Friday, April 6, 2018

ኦሮሞዎች በቢላዋ አስገዳጅነት ኣብይን ወደ ሥልጣን አምጥተውታል ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ


ኦሮሞዎች በቢላዋ አስገዳጅነት ኣብይን ወደ ሥልጣን አምጥተውታል

ጌታቸው ረዳ
 ኢትዮ  ሰማይ (Ethiopian semay)
ይህ ርዕስ በልብ ወለድ የተጠቀሰ ርዕስ አይደለም። እውነት ነው። አባ ገዳ ‘በየነ ሰንበቶ’ የተባሉ የኦሮሞዎች የገዳ አመራር አባል ናቸው ይህንን በፋሺስቶቹ በነ በረከት ስሞን ፊት ባለፈው ሰሞን በተጠራው የሰላም ውይይት ጉባኤ ተገኝተው የተናገሩት ንግግር ነው። ኦሮሞዎች ዛሬም ገዳ በሚባል ፖለቲካውን ወደ መቆጣጠር ቀስ ብሎ እያደገ የመጣ የአረባዊ መልክ ህብር ያለው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቃላማን የተካ  ‘ጥቁር ነጭ እና ደማዊ (ቀይ)’ ቀለም ያለው የራሱ ሰንደቃላማ የፈጠረ የሽማግሌዎች ኮሚቲ አለ። ይህ ቀለም ኦሮሞዎች በሚለብሱት ልብሶች/ክራባታዎች እና በሚያውለበልቡት ባንዴራ በይፋ ይታያል።

የጥንቶቹ የኦሮሞዎች ገዳ የሚባል በወታደራዊ ስልት የተደራጀ፤ ተስፋፊና የሴቶችን እኩልነት የማይቀበል፤ ትዳር ለመያዝም ሆነ ሥልጣን ለመረከብ ሰው በመግደል ወይንም የወንድን ብልት በመስለብ በማሕበረሰቡ ፊት ማስመስከርን የሚጠይቅ እጅግ ጥንታዊ የሆነ የጥንት አደራጀጀት፤በዛው ዘመን ስም እና በዛው ዘመን ባህሪ የታወቀበትን ስም (ገዳ) በዛሬው ዘመን “ገዳ” የተባለው ስም  ይዞ ብቅ ብሎ ለምን እንደተደራጀ ግልጽ ባይሆንም፤ መሬት ላይ ያለው ሃቅ የሚያመለክተው ግን “አባ” (አባ ገዳ) ተብለው ሚጠሩ የዚህ ድርጅት ሽማግሌ አባሎች እውጭ አገር ሁሉ እየመጣ እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። የህ ድርጅት ወደ ውጭ ሲመጣ ሻዕብያዊው ተስፋየ ግበረአብን የኦሮሞ ዜግንት ከሰጡ አባገዳዎች ጋር ግንኙነት ያለው ይሁን አይሁን የታወቀ መረጃ ባይኖርም ከተለያዩ ኦሮሞ ማሕበረሰብ ጋር እንደሚገናኙ ግን ምንጮች አሉ።

ያም ሆነ ይህ ይህ የሽማግሌዎች ድርጅት ከኦሮሞ ፖለቲከኞች በበለጠ በማሕበረሰቡ ዘንድ ጉልበት የተቸረው ከጊዜ ወደጊዜ ፖለቲኸኞቹን በመወጠር ‘ቄሮ’ ተብሎ ከሚታወቀው ህቡዕ የኦሮሞ ወጣቶች አደራጀጀት የሚንቀሳቀሰው ጋር የጠበቀ መረዳዳት ያለው ይህ ማሕበር በወያኔዎች ካምፕ እና ባለሠልጣኖች ፍራቻ ለቅቆባቸዋል። ይህ የሽማግሌዎች ድርጅት ከተለዩ ሃይማኖት ተከታዮች የተወጣጣ አንዳንዶቹም ዘመናዊ ትምህርት ቀመስ የሚመስሉ ሽማግሌዎች ያሉበት ስለሆነ ፖለቲካው “በነገድ” የተደራጀ ቢሆንም ምን እየተደረገ እንዳለ ምን መናገር እንዳለባቸው፤ምን መጠየቅ እንዳለባቸው የሚያውቁ አባሎች ስላሉበት ከፖለቲከኞች በላይ በኦሮሞዎች በኩል “የሚደመጥ” በወያኔዎች በኩል ግን “የሚፈራ” የሕብረተሰቡ ድርጅት እየሆነ መጥቷል። ወያኔዎችንም እስከማስጠንቀቅ ድረስ የሚደርስ ጉልበት እያገኘ መጥቷል። ይህ ድርጅት በውስጡ ኦነጎች የመሳሰሉ አፍራሾች ሰርገው ገብተውበት ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ማሕበሩ ‘ሕብረተሰቡን የመጥራት የማሳደም ዝም የማሰኘት ጡንቻ’ እንዳለው ከሚናገሩት ንግግሮች መረዳት ይቻላል።
    
    ከላይ የጠቀስኩት የሰላም ጉባኤ ብሎ ወያኔ የጠራው ስብሰባ ላይ እኝህ የተጠቀሱ የገዳ አመራር አባል የሚከተሉት ብለው ነበር

    “መንግሥት ማለት እኮ እኛ ነን። ወደላይ የወጡት እኮ የኛ ልጆች ናቸው።….አንድ ነገር ልንገራችሁ፡ ሰሞኑን የተደረገቺው የጠቅላይ ሚኒሰትር ሽግግር የኛ ልጅ ባይሆን ኖሮ (ወንበሩን ባይሰጠው ኖሮ) ሃቁን ልንገራችሁ ማንም ይስማው! ይህች አገር ጉድ ትሆን ነበር፡ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው። ሁሉም ቢላውን አስልቶ ቁጭ ብሏል፡ (ሲጠባበቅ ነበር) እሰኪ እናያለን! ሲል ነበር (አብይ ካልመረጡት ጉድ ይፈላል ሲል ነበር) ግን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ይጠብቃታል፤ ያው ነብሳችን ተመለሰች (ሰላም ሆነ አብይ በመመረጡ ኡፈይ ኣልን)።ያ ነገር ባይሆን ኖሮ (አብይ ባትምርጡት ኖሮ) ጉድ ይፈላ ነበር። እስካሁን ድረስ መቶ ሺ ኮማንድ ፓስት ለ100 ሚሊዮን ሕዝብ ከገጠመው ሊመልሰው ይችላል? አይመልሰውም! መንግሥት ከአባገዳዎች ጋር መስራት አለበት። የምነሰማችሁ የሃይማኖት አባቶች ብቻ ስትሉ እንሰማለን፤ አንድ ቀን የአገር ሽማግሌዎች ስትሉ አንሰማም። አባ ገዳ ሁሉም ሃይማኖት ያቀፈ ነው…

    በማለት አቶ በየነ ሰንበቶ የተናገሩትን ስናጤነው፤ ይህ አካል የኦሮሞን ሕዘብ ማንቀሳቀስ ማሳደም    ማስታገስ ማስነሳት ማስተባበር የሚችል አቅም አንዳለው ከተናገሩት ንግግር መረዳት ይቻላል። አብይ ባትመርጡት ኖሮ “ኦሮሞዎች በየቤታቸው ቢላዋ ስለው ሲጠባበቁዋችሁ ነበር” ብሎ ሳይፈራ “በወያኔ /የጎስታፖ/ አራዊቶቹ ፊት ለፊት ደፍሮ” የሚናገር ሰው ፈጽሞ የማየታለም ነገር ነበር። ይህ ድርጅት በጣም ሃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ የወያኔ አራዊቶች ይህንን የአቶ በየነ ንግግር በግል የተናገሩት ቢሆን ኖሮ ከአዳራሹ ከመውጣታቸው በፊት በጐስታፖ ነብሰገዳይ ደህንነቶቹ አስጐትተው ወደ ጭለማ ነበር ገፍትረው ለግርፋት ይዳረጉ ነበር። ሆኖም ወያኔዎች የዚህ ማሕበር ሃያልነትና ተሰሚነት ከፍተኛ ስለሆነ ሰውየን መነካካካት የወያኔ የሥልጣን ዘመን ማክተሚያ ምክንያት እንደሚሆን ስለሚያውቁ ያችን ንግግርና ማስጠንቀቂያ ውጠው ከውሰጥ መንፈሳቸው ተረብሾና ደንግጦ እነ በረከት ስምኦን እና ያ “ማሞ ቂሉ” ፕረዚዳንት ከበረከት ጎን አጠገብ ቁጭ ብሎ በአግራሞት እጆቻቸውን አጣጥፈው ሳይወዱ ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ሆነው ዝም አሉ።
  
እንግዲህ ወደዱም ሳይወዱም ኣብይ ተምርጧል። አብይ በኦሮሞዎች ቢላዋ አስገዳጅነት ወደ ሥልጣን አምጥቷል ሲባል በምርጫው ወቅት ሳይሆን ወደ ጠ/ሚኒሰትርነት ለውጥ ድረስ ሊመጣ የተቻለበት ምክንያት የኦሮሞዎቹ (ቄሮ) እና አማራዎች ያልተጠበቀ የጋራ አድማ መሆኑ ማየት አለብን። ያቺ ‘አቶ በየነ ሰንበቶ’ የተናገርዋት “የቢላዋ” ንግግር ግን አብይ ከተመረጠ በላ ያለው አንደምታ (ቶን/መልዕክት) ነች ዋናዋ መልዕክታቸው። ሥልጣን ከወጣ በላም ቢሆን በልጃችን ኣብይ ላይ ተጽእኖ እናመጣበታለን የምትሉ ከሆነ “ያቺ የተሳለች ቢላዋ” ከሞፎድፎድያዋ (ከአፎትዋ) እናወጣት እና ጉድ ይፈላል! የሚል ነው ዋናው እኛ ማየት ያለብን መልዕክት።  
     
     ለዚህ ደግሞ ምክንያቴን ላቅርብ። ኦሮሞዎች ለምን ጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን እንደፈለጉት ካአለ እነሱ በቀር የሚያውቅ ባይኖርም፤ እዛ ቦታ ላይ የደረሰ ኦሮሞ ስርዓቱን ለመጋፈጥ ይችላል በሚል ቀመር (ስልት) ከሆነ እና ያ ስልት ደግሞ (እውነት አብይ  መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት ዓላማ ሰንቆ ከሆነ) እሱን  የሚጫኑት እና አላሰራም የሚሉት ‘የወያኔ አራዊቶች’ ከገጠሙት የኦሮሞና አማራ ሕዝብ ጠርቶ ‘ሰበብ’ ተደርጎ ሥርዓቱን በሕዝባዊ አመጽ “ለማናጋት” ከሆነ ጥሩ ስልት ነው። በጣም ጥሩ ስልት። ችግሩ ግን፤ በሁለቱም በኩል ያለው ማለትም ልጃችን (ልጆቻችን) በሚሉት እና በሚሏቸው ኦሮሞዎች እና በገዳ መካከል (ሕዝቡ) አንድ አይነት ፍላጎት ፤ግብ፤ስልት ተከትለው እዚህ ድረስ መምጣታቸውን እንዴት ማወቅ አንችላለን ነው። ማለትም አብይ የያዘውን ስልጣን ረክቶ በሰርዓቱ መዘውር ላይ እየተሽከረከረ እዚህም እዛም የሚታዩ ለውጦች በማምጣት ረክቶ ዝም የሚል ከሆነ፤- አባገዳዎቹስ (ቄሮዎቹ) አብረው ከሱ ጋር እዚህም እዛም በሚነካካቸው ቁልፎች ረክተው ፤ልጃችን ስለሆነ ‘መጋፈጡ’ አያስፈልገንም ብለው አብረው ዝም ማለቱ ይመርጣሉ? ወይስ እዛ ድረስ የገፉንህ እና የተጠቀምንበት ሰልት ሥር-ነቀል ለማማጣት ነው እና ቄሮዎችን አንቀሳቀስን ላንዳፍታ ‘ጋብ’ ብሎ የነበረው ሕዝባዊ ማዕበል አስነስተን አንተንም ስርዓትህንም እናስወግዳለን? የሚል ይሆናል? ነው ዋናው ጥያቄ።
 
    የኔ እያታ ይህንን ይመስላል። ኦሮሞዎችና ትግሬዎች በነገድ ሰክረዋል። ለ27 አመት ሲያጨሱት የነበረው፡የጎሰኛነት ሱሰኛ ጭስ ደግሞ የጎሳ ፖለቲካ ነው። ከልጅ እስከ አዋቂ ድረስ ይህንን ሲጋት የነበረ ማሕበረሰብ የራሱን ልጅ ሥልጣን ማማ ላይ ሲወጣ እሱ የሚመራውን ሰርዓት ለማናወጥ ፍላጎታቸው ምን ያህል ይጓዛል የሚለው ጥያቄ ጭሮብኛል።
  
   ሌላው ጥያቄ-፤ ምናልባትም የኛ ልጅ የሚሉት አብይ ለመረበሽ ባይፈልጉም፤ ወደ ብጥብጡ እንዲገቡ የሚያስገድዳቸው ክስተት ብቅ ሊል ይችላል። ይኼውም ወያኔዎች በግልጽ የአብይ መመረጥ አልወደዱትም። ለዚህም እሱን ለመጥለፍ በሚተንጉት ሴራ እየተጠለፈ መቸገሩን ሲያዩትና እሱ ግን ሕዝቡ እንዳይሰማ ወይንም “ሰላም” ለማምጣት በሚል “በአጉል ተግደርዳይነት” እየተጓዘ ካዩት አብይን ወደ ኦሮሚአቸው በመጥራት “ታውን ሆል ሚቲንግ” የሚሉትን ጉባኤ ጠርተው እየተካሄደ ያለው ሽፍንፍን ግልጽ እንዲአደርግላቸው ይጥሩታል። እዚህ ላይ መርሳት የሌለብን መካከለኝ ተጫዋጭ የሚሆነው “ለማ መገርሳን” አትርሱ። ለማ በሁለት ምድጃ የሚንቦገቦገው እሳት ይለበለባል። ከላይ እና ከሕዝቡ።
  
    በሕዝብ (በቄሮ) በኩል የሚቀርቡ በአብይ ላይ ያሉዋቸው ቅሬታዎችን ለማለዘብ ለማ ከፍተኛ ችግር ይገጥመዋል። ለምን? እሱ እመሃል ያለ ሰው ነው። የሕቡን ድምፅ ማድመጥ አለበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሚወደው የትግል ጓዱን መጋፈጥ ሊሆንለት አይችልም (የሰው ልጅ ኢንስቲነክት የሚነገርን ያ ነው)። ሰለዚህ ቅርቃር ውስጥ ይገባል። ሆኖም አብይ ወደ ኦሮሚያ መጥቶ አላሰራም አሉን ብሎ ቅሬታውን ለሕዝብ ካስተላለፈ የእርሱ ወኪል የሆነው ለማ መገርሳ ‘ሕዝቡን በማስተባባር’ ወያኔ ኦሮሚያ በሚባለው አካባቢ ላይ ሥርዓቱን መዘርጋት እንደማይችል “የሰዶም ገሞራ አሲድ” በስርዓቱ ላይ ሊያፈስሱበት ይችላሉ።
  
    እዚህ ላይ መጥፎ ክስተት ሊከሰት ይችላል። ሥርዓቱ እንደለመደው ወደ ጠምንጃ ዞሮ “ወታደራዊ አዋጅ” አውጆ ግድያ ውስጥ ይገባል። አብይንም ለማንም ልሰር ይላል። ያ ወያኔ መቃበር ያፋጥነዋል። እንዲህ ሲሆን በስርዓቱ ውስጥ ያሉ ኦሮሞ ወታደሮች ከኦሮሞ ክልል ጋር ካሉ ኦሮሞ ወታደሮች “ግምባር በመፍጠር” በትግሬዎቹ ስርዓት ላይ “ወታደራዊ ግጭት” በመቀስቀስ አገሪቱ ወደ ብረት ፍልሚያ ትገባለች (“ኢትዮፓትርዮሰትስ ራዲዮ ሁለት ወር በፊት የሰጠሁት ቃለ መጠይቅን አስታውሱ)። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን፤ ኦሮሞዎች ሲነሱ አማራዎችም ፍልሚያው ላይ ይገባሉ። የሶማሌው ክልል ሓላፊ ‘ጸረ አማራው’ አብዲ ትግሬዎችን በመደገፍ ኦጋዴን ሶማሌ አካባቢ የሚኖሩ በሰላማዊ የኦሮሞና የአማራ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ፍጅት ሊያመጣ ይችላል። ሰውየው “የአልሸባብ አይነት ሕሊና የተቃኘ አክራሪ ነው”። ይህ ደግሞ በግልጽ በወያኔ ትግሬዎች እና በሶማሌው ላይ የታየው የመደጋገፍና የመተዛዘን ግንኙነት እንዲሁም “አብዲ” በራሱ ደምጽ የተቀዳ የሶማሌ ሽማግሌዎችን ሰብስቦ የተናገረው ማሕደር ማስታወስ አስፈላጊ ነው።
    
    “ለትግሬዎች ያለው ፍቅር  ገልጾ፤  ሶማሌዎች ግን አማራዎችን በጠላትነት ማየት እንዳለባቸው” የተነጋረውን ስናስታውስ፤ ወያኔዎች እና ሶማሌዎች ወግነው በአማረውና በኦሮሞ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ክፉ ትዕይንት ሊያመጡ ይችሉ ይሆናል (ከጅማ በበለጠ አክራሪ እስላም በብዛት የተከማቸበት አካባቢ ነውና)። እንዲህ ሲከሰት ሶማሌም ትግሬውም የመነጠል አባዜአቸውን በመምዘዝ ሕዝባዊ እምቢተኛነቱን ለማስቆም ጥረው እምቢ ሲላቸው “ያችን የመገንጠል ካርዳቸውን” ማውለብለብ ሊጀምሩ ይችላሉ።

    እንዲህ ሲሆን ‘ሻዕቢያ’ ያችን እሳት እንድትቀጣጠል እና ባድሜን መልሶ ለመውሰድ አመች ስለሚሆንለት ሌላ ተጨማሪ የብጥብጡ ሃይል በመሆን በወታደራዊ ግጭቱ ውስጥ ጀሌዎቹንም ሳይቀር በማስገባት (ኦነግ..ግ7፤ድምህት፤ኦብነግ ….) መካፈሉ አይቀርም። ባድሜ መቸ እንደምንወስዳት ባራሳችን ሰልት እና ጊዜ አስለትን መውሰዳችን አይቀርም ሲሉ ሁሉቱም ኢሳአስና ኤፍሬም ስብሓት ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ወደ አማርኛ ተርጉሜ በራሴው ብሎግ ከአመታት በፊት እንደለጠፍኩት ታስታውሳላችሁ።
   
    ወደ ኦሮሞዎቹ ስንመለስ፤-እዚህ ላይ ገዳዎቹ በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ እምነት እንደሌላቸው እና ግብጻዊ እና አረባዊ የሆነ ቀለም ያለው የራሳቸው ባንደሬ ፈጥረው እንደሚያውለበልቡ ሁሉ ብጥብጥ ሲነሳ አገር እናድን ብለው እስከመጨረሻ ድረስ ስለ ኢትኦጵያዊነት ይቆማሉ ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲቀርብ 50/50 የሚል መልስ እሰጣለሁ። በዚህ ዝቅተኛ ደረጃ የመደብኩዋቸው ምክንያት፤ “ቄሮ’ የተባለው ኦረሞአዊ ወጣት ኢትዮጵያ ምትባል አገር እንዳያውቃት ሆን ተብሎ በወየኔዎችና በኦነጎች የተሰለበ ነው። ስለሆነም የነ ለማ እና የነ አብይ አዲስ ‘ኢትኦጵያዊ’ ቅኝት ይህንን በኦሮሚያነት እና በአመርኛ እና አማራ ጥላቻ አሳድሮ “አኖሌ ሃውልትን ያቆመ” የተሰለበ ወጣት እና ሽማግሌ (እርግጥ በውስጣቸው ጥሩ ሽማግሌዎች ሊኖርዋቸው ይችላሉ- ስለ ኢትዮጵያዊነታቸው የሚሰማቸው) ወደ መሃል ጎትተው የማስገባት ያላቸው አቅም ምን ያህል ነው? የሚለው ጥያቄ ከባዱ ጥያቄ ነው። እነሱ የሚተረጉመት “ኦሮሚያ ፌደራሊዝም” (3/4ኛው በሕገ ወጥ በጠመንጃ ከወያኔ ጋር ሆነው የነጠቁትና የከለሉት የኛ ነው ያሉትን የይዞታ መሬት) ካልተሳካላቸው ‘አገር’ ማፍረስን እንደ ምርጫ ሊከተሉት ይችላሉ ወይ? የሚለው ጥሩ አነጋጋሪ ነው።

    በዚህ ነፈሰ በዛ፤ ወያኔ በለመደበት ሰይጣናዊ ባህል አብይን የሚያስችግሩ ወጥመዶች ካጠመዱበት እና አብይም ይህንን ሴራ ለማጋለጥ እና ለመቋቋም ሽንጡን ገትሮ (ምናልባት “ኢፍ” ምናልባት እንበልና) ከተነሳ ኦሮሞዎችንም ይህንን የሴራ ጉንጎና በየጊዜው ወደ ሕዝቡ እየወረደ ካሳወቃቸው፦ ሲያሳውቃቸውም ግልጽ እና የማያወላዳ መረጃ መግቦ በለማ መገርሳ በኩልም ቢሆን ሕዝቡ የወያኔ አመኬላ ሴራ እንዲሰብር ጥሪ ካደረገ፡ አብይ ሲመረጥ ሰሞን በአቶ በየነ ሰንበቶ ልሳን የተነገረችንን ያቺን በየቤቱ ተስላ ስትጠባባቅ የነበረቺው የአልገዛም ቢላዋ ከአፎትዋ መውጣትዋ አይቀሬ ነው። ከኔ በተለየ የሚተነትኑት ተንታኞች እንደሚሉት አሁን ኳስዋ ያለቺው ‘በአብይ ስር ነች”  እንደሚሉት ሳይሆን፤እኔ የምለው ‘ኳስዋ አሁን ያለቺው በአብይ እግር እና በገዳ ሽማግሌ ቄሮዎች እግር ነች”።ሁለቱም ተስማምተው በወያኔ በር ጠባቂዎች ላይ ግብ ያስገባሉ ወይስ ሁለቱም ጋርም ንትርክ ተከስቶ የወያኔ በር ጠባቂዎች መከላከላቸውን ትተው ወደ መሃል ገብተው ሁለቱንም ማኖ አስነክተው ኳስዋን ለመቆጣጠር ይችላሉ? ከሆነስ አስከ መቸ? የአማረዎች ሚና እዚህ ያልተነተንኩበት ምክንያት ርዕሱ ኦሮሞዎች የሚመለከት ስለሆነ ነው። አማራወስ የፖለቲካ ተቃዋሚውስ አለው ድርሻ እና አደረጃጀት፤ ሕዝብን የማስከተል ብቃት፤ከብበውን ያሉት የውጭ ሃይላትንስ፤ የሚለው በሚቀጥለው እንመለስበታለን።-
   አመሰግናለሁ።
  ጌታቸው ረዳ ( ኢትዮ- ሰማይ)