Friday, June 24, 2016

“ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች መንደር! ጌታቸው ረዳ (Editor- Ethio Semay)




ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች መንደር!
ጌታቸው ረዳ (Editor- Ethio  Semay)
“Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa - during the Badime war between Eritrea bandits and Ethiopia gallants)


ከላይ የሚታዩ ፎቶግራፎች፤ ዓለም ያከበራቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ኃይለሥላሴና የዚህ ትችት አዘጋጅ ጌታቸው ረዳ ናቸው።
ሰሞኑን በነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ አቶ አለም ፈቃደ እና በባንዳው ንአመን ዘለቀ ለመተቸት አስቤ ያንን በይደር አቆይቼ ይህንን ቀዳሚ አድርጌዋለሁ።የአቶ አለም ፈቃደ ታላቁ አንዳርጋቸው ጽጌ በምን ትአምር “ታላቁ አንዳርጋቸው” ብለው እንደሾሙት ለመጠየቅ  የተበላሹ የኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ሚዲያዎች ባሕሪ በመሆኑ ለምደናቸዋልና ወደ እዚሁ ጽሁፍ ይዤአችሁ ላምራ።  ይህ ጽሑፍ በሳምንታዊ የትችት አምዴ ከሁለት አመት በፊት በድረ ገጾች ተለጥፎ የነበረ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት መጠነኛ መሻሻል ተደርጎበት የቀረበ ነው። 

ከዚያ በፊት ከአንባቢዎቼ የተላኩልኝን “የቴክስት” መልእክቶች ጥቂቶቹን ላስነብባችሁ። በአንዲት እህት ጽሑፍ ልጀምር። እንዲህ ይላል፤-

“Good Morning our Hero, Gecho!!! I ask God to stand next to you as he stands for his kids. I went to bed with tears and wolk up with tears. You did an excellent job. You expose Shaabiya gangs and Ginbot 7 to our society to what is going on in Eritrea prisons. I can’t continue- my eye still burns. Have a bless day. We love you. Keep up the good work. Peace!”

ሌላኛው ደብዳቤ፤ የሚለው፤-

“ወንድሜ ጌታቸው ረዳ፤ እንደምን አለህልኝ። ሁሌም ታስደስተኛለህ። ያንተን ጽሑፍ ሳነብ፤ ሕሊናየ ይበረታል። ምነው እንደ ቀድሞው አሲምባ ድረገጽ ላይ ጽሑፎችህን አላያቸውም እሳ?” ይላል። 

ጽሑፎቼ በድረገጻቸው እንዳይለጠፉ የወሰኑት “ የኢሕአፓና የወያኔ አርበኞች ዋለልኝ መኮንን እና ማርታ መብራቱን ተችተሃል” ብለው ነው። ብዙዎቹ ፤ ሁሉም በሚያስብል ድምዳሜ፤የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ ሚዲያዎች፤ መሪዎቻቸውን እንዲተቹ/እንዲወቀሱ/እንዲታረሙ/እንዲነኩ አይፈቅዱም። መላዕክቶቻቸው ስለሆኑ መላእክቶቻቸውን መተቸት በጠላትነት ያስፈርጃል። ሌሎቻችሁም እንዲሁ ላበረታታችሁኝ አመሰግናለሁ። ለማንኛውም፤ ትችቶቼን ለማንበብ Welkait.com እና Ethiopatriots.com ወይንም በራሴው ድረገጽ በ Ethio Semay ወይንም ብዙዎቹ እኔ በማላያቸው ድረገፆች ላይ ፈላልጋችሁ ልታነብቡኝ ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ።
ወደ ጽሑፌ ይዣችሁ ልግባ።

ወያኔና ሻዕቢያ በውጭ ሃይላት ተደግፈው በሕገ ወጥ መንገድ መንግሥትነት ተቆጣጥረው አንድ አገር ለሁለት ከፍለው፤ በ1998 ተጠያቂነት በሌለው ጦርነት ውስጥ የ70 ሺሕ ሕዝብ ህይወት አጥፍተው ሲያበቁ፤ሰሞኑን ደግሞ ዛራቸው ተነስቶባቸው ቁጥሩ ያልታወቀ የሰው ህይወት እንዳጠፉ በጉራ ሲነታረኩ አደምጠናቸዋል።

በሰሞኑ ግጭት የተለያዩ አስተያየቶች/ትችቶች/ቃለ መጠይቆች ተሰንዝረዋል። ጦርነቱ ተጀምሯል፤ ማን  ያሸንፍ ይሆን? የሚሉ ሰነፍ ተቺዎች አንብቤአለሁ፤ ጦርነቱን ለማቆም ባድሜ ለኤርትራ ያለ ቅድመ ኩነት/ሁኔታ መሰጠት አላበት፤ የሚሉ፤… ወየኔ ነው ጀማሪ፤….. አይደለም ሻዕቢያ ነው ጀማሪ….. እያሉ ንትርክ ውስጥ የሚገቡ በሁለቱ ወረበሎች የደነዘዙ ብስለት ያጡ ጸሐፍትም አንብቤአለሁ። አንዳንዱ ሰላምና የሰው ልጅ ህይወት በከንቱ እንዳይጠፋ በመስጋት ስጋታቸው በመግለጽ ሰላም እንዲመጣ ሁለቱንም የሚማጸኑ፤ ወይንም አንደኛውን ኮንነው ሌላኛውን ሳይኮንኑ ፤ ወይንም ሁለቱንም ወንጀለኞች እያወገዙ እርቅ ማምጣት አለባቸው ብለው የሚወተውቱ ተቺዎች… አንብቤአለሁ። ይህ ሁሉ ከተጨባጩ ሃቅ የራቀ ስለሆነ፤ መነሻውና ማቆሚያው በቅጡ ካላወቅነው፤ ሰላም ፤ሰላም፤ሰላም ብቻ ስለተመኘን ሰላም ሊመጣ አይችልም።

ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፤ ኤርትራኖችም ሆኑ ወያኔዎች፤ ሁለቱም ከሥልጣን ተወግደው፤ ኤርትራን የሚረከብ ቡድን “ኢትዮጵያዊነትን” አክብሮ አንድ አገር የሚያደርግ፤ወይንም ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የባሕር ወደባችንን በፈቃዱ ለኢትዮጵያ እንዲያስረክብ የሚፈቅድ ቡድን ሲፈጠር ያኔ ወሳኙና የሰላም ምንጩ እና መፍተሄው ይህ ይሆናል።ያ አናደርግም የሚሉ ከሆነ እና የኢሳያስና የሻዕቢያ  መንገድ እንከተላለን የሚሉ ከሆነ፤ ጊዜ ይፈጃል እንጂ በመጪው ‘የነቃ ትውልድ” ከባንዳነት የጸዳ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ ሲደረግ፤ ወይንም የኢትዮጵያ አምላክ በአስገራሚና አስደንጋጭ ተአምራቱ ‘ባንዳው’ መለስ ዜናዊና ‘አበ ነብሱ’ የነበሩት አባ ጳውሎስን በተአምር እንዳስወገዳቸው ሁሉ፤  አንድ አገር ወዳድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ወታደር ወይንም ሲቪል ወደ ስልጣን በመውጣት፤ ባንዳዎች የወሰኑት ውሳኔ ሽሮ ከላይ የተቀስኩትን የሰላም አማራጭ መንገድ አንወስድም ብለው የሚያንገራግሩ ኤርትራ ቡድኖች ከተከሰቱ፤ የናፈቁትን ጦርነት ከፍቶ፤ ዓሰብን ለ30 አመት የተኮናተሩትን ዓረቦችን አንደለመዱት ማራወጥ እና ባሕሮችንን መለስን መቆጣጠር፤ የአሉላ አባ ነጋ ታሪክ መድገም የመጨረሻው አማራጩ የመፍትሔ ሃሳብ ሲፈጸም ብቻ ነው ሰላም እያልን የምንኳትተው ሕልም እውን የሚሆነው። 

ካልሆነ ሰላም ስለተፈለገ፤ መነሻውና ምክንያቱ ሳንዳስስ ‘ሰላም’በገዛ ፈቃዱ በነዚህ ወረበሎች ጊዜ ሊመጣ አይችልም።ሁለቱም ወረበሎች የሚሰጡት መልስ ለጦርነቱ መነሻ እና ለሰላም ጠንቅ በመሆኑ፤ ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የኤርትራ መሬታችንና በባርነት የያዙትን ሕዝባችንን በድርድር ያስረክቡን። ካልሆነ ጦርነቱ መቼም ቢሆን አይቀሬ ነው። የግንቦት 7 ባንዳዎችም ሆኑ የተቀራችሁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ኢትዮጵያ አገራችን እንዴት እና ለምን እንደተበደለች ምክንያት አለኝ፤ ምክንያቴን አንብቡ።


          
                      በዚህ-ጽሑፍ ሻዕቢወያኔዎች 25

አመት-መልስ ያጡበትና ያሳፈራቸው አንድ አጭር እና ግልጽ ጥያቄ እንመለከታለን። ድሮ በልጅነታችንእንእኒ” (ሲነበብ ይጥበቅ) የሚባል ዘመን ነበር ሲሉ ወላጆቻችን ያጫውቱናል።  እኛም ያንኑ ትረካ ተቀብለንዝናብ ሲዘንብጓደኛሞች የሆንን ሁሉ ሁሌም በምንጫወትበት ሞቃታ ስፍራ ሰብሰብ ብለን ተጠጋግተን በብርዱ ላለመጠቃት ተኮማትረን ተቃቅፈን  ስለዘመኑ እውነተኛነት በዓይናችን ያየን ይመስል የራሳችንን ቅጥያ ጨማምረን አጣፍጠን ከፊት ለፊታችን የሚታዩ የድንጋይ ኮረቶች ሁሉ የዛው ዘመን የአምቧሻ ቅሪት መሆኑን በእርግጠኝነት እናወራ ነበር። ዘመኑምዘመን እንእኒይባል ነበር። በዛ ዘመን ምን ነበር? ብለን ስንጠይቅ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ነበር ማረስ መዝራት፤ መውጣት መውረድ አያስፈልግም ነበር።ብዘመን እንእኒ ሕምባሻ እንተሎ እምኒድንጋይ ሁሉ አምቧሻ የነበረበትየእንእኒ ዘመንአጣፍጠው ወላጆቻችን የነገሩንን እና እኛም ጨማምረን ስለ ዘመኑ መልካምነት እናወራ ነበር።ታዲያ እግዚሃር በሰው ልጆች ስነ ምግባር ተቆጣና አምቧሻው ወደ ድንጋይ ለወጠው ይባላል። ኤርትራኖች ምድሪ ባሕሪነፃ ስትወጣ ወደዘመን እንእኒተመልሳ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ሆኖ አንደሚቀየር ለእናቷ ኢትዮጵያም ከሚትረፈረፈው አምቧሻዋ አንደምታጎርሳት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው የኤርትራ ኢኮኖሚስቶች ያልቀባጠሩት ዲስኩር አልነበረም።
 
አንድ እውቅ የጦቦያ ጸሐፊ (ማን መሆኑን አላስታወስኩትም አሁን) ኤርትራ ነፃ ስትወጣ፤ድሮ በጥንት ጊዜ ራሴን ችዬኤርትራስባል የነበርኩኝ  “አገርነኝ  ታዲያኢትዮጵያየምትባል ከኋላየ የተፈጠረች 60 አመት ዕድሜ ያላት አገር በጉልበት አጠቃልላኝ ነው እንጂ አገር ነበርኩኝ፤ አሁን  ግን ነፃ አውጡኝ፡ እያለች እረፍት ስለነሳችን ነፃነቷን ለመስጠት ተዘጋጅተናል እና ኤርትራ የምትባል አገር በፈጠርካት በዚች ዓለም-ምድር ተዘግባ ታውቃት ነበር? ብለው እግዚሐርን ሲጠይቁትኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ብሎ መዝገቡን ሲፈትሽ ማግኘት አልቻለም። አንዲህ የምትባል አገር አላውቅም! ምነው ጊዜን ባታባክኑብኝብሎ እግዚሓርም ራሱ ተገርሞ ነበር ይባላል። ትክክለኛ አባባሉ ባይሆንም በማጠጋጋት (ፓራፍሬዚንግ) አባባል እንዲያ ብሎ ጽፎ ነበር።ኤርትራ ዛሬ 22 አመቷ ነው ነፃ ከወጣች። እገምጠዋለሁ ያለቺውየዘመን እንእኒ ቅዠትድንጋይ ብቻ ሆኖባት ፈዝዛ ቀረች። 
ኤርትራ ሁሉም ሞክራዋለች። ግድያ፤ ዘር ማጥፋት፤ ሕዝብን ወደ ባርነት መለወጥ፤ ጥቁር ገባያ፤ ሌብነት፤ ስም ማጥፋት፤ ውሸት፤ጉራ፤ ወንጀል፤ ጦርነት፤ሽብር፤ስደትና ዕብደት፤ ሁሉንም ሞክራዋለች። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገችየቀራት አማራጭኢትዮጵያዊነትዋንበቁርባንተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። ካልሆነ ግን የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት እንዲቃጠሉ የወሰነባቸው በሽታ የለከፋቸው የአውስትራሊያ በጎችን በምጽዋት ተመጽውታ መሳቂያና መሳለቂያ እንደሆነቺው ሁሉ ኤርትራም በውንብድና የፖለቲካ በሽታ ተለክፋ የመጨረሻ ዕድልዋ ‘መበላሸት፤ስደት፤ጦርነት፤ሞት፤ውርደት’ ይሆናል።በውንብድና እና በውሸት በሽታ ተለክፈው ለሚሰቃዩ ኤርትራኖች እና የወያኔ ትግሬዎች ፈውስ አለን። ኢትዮጵያነት!!
ኢትዮጵያዊነት ለምን? የሚሉ የኢሳያስ አለቅላቂ የግንቦት 7 መሪዎች እና ንአምን ዘለቀ፤ብርሃኑ ነጋ… እና የታሪክ አተላዎች እነ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርገስ፤ ካሳ ከበደ የመሳሰካችሁ አሳፋሪ ባንዳዎች ክቡር ፕሮፌሰር አስራት የተናገሩትን እናስታውሳችሁ። ጥቅሱን ያገኘሁት ከፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ ነው። 
 For the record, both Mr. Meles and Mr Isaiass, and many others, were sitting and listening at the 1991 (July 1-5), "Charter" conference in Addis when the martyred Professor Asrat Weldeyes had said:

   I submit that this conference has no authority to decide, to desist or to delete anything in the name of the Ethiopian people. However, one recognizes the prevailing de facto situation in the country, including the cessation of bloody hostilities among brothers as well as the current momentum for peace and democracy. EPRDF and EPLF can use their special close relations to see to it that the spirit of Ethiopianity and forgiveness be brought to bear to work urgently for a lasting peace between the brotherly and sisterly (Ethiopian-Eritrean) people.

“አትዮጵያዊነት!!!” የዘላቂ ሰላም መፍቻውና ቁልፉ እሱ ብቻ ስለሆነ በዛው መንገድ ተዳኙ ነው ያሉት። ያ ጥሳችሁ፤ረግጣችሁ፤ንቃችሁ በመንገዳችሁ ከቀጠላችሁ ግን፤ ዘላቂ ሰላም ሳይሆን ዘላቂ ጦርነት ብቻ ነው የሚከተለው ብለው ነበር። እውን “ኢትዮጵያዊነት” እየተናቀ፤ ባንዳነት እየጎለበተ ከሄደ፤ ሰላም የሚባለው የነ ሻዕቢያ እና ወያኔ እንዲሁም ከጥቂት አመታት በፊት የተፈጠሩብን የግንቦት7 አዲሶቹ ባንዳዎች የሚዋሹት “የሰላም መንገድ”፤ አጭበርባሪዎች የቀየሱት የባንዳዎች መንገድ ስለሆነ ሕዝባችን ለሁለተኛ ጥፋት እንዳትራመድ እነዚህን በጠራ ዓይን እና ሕሊና መርምራቸው። ታሪክ አለን! ታሪካችን ባንዳዎችም ሆኑ የተባባሩት ግሳንግስ መንግስታት ማሕብር ሊጠመዝዙት አንፈቅድም። አገር ወዳድ ወይንም ባንዳ የሚያስብለን ታሪካችን እና መልህቃች በጊዜአዊ አስቸጋሪ ማዕበል ስንለቅ ወይንም አጥብቀን ስነይዝ ነው። ሁለታችን የሚለየን ታሪክ በማጉደፍ እና ታረክ አጥብቆ በመያዝ ነው። የወላጆቻችን አደራ አናስበላም። አርበኞች ነበሩን፤ ታሪክና ታሪካቸው አለን;፡ታሪካችን እና ጭብጨጣችንም እነሆ አንብቡ። ኢትዮጵያ አለቀላት ብለው ከጠላቶች ጋር የሚደባለቁ ከሃዲዎች “ኢትዮጵያ እንዳላለቀች”  ዛሬም ነገም አለን! አለን! አለን! እንላቸዋለን።፡ታሪካችን እነሆ። መልካም ንባብ….

ጣሊያኖች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ Ethiopia E Finita !!!! (ኢትዮጵያ አለቀላት) የሚል መፈክር የያዙ ትሬንታ ኳትሮዎች አዲስ አበባን ወርረዋት እንደነበር ጆን ስፔንሰር Unity and territorial integrity (የግዛት ውሁድነት) በሚለው መጽሐፉ ጠቅሰው እንደነበር አንድ ፀሓፊ በጦቢያ መጽሄት ላይ ጠቅሰው ነበር። የተጠቀሰው መፈክር፤ ዛሬ ያለምን ጥርጥር ኤርትራ ካለ ኢትዮጵያ መኖር የማትችል በጉራ ብቻ የተነዳች፤ ኗሪዎቿ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ሰሓራ የሚሰደዱባት፤ደካማ አውራጃዎችን የያዘች፤ ያለቀላት ተበላሸች መንደር ነች። ሰርጓም ሞትዋም 25 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ዕጣ ፈንታዋነፃነት” “የኤርትራ መጠለፍ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ አገላለጽ) ብላ የገለጸቺውን ነፃነቷን እንደገናመከለስአለባት (ከአመዳም ሕይወት ለመውጣት ስትል!)።ለ25 አመት የተሰጣት  “የኦክሲጅን ስሊንደርአልቋል! ከዚያ ወዲያ መቀጠል full of difficulties/ ነው። ብልሽት!


ኤርትራዊው አማረ ተኽለ ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ ለዶክተሬት ዲግሪው መመረቂያ የጻፈው የምርምር ወረቀት The creation of the Ethio-Eritrean Federation; a case study in post-war international relations, 1945-1950. ላይ እንዲህ ይላል፤

ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩት የአካባቢው ታሪክ የማያውቁ ወይም ሊቀለብሱት የሚፈልጉ የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ ፖለቲካ የሚጋሩ ብቻ ናቸው። ይላል።
 
 አማረ በድሮ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱን አምኖ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላ ታስሮ ሲፈታ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስራ ለመመለስ ሲሞክርይህ ሰውዬ አባርሩልኝብሎ / ጐሹ ወልዴ አንዳይቀጠር የከለከለው ሰው እንደነበር ኤርትራኖች ፅፈውበታል። አማረ ተኽለ የዛሬ አያድርገው እና ያኔ ሕሊናው ሲከተል በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ የኤርትራ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩ ሰዎችን “/Neo Fascist ፋሺስትናቸው ብሎ ለዲዘርተሼን በጻፈው የመመረቂያው የጥናት ጽሑፍ ነግሮናል። ጊዜ መስተዋቱ! ያኔ የተናገረውን ረስቶ ዛሬ እራሱ ወደ ኒዮ ፋሺስቶቹ በመቀላቀልየኤርትራ ርዕሰ ውሳኔ ኮሚሽነር/አስመራጭበመሆን የውስጥ እና የውጭ የወረበሎች ስብስብ ያዘጋጁትን የወያኔና የሻዕቢያ ሬፈረንደም ባዘጋጁት ሴራ ውስጥ በመሳተፍ እንድትገነጠል ከጣሩት ቀዳሚ ኤርትራዊያኖች አንደኛው / አማረ ተኽለ ነበር።
ባለ ሁለት ምላሱ አማረ ተኽለ ወንበዴዎቹ ያዘጋጁትን የግንጣላ ሴራ ስለ ሪፈረንደሙ እንዲህ ይላል፤

 “the referendum process as one of the fairest and freest of referendums ever.”
 በማለት የኒዮ ፋሺስቶቹ ሬፈረንደም ከማድነቁ በላይ፡ የሻዕቢያ ተቀጣሪ ሆኖ ቱልቱላውን በመንዛት ኤርትራ
 
Eritrea is in the stage of democratic transition በሚል ንኡስ ርዕስ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ድልድይ እንድትራመድ እየመራት ያለው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ አፍሪካ በታሪኳ ያላየቺው ጠንካራ መሪ በማለት።

 There is, as is almost universally agreed by African social scientists, the need for a strong leadership to guide this process. Eritrea is blessed with such a strong leadership whose source of legitimacy is a Rousseauean General will of the population has shaped and shares the vision of the government. It is this leadership that you demonize as authoritarian either out of ignorance or political malice. 

ሲል የምሁርሊጥ”-ነቱን አይ ኤው’ የወያኔ አፈ ቃላጤ ለነበረው ፖል ሄንዝ March 21 /1999 በባድሜ ጦርነት ጊዜ በጻፈው ጽሑፉ ነግሮናል። አሁን አለማፈር ጠንካራ መሪ ብሎ ሲያሞግሰው የነበረው ኢሳያስን በመቃወም፤ የኤርትራ ነፃነትበኢሳያስ ዲክታቶሪያል ባሕሪ እየተረገጠ ነው፤ ሲል ተቃዋሚ ሆኗል ዛሬ ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸችበረዶ ውስጥ ተቀብራ መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶባት ያለች መንደር’ እንደሆነች እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ደጋፊዎቿ የሆኑ የውጭ አገር ሰላዮች እና ጸረ ኢትየጵያ ሃይላትም ይህንን እየደገሙት ነው።
ለምሳሌ’- December 2013, Herman Cohen አንዲህ ብሏል።

ሲል ሌላው ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውአምባሳደር ዴቪድ ሺን-David Shinnደግሞ ገና፤ በጣም ገና፤ ያኔ አዲስ አበባ ውስጥ አምባሳደር ሆኖ ተሹሞ እያለ EEDN በተባለ ዝግ የድረ-ገጽ የወይይት መድረክ ላይ ዴቪድ ሼን ጸረ ኢትዮጵያ ነው ስላልኩኝ እሱን ደግፈው በኔ ላይ ተረባርበው ሲጮሁብኝ ለነበሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ዛሬ እውነተኛ መልኩን January 13th, እንዲህ ሲል
 The idea that Assab belongs to Ethiopia is outdated”  ሲል ገልጿል።

