Tuesday, December 3, 2024

የዛሬ 41 አመት ከአክሱም ጽዮን ድቁና እና ቅስና ተቀብለው ወደ የገጠራቸው ሲመለሱ በወያነ ታፍነው ደብዛቸው የጠፉ ነብሳት ዛሬም ደማቸው ለፍትሕ ይጮሃል! ጌታቸው ረዳ 12/3/24 Ethiopian Semay

 

የዛሬ 41 አመት ከአክሱም ጽዮን ድቁና እና ቅስና ተቀብለው ወደ የገጠራቸው ሲመለሱ በወያነ ታፍነው ደብዛቸው የጠፉ ነብሳት ዛሬም ደማቸው ለፍትሕ ይጮሃል!

ጌታቸው ረዳ

12/3/24

Ethiopian Semay

የትግራይ ፋሺሰት ፖለቲከኞቹ እና አቡነ ሰላማ በሚል የተደራጁ መናፍቃን ቀሳውሰት ሕጉ ካልቀየሩት በቀር እኔ እንደማስታውሰው አክሱም ውስጥ በየአመቱ በሕዳር ወር የጽዮን በዓል ሲከበር የቅስና እና የድቁና ትምህርታቸው ላጠናቀቁ የቤተክሕነት ሰዎች የድቁና እና የቅስና ማዕረግ የሚሰጥበት ዕለት ነው።

ታዲያ ለዛሬ የምንመለከተው በ1975 ዓ.ም የዛሬ 41 አመት አክሱም ውሰጥ ድቁና እና ቅስና የምስክር ወረቀት አግኝተው ወደየ ገጠራቸው ሲመለሱ ጸረ ኦርቶዶክሱ የወያኔ ፋሺሰት ቡድን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች (ለመሳለም የሄዱ 1500 ምዕመናን) ለምን ወደ አክሱም ጽዮን እንደሄዱ እያደነ ሲያስራቸው፤ ሲገድልን ሲጨፈጭፋቸው እንደነበር በተለይ ደብዛቸው የጠፉ 50 ዲያቆናት እንዴት እንደጨፈጨፋቸው እንመለከታለን። 

ከላይ የሚታዩት ሃውልቱ ሥር የተቀመጡ የሃይማኖትና የፖለቲካ ቆሻሾች “ሀገረ ትግራይ” ሚባል የቅዠት ሀገር ለመመሥረት ባሴሩት የሴራ አንደነት ፍቅራቸወን ለመግለጽ ሃውልቱ ሥር ሆነው የተነሱት ማስታወሻ ሲሆን፤ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ድያቆን ብርሃነ ገብርህይወት ይባላል። እንዲረሸኑ ወደ ሞት ሲወሰዱ የነበሩ ከ50 ተረሻኞች መካከል ዕድል አግኝቶ ለማምለጥ የቻለው ብርሃነ ሆድ ዕቃው በ7 ጥይት ተኩሰው አንጀቱን ከዘረገፉት በሗላ ሕክምና ሄዶ የተዘረገፈው አንጀቱን ገልጦ ለጋዜጠኞች ሲያሳይ ነው።

