Thursday, December 20, 2018

አብዮታዊዉ ሠራዊት መሣሪያ ይዞ ውሐና ምግብ እየለመነ ወደ እየቀየው ተመመ!!! (ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ)


አብዮታዊዉ ሠራዊት መሣሪያ ይዞ ውሐና ምግብ እየለመነ ወደ እየቀየው ተመመ!!!

 (ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ)

NotE from the editor;- (ኢትዮ ሰማይ)

ወደ ታሪኩ ከመግበታችን በፊት የዚህ ድረገጽ አዘጋጅ ይህንን መልዕክት ያስተላልፋል።
ታሪኩን ስታነቡ ስሜት ይነካል። ወያኔ በሃገር ክሕደት መከሰስ አለበት ብለን ስንወተውት የነበርነውም በኢትዮጵያ ወታደሮች እና የትግሬ ወታደሮች (የፋሺስት ወታደሮች) የተደረገው ጦርነት፤ በሉዓላዊ ሃገር ተከላካይ ወታደሮች እና በሃገር አፍራሽ ፋሺስት ትግሬ ተዋጊዎች ማሃል የታየው ልዩነት ነው።  የትግሬ ፋሺሰት ወታደራዊ ሃይል ካለ “የደቡብ፤የምስራቅ፤ የምዕራብ እና የመሃል አገር ሕዝብ” ትብብር ነበር “ኢትዮጵያን አሸንፈን መንግሥት ተቆጣጥረናል” ብለው እንደ በፊቱ ዛሬም ኢትዮጵያን አምበርክክን ሥልጣን እንደበፊቱ እንቆጣጠራለን” የሚሉ ከሆነ “ያው ፍጥጫው እየደለበ ስለሆነ” ጥንካሬአቸው በቅርቡ የምናየው ይሆናል።
እዚህ ላይ አንባቢዎች ልትገነዘቡት ምፈልገው “የትግሬ ፋሺስቶች እና የዓረብ ቡቹላው ሻዕቢያ” የኢትዮጵያን ሠራዊት አሸንፈው ሳይሆን ምስጢሩ በጣም በርካታ ቢሆንም አንደኛው ምስጢር ግን “የደርግ ኮሚኒሰት መንግሥት” አፍርሶ የአሜሪካን ቡቹላ “ካፒታሊስት-መንግሥት” (ወያኔ) ሥልጣን ላይ ለማውጣት ስለነበር፤- “ወሳኙ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በአሜሪካኖች የስለላ ሳተላይት ድጋፍ እንደሚያገኙ በተስማሙበት መሥረት ታግዘው ነበር አሸናፊነቱን የተጎናጸፉት (ሌሎቹን ምክንያቶችን ሳንዘረዝር)።
ሱዳን ካርቱም ከተማ ውስጥ በፕረዚዳንት ቡሽ ልኡካን እና ከወያኔም እነ ስየ አብርሃ እና የወያኔ አመራሮች እንዲሁም እነ ጴጥሮስ ሰለሞን..ከሻዕቢያ ስበሰባ አድርገው በተፈጸመው ‘ሴራ’ የተካሄደ ጦርነት እንደነበር ካሁን በፊት ማስረጃውን አቅርቤ በዚህ ድረገጽ እና በሌሎች ድረገፆች ለጥፌዋለሁ)። ዋናው ተልዕኮ  ኤርትራን እና የትግሬ ሪፑብሊክ ለመመሥረት እንደነበር የታቀደው ሴራ ዛሬ የትግሬ ፋሺስቶች ከሥልጣናቸው “ሙሉ ቁጥጥር” ባልጠበቁት ስልት ሲንሸራተቱ በማየታቸው ዛሬ እነሆ የትግል መነሻ ምክንያታቸውን እንደ ዱሮ ሳይሸሽጉ በግልጽ “የምታከብረንን የትግራይ ሪፑብሊክ አገር እንመሰርታለን” እያሉን ነው። ለማንኛውም አሳዛኙ ጦርነት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ያንብቡ እና ይህ ታሪክ ስታነቡ “በፋሺሰት ትግሬዎች” ላይ የምታሳድሩት የቁጣ ስሜት ገምቱት። እነሆ…….

አብዮታዊዉ ሠራዊት መሣሪያ ይዞ ውሐና ምግብ እየለመነ ወደ እየቀየው ተመመ!!!

 (ከሻለቃ ላቀው መንግስቴ)

12/14/2018

ባቄሎ የመጨረሻዋ ጠረዝ

ጓድ መንግሥቱ /ማሪያም ግንቦት 1983 አጋማሽ ላይ ሐገሪቱን የሕዝብ እልቂትነ ለማሥቆምና ለሐገር ደህንነት ሢባል ሐገሪቱን ለቀው እንዲሄዱ ተደርጓል የሚለው የዳሪዎሥ ሞዲ የሬዲዮ መግለጫ ደብረ ብርሀን ጠባሤ ካምፕ ውሥጥ ተሠብሥበን የነበርንውን ተሥፋ አጨለመ፡፡

ጀነራል ከበደ አርምዴ እንዲህ ይሆናሉ ብዬ ባልገመትኩት ሁኔታ፡አገሪቷንም ሕዝባችንንም የትም በትኖ ለአውሬ ጥሎን ሄደ፡፡ተሥፋችን ምንድን ነው፡፡ከጠረፍ እሥከጠረፍ የተዘረጋው ሠራዊት መጨረሻ ምን እንዲሆን አሥቦ በትኖን ሄደ፡፡የእውነት አነቡ፡፡ኮለኔል ግርማ ተካ ኮለኔል ዘርይሁን ፈረደ ሁሉም እምባዎቻቸው ይወርዳሉ፡፡ሁላችንም የቀረችንን የውጊያ ቀጠና ጣርማ በር፡ለሚ መዘዞን እሥከመጨረሻው ተናንቀን ከማ

ለፍ በቀር አማራጭ እንደሌለን ቃል ገብተን መሪ የሌላት አገር ወታደሮች መሆናችን እርግጥ ሆኖ በጀነራል ከበደ አርምዴ/605/ኮር አዛዥ ኮለነል ግርማ ተካ 605 ኮር ድርጅት መኮንን፡ሌኮ ዘርይሁን ፈረደ አሥተዳደር ሆነን ሽፍታ መሠል መሪ የሌለው ተዋጊ ሆነን ወደ ጣርማ በር አመራን፡፡በውጊያ የተመናመነው 6 ሜካናይዝድ ብርጌድን ለመጨረሻ እድል መሞከሪያ ተማምነንበት ልንዋጋ ወሥነናል፡፡ በለሚ ግንባር ሥጋቱ ወደ መሐል እየገፋ ሢመጣ ቤተመንግሥቱን ሢጠብቅ የነበረው ልዩ ጠባቂ ብርጌድ ሁኔታው ሁሉ ጨለማ ሆኖበት የማእከላዊዉ መንግሥት ከአናቱ መፍረሡ ግራ አጋብቶት ሞራሉን ቆፈን ቆፍኖት በፅልመት ተውጧል፡፡የሚበላ ምግብ መጣፈጡ አቁሟል፡፡

በሕዝብ መሐል ማእረግ ለብሦ መሄድ ሞት መሥሎ ታየ፡፡

ቁልፍ ቦታዎችን ለዋሥትና ይዞ ከወያኔ ጋር እንኳን ለመደራደር ወኔ የነበራቸው የመከላከያ ሐላፊዎች ለመኖራቸው አጠራጣሪ ድባብ ወረሠን፡፡ከሁሉም ግን የነበረን ምርጫ ጣርማ በርን ፋይላችን የሚዘጋባት፡የሠማእታት ደብራችን እንድትሆን ፈቅደን ነገር ፍለጋ በሚመሥል መልኩ ደብረ ብርሀንን ለቀን ጣርማ በር መሽግን፡፡የደብረ ሢና ሆቴል ባለቤት አቶ ተገኝ ምግብ እያመጣ ሊንከባከበን ሞከረ፡ መሠሪያም ይዞ አብሮን በቁጭት ተሠለፈ፡፡በነገራችን ላይ ይህን ሠው ወያነ ሥልጣን ከያዘ በሁዋላ ገድለው ጫካ ጥለውታል፡፡ውጊያው ቀጥሏል፡፡ወያነ ድሉን ያረጋገጠ በሚመሥል መልኩ በተኩሥ ጣርማ በር ላይ እያጫወተን በአምቦ መሥመር ጉዞውን እያሣመረ ነበር፡፡

ጣርማ በር መዘዞ የነበረ ጦር

ጦሩ ተሥፋው ተመናምኖ በራሡ ጊዜ የውጊያ ቀጠናውን እየለቀቀ ወደ መሐል አዲሥ አበባ መጓዝ ጀምሮአል፡፡ግንቦት 15 ይመሥለኛል እንደምንም ሥለባንዲራ ብለን እንዲቆም ያደረግንውን ጦር ጀነራል ረጋሣ ጂማ የሦሥተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ ባንዲራዋን በቀኝ እጃቸው ይዘው ሠራዊቱንልጆቼ በእዚህ እድሜዬ ፈርቼና ሸሽቼ ወደ ልጆቼና ሚሥቴ ልግባ፡፡ልጆቼ ዘመኔን በሙሉ ጦርነት ውሥጥ አሣልፌአለሁ በዚህ እድሜይ እናንተንና ይቺን ባንዲራ ይዤ ልፈር፡፡

አሟሟቴን አሣምሩልኝ ልጆቼ ጊዜ ይቀያየራል እኔም እናንተም ለዚህ ደረጃ በቅተናል ግን ታሪክ ሠርተን እንለፍ ብለው ተንበረከኩና በባንዲራው ፊታቸውን ሸፈኑና ሢነሡ የአባትነት እምባቸውን ከአይናቸው ፈነጠቁ”” የባንዲራችንን ሀይል በእውነት መገመት ያሥቸግራል፡፡ሠራዊቱ መፈክር እያሠማ ከርሥዎና ከባንዲራችን በፊት ብሎ መንፈሡ ወደ ነበረበት ተመልሦ ምሩኝ ልዋጋ አለ፡፡ውጊያው መሥዋእትነትን እየጠየቀ፡መንግሥትም የፖርቲ ሢቢል አባሎችንና የተለያዩ ታጣቂዎችን ከሠንዳፋ በመለሥ በኛ ግምባር አሠልፎአል፡፡ከሁዋላ በአምቦና በጅማ እቅጣጫ በናዝሬት መሥመርም ነገሮች ተበለሻሽተዋል፡፡

ሠራዊቱ የሚችለውን ሞክሮ ወደ መሐል ፍሠቱ ቀጥሏል፡፡የመጨረሻ ባቄሎ ላይ 17/10/1983 የመጨረሻ ውጊያ ገጠመን የጀነራል ከበደ አርምዴ ሬዲዮ ሠራተኛ አይነት 77 ሬዲዮ ይዞ ከሁዋላቸው እየተከተለ ጭንቅላቱ ተመቶ በታማኝነት ወደቀ፡፡ሬዲዮኑን ከላዩ ላይ ተቀብለን ከቅርብ ርቅት በመትረየሥ የሚዘንብብንን ጥይት መከታና ከለላ ያላቸውን የተፈጥሮ መሬቶች እየተጠቀምን በማፈግፈግ ላይ ነን 6 ሜካናይዝድ አዛዥ ሻለቃ አየለና ኤርትራዊዉ የፖለቲካ ሀላፊው ሻለቃ ገብረሥላሤ በኛ ትእዛዝ ሥር ነበሩ ረፋዱ ላይ ጀነራል ከበደ ለብቻቸው ፈንጠር ብለው አረፍ ብለዋል ፡፡አጃቢያቸው ወንዱንም ሤቱንም አንቺ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ተወላጁ ደበላ ወደ እኔ እየሮጠ መጥቶ ሻለቃ ሠውየው ራሧን ልታጠፋ ነው ድረሽ ይለኛል፡፡ሮጬ ሥሄድ ሁኔታቸው ተቀያይሮ ፊታቸው በሚያሥፈራ መልኩ አብጦ ወረቀቶች አየቀዳደዱ የመጨረሻ ዉሣኔ እደደረሡ ሣያሥቡት ሽጉጣቸውን ከመሬት ለቀም አድርጌ ምን መሆን ፈልገው ነው፡፡ለቤተሠቦችዎ አያሥቡም፡፡

