የኦሮሞ
ሁቱዎች በወለጋ
መልካም
የፈረንጅ ገና በዓል!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 12/25/24
ማሳሰቢያ
ባለፉት 36 አመታት ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተደጋጋሚ ችላ ተብሏል? የዜና ዕጥረት
ሳይሆን 90% ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችና ምሁራን በ36 አመት ውስጥ የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተደጋጋሚ እየተፈጸም እንደሆነ ቢነገራቸውም ፤ 90% (አብዛኛው ማሕበረሰብ) ደንታ ቢስ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።
በሕዝብ ችላ የተባሉት የዚህ ዓይነት አረመኔያዊ ድርጊቶች ሲደጋገሙ ከፍተኛ ተቃውሞ አለማሳየትና ዳተኛነት ከገዳዮቹ ይልቅ ቸልተኞቹ ለወንጀሉ መደጋገም በር ከፋቾች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።
ይህ ቸልተኛነት
የታሪክና የስነ ልቦና ምሁራን ሊያጠኑት የሚገባ ርዕስ ቢሆንም ፤
እኔም ሆንኩኝ ጥቂቶች ሳንሰለች ለብዙ አመታት የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋዎች ለሕዝቡና ለዓለም ደጋግምን ለማሳወቅ የምንጽፋቸው
ሰነዶች በህይወታችንና እና በሥራችን ከፍተኛ ጫና ያሳደረ እንደሆነ ብናውቅም እኛ ጥቂቶች መስዋዕት በመክፍል ወጣቱ እንደተፈለገው
ባይሆንም አሁን ባለበት የመጋፈጥ ደረጃ ሲደርስ በአቦ ሰጥ የመጣ ክስተት ሳይሆን ባበረከትናቸው የጊዜ፤ የሰነድ የገንዘብና የጉልበት
መስዋዕቶች አድርሰነዋል የሚል እምነት አለን። ያለፉት የ36 አመት ትግሎች እዚህ እንዲደርስ ስንት መስዋዕት እንደከፈልን በብዙዎቹ
ወጣቶችና ምሁራን ትግሉ ውስጥ ስላልነበሩ አይታወቅም።
ዕንቅልፍ አጥተን የምንጽፋቸው ሰነዶችና የሚሰራጩት የሕዝብ ዕንባዎች ቸል ብላችሁ ማየት እንደሌለባችሁ ለማሳሰብ ነው።
አብሮ ለማሳወቅ
የምፈልገው ነገር ደግሞ ‘ብዙ ሰዎች’ ስም ሳይጠቅሱ ሰለ አንድ ጉዳይ ሲጽፉ አያለሁ። ያ ደግሞ ተባባሪዎችና አስተባባዮች ምንነታቸው
እንዲደበቅ የሚረዳ ስለሆነ ፤ እኔ እንደምታውቁኝ የሰዎች ስም በመጥቀስ ሳልደብቃቸው የምጋፈጥ ባሕሪ ስላለኝ እዚህ ላይም ስም ተጠቅሰው
ስታዩ፤ ለዋዛ ሳይሆን ለቁም ነገር መሆኑን ተቀበሉኝ።
አሁን ወደ
ዋናው ጉዳይ እንግባ።
ከዚህ ጽሁፍ ግርጌ አብሮ የተያያዘው ቪዲዮ በአምሐራ ሕዝብ ጀነሳይድ አልተፈጸመም ለሚሉ ለአስተባባዮቹ ለነ ዶ/ር ዮናስ ብሩ እና እንዲሁም <<እኔ ሰው ለመታረዱ አላውቅም! እኔ አራጆች ብየ አልጠራቸውም፡ ያውም ማን እያረደ እንደሆነ በማናውቅበት ሁኔታ አራጆች የሚለው የአማርኛ ቋንቋ ባንጠቀም ጥሩ ነው>> ለሚለው ‘የገበታ’ ሚዲያ አዘጋጅ የሕግ ምሁር ለሞገስ ዘውዱ ተሾመ እና ለመሳሰሉ አስተባባዮች እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ:: በዚህ ቪዲዮ የምታደምጡዋቸው ተጠቂዎች “ሲዋጉ የተጨፈጨፉ” ሳይሆኑ ዕለታዊ ኑሮአቸው በሚኖሩ ምስኪን ነገዶች ላይ በየመኖርያ ቤቶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ልክ እንደ ረዋንዳው እና እንደ ጀርመን ሃይማኖትና ዘር ያተኮረ ጭፍጨፋ የተፈጸመባቸው እንጂ አስተባባዮቹ እንደሚሉት የጦር ወንጀል የተጸመባቸው ወይንም በማቆነጃጀት አሳንሰው “ዘርን ማፈናቀል” ብቻ ሳይሆን “የጀነሳይድ” የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል እንደሆነ ከተጠቂዎቹ አንደበት እናደምጣለን።
ወለጋ ውስጥ “የኦሮሞ ሁቱዎች” በአምሐራ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት
የዘር ማጥፋት ወንጀል ልክ ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ
በመጻሕፍት ዘግበው ለዓለም ያሳወቁ እንደ እነ
1) Machete Season –The Killers
In Rwanda Speak (Jean Hatfield)
2) When Victims Become Killers
(Mahmood Mamdani)
3) We wish to inform you that
tomorrow we will be killed with our families (Philip Gourevitch)
4) Conspiracy
to Murder – The Rwanda Genocide (Linda Melvern)
5) The
Butchers in Rwanda
የመሳሰሉ እዚህ ለመዘርዘር
ቦታ የማይበቃቸው የሩዋንዳ ዕልቂት ደራሲያን እና ሪፖረተሮች/ጋዜጠኞች/ የጻፉዋቸው መጽሐፍቶችና የጥናት ሰነዶች ስታነቡ ከዓለም
ዓይን ተደብቆ ያለው የ35 አመት ዕልቂት በኢትዮጵያ ተመሳሳይ ነቱ የሚገርም ነው።
በተጨማሪም “ኦሮሚያ”
ተብሎ በተሰየመው “አፓርታይዳዊ ክልል” በከርስትያኖችና በእስላም
አምሐራ ሕዝብ እና በጋሞ ነገዶች እንዲሁም የመሳሰሉ ሌሎች ማሕበረሰብ አባላት ላይ የተፈጸመው “ጀነሳይድ” በመካድ አልተፈጸመም እያሉ በየሚዲያው የሚፈላሰፉ ምሁራን
ይህንን ዕንባና ሰቆቃ ደጋግመው እንዲያዩትና የሩዋንዳው ዕልቂትና ይህ እልቂት ልዩነት እንደሌለው እሳቤአቸው እንዲያስተካክሉ ደግሜ
ይህ ቪደዮ እንዲያጤኑት እጋብዛለሁ።
በዚህ ልደምድም፡
አንዳንድ ሰዎች ይህ የአምሐራ ጭፍጨፋ ሁሉንም አምሓራ እንደ የሩዋንዳ ቱትሲ ዕልቂት ሁሉንም ቱትሲ በያሉበት ያዳረሰ ዕልቂት ስላይደለ ጀነሳይድ ሊባል አይቻልም፤ ሲሉ እሰማለሁ። ለዚህም መልስ በጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ አባባል ልደምድም <<ወለጋም፤ አርሲም፤ ደብረዘይትም፤ ባሌም፤ ሐረርም……ወዘተ እየለ ይቀጥልና “አራጆቹ አቅም ካገኙ” አምሐራ አለበት በሚባልበት ምድር ሁሉ በመሄድ ያጠፉታል። “ሂትለር” እቅም ባከማቸ ወቅት እስከ አውስትርያ፤ ሆላንድ ፤ መላው ኣውሮጳ ወዘተ… ተሻግሮ “ይሁዲዎችን” ጭፍጭፏል። አምሐራም አራጆቹ አቅም ሲያገኙ ከምድረገጽ ከማጥፋት አይመለሱም። ስለዚህ የሕልውና አደጋው ከፍተኛ ነው።>>
ይህ ቪዲዮ ያቀረብኩበት ተያያዢነቱ በገና በዓል ተጠቂዎቹ ከሰዎች ለምነው ያገኙት ቆሎ ሲበሉ የተቀረው ሸሞንሟናው አዲስ አበባው የኪነት ባለሙያዎች እና ባለጊዜ ከተሜዎቹ ግን ቁርጥና ዊስኪ የተራጨበት ቀን እንደነበር ተጠቂዎቹ ከዚህ በታች በተለጠፈው ቪዲዮ ካንደበታቸው ትሰሙታላችሁ።
መልካም የፈረንጅ ገና በዓል!
ሰላም ለናንተ ይሁን
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
Welega genocide አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም የአማራው ፈተና #Amhara Genocide
Ethiopia
https://youtu.be/Z5kjsjz-_LU?si=s8y0dwOgVcf0-rjN