Tuesday, September 24, 2019

በፋሺሰቶቹ ወያኔዎች ሥርዓት የስለላና የጠለፋ ዋና መሪ የነበረው ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ እስር ቤት ውስጥ ግፍ የፈጸሙ ግለሰቦች እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሕልሙም በውኑም አልሞት አያውቅም ሲል እራሱን ነፃ ለማውጣት ሲያጭበረብር ይኼው። ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)


በፋሺሰቶቹ ወያኔዎች ሥርዓት የስለላና የጠለፋ ዋና መሪ የነበረው ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ እስር ቤት ውስጥ ግፍ የፈጸሙ ግለሰቦች እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሕልሙም በውኑም አልሞት አያውቅም ሲል እራሱን ነፃ ለማውጣት ሲያጭበረብር ይኼው።
 ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)

ዛሬ የምንነጋገረው 4 ወር ሥልጣን ላይ ከወጣ በተለጠፈው የቪዲዮ ሊንክ በምሥጢር የተቀዳ ኢሕአዴጋዊ ስብሰባ ላይ የተናገረው ንግግሩ ነው። ከእዚህ ጽሑፍ ተያይዞ የምታደምጡት ሥዕለ ድምፅ ከድምጽ ፋይሎቼ ያስቀመጥኩት አንዱ ‘አናርኪያዊ ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ” እንዲህ ይላል።


“በምርማራ ቦታ ፤ፖሊሶች ወንድ ታስሮ አፉን እንዲከፍት አድርገው ሽንት ሲሸኑበት ነበር።በዚህ ደረጃ የሚያዋርድ ሥርዓት ኢሕአዴግ አስቦም አልሞም አያውቅም።” ሲል መርማሪ ግለሰዎች የፈጸሙት እንጂ በመንግሥት ደረጃ አልተፈጸመም ይለናል።


ልብ በሉ! ይህ ግፍ የተፈጸመባቸው እስረኞች “አማራዎች ናቸው (እነማን እንደሆኑ ለብዙዎቻችሁ ግልጽ ነው ብየ አምናለሁ። እስረኞቹ በአማርኛ የእጅ ጽሑፍ የላኩት ሰነድ በታይፕ በወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በወቅቱ ተሰራጭቶ ስለነበር ስማቸውን ታገኙታላችሁ)።


እንዲህ ያለ ግፍ የተፈጸመባቸው አማራዎች እንጂ ትግሬዎች ወይንም ኦሮሞዎች አይደሉም። አማራ ደግሞ በወያኔ/ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ /በወያኔ/በኢሕአዴግ/ በወያኔ/ በመንግሥት ፖሊሲ የአማራን ህይወት ሰላም እንድታጣ እናደርጋለን’ ብሎ በፕሮግራሙ ቀርጾ “ኦርቶዶክስን፤ ሰንደቃላማችንን እና አማራን/ኢትዮጵያን” ሦስቱ/አራቱ/ በጠላትነት ፈርጆ ወደ ሥልጣን በመምጣት “ነፍጠኛ በሚል ስም” ሰይሞ ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ እስከ አሳምነው ጽጌ እና ኣእላፍ አማራዎችን ከምድረገጽ እንዲጠፉ ያደረገ ሥርዓት መሆኑን ልብ በሉ።


አብይ እራሱም የአማራ ጥያቄዎችንና እሮሮዎችን እንዴት እያሳነሰ ወደ ታች እያወረደ፤ በአደባባይ ወጥቶ በግልጽ ሲናገር እንደነበር ከመጀመሪያ አገራዊ ጉብኝቱ ከመቀሌ ጀምሮ ወደ ባሕር ዳር መጥቶ ቆይቶም እስከ ደሴ እና አዲስ አበባ መድረኮች ንግግሮቹን ማስረጃዎች ናቸው። እነዚህ ለማንበብ በራሴው ኢትዮ ሰማይ ድረግጽ ታገኝዋቸዋላችሁ።


ስለዚህም የአብይ ቅጥፈት እና አጭበርባሪ ልሳን መመክት አስፈላጊ ነው እና ተከታተሉኝ።  የአብይ አድናቂዎች እና ተከታዮቹ ላያምኑ ይችላሉ። ሳይወዱ ባርያ ከሆኑ ሰዎች ይልቅ ወድደው ባሮች የሆኑ እነዚህ የሕሊና ባርያዎች ከባርነት የወጡ የመሰላቸው አሳዛን ባሮች ስለሆኑ ከነሱ የሚጠበቅ የለምና ወደ እውነታው እንሂድ።


“በምርማራ ቦታ ፤ፖሊሶች ወንድ ታስሮ አፉን እንዲከፍት አድርገው ሽንት ሲሸኑበት ነበር።በዚህ ደረጃ የሚያዋርድ ሥርዓት ኢሕአዴግ አስቦም አልሞም አያውቅም።


የሚለው አጭበርባሪው አብይ አሕመድ ግን በራሱ ፓርላማ ላይ ቀርቦ “በዜጎች ላይ ግፍ የፈጸመው መንግሥት ነው”፤“መንግሥት አሸባሪ ነው፡ እኛ አሸባሪዎች ነን!!” ሲል ይቅርታ የጠየቀበትን ንግግሩን ለውጦ በግል አቻዎቹን ጠርቶ ሲናገር ግን “እስር ቤት የተፈጸመው ኢሰብኣዊ ድርጊት አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚመራው ኢሕአዴግ ሳይሆን ‘ግለሰቦች’ የፈጸሙት ነው” በማለት “ኢሕአዴግ በሰብኣዊነትና በሕግ የሚመራ ሥርዓት ነው” ሲል ፋሺሰታዊው የህወሓት ዲሞክራሲያዊ አብዮትን ያሞካሻል።


ታስታውሱ እንደሆን ግብረሰዶም የተፈጸመበት አንድ እስረኛ እና ተፈጽሞብኛል ብሎ ለተናገረው ለአንድ ታሳሪ እስረኛ አባይ ፀሃየ እና አዲሱ ለገሰ በሰላዮቻቸው በኩል ምስጢሩን ካወቁት በሗላ ‘ወደ እስር ቤት በመሄድ “ምስጢሩን” ለማንም ሰው ነግራችሁ ብትገኙ “በህይወታችሁ እንደፈረዳችሁ ቁጠሩት” ብለው  እነዚህን ሁለት ሰዎች እንዳስጠነቀቅዋቸው ታሳሪው ምስክር ከተፈታ በሗላ የተናገረውን በዩቱብ እንዳደመጣችሁት ተስፋ አለኝ።

የግለሰቦች ተግባር ቢሆን ኖሮ፤ እነዚህ የሥርዓቱ መሪዎች ግለሰቦቹን በይፋ ፍርድ ቤት ቀርበው ያስቀጥዋቸው ነበር። ሆኖም “አብይ” የሚመጻደቅበት “የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ድርጅት” መሪዎች ግን በረሃ እያሉ “ሰው ሲገድሉ፤ ሰው በእሳትና በፈላ ዘይት እያቃጠሉ ሲመረምሩ፤ ብዙ ግፍ ሲፈጽሙት የነበሩ ግፈኞች ስለነበሩ፤ እስር ቤት ውስጥም እንድያ ያለ ዘግናኝ ግፍ በራሳቸው አመራርና ትዕዛዝ የሚካሄድ ዘግናኝ ግፍ መሆኑን ስለሚያወቁ በተገላቢጦሽ “ተጠቂዎችን ነበር በተቃራኒ ምስጢሩን እንዳያወጡ  ያስጠነቀቅዋቸው”።


እነዚህ ሁለት ሰዎች በተለይ አባይ ፀሐየ የኢሕዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ (ፋሺዝም ማለት ነው) ከሚመሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከፈጠሩት አንዱ እና ቁንጮ የፖሊሲ እና የፖለቲካው ሞተሩ ነው። አብይ አሕመድ ግን የዚህ ፋሺሰት ሥርዓት የስለላና የደህንነቱ መዋቅር ዋናው አንቀሳቃሽ እና ምስጢር ጠላፊ በነበረበት አሳፋሪ አገልግሎቱን ለመደበቅ ሲል የተፈጸሙ ወንጀሎች ሁሉ “ተራ ፖሊሶች/መርማሪዎች የፈጸሙት እንጂ መንግሥት አይደለም እያለ የምርመራው ክፍል “መንግሥታዊ መዋቅር” እንዳልሆነ እና መዋቅሩ ከላይ ሳያዛቸው ማንኛውንም ግፍ በራሳቸው እንደሚፈጽሙ አድርጎ ለማቅረብ የወንጀል ታሪክ ለመደበቅ ሞክሯል።


ኢሕዴግ ብሎ ራሱን የሚጠራ የፋሺሰቶች ጥርቅም “አዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች” እራሱ ቦምብ እያጠመደ ሲያጋይና ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድል እንደነበር ጃፓናዊ አሜሪካዊው የመለስ ዜናዊ ወዳጅ አምባሳደር ያማሜቶ ለዋሺንግቶን ያስተላለፈው ምስጢራዊ የፋክስ ምስጢር ‘በዊኪ ሊኪ’ ተጠልፎ ይፋ መሆኑን እናውቃለን።


 አጭበርባሪው አብይ አሕመድ ግን ህወሓት/ኢሕአዴግ በእንዲህ ያለ የሽብር ስራ ተጠምዶ ሲፈጽም እንደነበር እያወቀ፤ ዛሬ ያንን ድብቅ ሽብሩን እና ሰብኣዊ ጥሰቱን ለመደበቅ እንዲያመቸው “የግለሰቦች (ፖሊሶች/መርማሪዎች) በራሳቸው ተነሳሽነት የፈጸሙት ድርጊት እንጂ “ኢሕአዴግ አያደርገውም ብሏል።

 አዎ ሊያምን አይችልም። ምክንያቱም እሱም የስለላውና የጠለፋው የማሰቃያ ቅርንጫፍ ክፍል አንደኛው ቅርንጫፍ መሪ ነበርና ራሱን ነፃ ለማውጣት ነው “የምርመራ ግፎች የመርማሪ ግለሰቦች እንጂ ኢሕአዴግ በውኑም በሕልሙም አያደርገውም” እያለ ወያኔ /ኢሕዴግ የፈጸመው ወንጀል ነፃ ሊያደርገው እየሞከረ ያለው። ለዚህ ነው ባለፈው ሰሞን ኦርቶዶክስን ይቅርታ አልጠይቅም የሚለው።


 አሜሪካ አገር ውስጥ አንድ ሰራተኛ በሌሎች ተገልጋየች ላይ ጥፋት ከፈጸመ “የኩባንያው አስተዳዳሪዎች/ መሪዎች/ ባለቤቶች” በኩባንያው ስም ይቀርታ ይጠይቃሉ። አጭበርባሪው አብይ ግን እኔ ቤተክርስትያን አላቀጠልኩም ከሕናት አልገደለኩም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም ብሏል። የሠለጠነ የተደመረ ጭንቅላት የወያኔዎች ኢሕአዴግ ምሩቅ ተማሪ ማለት ይኼ ነው!


ከዚህ ሌላ በዚህ ቪዲዮ ውስጥ- ትግሬዎች ተጠቃሚ ነበሩ የሚለው “ውሸት’ እንደነበር እና ዛሬ ያንን ውሸት ቦታ እንደሌለው በከንቱ ሲዘባርቅ ታደምጡታላችሁ።


እውነታው ግን እኔም ሆንኩ ጥቂት ጓዶቼ “ትግሬዎች ተጠቃሚዎች ነበሩ ብለን በግሃድ ተከራክረናል፤ዛሬም ተጠቃሚዎች ናቸው። ያ ካልሆነ ሌላውን ማሕደር ወደ ሌላ ቀን አቆይተን “የወልቃይትና የራያ ሰፋፊ ለም መሬቶች በጠብመንጃ ሃይል ወደ ትግሬ ቀላቅሎ የነጠቃቸው ለም መሬቶች ለማን ነው የሰጠው? ትግሬዎች የበላይነትን ተጎናጽፈው እዛው የነበሩ ነባር ኗሪዎችን አፈናቅለው፤ ገድለው፤ ገርፈው፤ አስሰድደው፤ ሴቶችን ዘርፈው (ሬፕ በማድረግ) የትግራይ ታጋዮቹ እና አዳዳዲስ ሰፋሪዎች በማስፈር በሺዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገው ለማን ጥቅም ሲባል ነበር? ለትግሬዎች ነው፤ አይደለም እንዴ?


የፋሺሰቶች ስነ ምግባር “አሞጋሽ” የሆነው አብይ አሕመድ ትግሬዎች በህወሓት ሥርዓት አልተጠቀሙም ብሎ ሲል ይህን በምን ሊመልሰው ይቻለዋል? ለማንኛውም በምስጢር የተቀዳው የአብይ አሕመድ አጭበርባሪ ልሳን አድምጡ። እነሆ። አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
  ዶር አብይ አህመድ አስደንጋጭ ትእዛዝ ሲሰጡ በድብቅ የተቀረፀ ቪዲዮ ይፋ ሆነ