Thursday, April 1, 2010

ማን ከማን ጋር ተቧድኖ ማንን ለማሳጣት

ማን ከማን ጋር ተቧድኖ ማንን ለማሳጣት (ሳ -ጠበቅ ተደርጎ ይነበብ) በሚል ርዕስ ግዛቸዉ የተባለ የመድረክ ፖለቲከኛ ትግራይ መቀሌ ድረስ በመሄድ በቅንጅት ስም ልክ ብርቱካን መዲቅሳ መኔሶታ /አሜሪካ ድረስ መጥታ እንደተጫወተቺዉ ዓይነት የፖለቲካ ችርቸራ የመድረክ ፖለቲከኛዉ ኢንጂነር ግዛቸዉ የተባለዉም ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ለፓለቲካዉ ንግድ ያመቸዉ ዘንድ የትግራይን ሕዝብ “ይቅርታ” የመጠየቁን ጉዳይ ሽበት ካወጣ አዛዉንት ምሁር ሰዉ እንዲህ ዓይነቱ ቅሌት (ለነገሩ የሰዉየዉ ቅሌት አሜሪካ ከነ ብርሃኑ ጋር አገር ላገር ሲዞር የታዘባችሁት ቅሌቱ አዲስ አይደለምና) እንዲህ ዓይነት አስገራሚ ጉድ ከምን ተነስቶ ይህ ዉሃ የማይቋጥር “ክስ” ከመድረክ “ገልቱዎቹ” ጋር ተማክሮ የሜኔሶታዉ የብርቱካን መዲቅሳ ጨዋታ መቀሌ ላይ እንደገና ሊደግመዉ ከምን የተነሳ እንደሆነ የሚመረምር ይህን በሚመለከት ሰሞኑን እየሰራሁ ስላለሁ እስከዚያዉ ፋሲካዉን በዓል በሰላም እንድታሳልፉት ምኞቴ ነዉ። እምለሳለሁ ጠብቁኝ። በጊዜዉ ባለመዉጣቱ እንደምታዉቁት ትንሽ በልዩ ስራ ተጠምደን ስለነበር ነዉና ቀልቤ ዛሬም ነገም ከናንተዉ ዉድ ኢትዬጵያዊነትን መርህ፤ እዉነትን እና ድፍረትን መመርያችሁ” ከምታደርጉ አንባቢዎቼ ጋር መሆኑንም በደስታ እገልጻለሁ።

ቡድኖቹ ዛሬም ትናነትም በተለያዩ ሰልፎች እየተቧደኑ በፈረደበት ሃይሉ ሻዉል እና አማራ ላይ መሆኑን ልብ በሉ። የነ ክንፉ አሰፋ እና የነ አቡጊዳ ዌብ ሳይቶች የነ ኤልያስ ያዉ “በየሚለየኔሙ ሊሂቃኖቻች ” እና በሻዕቢያ አምደኞች (አማኑኤል በእደማርያም- የታወቀዉ ጸረ ኢትየጵያ ዘረኛ እና ትምክህተኛ የሻዕቢያ አላዛኝ- የማሳሰሉት New relationship between Eritreans & Ethiopians: A view from Eritrea, Amanuel Biedemariam ብለዉ ዝግጅቱን እንዲያቀርብላቸዉ፤ የእነ ኢሳያስ አዳዲሶቹ ኢትየየጵያዊያን ጠበቆች እነ “ንአምን ዘለቀ” ያዘጋጁት “ኢትዮጵያ ከየት ወደየት” በሚል በተዘጋጀዉ መድረክ ላይ የሚገኘዉ ኤርትራዊዉ ትምክህተኛን ያጤነዋል) እንዲሁም ትግራይ እና አማራዉን ለማቋሰል በሚጥሩ አምደኞች እና ጸሃፍቶቻቸዉ በሻዕቢያዎች የታጠረ ዱር መሆኑንም ልብ ሳትሉ አልቀራቺሁም። ለማንኛዉም ስካሩ ሲበርድ ማን ምን እንደሆነ ይታወቃል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ!

ከፖለቲካዉ መድረክ ለሳምንት ከተለየሁ በሗላ ድረገጾቹ ይዘዉልኝ የቆዩ ታሪኮች ለማንበብ ጊዜ ሲያጥረኝ ይግረም ብሎ ደግሞ ለአረጋሽ አዳነ “ገንዘብ እንርዳ” የሚሉ ብቅ ብለዋል የሚል ወሬም እየተናፈሰ ነዉ የሚል ጽሁፍ ሳነብብ “ወይ የሄ ዲያስፖራ! ይህች አገር! ምን ይበጅሽ ይሆን? አሰኘኝ። ለማንኛዉም ግራም ነፈሰ ቀኝ - አዳዲስ በራዦቹ እና አወናባጆቹ (የወንጀለኞቹ አጨብጫቢዎች እና አጎዛ አንጣፊዎቻቸዉ) የትም እንደማይደርሱ እናዉቃለን እና በተለያዩ ቡድኖች እየተቧደኑ በዉሸት እና በስሜት ሜዳ የሚቆራቆሱ የሻዕቢያ “አዝማሪኖዎች” እየተንሸራተቱ ሲወድቁ ብታዩ እዘኑላቸዉ እንጂ እንዳትስቁባቸዉ። አደራ፤ ዛሬም ነገም ያዉ የተለመደዉ አደራየን ተቀበሉ። መልካም አዉዳመት! ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com