 ከትናንት በስትያ የአክሱም አመታዊ የሕዳርጽዮን በዓል አስመልክተው የወያኔ የዜና ማዕከሎች አክሱም ውስጥ ባለፈው ጦርነት በሻዕቢያ ወታዶች (?) የተጨፈጨፉ ሰላማዊ ሰዎች እያነሱ ፍትሕ ሲፈልጉ ነበር። ያ ተገቢ እንዳለ ሆኖ የትግራይ ሚዲያ ተብየዎችና መሳቂያ የሆኑት የትግራይ ምሁራን ተብየዎችም ጭምር ድርጅታቸው ከበረሃ ጀምሮ እስከ ሥልጣን ጊዜው 17+27+5 አመታት በወያኔ የተጨፈጨፉ ሰለማዊ ሰዎች በሺዎቹ ሲሆኑ አንድም ቀን የተገደሉና የታሰሩ ደብዛቸው የጠፉ ንጹሃን እንዴት እንደተገደሉ፤ ማን እንደገደላቸውና እንደደበደባቸው አመጽ እንደፈጸመባቸው ጥናት አድርገው አያውቁም ወይንም እንዲጠና ወይንም ስለነዚህ ንጹሃን ነብሳት ኣንስተው ፍትህ ጠይቀው አያውቁም። በኔ ውሳኔ እንሱም ወንጀል በመደበቃቸው የወንጀሉ ተባባሪ ናቸው። በሚገርም ሁኔታ በመስቀል እና በቤተክሕነት ጃንጥላ ሥር የተጋረዱ የሃይማኖትና የፖለቲካ ወንጀለኞች ትግራይ ውስጥ ስፍር ቁጥር የላቸውም።

ስለሆነም የዛሬዎቹ  የወያኔ ትግራይ ቀሳውስት እና የትግራይ ወጣቶች ቤተ ዕምነትን የማበላሸትም ሆነ ፍትሕን የመጋረድ ታሪካቸውን እንመልከት

እኔን ለብዙ አመታት የተከታተላችሁኝ አንባቢዎቼ ትግሬዎች (98%) በታሪክ ይቅር የማይባል የተለያዩ ሀገራዊ ወንጀሎች በኢትዮጵያ ላይ እንደፈጸሙ ብዙ ጊዜ ጽፌአለሁ። ሕዝብ አይወቀስም ፤ አይከሰስም የሚሉ ኢትዮጵያውያን ደደቦች እንዳሉና እንደሚያላዝኑብኝ ባወቅም፤ ደደብነታቸውን ለማሳወቅ ብዙ ስላልኩ በዚያው እንቀጥል።

እኔ የተገኘሁበት ይህ ማሕበረሰብ ከዚያ ማሕበረሰብ መወለዱን የሚኮራ አለ፤ እንደ እኔ ባልወለድበት የሚሉም ጥቂት ይኖሩ ይሆናል። የመኩራትን ያለመኩራት በየምክንያታችን መብታቸው የተጠበቀ ነው። አንድ ሕዝብ የሚያኮራ እና የማያሳፍር ታሪክ ሲሰራ እንደ ሁኔታው “አኩሪም አሳፋሪም” አለ። የትግራይ ማሕበረሰብ ችግር በተለይ ምሁሩ የሚያኮራውን ብቻ እየመዘዙ የሚያፍሩበትን እየደበቁ የመጓዝ ባሕል የተለመደ ሆኗል። ስለዚህም ነው ወንጀለኞች ሲዝናኑና ሲከበሩ የናየው።

ላለፉት 49 አመታት ትግራይ ውስጥ ለመኖርና የትግራይ ተወላጅነትህ ሳትነጠቅ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባበት ብቸኛው መንገድ የ“ትሕነግ” (TPLF) ፓርቲ አባል ሆኖ መቀላቀል ወይንም አጨብጫቢ ሆኖ እንደ ልብህ ትግራይ መግባትና መውጣት እንደትችል፤ እንደ ኢንጂነር እምብዛ ታደሰ አካላትህ በቢላዋ ተቆራርጦ ለጅብ ከመጣልና ከግድያና ከመገለል ወይም ተሰውሮ ከመጥፋትና ንብረትህ ከማስወረስ ያለው ብቸኛ መንገድ ሁለቱ አማራጮች እነዚህ ናቸው።

