Thursday, December 19, 2024

ካለፈው የቀጠለ ለዮናስ ብሩ መልስ የባሌ ሮቢ የጀነሳይድ አዋጅ 12/19/24 ጌታቸው ረዳ (Ethiop

ካለፈው የቀጠለ ለዮናስ ብሩ መልስ

የባሌ ሮቢ የጀነሳይድ አዋጅ

12/19/24

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian seamy)

እንደምታስታውሱት ባለፈው ከ11/16/24 “እንደ እነ / ዮናስ ብሩ ዶክተር ከመባል ማይምነት ተፈልጎ የማይገኝ ወርቅ ነው።” በሚል ርዕስ ክፍል 1  ትችቴ ላይ ዶ/ር ዮናስ ብሩ በየሚዲያው እየተጋበዘ ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፍጅት (ጀነሳይድ) አልተፈጸመም እያለ ሲሞግት መኖሩን ተነጋግረናል። እውነታው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖትንና ዘርን ያነጣጠረ ጥቃት በወያነ ትግሬዎች ሥርዓት 27 ዓመት፤ በኦሮሙማ አብይ አሕመድ ሥርዓት ከ5 ዓመት በላይ ያላባራ ጭፍጨፋ በአምሐራ እና በጋሞ እንዲሁም በአኙዋክ እና በመሳሰሉ ሌሎች ማሕበረሰቦች እንደተፈጸመ የማያወላዳ ማስረጃ ሞልቶ ተትረፍርፏል።

ችግሩ በተለይ አምሐራው ግምባር ቀደም ተጠቂና ተደጋጋሚ የጥቃት ኢለማ ቢሆንም፤ ከአብራኩ የወጡ አገር ውስጥም ይሁን ባሕር ማዶ የሚኖሩ አምሐራ ወጣቶችና ምሁራን እኛ ጥቂቶች በሕዝባቸው እና አባት እናት ወንድም እህታቸው እየደረሰ የነበረው ጥቃት ለማሳወቅ ብንሞክርም እኛኑን ከመዝለፍና ነገሩን ታባብሱታላችሁ ከማለት አልፈው ፤ አምሐራን ግምባር ቀደም ጠላት አድርጎ ከፈረጀ ሻዕቢያ ጋር ወዳጅነት የመሠረቱ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማጀብ የኤርትራን ባንዴራ እያውለበለቡ የአምሐራ ስቃይና ድምጽ ከመሆን ይልቅ የኤርትራ ማዕቀብ ይቁም እያሉ ዓለም ሲያደነቁሩ ፤ ግማሾቹ ደግሞ ጀነሳይዱን ለሚመሩት ጨፍጫፊ ሥርዓቶች የመድረክ ፕሮፓጋንዳዎችን በማሰራጨት ፤ የዕውቀት ፤ የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ሥርዓቶቹን እያጀቡ ሕዝባቸው ለረዢም ጊዜ ለጥቃት መጋለጡን አንዳንዶቻችሁ የምታስታውሱት ታሪክ ነው።

ወደ ዋናው አዋጅ ከመግባቴ በፊት ልብ እትሉት የምፈልገው ነገር አለ። አምሐራ ወጣቶች ዛሬ በስንት መከራ አብይ አሕመድ ባመጣው ትንኮሳ ሳያስቡትና ዝግጅት ሳያደርጉ ወያኔ በከፈተው ጦርነት የመሳርያም ሆነ የእርስ በርስ የመነጋጋር ዕድል በማግኘት አሁን ወዳለው “የፋኖ እንቅስቃሴ” ቢደርሱም፤ተዋጊዎቹ እርስበርሳቸው በጫካ ሥልጣን ጥም ተማርከው የተጠበቀው ትግል ሊያካሂዱ አልቻሉም።

