የቀጨኔ ሕዝብ ‘አይሁድ’ ለማድረግ እየተደረገ
ያለው ሴራ
ጌታቸው ረዳ
(ለኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ የተላከ ደብዳቤ)
Cross symbol is for Orthodox christian religion flowers in Ethiopia. It is not race/ethnic symbol |
ባለጅ
Note from the Editor –Ethiopian
Semay-
This document is sent to to Ethiopian Semay blogger. This document shows how another new agenda of the Zionists in Ethiopia is at work to destroy Ethiopia against the Kechene Amhara Community inside Shewa locality with the collaboration of the Tigrayan thug rulers. The burrow/hole made by the Wild Village Rats (Weyane) in the holy land garden of Ethiopia are everywhere and needs to close ASAP; or else Ethiopia will be the home for all kinds of foreign burrows (if not already). This is another Felasha fabrication another round of enslaving Ethiopians; what the renowned an Ethiopian historian Professor Aleme Eshete calls it “the modern slave trade”. Read the Amharic version for more detail sent by a friend of the Ethiopian Semay editor.
ባለጅ
ለዚህ ጽሁፌ ያነሳሳኝ ከECADF ድህረ ገጽ ተወስዶ ፌስቡክ ላይ ተለጥፎ ባየሁት ታሪክ ላይ ተመርኩዤ ነው።http://ecadforum.com/2015/08/16/the-secret-jews-of-ethiopia/ ታሪኩ የተጻፈው መቼ እንደሆን ባላውቀውም ጀሩሳሌም ፖስት ላይ የተገኘ ነው።ጸሃፊዋም ከራሺያ የመጣች አይሁድ ነኝ ባይ አይሪን ኦርሊንስኪ ነች።ይቺ ሴት የቀጨኔ ህዝብ አይሁድ ነው ብላ የተወሰኑ ወጣቶችን በጥቅማጥቅም በማማለል አብራቸው ባለጅ የሚል ዶክመንታሪ ፊልምም እየሰራች መሆኑን ሰምቼ ክሊፑን ዩቲዩብ ገብቼ አይቸዋለሁ።አንባቢዎችም ባለጅ ብላችሁ ጉግል ብታረጉ ታገኙታላችሁ።ለማንኛውም እኔ ከዚሁ ከጠንካራውና ካልበገሬው የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ሆኖ ከኖረው ጀግና ህዝብ ከባለጅ (ከባለእጅ) አማራ የተወለድኩ ልጅ ነኝ።ማንም እንደሚያውቀው ይህ ህዝብ በሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ጋራ ስር ቀጨኔ መድሃኒአለም ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ነው።አናኗሩም በአብዛኛው ከእደጥበባት ማለትም ከሽመና፤ከብረታብረቶች እና ሸክላ ስራ ውጤቶችን ለሌው ህብረተሰብ በመሸጥና በመለወጥ እንዲሁም በንግድና የታክሲ ስራ ግልጋሎት በመስጠት ነው።
ለዘመናት ይህ ህብረተሰብ ማረሻውን፤ዶማውን ሰርቶ ገበሬው አርሶ እንዲያበላ የረዳን፤ጎራዴና ጦሩን ሰርቶ ሃገራች እንዳትደፈር ያደረገ፤ሸማውን ሰርቶ ገበናን የሸፈነ፤ሸክላውን ሰርቶ ህዝብ አብስሎ እንዲበላ ሲያደርግ የኖረ፤የቤተክርስቲያን ጉልላቱን፤ጽናጽኑን፤ከበሮውን፤መስቀሉን፤መቋሚያውን፤ብራናውን እየሰራ ቅድስት ቤተክርስቲያን ደምቃና አምራ እንድትኖር ያደረገ፤አረንጓዴ፤ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ አላማችንን ለመጀመሪያ ጊዛ ለጀግናው ቴዎድሮስ አሳምሮ ሸምኖ የሰጠ፤ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህልውና መሰረት የሆነን ህዝብ ውለታው ተክዶ፤ባለጅ፤ቀጥቃጭ፤አንጥረኛ፤ፋቂ፤ሸክላ ሰሪ ቡዳ እየተባለ ሲብጠለጠል ቢኖርም ይህ ልበሙሉና ኩሩ ህዝብ በነዚህ ተራና ኋላ ቀር ተልካሻ ወሬዎች ሳይበገር የማንንም የመንግስትንም ጭምር እርዳታ ሳይፈልግ በራሱ ጭሮ አዳሪ ህዝብ ነው።
ይህ ህዝብ አሳፋሪ በሆነ መንገድ መቼና ለምን ስም ተለጠፈበት ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ አቶ አብራሃም አለሙ የሚባሉ ወያኔ ከስራቸው ያባረራቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ዲፓርትመንት ዲን የነበሩ ወንድማችንን ኢንተርቪው በአቶ ደረጀ ደስታ በኢሳት ቴሌቪዥን ያገር ልጅ በሚለው ዝግጅቱ ላይ ፌብሩዋሪ 21/2012 አቅርቧቸው በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ ስለኦሮሞ ህዝብ አመጣጥና ባህልም ሲተርኩ ባንድ ወቅት በሸዋ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቦታ ጠቧቸው ግቤ ወንዝን ተሻግረው መካ ወሬ በምትባል ሴት እየተመሩ ጅማ ላይ ይኖሩ ስለነበሩ ኦሮሞዎች ታሪክ ሲናገሩ ወንዶቹ በዚች መሪያቸው ቅናት አድሮባቸው እንዴት በሴት እንገዛለን በማለት ሴራ ጠንስሰው ከስልጣኗ እንዳወረዷትና በኦሮሞ ዘንድ ሁለተኛ ሴት ልጅ መሪ እንዳትሆን በተሸረበበትና ስልጣኗን በተነጠቀችበት ወቅት በተጨማሪ አፈሩን አቅልጦ ብረት አውጥቶ ቀጥቅጦ፤ጦር ጎራዴ እየሰራ ለገዢው መደብ የስልጣን ምንጭ የሆነውም ባለጅም ቀጥቃጭ በኦሮምኛ ቱምቱ የሚል ስም ታርጋ ተለጥፎበት በህብረተሰብም ዘንድ የተናቀ እንዲሆን ዘመቻ ተከፈተበት ይላሉ እኝህ ምሁር።ለማንኛውም የኚህ ታላቅ ምሁርን ትረካ ዩቲዩብ ግቡና እዩት ሙሉ ታሪኩን
https://www.youtube.com/watch?v=U0L1r1pXQ7s
ስለ ስም ልጠፋው ይህን ካልኩ እምነቱ ደግሞ አይሪን እንዳለችው አይሁድ ሳይሆን ጥርት ያለ ኦርቶዶክስ ነው።ቅልቅልም የለውም።ምንም እንኳን መነኮሳቱ በድብቅ የሚያመልኩት ቢኖርም።ሌላው እሷ ልትጠቅሰው ያልፈለገችው ነገር በቀጨኔ ህዝብ ትልቁ ክብር ወይም በአል ገናና ፋሲካ ናቸው።ገና ጌታችን ኢይሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሲሆን፤ፋሲካ ወይም
ትንሳኤ ደግሞ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ስለሆነ እንደዋነኛ የክርስቲያን መገለጫዎች ስለሚያያቸው ነው።
የአይሁድ እምነት መለያ የሆነው ኮከቡን በሰሜን ሸዋ አካባቢም ሆነ ቀጨኔ ውስጥ ዞራ በፈለገችባቸው የተለያዩ ገዳማት ሁሉ አንድም ቦታ እንዳላየች ራሷ ገልጻለች።ታዲያ የክርስቲያን መለያው መስቀሉ ከሆነ የአይሁድ እምነት መገለጫ ኮኮቡ አይደለም እንዴ?አንድ ህብረተሰብ ምንም መሃይምና ኋላ ቀር ቢሆን ለዘመናት በኖረበት አካባቢ ታሪኩንና እምነቱን በድንጋይም ሆነ በእንጨት ላይ በስእልም ሆነ በተለያዩ ቅርጻ ቅርጽ መልክ የማንነቱን ማገለጫ አሻራ ይተዋል በድብቅም ቢሆን።ይህ ህዝብ በኖረባቸው አካባቢ ኮኮብ የሚባል ቅርጽም ሆነ ምስል አንድም ቦታ አይገኝም።መስቀሉን ግን የባለጅ ሴቶች ግንባራቸውና ደረታቸው ላይ ይነቀሱት ነበር።ተገድውም አይደለም ወደውትና ኮርተውበት ሊያጌጡበት እንጂ። በድብቅ የሚመለከው ነገር ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙ መላ ምት መስጠት ይቻላል።
በአጼ ሱሲኒዮስ ዘመነ መንግስት የሮማ ካቶሊኮች ንጉሱን አሳስተው ካኮተለኳቸው በኋላ ህዝቡ ሲሰማ ከፍተኛ ቁጣ በማስነሳቱ አጼ ፋሲል በምትኩ ነግሰው ካቶሊኮቹ ካገር በተባረሩ ጊዜ እሳት ጭረው ነበር የወጡት።እሱም ምንድን ነው፤ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መነኮሳት ማለትም አንዱን ከጎንደር ሌላኛውን ከጎጃም ሁለቱንም በድብቅ በተለያዬ መንገድ የካቶሊክ እምነታቸውን ስብከዋቸው ካገር ከወጡ በኋላ አንደኛ ቅባት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ጸጋ የሚል ከኦርቶዶክስ የተለዬ እምነት ይዘው በመውጣታቸውና ተከታዮችም በማፍራታቸው ነገሩ ስር ሰዶ በሃገራችን ክርስቲያኑን ሲያስተላልቀው ኖሮ ኋላ ግን በአጼ ዮሃኒስ አማካኝነት ሶስቱም እምነቶች ማለትም የኦርቶዶክስ፤የቅባት እና የጸጋ አማኝ አባቶችን ቦሩ በሚባል ቦታ ላይ ሰብስበውና አከራክረው ከሶስቱ አሸናፊ ሆኖ የወጣው የኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት ይሆናል ብለው ባሳሰቡት መሰረት እነዚያ አባቶች በዚያን ዘመን ፍትህ በተሞላበት መንገድ ተከራክረው ኦርቶዶክስ ባሸናፊነት ወጥታ የኢትዮጵያ የክርስቲያን ሃይማኖት ሆናለች።ይህ ማለት ግን ቅባትና ጸጋ የሚባሉት እምነቶች ባንድ ቀን ተነው ጠፍተዋል ማለት አልነበረም።በርግጠኝነት መናገር ባልችልም ከቅባትና ጸጋ አንደኛውን ሊሆን ይችላል በድብቅ ዘመዶቼ ያውም በሽማግሌና አሮጊት መነኮሳት ብቻ ወጣትና ጎልማሳውን ሳይጨምር።ህጻናታም እንደተወለዱ እንደማንኛውም ኦርቶዶክስ ወንዱ በአርባ፡ሴቷም በሰማኒያ ቀኗ ይጠመቃሉ፤ለአቅመ አዳምም ሲደርሱ ቆርበው በአክሊል ይጋባሉ።በልጅነታችን እንደማንኛውም ኦርቶዶክስ የፍልሰታን ውይም በዘልማድ አነጋገር የልጅ ጾምን እየጾምን ቁርባኑን ስንቆርብ ኖረን አድገናል፤አሁንም እየሆነ ያለው ይኸው ነው።ይህንንም ያልኩበት ምክንያት ዱሮ የገና በአል ሮብ ወይም አርብ ላይ ሲውል የኔ ዘመዶች ስጋ ብሉ ሲባሉ፤አንበላም በሚል ከቄሶች ጋር ጭቅጭቅ እንደነበር አስታውሳለሁ ያሁኑን ባላውቅም።
ሌላው መላምት አይሪን የባለጅ መነኮሳት የሂብሩ ጽሁፍ ሲያነቡ አይቻለሁ ስላለች(ማየቷን እንኳን በጣም እጠራጠራለሁ)ብሉይን ያጠብቁ ይሆናል።ይህንን ያልኩበት ምክንያት ስለትኩቶ አንስታለች።ትኩቶ ማለት በቀጨኔ አካባቢ አንድ ሴት የወር አበባዋ ሲመጣ ከመኖሪያ ቤቷ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ፈንጠር ብላ የተሰራች ትንሽ ጎጆ ውስጥ ከቤተሰቦቿ ተለይታ እስክትጠራ ድረስ ማለትም ለሰባት ቀን እዚያች ትንሽ ጎጆ ውስጥ ትቆያለች።በሰባተኛ ቀን ውሃ ተፈልቶላት ታጥባ ልብሷንም ቀይራ ከቤተሰቧ ጋር ትቀላቀላለች።አይሪን እንዳለችው ለመታጥጠብ ወደ ወንዝ አትሄድም እንደ አይሁዶች።ይህ ህግ በብሉይና በአይሁድም ህግ ውስጥ ያለ ይመስለኛል።ሆኖም ግን አሁን በቀጨኔም ሆነ በዘመናዊው አይሁድ ህዝብ ዘንድ የቀረ ይመስለኛል።
ይች አገር ሰው አልባ ሆናና በሯ ተበርግዶ እንደ አይሪን አይነቶቹ መፈንጫ ሆና አርቲ ቡርቲ ታሪክ እየተሰራ ልጆቿን ስትነጠቅ መኖሯ በጣም የሚያሳዝን የሚያምም ነገር ነው።በምን ስሌት ነው የቀጨኔ ህዝብ አይሁድ ሊሆን የሚችለው?በሳይንሱም ሆነ በስነፍጥረት ህግ መመዘኛውን አያሟላም።የአይሁድ ሃይማኖት እንኳ አምላኪ ነው ብለን ብንቀበል እንዴት ነው እስራኤላዊ ሊሆን የሚችለው?ይቅርታ አድርጉልኝና ፈላሻም የአይሁድ ሃይማኖት አምላኪ እንጂ እስራኤላዊ አይደለም ለኔ።በሌላ አነጋገር እኮ የእስልምና ሃይማኖት የሚያመልኩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን አረቦች ናቸው እንደማለት ነው።ይቺ ሰው የቀጨኔን ህዝብ በደልና ችግርም ልትነግረን ሞክራለች።በጣም የገረመኝና ያስደነገጠኝ ነገር፤”የቀጨኔ ህዝብ ያመረተውን ምርት እንኳ ገበያ ወጥቶ ራሱ መሸጥ አይችልም፤በወኪሎች ነው የሚያሸጠው”ብላ ለአለም ህዝብ በድፍረት ስትናገር፤ራሴን የጠየቅሁት ጥያቄ ይቺ ሰው ስለኔ ወገን ነው የምታወራው ወይስ ስለሌላ?ብዬ ራሴን ጠየቅሁ።መቼም ከመሬት ተነስታ ይህን ማለት እንደማትችል አምናለሁ።ሊሆን የሚችለው የሴትየዋ ጥረት ከተሳካ ወደ እስራኤል አገር እንሄዳለን ብለው የቋመጡ አድር ባዮች አጋነው ተናግረው እርሷንም እንዲህ ያለ ቅጥ ያጣ ሃሰተኛ ግንዛቤ ያስጨበጧት ይመስለኛል።ይህ ክህደት ደግሞ በሰማይም ሆነ በምድር ዋጋ ያስከፍላል።የተካደው ሃይማኖትና ቅድስት ሃገር ስለሆኑ።ሰው ከልጅነት እስከ እውቀት ቁርባን እየቆረበ ስጋወደሙ የተቀበለበትን ሃይማኖት፤አፈሯ ያፈራውን እህልና ውሃ በልቶ ጠጥቶ እየፈነጨ ያደገባትን መሬት እንዴት ይክዳል?አይደለም የራሳችንን ምርት ቀርቶ የሌላውንም ምርት በመግዛትና በመሸጥ የንግዱን ዘርፍ ማጋነን አይሁንብኝና ካጋነንኩም የሰፈሬ ልጆች አርሙኝ መርካቶን ከጉራጌዎች ያውም ካልበለጥን፤ባለመተናነስ የምንቆጣጠረው የቀጨኔ ሰዎች ነበርን ያሁኑን አላውቅም።ለምሳሌም ያክል።በኃይለስላሴ ዘመን ሁለት የታወቁ ቡና አስመጪና ላኪዎች ነበሩ።አንዱ ሻፊ አበጋዝ ሲሆን ሌላኛው በለጠ ሺበሺ የባለጁ ወይም የቀጨኔው ተወላጅ ነበር።መርካቶ አደሬ ሰፈር ይገኝ የነበረውም ቡና በረንዳን ባብዛኛው ይቆጣጠሩት የነበሩት የኔው ዘመዶች ነበሩ።ብዙ ማለት ይቻላል።በትምርቱም ዘርፍ ብዙ ምሁራንን አፍርታ ለሃገር ያበረከተች መንደር ነች ቀጨኔ።በድርግ መንግስት ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገለውም ሻንበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ የዚያው መንደር ተወላጅ ነው።በቅርቡም ወያኔ አማራን ከማደህየቱ ከማሳነስ አጀንዳ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ወህኒ የተወረወረው የkkk ኩባንያ ባለቤት የነበረው ባለሃብት ከተማ ከበደም ቀጨኔ ያፈራችው ልጅ ነው።ስንቱን ዘርዝሮ ይቻላል እንጂ ብዙ ባልኩ ነበር።የቀጨኔ ህዝብ ከማንም ባላነሰ በዛች አገር ተጠቃሚ ነበር በሁሉም ዘርፍ ከተራ ስድቡ በስተቀር።ስድቡም ቢሆን ህዝቡ የበለጠ እየተዋወቀ ሲመጣ በተለይም በደርግ ጊዜ የከሰመ ጉዳይ ነበር አሁን ለምን ማጠብረር እንደተፈለገ ባላውቅም።ድግሞም ኋላ ቀርነት የጣለብን ጉዳይ እንጂ የተለየን ፍጡር ሆነን አይደለ።ለነገሩ ይህ መናናቅና ስም መለጣጠፉ የአማራው ሲሆን ይጋነናል እንጂ ትግሬውም፤ኦሮሞውም የአንዱ አካባቢ ሌላኛውን ይንቀዋል፤ስምም ያወጣለታል።ይህ ጉዳይ እስከ አሁን ድረስ በሰለጠነውም አለም አለ።እንግሊዙ አይሪሹን ይንቀዋል።
እስራኤላውያን ፈላሻዎችንም ሲነጥቁን ይህንኑ ነበር ያሉን።ጥያቄው ግን ፈላሻዎቹ አሁን በእስራኤል ውስጥ ደልቷቸዋል ወይ? ነው ጥያቄው።የምንሰማው የሚያመክን መርፌ እየተወጉና የተለያዬ አይነት ዘረኝነት እየተፈጸመባቸውና እየተበደሉ እንደሆነ ነው።ታዲያ አይሪን አጠገቧ ላሉ ፈላሾች መፍትሄ ለምን አታፈላልግም መጀመሪያ ሌላውን ለተመሳሳይ ችግር ለመዳረግ ላይ ታች ከምትል?
የቀጨኔ ህዝብ ከደንብያም ይምጣ ከደጀን በሰሜን ሸዋ በመርሃቤቴ፤ሞረትና ጅሩ ወረዳ ውስጥ በብዛት የሚገኝ ህዝብ ነበር።አጼ ሚኒሊክ አዲስ አበባ ላይ አንዲሰፍር እስካደረጉት ድረስ።ሚኒሊክም ይህን ያደረጉበት ምክንያት የማይካደው ነገር ሴትዬዋ እንዳለችው ሌሎች ያገሉት ስለነበር “ይህን ወርቃማ ህዝብ ጦሩን፤ጎራዴውንና ጋሻውን ሰርቶ እሱም አብሮን ተዋግቶ ሃገሬን ያስከበረ ህዝብ እየሰደባችሁ እውቀቱን ገላችሁ በጅብ ልታስበሉኝ ነወይ”ብለው መኳንቶቻቸውንም ህዝቡንም ገስጸው “በሉ ቶሎ ብላችሁ ካጠገቤ አምጡልኝ” በማለት እንጦጦ ጋራ ስር የሚገኝ ቦታ እንዳሰፈሯቸው ታሪክ ይዘግባል።ይህም ቦታ በወቅቱ ቀጭኔ ይበዛብት ስለነበር ስሙ ቀጨኔ ተብሎ ተጠራ።በነገራችን ላይ ይህች ሴት ሰለባለጆች ወደሰሜን ሸዋ አመጣጡን ስትዘግብ በሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ከደንብያ እንደመጡ አትታለች፤ዝቅ ብላ ደግሞ ሚኒሊክ አዲስ አበባ እንዳስመጧቸው ልትነግረን ትሞክራች።በነገራችን ላይ ይቺ ሰው የመጀመሪያዋ አይደለችም በቀጨኔ ህዝብ ማንነት ላይ ለመስራት የሞከረችው።ፕርፌሰር ኤፍሬም ይሳቅም ሞክረዋል በደርግ ዘመን።የሳቸው መላምት ደግሞ የሚለው የቀጨኔ ህዝብ በ12ኛው ክፍለዘመን ተነስቶ የነበረው ይኩኖ አምላክ ይባል የነበረው ንጉስ ዮዲት ጉዲትን ለመበቀል የሷ ወገኖች የሆኑትን የኢትዮጵያ አይሁዶች ያሳድድና በግድ ክርስትናን እንዲቀበሉ ያደርግ ነበር።ምንም እንኳን አስገድዶ ክርስትናን እንዲቀበሉ ቢያደርጋቸውም ወደቆላማውና ገደላማው ሰሜን ሸዋ ሸሽተው ማለትም ልዩ ስሙ ሞረት በሚባለው ቦታና አካባቢው ያባቶቻቸውን የአይሁድ እምነት በድብቅ እያመለኩ መኖር ጀመሩ ይላሉ።ለማንኛውም ደጉ ንጉስ ሚኒልክ የጀመሩት ኢትዮጵያን በስልጣኔ የማበልጸጉ ምኞት እንደሳቸው ፍላጎት እንደርግማን ሆኖ በሌሎች መኳንንቶች ባይወደድላቸውም ይህን ህዝብ አጠገቤ አምጡልኝ ሲሉ የጥበብ ናፋቂነታቸውን ያመላክታል።ሆኖም ግን እሳቸው ጀምረውት የነበረው ህዝብን ከህዝብ ማቀራረብና ኋላ ቀር አስተሳሰብን የመቅረፍ የህዝቡንም የእጅ ጥበብ እንደ አውሮፓውያኖች ወደተሻለ ደረጃ አሳድጎ የስልጣኔ ምንጭ የማድረጉ ህልምና ሙከራ በኃይለስላሴ ጊዜ እንዲቀጥል አልተደረገም።ለዚሁም በቂ ምክንያት ነበረው።
ጀነራል መንግስቱና ግርማሜ ነዋይ ንጉሱን ከስልጣን ለማውረድ ባደረጉት ሙከራ ነገሮች እየተበላሹ ሲመጡ ክቡር ዘበኞችን ወደቀጨኔ መድሃኒአለም እንዲሸሹ ነበር ጀነራል መንግስቱና ግርማሜ ነዋይ ያሳሰቡት።ሁለቱ ወንድማማቾች በመጨረሻዋ ሰአት ወደ ሰሜን ማለትም ወደ ቀጨኔ ለመሸሽ ሞክረው ስላልቀናቸው ወዳልፈለጉት አቅጣጫ እንዲሄዱ ተገደው ነው ዱከም ላይ የተያዙት።የቀጨኔ ህዝብ ግን ወደሱ የሸሹትን የክቡር ዘበኛ መኮንኖችና ወታደሮች ሸሽጎ አብልቶ አጠጥቶ የወታደር ልብሳቸውን እየጣሉ ሲቪል ልብስ እያለበሰ ከህዝብ እየተቀላቀሉ እንዲሰወሩ በማድረግ ህይወታቸውን በማትረፍ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከክቡር ዘበኞቹም የተረከበውን መሳሪያ ለመንግስት አልሰጥም ብሎ በአጎራባችነት በሚኖሩት በኦሮሞ ተወላጅ ባላባቶች በነሸዋረገድና ማሞ በሼ በኩል የቀጨኔን ያገር ሽማግሌዎች ንጉሱ በታቦት አስለምነው ነው እንዲያስረክብ የተደረገው።ይህ ክስተት የቀጨኔን ህዝብ በንጉሱና መሳፍንቶቻቸው ጥርስ ውስጥ እንዲገባ አድርጎት ኖሯል።በመሆኑም፤ከጦር ሰራዊቱ ጋር ሲዋጉ የሞቱትም ብዙ ስለነበሩ ብዙዎቹን የእንጦጦ ጅብ በልቷቸው ስለታዩ ባሳፋሪ ሁኔታ የቀጨኔ ህዝብ በላቸው ተባለ።የቀጨኔ ህዝብ ከእህልም ዘር እንኳ ምርጥ እህል መርጦ የሚበላ ቆራራና ቆፍጣና ህዝብ ነው።እንደ አሳማ ያገኘውን አያግበሰብስም ይጠየፋል እንኳን የሰው ስጋ ሊበላ።ይህ ሁሉ ነገር ኋላ ቀርነት የጣለብን ነው።
በንጉሱ ዘመን ያ ሁሉ ህዝብ በሚኖርበት አካባቢ የረባ ክሊኒክ እንኳ አልተሰራለትም ነበር።ትምርት ቤትም ቢሆን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ብዙ ኪሎ ሜትር ነበር እየተጓዝን ስንማር የነበነረው።ከዚያ ህዝብ አብራክ የወጡት እነ ፍቅረስላሴ ወግደረስም ስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን ምንም የፈየዱለት ነገር አልነበረም።ኋላ ቀርነት የገዢ መደቦች መሰሪነትም ተጨምሮበት በህዝባችን መሃል ለዘመናት ተንሰራፍቶ የኖረውን መጠራጠርንና አለመግባባትን ደርግም በአግባቡ ሊፈታው ባለመሞከሩና ወያኔ የሚባል መሰሪ ሃገሪቷን ከተቆጣጠራት በኋላ ህዝብን ከህብ የማባላቱን አጀንዳቸውን በደንብ እንዲወጡበት አሳምሮ ጠቀማቸው።
ኢትዮጵያን በተለይም አማራውን ለማሳነስ ከቻሉም ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ የውጪ ጠላቶቻችን በወኪሎቻቸው በወያኔዎች ቆሻሻ እየቆፈሩ ባረጀ ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ በታትነው እየጨረሱን ነው።ትላንት የቅማንት ማህበረሰብ ስም ሲለጠፍበት ስለኖረ ወቅት ተጠብቆ ዛሬ ከወገኖቹ ሊያቆራርጡት ሲሞክሩ እያዬን ነው።አይሪንም ዛሬ በራችን ተበርግዶ ስላገኘችው የቀጨኔን ህዝብ የዚሁ ዘመቻ ሰለባ ልታደርገው ብትሞክርም አይሳካላትም።በነገራችን ላይ እስራኤልም ያላችሁ ሆነ ሌሎች ወገኖች አለምነህ ዋሴ የሚባል ጋዜጠኛ የምታውቁት ከሆነ የቀጨኔን ህዝብ አስመልክቶ በሴትዬዋ ተከፍሎታል ይመስለኛል በማያውቀው ጉዳይ እየዘባረቀ ስለሆነ እንዲታቀብ ንገሩት።የቀጨኔ ህዝብ ወይም ባለጅ አማራ ኩሩ ኦርቶዶክስና ንጹህ የአማራ ህዝብ ነው።ከምንም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።አይሸጥም፤አይለወጥም።(አራት ነጥብ!)
“የምኒሊክ አገር ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር! ሰለሞን ነኝ ከካናዳ
to respond write to
Ethiopian Semay getachre@aol.com