የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንኳን ደህና መጡ!
ሐዋርያው ሉቃስ ግራኝ አሕመዱ አብይ
አሕመድ ይሰቀል ስላሉ ሓጢያታቸው ምኑ ላይ ነው?
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
1/28/2024
ሰሞኑን የሰማሁት ዜና አቡነ ሉቃስ የተበሉ አርበኛ ኢትዮጵያዊ አቡን ቀደም
ብለው የአፓርታይድ መሪ አብይ አሕመድ ‘እየፈጸመብን ካለው መከራ የሚያላቅቀን አንድ ጥይት ያለው ወታደር እንዴት ይታጣል’ በማለታቸው ፤ ቀን
ቆጥረው ሰሞኑን አዛውንቱን አቡነ ሉቃስ ፍርድቤት እንደሚከሰሱ ሰምቼ ገረመኝ።
በአፓርታይዶቹና በፋሺሰቶቹ ትግሬዎች ስትረገጥ የነበረቺዋ ኢትዮጵያ እንዳይበቃ እነሱን የተኩ አፓርታይድና ፋሺሰት ኦሮሞዎች እየገዝዋት ያሉዋት አገር ግራኝ አሕመድ ካደረሰው ጉዳት እኩል የፈጸመው ወንጀለኛው “የኩሽ ኦሮሙማ ማኒፌስቶ” መሪው አብይ አሕመድ ይሰቀል ማለት ፍትሓዊ ነው። ግራኝና ጣሊያኖችን ይሰቀሉ ማለት እንደሚያስገድል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በጣሊያንም፤በ27 አመት የትግሬዎች አስተዳደርም ምሁራን ፤ጋዜጠኞች፤ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ ሥርዓቱን የተቃወሙ የፓርላማ አባላት፤ አክቲቪስቶች ፤ የስነ ጥበብ ባለሞያዎች፤ ሠራተኞች፤ ወጣቶች፤ዕርጉዞችና እመጫቶች ፤ ጠበቆች፤ ነጋዴዎችና የሕክምና ባለሞያዎች እንዲሁም አስተማሪዎች ብዙ የሰላም ሓዋርያቶች፤ቀሳውስቶች ድያቆናት፤አቡኖች ሲረሸኑና ሲጋዙ የነበረበት ሁኔታ ነው። ዛሬ ያንኑ የቀጠለ ሆኖ ሳየው ቢገርመኝም፤ ኦርቶዶክስ መሪዎችም ሆኑ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ቡድኖች ሐዋርያውን መኮነናቸው ስሰማ ቅር የሚያሰኝ ነው። ለግራኝ ሕይወት የሚስገበገቡ ግራኝ አሕመዶችና ሽብርተኞች ብቻ እንጂ “ፍትሕን” የሚጠይቅ፤ አድልዎና ግፍ እንዲያጥር ጥሪ የሚያቀርቡ ጸረ ግራኝ የሆኑ ሐዋርያት የዘመናችን አፓርታይድ መሪ ባጭር እንዲቀጭ መጸለይም ሆነ መቀስቀስ እንዴት እንደሚያስኮንን የሚያስረዳኝን ሰው እጠብቃለሁ።
አብይ አሕመድ የተቀመጠባት አዲስ አበባ መዲና የሚጠራት “ፍንፍኔ” በሚል ይጠራታል። ይህ ሰው “የኦነግ ጥራጊ ፖለቲካ” ተሸክሞ ዛሬም ተባባሪዎቹን ሲያነጋግራቸው አዲስ አበባን “ፍንፍኔ” እያለ ነው። እኛ ደግሞ አዲስ አበባ በፍንፍኔ መጠራትዋ ብቻ ሳይሆን የሰላም ሐዋርያት የሚኮነኑባት መዲና ከሆነች ወደ 33 አመትዋ ተጠግቷታል እንላለን።
እስኪ የህችን
ከኛ በተለዩን ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ጻሐፊ የጻፍዋትን ማስታወቂያ አብረን እናንብባት።
የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንኳን
ደህና መጡ!
<<የሰላም ሐዋርያት ወደሚኮነኑበት አገር እንኳን ደህና መጡ! ነቢያት ዛሬም ወደ ሚወገሩበት መዲና ጥሩ እግር
ጥለዎታል።ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም ሥር እየሰደዱ ሚገኙበት አሮጌ አገር አዳዲስ ጋንግስተሮችን
ያገኛሉ።ማስታወሻ ደብተርዎን ይቆጥቡ።ብዙ የሚያስጽፍ ድርጊት አለና! ለማንኛዉም እንኳን ወደ ማፊያዎች አገር መጡ! ስለ ሕግና ስለ ሕጋዊነት ብዙ
ይሰማሉ! እንኳን ደህና መጡ ብቻ!>…..<ስለ ንግድና እንቅስቃሴ የሚአስተምረውን ሥነ ኣእምሮ አወቃለሁ ባልልም ቱሪስት ድርጅት (እሱም ስሙን ቀይሮ ካልሆነ) የተነሳሁበትን ዓይነት ማስታወቂያ
ገና ከቦሌ እላይ እና ቀጥሎም የአራዳነት ማእከል በሆነዉ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ቢለጠፍ ከ24ቱ የዓለም ድንቅ ነገሮች አንደኛዉ
እንደሚሆን እገምታለሁ።>> (ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ጦቢያ ቁጥር
10/1993 (ጦቢያ መጽሔት)
አዎን ከዓለም አካባቢ በጥራጊ
መልክ የመጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም አንደ ዱባ ሥር ሰድዶ/ተንሰራፍቶ/ የሚገኝባት ጥንታዊቷ አገር፤ ዛሬ ባለ ብሔሮቹ <ዘረቢሶች> ናችሁ ቢሉንም ከስርዓቱ
ባሕሪይ የተያያዘ በመሆኑ ለመነጋገርያ አና ሌሎች ማስገንዘቢያ ይረባ እንደሆን እንጂ ሰዎቹ ቢወቀሱም ቢመከሩም “ተፈጥሮን ተመክሮ” ሊያድነውና ሊመልሰዉ እንደማይችል
ከነ “በኒቶ” እና ከነ “ሂትለር” የወል ባሕሪይ ተገንዝበናል፡ ትግሉ ይቀጥላል።
ለሐዋርያቶቻችን ድምፅ እንሁን።
ኢትዮጵያ የተነጠቀቺው ነጻነትዋ እስኪመለስ ድረስ ፤ የተዋረደቺው ሰንደቅዓላማችን ከተጣለቺበት እስክትነሳ ድረስ ሐዋርያቶች ድማጻቸው እንዲቀጥል እንጠይቃለን!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay