Friday, July 14, 2023

አየ ትግሬ! ትግሬ መሆኔን እያደረ ነው የመረረኝ ጌታቸው ረዳ 7/14/

 

አየ ትግሬ! ትግሬ መሆኔን እያደረ ነው የመረረኝ

ጌታቸው ረዳ

7/14/23

ብዙ ሰዎች እንዲህ ስል ይደነቁም ይደነግጡም ይሆናል። አልተለመደምና አልፈርድባቸውም። ትግሬ ሆኜ አልወለድም የማለት አፍ ቢኖረኝ ለናቴ ያን ነበር የምላት። አይግረማችሁ።

በትግሬነቴ ብዙ አይቻለሁ። እነሱን ለመግለጽ ግጥም ጽፌአለሁ፤ ትችት ጽፌኣለሁ፤ መጽሐፍ ጽፌአለሁ፤ ቃለ መጠየቅ አድርጌአለሁ። የትግሬዎች ባህሪ የሚያውቀው ትግሬ መሆንን ይጠይቃል። ሌላው አያውቀውም። አውቀዋለሁ የሚል ከሆነ ሁሌም የምናውቀው ገራገር የዋህ ነው፤ ወይንም ራሱን የሚያታልል ሞኝ ነው። እመኑኝ። በጣም ተንኮለኛ፤ ቀናተኛ፤ ገንዘብና ወርቅ እጅግ ወዳጅ (ተኮላ ወልደሓጎስም፤ የዛሬው ሁኔታው የት አንዳለ ባላውቅም፤ በጤና ይሁን አይሁን ባላውቅም - አሞት ከሆነም እግዚሃር ይማረው! በመጽሐፉ ነግሮናል)፤ ሰው የሚንቅ፤ ተሎ የሚግል ንዴታም፤ በራሱ ልሳን እምነት የሌላው ሰልጡን ልሳን ብሎ የጎረቤቶቹ ልሳን የሚዋስ እጅግ አስገራሚ ትውልድ የታየበት ፤ በጦር ሜዳ ሃይለኛ ተዋጊ፤ትዕቢተኛ፤ *ወገንተኛ (በዛሬው ቃላት ዘረኛ)፤ሃይል ካለው ባለጊዜ ጋር የሚያሾር፤ ቂም ቋጣሪ፤ጉረኛ፤ ዘፈን ወዳጅ፤ ጨፋሪ፤ እርስ በርሱ እንደ ውሻ የሚናከስ፤ በሌላው ባዕድ ግን “እንድ” የሚሆን፤ ጠላት የሚባል የመፍጠር ክህሎት ያለው፤ያንን እስከ ዘላለሙ በጠላትነት እያወሳው የማመንዠክ ባህሪ ያለው፡መመራመር ያቆመ ፤ እንደ ከብት ባንድ መንጋ ባንድ ገመድ የሚጎተት ማሕበረሰብ ነው።

ወንድማማቾች ነን ወልደን ተጋብተናል እኮ ለሚለው ገራገር ሰው ጭራሽኑ ያፌዝበታል፡ተጎጂ ነኝ የማለት ባህሪው መረን የለቀቀ ነው (ቪክቲማይዘሺን)፡ ቡድነተኛና አሽሙረኛ “ጠላቱን የሚያከብር” ወዳጁን የሚጎዳ አቋመ ቢስ፤ ወላዋይ ነው (የራስ መንገሻን የምስክርነት ሁለት ምላስ እንደ ምሳሌ ውሰዱ) (አብዛኛው ሰው ማለት ነው)።

በተለይ የዛሬው ትውልድ “እንደ ገደል ማሚቶ ደጋግሞ የመጮህና ውሸትን ፈጥሮ” እውነት የማድረግ ሳያፍር ያንን ይዞ የመዝለቅ ተክህሎው እጅግ ፤እጅግ ተክኖበታል።

እኛን በደምብ የሚያውቀን ኢትዮጵያዉያን ሳይሆኑ ዓረብ ብቻ ነው።የሩቆቹ ዓረቦች ሳይሆኑ አክሱም በግዛቶችዋ ሥር አድራጋቸው የነበሩትን ውሱን የአካባቢያችን ጎረቤት ዓረቦች ማለት ነው። በደምብ ስለምያውቁን “እባብና አበሻ ካየህ አስቀድመህ አበሻውን ግደል” ይላሉ። እስከዚያ ድረስ ያውቁናል። ለምን ቢሉ “እባብ ተንኮለኛ ቢሆንም አያስብም ኡውር ነው ይላሉ፤ አበሻ ግን በሁለቱ የተካነ ነው ይላሉ። ተንኮለኛና ቂም ቋጣሪ ነው ይሉታል ፤ እየሳቀ ቀን ጠብቆ ያጠቃሃል፤ ይላሉ። እነሱ አበሻ የሚሉት በርቅል መጠርያ ኢትዮጵያንም ኤርትራንም ቢሆንም ምሳሌውን የሚጠቀሙበት “ብዙዉን ጊዜ ለትግሬውና/ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራኖችንም ማለት ነው”።

ይህ ሁሉ ምሳሌ ለምን አመጣሁት? ፈረንጆች Hot News የሚሉት አትኩሮት የሳበ የወቅቱ ትኩስ የምንለው ዜና አለ።

የቅርቡ ዜና ትግራይ ውስጥ እያየነው ያለው ሌሎችን ባገለለ መልኩ ከኦሮሙማው የሃይማኖትና የፖለቲካ ቡድን ጋር ለይቶ ፍቅር ማሳየት፤ የመተቃቀፍ፤ እጅ ለእጅ እየተያያዙ መሳሳቅ፤መሸላለም፤ መተቃቀፍ፤ ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ጠላት የተባለው አደገኛውን ቡድን ሌላውን ለማብገንና ለመለየት በዕልልታ መቀበል፤ ትግራይ ውስጥ በተከታታይ እያየን ነው።

በቅርቡ አንድ ደንቆሮ ትግሬ በዚሁ በራሴ ፌስቡል ላይ የስድብ ውርጅብኝ በማውረድ አዳነች አበቤን ለምን ጠመድካት” ሌሎቹ ይቅርታ ሳይጠይቁ እርስዋ ግን “የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቃለች” በማለት ትችት መሳይ ጽፎብኝ አይቸዋለሁ። ይህ የውሸት ሽፋን የወየኔ ካድሬዎች  ውስጥ ለውስጥ ሞኙን ትግሬ የሚያሞኙበት ዘዴ እንጂ አዳነች አቤቤ ለትግራይ ሕዝብ በድየዋለሁና ይቅርታ ብያለሁ ያለቺበት አንድም ቃል በጽሑፍም በቃልም አልሰማንም። ጠይቄው ሊያቀርብም አልቻለም።

በአንጻሩ ግን፤ አዲስ አበባ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ በስመ ትግሬ ተሰብስቦ ከየቦታው እየተለቀመ እንዲታሰር፤ እንዲደበደብ ንብረቱም እንዲዘረፍ የቀይ ሽብር  ዓይነት ዘመቻ ከፍታ “ትግሬ አዳኝ/hunters/” ቡድን አሰማርታ በሐላፊነት የመደባቻቸው የአብይ አሕመድ ልዩ አድናቂና ካድሬ ወጣቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዮናስ ዘውዴ እና የመሳሰሉ በፎቶግራፉ ላይ እንደምታዩት ሽማግሌ፤ዐርጉዝ፤ ህጻን ፤ በሽተኛ ወዘተ “ብቻ ትግሬ የተባለ ሁሉ” ሰብስባ እንዲታሰር አደርጋ ብዙ ሰው ያለ ፍርድቤት ማዘዣና ያለ ፍርድ ቤት ጥያቄ ያንገላታች ሴት ናት።

አስገራሚው ደግሞ እንደ ሌሎቹ ሁሉ፤ አርስዋም “አማራውና ዓፋሩን” ረግጣ በመሄድ፤ መቀሌ ድረስ በርራ   ከአማራውና ከሌሎቹ ዜጎች በተሰበሰበ የቀረጥ ገንዘብና መዋጮና በዕርዳታ ይዛ ሄዳ ተመሰገነቺበት።

 ስትሄድም ትግሬዎች አንደምታዩት ጥልፍ አስጠልፈው በትግሬ ቀሚስ አሳምረው ፤ ፈንድሻ እና ቀጤማ እየነሰነሱ ዕልል እያሉ አቅፈው እየሳሙ ተቀብለዋታል። አማራ የተባሉት ቀሳውስትና ጳጳሳት ግን ምን እየደረሰባቸው እንደሆነ የምታውቁት ነው። ለምን እንደዚያ እንደሆነ ግን በዚህ ሦስት ቀናት በለጠፍኳቸው መጣጥፎቼ ገልጫለሁ።

ትግሬ ወዳጁን የሚጠላና የሚገፈትር ፤ በገዛ ወዳጁና ወገኑ ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ  ከጠላት ጋር የሚዶልት ጠላቱን የሚያከብርና የሚወድ እጅግ አስቸጋሪ  ትውልድ በብዛት ተበራክቶ ወጥቷል። ቄሱም ሳይቀር። ትግሬ መሆኔን እያደረ ነው የመረረኝ የምልበት ብምክንያት ነው።

ጌታቸው ረዳ