የርሥዎ ሞት ሁኔታዎችን የሚቀይረው ነገር አለ? የተቻለው ሁሉ ተሞክሯል የምንለውጠው ነገርም የለም ይልቅሥ አየለ ብረት ለበሥ እንዲልክልን አደርጋለሁ ብዬ አረጋግቼ ብረት ለበሡ መጣ ጀነራሉን፡ኮ/ግርማንና ዘርይሁንን ከውሥጥ አሥገብቸ እኔ ከላይ አናቱ ላይ ተቀምጬ ሀያ ሜትር እንኳን ሣንሄድ የብረት ለበሡ ጎማዎች ተመቱና መንገድ ሥቶ መንገድ ጠርዝ ቦይ ውሥጥ ገባን ሌላ ፈተና፡፡ጀነራል ከበደ እጅግ ወፍራም በመሆናቸው ከብረት ለበሡ ውሥጥ ለማውጣት ፈተና ነበር፡፡ሦሥቱንም እንደምንም አውጥተን በእግር ጀመርን፡፡ብረት ለበሡ እንደምንም ንፋሥ እየተሠጠው አልፎን ሔደ፡፡እሥከ ሠንዳፋ ደብረ ብርሀን ሥንደርሥ መኪና ቀርቦልን ከሦሥተኛው አብዮታዊ ሠራዊት ጋር ተቀላቀልን፡፡አዛዦቻችን ለሥብሠባ መከላከያ ፈልጓቸው ገቡ፡፡19/10/1983እኔና ኮለኔል ግርማ በአሥር አለቃ መኮንን ተጫኔ አሽከርካሪነት እሣቸውን ወሎ ሠፈር እኔና መኮንን ተጫኔ ደግሞ ወደ አየር ጤና አመራን እኔ እንዲህ በአዋራ ተጎሣቁየ ቀጥታ ወደ ቤት አልሄድም ብዬ አየር ጤና ግሪን ፓርክ ሆቴል ገብቸ አደርኩ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ልብሥ አምጥተውልኝ፡እኔ ከግሪን ፓርክ ወያኔ ከጅማ መሥመር እነሡ በድል፡እኔ ደግሞ ለእኔም ሆነ ለቤተሠቤ ቢጠቅምም ባይጠቅምም ነፍሤን ቋጥሬ ወደ እቤት ገባሁ፡፡አባቴን ሣየው የገነፈለ እምባ ከቁጥጥሬ ውጭ ሆኖ አነባሁ፡፡በበራችን ላይ ወያኔ በታንክ በተሽከርካሪ አየተግተለተለ ገባ፡፡አብዮታዊዉ ሠራዊት ጨፍጫፊና ፀረ ሕዝብ ሆኖ ታሪኩን ለባለድሎቹ ወያኔ አሥረከበ፡፡መሣሪያ ይዞ ውሐና ምግብ እየለመነ ወደ እየቀየው ጦራችን ተመመ ፡፡፡፡፡፡ዝርዝር ታሪኮችን ብዙ ቆራርጫለሁ፡፡ለፌሥ ቡክ እንደ አይጥ መርዝ በትንንሹ የቀረበ ነው፡፡ የኢትዮ ኤርትራ ውጊያ 10 ክፍለ ጦር የውጊያ ውሎም አለኝ ይቀጥላል፡፡፡፡፡፡፡፡