Monday, September 23, 2024

ባዶ ቤት በቁንጫ ይወረራል! ሽግግርና ድርድርድር ከማን ጋር? ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 9/23/24

 

ባዶ ቤት በቁንጫ ይወረራል! ሽግግርና ድርድርድር ከማን ጋር?

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 9/23/24

በሙሶሎኒ የፖለቲካ ዘረመል የተደቀሉ የወያኔ ትግሬዎች በአገር በቀል “ጣሊያናዊ ቅኝ ግዛት” ሥልት ተቃኝተው ኢትዮጵያን በዘርና በቋንቋ ሸንሽነው ስተዳዳር አማራን፤ አማርኛ ቋንቋን፤ በጣሊያኖች ቦቴ ተረግጣ ወድቃ የተነሳቺው ብሔራዊ ሰንደቃላማችንን እና የአማራ መደበቂያ ብለው የጠርዋትን ኦርቶዶክስ ሃይማኖታችንን በጠላትነት ቀለበት እንዲታዩ ዓልመው ለማጥቃት ሥልጣን የተቆጣጣሩት ትግሬዎች ያንን ሲፈጽሙ ለ27 አመት ለነሱ ያልተምበረከከው ኢትዮጵያዊ ዜጋን ደግሞ ገድለው፤ ዘርፈው፤ ቀጥቅጠው ካሸበሩት በላ መሪያቸው በፈጣሪ ትዕዛዝ ተወገደ። ጥቂት ዓመታት ከገዙን በላ የተቀሩትም በሕዝቡ እምባ ከሥልጣን ተወገዱ። ሲጠረጉ፤ በምትካቸው የተተካው አድፍጦ የቆየው አገልጋያቸው ነበር።

አገልጋያቸውም ኦሮሙማ በሚል ድብቅና ግልጽ ፕሮጀክት አንግቦ ወደ ሥልጣን የወጣው ኦነጉ አብይ አሕመድም ነብሰ-ገዳዮችን፤ ወንጀለኞችን ፤ አጭበርባሪዎችን ፤ አገር ገንጣዮችን አክራሪ የሃይማኖት ጀሌዎቹንም ሁሉም ያለ ምንም “ቁጥጥር እና ውል” ወደ አገር እንዲገቡ በማድረግ “ረገብ ብሎ” የነበረው ግንጠላቸውን እና የመግደልና የሽብር ጥማታቸውን ለማስቀጠል ባንዴራቸውን ሳይቀር ማውለብለብ እንደሚፈቀድላቸው ቃል ገብቶላቸው ገብተዋል። በገባላቸው መሰረት፤ ኢትዮጵያን ዛሬ ባለችበት አሳዛኝ ክስተት እንድትገባ አደረግዋት። እርሱም ሥልጣኑን እርካብ አጥብቆ በመያዝ ሰላም አመጣለሁ ብሎ ይቅርታ ጠይቆ ያታለለውን ሕዝብ ለኑሮ ውድነት፤ ለስደትና ለባሰ ዕልቂት ዳረገው።

ይህ እንዲህ እያለ፤ እዚህ ላይ ታሪክ መርሳት የሌለበት ተጠቃሽ ሰው ባገሪቱ ብቻውን የተስፋ ሻማ አብርቶ ከጥቂት ተከታዮቹ ጋር ሰለማዊ ትግል እታገላለሁ ብሎ ብዙ ዋጋ የከፈለ እስክንድር ነጋም ሲታገላቸው የነበሩት ሁለቱ ሥርዓቶች ለመጣል ወይንም ሥርዓት ላማስያዝ ሕዝቡ እንዲያግዘው የተቻለውን ያህል ቢጥርም ሕዝቡም እንደ ወትሮው “ዳተኛ” ሆኖ ብቻውን ተስፋ በመቁረጡ “አፓርታይዳዊው ሥርዓት” በጥይት እንጂ በሰለማዊ እንደማይገረሰስ ውሳኔ ደርሶ ጫካ ገብቶ ፋኖን ተቀላቀለ። ብዙዎቹም የእርሱና የመሰሎቹ ኮቴ በመከተል ጫካ ገብተው ዛሬ አታላዩና ኦነጋዊውን  ሥርዓት እያዋከቡት ይገኛሉ።

ለብዙ አመታት “አማራው ወደ ጫካ ይግባ” ስል ብቸኛ ውትወታ ሳሰማ የነበርኩኝ እኔም ውትወታየ ግብ መትቶ እነሆ እንደተፈለገው ጫካ የገቡት “ፋኖዎችም” ባንድነት ባይታገሉም እሰይ የሚያሰኝ አመርቂ ተስፋ እየገነቡ ነውና አማራው እንደ ድሮ  ፋሺሰት ትግሬዎችም ሆኑ ናዚ ኦሮሞዎች የለመዱበትን አማራን የመናቅ ባሕሪያቸው ሁለቴ እንዲያስቡበት አድርጓቸዋል። አሁን መበርታት ብቻ ነው።

ሁኔታው እንዲህ እያለ”  ውጭ አገር የሚኖሮው ልደቱ አያሌው ኢትዮጵያዊያን ምሁራንና ፖለቲከኞችን እንዲሁም ወያኔዎችና ኦነጎችን በመጋበዝ በርዕዮት ሚዲያ (ቴድሮስ ፀጋዬ በሚያዘጋጀው ድረገጽ ቲ/ቪ) በርከት ያሉ የውይይት ክፍሎች ባመስተናገድ “ከአብይ ገሃነም መውጫ ”“ሠላም አንዴት ይምጣ?” “ዘላቂ ሰላም፤ሃቀኛ አገራዊ ውይይትና ድርድር በአዲስ የሽግግር ሂደት፤ ጭፍጨፋው እንዴት ይብቃ? | አገዛዙን ለማስወገድ ወይም ለማስገደድ እንዴት እንተባበር? ወዘተ….. የሚሉ ውይይቶችን በማዘጋጀት በርት ያሉ ከላይ የተጠቀሱት ብዙዎቹ የምናውቃቸውና በሃገረ ትግራይ ቅዠት የተቃኙ አዳዲስ የወያኔ ቡቃያዎች እያነጋጋረ ነው።

የልደቱ ሃሳብ በጎ ቢሆንም እየተከተለው ያለው ስልት ግን ድሮ ተሞክሮ የወደቀ ስልት ነው። ይሄውም ካሁን በፊት እዚህ ውጭ አገር ተሞክሮ ውጤት ያላመጣና ያውም ማሞኚያ መንገድና አክራሪ ሃይሎችና ተገንጣዮች የብዙ አምሐራ ነብስ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ያዘዙ ሃይላት ሰው መስለው እንዲታዩ የተጠቀሙበት መድረክ እንደነበር እናስታውሳለን (ሌንጮ ባቲን፤  ሌንጮ ለታን ፤ ዲማ ነገዎን፤ ፕሮፌሰር ሕዝቄል ጋቢሳ ፤ ጃዋር መሐመድ  ወዘተ…ወዘተ… ኦነጋዊው ወኪላቸው ወደ አዲስ አባባ እንዲገቡ ከጠራቸው በላ ምን እንዳደረጉና ምን ይናገሩ እንደነበር እናስታውሳለን።

ልደቱ ዛሬም ደግሞ ያመጣቸው እነኚያን የምናውቃቸው ሰዎች (አክራሪ ብሐረተኞችና ከአማራ ጋር አንዳትጋቡ ከተጋባችሁም ተፋቱ የሚሉ እነ (አሉላ ሰለሞን) ወይንም አማራዎች ሱቃችሁ አንድ ነገር ለመግዛት ፈልገው ኦሮሙኛ ካልተናገሩ ዕቃ እንዲገዙ አትፍቀዱላቸውአማራዎች ኦሮሞን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው (ኦነጉ በቀለ ገርባ) እንዲሁም ከትግሬዎች ደግሞ አዳዲስ የወያኔ ቡቃያዎች ኢሳያስ ሃይለማርያም፤ እና ግደይ ምዑዝ (ኢትዮጵያ ላይ ጥላቻቸው የበረታባቸው ፤ የሃገረ ትግራይ አቀንቃኝ ብሔረተኞች) እና የመሳሰሉ የኢትዮጵያን መፍረስ የሚመኙና የሚተጉ ግለሰቦችን ኢትዮጵያን በጠላትነት የፈረጁ ኢትዮጵያ አገራችን ነች የማይሉ፤ ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሔ ሰጮዎችና መፍትሔ አፋላላጊዎች ተደርገው በልደቱ አይን የታጩ ያንን የሰለቸን ነገር ሲደግመው እያየሁ ነው።

እነዚህ ሰዎች ከኢትዮጵያ መፍረስ ሌላ አማራጭና ፍላጎት እንደሌላቸው “ፋይላቸው” ይመሰክራል። “ቲ ዲ ኤፍ” ብለው የሚጠሩት  “ዱርየና ዘረኛ ተዋጊያቸው”  “ተጋድሎ ትግራይ ቦሎ ነቲ  ዓሻ አምሓራይ” እያሉ ሽሮና በርበሬ ሊጥ እና የመጠጥ ቤቶች ቢራና አረቄ እየዘረፉ ሰክረው ህጻናት ልጃገረዶችንና  ሴቶችን እየደፈሩ፤ ደሴን አልፈው ሰሜን ሸዋ ሲገቡ ያንን የተላኩበትን ዘረኛ ተልዕኮአቸው ለመፈጸም የታነጹበትን ዘፈናቸው እየዘፈኑና እየጨፈሩ “በተጋዳላይ ትግራይ” ቅኝት “ሓቢርና ንሕሰብ ብዛዕባና ናብራ - ሎሚስ ይኣኽለና ግዝኣት ናይ አምሓራ” (የአማራ ጨቋኝ አገዛዝ ለማብቃት አንድ ሆነን ስለ ለራሳችን ኑሮ ብቻ በማትኮር እናስብ” እያሉ የአማራን ማሕበረሰብ ከጫፍ አስከ ጫፍ እረፍት ያሳጡትን ሥርዓተ-ቢስ ዋልጌ ተዋጊያቸውን ወደ ሃገረ ትግራይ ምስረታ እንዲያስብ የሚቀሰቅሱ እነዚህ እና የመሳሰሉ የወያኔ ቡቃያዎችን ነው ልደቱ ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም የሚጨነቁ ናቸው ብሎ ተስፋ ጥሎባቸው እየደጋገመ የጋበዛቸው።

ልደቱ አያሌው ከተገንጣዮች ጋር አብሮ መስራት መሞዳሞድ ችግር የለበትም። ሌላ ቀርቶ ለፈርጀ ብዙ ችጋራችን ዋናው ቀያሽና ተጠያቂ የሆነው ጥቁር ጣሊያን ብለን እኛ ጥቂት ትግሬዎች የምንጠራው ለመለስ ዜናዊ ሳይቀር ልቡ የሚደማ የዋህ ፖለቲከኛ ነው። ጋዜጠኛ ያየሰውና ልደቱ ከነዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር መሞዳሞድ ችግር የለባቸውም። ከነዚህ ጋር መተሻሸትና ማሞገስ ሥልጡን ፖለቲካ ነው ይሉታል።

ልደቱ መለስ ሲሞት ለ ለትምህርት ሄዶ እያለ  አንድ ጋዜጠኛ ስለ መለስ ሕልፈት ምን እንደተሰማው እንዲገልጽለት ሲጠይቀው እንዲህ ያለውን ላስታውሳችሁ፦

 “ኢትዮጵያ  አንድ ሰው አጥታለች!!” “መጽሐፌን አይተህ ከሆነ ተቃዋሚዎች እሳቸውን ከሚያይበት ዓይን መቀየር እንዳለበት መለወጥ እንዳለበት (እኔ ከተቃዋሚው) ለየት ባለ ዓይን ነበር የማያቸው” “ያኔ ብዙ ሰዎች እንደዚያ ብየ በመጻፌ ብዙ ሰዎች ደስ ያላለቸው እንደነሩ አውቃለሁ።ዛሬ (እኔ ያልኩትን) የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚያ መልኩ እያሳየ ይመሰልኛል። በመሞታቸው አዝኛለሁ፡ ለቤተሰቦቻቸው፤ ለኢትዮጵያ መንግሥትም ‘ለኢትዮጵያ ሕዝብም’ መጽናናትን እመኛለሁ። የፖለቲካ ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ወቅት የማይታጡ ምናልባትም ለወደፊቱ ለሃገሪቱ በጎ ተግባር ለማበርከት ዕድሉ ይኖራቸው ነበር ብየ አስባለሁ። እና “ኢትዮጵያ አንድ ሰው አጥታለች ብየ አምናለሁ!” ከፓርላማ ውጭ እኔና እሳቸው በጋለ ስሜት ስንከራከር እንደነበር እና ከዚያ መድረክ ውጭ በአካል ስታገኛቸው “ሰውነታቸውን/ (ሰብዕናቸውን) የምታየው ያኔ ነው”። እና ምናልባትም እሳቸውን የምናይበትን ዓይን ቀደም ብሎ ቢለወጥ ኖሮ የአገሪቱን ችግር ሳይሆን የመፍትሔ አካልም አድርገን አይተናቸው ቢሆን ኖሮ ‘ተገቢውን ዕውቅና እና ምስጋና’ ሰጥተናቸው ቢሆን ኖሮ ምናልባት አሁን ከሰሩት የተሻለ ይሰሩበት የነበረ ዕድል ይኖራቸው ነበር ብየ አምናለሁ።>> ይላል ልደቱ ስለ ወዳጁ መለስ ዜናዊ ሕልፈት የተሰማው ሐዘኑን ሲገልጽ

አቶ ልደቱ እያለን ያለው ‘መለስ ዜናዊ’ በአካል ስታገኘው እጅግ ሰብአዊ ነው፤ ችግር አምጪ ሳይሆን መፍትሔ አመንጪ አድርጋችሁ ብታዩት ኖሮ ተገቢውን “ዕውቅና እና ምስጋና ስላልቸራችሁት” ዕንቅፋት ስለሆናችሁበት እንጂ ለኢትዮጵያ ከአፓርታይድ ባንቱስታዊው አስተዳዳር ውጭ የተሻለ መፍትሔ ያመጣ ነበር እያለ እኛ ለመለስ/ለወያኔ/ አስተዳደር ያለመሻሻል “ዕንቅፋት እየሆንበት” እንደሆነ እኛን አምርሮ ይወቅሳል። “መለስ በማጣታችሁ ኢትዮጵያዊያን ጽናቱን ይስጣችሁ ይለናል።ይገርማል!!!

  ወያኔነት ከዚህ ወዲያ ካለ ንገሩኝ” ብየ ነበር መለስ ሲሞት ባንድ ጽሑፌ ልደቱን ተቺቸው የነበረው።

ስለዚህ የተጠቀሱት በርካታ ሰዎችና እዚህ ያልተጠቀሱ ግለሰዎች ኢትዮጵያን አማራን ሰንደቅ አላማን አማርኛ ቋንቋን እና በመሳሰሉት የአገሪቱ ምሰሶዎች መዳከምም አለባቸው ብለው ስለሚያስቡ የነሱ አካል አድርገው ስለማያዩዋቸው ከነዚህ ጋር የሽግግር መድረክ መስርቶ ሰላም ይመጣል ብሎ መቃዠት ውጤቱ አብይ ወደ ሥልጣን ሲገባ እነዚሁ የሰላም አፈላላጊዎች ተብለው የነበሩት ግልብጥ ብለው ትከክልኛ ቆዳቸው እንዴት እንዳሳዩት የምናስታውሱት ነው።

የልደቱ ሙከራ ካለፉት አወያዮች የሚለየው ነገር ቢኖር “ኦነግና ህወሓት” ወደ ኢትዮጵያዊነት ተመልሰዋል ይሉን እንደነበሩን የመድረክ አዘጋጆች ከእነ እንደ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው፤ ብርሃኑ ነጋ ወዘተ….የመሳሰሉት ይለያል። ልደቱ ግን በግልጽ እንደ ተጠቀሱት ባይልም፡ እባቡም ፤ ጃርቱም ፤ ዕርግቡም ፤ ጅቡም፤ ቆቁም ፤ ጊንጡም አሕያውም ፤ ሚዳቋንም…. ሁሉም አሰባስቦ በየጥሩምባቸው ያስጮሃቸዋል። ይህ ደግሞ በፖለቲካ የተፈጥሮ ሕግ የማይሰራ ነው። ወንጀል የሰሩ ሰዎች ፤ኢትዮጵያ አይደለንም የሚሉ ሰዎችና ቡድኖች መፍትሔ ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ "ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ መጠበቅ ነው"።

የውይይትና የመፍትሔ አካል ይሁኑ እንኳ ቢባል (ምክሬ አገር ውስጥ ላለው ለአማራው ነው) ወቅቱ አሁን ሳይሆን ብረታችሁን አቀጣጥላችሁ፤ ታብየው የፉከራና የንቀት አፋ ከሚደፍቁ የትግራይ ብረተኞችን ኦሮሞ ብሔረተኞች እኩል ተገዳዳሪ ጡንጫ መገንባታችሁን ስታረጋግጡ ያኔ እባቡም ፤ ጃርቱም ፤ ዕርግቡም ፤ ጅቡም፤ ቆቁም ፤ ጊንጡም ፤ አሕያውም ፤ ሚዳቋንም ፤ ከብቱም…. ተሰባስበው ጡሩምባ ሲነፉ ፤ ‘የናንተንም የጡርምባ ድምጽ እንዲሰሙት ይገደዳሉ’። የጥሩምባችሁ ድምጽ ይዞ መምጣት ያለበት “በነገዳችሁ ላይ ጭፍጨፋ ያዘዙና የተካፈሉት ሁሉ የሚቀጡበት “ገለልተኛና ዓለም አቀፍ ሰዎች የሚካፈሉበት “ ፍርድ ቤት እንዲቋቋምና ወንጀለኞቹ ተመልሰው እንደ በፊቱ ፖለቲካና በከፍተኛ ሥልጣን እንዳይሳተፉ” እንዲደረግ ዓለም አቀፍ አገሮች የሕግ፤ የማሕበራዊ ፤ የሥነ መንግሥት የሽግግር ልምድ ያካበቱ የውጭ ሰዎችንና የተባባሩት መንግሥታት ታዛቢዎች ባሉበት ካልተዋቀረ ፤ የተለመደው “በሽግግር ስም መተቃቀፍ’ እዚህ እንደምንሰማው ቀልድ “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” ውይይት እልባት እንዲኖሮው ከፍተኛ ሚና መጫወት አለባችሁ።

ሁሉም ጎጆና ጠመንጃ ገንብቷል፤ ያልሰራው አማራ ነበር፡ ከድንፋታ ደንፊዎች ጋር እኩል ለመቀመጥ “መጀመሪያ” ደንፊዎችና ትምክሕተኞቹ የያዙትን መያዝ አለባችሁ። ገዳዮቹ ትላልቅ ዋርካዎችን ገዝግዘው ቆርጠው አገሪትዋ ባዶ ስላስቀርዋት ቁንጫዎቹ ገብተው ለበርካታ አማታት ጨፈረውባታል። አገሪቷ ሰው እንዳይኖርባት አደረጉ! አሁን ያንን መደግም የለበትም። እንደ ደንፊዎቹ ታጥቀህ ቅረብ። የ “Garbage in Garbage out” ፍልስፍና አያስፈልግም! ተሞክሮ የወደቀ ነው! ወንጀለኞችና ዘረኞች መጋፈጥ አማራጭ የሌለው አዲስ ስልት መሆን አለበት

በዚህ ዓለም ጉልበትና ገንዘብ ገዢዎችና አስከባሪዎች ናቸው። ከዚህ የዓለም ነባራዊ ሃቅ ብንሸሽም በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለዚያ ተገዢነታችን አይቀሬ ነው። የመጎንበስ ውጤት አይተነዋል። ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ አንደለው <<ፋሽስቶች ያሉትን ሁሉ በጭፍንነት የሚያደርጉ ሕግ የማያውቁ ናቸው!” እውነት ነው። ከዚያ ጥቃት ለመዳን መዘጋጀት ያስፈልጋል፡ “ሕግ ያልገዛው ነፃነት ሃይል ይገዛዋል” የሚባለውም ለዚህ ነው።

አበቃሁ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)