ሁለት አስገራሚ የዚያ መሕበረስብ ክፍሎችን እንፈትሽ ፡ “የትግራይ ካሕናት እና ወጣቶች”። ትግራይ ውስጥ ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ “ጥንታዊው እውነተኛው ኦርቶዶክስ ወይንም ጥንታዊው እውነተኛው እስልምና” ትግራይ ውስጥ በትግራዋይነት የፖለቲካ መርዝ ስለተመረዘ፡ ብዙዎቹ የዚህ ዘርን እና ቋንቋን መሠረት አድርጎ ያንድ ሀገር ህዝብ እንዲለያይ ያደረገ የትሕነግ ዘረኛ ፖለቲካ አቀንቃኞች ናቸው። ከመከተል አልፈው፤ ትግራይ ከኢትዮጵያ ሀገርነት አንድትነጠል በይፋ ሳይሸማቀቁ ጥላቻንና የትግራይ ሕዝብ “ወርቅነት” የሚያስተምሩ “የጳጳሳትን ቆብ ያጠለቁ “የሕሊና ቀውስ የተጣባቸው” እንደ እነ ሰረቀበርሃን የመሳሰሉ ዕብዶችን እንደ እውነተኛ ቄስ አምነው ዘረኛነትና ጥላቻ ሲሰብካቸው አፋቸው ከፍተው ያደምጡታል።

ሌላ ቀርቶ ሴቶችን ያስወለዱ እና ሴቶችን የደፈሩ ጳጳስ ተብየዎች “አባ ሰላማ በሚባለው ወያኔ ያደራጀውና የሚመራው ፖለቲካዊ የሃይማኖት ድርጅት ውስጥ ሕገ ወጥ የጵጵስና ቆብና ካባ የለበሱ ሕዝቡ የኔ ጳጳሳት ብሎ የተቀበላቸው ከላይ በምታዩዋቸው ሃውልቱ ሥር የተኮፈሱ ፎቶዎች መካክል ውስጥ አሉ።

አስገራሚ የሚያደርገው ይህ ክስተት የሕዝቡ ተባባሪነት ነው።  የትግራይ ሀገርነት ለማመቻቸት በወያኔዎች የተቀረጸ <<ፖለቲካ ውስጥ የሚዘባርቁ ካህናት>>  በሚመሩት ይህ ፖለቲካ የተላበሰ የሃይማኖት ድርጅት እየተመሩ እነዚህ ጳጳስ ተብየ መናፍቃን አምነው ሻማና ጥዋፍ አብርቶ ኦርቶዶክስ ነኝ እያለ በሕዳር ጽዮን አከሱም ከተማ ውስጥ ሲጨፍር ያየነው ሕዝብ ጥናት ያስፈልገዋል።

የትግራይ ሕዝብ ወርቅ ሌላው ሕዝብ መዳብ ፤ የትግሬዎች ነብስ ክቡር ፤ የአማራና የዓፋር ሕዝብ ነብስ ርካሽ’ አድርጎ ለትግራይ ሕዝብ ብቻ ጥብቅና የሚቆሙ እነኚህ ቀሳወስት ባንድ አምላክ የተወለደ አንድን ሕዝብ ለያይቶ ናዚያዊ ሰበካ የሚሰብክ ቄስ እና የመሳሰሉ እነኚህ  <<ሃገር ገንጣይ መናፍቃንን>> እየተከተለ የሃይማኖት መሪዎቼ ናቸው ብሎ ተቀብሎ የሚያንጨበጭብ ሕዝብ ኦርቶዶክስ ተከታይ ነኝ ቢለኝ ለእኔ ፌዝ ነው

ትግራይ ውስጥ ያሉ የግንጣላ ፖለቲካ የሚያካሂዱ (ፖለቲካል ክሪሚናልስ) እና ከትምህርት ቤቶች እስከ ወጣት ቡድኖች ድረስ ሰረቀብርሃን የተባለ ዕብድ ቄስ “ሮሌ ሞዴል” (አርያአችን ነው) በማለት በየአድራሹ እየሰበሰበ ስለ ፖለቲካና የትግራይ ሀገርነት ሲሰብካቸው ማየትና እነዚህ ደናቁርት ትውልዶችም በጭብጨባ እየተቀበሉት ማየት የሚገርም ዘመን ነው።

ይህ ወያኔ (ትሕነግ) የተባለ ደም የጠማው ድርጅት ትግራይ ውስጥ ብዙ ደም አፍስሷል። አሁን እንደ ቄስ መስለው የጠመጠሙ ቀሳውስቱ ተባባሪዎች ነበሩ። የትግራይ ቀሳወስት ወያኔ ካደራጃቸውከ1968 ዓ.ም አካባቢ የመጀመሪያ መቅሰፍት የመራው መምህር ገብረኪዳን ደስታ በሚባል “ፋሺሰት” ነበር። ገዳማትን በመውረር፤ብዙ ካሕናትና ቀሳውስትና አረጋውያን የትግራይ ተወላጆችን እየደበደቡ የግድ ጠመንጃ ይዘው ነብስ እንዲያጠፉ ፤ታጋይ እንዲሆኑ ማድረግ ወያኔ በሃይማኖት ተከታዮች ላይ ካደረሳቸው ጥቃቶች አንዱ ነው።

 እነዚህ ታጋይ የነበሩ ቀሳውስት ናቸው ዛሬ ሰው ሲገድሉ ኖሮው ሽበት አውጥተው ጉዳቸው ሳይታወቅ እውነተኛ ቀሳውስት መስለው በየቤተክርስትያናቱና ሃውልቱ ሥር ካባ ለብሰው ሰው መስለው ቆመው መሰቀል ይዘው የሚታዩትና የሚሰብኩ። ሕዝቡ እነኚህን ነው የሃይማኖት መሪዎች አድርጎ በዕልልታ እየተቀበላቸው ያለው። ጉድ አገር ማለት ይህ ነው!

ከአመታት በፊት ባሳተምኩት መጽሐፌ ገልጬው የነበረው የድያቆን ገብረህይወት ታሪክ (ሙሉውን ለማንበብ በድረ ገጼ ላይ አለ ትግረኛም አማርኛውም) ባጭሩ ላቅርብላችሁ፡

እንዲህ ይላል፦

ብርሃነ ትዉልድና ዕድገትህ ብትነግረኝ?

 ብርሃነ፦ ትዉልዴ አድዋ አዉራጃ ሲሆን፤ቀበሌዉ ጣቢያ ኮረም መንደሩ እንዳ መትከል ስብሃቱ ይባላል።

 አድዋ አዉራጃ እያለህ የደረሰብህ በደል ምነድ ነዉ?-

ብርሃነ፦ ቤተክህነት ተማሪ እያለሁ 1975 . ከአክሱም ጽዮን ድቁና ተቀብዬ ስሄድ በወድቅት ሌሊት የማላዉቃቸዉ ሰዎች ኢሳ ወደ ሚባል ወረዳ አስረዉ ወሰዱኝ። በአሁኑ ወቅት ያለዉ ጳጳስ ከደርግ ጋር ሰዉ እንዲገደል ያወጀ ስለሆነ ቅስናንም ሆነ ድቁናን ሊባርክ አይችልም።የሚል ምክንያትም ስጡኝ። 

ጳጳሱ ማን ነበሩ? 

ብረሃነ፦ ስማቸዉን ዘንግቼዋለሁ በዚያ ሰዓት ስማቸዉ መታወቂያየ ላይ ነበረ።

 የትግራይ ተወላጅ ናቹዉ? ብርሀነ፡- እኔ እንጃአማርኛ ነበር የሚናገሩት።

በተያዝክበት ወቅት ማለትም 1975 . አካባቢዉን የሚያስተዳድረዉ ደርግ አልነበረም እንዴ?

 ብረሃነ፦ ከተማዉ ደርግ ነዉ፡በገጠር ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩት ወያኔዎች ነበሩ። 

ከገጠር ነበር ያያዙህ? ብርሃነ፦ አዎ! ከገጠር ነዉ የያዙኝ።

ሌሎችም ቅስና እና ድቁና የተቀበሉ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ታስረዉ ነበር እነሱም ከእስራትና ከቅጣት በሗላ መታወቂያቸዉ ተቀምተዋል።

የምን መታወቂያ?

