Monday, January 10, 2022

ደሞተራው አብይ አሕመድና ቤተሰቦቼ፤ ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 1/10/2022

 

ደሞተራው አብይ አሕመድና ቤተሰቦቼ፤

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

1/10/2022

አውነት ለመናገር፤ ዕድሜየ ሙሉ ወያኔን ስቃወም፤ እነሱ በሚቆጣጠሩት በረሃ ውስጥ ከወያኔ መሪዎችም ጋር በተጋጋለ የፖለቲካ ተቃርኖ ስወያይ በኔም ሆነ በዘመዶቼ ላይ አንድም ቀን ያደረሰው አስከፊ እርምጃ አልነበረም።

በሚገርም ሁኔታ “ዛሬ” አብይ አሕመድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ  እኔንም ሆነ ቤተሰቦቼን እየተበቀለ ነው።

አብይ አሕመድ በትግሬ ጥላቻነቱ በጅምላ ካሰራቸው ወንድሞቼ እና እህቴ አንዷ አህቴ በጠና ታማለች። በዚህ በጣም ተበሳጭቻለሁ። አብይም ሆነ እነ “ካቡጋ” ጀሌዎቹ የኔን መበሳጨት እጅግ ይፈልጉታል፤ ያስደስታቸዋል።

በትግሬነታቸው ብቻ ተለይተው ወደ “ኮነስንትሬሽን” የማጎርያ ሥፍራዎች ታፍሰው ከተወሰዱት በየከተሞቹ ከሚገገኙት ንጹሃን ትግሬዎች አንዷ ትንሿ እህቴ “ማርያማዊት” በታጎረችበት ማጎርያ ሥፍራ በብስጭት ታምማ እየተሰቃየች ትገኛለች።

የሩዋንዳው “አር. ቲ. ኤል. ኤም” ራዲዮ ጣቢያ ዋና አዘጋጅ የነበረውን “ካቡጋ” የተባለው ከሁቱ ነገድ የተወለደ የቱትሲን “ዘር አጥፊ” እነሆ በአገራችን ደግሞ እሱን የተካው መሳይ መኮንን የተባለው “የኢሳቱ ካቡጋ” ትግሬ ነገድ የተባለ ሁሉ በመላው ኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ከመኖርያ ቤታቸው እየታፈሱ ወደ ማጎርያ ጣቢያዎች እንዲወሰዱ ለዘር አጥፊው “ለአብይ አሕመድ” በደብዳቤ በተማጸነው መሠረት፤ ተግባራዊ ሆኖ ቁጥራቸው በውል ለማወቅ የሚያስቸግር በሺዎቹ የሚገመቱ የትግራይ ተወላጆች እየታፈሱ አንዳንዱ እየተገደሉ ንብረታቸው ተዘርፎ፤ከሥራቸው ተፈናቅለው ያለ ንጽሕና እንደ ከብት ማጎርያ በሺዎቹ ተፋፍገው በ ኤ ች አይ ቪ፤ በዲያቢተስ፤ በተላላፊ በሽታዎች እና የሳንባ ነቀርሳ በተያዙ  በሽተኞች  “ሆን ተብሎ” ዘር ለማጥፋት አብረው እንዲተኙ ተደርጎ ታስረዋል።

ፖለቲካ ምን እንደሆነ እንኳ የማይገባት እህቴ በማታውቀው ምክንያት ትግሬ በመሆንዋ ብቻ ምስኪንዋን እህቴ ከመኖርያ ቤትዋ ጎትተው “ትንሽ ህጻን ልጅዋን” ለጎረቤቶች አደራ የምትልበት ዕድል እንኳ ሳይሰጥዋት እንደ በግ ተጎትታ፤ ታፍሳ እነሆ ከታፈሰች “ወራቶች አልፈዋት” በብስጭት ታምማ እየተሰቃየች መሆንዋን ዜናው ሲነገረኝ እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም።

ሌላው ወንድሜ ምንም ሳይኖሮው አስረው አሰቃይተው፤ ማስረጃ ሲያጡበት በ20000 ብር ዋስ ለቀቁት። በለቀቁት በ3ኛው ቀን እንደገና ከሌሎቹ ጋር አብሮ ታፍሶ እነሆ እርሱም በኩላሊት ተሰቃይቶ ሰውነቱ ከስቶ እየተሰቃየ ይገኛል። ሌላኛውም እንደዚሁ ትግሬ ስለሆነ አፍሰው አጉረውታል።

እናንተ ኢትዮጵዮዊያን አስኪ ፍረዱ! እነ አባይ ወልዱ፤ እነ ስብሓት፤ እነ ቅዱሳን ነጋ ፤ እነ አባዲ… ወዘተ..ቁንጮ “የወያኔ መሪዎች” ተፈትተው “ከምንም የሌሉበት” ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን “ትግሬ በመሆናቸው” ታስረው ሲሰቃዩ ማየት እንዴት ሊሆን ቻለ? ብለን ብንጠይቅ  “መደመር ማለት ከገዳ ሥርዓት የተቀዳ ነው” ብሎ “ኩሊው አብይ አሕመድ” ሲነግረን “የገዳ ኦሮሙማው ፍትሕ” ምንነቱን ያየንበት አሳዛኝ የሆነ የበሰበሰ ሥርዓትና ዘመን የመድረሳችን ምዕራፍ ምልክት ነው።

እህቴ ታማለች ብትሞት አብይ አሕመድና ተባባሪዎቹ በሕግም፤ በታሪክም ሓለፊነትን ይወስዳሉ።

 ንዴቴን መግለጽ የማልችለው ቃላት ስላጣሁኝ አሁን  ማለት የምችለው “አብይ አሕመድ አዲስ አባባ ውስጥ በየፓርኩ እየተዘፈቅክ ለሥልጣን ትርዒትህ ስትጓጓ በመሃሉ “ካልተገደልክ” ያንን አምልጠህ ወደ አሜሪካ ከነቤተሰብሕ ከሸሸሕ ከመምጣትህ በፊት ሌላ አገር ብትሸሽ እንደሚሻልህ በዚህ አጋጣሚ ምክር ላስተላልፍልህ እሻለሁ።

ቂጥህን ሳትጠርግ የወያኔ “የሥለላ ኩሊ” መሆን አምሮህ ሕዝብን ለ27 አመት ያሰቃየኸው እንዳይበቃህ ዛሬ ወደ ሥልጣን ተጠግተህ እኛ አመቻችተን ፤ሞተን ደክመን “በሰጠንህ ኢትዮጵያ” ዘመዶቼን የማሰር የሞራልም የሥልጣንም ይሁን የዜግነት መብት የለህም። የዜግነትህ ምስክርነት ተግባርህ ነው።

ለማንኛውም አንተም የመለስ ዜናዊ ዕጣ እንዲደርስህ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ፈጣሪ ዘርግላችና ጉድህን እስክናይ መጠባበቅ ነው።

ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY