Saturday, November 20, 2021

የአዲስ አበባው የታማኝ በየነ ንግግር ሲፈተሽ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ETHIOPIAN SEMAY) 11/21/2021

 

የአዲስ አበባው የታማኝ በየነ ንግግር ሲፈተሽ

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ ETHIOPIAN SEMAY) 11/21/2021

“ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: Ethiopis

https://youtu.be/WhB-U6qymJk

ታማኝ በየነ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተሰጠው የተፈጥሮ ጸጋ መስህብ ምክንያት መንግሥትን፤ ሥርዓትን ድርጅትን የመገልበጥ፤የማስለወጥ፤የማስጠላት እና የማዳከም ሲፈልግም የማጠናከርና የማደራጀት፤ የማስጨፈር፤ የማስለቀስና የማ’ሳቅ አቅም አለው። ይህ ስጦታ በተፈጥሮ እንጂ በትምሕርት አይገኝም። ዘፋኝ ነው፤ ተነጋሪ ነው፤አስተዋዋቂ ነው፤ሙዚቀኛ ነው፤ እምባ አቅራሪ፤አዛኝና ርህሩህ ነው፤ተንኮለኛም ነው፤ ስሜት የሚጋልበው ከፍተኛ ሃገራዊ ፍቅር የሚታይበት ዜጋ ነው። ሃገራዊ ፍቅሩ መጠን ስለሌለው፤ በዚህ ሁሉ በጎ  ባሕሪው ጥቂት ለሆኑ በራዥ ከላሽ እና አደገኛ ቡድኖችና ግለሰቦች በትግል ስም ሲደግፋቸውና እያቆለጳጰሰ ሲያሞጋግሳቸው ብሎም “የተሸለመውን የአምበሳ” ሽልማት ሲሸልምና ሲያሞካሻቸው የታየበት ጊዜም ጥቂት አይደለም። ለዚህም በራዦችና ጸረ አማራ ሃይላት እውነተኛ አገራዊያን ተመስለው እንዲታዩ ረድቷቸዋል። በዚህ ምክንያት ማን ከማን መለየት በሚደረግ የመነፅር ፍለጋ ጉዳት አድርሷል።

ባለፉት ወቅቶች ታማኝ መንካት፤መውቀስ ፈጣሪን መንካት መስሎ የሚታያቸው ብዙ ሰዎች በኔ ላይና በጥቂት ተቺዎች ላይ የስድብ ናዳ አውርደውብናል። ታማኝ ሰው ነውና ሲሳሳት “ተመለስ” ብሎ ማለት እንደ ታቦት የሚመለከቱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አጃቢዎቹ ዘንድ አያስወድድም።

ታማኝን ከዋሃቢስቶቹ የአሕመድ ግራኝ “ቢጫ” ባንዴራ አውለብላቢዎቹ “ኢትዮጵያ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ታያችሁ ነበር፤ አንድ ቀን ግን እንገጠል ስትሉ አልሰማሁም” ከሚለው የውሸት ንግግሩ  ጀምሮ፡ “የኢትዮጵያ ሙሰሊም አክርሮ ጎራዴ የሚይዝ ከሆነ እኔ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙስሊሙ ጎራዴ እመርጣለሁ”። ሲለው የነበረውን ንግግሩን ስተቸው እንደነበር የድሮ አንባቢዎቼ ታውቃላችሁ።

ኢሳት የሕዝብ እንጂ “የብርሃኑ ነጋ” የግንቦት 7 አይደለም ውሸቱን ጀምሮ፤- “አማራዎች ያዘጋጁት የሐዘን ጥሪ እና የድረሱ ጥሪ” ስብሰባ ረግጦ ወደ “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ” አዳራሽ ስብሰባ ሄዶ ያሳየው “ድርጅታዊ ፍቅር” ንግገሩን ጀምሮ ስንቱን፤ ስንቱን ተቺቼዋለሁ። ስለዚህ ዛሬም “የአብዩ አሕመድ ታማኝን” የምትወዱት በመተቸቴ ቅር ቢላችሁም እነሆ ዛሬም መጥቻለሁ።

ታማኝ ሰሞኑን ለጦርነቱ ድጋፍ ለመስጠት ወደ አገር ቤት መሄዱ እርግጥ ነው። በዚህ ላይ ተቃውሞ የለኝም። የሚበረታታ ነው። ልጁ ችግር አለ ሲባል ለአገሩ ፍቅር ያለው ስሜት “ዳርቻ የለውም”፤ ድረስ ሲባል “ቶሎ ፈጥኖ ደራሽ” ነው። ግን አብይ ኣሀመድ የሚመራው “አፓርታይዱ መንግሥት” ከሚያቆለጳፕሱና ከወንጀሉ ነጻ የሚያደርጉ ንግግሮቹ ግን መታቀብ አለበት።

የሰሞኑን ንግግሩን እስክመለሰው ድረስ በዚህ ሦስት አመት ውስጥ  የተናገራቸው እጅግ ቀፋፊ ሁለት ንግግሮቹን ላስቀድም፤

አንደኛው እንዲህ ይላል፡“

ዶክተር አብይ የተሸከመውን ችግር እኛ ለአንድ ቀን መሸከም አንችልም። ዶክተር አብይ በገዛ ፈቃዱ ለቅቄአለሁ ቢለን ምን ሊውጠን ነው” (ታማኝ በየነ)

 

ታማኝ ሚሊዮኖች ተከታዮች አሉት። በተከታዩ ብዛትና የማይከተሉትንም ጭምር ይህ ንግግርሩ በጣም ብዙ ሰው የአብይ ደጋፊ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህ ንግግር መቸውንም ቢሆን የማይረሳ ይቅር የማይባል ነው።

አብይ እና አብረው የተኮለኮሉት የዘር ማጥፋት የተካፈሉ በወንጀል የተጨማለቁ ዕርኩሶችን መተካት የሚችሉ በርካታ ዜጎች አሉ።ይህ ሰው አማራውንም፤ወላይታዎችንም  ፤ጋሞውንም፤ ኦርቶዶክሱንም አረጋዊያን እናቶችን ወዘተ… አስለቅሷል።

 

እስኪ እንደገና ልጥቀሰው እንዳትረሱት፡ አብይም ሆነ አብረውት ያሉ ብዙዎቹ “ዱርየ” ባለሠልጣኖቹ “አማራን እና ኦርቶዶክስን እንዲሁም የጋሞ ሰዎችን” በጥይት በገጀራና በካራ እንዲታረዱ ትጥቅና ገንዘብ ለግሰው ወንጀለኞቹን ጉልበት እየሰጡ መጨረሻ “እስላማዊ ኦሮሞ ኢንተርሃሙዌው” አዲስ አበባ ድረስ ተንሰራፍቶ ከተሞችን ሲያቃጥሉ፤ አረጋዊያን ቤቶች ሲያፈርሱ “ለሹማሙንቶች እና ኦሮሞ ከንቲባዎችን” አቤት ቢባል “አቤት ባዮች እና ጋዜጠኞችን እንዲታሰሩ ያደረገው እራሱ ታማኝ የሚያቆለጳጵሰው “አብይ አሕመድና ሹሞኞቹ ናቸው”። አብይ አሕመድ “ግድየለም አትንኳቸው ታፍነው ስለነበር  አሁን ነፃነት ስላገኙ ነው “ሰው  እያረዱ” ያሉት  “እያደሩ” ሲሰለቻቸው ይተውታል”፡ ሲል  ግድያውን ሲያበረታታ ነበር።

ታዲያ ይህ ሰው ሥልጣን ቢለቅ ምን ይመጣብናል ተብሎ ይገመታል? በወቅቱ ቢወርድ ኖሮ ኪሳራው አሁን ካለው ኪሳራ ያንስ ነበር። ነገሩ የሽግግር መንግሥት እና የሰላም ዕርቅ እንዳይመሰረት አውቆ ነገሩን ሲያጓትት እነ ታማኝም  ገበያ ሲያስፋፉለት እዚህ ደረሰ።እርሱን መተካት ይቻል ነበር።

የዘር ጭፍጨፋው የመንግሥት ድጋፍ አለው ብለው የቁርጥ ቀን ልጆች እነ እስክንድር ነጋ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግሥታት የዓለም መድረክ ስላቀረቡት “አብይ አሕመድ” ለምን አጋለጣችሁኝ ብሎ “የውሸት ምስክር አዘጋጅቶ” በዘር ማጥፋት ክስ “የአብየን ወደ እምየ” ገልብጦ እስር ወረወራቸው።

 “አብይ ከወረደ ምን ይውጠናል” ሲለን ታማኝ በየነ “የተዋጡት እነ እስክንድር ምን እንደዋጣቸው አልነገረንም፤ ወይንም ለምን ዋጥካቸው ብሎ ቅዋሜ አላቀረበለትም። አብይ አህመድ “ጡት የሚያጠቡ እናቶች” ህጻናት ልጆች  ባዶ ቤት ትተው ጭምር  ነው የዋጣቸው።

 

ስልተኞች ከሚጠቀሙባቸው “በጣም ስኬታማ ከሆኑ አዘናጊና አደንዛዥ ከሆኑ ስልቶች ውስጥ እኛን የማሳመኛ መንገዳቸው አንዱ “ለሰይጣን” አሜን ብሎ መገዛት ምርጫችን መሆኑን ማሳመን ነው።ስልቱ መላዕክቶቹ በአጋንንቶች ስለተሸነፉ ከሁለት አጋንንት መካከል ትንሹን ጋኔል መምረጥ እንዳለብን ይመክራሉ።

ችግሩ አማልክቶች ብቅ ባሉ ቁጥር በሰይጣኖቹ ይዋጣሉ።ምክንያቱም ይህ ሰይጣን ከለቀቀ ምን ይውጠናል እየተባለ ሰይጣን እንዲመለክ፤ ከሰይጣን ሌላ ሰይጣን እንደ ንብረት እየተላለፍን  ከፍተኛ ማደንዘዣ ሴራ በኢትዮጵያ ተሸርቧል።

አሁን አየተደረገ ያለው የህይወትና የንብረት መስዋእትነት አብይ ገና 3  ወር ሲያደርግ ቢደረግ ኖሮ ወያኔ  ሊያደርሰው የሚችለው ጉዳት እጅግ ይቀንስ ነበር። ችግሩ አስቀድመን ስንናገር ነበር፡ አብይ በጣም አታላይነቱንና ብሔረተኛነቱን በግልጽ ነግሮናል። እኔ አሻግራችሗለሁ፡ አብዮት የሚባል አላደርግም፤ የማደርገው |”ጥገናዊ ለውጥ ነው” / ሲል እነ “ልደቱ አያሌው” ደግሞ “መቀሌ” ድረስ ሄደው አዎ እኛም አብዮት አንፈልግም “እኔ እራሴ ጸረ አብዮተኛ ነኝ” የሚያስፈልገን “የጥገና ለውጥ ነው” እያሉ እነ ልደቱም መጨረሻ በጥጋናዊው መሪው “ተዋጡ ተገረፉ፤ ታሰሩ፤ሕክምና ተከለከሉ፤ አገሪቱ ለውርደት ተጋረደች”። (‘ጥገና’ የተባለው የተፈራው ‘አብዮት’ ከሚያመጣው ጉዳት በላይ ብዙ ጉዳት ደረሰ)።

ይህ እያወቀ ታማኝ በየነ ሐፍረት ሳይሰማው ከጓደኛው ከፕሮፌሰር አልማርያም ጋር ሆኖ በጋራ በእንግሊዝኛ ጽፈው የአፓርታኢዱ አብይ አህመድ ገበያ ሲያሻሽጡ ነበር።

ከፕሮፓጋንዳቸው ጥቂቱን ላሳአችሁ፡ እንዲህ ይላል፡

 

“(ጠ/ሚኒስትሩን) ከሥር ያሉ አላነቃንቅ ያሉዋቸው ይመስለኛል።

 

“ኢትዮጵያውያኖች፣ ያገኘነዉን ታላቅ ሰጦታ እንዳናጣ  ዓይናችንን ከፍተን መጠበቅ አለብን!”

 

“የአሉባልታ መሳሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና የመንግስታቸውን ሕጋዊ ቅቡልነት ለማሳጣት እና ወገን እና ሀገር ወዳዱ መሪ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የለውጥ ሂደት አንጸባራቂ ኮከብ በመሆን የተጎናጸፉትን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ አመኔታ ለመሸርሸር እና ለማጥፋት ሲባል ሆን ተብሎ ታስቦበት፣ በስሌት እና በታቀደ መልኩ እየተካሄደ ያለ መሰረተ ቢስ ዘመቻ እንደሆነ እናምናለን።”

እያለ እኛኑን መሰረተ ቢስ እያለ ሲያጣጥል ስንቱን አማራ ስንቱን ጋሞ ስንቱ ክርስትያን ተፈጀ!

አክቲቪስቶቹና ፖለቲከኞቻችን ካለፈው ያልተማሩ፤ ነገር  ግን ብልህ ተናጋሪዎች ናቸው፤ ግን ተሎ የሚነጠቁ በጥገና የሚያምኑ ፈዛዞች ናቸው።

አሁን ታማኝ ከሁለት ሰይጣን አንዱ ለዘብተኛ ሰይጣን የሆነው “በኦሮሙማው መንግሥት” እየተመራን ወያኔ የተባለው ‘የባሰውን ሰይጣን” መውጋት አለብን፤ ድርድር የሚባል የለም ብሏል።

ምክንያቱን ሲያብራራ  

“ዕድል ተሰጥቶት 27 አመት ገዝቶ “ኤክስፓየር” ያደረገ ቡድን ተምሶ ሲመጣ እንደ ቅዱስ ሲነገርለት እሚገርም ነው።ያልተነቀለ ጥፍር ለመንቀል፤ያልተኮላሸ  ወንድ ለማኮላሸት ወይስ ለምንድነው የሚመጣው?”

ይላል፡

ከዚህ ጽሑፍ ጋር አያይዤ የለጠፍኩትን እነ እስክንደር የቀረጹትን “ቪዲዮ” እዩና አብይ አሕመድ ብልት እንዴት  እንደሚያኮላሽ፤ እንዴት እስረኛን እንደሚደበድብ እንአቶችን እንዴት እንደሚያስለቅስ ጭካኔውንም እስኪ አመዛዝኑት።

አብይ እኮ የትልቁ ሰይጣን የመለስ ዜናዊ ተማሪ ነው። አብይ እኮ ነበር  ጥፍር እንዲነቀል ወንድ ልጅ እንዲኮላሽ ስልካቸውን እየጠለፈ  በውሸት እንዲያዙ ሲያሳስርና ሲያስደበድብ የነበረው። አሁንም ያው ነው!! እንዴት ፤እንዴት እንዴት ተማኝ፤ ጥፍር ሲነቀል፤ ወንድ ሲኮላሽ በዚህ 3 አመት አልሰማህም?!  

 

የገረመኝ ደግሞ እንዲህ ይላል፤

“የዛሬ 10 አመት እንደዚህ ሚዲያ ተደርድሮ መናገር አይቻልም ነበር በነሱ ዘመን ዛሬ ቢያንስ ሃሳቤን ለመግለጽ ይህንን ዕድል አግኝቻለሁ።” (ታማኝ በየነ)

እውነት ይህ አሁን እንደ ነፃነት ሊታይ  ይችላል? ልደቱም  እኮ ወያኔዎችን በአዲስ አባባ የተቃዋሞ የምርጫ ውይይት ቀርቶ መቀሌ ድረስ እንኳ ሄዶ እኮ በጣም በሚገርም ድፍርት እኮ ነው ሲዘፋቸው  እና እራቁታቸው ሲያስቀራቸው የነበረው።

እንዴ! ታማኝ ለመሆኑ የባልደራሶችን አፈና ትከታተል ነበር? የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዳይሰጣቸው ከመታገድ ጀምሮ ከ3 በላይ  ሆነው እንዳይሄዱ ታግደው ነበር እኮ! ሌላ ቀርቶ እስክንድር እና አንድ ወዳጁ እግር ኳስ ለማየት  ‘አሰታድዮ’ ድረስ ሄደው  “ሕጋዊ የመግቢያ ቲኬት” ያስቆረጡትን ቢያሳዩ፤ ከማንኛውም ዜጋ በተለይ ተለይተው  እንዳይገቡ በፖሊስ ታግደዋል እኮ!! እስክንድር “እገባለሁ እኔ ሕጋዊ ቲኬት  ይዣለሁ በሕግ አምላክ አትከልክሉኝ ገብቶ የማየት መብቴ ነው፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ፤ በሕግ አምላክ!” ሲላቸው በጆሮየ ሰምቻለሁ ፤ አንተ አልሰማህም?  

እንደገና

“አዚህ አሁን አገር ውስጥ ስላለሁ( ውጭ አገር ካሉት)“ትንሽም ብትሆን” የበላይነት አለኝ።” ትላለህ፡ አገር ውስጥ ሆነህ በአብይ አሕመድ አልተዋጥክም።ለሁለት ሰይጣኖች አንገዛም አገራችን አንለቅም ብለው ትዳራቸውና ልጆቻቸው ውጭ አገር ጥለው ኢትዮጵያን መኖር የመረጡ ቅዱሳን ታጋዮች አገር ውስጥ ሆነው የታገሉ እመጫቶች አና ወጣት ጋዜጠኞች በአፓርታዱ ሥርዓት እንዳንተው በነፃ መናገር ቀርቶ ቤተሰብ ጥለው እስር ቤት ገብተው  የተዋጡትስ ምን ዓይነት የበላይነት ቢሰጣቸው ትምርጣለህ?

ለማንኛውም አገር ወዳድነትህን ሳደንቅ ‘ክምትናገራቸው አወዳሽ ንግግሮችህ” ብትቀንስ ከትችት ትድናለህ።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ETHIOPIAN SEMAY)