ከአዘጋጂው-ማሳሰቢያ፡(getachre@aol.com)
www.ethiopiansemay.blogspot.com
When you want to minimize or magnify this page: - use Ctrl and the + sign on your key together or to minimize use the Ctrl and - sign on your keyboard. የኢትዮጵያን ሰማይ አንባቢዎች ሆይ። ይህ “ሆድ ሲያውቀው ማታ ዶሮ” የሚል እዚህ የቀረበው ትችት የሻዕቢያው ሰላይ የተስፋዬ ገብረአብ
የተሸሸገ የመንንት ምስጢር ሰሞኑን በሰነድ አስደግፈው ለህዝብ ይፋ
አድረገው ያጋለጡት በብርሃኑ ነጋ በግንቦት 7 የሚደገፈው (አንዳንዶቹም የግንቦት 7 ንብረት ይሉታል) የኢሳት ቴ/ቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት ድጋፍ ሰጪ አባል
የሆኑት “ዳኛ ወልደሚካል መሸሻ” የተባሉ ኢትዮጵያዊ ላይ ያነጣጠረ ነው። እኔም በዳኛው ላይ ያለኝን ቅሬታ (አቶ የሶማው ያቀረቡትን
ጽሑፍ) ለማቅረብ ስዘጋጅ ነበር ፤ወንድሜ አቶ ሶማው በግሩም አቀራረብ የቀደሙኝ። ስለዚህም የሳቸውን ትችት ሁላችሁም አንደታጠኑት
ነው የምማጸነው። ዳኛው ጥሩ ስራ ቢሰሩም፤ “አድርባይ/ወላዋይ” አቋም በመያዝ ተስፋን ያክል መርዘኛ ሰው ቦታ ሰጥተው ሲያሰድቡን
እና “ሲያስጎረጉሩን/ሲያጃጅሉን” የነበሩት እንደ እነ ክንፉ አሰፋ የማሳሰሉ መርዘኛ እና ቡድንተኞችና በታኝ ጋዜጠኞች አንዲሁም
መላው የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጉድ እያወቁ ለሁለት ዐመት “ሸሽገውት” ለምን አንደቆዩ ጸሐፊው ያስገረማቸውን ያህል እኔም አስገርሞኛል።
እነዚህን ነው ዳኛው “ሲያቀብጣቸው በጥሩ ስራቸው ላይ ከማተኮር ይልቅ
“ የሻዕቢያ” መጽሐፍ አራሚዎችና አሻሻጭ ደላሎች እና መተላለፊያ ድልድይ ሆነው ሲየገለግሉ የነበሩትን “ሚዲያዎች” እን
ግለሰዎች “መካባቸው” ያስገረመኝ።
ሚዲያዎች ይቀርታ መጠየቅ አለባቸው። የአማራ ሕዝብ በኦሮሞዎች፤ በሐረሬዎች ወዘተ ወዘተ…
እንዲጠላ እና አንዲገደል የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸምበት የተቻለውን ያህል በመጣር ፤መጽሐፈት ሳይቀር በአማራ ሕዘብ ላይ ግድያ
እና ጥላቻ እንዲፈጸምበት የጻፈ፤ የዋሁ አማራው ሕዝብ በመጽሐፉ ላይ
”በበግ” እንሰሳ የሚመሰል “እራሱን” *የበግ ነጋዴ* በማለት አማራውን
“ለጭዳ/ለ ዕርድ” የሚያዘጋጅ አደገኛ የዘመናችን “ወንጀለኛው ጋዜጠኛ” ፤ በጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ሳይቀር ‘አማራን ሕዝብ በመጨፍቸፍ
የዘር ማጥፋት የፈጸመው “ኦነግ” የተባለው ሽብረተኛ እና ወንጀለኛ ድርጅት “ተስፋ ገብረአብን “ኦቦ” የሚል የታጋይ ክብር መጠሪያ
“ማዕረግ” የተሰጠው “የሻዕቢያ እና የኦነግ” ጠበቃ፤ መሆኑ እያወቁ ሚዲያዎች በዚህ ጨዋታ ተነክረው እንደነበሩ ‘ዳኛው’ እያወቁ
“ግለሰቦች በማይገባ ‘ማካብ’ ባሕሪ ውስጥ መግባታቸው የሚያስተቻቸው ስለሆነ፤ ይኸው የጥሩ ኢትዮጵያዊው የአቶ ሶማው ትችት ባዳኛው
ላይ የቀረበው አንድታነቡት እጋብዛለሁ። አመሰግናለሁ። ትችቱ ይኸው ከዚህ በታች ፡ መልካም ንባብ! (ጌታቸው ረዳ
ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)
“ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ”
(የሶማው)
በቅድሚያ አቶ ዓለማየሁ ስለሰሩት ጀግንነት ከልብ የምነጨ አድናቆቴን እገልጽሎታለሁ
ነገርግን ይህን የመሰለ መረጃ ሳይወጣ መቆየቱ የሚያሳዝን ነው። አቶ ወልደሚካኤል መሸሻ እንዲወጣ ላደረጉትን ትብብር ምስጋናዬ ይድረሶት።
ነገርግን እስከ ዛሬ ድረሰ ለሚዲያ ያላወጣሁብት ምክንያት ብለው የሰጡት ማስተባበያ ውኃ የማያነሳ ነው። ምክንያቱ ይህ መረጃ ለኢሳት
ድጋፍ ኮሚቴ ከደረሰው ሁለት ዓምት ሊሞላው ምንም ጊዜ አልቀረውም ነገረግን በግንቦት7 መሪዎች ጫና እንዳይወጣ መደረጉ እኛ የኢሳት
ድጋፍ ኮሚቴዎች ማለትም አቶ ወልደሚካኤል መሸሻ፣ አቶ ካሳውን
አሊ፣ አቶ ብስራት ኢብሳ፣አቶ ፋሲል የኔዓልም፣ አቶ ዘውዱ ከበደ እና ወንድወሰን ገብረሂይወት
እንዲሁም ከአንድ ዓመትበፊት የለቀቀው ብራስልስ የሚገኛው ተስፋዬ የምናውቀው እና የማንክደው ሚስጢር ነው። በዚህም ጉዳይ ብዙ ተነጋግረናል።
እውቁ እና ታላቁ ኢትዮጵያዊ አቀንቃኝ ጥሌ ስያቀነቅን “ ሐሰት ለመናገር አትሻ ምላሴ ለእውነት እሞታለህ አልሳሳም ለነፍሴ” ሲል
የሙያ አጋሩ እና ታላቁ አቀንቃኝ ሙሃሙድ “ ቆሞ የምናየው በመልካም ሰውነት ነገ የጉድጓድ ነው የዛሬ ሰውነት” በማለት ጨርሶታል።
ነገ ሟች ነን እውነት እውነቷን እንጫወት። ታዲያ የተስፋዬ ሰላይነት እንዲደበቅ ያደረጉና በመጽሀፉ ክለሳ፣ህትመትና ፕሮፓጋንዳ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ያደረጉት የግንቦት7 መሪዎች እና
ኢሳቶች ለምን በዚህ ጉዳይ አልተተቹም?
ፋሽስቱ ተስፋዬ (ፌሊሲዮን ካቡጋ)
ስለተስፋዬ ማንነት በተለያዩ ጊዜያት ሰላይነቱን እና ፀረ-የኢትዮጵያዊነቱ፣ መደዴ ዘረኝነቱ
ግልጽ ካደረጉት መካከል እኔ
ከማውቃቸው መካከል በግሪን የሎርድ ቅጽል ስም የሚጠራው ሰው በፓልቶክ፣ ጌታቸው ረዳ
የኢትዮጵያ ሰማይ በሚለው ብሎጉ “ ትቁር አሞራው ሙሴ” በማለት እንዲሁም መምህር አንተነህ ጌትነት ኤርትራ ለትግል ደርሶ የተመለሰ
በግንቦት7d ዌብ ሳይት ላይ ማነነቱን አስረግጠው ነግረውናል። በእኔ እምነት ተስፋዬ ሰላይ ብቻ የሚለው ስም በቂው አይደለም የዘር
ፍጂት እንዲነሳ የቀሰቀስው ሁለተኛ አፍሪካዊው ካቡጋ ጭምር ነው እንጂ። ይህን ስል ለአማራ መጨፍጨፍ( ጀኖሳይድ) በአስተባባሪነት
ሻቢያ፣ ወያኔ እና ኦነግተጠቃሾች ናቸው። ይህንንም እያወቀ ከነዚህ ፋሽስቶች ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ከፈጥሩት ውስጥ ከሻቢያ፣ ከኦነግ
እና ከተስፋዬ ገብርአብ ጋር ከፍተኛ ግኑኙነት( ቁርኝት) ያላቸው ግንቦት7 እና ኢሳት በመጀመሪያው ረድፍ ይምደባሉ። ይህን እያወቁ
ጀሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው “ አውቆ የተኛን...” እንደሚባለው ነው።
አቶ ወልደሚካኤል እስኪ ልጠይቆት?
ሀ/ የተስፋዬ የደራሲው ማስታወሻ ለቀማውን፣እርማቱን እና ህትመቱ በአንዳርጋቸው መከናወኑን
አያውቁም ነበር? ለምንስ በዚህ ጉዳይ አንዳርጋቸውን ተጠያቂ አልደረጉም? አንዳርጋቸው አፉን ሞልቶ የተስፋዬን መጽሃፍ እስኪታተም
ድረስ የረዳሁት ከተስፋዬ 60.000 ብር ስለምናገኝ ነው በማላት አፉን ሞልቶ ለትግል የሄዱትን ታጋዬት ቅስም መስበር ምን ይሉታል?
“ ቃሉን ከሚበላ ሰው የበለጠ አውሬ የለም።”
ለ/ አንተነህ ሙሉጌታ “ የሁለት ዓለም ሰዎች” መጽሃፍ ለማሳተም ያስገባ ሲሆን የተስፋዬ
መጽሃፍ ቀድሞ እንዲወጣ መደረጉን አያውቁም? በዚህ ጉዳይ አንተነህ እና ብርሃኑ የተካረረ ፀብ እንደገቡ መቅረታቸውን አያውቁም ነበር?
ያ ሁሉ ችኮላ ኢትዮጵያን ለመገነባት ወይስ ለማጥፋት? መልሱን ለእርሶ እተወዋለሁ።
ሐ/ የግንቦት7 ( የአንዳርጋቸው እና የብርሃኑ ጦር ኤርትራ መክተሙን አያውቁም? ጦር
ስልዎት ግር እንዳይሰኙ በ4 ዓምት ውስጥ 30 ሰዎች የድረሱት እስክግንቦት 2013 ባለኝ መረጃ ማለቴ ነው።
መ/ ተስፋዬ ወደኤርትራ የሄደው ከአለቆቹ መመሪያ ለመቀብል ነው ይሉናል ተስፋዬስ መመሪያ
ለመቀበል ከሄደ የግንቦት7 ታጋዩ አንዳርጋቸ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ከሚፈልግ ሻቢያ ብብት ስር የተሸጎጠው?ለምን ይሆን? እባክዎን
ይመልሱልኝ? በኢትዮጵያስ ህዝብ እየቀለደ ያለው ማን ነው?“ ዳር ቆሞ የሳቀ ማሃል ገብቶ ያለቅሳል” ይባላል ።
በኢትዮጵያ ህዝብ የቀለደ የኢትዮጵያ አምላክ እንደሚቅጣው ከመለስ(ለገሰ) እና ከታጋይ
ጳውሎስ
ቅጣት መማር በቂ ነው። አይመስሎትም?
ሠ/ ይህ መንግስት ያለነፍጥ አስገዳጅነት ስልጣን ሊለቅ አይችልም የሚል ህልም አለኝ
ይሉናል ታዲያ ግንቦት7 ህልሞን ሊፈታሎት ነው ሻቢያ ስር የተሸጎጠው?ኧረ ኧረ ግፍ ይፍሩ ሻቢያ ጠላታችን ነው እያሉ በሌላ በኩል
ነፍጥ የያዘውን እንርዳ ይሉናል። ነፍጥ እዣለሁ የሚሉ ያሉት ኤርትራ ውስጥ እንደሆነ አጥተውት ነው?
ረ/ ሰለኢሳት እና ስለተወስኑ የነፃ ሚዲያ ጋዜጠኞች ያሉን ደግሞ “ ከሀገር ኮብልለው
ከወጡ በኋላ የጉሮሮ አጥንት እየሆኑ ናቸው ያሉዋቸው ክንፉ አስፋ፣ ኤልያስ ክፍሌ ( እህቱም ሂሩት ክፍሌ ማንነቷ ለምናውቅ ውስጡን
ለቄስ ማለቱ ይሻላል? ይህ ከእኔ የተጨመረ)፣ ደረጀ ሐብተወልድ ( ዶሮው ፍርድ ቤት ቀረበ)፣ፋሲል የኔዓለም የግንቦት7 አባል እንደሆነ
እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ ታዲያ ይህ ሰው ነፃ ጋዜጤኛ የሚሆነው በየትኛው መለኪያ ነው? እና አበበ በለው የመሳሰሉት ሙያቸውን
ሽክን አድርገው ወያኔ መደበቂያ እያሳጡ ያሉ እና እሳት የላሱ፤ እንደሻማ ደግመው ደጋግመው እየቀለጡ፣እየወደቁ፣እየተነሱ (የትኛው
ጦር ሜዳ? የእኔ ጥያቄ ነው) ከእውነት ላይሸሹ ቃልኪዳናቸውን ሁሉ እንዳደሱ
ቀጥለዋል? ባንጻሩ ደግሞ ተስፋዬን የመሳሰሉ የእናት ጡት ነካሾች በሀገር የጀመሩትን
ወኔ መስለባቸውን እውጭም ከውጡ በኋላ አባዚያቸው አለቀቃቸውም ብለውናል። እኔ ደግሞ “ ከዝንጀሮ ቆንጆ...” ብለዎት ምን ይሰማዎታል?
ደምስ በለጠ የሚባሉ “ የጋዘጤኝነት ሙያ እና በውጭ ያሉ ሚዲያዎች አገልገሎት ሲገመገም” ከሚለው መጣጥፉ
በመውሰድ እርሶ ያደነቋቸውን ጋዜጠኞች በነዚህ ሶስት መስፈርቶ ብከፍላቸው ቅር ይሠኙ ይሆን? ፍርዱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልተወው።
1/ ወገንተኛ ጋዜጠኛ ( Advocacy Journalist)፡ እነዚህ ጋዜጤኞች አገልግሎታቸው
ለተወሰነ ቡድን ወይም ስብስብ ብቻ ነው ይለናል። እውን እርሶ የገለጿቸው ጋዘኞች በዚህ ክፍል የሚመደቡ አይደሉም? ይህን ለሂሊናዎ
እተወዋለሁ።
2/ ተለማማጭ ና ደብተራ ጋዜጤኛ ፡ እነዚህ ደግሞ እንደውሻ ጭራቸውን የሚቆሉ ያለቆቸውን
ፍላጎት ብቻ የሚያራምዱ እንደ ደረጀ ሐብተወልድ እና እንደ ፋሲል የኔዓልም የመሳሰሉትን የኢሳት ጋዜጤኞችን ያካትትታል። ለምሳሌ
የኢትዮጵያ ህዝብ ኤርትራን ውስጥ ትግል እንደማይሰራ እና እነ ኮሌኔል ታደሰ ፣ተስፋዬን እና የመሳሰሉትን ዕንቁ ኢትዮጵያዊ ያጠፋ
ሻቢያ እንዴት ለኢትዮጵያ ቅን ያስባል በማለት ቢቃወምም ኢሳቶቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓይንና
ጆሮ በማለት ማፌዙን ምን ይሉታል? የነፃ ጋዜጤኞቾ፣እንደሻም ደገመው ደጋግመው ወድቀው
እየተነሱከእውነት ላይሸሹ ቃል-ኪዳናቸውን ሁሉ እንዳደሱ ቀጥለዋል? ምን ማለቶ ነው ይህ ከአንድ ትልቅ ሰው እንዲህ ያለ ውሸት የሚጠበቅ
ነው። “አይ ኢትዮጵያ የሞተለሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” መቼ ይሆን ከአንቺ የሚርቀው? እባክሽን እምዬ “ኢትዮጵያ እጅሽን ወደ እግዚአብሔር
ዘርጊ!!!”
3/ ውጥንቅት ጋዜጤኛ ( Jazz Journalist): የሚባለው ደግሞ እውነትን ከሃሜት
ጋር እየቀላቀለ በሌሎች ላይ የሚነዛ የአሉባለታ ጋዜጤኝነት ስለት ነው። አቶ ወልደሚካኤል የኢሳት ጋዜጤኛች በዚህስ አይካተቱም?