 …. የድቁና እና የቅስና መታወቂያቸዉ ነበር የተቀሙት።ከዚያ እዚያዉ ቆይተን 1981 / ቀሳወስትም ዲያቆናትም በግድ ወደ ግንባር ዝመቱ አሉን። በዘፈን ይቀስቅሱናል ፤ ሥራ መሥራት አልቻልንም ተሰብሰቡ እያሉ በስብሰባ ያስቸግሩናልይቆጡናል እንዲያ እያልን ስንኖር በ1981 . ግን ዉጥረቱ ሲበረታባቸዉ ነዉ መሰል ግዴታ ታገሉ አሉን። እኛአንታገልም፤የሃይማኖት ሰዎች ነን እናንተ ታገሉበት፡ እኛ ድሆች ነን ስንላቸዉ፡ማን አጥንቱን ከስክሶ ሊያኖርህ ፈለግክ?” በማለት በተለይም ቢሄንየተባለ ታጋይ አፈር በእጁ ከመሬት ቆንጥሮ በማፈስ ወዳፍንጫችን አስጠግቶ እንድናሸት አስፈራራን በአገራችን መኖር ካልቻልን ተሰድደን እንሄዳለን፡ ይለፍ ብቻ ስጡን ስንል ስትፈልጉ በሰማይ ሂዱ እንጂ አይሰጣችሁም እያሉ ያፌዙብን ነበር።

ታዲያ የት እንድረስ?” ስንላቸዉየራሳችሁ ጉዳይ! ከፈለጋችሁ አገራችሁን ነፃ አዉጡ። ነፃ አናወጣም የምትሉ ከሆነ ግን የዚህችን ምድር በረት አትረግጡም። አሉን።ከማን ነዉ ነፃ የምናወጣት?” ደርግም ኢትዮጵያዊ ነዉ እናንተም ኢትዮጵያዊያን ናችሁ።ስንል <ከበስተጀርባችሁ የሆነ ነገር አላችሁ!> በማለት ማሰር እና መቅጣት ጀመሩን።

ስንት ትሆናላችሁ?

 ብርሃነ;- 1500 እንሆናለን። 

ከዚያ ምን ተከተለ? 

ብርሃነ;- ፦ወላጆቻችን ታሰሩ። የእርሻ ማስታዎሻችንም ተወረሰ። ቀንደኛ ዓድመኞች ናችሁ በተባልን በተወሰንን ሰዎች ላይ ከባድ ቅጣት ተፈጸመብን። 6 ወር አስከ ዓመት በእስራትና በግርፋት ተቀጥተናል። ክንዶቹ ለረዥም ጊዜ በቀጭን ጅማት ነገር በመታሰራቸዉ ምክንያት ጣቶቹ ደም አስከ ማንጠባጠብ የደረሰ ጓደኛችንም ነበረ። 

በጅማት ታስሮ እጁ ደም ያንጠባጠበዉን ጓደኛህን ስም ታስታዉሰዋለህ?

 ብረሃነ፦ የአንዱ ስም አላስታዉሰዉም። ሰለዳም የሚባል ቀበሌ ነዋሪ ነዉ። ሌላዉ በግርፋት አንድ እጁ እና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ጓደኛየ ሃለቃ ሓዲሽ የባላል። ቢዚያን ወቅት <ሙሹሮችና ካህናት> ሳይቀሩ <በህማማት ጊዜ ከቤተክርስትያን> ተወስደዉ ከሽማግሌዎች በቀር ሁሉም ታፈሶ ተወሰደ። ለመሸሽ የሞከረዉን እንደ ጅግራ እያሯሯጡ በጥይት ያሳድዱት ነበር።

ይህ ሁሉ የተፈጸመዉ መቸ ነዉ? 

