ለትውስታ!!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
9/5/83
ፎቶ፤ አክሱም በወጣትነት ዘመን ነው። ዛሬ ለምነህ በማታገኘው “ውብ” “ድንቅ” የአብሮነት በመልካሙ ዘመን!
ይህ ፎቶ ከስንት አመታት በኋላ አክሱም ያለቺው እህቴ ዛሬ ልካልኝ ደስታውን መቋቋም አልቻልኩም። ይኼው እንዲህ ያማረብን ነበር፤ ተወበዳጁ በንጉሡ ዘመን። ከታች ያለው ፎቶ “እስላም ክርስትያን ሳንባባል” ስንዋደድ የነበርነው የልጅነት ጓደኛዬ “ማዕሩፍ ኑርዬ” ነው። ማዕሩፍ ዛሬም ከተወለደባት ከአክሱም ከተማ አልተንቀሳቀሰም። ዛሬም እዛው ይኖራል። ከስንት ዘመን መለያየት በኋላ ሰሞኑን በስልክ ስንገናኝ “ተላቀስን” ! መልካሙ አስለቃሽ የደጋጎች ሰዎች ዘመን።
የዛሬዎቹ የተማሩ የተመራመሩ ተብየዎች ባልነበሩበት ዘመን “የጭካኔ ዘመን”
ይበሉት እንጂ ዘመኑ የደጋጎች የገራገር ሰዎች ዘመን ነበር (ሰሞኑን መጎስ ተሾመ በተባለው ተበጥራቂ በራሱ ሚዲያ ላይ “ተራቃቂ”
እንግዶችን በመጋበዝ “ሃይማኖቶቻችን በጨካኞች ሲመራ የነበረ” ሥርዓታችንና ባሕላችን የአረመኔ የጨካኞች ዘመን፤ የሚሉ እንግዶችን
ባሕላችንን ሲደበድቡት ሰንብተዋል። የራሳቸው ዘመን በቅጡ ሳይመረምሩ ዘመናችንን የጉረኞች፤የልዩ ነን ባዮች ፤የርሃብተኞች የጨካኞች
ዘመን እያሉ “የዲግሪ መረቂያቸው” እያደረጉት ያለው የደማቆቹ ኮዋክብት አገር “ሙሶሎኒና ሮማን ፕሮቻስካ” የዘለፍንን እንዳይበቃ
በራሳችን በዛሬው ወጠጤዎች ያ ደጉ ዘመን “ሲዘለፍ” ቸል ማለት አልቻልኩምና መልስ መስጠት አስፈላጊ ስለሆነ በዚህ ርዕስ እመለሳለሁ።
ለማንኛውም ሰላም እንሁን!
ጌታቸው ረዳ