቸውን አንዳርጋቸውን ወንጀል እና ጭካኔ ሥራ ላለማጋለጥ በ ”ሃሽ ሃሽ” “ዝም በል! ዝም በል” ተንኮል ቢጥሩም ሃቀኛ ዜጎች የወገኖች እንባ አንዳይታፈን ከሰለባዎች ጐን ቆመን ለሕዝብ አንዲታወቅ እናደርጋለን።

በእነታማኝ በየነ የሚመራ በየፓልቶኩ የሚነበነብ የአንዳርጋቸው ጀግንነት እና አርበኝነት ወይንም ክርስቶስነት በአድላዊ “ሰብአዊ ጥብቅና” እየተሞጋገሰ ያለው ይህ አስገራሚ ባሕል ዛሬም “አድላዊ ወገንተኛ ባሕሪ” በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ያልተላቀቀ መሆኑን በዛሬው ትውልድ እየቀጠለ እንደሆነ እና በመጪዋ ኢትዮጵያም (አገሪቷን ካልበተኗት) የሚቀጥል መሆኑን ጠቋሚ ማሳያ ሆኗል።

ይህ ወገንተኛነት የሚያመለክተን ነገር ቢኖር ለነፃነት አንቆማለን ብለው ወደ ኤርትራ በረሃ ለሽምቅ ተዋጊነት ስልጠና የሄዱ ዜጐችን በኤርትራኖች እና  በግንቦት 7 መሪዎች ለአሰቃቂ እሰር እና ድብደባ ተዳርገው አይቶ አንዳላየ “ስሞታቸውን” የሚያንኳስስ “አዲሰ ትውልድ” ማየት ብዙ ጭራቆችን እና ነብሰ ገዳዮች ከወያኔ ገራፊዎች በባሰ ለወደፊቱ አንደ አሸን አገሪቷ አንደሚሞሏት አልጠራጠርም። 
“የኢትዮጵያን ናዚ ኔት ወርክ ፓል ቶክ” ክፍሎች በዚህ እና በተያያዙ ጉዳዮች ምን ይላሉ።ለአንዳርጋቸው ልቅሶ ከተቀመጡት ውስጥ አንዱ Ethiopian Free Discussion Forum Voice Room በተባለ የትግሬን ሕብረተሰብ መፈጀት አንዳለበት የሚቀሰቅስ አደገኛ የፓልቶክ ክፍል (የዚህ ክፍል ዋና አዘጋጅ፤መኖሪያው “ኖር ወይ”’ የፓልቶክ ስሙ “መተማ” እውተኛ ስሙ “አሊ ሊበን” ይባላል) ልቅሶ እና ዛቻ አንጀምር። ልቅሶ ከተቀመጡት ውስጥ በሰማሁት በአንድ ወልቃይቴ ነኝ የሚል ግለሰብ አንጀምር። አንዲህ ሲናገር ይደመጣል፡-
“እኔ ትግርኛ በደምብ አድርጌ መናገር እችላለሁ። ምን አንደሚሉ እሰማለሁ ፤አውቃለሁ። ነገር ግን ወልቃይቴ አማራ እንጂ ከትግሬ ደም ወይንም ጋብቻ ትስስር ንክክ የለብኝም። የወልቃይት ሰው ነኝ። ትግሬ መሬቴን ወስዶታል! ትግሬ እየኖረበት ነው። አሁን በማንኛውም ትግሬ የተባለ ሁሉ መበቀል አለብን። እግሌ እገሌ ሳይባል ትግሬ የሚባል በሕይወቴ አንዱን ትግሬ ገድዬ መሞት ነው የምምመኘው። አጀንዳየ አንድ ትግሬ መግደል የኔ ግብ ነው።ወገኖቼ ሆይ! ትግሬን መበቀል አለበን!” ይላል።
አንድ አድማጭ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል።
እንዴ “ጌታቸው ረዳ፤ ገብረመድህን አርአያ ፤ አስገደ ግበረስላሴ ወዘተ….ም ጭምር ልትገድል ነው እንዴ ? ተው እንጂ ምን አይነት ንግግር ነው የምትናገረው? ብሎ ሲለው
“ነገርኩህ እኮ እንናተ ትግሬዎችን አታውቋቸውም፡…!”  በማለት እንደ እኔ የመሳሰሉትን ለወልቃይት መብት የጮህኩኝ የትግሬ ተወላጅም ጭምር ቢያገኘን ትግሬ በመሆኔ ብቻ አንደሚገድለኝ ዝቷል።

እንዲህ አይነት ነብሰገዳዮች አሜሪካ/አውስትራልያ/አውሮጳ/ካናዳ …  ሆነው ትግሬን ለመግደል መዛታቸው ያስታወሰኝ አስደንጋጭ የነብሰ ገዳዮች የብቀላ ባሕሪ በቅርቡ “የመለስ ትሩፋት”  የሚል በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተጻፈ መጽሐፍ ሳነብ በገጽ 3 ላይ ወንጀለኛ ሕሊና ስላለቸው ግለሰቦች በምርጫ 97 ወቅት ወያኔ በአዲስ አበባ ከተማ በመዘረሩ ምክንያት አንዲህ ይላል።

 “የአዲስ አበባ ሕዝብ አንዴት ይጠላናል?” በማለት አንዳንድ የሥርዓቱ አገልጋዮች ግማሹ በእንባ ፤አንዳንዱ የባሕር ዛፍ ቅጠል እቤቷ ውስጥ ጎዝጉዛ በሃዘን ሲያለቅስ/ስታለቅስ አንዳንዱ ደግሞ በሕዝብ ላይ ብቀላ ለመበቀል ሥራዬ ብሎ ሰውን ለመግደል የተሰማራ ወያኔያዊ ወንጀላዊ ሕሊና ተከስቶ አንደነበር አንዲህ የላል፦

“ከማልቀስ አልፎ……ሕዝቡን ለመበቀል እንቅስቃሴ ያካሄዱ ካድሬዎች ራሳቸውን ባጋለጡ ወቅት ድርጊቱን ለመፈፀም ያነሳሳቸው የሕዝቡን ጥላቻ በማየታቸው አንደሆነ ተናግረዋል። በተለይም የህወሓት ነባር ታጋይና የኮልፌ ካድሬዎች አለቃ የነበረው “ነጋ በርሔ” ግለሂስ ያደረገው በዘግናኝነቱ ይታወሳል። ይህ ካድሬ የስሞኦን ልጅ (በረከት ስሞን ማለቱ ነው) በመራው ግምገማ “እንባዬ የሚደርቀው አንድ ቅንጅት ስገድል ነው” በማለት በምርጫው ማግስት “ሽጉጥ” ይዞ ሲዞር አንደነበር በፀፀት ተውጦ ነግሮናል። ተኩሶ አለመግደሉን እሱ እና እግዚአብሔር ይቀው።” ይላል ደራሲ አቶ ኤፍሬም ለገሰ (የቀድሞ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበረ በቅርቡ በጻፈው በዓይነቱ ልዩ የሆነ አስገራሚ መጽሐፍ። (ደራሲው ምስጋና ይገባዋል! ሁላችሁም አንብቡት።በጣም፤ በጣም የሚመሰገን ሰው ነው። አደራ አንብቡት!)

እንግዲህ እንዲህ አይነት ወልቃይቴ ነኝ የሚል እና የመሳሰሉ ፍጡራን እዚህ ውጭ አገር ጥገኝነት ተፈቅዶላቸው ሲኖሩ ወያኔን ስለጠሉ መላውን የትግሬ ሰው ለመግደል (ትግሬ በመሆኔ እኔንም ጭምር ማለት ነው)  “በኢትዮጵያዊያን ናዚ ኔት ወርክ ፓልቶክ ክፍሎች” አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ በገባበት ሰሞን ሲዝቱብን ማየት ከወያኔዎች የናዚ ኔት ወርክ ወይንም ከሩዋንዳው “ራዲዮ ኮሊንስ” ክፍሎች የሚመሳሰሉ መሆናቸው ታዝቤአለሁ። ይህ ደግሞ የፖለቲካ ልሂቃንን ከልክ በላይ ማምለክ ፤አንድ ነገር ሲገጥማቸው፤ የሰማይ ጣራ ለማፍረስ መሞከር፤ ማልቀስ ማበድ፤ ወደ ክርስቶስነት እና ረቂቅ ነብሳት አድረገው ሊሂቃኑን መካብ፤ ከዚያ በተያያዘ “ሕዝብ እንጨፈጭፋለን” ማለት፤ አደገኛነቱ ይህ ነው።

ምነዋ የአማራው ሕዝብ ሲገደል፤ ሲደበደብ፤ሲንገላታ፤የአማራ ልጆች ህፃናት ከትምሕርት ገበታቸው ተፈናቅለው በየጫካው እና በየበረንዳው  ተጥለው ለጅብ እራት አንዲሆኑ ሲደረግ አነዚህ አንዳርጋቸው ተያዘ ብለው ሰማዩን ለማፍረስ የሚቃጣቸው አውሮጳ እና አሜሪካ በሰላማዊ ሰልፍ እያናጉ ያሉት ኢትዮጵዊያን ነን የሚሉን ጭሆታቸው እንደዛሬው በተከታታይ ለምን ለአማራው አላስተጋቡም? “ዌብ ሳይቶቹ እኰ ወደ አንዳርጋቸው ቤተክረስትያንነት እና መስጊድነት እየተለወጡ ነው” አንድ አንዳርጋቸው ነብስ ይበልጣል ከሚሊዮኖች አማራ ሕብረተሰብ? መልስ አንፈልጋለን!! ወይስ ግንቦት 7 እና የሻዕቢያ አባላት ሚዲያውን ስለተቆጣጠሩት?

“እኔም አማራ ነኝ!” ወይስ “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ!”  መፈክር ነው “ሰብአዊ ክብርን” ሚዛን ደፍቶ የሚያጎናጽፈው? በዘረኛው አንዳርጋቸው መጽሐፍ ስድብ ጀምሮ እስከ በወያኔ እና በኦነግ አንደ ቀራንዮው እየሱስ በእሾህ እየተወገረ ያለው አማራው፡ህብረተሰብስ “እኔም አማራ ነኝ” “ሁላችንም አማራዎች ነን” እንዳትሉ ምኑ ነው አሳፈራችሁ? ያውም እናንተ እማ አማራዎች እኮ ናችሁ ባብዛኛው ግምባር ቀደም ቀደም ጋጋተውን የምታደምቁ!  “አንዳርጋቸው ነኝ” ባዮች!  የራስዋ አርሮባት የሰው ታማስላለች! የሚባለው ለካ እወነት ነው።

ሕዝብ አንደ ሕዝብ የማይከበርበት፤ችግሩ የማይነገርለት፤ ግለሰቦች ግን የሚመለኩበት ምክንያቱ ምንድ ነው? ልሂቃን የሚመዘኑበት ፤ሃብታሞች የሚመሰገኑበት እና የሚለኩበት መመዘኛዎች አሉ። ለሕብረተሰብ የተሰው የፖለቲካ፤የሃይማኖት፤አገራዊ አርበኞች ሲሰው አንደየወቅቱ መመዘኛዎቹ ቢለያዩም በዛሬ ወቅት በሰለጠነው የኢትዮጵያዊ ትውልድ ዘመን ግን “የፖለቲካ ልሂቃን ክብር ሲሰጣቸው” አስቀድሞ መምጣት ያለበት  “ሰብአዊ ነክ” ጉዳዮችን ቀዳሚ መስፈርት በማድረግ አንደሆነ ነበር የጠበቅኩት። ግን ውጭ አገር የሚኖሩ ተቃዋሚዎች እና የሕግ ምሁራን አብዛኛዎቹ ‘በሰብአዊ ዓይን ጥብቅና የሚጮኹላቸው” ወይንም “በወንጀል የሚከሷቸው” “ለሚያመልኳቸው” ወይንም “ለሚቃወሟቸው” ብቻ ነው!” የሚከተሉት የ “ፒክ ኤንድ ቹዝ” አክቲቪዝም ጥብቅና መመሪያቸው።

በዓለም መስፈርቱም “ሰብአዊ ነክ ጉዳይ ለሁሉም ወገን የሚመለከት“ ነው። ሆኖም፤ ውጭ አገር ያሉ ተቃወሚዎች፤ መሪዎቻችን፤ ክርስቶሳችን፤ አርበኞቻችን ሽልማቶቻችን ፤አንጐላችን ናቸው የሚሉላቸው ሊሂቃኖቻቸውን ግን ፤ዜጎች በሰይል/ ቶርች ያሰቃዩ፤ አንድነትን የሚያፈርሱ፤ከጠላት ጋር የሚዶልቱ፤ አገር ለፖለቲካ ችርቸራ የሚያቀርቡ፤ሕብረተሰቡን (በተለይ አማራውን) የሚያሳንሱ፤የጠላት ፕሮፓጋንዳ ለሕዝባቸው የሚሰብኩ፤ ለዘር ጥቃት የሚያጋልጡ፤ ፕሮፓጋንዳቸውን አንደ ናዚ ፕሮፓጋንዲስቶች በመጽሐፍ ጠርዘው ለትውልድ በመተው፤ለሚያስጠጓቸው አገሮች ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲሉ የታሪክ፤የማሕበራዊ የሰብአዊ ነክ ጉዳዮች፤ሉአላዊ ጉዳዮችን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራዊ ወይንም ሰብአዊ እሴቶችን በመጫሚያቸው ረግጠው የራሳቸው ዝና እና የድርጅታቸው ጠቀሜታ በማስቀደም ተምበርካኪ ባህሪያቸው ለሚከተላቸው ትውልድ እያስተማሩ መሆናቸው በተጨባጭ ከነማስረጃ እየቀረበላቸውም ቢሆን፤ የሰለባዎቻቸው ጩኸት እና ክስ፤ ደማቸው ደመ ከልብ አንደሆነ ቆጥረው ፤ሰለባዎቻቸውን በመዝለፍ - “አንዳርጋቸው አርበኛችን ነው” “ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን!” የሚል በጣም ጸያፍ እና አስደንጋጭ መፈክር ሲያስተላልፉ እየታዘብን ነው። አንዳርጋቸውን የሚወነጅሉ ማሕደሮች ወይንም እሱ ወደ ጫካ የሄደበት መንገድ መሄድ መሸከም በቻሉ ጥሩ ነው፤ ሆኖም ከአፍ ፉከራ አንደማያልፍ ስለምናወቅ ትርፉዬው ‘ትዘብት’ ነው።

የትግራይን ሕዝብ በያለበት በተገኘበት እንገድለዋለን የሚሉ ወንጀለኞች የቆየ ዛቻ ቢሆንም፤ እጅግ እየተበራከቱ የመጡት  አንዳርጋቸው በወያኔ ከተያዘ በሗላ ነው። እውን እንዲህ የሚያስተጋቡ ሰዎች፤ አንመሰርታለን የሚሉንን አዲስ ሥርዓታቸው የሚተልሙት እነዚህ በክርስቶስነት እና አርበኛነት የሚያወዱስዋቸው ሰዎች መመዘኛ እና መሪነት ከሆነ በሚመጣው ሥርዓትም ፤ ዜጐች ስለተናገሩ እና ስለጻፉ ወይንም ስለተቃወሟቸው ብቻ “ በለመዱት የድብደባ ፤ የማስፈራራት እና የእስራት፤ አንዲሁም የሕዝብ ጭፍጫፋ” መንገድ አንሚቀጥሉ እየነገሩን ነው። ይህ በሚሆንበት ወቅት አሁን እያሞገሷቸው ያሉ እና መጪው ስርዓት አንዲመሩ እየደገፏቸው ያሉ አምላኪዎቻቸው ፤መሪዎቻቸው ለሚሰሩት ሰብዓዊ ግፍ ከምንም እንደማይቆጥሩት ከዚህ ከግንቦት 7 እና ደጋፊዎቻች እና ኣባሎቻቸው ግልጽ “ፓተርን”/አብሪ/ መንገድ ነው።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆንላችሁ የሚችለው፤ ጥሩ ግጥም እና አማርኛ ቋንቋ መጻፍ የሚችሉ “ የአማራ ነገድ ተወላጆች” (አይደለንም እስካላሉ ድረስ) ስዊዘርላንድ ኗሪ የሆነች “የግንቦት 7 ኣባል እና የትግሬ ዘር ማጽዳት ቅስቀሳ የሚያካሂደው የግንቦት 7ቱ ፓልቶክ ክፍል “ካረንት አፈይርስ” አባል የሆነችው “ ስርጉተሥላሴ” እና ……የሺጥላ የተባለው እዚህ ሳንሆዘ ከተማ ሲኖር የነበረ ወጣት “ገጣሚ” የሚጽፉትን አድናቆት በጥሞና ስትመረምሯቸው፤ እነዚህ ፀሐፊዎች ‘ለሰው ልጅ መብት የቆሙ ይምሰሉ እንጂ” በተግባር “ አንዳርጋቸው ጽጌ ገና ለገና ትግሉን ሳይጀምረው፤ በበርካታ የግንቦት 7  ታጋዮች ላይ “በሰይል/በቶርች/” እንዲሰቃዩ ውሳኔ ያስተላለፈው” አንዳርጋቸው ጽጌን በእንደዚያ ያለ “አምልኮት” ተጐንብሰው ሲያንጸባርቁ፤ በእንደዚህ ዓይነቶቹ ዜጐች የሚደገፍ መጪው ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰተ የሰው ልጅ መብት ክብር የሚጋፋ አንደሚሆን እና ግፉም በደጋፊዎቹ “የሚደገፍ” አስፈሪ ሥርዓት አንደሚሆን ከወዲሁ ማወቅ አያዳግትም።

አንድ ነገር በጊዜው ካልታረም “ግፍ እና ግፍ ፈጻሚዎች” እየተለመዱ ወደ ክርስቶስነት እና ቅዱሳን መናፍስት እየሆኑ ሲሰበክላቸው፤ እየለመድናቸው “ገራፊዎቻችን” አንድናከብር እንገደዳለን ማለት ነው። እነ ኢሳያስ እነ መለስ በጭካኔ መንገድ ሲጓዙ እንደጀግኖች ተቆጥረው ፤እነሱ ያሰቃዩዋቸው እና ደብዛቸው ያጠፏቸው ዜጎች ግን አንደ ጉንዳን ሳይታዩ ቀርተው “ነብሰገዳዮች እና ገራፊዎች” ወደ ዙፋን ወጥተው ዛሬ ምድሪቱ ወደ ሲኦል ለውጠዋት አይተናል።(“የመለስ ትሩፋቶች፤ ባለቤት አልባ ከተማ” ደራሲ “ኤርሚያስ ለገሰ” የስርዓቱ አውሬአዊ ገጽታ ያልጠበቅናቸው ጉዶች በጥሩ አማርኛው ዘግቦ ገልፆልናል።)  የነ መለስን እና ኢሳየስ ጭካኔ ስናወግዝ ስብእናችን እና ስማችን አንዳልጐደፈ ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በመጪዋ ኢትዮጵያም ሆነ በዛሬው ተቃዋሚ ድርጅቶች የነ መለስ እና ኢሳያስ ዓይነት የመብት ረገጣ እንደገና በሕዝባችን ላይ በምንም መልኩ መታየት እና መደገም የለበትም ለምንል ዜጎች ደግሞ “የአንዳርጋቸው የምንጠራ ዘመቻ” በሚሉት አዲስ የቀይ ሽብር ዓይነት “ምንጠራ” ለምን አንዳርጋቸው ወቀሳችሁ ብለው ካሁኑኑ የፎከሩብን “መንግሥት ሲሆኑ” እነኚህ የግንቦት ካድሬዎች በቀይ ሽብር ዓይነት “እንደማይመነጥሩን” ምንም ዋስትና የለንም።

ይህ ምንጠራ የሚሉት “የሙቀት መልቀቂያ” ወያኔዎችንም ሳይሆን የሰብአዊ መብት የሚጋፉ የፖለቲካ መሪዎቻቸውን  ለምናጋልጥ ተቃዋሚዎች በነሱ አጠራር  “በተቃዋሚ ሥም የተሰገሰጉ “ወያኔዎች” ተብለን በብዕራቸው የምንጠቀስ ተቃዋሚዎችም  የሚመለከት “ምንጠራ”  መሆኑን ከሚጽፉት “የሙቀት መልቀቂያ” ማየት ችለናል።  የግንቦት 7 አለቅላቂ የሆነ አንድ ኤርትራዊ (ከላይ በፎረሙ ሰሌዳ ላይ እንደምታነቡት “ዛንዜራ” በሚል የፓል ቶክ ስም የሚጠራ) በተጠቀሰው በግንቦት 7 ፓል ቶክ ክፍል ውስጥ ገብቶ በትግርኛ  ተርጉሞ የጻፈው “የምንጠራ ዘመቻ” አንዲህ ይላል፡ “ወፈራ አንዳርጋቸው” ይለዋል። ዘመቻው በማን እና በእነማን አንዳነጣጠረ ደግሞ ቆየት ብዬ ወደ ታች አቀርበዋለሁ።

በጣም የገረመቺኝ ከግንቦት 7 “የምንጠራ ዘመቻ ግብረሃይሎች” አበራታች አንዷ የሆነቺው ከላይ የጠቀስኳት የካርንት አፈይርስ ፓል ቶክዋ- በራስዋ አባባል “ሥርጉተ ሥላሴ ወይንም በፓልቶክ ሥሟሥርጉት’ በዘሓበሻ ካቀረበቺው ጽሑፏ አንዱ አንዲህ ይነበባል”
ከእንግዲህ ማናቸውም ተቋም፣ ድርጅት፣ ግለሰብ ስለ አንድ ሰው ብቃትታታሪነትትጋትና ታሪክ ለሚበክል አቅመ ቢስበዘመቻ ተነቅሎ” እንዲወገድ የማድረግ ሂደቱን ሊያዘወትሩበት ይገባል። ይህን ህዝባዊ ሃላፊነት መርኃቸውና መሪያቸው ማደረግ ይኖርባቸዋል። በስተቀር ዘመቻ አንዳርጋቸው በስውር ትል ይወረራል።  ( ታማኝ ጠብቁ ከሥርጉተ ሥላሴ  28.07.2014 በዘሓበሻ  ድረገጽ ተለጠፈ ጽሑፍ)።

ልጅቷ በጽሑፏ ያወቅኳት በዚህ አመት ነው። አንዳውም አማርኛዋን አይቼ እጅግ ወድጃት ነበር። አንዳንድ የቅርብ ወዳጆቼ ሴትዮዋ ከሙያ ምስክር ባልተናናሰ  ካረንት አፈይርስ ሆና የምትናገረው “ዘረኛ” ምላስ እንዳላት ነግረውኛል። ምን ስትል አንደነበረ  መረጃ ካላቸው አንዲያፈላልጉልኝ እሞክራለሁ። ምክንያቱም ሴቲዮዋ ያወቅኳት እዛው ዘሓበሻ በተባለው ድረገጽ “ለልጅ ተክሌ፡ መልስ በጻፈቺለት ቀን ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ዓይኔን ከፍቼ ልከታታላት የሞከርኩት። ቢሆንም፤ በዘሐበሻ ተለጥፎ ያየሁት ቪዲዩ እሷ ከሆነች፤ አስቀድማ የአንዳርጋቸው አድናቂ እና የግንቦት 7/ የካረንት አፈይርስ ሰብሳቢ/አዘጋጅ መሆኗን መገንዘብ ችያለሁ። እኔ ይህ ሁል አለዋቅኩም “የት ተደብቀሽ ነበር” ብያለሁ የጽሑፏን ውበት አይቼ!

አሳዛኙ ነገር ግን ይህች ወጣት ግንቦት 7ን “በኽር ልጄ ነው” ትለናለች በኩራት! “በኽር ልጄ” የምትለውን ግንቦት 7 “ወላጆቹ እነ ማን ናቸው”?  በሉዓላዊነታችን የሚያሾፉ “ለኤርትራ ነፃነት“  የሚሳሱ፤ በየሻዕቢያ ፈስቲቫሉ እየተጋበዙ ባልተገረ ምላሳቸው “ነፍጠኛ” እያሉ የሚዘልፉን “ባንዳዎቹ” እነ ኤፍሬም ማዴቦ ናቸው የበኽር ልጄ” የምትለው የሥርጉተ ሥላሴ ልጅ “አባቶቹ!”። የሴትዮዋ ዴሉዥን ሕዝባዊ ሃይል ተብሎ በሚጠራው ተዋጊ ሃይል (በስም) ተመልምለው ለነበሩ ታጋዮች መብት መከበር ላላት አክብሮት ሳጤነው ግንቦት 7 የተባለው “በኽር ልጇ” ኤርትራ ውስጥ ሆኖ የፈጸማቸው “ሰብአዊ ግፎች” ምንም ደንታ የማይሰጣት የሻዕቢያዋ “ሶፊያ ተስፋማርያም” ቦታ የምትተካ ትመስላለች ። “የግንቦት 7ቷ ሶፊያ” እና የሻዕቢያዋ ሶፊያ” ሁለቱም የ “ካሊጐላ”ን ሕግ አክባሪዎች ናቸው። ካሊጐላ ማለት ሮማ ውስጥ በ10ኛው ክ/ዘመን የነበረው አጼ ጋዩስ/ሁልዮስ ነው።    

በኽር ልጇን የወለዱላት የመሳሰሉት ግብዝ ሰዎች የሚመራው ግንቦት 7 የተባለው የባንዳ ስበስብ፤ ለዚህች ሴትዩ ምን ማለት እንደሆነ አንዲህ ትገልጸዋለች።
 ጌጥ የለም! ምቾት የለም! ዘመቻ እንዳርጋቸው ዕውን ይሆናል!  አረሞች ስሙኝ ልነገራችሁ እናንተ የምታስቡት የግንቦት 7 አባላት ተመዝግብው ወርሃዊ ክፍያ ዬሚከፍሉትን ብቻ ነው። ለእኔ ግንቦት 7 የበኸር ልጄ ነው። ግንቦት ማህደሬ ነው።  ግንቦት 7 ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የመንፈስ ልጆች አሉት…”
በማለት የከረንተ አፈይርስ ፓል ቶክ ባለቤት “ሥርጉት” እኛን ከበኽር ልጇ ጋር በማስተዋወቅ  ወደ ኤርትራ በረሃ ለመውጣት የተዘጋጀች ትመስላለች“ ግን ! ግን ሁሉም ነገር ወደ ሃረና ብላ ከዘመተች በሗላ “አንደ እነ ሽታው፤ አንደ እነ ኮስሞስ እና እንደ እነ እና…እነ…የመሳሰሉ …. የአንዳርጋቸው ሰለባዎች ኤርትራኖች በሄልኮፕተር (ወፌ ላላ) ገልብጠው አንዳሰቃይዋቸው ሁሉ፤ እሷንም በሄሊኮፕተራቸው ገልብጠው ቢፈትንዋት  “በዘመቻ አንዳርጋቸው “ጌጥ የለም! ምቾት የለም! ዘመቻ እንዳርጋቸው ዕውን ይሆናል!” ብላ ወደ ሃረና የሔደችብትን መፈክር  በምን ትተካው ይሆን?  ምቕናይ ጽቡቕ ! (መሰንበት ደጉ!)  

ይህች ጓድ እህታችን “የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት?” ደራሲ አንዳርጋቸው ጽጌን “አንዳርጋቸው  የጭንቅላቴ  ልብ ነው! “ ትለናለች (ምሕረት የውርድ!)  ከእንግዲህ ወዲህ  ጌጧ፤ምቾቷን ትታ ወደ ትግል አንድትሰማራ ቃል መግባቷ አይከፋም፤ የሚገርመው ግን አንዲህ ስትል ነው፡-

“የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች በወያኔ ላይ ከምንሰነዝረው ጥይት ይልቅ በወገናችን ላይ የምንለቀው የቦንብ ናዳ ይልቃል ወይ ይበልጣል። እኔን የሚታገለኝ ቀፎ የነፃነት ትግሉን በነቀዝ እያሳረረ የወያኔን ተክል በእንክብካቤ እንደሚያስድግ አያወቀውም።  ከእንግዲህ ግን እንዲህ እዬተላላሱ መቀጠል አይቻልም። በፍጹም። አንድ የነፃነት አርበኛ የሁለቻንም ሃብት ሆኖ ሰፊ ጥበቃ ማደረግ ስንጀምር የወያኔ ከበሮ መተንፈስ ይጀምራል። ተሰውረው ሲበሉን የነበሩ የራሳችን ተወሳኮችን በሙሉ በአደባባይ ወጥተን የምናጋልጥበት ዘመን ላይ ነን። ቀደመው እራሳቸውን ወቅሰው ከእኩይ ተግባራቸው ከተመለሱ እሰዬው ነው። በስተቀር ጉሩቧቸውን እናንቃቸዋለን ማረገፍ ደግሞ በውጪ ላለው ኢትዮጵያዊ የተመክሮው ማሳ ፍሬ ገብ ነው።” ምንጭ -አንደላይኛው።

“ተሰውረው የሚበሉን የራሳችን ተውሳኮችን በሙሉ በአደባባይ ወጥተን የምናጋልጥበት ዘመን ላይ ነን። ቀድመው እራሳቸው “ካላጋለጡ” በስተቀር “ጉርባቸውን እናንቃቸዋለን።” በማለት “የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች” በማለት የምትጠራን “ተቃዋሚዎችን” በኸር ልጇን፤የወለዱላትን እነ ኤፍሬም ማዴቦ የመሳሰሉ “ፉንጋ ባንዳዎችን” መሰሪ ባንዳነታቸውን ስለጠቆምን፤ በተውሳክነት እየፈረጀችን፤ እርሷ እና መሰል ጓዶቿ በአደባባይ የምታጋልጠን መሆኗን እና፤ ይህች የግንቦት 7 እናት ካድሬ “የግንቦት 7 የአብዮቱን ካምፕ” ያስተላለፈችልንን “የራስ ማጋለጥ/ሂስ ግለሂስ” አዋጅ ተጠቅመን እራሳችንን ወቅሰን ካላጋለጥን “ጉርባችንን/ጐሮሮአችንን” አንደምንታነቅ እና “ማራገፍ” “ማርከፍክፍ” (መግደል ይሆን?) የእርሷ እና የመሰል ጓዶቿ ተሞክሮ ፍሬ አንደሆነ አስጠንቅቃናለች።  (ምቕናይ ጽቡቕ! መሰንበት ደጉ!)  

“አንዳርጋቸውን” የተቸ፤ “ታማኝን የተቸ፤ ግንቦት 7ን፤ ኤፍሬም ማዴቦን ወዘተ ወዘተ…የተቸ ተቃዋሚ ሁሉ “ሰውር ትሎች” በማለት ስም ስትሰጠን፤ ስውር ትሎች የምንባለው “የነፃነት ቤተሰቦች” ደግሞ በየቀበሌአችን እየተሰበሰብን እራሳችን  በሂስ እና ግለሂስ ካጋለጥን “እሰየው” ካልሆነ ግን  በዘመቻ አንዳርጋቸው “ጉርባችንን እየታነቅን” እና “እየተነቀልን” (በታማኝ በየነ እና በብርሃኑ ነጋ የካረንት አፈይርስ ፓልቶክ ተዋጊ ህዝባዊ ሃይል ኮማንዶ ጦሮች (ምናልባትም  በሻዕቢያ ፍሊት/ዲዲት- እንደ ትሎች እየተረጨብን እንደምንራገፍ  ያስተላለፈችልንን የዚች ጓድ እህታችን  የ “ትሎች፤ካንሰሮች….” የሚል  “የመንቀል ዘመቻ” ባሕል  እጅግ አስፈሪ ባሕሪ ለማነጻጸር አሁን ወደ ሗላ ወደ ደርግ ባሕሪ ልወስዳችሁ ነው። ይህ ባሕሪ አንደ ዋዛ ማየት የለባችሁም። መንግሥት ቢሆኑ እነዚህ ጸሓፊዎችና ገጣሚዎች ካድሬዎች ሆነው ሊሰሩልን የሚችሉትን ነገር ነው እየጠቆሙን ያሉት። ገና ለገና!

የደርግ ብልሹነት ዋናው ባሕሪ አሁን ይህች አህት በምታስተጋባው ““የንቀል፤ የ “ነስንስ” እና “የመንጥር” ዘመቻ መልኩ በመሄዱ እራሱን ለውድቀት እንዴት አንደጣለ እንመልከት።
የደርግ መንግሥት በመጀመሪያ የመንቀል ዘመቻው ያካሄደው በትግራይ ተወላጆች በአንደኛ ደረጃ ተጠርጣሪ በማድረግ ነው (ቀይ ሽብር በፊት እና በሗላ )። ከዚያም “ስውር ትሎች” ሲላቸው የነበሩትን ሁሉ ሳይውል ሳያድር “የራሱን ሰዎች” ወደ ማጥመድ ደረጃ ተሸጋገረ። ይኼ የተሳሳተ ፖለቲካዊ ቀመር ክስረቱን አፋጠነው። ካሁን በፊት ሕዝባዊ ሃይል በተባለው የግንቦት 7 አዲስ ምልምል ተዋጊ ሰልጣኞች ላይ የደረሰው ድብደባ እና እስራት ግፉ በደተፈጸመባቸው ሰዎች በሰፊው ተነግሯል። ይህ ሲሆን አንደ እነ ሥርጉተ ሥላሴ እና መሰል ‘የካረንት አፌርስ’ ባለቤቶች እና  ጀሌዎች የተሰጠው መልስ ግን “ሰዎቹ የወያኔ ሰላዮች እና በራሳችን ላይ የተሸሸጉ ትሎች” ናቸው የሚል ነበር (በየፓልቶካቸው ሲደርሱት የነበረው የደም ድርሳን ክሕደት)። ስለዚህም እነሱን ማጥራት/መንቀል ሕጋዊ ነው፤ በማለት የግንቦት 7ን ወንጀል ተከላክለዋል። እንዳውም፤ ይህች ጓዲት የምትሳሳለት ‘ኢካድ ፎረም/ካረንት አፈይረስ ዲስካሽን ፎረም” የተባለው የግንቦት 7 ድረገጽ እና ፓልቶክ ላይ “እነዚያ የግንቦት 7 ሰለባዎችን” “ተፈላጊ ወንጀለኞች” ናቸው በማለት  በየአሉበት ታድነው አንዲገደሉ የበየነ አስገራሚ ኔት ወርክ ነው።

ይህ የመግደል እና የአድኖ/ሃንት አባርሮ መግደል (የመንቀል’ የማራገፍ) ዘመቻ ማስተጋባት ባሕሪያቸው አዲስ አይደለም። ይህች ጓዲትም ፖላቲካው አንደ አማርኛ አሳምሮ መጻፍ እየመሰላት አንዳመጣባት ስታወርደው የሚያስከትለው መዘዝ/ቅራኔ አላወቀቺውም። እየጋለ እያስችገራት ያለው ስሜቷን በመቆጣጠር ፖለቲካዋም አንደ አማርኛዋ ቢሰለጥን ግሩም ትሆን ነበር። እኔም እወድላት ነበር። ታድያ ምን ይሁን፤ አምላክ ሲፈጥር ሁለቱም አይሰጥም መሰለኝ አማርኛዋ እና ውበቷ ሰጥቶ ፖለቲካዋ አወላግዶ ሰጣት። (በአምላክ ማመካኘት ከተቻለ)። አንደ ዕድል ሆኖ አንደ እሷ ዓይነት ደፋር፤ውብ ፀሓፊ እና ውብ ሴት ልቤን ይጐቱቱታል። ግን ፖለቲካዋ ግን ያልተከረከመ ነው። ረጋ ብትል እንዴት ጥሩ ነበር።

አዲግራት ውስጥ በተገንጣዮች የእጅ ቦምብ ተወርውሮበት ቆስሎ መከራውን ያየው (ገና የደርግ ደጋፊ ከመሆኑ በፊት) የተማረ እና የተመራመረው ታደሰ ገ/እግዚአብሔርን የመሰለ (በሗላ የደርግ የፖለቲካ ት/ቤት ሃላፊ ሆኖ የደርግ ቀኝ እጅ የሆነው)“ትግሬ” በመሆኑ ብቻ ደርግ በአሰቃቂ ድብደባ ደብድቦ ሲገድለው፤ የደርግ ደጋፊዎች የተባሉት “ሃርድ ኮሮች” የሰጡት ምላሽ ያው ግንቦት 7 ጀሌዎች ዓይነት አንደነበር (በወቅቱ በአገር ውስጥ ባንኖርም) ካነብባነቸው መጽሐፍቶች ለመገንዘብ ችለናል። የደርግ ሃርድ ኮሮች  “ወያኔ” የመለመላቸው በውስጣችን ሰርገው የገቡ አብዮቱን የጐተቱት “ተባዮች” መመንጠሩ አብዮቱን ወደ ፊት ያራምደዋል፡ የሚል አምነት ነበራቸው። አሁን የካረንት አፈይርስ ክፍል እና መሰል ፓልቶክ ክፍሎች ያመነውንም ያላመነውንም ፤የተቃወማቸውን ያልተቃወማቸውም፤ አንዳውም ትግሬ የሚባለውንም ሁሉ ሳይቀር “ አምበጣ በሊታ፤ ካንሰር’ ተባይ፤ ተውሳክ” በማለት በየፓልቶካቸው እና ድረገፆች የሚያራምዱት ተመሳሳይ ነው። ደግነቱ ሥልጣን አልያዙም!

የከረንት አፈይርስ ሰብሳቢ ነኝ የምትለን “ሥርጉት” በኽር ልጀዬ ነው  የምትለን “ግንቦት 7ን” ለሕዝብ ማስተዋወቋ  ባልከፋ፤ መጠየቅ ያለበት ግን፤ “ግንቦት 7 ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የመንፈስ ልጆች አሉት…” የምትለንን ይህች በጉርባችን ለማነቅ የምትዝትብን ሴትዮ በከረንት አፈይርስ ፓል ቶክ ክፍሏ ውስጥ የተሰገሰጉት “የመንፈስ ልጆቿ እና የበኽር ልጇ ቋሚ አባሎች” ምን እያሉ ያመሻሉ ምንስ እያሉ ሲደሰኩሩ ይውላሉ? የሚለውን አንመልከት አንዲያውም እሷ የምትለን ይህ ነው፡ “ከረንት ቤቴ ሲዳከም እኔን ሊጎረብጠኝ ይገባል።”  የእኔ መጎር ደግሞ በኢትዮጵያዊ ብቸኛ ተቋሜ ላይ ጥቃት በሰነዘረው ጠላቴ ላይ በእጥፍ ረመጥ ልኬ እንዲጎረብጠውእንዲያርመጠምጠው የማደረግ አቅሜን በታታሪነት በመገንባት ነው።” ትላለች።

Ethiopian Free Discussion Forum Voice Room (EFDFVR) የሚባለው ኖርወይ በሚኖረው ትክክልኛ ስሙ “ዓሊ ሊበን” የፓልቶክ ስሙ “መተማ” በማለት እራሱን የሚጠራ ግለሰብ የሚተዳደረው ይህ አደገኛ ፓል ቶክ ሩም እና “የካረንት ቤትዬ” የምትለው ጸረ ትግሬው Ethiopian Current Affairs Discussion Forum(ECADF) የግንቦት 7 ፓልቶክ፤ ሁለቱ ክፍሎች በእኛው በትግሬ ማሕበረሰብ ላይ የሚነዙትን “ዘረኛ” ዘመቻ ምን እንደሚመስል? እንመልከት፤
ሙያየ ምስክር (አውነተኛ ሥሟ “ብዙ ወንደማገኝ” በተባለች በደርግ ጊዜ  የኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ አባል ነበረች የሚባልላት ዛሬ ካናዳ የምትኖር የጸረ ትግሬዋ የካረንት አፈይርስ ዋና ሰብሳቢ እንጀምር። በካረንት ፓል ቶክ ክፍል ሆና የድምፅ ማጉያ ይዛ እንዲህ ትላለች፡
ትግሬ የሚባል አትመኑ! ኢትዮጵያዊያን ነን እያሉ እኛን ለማሳመን ኢትዮጵያዊያን ነን ቢሉም፤ የፈለገው ጊዜ ወያኔን አንቃወማለን ብለው 100 ጊዜ ቢነግሩንም “ትግሬ ምንም ጊዜም ቢሆን ትግሬ ትግሬነቱን አይተውም። ትግሬ ትግሬ እንጂ ፤ ሌላ ሊሆን ከቶ ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልም! ትግሬ ትግሬ ነው! አትመኑዋቸው!” ትላለች።
 ድምጿ በአውድዮ የተቀረጸ ማሕደር አለ።
በዚህ ብቻ አላበቃችም። እንዲህ ትላለች።
“ ትግሬ ዘረኛ ከሆነ እኔስ ለምን ዘረኛ አልሆንም? ከእንግዲህ ወዲህ እኔም ዘረኛ ነኝ!”
ስትል በጸረ ትግሬ ዘረኛነትዋ አንደምትኮራ እና አድማጮቿም “ትግሬ የሚባል ማመን እና ማስጠጋት አንደሌለባቸው በከረንት አፌይርስ ዲስካሽን ፎረም (ኢካዴፍ) ፓልቶክ በይፋ ያወጀችበት ክፍል ነው። የጓዲት ሥርጉት (ሥርጉተ ሥላሴ) “ካረንት ቤትዬን የሚተችልኝ አልወድም” ፤ “ካረት ቤቴ ሲዳከም እኔን ሊጎረብጠኝ ይገባል” የምትለው ዘረኛ ክፍሏ ይህንን ይመስላል።

ምን እሷ ብቻ! ሌላዋም አንዲህ ትላለች- አውዴው አንዲህ ይደመጣል፡
 “እናንተ ሰዎች፤ ይህ ትግሬ ሚባለው 5 ሚሊዮ ማይኖሪቲ- ነቀዞች እኛ 80 እስከ 90  ሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያዊያኖች ከተባባርን አነዚህን 5 ሚሊዮን ነቀዞችን ማምበርከክ አንችላለን። ያስቸገረን ነገር ትብብራችን አንድ ባለመሆኑ ነው።…..” በማለት ስድብ እና ንቀት የተሞላበት ሰፊ ቅስቀሳ አድርጋለች። (ይህንን አስመልክቶ “ካረንት አፈይርስ ክፍል ስትጮሕ የሰማሗት አራዊት” በሚል በወቅቱ ጽፌ ነበር)
ይህ ክፍል ባለፈው ሰሞን አንዳርጋቸውን አስመልክቶ ገለፃ ለማድረግ “ታማኝ በየነ” በእንግድነት ጋብዞት ሲገባ “የድሮ ደምበኛችሁ ነኝ”  ይበላቸው እንጂ ድሮ “እናት ክፍሌ” ብሎ ነበር የሚጠራቸው።እንዲህ ያለው የትግሬ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻ በሚካኼድበት ዘረኛ እና አደገኛ ክፍል “የናት ክፍሌ” ናችሁ እያሉ የሚያሞግሱትን የፓል ቶከ ክፍል  እነ ታማኝ በየነ እና የግንቦት 7 መሪዎች በታሪክ ተጠያቂዎች ናቸው አንላለን።
እንደ እነዚህ የመሳሰሉት “ኢትዮጵያን ንዮ ናዚ ኔት ወርኮች” በእነ ታማኝ በየነ የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ሲሞገሱ “ትግሬን የሚገድሉ ናዚዎች” አይፈለፈሉም ማለት አንችልም። “ኮሎምባይን እስኩል” ህፃናትን እና አስተማሪዎችን የጨፈጨ የ15 አመት ወጣት አሜሪካዊው ናዚ ‘ጄፍ ውይስ” በናዚ ኔት ወርክ ፓል ቶክ ክፍሎች በመግባት ‘ናዚዎች የሚናገሩት አንደበት” ሕሊናውን ስለቦወዘው፤ አንዲያ ያለ ወንጀል ሊፈጽም አንደቻለ አንብበናል። በፓልቶካቸው ውስጥ በመግባት አንዲህ ይላል፡
I'm interested in joining the group," Weise wrote, "as I support your ideals ... even though I am young." በመቀጠል እራሱን "NativeNazi" or "Todesengel," የሗለኛው የጀርምን ቃል “መልአከ ሞት” ማለት ነው፡ ዘጋቢዎች አንዲህ ሲሉ የወጣቱን በንዮ ናዚ ፓል ቶክ ኔት ወርኮች ቅስቀሳ መማረክ አንዲህ ይላሉ፡ , “Weise expressed admiration for Adolf Hitler and uncertainty where his own bigotry fit within his Native American community. Over the next year, Weise typed 34 entries onto the Libertarian National Socialist Green Party's Web site, leaving investigators with a disturbing insight into possible motives behind Monday's deadly school shooting in Minnesota.” ይላሉ።

የከረንት አፈይርስ ዘረኞች የሚያስተላልፉት ደምፅ በትግሬ ሕብረተሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻቸው ካልተቋቋምነው እና በጽሑፍ ለሕዝብ ካላሳወቅነው፤ ምንም የማያውቁ የዋሆች በቤተሰቦቻችን እና በራሳቸን ላይ ጥቃት መፈጸማቸው አይቀርም። “የራሳችን ተውሳኮች ጉርባቸውን አንአንቃቸዋለን፤ አናራግፋቸዋለን፤ እንነቅላቸዋለን” ……”ትግሬ ምንም ጊዜ ትግሬ ነው  አትመኗቸው፤ አርቋቸው……ካሁን ወዲያ እኔም ዘረኛ ነኝ”  የሚሉን አነ ጓዲት ሥርጉተ ሥላሴ እና ወ/ሮ ሙያየ ምስክር የሚዝቱብንን እንገነዘበዋለን።

ዘረኛ ነኝ ብሎ የሚናገር አንድ ሰው፤ ዘረኛ የሚሰራው ሥራ ደግሞ ምን አንደሆነ ለናንተ አልነግርም። ያው የ15 ወጣት ዘረኛ ሥራ ውጤቱን ከላይ አንብባችሗል። ካረንት አፈይርስ አንደዚህ ያለውን ዘረኝነት የሚስተጋባውን ክፍል ነው ጓዲት ሥርጉት “ከረንት ቤቴ ሲዳከም እኔን ሊጎረብጠኝ ይገባል።የምትለን። አንደዚህ ዓይነቶቹ  የኢትዮጵያን ናዚ ፓል ቶኮችን ነው እነ ታማኝ በየነ “እናት ክፍሎቻችን” የሚሏቸው። በዚህ ዘረኛነታቸው ምክንያት አንዳንድ የከረንተ አፈይረስ አባሎች እና ደምበኞች እነ “ድሉ ዘገዬ” የተባለ “የዋህ ዲያቆን/ በአሜሪካ የሪፓብሊካን ፓርቲ አባል/መራጭ ነው” እና እጃጁ (ጣሊያን አገር የሚኖር) የተባሉት ሰዎች (እውነት ከሆነ ከካረንት እራሳቸው አንዳሰናበቱ ይነገራል። ለዚህ ይሆናል አሁን ክፍሉ ባዶ እና የተዳከመ “የለየላቸው የግንቦት ዘረኞች እና ፀረ ትግሬ የሆኑ ብቻ ተቸክለው ለግንቦት 7 አገልጋየች ሆነው የቀሩት። ለዚህም ነው ጓዲት ሥርጉት ክፍሏ ስለተዳከመ “ከረንት ቤቴ ሲዳከም እኔን ሊጎረብጠኝ ይገባል። የምትለን። ለመዳከሙም በሽታውን ከመመርምር ይልቅ ዘረኛውን ክፍሏን “ተቻችሁ” እያለች እኛኑን ትከሳለች። ስለሆነም ‘በጉሮኗችን” ልታንቀን ዘመቻ በማዘጋጀት ላይ ትገኛለች። ጌጥ የለ! ምቾት የለ!

ዛሬ የካረንት አፈይረስ ፓል ቶክ ከተዳከመ በሗላ እሱን ተክቶ ጸረ ትግሬነት ከፍተኛ ቅስቀሳ የሚካሄድበት አሁን በርካታ ጐብኚዎች እያገኘ ያለው ሌላው “ኢትዮጵያን ናዚ የፓል ቶክ ኔት ወርክ Ethiopian Free Discussion Forum Voice Room የሚባለው ነው። አስቀድሜ አንደገለጽኩት “ደብተራ በሚባለው ክፍል ከአካስተዳዳሪዎቹ አንዱ ሆኖ ሲሰራ የነበረ እና ዛሬ ይህንን የራሱ ክፍል ከፍቶ ከኖርወይ ጸረ ትግሬ ዘመቻ እያስተባበረ የሚገኘው ዘረኛ ግለሰብ “መተማ” በመባል በፓልቶክ ስም የሚታወቅ ግለሰብ ነው። ከላይ አንደገለጽኩት ደምበኛ ስሙ ዓሊ ሊበን ይባላል።

ግለሰቡ የትግሬ ጥላቻው በጣም ስለበረታበት እንዲህ ይለናል።
“ወያኔዎች እና  ትግሬዎችን በየመጠጥ ቤቱ፤ በየጉራንጉሩ ስታገኝዋቸው በስለት በጥይት በድንጋይ በብትር ባገኛችሁት ነገር ግደልዋቸው፡ ይላል። ይህ አንግዲህ ያለ ምንም የሕግ ክስ እና ማጣራት ነው የግድያው ትዕዛዝ የሚያስተላልፈው። አንዲህ ይላል፤
“ከትገሬ የሚመረጥ ‘ሰው ነው’ ብለህ የምትጠራው ’ ሰው’ የላቸውም። ከዝንጀሮ ምን ቆንጆ  ይመረጣል? እከሌ እከሌ የሚባል የላቸውም። አምበጣ በሊታ የሚባልላቸው ሁሉ! እባካችሁ ወንድሞቼ እስኪ አምበጣ ይበላሉ ይባላል እና የምታውቁ አስረዱኝ? አምበጣ መብላት-ኸረ አረ ጉድ!!! ….”  …… “ አይቀርም ኦ ኤል ኤፍ በየአካባቢው እየተዋጋ ነው። ምንድ ነው ወደ አክሽን መግባት አለብን! ሕዝቡን ለበቀል አታስነሱ የሚሉ አሉ። ኖ ኖ ኖ!!! ሕዝቡን ለበቀል ነው ማስነሳት ያለብን። በየከተማው የሚገኙትን ወጣቶቻችንን ለበቀል ማሰለፍ አለብን።” ይላል።
 እንደዚህ የሚለው ለወያኔ አባሎች እና ባለስልጣኖችንን ነው የሚል መከራከሪያ ቢመጣም እሱም በመደበላለቅ አንዴ ሕዝቡ ይላል አንዴ ለወየና እና ተከታዮቹ ይላል። ቢሆንም  በጥናት ያልተካሄደ አናርኪ ብቀላ በትግሬ ሕብረተሰብ በየመንገዱ እና በየመጠጥ ቤቱ እየጠበቁ ማጅራት መምታት (ያውም ባዶ አጅ የሚወሰድ የዱርዬ የማጥቃት እርምጃ) ላይ ምን አይነት ጥቃት እንሚያስከትል እና በትጥቅ እና በድርጅት  የተደራጀው ትግሬውም እራሱን ለመከላለከል ሲል ከወያኔዎች ጋር  ሆኖ የሚወስደው እርምጃ “ምን ዓይንት አስከፊ አጸፋ” በማንኛውም ተጠርጣሪ ዜጋ ላይ አንደሚሰነዘር ይህ “ጅል” ሰው የተረዳው አይመስልም።

አንዴት አንደሚደረግ ደግሞ ሲመክር “ትንሽ ፋይናንስ ብቻ ማድረግ ነው” ፤ ልክ እየጠበቁ ብቻ ማጅራት ማጅራታቸውን እያሉ የሚጥሏቸውን እንፈልጋለን! እርግጥ አነዚያ ሰዎች ገንዘብ የላቸው፤ ሥራ የላቸውም ፤ አንዳንድ ነገር ኦርጋናይዝ እንዲሆኑ ፋይናነስ አንዲያገኙ “ፈንድ ረይዚንግ” ማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች አገራቸውን ለቅቀው ፤ አገራቸውን “ደደቢትን’፡ለቅቀው በየክፍለሃገሩ አገራችን ውስጥ ነው ያሉት።ጠጥቶ ሲወጣ በጭቤም ይሁን በጉራዴም ይሁን መግደል ነው። በእኛ አገር እኰ ነው ቁጭ ያሉት!” ይላል አቶ አሊ ሊበን በጥላቻ እና ስሜት ተውጦ

አንዱ ሰው “መተማ ለምን ድነው እንዲህ ዓይነት የድንቆሮች ዘመቻ የምታደርገው” ይገርማል!” ብሎ በመጻፉ ፡ መተማ አንዲህ ይላል “ምንድ ነው የምትገረመው” ገና ጆሮህ ይቆረጣል። ተመለክቱ ወንድሞቼ “ከደደቢት ትግሬ ተነስቶ “ጅጅጋ” ምን ይሰራል? እዛ ጅጅጋ ያሉ ወጣቶችን ኦርጋናይዝ አድርጐ ለአገሩ ባይተዋር ስለሆኑ አየተደበቁ መግደል ነው።በየአሉበት በክፍለሃገር፤ወረዳ፤ቀበሌ በየገጠሩ ሁሉ እየለቀሙ መግደል ነው። 85 ብሔረሰብ አንድ ሆነን ከተነሳን ባንድ ምሽት “በብዙ ሺሕ” የሚቆጠሩ  ሊያልቁ ይችላሉ።
አንዱ ደግሞ እንዲህ ሲል “መተማን” ይጠይቀዋል፦ “Are you drinking?” ብሎ ይጠይቀዋል። ኖ! ለምንድነው የምጠጣው? ሌባ ! ገና ትለበለባለህ! በየክፍለ ሃገሩ ሥራ ያጡ ወንድሞቻችን ፋይናንስ አድርገን አነሱን ብቻ ማስነሳት ነው። መምታት አይደለም ፤አንዲሞቱ ነው የሚፈለገው! ባንድ ምሽት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደል አንችላለን።”
ካለ በሗላ ፤
አንዱ “ሞክር እና እሲኪ እናያለን!” ብሎ ስለጻፈ ፤ “መተማም” “ኦኬ! ቆዩኝ ወንድሞቼ ይህንን ሰው ላሰናብት በማለት በቀይ ቀለም  አሰናበተው። አንዱ ጣልቃ ይገባ እና “መተማ! አውነትህን ነው። ትግሉ የተጀመረው አሁን ይህ ክፍል ከተከፈተ በሗላ ነው። ወያኔ “ከነዝርያዎቹ” ከነቡችላዎቹ ይወድማል።”  እንግዲህ ዝርያ ማለት በሐረግ የተያያዘ ነገድ ማለት ነው። በሐረግ ከወያኔ ጋር የተያየዛው ዘር ማንዘር/ዝርያ ደግሞ ትግሬ ማለት ነው። “ቡችላ” ደግሞ የፖለተካ/የእምነት ተካታይ/አገልጋይ ማለት ነው።

ቀጥሎ አንዱም ተከትሎ አንዲህ ይላል። “6 ሚሊዮን አገይንስት 80 ሚሊዮን” ነው የተነሳነው። ቆጨራ አንኳ ይዘን ብንንሳ 6 ሚሊዮኑን ሰዎች መቆራረጥ እና መክተፍ አንችላለን ብየ ነው የማስበው። ዕቅድ መንደፍ አለብን። በተለያዩ ጊዜዎች መግደል ሳይሆን ልክ አንደ እጅብት አፕራይዚንግ በማድረግ ባንድ ቀን እና ሰዓት ማድረግ አለብን። ግራውንዱ አሁን እየተነጠፈ ነው ያለው ፤ በዚሁ ቅስቀሳው አንቀጥል!። እኛ ኢትዮጵያዊያን “ፕሊስ” አፍ ብቻ ሳይሆን “ፋይናንስ” አንድናዋጣ እና ይህንን ሥራ እውን ለማድረግ “ከባክ ግራውንድ” የሚያስተባብሩ ሰዎች ተመርጠው፤በየቦታው “የሰክየሪቱ፡ የፋይናንሱ ሥራ አንዲጀመር ማጠናከር አለብን አላለሁ።”  ይላል። እዚህ ክፍል ውስጥ “ኦ ኤል ኤፍ” “የአዋሽ ዓፋር” “ኤርትራኖች” “አክራሪ እስላሞች” ያለ ምንም ስጋት ጸረ ትግሬ የሚያናፍሱበት ክፍል ነው። እጅግ ፤ እጅግ አደገኛ የሩዋንዳ ዓይነቱ እልቂት አንዲፈጸም የሚጥር ስብስብ ነው።
 አስፈሪ ክፍል!

አንዳርጋቸውን አስመለክቶ ኖርወይ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ዋና አስተባበሪው ክፍል ይህ ክፍል ስለነበር “አንዳርጋቸውን በመጥፎ የተቸ  “አለቀለት” ባውንስ! አማካሪዎቹ ደግሞ ኤርትራኖች ናቸው “ዛንዜራ” የተባለው የሻዕቢያ ውሻ መተማን አንዲህ ሲል ያማክረዋል። አንዳርጋቸውን ለመተቸት የሚመጡ ሰዎች “ሶፍት ዌር እሰጣሃለሁ እስከመቸውም እዚህ ክፍል አንደማይደርሱ “የሚፍቅ ሶፍት ዌር” ነገ አመጣልሃለሁ። ይለዋል። እሱ ደግሞ “በጣም በጣም ጥሩ! እሺ!” ይለዋል። ይታያችሁ “ሻዕቢያ” በኢትዮጵያዊያን የመወያያ መድረክ ውስጥ ምንኛ ጉልበት እና ነፃነት አንደሚሰማቸው። ሻዕቢያዎች ወያኔን የሚተካ አሽከር የሚሆናቸው ተቃዋሚ አግኝተዋል።

ከዚህ በላይ የሰማችሁት በጣም የከፋ የዘር ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻም ሆነ ደርግ ሲያደርገው አንደነበረው “ሥራ አጥ እና ማጅራት መቺውን” በገንዘብ እየገዙ ያለ አገሩ እና መሬቱ ጅጅጋ እና ሌሎች ክ/ሀገሮች  ድረስ መጥቶ እየገዛን ነው የሚሉትን ወያኔን ለማጥፋት በስመ ወያኔ “ትግርኛ ተናጋሪውን” በሙሉ ወያኔ እየመስለው የሚገድል ናለው የተቦወዘ፤ በሽተኛ እና መጅራት መቺ እና ሰካራም ላምፐኖችን በገንዘብ ገዝቶ ለግድያ ማዘጋጀት (ሰውየው አንዳለው 6ሚለዮን ለመጨፍጨፍ) የሚደረግ ቅስቀሳ የሚያስከትለው መዘዝ ተጠያቂዎች ናችሁ? ተብለው ቢጠየቁ “ተጠያቂዎች አይደለንም ብለው በሗላ አንደሚሸሹ አያጠራጥርም። አንዳወም መተማ ፕሮፌሰር ሙሴ ዘንድ ለቃለ መጠይቅ ሲቀርብ “አላልኩም” በማለት ለመዋሸት ይቃጣዋል። አስገራሚው እውነታ ግን ሌላውን በገንዘብ ገዝተው አድርግ የሚሉትን ግድያ  እራሳቸው ሄደው ማድረግ አይችሉም። ምክንያቱም “ኖርወይ ላይ አሜሪካ እና ለንደን፤ ኔዘርላንድ ሆኖ በሞቀ ኤክሰክዩቲቭ  ወንበር ላይ ተቀምጠህ ፤ በመሽከርከር ‘ማይክ ጨብጠህ”፤ ቢራ በጎን አስጠግተህ ማጅራት መቺን ማዘጋጀት እና ከሞቀው ወንበር እራስን አስነስቶ አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ በገንዘብ የሚገዛ  “ማጅራት መቺውን” ማደራጀት ጋር ልዩነቱ የተለያየ ነው እና። ራዲዮ ኮሊንስ የሰራውም ይህንኑ ነው!

ብቻ ማጅራት መቺ አደራጅቶ ነፃ ከሚያወጣን የግንቦት 7 ደጋፊ ቡድን እና ፓል ቶክ ይሰውረን! በነገራችን ላይ መተማ የተባለው የግንቦት 7 ደጋፊ ደካማ ግለሰብ እና ሻዕቢያዎች አንደልባቸው የትግራይን ሕዝብ የሚዘልፉበት እና የሚቆጣጠሩት ይህ “የኢትዮጵያን ናዚዎች ኔት ወርክ ፓል ቶክ ሩም”  አንደ የጓዲት ሥርጉተ ሥላሴ “ካረንት” እየደከመ ሲሄድ ወይንም ከነጭራሹ ሲዘጋ “መነሻው” ምን አንደሆነ እንደሚገነዘበው ተስፋ አደርጋለሁ።          
በሌላ ቀን የግንቦት 7 አባሎች ኤርትራ ድረስ ሄደው ዕርዳታ ጠይቀው ወያኔን ማስወገድ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን “ጐረቤት አገር” ለሚሏቸው ለኤርትራኖችም  ከወያኔ ራስ ምታት ነፃ ለማውጣት አንደሚጠቅም የገለጹበት ሰፋ ያለ የፕሮፓጋንዳ ንትርክ በሚቀጥለው እንመከለከታለን። (የግንቦት አባሎች ባንዳዊ ሥራ እና የሰብሓት ነጋ አባባል ስለ ኤርትራ ተቆርቋሪነት ተመሳሰይነቱን በሰፊው እንመለከታለን); ለወደፊቱ ኤርትራን የሚነካ በግንቦት 7 መንግሥትም የማይታሰብ ነው ማለት ነው።ወዬ! ይህች ዛሬም በጭልምልም መብራት የምትኖሮዋ ፊያሜታ ጊላይ ስንቱን በፍቅር ነደፈቺው!

አንድ ነገረ ግልጽ ለመሆን ግን በዘመቻ መንጥር “ጌጥ የለ ፤ምቾት የለ” የሚለን  የጓዲት ሥርጉት እጅ “ጉርባችንን እስኪአንቀን” ድረስ ስለ “ንቀል” እና ስለ “መንጥር” ፤ ስለ “ነስንስ” የግንቦት 7 ዘመቻ አራማጆች መተቸት አንደማንቆጠብ ጓዲት “ሥርጉት” አንዲያውቁልን አንደ እሳቸው በትሕትና ጎንበስ ብለን አንገልጻለን። በነገራችን ላይ ከተከላካይነት  ከአጥቂነት ተሸጋግሯል እያሉን ያሉትን የግንቦት 7 ካድሬዎች ይህ ዘመቻ አንዳርጋቸው የሚሉት “የንቀል” እና “የአርግፍ” ዘመቻም ይሁን ለኤርትራ ተወክሎ የሚሰነዘረው “ቅንዘራ” ካሁኑኑ ባይቀጥል ለድርጅታቸው መቆየት ይበጃል አንላለን። አገርን ለድርድር የሚያቀርብ ቡድን ከዚህ በባሰ ብዕራችን አንደሚያሾል ካሁኑኑ አንዲያውቁት አሳስባለሁ። አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)  you can Google “Ethiopian Semay” on Google.com you are welcome to sned your feedbacks and reactions on my email getachre@aol.com