ብርሃነ፦ ከዚያ በፊት ለብዙ አመታት አደርገውታል፤ግን የካቲት ወር 1981 . ጀምሮ ማለት ነዉ ይህ ክስተት። 

ትግራይ ነጻ ከወጣች በሗላ ማለት ነዉ? 

ብረሃነ፦ አዎ:: ከዚያሰዉ እንደ አዉሬ በአካባቢዉ እየተበተነ በአካባቢዉ በቀን ሰዉ የሚባል አይታይም ነበር። እነሱም እንደ ጅግራ እያደኑ ይዉላሉ፤መሬታችንም ለታጋይ ቤተስብ ታድሎ የምንቀምሰዉ የምንልሰዉ አልነበረም።

ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚያስተላልፉ የነሱ ካድሬዎች ካዩን ጥይት ይተኩሱብናል፤ የተኮሱብን ጥይት አልመታንም እንጂ ቁጥር የለዉም።ከዚያ በሗላ እየተንከራተትንና እየተራብን ቆይተን ህዳር 21/1983 . ገረዳ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ለአቶ በርሄ እህል ስንሸከምላቸዉ ዉለን፤ቤት ገብተን ገበታዉ ቀርቦ እህል ልንበላ ስንል ቤቱ ተከበበ። የማይታወቁ ታጣቂዎች ናቸዉ። ከተሰበሰበዉ ሰዉ እኔን ጠሩኝና ዉጣ አሉኝ። መጀመሪያ እህል ይብላ እና ዉሰዱት ብለዉ የቤቱ ባለቤት ቢጠይቁም <<አስቸኳይ መልዕክት ስላለን ነዉ፤አሁን ይመለሳል>> ብለዉ ወሰዱኝ።ሌሎችም ከያቅጣቻዉ ተሰበሰቡ።ወደ 50 እንሆናለን። ሁላችንም በስብሰባ ላይ የምንከራከራቸዉ ነበርን። <<እነዚህ ካልጠፉ ወጣቱ አይታገልም፤በታኞች ናቸዉ ፤ ከደርግ ለይተን አናያቸዉም>> በማለት ከዚያ በፊት እንዳጠፏቸዉ ወጣቶች እኛንም ለማጥፋት ተዘጋችተዉ እየወሰዱን ሳለ፤ እርስ በርሳችን እንነጋገር ነበር። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ይሆናል።

የት ነበር የሚወስዷችሁ? 

ብርሃነ፦ ጫካ ነዉ፤ እኛ አናዉቀዉም። ኢሳ የሚባል በረሃ ነዉ። ምን ይሻላል? ለመሞት ለመሞት እዚሁ እንሙት እየተባባልን እንደገና ጉዞ ጀመርን። አልፎ አልፎ ነዉ እንጂ እኛን ባንድ ላይ አይወስዱንም ነበር። አንድ እዚህ፤ አንድ ደግሞ ራቅ አድርገዉ ሊወስዱን ከፊት ያለዉን ገፍቼ ሸሸሁ። ቁጥር የሌለዉ ጥይት እላየ ላይ ዘነበ። ፀጉሬ ላይ ትንሽ ነካኝ እንጂ አልመታኝም። አምልጬ ሕግ ያለ መስሎኝ ወደ ዋናዉ አለቃ ሄጀ <የማይታወቁ ታጣቂዎች ሌሊት መጥተዉ በደል አደረሱብኝ፤ በነዚህ ሰዎች ላይ ክትትል ይደረግልኝ፤ከየት እንደመጡ ማን እንደላካቸዉ ይጣራልኝ> ብየ አቤቱታ ሳቀርብ፡ <<እኛ እናጣራዋለን፤ እንከታተላቸዋለን>>ሚል መልስ ሰጡኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ጥር 23 ቀን 1981 . ሥራ አድሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወደቤቴ ስሄድ……..