 ልብ በሉ። አገራችን ምን ያህል የባንዳዎች ብዛት እና የውጭ ጣላት እየተረባረቡባት እንዳሉ ጥልቅ ግንዛቤ ይኑራችሁ።ለዚህ ነው ይህነን ሰፊ ትንታኔ አንድታነቡ በትዕግስት የምጠይቀው። የኦጋዴን እና ኤርትራ ተገንጣዮችን የሚያበረታታው የዴቪድ ሺንንአናርኪንግግር ወደ ጎን እንተው እና ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያብርድልብስመኖር እንደማትችል ካወቁ Ambassadors Princeton Lyman, Herman Cohen, David Shinnኤርትራን ከቀዝቃዛው በረዶ እናወጣት ብለው አዲስ ዘመቻ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የፈረንጆቹ ኰቴ ተከትለውም አዳዲሶዩ የግንቦት 7 ባንዳዎችም “ኢሳያስን ወደ ፍርድ አታቅርቡት” “ኢትዮጵያን ይወዳል” “አማርኛ ስለማይችል ነው እንጂ አማራን ጠልቶ አይደለም” “አማራዎችን ጠልቶ ወይንም ገድሎ አያውቅም” “አይገድልም’ ‘አይሰርቅም’፤ ‘ዜጎች አያንገላታም፤ አይገርፍም፤” በተጨማደደ ሸሚዝ፤ በበርባሳ ጫማ፤ በጨረጨሰ መኪና የሚጓዝ፤ ካለ ውሃ ዊስኪ የማይቀምስ፤ ምርጥ ሕክምና ፤ምርጥ ትምህርት በነፃ የሚሰጥ፤ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን መሪ ነው” የሚሉን እነ ብርሃኑ ነጋ፤ እነ ንአምን ዘለቀ አነ አንዳረጋቸው ጽጌም ያው በነ ሄርምን ኮኸን መንገድ እየተጓዙ ነው። ያውም ዓይን ባፈጠጠ ጥብቅና እና በሚያሳፍር  መልኩ።  

የግንቦት 7 ባንዳዎች ኢሳያስን የማድነቅ ዘመቻቸው እጅግ አስገራሚና ለመግለጽ የሚያስቸግር ነው። ኤርትራኖች ተጉዘውበት ስሕተት መሆኑን አውቀው ኢሳያስን እያወገዙ ባሉበት ወቅት ነው ዛሬ የግንቦት 7 ባንዳዎች በአሳዛኝ የታሪክ ጨለማ እየተጓዙ ያሉ። አድናቆቱንና ባንዳነቱን ለግንቦት 7 የተውለት እውነታው ማየት ያቃታቸው ከመሪያቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሆነው የሕዝባቸውን መከራ ሲያበራክቱ የነበሩ ውጭ አገር በድሎት ሚንደላቀቁ ኤርትራዊያን ሊህቃን መርሳት የለባችሁም። ኤርትራኖቹ መከራው በኢሳያስ ብቻ እንደተፈጠረ አስመስለው በመውሰድ ኢሳያስ ከተወገደ ኤርትራ ከቆፈኑ/ከብርዱ ማስወጣት ይቻላል፤ የሚል የሞኝ ዘመቻ ይዘው ቀጥለዋል። ሁሌም ጽሑፎቻቸውን ሳነብብ፤ ያለመማራቸው ይገርሙኛል። ለኤርትራ መሰረታዊ ስቃይ መነሾግንጠላው መሆኑን ሊገባቸው አልቻለም። ማትኰር የነበረባቸውአረቦች፤አንግሊዞች፤አሜሪካኖች እና ጣሊያኖች እንዲሁም እራሳቸው የተጣመሙ የኤርትራ ምሁራን ያጣመሙት የኤርትራ ጥያቄ እና ትግሉ ከጅምሩ የተወላገደ መነሾ መሆኑን መረዳት አቅቷቸዋል። ዛሬም ሊሂቃኖቹ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ጉዞ፤- ለሃፍረታቸው መሸሺያ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከመወሃድ ኤርትራትሙትብለው ፈርደውባታል።
 
ሞት የውርደት መሸሻ ዋሻ ነውና፤ ከውርደታቸው ለመሸሽ ሲሉ ሞቷን እያቀላጠፉላት ይገኛሉ። ወዳጄ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃንየ በቅርቡኤርትራ ሞታለች….” ብሎ በትግርኛ ጽፎ በላከልኝ 46 ገጽ ላይ የኔን አባባል ያረጋግጣል።

 ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ መኖርም ሆነ በፌደረሽን መኖር እንደሚጎዳቸው የድሮ የባሕር ነጋሽ ተወላጆች በፌደረሸን ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሆነው የመጡ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኞች አስመራ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት በአቤቱታ መልክ ገልጸዉ እንደነበረ ታሪክ ዘግቦታል። ኤርትራ እስከ 1889 . (..) ድረስ፤ መረብ ምላሽ/ምድሪ ባሕሪ/ባሕረ ምድር/ባሕሪ ነጋሲ/ባሕረ ነጋሽ እየተባለች ስትጠቀስ የነበረቺው የጥንቷ ኢትዮጵያ አካል የአሁኗኤርትራ” (በፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ አጠራርየባርነት ስም”) ኗሪዎችሓንቲ ኢትዮጵያ/አንድ ኢትዮጵያ’ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ብለው በመነሳትማሕበር ፍቕሪ ሀገርድርጅትን የመሰረቱ ወላጆቻቸው መገንጠሉ ኤርትራን እንደሚጎዳ እና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ራሷን ችላ መኖር የማትችልበት ምክንያት ለሕብረቱ ጥያቄ  ምክንያቶቹ ካቀረቡዋቸው ነጥቦች ውስጥ በምጣኔ ሀብቱ እና በቤተሰባዊ ግንኙነት በሚመለከት ከክረስትያኖቹ እና ከእስላም ማሕበረሰብ ተወክለው አቤቱታ አቅራቢዎች በሁለት ነጥቦች የሚከተለውን አቤት ያሉበትን አቤቱታቸውን ታሪክ ዘጋቢዎች በጦቢያ መጽሄት ላይ ያኔ ኤርትራ ነፃ ወጣህ ባለችበት ወር ከዘገቡት ሰነድ ልጥቀስ።
 እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ በጥሞና አንብቡት፡

                  “እኛ በዛሬው ኑሮአችን ከኢትዮጵያ ተለይተን ለመኖር የማንችል ስለመሆናችን የሚጨበጥ ማስረጃ የምትጠይቁ ሁሉ ይህን የመሰለውን ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉ ብዙ ማስረጃዎችን ላቀርብላችሁ ዝግጁ ነኝ። ከሁሉ አስቀድሞ መርማሪው ኮሚሲዮን ባቀረበው ውስጥ እንደተገለጸው እኛ የኤርትራ ሕዝብ ለኑሮአችን በቂ የሆነ እህል በደጋው አገር ለማብቀል የማንችል መሆናችንን አረጋግጠናል። ይህም በመሆኑ ስንዴ ጤፍ እነዚህን የመሳሰሉትን ለኤርትራ ሕዝብ ምግብ የሚያገለግሉት ከኢትዮጵያ መግዛት አለብን።..”  

ዛሬ፤ ያ እውን ሆኖ ጤፍ፤በርበሬ፤ ቡና የመሳሰሉ ምግብ ቅመሞች ወደ ኤርትራ የሚገባው በጥቁር ገበያ በትግራይ መንደሮች፤በጁቡቲ፤በየመን፤በሱዳን ዞሮ እየገባ ነው፤፡

 እንደዚሁም ደግሞ የእስላሞች ሊግ ቃል አቀባይ ባደረገው መግለጫ የሚከተለውን ተናገረ፦
                   “ የኤርትራ መሬታችን ጤፍ የማያፈራ መሆኑን በኢትዮጵያ ሰሜን የሚገኘው የትግራይ ክፍል እንደዚሁ በመሬት በኩል ድሀ ሆኖ ለኤርትራ ምንም ዓይነት ጥቅም የማይሰጥ በመሆኑ በየአመቱ በብዙ ሺሕ ሕዝብ የሚቆጠሩት ሕዝባችን ከብቶቻቸውን እየያዙ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጐንደር አውራጃዎች ተሻግረው ከብቶቻቸውን ያበላሉ። በዚህ ሁኔታ የትግራይ መሬት በምሥራቅ ኤርትራ ክፍል ላሉት በቆላ ውስጥ ለሚኖሩት ሕዝቦች ከብት የሚያግጡበት ሥፍራ ሲሆን፤ ጐንደር ደግሞ በምዕራብ አውራጃ ለሚኖሩት የሚበዙት እስላሞች ለሆኑት ሕዝቦች ከብት ማሰማርያ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህም በምሥራቅና በምዕራብ ኤርትራ (በምፅዋ እና እሱንም በመሳሰለው አውራጃ) ላሉት ክርስትያኖች እስላሞች ለኑሮአቸውን ከኢትዮጵያ ውስጥ አድርገዋል። እነሱም ከኤርትራ ውስጥ ለመኖር ቢፈልጉ ኖሮ በረሃብ ባለቁ ነበር።’ ይል እና በመቀጠልም፤-……

“ ለሕዝቧ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምግብና እህል ከኢትዮጵያ በመግዛት ብቻ የምትደገፈው ኤርትራ ከጥቂት ጨው በስተቀር ወደ ውጭ የምትሸጣቸው ሌላ ዕቃ የላትም። ይህም በመሆኑ ያገር ውስጥና የውጭ አገር ንግዳችን የሚበዛው ክፍል በትራንዚት ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ የንግድ ዕቃና ለኤርትራ ሕይወት የሚያስፈልግ ምግብ ብቻ ሆኖ ይገኛል። ይህን የመሰለው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገው ንግድ ቢቋረጥ የምፅዋ ወደብና መላውም ኤርትራ ንግዶች ሥራቸውን ያቆማሉ። ከእነዚህም ከኤኮኖሚ ማስረጃዎች በስተቀር ይበልጥ ጠቃሚነት ያለውና ከአእምሮአችንም ምንጊዜም የማይለየው ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን አንድ የኢትጵያ ሕዝብ ክፍል ሆነው የነበሩበት መሰረተታዊ ጉዳይ ቀርቦ ይገኛል። የጋራ ጥንታዊነታችን የልምዶቻችን የቋንቋዎቻችን ፤የሃይማኖቶቻችንና የጥቅማጥቅሞቻችን መተሳሰር በጣም ጥልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ግልጽና ተገቢ በሆነ አኳሗን በሚያጠግቡ ለመግለጽ ምቹዎች ናቸው።

በማለት በምጣኔ ሃብቱ ረገድ የሚደረስባቸው መከራ ከላይ የተነበዩት ፍራቻ ትክክል ሆኖ ይኼው በዓይናችን እያየነው ነው (ድበቁ የኤርትራ ርሃብ በሚል የተዘገበ ቪዲዮ፤ ወይንም እኔ በአንድ ዘገባ ባቀረብኩት ውስጥ ኤርትራኖች መንገድ መውጣት እያፈሩ ቤት እያንኳኩ  ህጻናት ይዘው ቁራሽ እንጀራ እንዴት እንደሚለምኑ፤ ያቀረብኩትን አስታውሱ)።

ቀጥሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የመዋሃድ ጉዳይ ዋል እደር ማይባልበት መሆኑን እና ተሎ እንዲፋጠን ሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ኤርትራኖች በተመሳሳይ መልክ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል። ያካተቱት ዝርዝር ሐተታ ረዢም በመሆኑ፤ የመጀመሪያዋን ብቻ ልጥቀስ፦ አንዲህ ይላል፤-
 እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ሁለት መቶ ሺህ የምንሆን ኤርትራውያን በኤርትራ ውስጥ የሚኖር ወንድሞችና ዘመዶች አሉን። የእነሱንም ችግር ብዙ ከመሆኑ በስተቀር በዚያ ክፍል በሚገኘው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ውስጥ አለመጠን ተጨቁነው ይኖራሉ። የሚበዙት የተማሩት ኤርትራውያን ከኤርትራ እየተሰደዱ ባሁኑ ጊዜ በእናት አገራቸው (ኢትዮጵያ) ውስጥ በነፃነትና በመልካም የኑሮ ደረጃ ተደስተው የሚኖሩ መሆናቸውን እዚህ ላይ ማንሳት አስፈላጊ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ካገራችን መለየታችን ብቻ ሳይሆን ከወሰን ባሻገር ያሉት ወንድሞቻችንና ዘመዶቻችን በችግርና በጭቆና ውስጥ እንዲኖሩ ማወቃችን ነው። ስለዚህ የኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት አንድ ውሳኔ አንዲያገኝ ልመናችንን እናቀርባለን። 
ሲሉ እነሱም በበኩላቸው ጥያቄአቸው ለኰሚሽኑ በደብዳቤ ገልጸዋል።
 የትግሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን የባሕር ወደብ አልባ ለማድረግ ለኤርትራኖች ወግነው የተጠቀሙባቸው የቅን ግዛት ካርታዎች እና ውሎች በዛሬው ዘመን ውድቅ መሆናቸውን ለማየት የተለያዩ ካርታዎችን እንመልከት እና ውይይታችንን እንደምድም። ድርጎቹ እነ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም ንአመን ዘለቀ የመሳሰሉ አዳዲስ ባንዳዎችም ፤ “የኤርትራ ነፃነት በሕግ የታወቀ ነው፤ ያለቀለት ነው፤ ኤርትራ፤ ዓሰብ፤ ወዘተ… ወደ እሚለው ዝባዝንኬና ጥያቄ አንመለስም”  የሚሉን ጨለምተኞች እና ባንዳዎች ወይንም የሻዕቢያ ቅጠር ወታደር ሆኖ የቀን አንጀራ ፍለጋ የተሰማሩትን ድሃ “ትግሬዎችን” ከወቅርቅ ለቀማ ሸቅላቸው እያሰናከለ ወደ ትግራይ ድምበር ሾልኮ ገብቶ ትግሬዎችን የሚጠልፉት “ ዓሰብ! ዓሰብ! የሚሉ የአማራዎች ጥያቄ ነው” የሚሉ  የኢሳያስ ሎሌዎች የሆኑትን የ“ዲምሕት” ባንዳዎች ሁሉ እነዚህ ካርታዎች እንዲያጤንዋቸው እንጠይቃቸዋለን።
ሦስት ካርታዎችን እንመልት
 የሚከተሉት 3 ታሪካዊ የተለያዩ የኢትዮጵያ መልክአ ምድሮችን እንመለከታለን። ይህ መልክአ ምደር/ማፕ የፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ የምርምር ውጤቶች ስለሆኑ አስቀድሜ ለሳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በእነዚህ መልክዓ ምድሮች የምንመለከተው ቁም ነገር ጣሊያን ከአፄ  ምንሊክ ጋር ያደረገው የድምበር ውል በማፍረስ እራሱ ያዘጋጀው 1888 እስከ1928  ኢትዮጵያን ያዋሃደ የመጀመሪያው የኮሎኒ/የወረራ መልክዓ ምድር /ካርቶግራፊን እንመለከታለን። ከዚያ 5 አመት ግራ እና ቀኝ በጀግኖች እየተዋከ ቆይቶ 1933 . ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ተባረረ። 

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ጣሊያን በሠራው ካርቶግራፊ እና እራሱ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ግዛት መሆናቸውን የሰራውን እና ውሉን አፍርሶ የሰራውን መልክዓ ምድር ተከትለው ሕዝቡን በማማከር እና ከላይ ባስነበብኳችሁ የኤርትራ ጥያቄና ፍላጎት እሳቸውም ጠቅልለው ሕጋዊ መልክዓ መሬታቸውን እስከ 1966 . ድረስ አስተዳደሩ።
 ከዚያ ደረግ 1966 እስከ 1991 . ድረስ የተረከበውን ሕጋዊ መልክዓ ምድር ሲያስተዳድር ቆይቶ በዚያ 17 አመት ውስጥ ውስጣዊ የድምበር አስተዳዳር ለውጥ አደረጎ ዓሰብን እና ሌሎችን በራስ ገዝጀሪ መንደሪ’ (ሪዲሰትሪክቲንግ) ሕግ በመከተል አስተዳደሩ ወደ ወሎ አዛውሮታል።
 የመረብን ወንዝ ጥሼ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ድምበር ከገባሁ በጣሊያን እና በምንልክ የተደረገው ዉል አይጸናም ብሎ የፈረመበትን ዉል ድምበር ጥሶ 1928 . ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወርሮ የኮሎኒ አዲስ መልክዓ ምድር የሰራበትን ብቻ ሳይሆን፤ እኔ በሆነ ምክንያት ኤርትራን ለቅቄ ስወጣ፤ ኤርትራ ለሕጋዊ ባለቤቷ ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ፡ ያለውን ዉል ሁሉ ማጤን ያስፈልጋል። 
 ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በወላጆቻቸው አስተዳዳር ሥር በአጥንታቸውና በደማቸው ተከብሮ የቆየው የባሕር ነጋሽ ምድር ዛሬራሳቸውንወያኔብለው የሚጠሩ ትግራይ ውስጥ የበቀሉ ባንዳዎቹ የኤርትራ ጉዳይ የኮሎኒ ጥያቄ ነው፡ በቅኝ ግዛት የያዘቻት ደግሞ ኢትዮጵያ ነች፡ ስለሆነም መለክዓ ምድሩን ለማካለል በኮሎኒ/በቅኝ ግዛት ደምብ እና ካርታ ተደራድረን ኤርትራን ጉዳይ እንፈታለን ያሉትንም ቢሆንየኮሎኒሕግም ቢሆን አልተከተሉም። አሁን አሁን ከአልጄሪስ ስምምነት ወዲህ ብዙ የወያኔ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ስምምነቱ የወያኔ መሪዎች እንጂ የሕዝብ ውሳኔ እንዳልነበረ ሁለት ያታወቁ የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ይገልጹታል፡-
 “Before anything else, the people living in the region called “Eritrea” are, Tigreans. The idea of “Tigreans” and “Eritreans” as separate peoples, was never ours. See editorial (December 1993) Ethiopian Commentator, Haile Mariam Abebe.).
ሻዕቢያዎች እየነገሩን ያሉት ኤርትራ ነፃ የወጣቺው በሕግ ሳይሆን በጉልበታችን ነው። ብለዋል። በትግሬ ምሁራን የሚገለጸው እውነታው ግን እንዲህ ነው፦
“When the EPLF was pinned down by Mengistu’s army in Nakfa, the Tigrean fighters arrived for its rescue twice. During the “Red Star Campaign” of 1982, for instance, Tigreans fought in Nakfa on the Eritrean side, for nine months. Furthermore, without the supreme sacrifice of the Tigreans, the demand for Eritrean independence would have been little more than a bargaining chip for a negotiated settlement.”  ( Alem Abbay (1993) “An Unappreciated Gift Horse in the Mouth”, The Ethiopian Times, March/April 1,No. 2)  
አለም ዓባይ ከላይ የነገረን፤ “….ሻዕቢያ በመንግስቱ (ኢትዮጵያ) ወታደር ናቕፋ ላይ ተገፍቶ ትንፋሽ አጥሮት ከተራሮቹ ግድግዳ ተጣብቆ ሞቱን ሲያጣጥር  የወያኔ ትግሬ ተዋጊዎች ወደ ናቕፎ ገስግሰው ቶሎ ደርሰውለት ከፍተኛ መስዋዕት ከፍለው ከደርግ ሃይለኛ ብትር ባያድኑት ኖሮ የሻዕቢያ መጨረሻ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር በደርድር ይቋጨው ነበር።እንዳለው ሁሉ እውነትም ሻዕቢያ ዓሰብን ለመስጠት ዝግጅነቱን ለደርግ መግለጹ ይታወሳል።
ወያኔዎች የኰሎኒ የግዛት ማፕ ብለው ወደ ዓለም መድረክ ለድርድር (ለሴረው) ሲቀርቡ ይዘውት የመጡት ማፕየኰሎያሊስትዋ ጣሊያን እንጂ” “የኰሎኒያሊስትዋ ኢትዮጵያአይደለም። ምክንያቱ ምንድ ነው? ቢባል፤ የመጨረሻዋ ኢትዮጵያ ኮሎኒያሊስት ነች ሲሉ የደሰኮሩበትን ሁለቱወንበዴዎችበግብር ለመተርጎም የኢትዮጵያን ኮሎኒያል ካርታ ይዘው ከሄዱ ከታች የሚታየው 3ኛው ካርታ ሕጋዊ ሊሆን ነው። ደግሞ ዓሰብን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባ መሆኑን በደምብ ስለሚያውቁ እና ስጋት ስላደረባቸው፤ በለመዱት ዓመጽ እና ቅጥፈት ከውጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተመካክረውኢትዮጵያየት ትደርሳለችኢትዮጵያን አምበርክከናታልስለዚህ የበሰበሰ ጣሊያን ማፕ ብቻ ይዘን አንቅረብ ብለው ኤርትራን አስገነጠሉ።
 በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ካርታዎችም ቢሆን መርጠው (ፒክ ኤንድ ቹዝ) ነው ለግንጠላ የሚያመቻቸውን የበሰበሰውን የድሮ ማፕ የተጠቀሙበት።እንደነገርኳችሁ በማፕ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ ጣሊያን የሰራው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ያዋሃደው 1928 እስከ 1933 . የመጨረሻውን ውሉን አፍርሶ የሰራውን አዲሱን የጣሊን ቅኝ ማፕ ሊጠቀሙበት በቻሉ ነበር። ሆኖም ገብሩ አስራት በመጽሐፉ አንደገለጸው በባንዳው ወየኔ አመራር ውስጥ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች ሆነው ኤርትራኖችን ለመጥቀም ከነሱ ጋር ወግነው አገራቸውን ኢትዮጵያ ፍትሕ በተጻረረ ሁኔታ ኤርትራን አስገንጥለው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ያለ ባሕር ወደብ አስቀርተው በጠላት አንደትከበብ አድርገው የፈርንሳይ ጥገኛ የሆነቺውን ከጅቡቲ እና ስርዓት ከፈረሰባት (ፈይልድ ስቴት) ከሶማሊዋ የሐርጌሳ የወደብ ተከራይ ቴናንት/ጥገኛ አደርገዋታል።
ሦስቱ ካርታዎች
ወያኔዎች ለኤርትራ ጥብቅና ቆመው የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሲዘጉ፤ የተጠቀሙባቸው ወጋ ቢስ የሆኑየፈረሱ የቅኝ ግዛት መከራከሪያ ውሎችብለው የሚሞጉቱባቸው በምኒልክ እና በጣሊያን ፋሺስት መካካል ተደረጉ የተባሉ ሦስቱ ዉሎች 1900/19002/1908(እኤአ) ውሎች ናቸው። እነዚህ ውሎች ዋጋ ቢስ ናቸው አንቀበላቸውም ብልን የምንሞግትባቸው ምክንያቶች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያቶች ነው። በቀላሉ አንዲገባችሁ ባጭሩ ላስረዳ፤-

1)    May, 1889 (ኤዘአ)ውጫሌ ውል እየተባለ የሚጠቀሰው ምኒሊክ ለመሳሪያ እና ለገንዘብ ልውጥ ኤርትራን ለጣሊያን ሸጧት የሚባለው ውል የያዘ እና ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ነች የሚለው በጣሊያን ቋንቋ የተጻፈው ከአማርኛው ትርጉም እና ውል የሚጻረር በመሆኑ ምኒልክ ውሉ እንዲስተካከል በትዕግስት እየጠየቁ አንዲስተካከል ቢጠይቁም ጣሊያን አልለውጠውም በማለቱ ምንሊክ 1893 ( ) በግልጽ አወጁ፡ ዋጋ አንዴሌለው ለጣሊያን እና ለዓለም አስታወቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ብሎ 1888 ድምበር ጥሶ (ኢ ዘ አቆጣጠር) ዓድዋ ላይ ጦርነት ከፍቶ ውርደቱን ተከናንቦ እጁን ሰጠ። ከዚያ በፊት የነበሩት ውሎች በሙሉ ፈረሱ።ለጊዜው ለሁለቱ ተዋጊዎች ደምበር ሆነው የሚያገለግሉ ሦስት ወንዞችን መረብ፤በለሳ እና ሙና እንደ ድምብር አጥር ሆነው ተወሰኑ።


2)    ምኒሊክ ሰራዊታቸው ይዘው ወደ ኤርትራ መዝለቁ ፤ጣሊያን ተዋጊ ትኩስ ሃይል፤ስንቅና መሳሪያ በባሕር እየተላከለት አንደሆነ እና በተጨማሪም እዚህ ለመጥቀስ የማያመቹ ሰፊ የሆኑ የመሃል፤የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎች ዝርዝር ትንተናዎች የሚሹ ሰፋፊ ያልተጠቀሱ ምክንያቶችም ጭምር ጦርነቱን መግፋት አደጋ አንዳለው በመገመታቸው ሰራዊታቸው ከድሉ በሗላ በደስታ ወደ እየ መንደራችን አንመለሳለን ብሎ መፍረስ በመጀመሩ እና በከብትና በሰውሕይወት ረሃብ እና በሽታ ትግራይ ውስጥ ግብቶ ብዙ ሰው ስላለቀ (የስንቅ ችግር) እና በመሳሰሉ ሁኔታው አመች ስላልነበረ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ልትቆይ ወሰኑ። ኤርትራ ሲቆይ ድምብር እንዳያልፍ ተፈራረመ።ኤርትራ ለቆ ሲወጣምኤርትራለባለቤቷ ለኢትዮጵያ አንደምታስረክብ 1896 እና 1900 (ኤአ) ውል ገባ። ኤርትራ ለማንም መንግሰት /ሃይል/ተዋዋይ አሳልፋ ለመስጠት ወይንም መሸጥ አንደማትችል ፈርማለች። (በሗላ ቃሉን አጥፎ ኤርትራ ለእንግሊዝ ሰጥቶ ወጣ፤ ወይንም አንግሊዝ በጉልቷ ነጠቀች)


የተጠቀሱት ስመምነቶች አስመልክተው አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ታላቁ የታሪክ ምሁር / ሃይሌ ላሬቦ እንዲህ ይላሉ።
 It should be emphasized that the treaties of 1902 and 1908 under which Eritrea claims the disputed territories are essentially flawed. These territories belong indisputably to Ethiopia and until Italy, in its attempt to provoke another war with Ethiopia annexed them in 1929 by force, they were administered by Ethiopia. What makes even more difficult the settlement of conflict between the two countries according to the colonial treaties is the fact that the geographical map of Eritrea has constantly changed during and after those treaties as the following instances highlight: 

Even under Italian rule, considerable part of Eritrea was under the sovereignty of Ethiopia. This includes the huge expanse of land under the control of Dabre Bizen and its dependencies (daughter monasteries) that were directly administered by the imperial Ethiopian government. If Eritrea insists that the border should be marked according to the above-mentioned colonial treaties, it is within Ethiopia's power to claim back these territories and those forcibly annexed by Zolli in 1928 and 1929. In both ways, Eritrea is bound to lose substantial mass of its land. Moreover, the control of Dabre Bizen and its dependencies will give Ethiopia a safe gateway to the important port of Massawa. Understandably, this will have serious consequences for Eritrea as an independent state.
ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው ደብረቢዘን ገዳም ሳይቀር በኢትዮጵያ ኣስተዳደርና ንብረት ነበር (በውጫሌ ውስጥ ተጠቅሷል)

http://www.ethiopianreview.com/2001/Article_HaileMLareboAPRJUN_2001.html

3)   ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ አልደፍርም ያለበትን የድምበር ውል እንደገና ጥሶ በመረብ እና በኦጋዴን ገብቶ 1928 (ኢዘአ) ኢትዮጵያን ወረረ። 5 አመት ሲዋከብ ቆይቶ ተሸንፎ ወጣ። ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎች ሁሉ ፈረሱ። 

4)  ከዚያ በእንግሊዝ ተንኮል ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መዋሃድ ሲኖርባት ከሃያላኑ አንዱ በመኖሩ ኤርትራን እና ትግራይን ገንጥሎ ለማስተዳዳር እንዲመቸው ፍላጎት ስላደረበት  ኤርትራ ውስጥ እቆያለሁ ብሎ ተንኮል ሰራ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት 4 ሐያላን መንግስታት ሲባሉ የነበሩት የመሰረቱት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ መርማሪ አካል በደረሰበት ጥናት መሰረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር ጉባኤ ኤርትራ በንጉሡ የዘውድ አስተዳደር ሥር ሆና ፤የራስ ገዝመብት ተሰጥቷት 10 አመት ከቆየች ወደ ኢትዮጵያ ትዋሃድ ብሎ ውሳኔ ሰጠ። 1900/1902/1908 የነበሩ ዉሎች እንደገናለሦስተኛ ጊዜበዚህ ባዲሱ ሕይወት እና አስተዳደራዊ ለውጥ ተሻረ።

5)  1944 . (ኢዘ ) ኤርትራ እላይ እንደተመለከታችሁት መሰረት በሕዝቡ ተወካዮች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሙሉ ውሕደት አደረገች። በዚህ ለአራተኛ ጊዜ የቆዩ ዉሎች በሙሉ ፈረሱ።

6)  ዓሰብ ከዋነኛው የኤርትራ ማሕበረሰብ 400 .ሜትር ርቀት ርቃ ትገኛለች። ለብዙ አመታት መላትም እስከ ደርግ ፍጻሜ ድረስ ከኤርትራ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ (ንግድ) እና ማሕበራዊ ግንኙነት ከኤርትራ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር። ዓሰብ ለደሴ 70/ ትርቃለች። የወደብ መጠቀሙ መብት እና ሂሳቡን በሕግ ምረኩዝ ስታሰሉትወያኔዎችባሕር ወደብ ለኛ መከልከላቸው ትግራይ ትግርኚ መደብ ሊጠብቁት የፈለጉት ሴራ አለ (ዓሰብ ወደብና አካባቢ አስቀድመው ወደ ትግሬ አጠቃልለውት እንደነበር በረሃ ውስጥ ያዘጋጁት ካርታ ይመሰክራል)፤ ወይንም በሥልጣን ያሉ ትግሬዎች ወደ ኤርትራ የሚያደሉት፤ ሙሉ በሙሉ ወይንም የሁለት ደም ዲቃላዎች ሆነው ይበልጥ ለኤርትራ በማዳላታቸው ነው። ከሁለቱ አንዱ። 

7)   ወያኔዎች አልጀሪስ ሄደው ባቋቋሙት ፈራጅ አካል 1902/1905/1908/ ጠሊያን የሰራው ካርታ እና ስምምነት አንፈረዳለን ሲሉ በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔይግባኝማለት እንደማይቻል የተፈራረሙበት ምክንያትም ከዚያ የተሰሩ ካርታዎች እና ውሎች ካቀረቡይዘውት የሄዱት ውሉየበሰበሰ፤የማይሰራ መሆኑን አስቀድመው ስላወቁ፤ይግባኝየሚያግድ ስምምነት ሆን ብለው መፈራረማቸውለ፤ግልፅ ሴራ መሆኑን ያሳየናልነ። ለወደፊቱም በሕጉ መሰረትአንድ የመንግስት ተወካይ/አካል/ ሆን ብሎ የአገሩን ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ከፈረመ ስምምነቱ እንደገና እንደሚመረመር የተባበሩት /ሕግ ይጠቅሳል። እነ ሻለቃ ዳዊትና ካሳ ከበደ ግን ይህንን ሊደብቋችሁ ይፈልጋሉ።                                  
 አሁን፤ ለማስረጃ ያቀረብኳቸው 3 የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እነሆ ተመልከቱ እና ወያኔዎች በሴራ እንዴት እንደጐዱን እና በሴራ የተፈጸመ ውል አንቀበልም የምልበትም ምክንያቴን ይኼው ተመልከቱ።  
Map 1. Ethiopia During Fascist Italy's Occupation (1936-41).
Map 2. Ethiopia between 1952-1987.

Map 3. The 1987 Border Regime of Ethiopia  (1987-91).

   በዚህ መረጃ መሰረት ኮሎኒዎች ነን ከተባልን የመጨረሻው የኮሎኒ ማፕ የቀረጸው እና የመጨረሻው ኮሎኒያሊስት ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እናቅርብ። ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ባዕድ ነች በለውናል። በኮሎኒያሊሰት ካርታ/ማፕ እንዳኛለን ካሉ እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ለምን ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? 1964 የካይሮ ውሳኔም ተገንጣዩ የመጨረሻው ቅኝ ገዢ የሰጠው መሬት/ቅርጽ ይዞ ይሄዳል ይላል። መጨረሻ ቅኝ ብለው ወያኔዎች የሰየሙንም እኛ ከሆንን፤ ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑ ኖሮ የኛን ካርታ ይዘው መከራከር ነበረባቸው።ልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው። 
ባንዳዎቹ በእውነተኛ ክርክር ጎሮራቸው ስለታነቁ ለዚህ ጥያቄ እስካሁን ድረስ መልስ ሲሰጡበት የሰማነው መልሳቸውኢትዮጵያ ያለ ወደብ 25 አመት ኖራለች ስለዚህ አያስፈልገንምወይንም በስብሐት ነጋ መልስ መሰረትዓሰብ ሳይሆን ጅቡቲ ነው ለኛ ለኢትዮጵያ የሚረባው” (ዓሰብን አትጠይቁ ወደ ትግራይ- ለትግራይ ትግርኛ መርሃ ግብሩ ስለሚጠቃለል ማለቱ ነው። ወያኔዓሰብበትግራይ ክልል ያካተተ ካርታ ሰርቶ እንደነበረም ታውቃላችሁ።) የመሳሰሉ የማሃይሞችና ተረብተኞች መልስ ከመስጠት በቀር ለጥያቄአችን ቀጥተኛ መልስ ሊመለሱልን አልቻሉም። 25 አመት ያለወደብ ከጅቡቲ፤ከሶማሊ ወደብ እየተከራዬን ኑረናል፤ ስለዚህ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል፤ የሚለውመልስ ሲያጡ የሚመልሱት መልስየውዳቂዎች መልስ ነው።  ለነገሩ ኑሮ አይባልም እንጂ ኤርትራም  እኮ 25 አመት ወደቧ ባዶ ሆኖ ኖራለች። ጥያቄአችን አጭር፤ቀጥተኛና ግልጽ ነው!!!  25 አመት ዳክረው መልስ ያጡበት ጥያቄ አሁንም እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን። 
ዛሬ የፈራነው እና የተነበይነው ተከሰተ እና ዓሰብ እና ምጽዋ ኢራኒያኖች እና ዓረቦች ይዘውታል።፡ይህንን ስንል፤ ውሸታሞች ሲሉን የነበሩት ዛሬ “ውሸታሞቹ” እኛ ወይንስ እነሱ? መልስ እንሻለን። ይህንን እንዳነበባችሁ ታስታውሳላችሁ? 
(ሳውዝ ፍሮንት በመባል የሚታወቀው ‹‹ፎረይን ፖሊሲ ዲያሪ›› በሚባል ፕሮግራሙ የቀረበው አጭር ግን ጥልቅ መረጃ የያዘ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ “Arab Coalition Expands into the Horn of Africa” በሚል ርዕስ ባሰራጨው ዘጋቢ ፊልም፣ ‹‹ይኼ ለኤርትራ ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን የገጠማትን የመነጠል ችግር የሚፈታ ነው፤›› ብሎታል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት የደረሰባትን ‹‹የሥርዓተ አልበኝነት›› ፍረጃም ነፃ ያወጣል ብሏል፡፡ ‹‹በእርግጥ ኤርትራ ማንም ቢሆን ገንዘብ የሚሰጣት ከሆነ ከመደገፍ ወደኋላ አትልም፤›› ይላል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የቀረበው ሐተታ፡፡ በአሰብ እየተገነባ ያለው ወታደራዊ ኃይል በአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ያልነበረና የመጀመሪያው መሆኑንም ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለአካባቢው (ለአፍሪካ ቀንድ) አደገኛ እንቅስቃሴ›› በማለት የአፍሪካ ቀንድ የዓለም አቀፉ የግጭት እንቅስቃሴ መናኸሪያ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ያስቀምጣል፡፡” 
ይህ ሃቅ ዛሬ እውን ሆኖ ከተገኘ በላ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል ሲሉን የነበሩ የወያኔ አለቅላቂ አሽከሮች (አይጋ ድረገፆች፤ ትግራይ ኦን ላይን እና የወያኔ ሎሌዎች ሁሉ) ዛሬ ዓረቦች  ዓሰብን ተቆጣጥረውታል ሲባል “ መንግሥታችን፤ እባካችሁ ወሳኝ የሆነ አርምጃ በመውሰድ ኢሳያስን አስወግዳችሁ  ስጋት የሆኑብንን ዓረቦችን ኣባርሩልን” ብለው ሲጮሁ ሰምተናል። ውሸታሞቹ እኛ ወይስ እነሱ? ነገ እስላመዊ ወንድማማችነትና እና ዓረባዊ ሕብርት ይዟቸው “ሶማሊም ፤ጅቡቲም” ወደቦቻቸውን ቢከለክሉን እና ኤርትራ /ግብፅ’ሳወዲ ኢራን ጋር ጦርነት ብንገጥም……. መሳሪያ በየት ይገባል፤ ምግብስ በየት ይወጣል፤ ሸቀጡስ በየት ይወጣል ይገባል? ይሆናል ያልነውን ሁሉ እየሆነ ነው እና መልስ ስጡን እንጂ! )

እንግዲህ ወደ ቁም ነገሩ ልመልሳችሁ እና ወያኔዎች
የኤርትራን ጉዳይ መፍትሄ ለማግኘት በኮሎኒያሊሰት ማፕ እንዳኛለን ካሉ ለምን እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? ጥያቄአችን አጭር እና ቀጥተኛ ነው። ለመረዳት አያስቸግርም።
ይህንን ለመመለስ 22 አመት ፈጀባቸው- አሁንም መልስ የላቸውም፤ ዛሬም ለጥያቄችን መለስ እየጠበቅን ነው። ወይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢ አልነበረችም በሉን ወይንም ነች ካላችሁ ደግሞ ጥያቄአችንን መልሱ። ካልሆነ ክርክራችሁ አንጅት የሚያሳርርየፖለቲካ ጨዋታ ነው ፕሮፈሰር / ሃይሌ ላሬቦ አንዳሉት 

“…the time gap that exists between these treaties and the Eritrean independence is so vast, and the change in status that Eritrea underwent during this same period is so intricate as to make any appeal to colonial treaties and OAU charter of no use beyond political gimmickry.” 
(Colonial Treaties in the Context of the Current Ethio-Eritrean Border Dispute and Settlement  4th International Conference of Ethiopian Studies, November 6-10, 2000, at the Institute of Ethiopian Studies, Addis Abeba University. Ethiopian Review Ethiopian Review, April 2001)   

ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ጉራዋን እና ዕብደቷን ካላቆመች መጪው ዘመን የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ እየጠበቃት ነው። ምርጫው የራሷ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)  Ethiopian Semay     getachre@aol.com