በሚገርም እና በሚያሳዝን ሁኔታ ወያኔና ኦነግ ከሚጠሉት በላይ እስክንድር ነጋ ላይ “አምሐራ ነን” የሚሉ የዘመነ ካሴ የጎጃም ፋኖ ደጋፊዎች “እስክንድር መገደል አለበት” እያሉ እንዲገደል ጥሪ ሲያቀርቡ መስማት እጅግ የሚገርም “በጭፍን የሚራመድ የወረበላ ቡድን የተደባለቀበት” ትግል ሆኖ የመታየቱ ክስተት ሲገርመኝ፡ የፋኖ ትግል ዕውር ድምብሩ እየተጓዘ መሆኑን የሚያሳይ ያስገረመኝ ነገር ደግሞ ‘ዘመነ ካሴ” ያሰማራው ተሳዳቢው “ዘመድኩን በቀለ” የተባለ የጀርመን ኗሪ “እስክንድር ለምን አስር ጊዜ እንደታሰረ ለምንስ አስር ጊዜ እንደተፋታ መመርመር አለበት” በማለት ለነፃነት የታገለው ኢትዮጵያዊው አርበኛ በዚያ ባልበሰለ ህጻናዊ ንግግር ሲናገር መስማት የፋኖ ትግል እኔ እስከማውቃቸው የጫካ የነፃነት ታጋዮችም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ለመተንተንም ሆነ አቅጣጫ ለማስያዝ አስቸጋሪና አይቼውም ሰምቼውም የማላውቀው ብልሽትሽት ያለ ክስተት መሆኑን ነው።

  የፋኖ አስደንጋጭ ክስተት በዚህ አላበቃም። አንዳንዶቹ ከወያኔ ትግሬዎች የባሱ እጅግ መንደርተኞች (አውራጃኖች/ጎጠኞች) በመሆን ከፍተኛ የጥበት ስሕበት ውስጥ ገብተው ትግሉን ከማበላሸታቸው ሌላ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ (ለትግራይ ያልሆነች ኢትዮጵያ ትበጣጠስ - የሚለው  ጓደኛየ የነበረው ሟቹ ‘’የወያኔ አፈኛና አመራር አባል የተናገረው ‘’የአሰፋ ማሞን” ንግግር በመኮረጅ ፤ ዛሬ እነኚህ አዲስ በቀል ጠባብ የአምሐራ የፋኖ ደጋፊ ወጣቶችም በስሜት እየተገፉ ያንን የወያኔ ንግግር ያደመጡትን “ለአማራ ያልሆነች “ኢትዮጵያ ትበጣጠስ” የሚል ድንቁርና እንደ ፋሺን/አዲስ ቅድ/ ይዘው “አገርን ወደ ገደል የማስገባት” ትንቢት ሲመኙ በየውይይት መድረኩ ተሰራጭቶ በዩቱብ አደምጣለሁ።

አንዳንዱም ጭራሽ ከወያኔ የቀዱት ቀጥተኛ ንግግር “ኢትዮጵያ ለአምሐራ ጠንቅ ነች” በማለት ፤ አምሐራ ያተረፈው የለም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ኢትዮጵያ ከምትባል ሀገር መካተት የለባትም፤ የሚሉ አምሐራዎች (አምሓራ መሆናቸው አረጋግጫለሁ) “ሪፑብሊክ ኦፍ  አምሐራ” ለመመስረት የሚመኙ ድንጋይ ያረጉዝም አሉ።

ይህ ሁሉ ዕብደትና “አዙሪት/ኮንፊዥን” የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደ ባለበት ዘመን የምንሰማው የአምሐራ ወጣቶች ድንቁርና ምሁራኖች የቤት ሥራቸው ባለመስራታቸው የተነሳ ነው። ለዚህ ነው ዶ/ር ዮናስ ብሩ በዚህ ተጠምዶ አምሐራ/እና ሌሎቹ ላይ (ኢትዮጵያ ውስጥ) ጀነሳይድ አልተፈጸመም በሚል እየተከራከረ የምንሰማው።

 አብይ ከመጣ በ6 አመት ውስጥ ወያኔ ከነበረበት 27 አመት የጭለማ ጊዜ ለአማራው ነገድ እጅግ የከፋ የዘርና የሃይማኖት ጭፍጫፋ የተፈጸመበት ወቅት ነው። አብይ አሐመድን ከዚህ ወንጀል ነጻ ለማውጣት መሟገት በጣም -ፍትሃዊ ብቻ ሳይሆን፤ የመሪው ተከታታይ ንግግሮችና ሰብኣዊ ባሕሪ እንዲሁም መሪው አስከብረዋለሁ ብሎ በጥርሱም በጥፍሩም እየታገለለት ላለው አፓርታይድ ፌደራሊዝም እውቅና መስጠትና የሥርዓቱን ተልእኮ ትርጉም በቅጡ አለመረዳት ነው ፡፡

በዚህ የሃይማኖትና የዘር ጭፍጨፋ  ወንጀል ግምባር ቀደም ተጠያቂዎች የሆኑት የተለያዩ ስሞች የሚከተሉ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ሲሆኑ፤ በጎን ድግሞ እንደ ቀያሽም እንደ ግብአት ሰጪም የወያኔ መሪዎች እና በድሮ አጣራሩ “ኦ ፒ ዲ ኦ”  ተብሎ ሲጠራ የነበረው እነ ለማ መገርሳ፤ አባ ዱላ እና አብይ አህመድ ወዘተ… ዛሬ “ብልጽግና” በሚል የሽፋን ስም በመጠራት ሥርዓቱን ለ6 አመት እየመራው ያለው አብይ አሕመድና አገልጋዮቹ ናቸው።

ከመሠረቱ ከ1983 ጀምሮ አፓርታይዱ ሲመሠረት ሥርዓቱ የተዋቀረው አማራን ያገለለ ነበር። አማራን በጠላትነት የፈረጀ የሚለው ገላጭ ሐረግ ልጠቀም፡። ስለሆነም አማራ ስርዓቱና የሥርዓቱ መሪዎች ሥልጣን ላይ እስካሉ አማራ እስካሁንዋ ሰከንድ ድረስ 36 አመት በዘሩ እልቂት ስደትና መፈናቀል እየተደረገበት ነው። ይህ ክስተት የጀነሳይዱ ከፍተኛው ገጽታ ነው። አማራን በማፈናቀልና በመፍጀት የተዋቀረው ይህ የጀነሳይደር ሥርዓት በግልጽ የሚናገረው ንግግር ስናስታውስ (የ6 አመቱ የኦሮሙማ አንደበቶች (ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/30/24) የሚለው ስታነቡ በአብይ አሕመድና በሺመልስ አብዲሳ የሚመራው መንግሥታዊ የኢንተርሃሙዌው ቡድን ከ20 በላይ የስልቀጣና የዘር ማጥፋት እንዲሁም የጥላቻ ቅስቀሳ ንግግሮቻቸው ስታነቡ የጀነሳይዱ ጥቃት አቀናባሪና ጥቃቱ በማን ላይ እንዳነጣጠረ ታያላችሁ።

እነ ዶ/ር ዮናስ ብሩና የመሳሰሉ ሰዎች የዘርና የሃይማኖት ጥቃት መፈጸሙ ቢክዱም ሥርዓቱ አምሐራን ነጥሎ ግምባር ቀደም ተጠቂ ያደረገ አፓርታይድ ስለሆነ ሥርዓቱን አንቀበለውም የሚል አምሓራ ለጀነሳይዱ የተጋለጠ ነው። ባጠቃላይ የጥቃቱ ዒላማ አምሐራ እና ክርስቲያን ስለሆነ ቢቀበልም ባይቀበልም <<ያመንም ያላመነም” የጥቃቱ ዒላማ ነው።

ዶ/ር ዮናስም ሆነ መሰሎቹ አምሐራ፤ ኦርቶዶክስ፤ አምሐርኛ ቋንቋና ዓድዋ ውስጥ “አምባ ሰሎዳ ተራራ” ላይ በጣሊያኖች ሬሳ ላይ የተውለበለበቺው ሰንደቃላማ በመንግሥታዊና በነፃ አውጪ ድርጅቶች ማኒፌስቶ ዋና ጠላቶች ተብለው መፈረጃቸው አያውቁም ብየ አልገምትም። አማራው ማህበረሰብ ምሬቱን እየገለጸ ያለውይህ ሥርዓት ማንነታችን እየለየ እየገደለን ነው እና ሥርዓቱ ይወገድልንሲሉ አብይ ደግሞ14 አመቴ ወደ ጫካ ሄጄ በደሜና በላቤ ታግየ የገነባሁት ሥርዓት ስለሆነ አስቀጥለዋለሁ እናንተም መጨፍጨፋችሁ ይቀጥላል ነውየመልእክቱ ቀጥተኛ አቋሙ (ንግግሩ ወደ መጨረሻ አቀርባለሁ)።

 ስለዚህም ኦነግ ሸኔ በሚል የቁልምጫ እና የመሸሸጊያ ስም መስርቶ አማራን እያስገደለ ያለው ሥርዓት በመሪነት የተኮፈሰው አብይ አሕመድ ተጠያቂ ነው (ኦነግ ሸኔ መስራች መሆኑንም ባለፈው አንድ ሳምንት “ታላቁን ምስጠር አጋልጣለሁ” በሚል ርዕስ የለጠፍኩትን ሰነድ መመልከት ነው። በደምብ ይጠየቃል እንጂ! ተጠያቂነቱ ከዚህ ይጀምራል።

አማራን በመጥላትና አማራን በማስጨፍጨፍም ይሁን አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት ስኬታማ ናቸው ብሎ የሹመት እውቅና ሰጥቶ፤ ግድያና ጥላቻ የሚያስፈጽሙበት ዕድሎች መርቆ የከፈተላቸው ነብሰ ገዳዮች እና ወንጀለኞች አብይ አሕመድ ነው። 3000 አመት እንገዛችሗለን ብሎ አዲስ ውስጥ በቴ/ቪዥን ቀርቦ የተናገረው ሌንጮ ባቲየአብይ አማካሪ የነበረ ዛሬ በዋሺንግቶን አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል። ሌንጮ ባቲ ደግሞ “የኦነግ” አመራር አባል ነው። የኦነጎች 3000 አመት የመግዛት ዛቻ ዘር ማጥፋት  እና ዘር ማጽዳት ነው። አደለም እንዴ?

እነ ታየ ደንዳኣ አማራው ቡራዩ ላይ ምን ይሰራል በጭነት መኪና ተጭኖ ወደ ጎጃም ይሂድብሎ የተናገረው የኦሮሞ ቄሮ ኢንተርሃሙዌው ካድሬ እናነፍጠኛን በቀበረን ቀብረነዋል፤አማራን ሸውደንም ሆነ አሳምነን በቁጥጥራችን አድርገን መቸም ቢሆን እንደማይነሳ አድርገን ቋንቋውን አጥፍተነዋል፡ ላሚትዋንም ወተትዋንም እጃችን ውስጥ ገብታለች…..” እያለኢንተርሃሙዌው ቡድን በተደጋጋሚ በግልጽ አዋጁን ለተከታዮቹ አበስሯል።

 ስለሆነም ብዙ የጀነሳይድ የጭፍጨፋ ክንውን ተካሂዶ ብዙ መጻሕፍቶች፤ ብዙ የደም ልቆሰዎች፤ብዙ ሺህ ቤቶች ፤ ብዙ መቶ ቤተጸሎቶች ተቃጥለው፤ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ንብረቶችና ሱቆች እንዲሁም ቤቶች ተዘርፈው ፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሴቶች ተደፍረው፤ ነብሰጡሮችና ህጻናት ታርደው ፤ ብዙ የሬሳ ክምሮች ፤ ብዙ ሚሊዮኖች መፈናቀልና በየጫካው መንከራተትና መደበቅ ፤ ብዙ ሺ የድረሱልን እሪታ የሚያሳዩ ቪዲዮ ማስረጃዎችና አቤቱታዎች ማየት በቂ ሲሆን፤ የሚቀጥለው የማሳያችሁ ሰነድ ደግሞ የባሌ ሮቤ ጸረ አምሐራው ኢንተረሃሜዌው ቡድን ያስተላለፈው የጀናሳይድ ጥሪ እነሆ ቪዲዮው ኦሮምኛ ቋንቋ ሲሆን ትርጉምም እነሆ አብሮ ቀርቧል።

ከዚያ በፊት ግን

የባሌ ሮቤ ቅድመ ጭፍጫፋ ከጀርመን EHRC ጽ/ቤት ለኦነጋዊው የአብይ አሕመድ መንግሥት ያስጠነቀቀው ደብዳቤ መጀመሪያ ላስነብባችሁና ከዚያም ወደ አምሓራን በመጨፍፍ የሚረካው ኢንተርሃሙዌው የባሌ ሮቤው አዋጅ እንመለከታለን።

እንዲህ ይላል፡

<<አስቸኳይ መግለጫ

 27 October 2019

አስቀድሞ ማስጠንቀቅ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ” EHRC (Ethiopian Human Rights Committee)

በባሌ ሮቤ ባለፈው አርብ ዕለት በግልጽ በጥቃት አድራሾቹ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ከሰኞ ጀምሮ ሊያካሂዱት ያስታወቁት የጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይፈጸም መንግሥት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃለፊነት አለበት።

በዛሬው ቀን ዕሁድ ጭምር ዜጎች ከሃይማኖት እና ዘር ተኮር መሰረት ያደረገን በህይወት ላይ ያነጣጠረን ጥቃት በመፍራት በቤተክርስትያን ተጠልለው ይገኛሉ።

የተቀሩት ቤታቸውን ቆልፈው በጭንቀት እያሳለፉ ነው። ስልካቸውን ለድረሱልን የስልክ ግንኙነት ለማድረግ ለመደወል ስለካቸው ካርድ መሙላት አልቻለም። ሱቆች ዝግ ናቸው።

ይልና በዛዚያ ባለፈው ሳምንት ዘርና ሃይማኖት ላይ ያነጣጣረ ጭፍጨፋ እንደተካሄደ እንደገና ያ መሰል ጭፍጨፋ እንዳይደገም በድጋሚ መንግሥትን ሲያስጠነቅቅ እንዲህ ይላል፤

“ በአካባቢው የገባው የጥቃት ሃይል በቁጥር ከጥቃት አድራሾቹ በትጥቅም በቁጥርም በጣም ስለሚያንስ ስጋት ጨምሯል። ይህንን በባሌ ሮቢ በጥቃት አድራሾች አርብ ዕለት ማስጠንቀቂያ የተሰጠበትን የ “ሰኞ እንመለሳለን” ቀጣይ ዘር እና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ እንዳይካሄድ የዜጎች ህይወት እንዳይጠፋ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ከግምት በማስገባት የዘጎችን ህይወት ለመታደግ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ይጠይቃል፤

(ስዩም ሀብተማርያም ጀርመን) >> (ድምቀትና ሰረዝ የተጨመረ)

አሁን ደግሞ ወደ ኦሮሞው ኢንተር ሃሙዌው ጨፍጫፊው ቡድን አዋጅ እነሆ! (የኦሮምኛ አዋጁ ቪዲየው ግን ከስር ለጥፌዋለሁ።)

በባሌ /ሃገር (ክልል) በሮቤ ከተማ ደግሞ የከተማው ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በመሃል ሜዳ ቆሞ በብዙ ሺሕ ሰው ፊት ከባሌ አባ ገዳዎች፤ ከሃይማኖት አባቶች፤ ከአገር ሽማግሌዎች እና ከቄሮዎች የአቋም መግለጫ ከተንጣለለው የገበያ አደባባይ በቪዲዮና በድምጽ የተቀረጻ ከድምጽ ወደ ጽሑፍ ትርጉም ላስነብባችሁ እንዲህ ይላል፦

ዶርዜና ነፍጠኛ ከሚባል ማንም ሰው ግንኙነት አድርጎ የተገኘ ሰው ፈጣሪ መአት እንዲያወርበት በሼኮች የተረገመ ሲሆን ይህንን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ከነፍጠኛ እና ከጠላት ለይተን አናየውም። ይህን በተመለከተ

1) ከዛሬ ቀን ከዚች ሰዓት ጀምሮ ከነፍጠኛ እና ከዶርዜ ንግድ አንገዛም አንሸጥም።

2) ከዛሬ ጀምሮ ግብ መጠጥ ልብስ ሲገበያይ የተገኘ ሰው የተረገመ ይሁን።

3) ከነፍጠኛ እና ከዶርዜ በልተህ ብትገኝ ፈጣሪ በሽታ ያድርግብህ፤

4) ይህ ድርጊት ፈጽሞ በሃይማኖት በሸኮች የተወገዘ ነው።

5) የኪራይ ቤት ወይንም ሱቅ በረንዳ ይህንን የመሳሰሉትን ከዛሬ ጀምራችሁ ካሁንኑ ሰዓት አከራይታችቸው ከሆነ እንድትነጥቁዋቸው። ያላከራያችቸው ከሆነም እንዳታከራይዋቸው። እንጠይቃችለን፡

6) መሬት እና ቤት እንዳትሸጡላቸው። አሁንም ለመውጣት ተዘጋጅተው ለመሸጥ ከፈለጉም እንዳትገዝዋቸው። መሬቱ የናንተ ነው፤ቤቱም የናንተ ነው።

7) የእህል ወፍጮ ቤት የንግድ ተቋማትም እንዲሁ የመኪና አገልግሎት የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ለነዚህ ሰዎች አትፍቀዱ፤ እናንተም እንዳትጠቀሙ። ይህንን አድርጎ የተገኘ ነፍጠኛ ነው ማለት ነው።

8) ዛሬ ሰልፍ የወጣነው ጀግናችን የቄሮ አባት የሆነውኦቦ ጃዋር መሓመድላይ ጠላት ለመግደል ሙከራ ስላደረገበት ድምጽ ሆነንለት ነው። ጃዋርን የሚቃወም መቼም ቢሆን የባሌ ሕዝብ ጠላት ነው።

9) የልጆቻችን ህይወት ያጠፉ የመንግሥት አካል የሆኑ፤ ደሞዝ የሚከፈላቸው መስተዳደሮች፤ ትናንት ልጆቻችንን የገደሉ፤ለፍረድ ይቅረቡልን።

 ይላል።

እንግዲህ ይህንን የዘር ማጥፋት ጥሪ ከተላለፈ በኋላ የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ድርጅት /ቤት የዘር ማጥፋት አዋጁ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አደጋውን ለማስቆም ለአብይ አሕመድ ያስተላለፈው አስቸኳይ ጥሪአስቀድሞ ማስጠንቀቅ የዜጎችን ህይወት መታደግየሚል የባሌ ሮቤ አክራሪዎቹ እና አባ ገዳዎቹ እንዲሁም ሼኮች እና ቄሮዎች ከሰኞ ጀምሮ ሊወስዱት የተዘጋጀውየዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አዋጅ/ጀነሳይድመግለጫ በጽሑፍ አስታውቆታል።

 የተፈራው እልቂትም ደረሰ። በዛው ዓርብ ዕለት አዋጅ ታውጆ ለሰኞ እንመለሳለን ያሉ ታጣቂዎች ዓርብ ጥቂት ቀናት በፊት በአማራ ብቻ ሳይሆን በጋሞ ነገዶች ላይም ጥቃት ፈጽመው ነበር። መንግሥት ይህንን ያውቃል። የጋሞ ነገዶችም አርባ ምንጭ ውስጥ ለዜጎቻቸው ስጋትና ደህንነት ሲሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰሚ አልነበረም። 

ይሁንና እነዚህ በሃይማኖታቸው እና በነገዳቸው ተነጥለው ለግድያ የታጩ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶርዜዎች እና አማራዎች (እስላም ጭምር) እንዲሁም ክርስትያኖች በቤተክርስትያን ተጠልለው በፍርሃት ቆፈን እየተንቀጠቀጡ፤ የአብይ አሕመድ መንግሥት እንዲያድናቸው የመንግሥት ያለህ/የአብይ ያለህ/ ሲማጸኑ ነበር። ይህ ደግሞ አበይ በደምብ መረጃውም ጥሪውም ደርሶታል።

 በሚገርም ሁኔታ ጋሞዎች ምን የሚል መልእክት ለአብይ አስተላለፈው ነበር? እንዲህ ይላል

 መንግሥት ሕግን ማስከበር የሚችል ከሆነ ያስከብር የማይችል ከሆነም እራስችንን ለመከላከል የምንጠብቅበት መንገድ ሁሉ ለመጠበቅ እንገደዳለንብለው ነበር።

ሆኖም አብይ ይህንን አቤቱታ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውምግድያው ይቀጥላል፤ ከዚያ ይሰክናልእያለ ነበር። በዚያው አዋጅ መአት ጋሞዎችና አማራዎች በሚያሳዝን አገዳደል ተጨፈጨፉ!!!! ይህ የሆነው ጥቅምት በፈረንጅ ኦክተበር መጨረሻ ገደማ 2019 ነው።

ዶ/ር ዮናስ ብሩ ግን ይህንን የዘርና የሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ ወያኔንም አብይንም እና ኦነግን በጀነሳይድ ወንጀል የሚጠይቅን ፍትሃዊ ጥያቄየፖለቲካ መፈክር/ለፖለቲካ ግብአት” ወይንም ጀነሳይድ ተፈጽሟል እየተባለ የሚነገረው እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመጠቀም ተብሎ ነው” የሚለው አባበሉ እጅግ አሳዛኝ ነው።

 በመጨረሻም፡ በአብይ አሕመድ ክፉ ንግግር ልደምድም።

አማራዎች እየተገደልን ነን ብለው አቤቱታ ሲያመለክቱም አብይ አህመድ ለሚታረዱ እና ለተፈናቀሉ አማራዎች (እስላምና ክርስትያን) አልቃሾች ይላቸዋል። 

 እንዲህ ሲል፤

አንድም ሰው እሚያመሰግን የለም። ከእስላም አፍአልሓምዱላህንተነጥቋል። ክርስትያናትም ማመስገን የለምማልቀስ ብቻነው። አልቃሽ ሕዝብ ደግሞ አይሻርም። ችግር ብቻ ነው የምሰማው።እናንተን እያረጋጋሁ ስራየን ልሰራ አልቻልኩም ሕዝቡ ሰላሙን ካልጠበቀ ይህ አሁን የሰማችሁት ልቅሶ ትናንትናም ብዙ ልቅሶ ነበር፤ አሁንም እናንተንም ሸኝቼ አዲስ አልቃሽ ይመጣል ሥራ እምባ መጥረጊያ ሶፍት ይዞ መቅረብ ብቻ ሆኖ ቀረ። ሁላችንም እየተጋፋፋን እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል? አደራችሁን በሚቀጥለው አመትም እንደዚሁ መሃረም ይዛችሁ እንዳትረሱ ወንድሙን ወንድሙን መንገድ የሚዘጋ ከሆነ እኔ ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?ሃይማኖታችሁ እንኳ የማይገዛችሁ ከሆነ? ምን አደርጋችለሁ እኔ! በልቅሶ ብዛት አገር አይገነባም እና ትንሽ እንኳን ብትሆን እያመሰገንን እንኑር በማለት

አንገቷ በሜንጫ ተቀንጥሳ የሞተችበት ባል፤ ህጻናት በካራ የታረደ እናት፤ ''ሰውን ሰው በልቷል ብሎአቤቱ ሆይ! አድነን ፤ወታደር ላክልን፤ በክልልህ የሾምካቸው መሪዎች እየገደሉን ነው፤ እነሱን አስወግደህ ጤነኛ መሪዎችን አምጣልን አብያተ ጸሎታችን ተቃጠለብን'' ፤ ብለው አቤት ለሚሉ የሃይማኖት መሪዎች እና ምእመናንእኔ ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?’ለምን አታመሰግኑኝም ማልቀስ ብቻአልቃሾችእያለ ጉልበት የሌላቸው እናቶች እና ደከማ ተጠቂውን የሚሳደብ፤ ለሚቀጥለው ዙርም 'መሃረም አትርሱ' የኔ ስራሶፍት ይዞ አልቃሹን እንምባ ማበስ ሆኖ ቀረእያለ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ነብሰጡሮች እና አረጋዊያን እና እናቶች ከመኖርያ ቤቶቻቸው እየተጎተቱ ወደ በረንዳና ጫካ ሲጣሉ፤ አብይ ደግሞ አቤት ስላሉአልቃሾች እና ምስጋና ቢሶችእያለ ያሾፍባቸዋል።

ጀነሳይድ አልተፈጸመም?! ግጥም አድርጎ እንጂ 

ጌታቸው ረዳ    ኦሮምኛ ለምታደምጡ ቪዲዮውም ከሥር እነሆ