ምንድነዉ ስራህ? 

ብርሃነ፦ የቤት ስራ፤ቤት በደቦ ስንሰራ ደክሞኝ እዚያ አድሬ ነበር። አባቴ ሞቷል..እናቴ አለች፤ የእናቴ ትንሽ መሬት ነበረችን፡ ቤቴ እንደደረስኩ በረቱን ከፍቼ ለበሬዎቹ ድርቆሽ ልሰጣቸዉ ስል…..ማላዉቃቸዉ ብትንትን ብለዉ ተኝተዉ አገኘሗቸዉ። ቤቱ ተከቦ ነዉ ያደረዉ። እናንተ እነማን ናችሁ? ስላቸዉ አንዱ እያናገረኝ ሌላኛዉ በሰባት ጥይት መታኝ። በሆዴ እና በአንጀቴ ላይ ደሙ እየተንዠቀዠቀ ሲፈስ እናቴ እንዳታይና እንዳትጮህ ውስጥ ግቢ አሏት። ከዚያ በሗላ <እግሬና እጄን አንጠልጥለዉ ጎትተዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ> አንጀቴ ተበጥሷል። እንጀቴ ይታያል፡ቅጠላቅጠል አልብሰዉኝ ተሰወሩ።ይህ ሁሉ ሲሆን ከሩቅ ይከታተሉ የነበሩ የአካባቢዉ ሰዎች እነማን እነደሆኑ አይተዋል።

ስንት ነበሩ? 

ብርሃነ፦ ወደ 10 ይሆናሉ።

ሕዝቡ ተከትሏቸዉ፤ << እነማን ናችሁ? ቁሙ! ነፍስ አጥፍታችሁ አትሄዱም>> ሲላቸዉእየሳቁሄዱ በመጨረሻ ከወደቅኩበት አንስተዉ በሰልፍ ተሸክመዉኝ ዓድዋ አዉራጃ አሰተዳደር ወሰዱኝ።<<የዛሬ ብርሃነ ዕድል ነገ ለኛ ነዉ። ይሄ ልጅ ምን አጠፍቶ ነዉ በወጣትነቱ የተቀጠፈዉ?>> ብሎ ህዝቡ አቤቱታ አቀረበ። በዚህ ወቅት ሕዝቡ መቷል ብሎ ስላመነ ጉድጓዴ ሳይቀር ተቆፍሮ ነበር። ጫካ ወስደዉ እንደጣሉኝ የተነገረኝም በሗላ ነዉ። ሕዝቡ አሰከረኔን ተሸክሞ <<ደርግን ግፈኛ ትላላችሁ እንጂ ይሄዉና የናንተም ግፍ!>> ሲሏቸዉ 15 ወጣቶች በሲሚንቶ የተሰራ የጣሊያን ጉድጓድ ዉስጥ አስገብተዉ አሰሯቸዉ። በአጠቃላይ ሕዝቡ 500 (አምስት መቶ) ይሆን ነበር። ወጣቶቹን ካሰሩ በሗላ ህዝቡን በዱላ በታተኑት።…………. እያለ ረዢሙን አሳዛኝ ታሪኩን ያትታል።

ልክ የዛሬ 41 አመት በሕዳርጽዮን ቀን በፋሸሲቱ ትሕነግ ታፍነው የሞቱት ድያቆናትና ቀሳውስት ስናስታውስ ገዳዮቻቸውና አሳሪዎቻቸው አነ ደብረጽዮን እና እነ ጻድቃን የመሩት ድርጅት ነበር።

ታዲያ ለሰሩት ወንጀል ሳይጠየቁ እንሆ ዛሬም ሃውልቱ ሥር ተቀምጠው በደም የጨቀየው እጃቸውና ገላቸው ሳይታጠብ በዓለም ሕግና በሰማያዊ የሃይማኖት ሕግ ሳይጸዱ፤ ንስሃ ሳይገቡ ከፖለቲካ ጳጳሶቻቸው ጋር ተቀምጠው የሃውልቱን ግርማ ሲያቆሽሹት ይታያል።

