Sunday, December 19, 2021

ስለ ፋሺሰቶች ብልህነት የሚያወድሱ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህራን “አብ-ሾዎች!” ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 12/19/2021

 

ስለ ፋሺሰቶች ብልህነት የሚያወድሱ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህራን “አብ-ሾዎች!”

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

12/19/2021

አንዳንድ ምሁራን ስለ ፈላስፎች ሲናገሩ “ናላቸው መቆጣጠር የመይችሉ ዕብዶች ናቸው” ይሏቸዋል። እኔ በተወለድኩበት በትግራይ ውስጥ በአገራችን የቤተክህነት ምሁራን ደግሞ እነዚህን ሰዎች “አብሾ” ይሏቸዋል። ወፈፌዎች” ማለት ነው። ዱጋ ፤ፆመ ዱጋ እና ቅኔ በቃላቸው ለመቀኘትም ሆነ ለመውረድ እንዲችሉ “አብሾ” የሚባል የሚጠጣ “ዱቄት” አለ። አብሾ በጥብጠው ከሆነ ነገር ጋር ያለ መጠኑ ሲሰጥዋቸው እርሱን ሲጠጡ ‘የሚናገሩት ሁሉ “ክብደት ያለው”፤ ነገር ግን ሊገባህ የማይችል እጅግ ጥልቅ ልፍለፋ ውስጥ በመግባት በሆነ ስብሰባ ቦታም ሆነ ለብቻቸው ሲናገሩ ማቆሚያ የላቸውም። ባሕሪያቸው ደግሞ “አለቆችን ማወደስ” ይወዳሉ። ሁለት ያስተዋልኳቸው የፍልስፍና መምህራን አሉ (አዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ) እነሱም ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ወጣቱ ዶ/ር (ካልተሳሳትኩ) ዮናስ ዘውዴ ከበደ ከነዚያ “አብሾዎች” የሚደመሩ ናቸው።

ሁለቱም ለአብይ ውዳሴ የማይቀባጥሩት ነገር የለም።መረን የለቀቀ መቀባጠር! ሱዳኖች እንዲህ ያሉ ቀባጣሪዎችን እኛ “ቀባጣሪ” ከምንለው ቃል በላይ አልፈው “ማዓረስ” (አቃጣሪ) ይሏቸዋል። ማቃጠር በአገራችን የተለመደው አንድ ወንድ ለሌላ ሰው በቀጠሮ “ሴት” ሲያመጣለት የሚገለጽ ቢሆንም፤ ቆየት ብሎ ግን ዋሾም ሆነ አወዳሽ “አቃጣሪ” በሚል ወደ መግለጽ ተሂዶ ተቀባይነት አግኝቷል። ዓረቦቹ ለነዚህ ሌላ ቃል አላቸው። አቃጣሪዎቹ ባሕሪያቸውን ለመሸፋፈን “እኔ ያወደሰኩት ምክንያት…. እንዲህ እንዲህ ስለሆነ ነው..” ለማቃጠራቸው ምክንያት ሲሰጥዋቸው “ከዛብ” ይሏቸዋል። “ዋሾ አምታቺ” ማለት ነው።

በዳኛቸው የሰለቸን ትችት ስለሆነ፤ በዳኛቸው ላይ ብዙም አልሄድም። ይህ “ዮናስ ዘውዴ ከበደ” የተባለ አዲስ የአብይ አሕመድ “አወዳሽ” በሕዝብ ፊት ሲናገር አብሾ ነው። ማቆሚያ የለውም። ከአጽናፍ ወደ አጽናፍ እየዘለለ አብይ አሕመድን መልኣክ ለማድረግ የማይቃባጥረው ንግግር የለም።

ልጁ ገና ሳያድግ ያደገ “ቁንጥጫ” የሚያስፈልጋው “ልቅ” ነው። ድረገጹን ስመለክት እጅግ ሲበዛ ለፍልስፍና መምህርነት ቀርቶ ለሚያስተምርበት ት/ቤት ተማሪነት አይመጥነውም። ብዙ ያልተማረው ነገር አለ። አንድ ነገር እንደዋጠች ደሮ አንገቱን እያሰገገ የሚመለከተው “የመንጋዎች ዕብዶች አለም” ውስጥ ገብቶ ራሱን ጨምሮ ሲደስትብትና ራሱን ሲክብ በተለያዩ ፎቶግረራፎቹ፤ጽሑፎቹና ንግግሮቹ ውስጥ ተመልከቼዋለሁ።

 አብይ አሕመድ የፋሺሰቶቹ ተማሪዎች የነበረ ከዚያም ያገለገላቸው አሁን ድገሞ የነሱን ቦታ ተክቶ የወገኖቻችንን ህይወት ያመሰቃቀለ እርኩስ ፋሺስት ነው። ታዲያ ይህ ወጣት ከሚገባው በላይ ተወጥሮ አብይን ለመኳኳል (ሮማንቲሳይዝ) አንደ እንቁራሪቷ አብጦ ሊተኮስ የሚቀረው ነገር የለም።  

 አምባገነን የሚባሉ ከትንሽዋ ካምፓኒም ሆነ ጽ/ቤት በመሪነት የተቀመጡ ሰዎች ለሥልጣን ሲቋምጡ የሚያሳዩት ባሕሪ ነው። ይህ ባሕሪያቸው የተለያየ ደረጃ ያለው ቢሆንም “የደመነብስ ቁጣ” ብየ የምጠራው የመጨረሻ ደራጃ ባሕሪያቸው “ንዳድ” ላይ ሲደርሱ እስራትን፤ግርፋትን አልፎ ወደ ግድያ በመሸጋጋር “የብዙሃን ጭፍጨፋና ስደት” የሚያስከትል ባሕሪ ያሳያሉ።ይህ ልጅ ይህንን ባሕሪ አብይ ሲፈጽመው እጅግ “ደስተኛነቱን” ይገልጻል። መሪየ! ብሎም ይጠራዋል።

ለምሳሌ አብረው የሚከንፉ “መንጋዎቹ” ስለ አብይ አሕመድ ለጥቂት ቀናት ባለመታየቱ ያሳሰባቸው “አብያችን የት አለ?” ብለው የውስጥ አዋቂውን “ፈላስፋው ዮናስን” ይጠይቁታል፡ እርሱም እንዲስ ሲል መለሰላቸው።

“በጣም ብዙዎች እየደወላችሁ የጠሚ ደኸንነት ጠይቃቹሀል። ጠሚ በስራ ላይ ናቸው። My PM is on Duty” ይላል። ይህ ልጅ ስከታተለው እዮኤል የተባለ የድመጺ ወያኔ የራዲዮ ዋና አስተናጋጅና የነበረ ከደቂቀ መምህር ገብረኪዳን ደስታ አንዱ ነው። ዮናስና እዮኤል በዕድሜ እኩል ናቸው። አምባገነኖችን ሲክቡ ከልክ ያለፈ መቀባጠራቸውን ስመለከት “ሰዎች እንዴት እንደሚፈጠሩ ይገርመኛል”።

አምባገነኖች ሲፈጠሩ ኩፉዎች ቢሆኑም አቀጣጣይ ሆነው ብቅ የሚሉ አጃቢዎቻቸው የአምባገነንኖችን ሥር (ሩት) ውሃ ስለሚያጠጡ  ትንሽየዎቹ ወደ ዘንዶነት ያሳድጓቸዋል። የአምባገነን ስነ-ባሕሪ “ከደመነብስ የሚመነጭ ኩፉ ባሕሪ” ስለሆነ የሥልጣን ጥማቸው የሚነጻጸረው ከተፈጥሮኣዊ ከግብረስጋ ግንኙነት (ሴክስ ድራይቭ) ፍላጎት የከፋ የሥልጣን ጉጉታቸው (ድራይቭ/ግፊት) እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ፖለቲካውን በመቆጣጠር ዜጎችን  “ቁም ስቅል” ያሳዩታል። የዚህ ባሕሪ አስከፊነት ደግሞ “ቋሚ” መሆኑ ነው።

ሊቃውንት ደግ ነገር እንዳለ ሁሉ  “አምባገነንነትም የፖለቲካ ቋሚ መገለጫ ሆኖ የሚቀጥል የሰዎች ባሕሪ ነው” ይላሉ። እንደውም አምባገነንነት ይጠፋል ብለው የሚሉ እራሳቸው ፖለቲከኞች ናቸው። ይህ ደግሞ “ማታለያ ነው” ይላሉ። ሁለንተናዊ ብልፅግና የጭቆና አገዛዝን ለዘላለም ያስወግዳል የሚሉ ሌሎች እንዝህላሎችም አሉ ይላሉ። ምክንያቱም ሲገልጹ “አምባገነንነት ራሱን የቻለ ገለልተኛ ባህሪ በመሆኑ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ፣ ለመተንበይም ሆነ ለመከላከል የማይቻል ነው። መፍትሄው ይላሉ “ሲነሳ” ወይንም “ብቅ” ሲል ግን በመቃወም ሊያደርሰው የሚችለውን የጉዳት መጠን መቀነስ እንጂ “ማጥፋት” አይቻልም” በማለት የሚከራከሩ አሉ።

እኔ ደግሞ አምባገነኖች እንዳይጠፉ ምክንያት የሚሆኑ እንደ ዮናስ ዩመሳሰሉ አምባገነንን የሚክቡ የምሁራን መንጋዎች “ከቤት ባርያነታቸው” (ሃወስ ኔግሮ” ባሕሪ እንዲታቀቡ ሕዝብ እንዲኮንናቸው ማድረግ ነው። እላለሁ። አምባገነን ያለ ባርያና ታዛዥ እንዲሁም አወዳሽ በምንም ተአምር ሊገዛን አይችልም። አምባገነኖች የሚተማመኑባቸው እነዚህ “ዕቃዎቻውን” በማስከትል ስለሆነ አቃጣሪዎችን በተማሪዎቻቸው እንዲወገዙ ማድረግ ነው። እንዲያ ሲሆን አምባገነኖች ሰው ሆነው የተፈጠሩ ግን እንደ ከብት መንጋ ባንድ ቃጭል (ደወል) የሚነዱ መንጋዎች እንዳይራቡ ይረዳል። ከብቶች የድምጽ ማጉያ ይዘው ስለ “ቢላዋ” ርሕራሄ ሲያስተምሩ ማድመጥ እንዴት አስገራሚ ዘመን መድረሳችን ነው ያሰኛል።

ትችቴን ለአንባቢ አዳርሱት!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ  ETHIO SEMAY