4/ በቀልተኛ ጋዜጤኛ ( Vendetta Journalist): የዚህ ዓይነት ጋዜጤኛ
የራሱን ስሜት እና ፍላጎት ስለሚያስቀድም የህብረተሰብ ጥቅም ወይም የጋዜጤኝነትን ሙያ ግዴታን አይከተልም። ታዲያ የኢሳት ጋዜጤኞች
በእርሶ ይመራሉ የሚባሉት እውን የህዝብን ጥቅም ያስከብራሉ? ሌሎችም አብዛኞች በነፃ ሚዲያ ስም የተቋቋሙ ባሌቤቶች በዚህ ይካተታሉ።
ከማውቃቸው ሚዲያዎች የፕሮፌሴር መስፍንን እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ብሎግን እና የጎልጉል ዌብ ሳይትን ሳላመሰግን
አላልፍም።
ተስፋዬ (ካቡጋ)፡ በቅድሚያ ቅንጣት ታክል ሰባዓዊነት ያልፈጠረበት ሰው እንዴት በጋዜጠኝነት
ይመደባል። የዘረኝነት
በሽታ የተጸናወተው በሽተኛ በየትኛው መመዘኛ ጋዜጤኛ ሊባል ይችላል? ግንቦት7 እና
ኢሳቶች ቆልላችሁት ነው ለዚህ እንዲበቃ ያደረጋችሁት። የአሜሪካ ድምጽም የግንቦት7 አጃቢ መሆናችሁ በላፈው በግንቦት7 ስብሰባ ከመገኘታችሁም
በላይ አንዳርጋቸውን እንደጀግና አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ድረስ ሄዳችሁ ቃለ-መጠይቅ ማድረጋችሁ ምን ያህል እንደቀለላችሁ እና ለኢትዮጵያ
ህዝብ ደንታ ቢስ መሆናችሁን ያሳየ ድርጊት ነው። ከዚህም በፊት አውሮፕላን ማሬፊያ ድረስ ሄዳችሁ ልከ እንደጀግና ስታደርጉት እሱም
ለሥራ እንድሚቸኩል እና ጊዜ እንደሌለው የተናገረውን አሁን ከሶስት ዓመት በኋል ድራማውን ደግማችሁ ስትተውኑት የሰማው ህዝብ እንዴት
እንዳቀለላችሁ ብታዩት!!! እውነቱን የምናውቅ ሰዎች ምን ያህል እንደአዘንባችሁ ብታውቁ ምን ያህል ማፈሪያዎች እንደሆናችሁ ትረዱ
ነበር!!!
አቶ ወልደሚካኤል ሰሞኑን ከኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ በፍቃዱ የለቀቀው ወንድ ወሰን ገብረሂይወት
በመልቀቂያው ላይ ምን ብሎ እንደጻፈ ላስታውስዎት።
ከዛሬ 2 አመት በፊት በጊዜያዊነት ተመርጠን እስካሁን በቆሁበት ግዜያት አንዳንድ ሊስተካከሉ
ይገባቸዋል ምላቸውን በግልጽ በመናገርም ሆነ ኢሜል ወይም በድህረ ገጽ እንዲወጡ ያደረኳቸው ሃሳቦች ለድርጅቱም ለሐገራቸን ነፃ ሚዲያ
መጠናከር ይጠቅማለ- በማለት ነበር።
በጣም የሚገርመው አንድም የድርጅቱ ወይም የአምስተርዳም ሃላፊ ወይም የኮሚቴ አባል በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያነጋግረኝ የቻለ ያለመኖሩ
አስግርሞኛል። ባአለፈው በተደጋጋሚ በአምስተርዳም ለተደረገው ዝግጅት ህዝብን ጠርተን እናመስግን ከወጭ ቀሪ የተገኘውን ሂሳብ እናስረዳ
አዲስ ምርጫም እናካሂድ ብዬ ብጎተጉትም ነገ ዛሬ እየተባለ ማካሄድ አልተቻለም፤ በጣም የሚግርመው በኢሳት የአውሮፓ ስብሰባም ሆነ
በቅርቡ እንኳን ለኢሳት 3
አመት መታሰቢያ በተደረገው ወይይት ከሌላ ሀገር መስማቴ ምን ያህል ኢሳት በድርጅት የታጠረና በጥቂት ግለሰቦች ፈላጭ
ቖራጭነት
መያዙን የተረዳሁበት ነወ።
ከኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ አባልነት ስለመልቀቅ ብሎ በጠየቀበት ወቅት በኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ
ሆኘ በቆየሁበት 2ዓመታት ቆይታዬ ከውጭ ከምሰማው ይልቅ በጥቂት ቀርቤ የተረዳሁት ጭብጥ እና ለራሴም የህሊና ፍርድ ሊያሰጣኝ የሚችል
መጠነኛ ግንዛቤ አግኝቻለሁ። በመሆኑም ወደፊት ሊስተካከሉ ይገባቸዋል የምላቸው ነጥቦች፡
ሀ/ ለአንድ ድርጅት ተጠሪነት እና የባለቤትነት ኃላፊነት ግንባር ቀደምተግባር ነው።ኢስት
ከተመሰረተ ጀምሮ እስከአሁን ምላሽ ሊሰጥበት ያልቻለ የአደባባይ ሚስጥር ነው።እንዴኔ ግንዛቤ በሥራው ላይም እያሳደረ ያለውን ተጽዕእኖ
የዚህ
ውጤት ይመስለኛል።
ለ/ በሙያ የተጠናከረ ኃላፊነት ሊወስድ የሚችል በግልጽ የሚታወቅ ኤዲቶሪያል ቦርድና
የአስተዳደር ክፍል ያለመኖር። በየጊዜው ከውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች እና ከውጭ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያለመቻል።
ሐ/ ከዲያስፖራው ኢሳት ለሚቀርጻቸውን ያለአድሎ ሊተላለፍ የሚገባው ፕሮግራሞች አንዳንድ
ጊዜ የመቆራረጥ ወይም የማይሆን ምክንያት ሰጥቶ ያለማቅረብ።
መ/ በእርምት መልክ የሚቀርብ ሃሳቦች ተቀብሎ ወዲያው ለማስተካከል ያለመቻልና ይቅርታ
የመጠየቅን ባህል ለማዳበር ያለመቻል።
ሠ/ ኢሳት በአምስተርዳም፣በሆላንድ እና አጎራባች ሀገሮች ካሉ ኢትዮጵያን ማህበሮች
ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለመፍጠር።
ረ/ በቋሚነት ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ አባሎችን ሰፊ ጥረት አድርጎ ከማሰባሰብ ይልቅ በጊዜአዊ
የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅቶች ላይ ሰፊ ጊዜ መስጠት።
ሰ/ ብዙው ኃላፊነት አንድ ሰው ደርቦ እንዲሰራ መደረጉ። ከኮሚቴ
አባልኔቴ ወቅት ከሰራናቸው ሥራዎች ውስጥ በተለይ በፋሲል የኔዓልምና ቤተሰቦቹ ላይ
የሚደረገውን ውስጣዊ ደባ እና ሰባዊነት የጎደለው የማንገላታት ሴራ ለማስቆም ግልጽ ድጋፍ መስጠት ( እውን አቶ ወንደሰን የፋሲል
ወንድሞች በወያኔ ስቃይ በልተዋል?ኧረ ተዉ እባካችሁ የፋሲል ወንድሞች ፌደራል ፖሊስ የነበረ፣ ወንድሙ እና እህቱ የቤአዴን አባል
እንደነበሩ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው እንደዚሁ የፋሲል ታናሽ ወንድም የቤአዴን የንግድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ለብዙ ዓመታት
የሰራ እና 2011 መጨረሻ በግል አለመስማማት የለቀቀ መሆኑ እየታወቀ እንዴት ስቃይ ደረሰባቸው ትለናለህ? ያሳዝናል ጊዜ ሁሉንም
ያሳየናል) አቶ ወልደሚካኤል የእርሶ ኢሳት በታጋይነት ሰበብ የግል ጥቅም ማሳደድ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን አያውቁትም?
ስለ ታማኝ ያሉንት ከልቦ ነው?
በልጃችን በታማኝ ላይ አትኩሮቱን ቢጥልም ታማኝ እንዲህ የዋዛ መስሎት ዘው ብሎ ለመግባት
ቢጥርም ታማኝ መሰሪ
ቀበሮ ቀርቶ ለቀድሞ ጌቶችም ያልተበገረ፣ ግንባሩ የማይታጠፍ ቆፍጣና ኢትዮጵያዊ ነው።
ታዲያ ለምን በአንዳርጋቸው ምትክ ኤርትራ ውስጥ አዋጊ እንዲሆን ለግንቦት7 ሃሳብ ያቅርቡ።በኢትዮጵያ ላይ ወለም ዘለም እርሱ ዘንድ
የት አለና ይሉናል።ተስፋዬ በኢሳት ሲፈነጭ አንድ ቀን እንኳን ቅሬታ ያላቀርበ ሰው እውነት ይህን ያህል መካብ ነበረበት።ክንፉ አሰፋ
እና መስፈን አማን ከታማኝ ጋር ያላቸውን ቀሬቤታ አያውቁትም ልበል? ተስፋዬ ካቡጋ ሁለቱን ብቻ እንዳታለለ ይነግሩናል? እውን ታማኝ
ከተስፋዬ ጋር ግኑኙነት እንዳለው ሳያውቁ ቀርተው ነው? ታምኝን ከፍጡር በላይ ማድረጋችሁ ወዴት እንድወሰደው አልተረዱም?እስኪ በቅርቡ
መልቀቂያ የጠየቀው ወንደሰን ገብረሂይወት በደብዳቤው የገለጸው እንዲህ ነበር ባአለፈው በተደጋጋሚ በአምስተርዳም ለተደረገው ዝግጅትህዝብን
ጠርተን እናመስግን ከወጭ ቀሪ የተገኘውን ሂሳብ እናስረዳ አዲስ ምርጫም እናካሂድ ብዬ ብጎተጉትም ነገ ዛሪ እየተባለ ማካሄድ አልተቻለም።
አዩት የእርሶ ጀግና? ካካካካካካካካካካካካ...
ከበደ ሚካኤል “ ትዕቢት እና ውርደት አካልና ጥላ ናቸው” ማለታቸው ይሄው በታማኝ
እያየነው ነው።
ስለ ስዬ ያሉን ከምሮ ነው?
እጅግ እጅግ የገረመኝ ደግሞ የስዬ የኢትዮጵያ ፍቅር ነው “ዲንቄም ፍቅር”። በመጀመሪያ
ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቋል? ሌላው ተስፋዬ ካቡጋ መሆኑን ሳያዉቁ ቀርተው ነው ወይስ እያሾፉ ነው? እስኪ በጽሁፎ
ላይ ያሰፈሩትን እንደገና ላስፍርሎት “ከህወሓት ክፍፍል በኋላ እንዳገኘሁት ኢንፎርሚሽን( ኢንፎርሜሽን ባሏት አንድ በጎጃም የሆነውን
ልንገሮት ሰውዬው ካድሬ ቢጤ ነው ስብሰባ እተጠሩ በየጊዜው ገበሬው እንዴት እያለ ነው? ይባላሉ። እንደዚያ ሲባሉ አንዱ እጁን ያነሳል
ምንድን ነው ሲባል “በእነሱ አነጋገር ፎርማሺን ይሏታል የዛን ቀን ፎርማሽን የምትለው የፈረንጆች ቃል ትጠፋው እና ሸውክ አለኝ
ሲላቸው ሁሉም ተሰብሳቢ አንዴ ይስቅበታል ያም ገበሬ ነገሩ ስላናደደው ምን ያስቃችኋል ፎርማሽንም ብለው ሸውክም ብለው ያው ሽውክ
ነው ምን ለውጥ አለው አለ ይባላል።”)
የእርሶም ኢንፎርሜስን ሸውክ ሸውክ ሸተተችኝ በነገራችን ላይ ይህ አህዛቡ ወይኔ አማርኛችንን
ለማጥፋት የመለስን ለጋሲ ጂኒጃንካ ሆኗል አይደለም ቋንቋው? አልፈርድቦትም። ስዬ እና ሞቹ ሃየሎም ከመለስ ጋር ግጭት የጀመሩት
ገና ከጠዋቱ እንድሆነ።ስዬ የደርግ( የኢትዮጵያ ተብሎ ቢጻፍ ይመረጣል የእኔ ነው) ወታደሮች እና ፖሊሶች በሙሉ እንዲባረሩ አይፈልግም።
የኢትዮጵያ መከላከያ ከግራ ከቀኝ መሳ ለመሳ ሆኖ ተውጣጥቶ እንዲመሰረት ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር ነግረውናል።” “ማን ይናገር የነበረ
ማን ያርዳ የቀበረ” እንደሚባለው አቶ ገብረመድህን አርአያ በቅርብ ባውጡት ” የህወሓት ፀር ኢትዮጵያዊ አካሄድ እና ዓላም በመቃወም
የሂይወት መስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?” በሚለው መጣጥፋቸው ስለ ስዬ የጻፉትን አላነበቡም?
ጊዜ ካለዎት ያንብቡት ስለስዬ እውቀት ያገኛሉ።ይህቺን” በማር የተለወሰች መርዝ” ተውት አድርገው የአቶ ገብረመድህንን መጣጥፎችን
ያንብቡ። ጥሩ ትምህርት ያገኛሉ!!!
ሌላው አማራው በበደኖ ሲጨፈጨፍ ስዬ በስልጣን ላይ እንደነበረ ረሱት እንዴ? ተስፋዬ
ስዬን አምርሮ ይጠላዋል ይሉናል። ስዬ በአማራ ጭፍጨፋ በግንባር ቀድምትነት ተጠያቂ መሆኑን ዘነጉት? “ አህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም”
ይባላል ስዬ እና ተስፋዬ ሁለቱም ፌሊሲዮን ካቡጋ መሆናቸውን ዘነጉ ልበል? ስዬ ማሞካሸት አህዛቡን ወያኔ ማሞካሸት መሆኑን አልተገነዘቡም።
በዘር ማጥፋቱ ወንጀል ሻቢያ፣ የኢትዮጵያ የሻቢያ መንግስት( ወያኔ)፣ኦነግ እና ተስፋዬ
ገብርአብ( ካቡጋ) በአንድነት መሆናቸውን ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም።
መደምደሚያ
አቶ ወልደሚካኤ የተነሱበት ዋና ዓላማ ተስፋዬን እና ደጋፊዎችን ለህዝብ ማጋለጥ መስሎኝ
ነበር። ነገርግን የተስፋዬን ሰላይነት እና አስጨፍጫፊነት ነግረውን ደጋፊዎችን መካብ ምን ማለት ነው? ለካ “ አፍንጫ ሲመታ ዓይን
ያለቅሳል” ስለሆኖቦት ዋናዎችን ግንቦት7ን፣ኢሳትን እና ሰዬን መካብ ብቻ ሆነ ቁምነገርዎን የእምቧይ ካብ አደረጉት። እንግዲህ በዚህ
አባባሎች ልሰናበቶት፡
“ ቀበሮ ስህተቱ የእኔ ነው ብላ አታውቅም ሁልጊዜም የሚሳሳተው ወጥመዱ ነው። / ዊልያም
ብሌክ “ጋዜጠኛ ሳይኖርህ መንግስት ከሚኖርህ፤ ጋዜጤኛ ኖሮህ መንግስት ባይኖርህ የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ ለአንዲት ቅጽበት እንኳን
ሳላመነታ ሁለተኛውን እመርጣልሁ!!!” ነበር ያሉት ቶማስ ጃፈርሰን እኛስ ታዲያ መንግስትም ጋዜጤኛም እንዲሁም የተቃዋሚ መሪ እንኳን
የሌለን ምን እንበል? ነገርግን በሀገር ቤት ትንታግ ወጣት ታጋዬች ተስፋችንን እያለመለሙ ናቸው እነሱን እግዚአብሔር እውቀቱን እና
ጀግንነቱን ያድላቸው!!! ለባንዲራችን ክብር ደግሞ እንደ “ኮሪያ ጀግኖቻችንን” መስዋአትነት የሚከፍሉ መሪዎችን ይስጠን። ጊዮርጊስ
በፈረሱ ይምራቸው። በሀገር ቤት ወያኔን እያርበደበደ ያለውን የሰላማዊ ትግሉን እንደገፍ።
እግዚአብሄር ለኢትዮጵያ በጎውን ቀን ያምጣላት
የሶማው ነኝ__