ይህ ትውስታ እንግዲህ ከፖለቲካ ንክኪ ያልነበራቸው የሃይማኖት ሥራቸው ብቻ የሚሰሠሩ ቀሳውስትና ካሕናትን እያፈኑ ሲገድሉና ሲያታግሉ የነበሩት ሰዎች ወደ ፍርድ እንዲቀርቡ የትግራይ ሕዝብ ፈቃደኛ አይደለም። ለዚህ ለነሱ ወግኖ ተባባሪነቱን ደጋግሞ አሳይቷል።

በታሪክ አንድ ማሕበረሰብ የፍትሕ ትርጉም እንዲገባው የማስተማር ሃላፊነቱ የሚወስድ ወጣት ትውልድ ነበር። ሆኖም በሚያሳፈር መልኩ የትግራይ ወጣት እንኳን ፍትሕ ለተጎዱ ሊጠይቅ ለወንጀለኞቹ ወግኖ የወንጀለኞቹንና የፋሺሰቱን ድርጅት ጡት እየጠባ ማደጉን ሳያፍር በግሃድ እንዲህ ሲል ለዓለም አስተጋብቷል።

  መቀሌ ውስጥ የወያኔ ጡት እየጠጣ እዳደገ በትምክሕት ሲጨፈር በቪዲዮ ተቀድቶ ያየነው ጭፈራ ላስታውሳችሁና በዚህ ጭፈራቸው ልደምድም።

<<ናዓና ዝመስል የለን(እኛን የሚመስል ተወዳዳሪ የለም)

ትግራዋይ ዝመስል ባዓል ስረ የለን(ትግሬን የሚያክል ባለ ሱሪ ወንድ

የለም) 

 “! ! ምስ ወየነ እየ ዝዓበኹ) ! ! ከወያኔ ጉያ ነው ያደጉት!)

! ~ ወያነ እንዳበልኩ እየ ዝዐበኹ” ( ! ! ወያኔ እያልኩ ነው ያደግኩት)

መቐለ ፤መቐለ!!! 

(መቀሌ! መቀሌ!) 

ናይና! ናይና ናይና!!”

 (የኛ ነች!! የኛ ነች!!)

ኣየኹም ናይና!!” (የኛዎቹ ኣይዝዋችሁ!!)>> .... 

እያለ 49 አመት የፋሺሰቶችን ጡት እየጠጣ ማደጉን በኩራት የሚደነፋ የእንደርታና የትግራይ ወጣት ትውልድ ፤ መጨረሻው ምን  ምን ይሆን? ብላችሁ ብትጠይቁኝ ፤ እንደ ወንጀለኛው እሱም  ያንን ፈለግ  ይከተላል። ሰውን ይገድላል፤ ለነብስ አይሳሳም ፤ ይዘርፋል፤ ሴቶችን ያምጻል፤ አጉራ ዘለል ጸበኛና ፋሸሲት ይሆናል። ስለሆነም ነው ካች አምና አምሐራ እና ዓፋር ምድር ግብቶ የፈጸመው አስነዋሪ ወንጀል ሲፈጽም ያየነው። ትግራይ ውስጥም እንዲሁ የገዛ ወገኖቹን “ሲገድል፤ ሲዘርፍ፤ ሴቶችን ሲያምጽ፤ ሰው ገድሎ አካላቱን ቆራር ሲጥል” ያየነው። ይህ ማፈሪያ የትግራይ አዲሱ ትውልድ "ወተት ላጠጣው" ለወያኔ እንጂ ለተጎዱ ሰዎች ጥብቅና ይቆማል ብሎ መጠበቅ “ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ” መጠበቅ ነው።

ሠላሙን ለናንተ!!!

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay