Friday, December 18, 2009

ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም!

ከለይ ፎቶግራፋቸዉ የሚታየዉ ብርሃኑ በርሀ (የዐረና ምክትል ሊቀመንበር)፤ ገብሩ አስራትስየ አብርሃ እና ቡልቻ ደምቅሳ፤ ሲሆኑ በመጨረሻ ልጁን ታቅፎ ሚታየዉ በወያኔ መሪዎች እና በጠባብ ብሄረተኞች የዘር አስተዳደር ፓሊሲ ምክንያት የተነሳ ባለቤቱ በጠባብ ብሔረተኞች የተገደለችበት እና እናቱ ያጣዉ ህጻን ልጅ የአማራ ብሔረስብ ገበሬ ነዉ።ዛሬ በእነ ገብሩ እና ብርሃኑ በርሄ ለዘለፋ ጥቃት እየተዳረጉ ያሉት በመኢአድ ዉስጥ ያሉት አመራሮች የአማራዉን ሕብረተሰብ ጥቃት በጽናት ቆመዉ የእነ ገብሩ እና ብርሃኑ አባዲ ፖሊሲ (አንቀጽ 39ኝን ጨምሮ) በመመከታቸዉ ነዉ። በመ ኢአድ መሪዎቹ ላይ እየዘነበ ያለዉ የተቀነባበረ የዘለፋ እና የስም የማጥፋት ዘመቻዉ ሴራ ዛሬም ህያዉ ሆኖ እየቀጠለ በመሆኑ ወደ ታሪኩ እንዉሰዳችሁ። መልካም ንባብ። ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም! ጌታቸዉ ረዳ የኢትዬጵያን ህልዉና እና አንድነት ካናጉት የወያኔ መሪዎች መካከል “ትልቁ አድርባይ” እና “ብሄራዊ ወንጀለኛዉ” ገበሩ አስራት የተባለዉ ትልቁ የወየኔ ዕቃ የትግራይ ህዝብ በርሃብ ሲያልቅ ለልቡ መታከሚያ ይሆነዉ ዘንድ ለርሃብተኛዉ ሕዝብ ከተመጸወተዉ እና ወያነ ከሕዝብ ባንክ በጠመንጃ አስፈራርቶ ከዘረፈዉ ካዝና $45 ሺህ ዶላር በላይ ከፍሎለት ለንደን እንግሊዝ አገር ድረስ አስታክሞት በሕይወት ቆይቶ ይሄዉና ተዘርዝሮ የማያልቀዉ የወንጀል የተባባሪነቱ እና ፈጻሚነት “እድሜ ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች” የሰራቸዉ አሳፋሪ ድርጊቶቹ ተሸፍነዉለት እና ድሮ ተዘንግቶት፣ ባለፈዉ ሰሞን ትግራይ ክፍለሃገር ዉስጥ በማይጨዉ ከተማ የዋህ ተከታዬችን ለማሞኘት በጠራዉ ስብሰባ የመኢአድ መሪን “ወያኔ” (ኢሕአዴግ) ናቸዉ ብሎ ሲወነጅል አብሮት የወያኔን ዘረኛ ፖሊሲ እና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተግባር እዉን ለማድረግ ለብዙ ዓመታት ሲታገል የነበረዉ ብርሃኑ በርሀ የተባለዉ ወያነ “በጠበቃነት”/ ሙያ ያሰለጠነዉ ሌላዉ የዓረና ትግራይ ምክትል ሊቀመንበር ነኝ ባይ ድግሞ -እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ “ራዲዬ- ስኒት” እተባለ በመኮነን ዘለለዉ የሚካሄድ የትግርኛ ራዲዬኦን ላይ በቃለ መጠይቁ በመሃንዲስ ሃይሉ ሻዉል ላይ ያንጸባረቀዉን ክፉ ጥላቻዉ እንዳይበቃዉ ማይጨዉ ከተማም በድጋሚ ኗሪዎችን ሰብስቦ “ሃይሉ ሻዉልም የተክለሃይማኖት ሰፈር (ተክለሃይማኖት ሰፈር ኗሪ የሆኑት የትግራይ ማሕበረስብ) ሳይቀር መርጠዉናል እያለ የትግራይ ሕዝብ ከኢትዬጵያ ሕዝብ እንዲነጠል ሲያደርግ የነበረ ሰዉ ነዉ” (ኢትዬሚድያ- ላይ- “ዛሬ ይህንን ሰንሰለት ሰብራችሁታል” በሚል ርዕስ ታደሰ ተስፋይ በተባለ ዘጋቢ “ዓረና” የተባለዉ ሌላዉ የወያኔ አንጃ ቡድን -ትግራይ ክ/ሃገር ዉስጥ በማይጨዉ ከተማ የጠራዉ ሕዝባዊ ስብሰባ የተዘገበዉን ይመልከቱ) ሲል ዉንጀላዉን በቅጡ ለመረዳት ግራ በሚያጋባ “ድፍን ዚቁን” ሲዘላብድ እና ፣ አያይዞም “ስለዚህም መኢአድ/ሃይሉ ሻዉል የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነዉ” ፣ በመሆኑም “ከ አክራሪዉ ሃይሉ ሻዉል እና ትግራይ ጠላት ጋር (ከመኢአድ ጋር) አብሮ የተሳሰረዉ ያለዉ ኢሕአዴግ እንጂ ዓረና ትግራይ አይደለም” ሲል ወያኔ ባሰለጠነዉ “የአወሻሸት ትምህርቱ” መኢአድን “በጸረ ትግራይ ሕዝብ” በመወንጀል፣ መኢአድን ዛሬም በድጋሚ “በመለስ የሚመራዉ የወያኔ ቡድን” እና “በገብሩ አስራት የሚመራዉ ሌላኛዉ የወያኔዉ ቡድን” መአከላዊ የጥቃት ኢላማቸዉ በማድረግ፣ እነ ገብሩ አስራት እና እነ መለስ ዜናዊ ከ ኦኖጎች እና ከኤርትራዉ ሕዝባዊ ግምባር/ሻዕቢያ ጋር ግምባር በመፍጠር የጋራ ኢላማቸዉ ያደረጉትን የአማራዉን ሕብረተስብ በመጨፍጨፍ (ኢትኒክ ከሊንሲንግ) እና ከመደበኛ ሥራዉ፣ ከግብርና እንዲሁም ከንግድ የሥራ ዘርፍ እና የጥሮታ መብቱን በመንፈግ በሕይት እና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱበት “ወያኔዎቹ እነ ብርሃኑ በርሀ እነ ገብሩ አስራት” ከወንጀላቸዉ ሳይጸጸቱ “የአማራዉን ሕብረተሰብ” ከእነ ገብሩ ዘረኛ ጥቃት በመከላከል እና የነ ገብሩን ወንጀል ለዓለምና ለኢትዬጵያ የመገናኛ ዘርፎች በማጋለጥ ለ18 ዓመት በጽናት ቆሞ የአማራዉን ሕብረተሰብ እየሞተ፣ እየተገረፈ እና እየታሰረ ብቻዉን ቆሞ የተከላከለዉ የድሮዉ የመላዉ አማራ ድርጀት የዛሬዉ “መኢአድ” ላይ ዛሬም ገብሩ አስራት እና መሰሎቹ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት የጥቃታቸዉ ኢላማ ማድረገቸዉ ይሄዉቀጥለዉበታል ፣፣ እነኚህ ግለሰቦች ለጥቃታቸዉ ኢላማ መነሻ ምክንያት ብንመረምር መልሱን ለማግኘት የሚያዳግት አይደለም፣፣ በእነ ገብሩ ድርጅት ሴራ ሕይወታቸዉን ያጡ የዚህ ድርጅት (የመኢአድ) አመራር አባሎች እና በሕይት ያሉ ድርጀቱን እየተከላከሉ የሕዝቡን ጥቃት በመዘገብ እያጋለጡ ያሉት መሪዎችን ለመተንኮስ የተነሳሱበት ምክንያት ይህ ድርጅት እነ ገብሩ አስራት በትግል ማኒፌስቶአቸዉ እና በፕሮፖጋንዳ ፖለቲካዊ ቅስቀሳቸዉ የመጀመርያ የጥቃት ኢላማቸዉ የደረጉት አማራዉን ሕብረተሰብ ማግለል በመኖሩ የመኢአድን አመራሮች ለመተንኮስ ያቀዱበት ዋነኛዉ ምክንያት የእነ ገብሩ ፋይል በመኢአድ አመራሮች እና በተከታየቹ፣ በደጋፊዎቹ እና የሰለባቸዉ ተጠቂ በሆነዉ ሕብረተሰብ “የሕሊና ማሕደር ዉስጥ” በጥንቃቄ ተመዝግቦና ታሽጎ እንዳለ ስለሚያዉቁ “መኢአድ” ተደራጅቶ ዛሬም የነ ገብሩን ድርጅት የ18 ዓመት የወንጀል ማሕደር ጉድ እያጋለጠ ፍትህ ፍለጋ እንዳለ ስለሚያዉቁ “መ ኢ አ ድ” የሚል ስም ፖለቲካ መድረክ ዉስጥ መገኘቱ እንደ ቅዠት እያባነናቸዉ መሆኑን ግልጽ ነዉ፣፣ ይህ ለምን ሆነ? የወያነ ትግራይ ብሔራዊ ወንጀለኞች አሁንም በሰለባቸዉ/በተጠቂ ላይ የሚያሾፉበት መድረክ እንዴት ሲኮን እና በምን ታምር እንዲህ ያለ ተደጋጋሚ ድፍረት ዐድሉ ሊያገኙት ቻሉ? የሚለዉን ጥያቄ መጠየቅ እንቆቁሉሹን መፍታት ያስችለናል፣፣ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ጨርቁን ገ ፎ፣ ሳንጃን በሞቀ እሳት እያጋሉ ገላን ማቃጠል እና እርቃኑን አስወጥቶ በእሳትና በፈላ ዉሃ እያቃጠሉ ገርፎ ፣ሰብአዊ ክብርን አዋርዶ፣ በሕግ ሳይጠየቅ እና ተገቢዉን ቅጣት ሳያገኝ በሰላም ተኝቶ በነጻ የሚንደላቀቁባት አገር በዓለም ዉስጥ ኢትዬጵያ ብቻ እንደሆነች እነ “ገብሩ አስራት” እነ “ብርሀኑ በርሀ” “እነ ‘ኣዉዓሎም ወልዱ” እነ “አረጋሽ ኣዳነ” እነ “አበበ ተክለሃይማኖት” በሚገባ ያዉቁታል፣፣ ወያኔዎች መጀመርያ ወደ ትግራይ ከተማ ሲገቡ የትግራይ ናሪ ተሰብስቦ ድምጹን በማሰመማት ሕዝቡን እና ገበሬዉን ያሰቃዩ የወያኔ ክፍሊ ሕዘቢ የተባሉ ገራፊዎች እና የወያኔ ከፍተኛ አመራሮች ፣የስለላ ክፍሎች እና ነብሰ-ገዳዬች እንፋረዳቸዋለን የሚሉ ከ 500 የማያንስ ሕዝብ ሰለማዊ የፍትህ ጥያቄ ለገብሩ አስራት ሲያቀርቡለት “በረሃ ላይ እያለን የሰራነዉ ወንጀል ካለ ለነጻነት ሲባል የተደረገ በመሆኑ አያስጠይቀንም” በማለት አርፋችሁ ቁጭ በሉ በማለት በሕዝብ እና በፍትሕ ያሾፈዉን ገበሩ አስራት ከእነ ወንጀሉ ለ18 ዓመት በሰላም ተኝቶ እንዳደረ አዉቋል፣፣ ይህ የሆነበት ምክንያትም ሠራዊትን፣ ሕዝብን፣ ሕብተሰብን፣ሉዓላዊነትን በጅምላ ያጠቁ የፖለቲካ ወንጀለኞች እንደገና ጥቃቱን ዳር እንዲያደርሱት መንገዱን ቀጤማ እየነሰነሱላቸዉ የሚታዩ ለመጣዉ ሁሉ “አርጋጆች” በብዛት የተፈለፈሉባት አገር ኢትዬጵያ ብቸኛዋ አገር በመሆኗም ጭምር ነዉ (ኢንጂነር ግዛቸዉ እና መረራ ጉዲና የተባሉ “ዕቃዎች/ ዉዥምብራሞች/አርጋጆች” ለወንጀለኞቹ ጥብቅና ቆመዉ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ “አዲስ ድምፅ” በተባለዉ የአበበ በለዉ ራዲዬን አርካኢቭ/ማሕደር ዉስጥ በመግባት ያድምጡ) ፣፣ ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ናት እንደሚባለዉ ወንጀለኞቹም ይዘገይ እንደሆን እንጂ እንደዚሁ እየተንደላቀቁ እስከ ወዲያኛዉ ሊዘልቁ እንደማይችሉ እና በአንድ መጪ ወቅት አንድ ሃገራዊ ቆፍጣና መሪ ሲነሳ ሰብስቦ እስር በማስገባት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንደሚያደርግ ምኞቴ የጸና ነዉ እላለሁ፣፣ የገበረመድህን አርአያ ለመጪዉ ትዉልድ ታሪክ እንዲሆን ያጠራቀመዉ “ግዙፍ ፋይል” እና የሺዎቹ ሕይወት ለሕልፈት መዳረግ፣ ግርፋት እና እንግልት ዘረፋና ፈርደገምድል፤ክህደትና ተንኮል የተዘገበበት ማህደር አፉን ከፍቶ ጊዜ እየተጠባበቀ ነዉና ፍትሕ ይዘገይ ይሆናል እነጂ አንድ ቀን ግን ፍትሕ አፉን ከፍቶ በነዚህ ጅቦች ላይ ያነጣጥራል! አንድ “ፈስያ እንተትሓንከልካ” የሚባል የትግርኛ አባባል አለ፣- “ፈስታ ስታበቃ አለማፈርዋ” (ፈሳም- ፈስታ ስታበቃ የፈሳዉ ማን ነዉ? ብላ ሌላዉን ንጸሁን ሰዉ ለማሳጣት “ፈሳም” ብላ በድርቅና መወንጀሏን ያስገርማል ማለት ሲሆን)፣ በሌላ አነጋገር “ሌባስያ ሌባ አይበልካ” የሚባልም አለ፣ “ሌባ “ሌባ” አይበልህ” የሚሉት አባባል ስናስተዉል አረና ወያኔዎች ቀንደኞቹ ወያኔዎች ራሳቸዉ ሆነዉ መሃንዲሱ ሃይሉ ሻዉልን “ወያኔ” ናቸዉ ብለዉ ሲከስሱ “የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” ሚባለዉ ተረት እነሆ በዓይናችን ለመመስከር በቅተናል። ወይ ጊዜ! (እናንተየ የጥንት ወላጆቻችን እንደዚህ ያለዉ ድረቅና በምን ቃላት እንደሚገለጹት ግራ ሲገባቸዉ ለካ ነበር “ምን የሚሉት ነዉ፤ ጭንቅ ያለ ነገር” በማለት አግርሞታቸዉ የገለጹት) ፣፣ ገብሩ እና ብርሀኑ፣ አረጋሽ እና ኣዉዓሎም የሚመሩት “የዓረና ድርጅት” መኢአድን የሚመሩት መሃንዲስ ሃይሉ ሻዉልን “ጸረ ትግራይ” (ወንጀለኛ፣ አክራሪ፤ወየኔ) ነዉ የማለት የሞራል ብቃቱ ከየት እንዳገኙት ድፍረታቸዉ ሳስበዉ እጅግ በእዉነት እጀግ አድርጎ ይደንቀኛል! ወንድሞቼ እና እህቶቼ አባቶች እና እናቶች ሆይ፦ አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ተክለሃይማኖት ሰፈር የሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች ከወያኔ ይልቅ “ቅንጀት”ን ነበር የመረጡት ብለዉ ኢንጂነር ሃይሉ መናገራቸዉ በምን ስሌት ፣በምን ትረጉም፣ በምን ቋንቁኛ፣ “ጸረ- ትግራይ” እንዳሰኛቸዉ ለኔ በጣም በጣም እጅግ በጣም ግራ የገባ አባባል ነዉ፣፣ ብርሃኑ በርሀ የተባለዉ ነብሰ ገዳዬች፤ገራፊዎች እና አምባገነኖች የሚመሩት ዓረና የተባለዉ ድርጅት ምክት ሃላፊ እና “የሕግ ጠበቃ” ነኝ የሚለን ይህ ሰዉ ፣ አዲስ አበባ የሚኖር “የትግራይ ማሕበረሰብ እንኳ ሳይቀር ለቅንጅት ድምጹን ሰጥጧል” ብሎ ማለት በየትኛዉ ትምህርት ቤት የተማረዉ ሕግ ነዉ “ጸረ ትግትሬነት “ ነዉ የሚል እምነት ሊያሳድርበት የቻለዉ? በመረጃ አስደግፈን ማቅረብ እንደሚቻለን እና ብዙ ጊዜ ካሁን በፊት መረጃዎቻችንን በተጨባች አስደግፈን እንዳቀረብነዉ ሁሉ አብዛኛዉ የከተማ የትግራይ ማሕበረስብ (በተለይ ቀለም የቀመሰዉ የከተማ ኗሪ) ከዚያ በፊት ሲነገር የነበረዉ ለወያነ ትግራይ ነበር ድምጹንም ድጋፉንም፣ጉልበቱንም ሕሊናዉም ስብሰባዉም ማህበሩም ገንዘቡንም ሌላ ቀርቶ ኤርትራ ነጻ ሙጣት አለባት ዓስብ እና ምጽዋ በኤርትራ አስተዳደር በሻዕብያ ቁጥጥር ይሁን ብለዉ የተስማሙት እነ ገብሩ አስራት የፓርላማ ድጋፍ የፈረሙት እነ ስየ አብርሃ ድምጽ እና ድጋፍ ሲሰጡ በየቀበሌዉ ተቀናጅተዉ የድምጽ ድጋፍ የሰጡት አዲስ አበባ ከተማ የሚኞሩ የትግራይ እና የኤርትራ ተወላጆች እንደነበሩ ብረሃኑ በርሀ ከመቸዉ ዘነጋዉ? ባዲስ አበባ የሞኖሩ የትግራይ ተወላጆች እና የትግራይ ልማት ድርጅት (ቲዲኤ) ከወያኔ ድርጅት ጋር በመተሳሰር ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረዉ በማድረግ የትግራይ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ባስፈላጊዉ መንገድ ወያኔን እንዲያጠናክር የተደረገዉ ስራ ብረሃኑ በርሀ ያዉቀዋል? ወየኔዎች አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ ትብብር እና ድጋፍ የለገሰዉ የትግራይ ተወላጅ እንደነበር ይዘነጋል? (ዉጭ አገር አለዉ የትግራይ ማህበረሰብ እማ ተዉት- ተነጋግረንበታል) በየሚድያዉ፣ እና በየኩባንያዉ ፣ ነጋዴዎች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና በኪነት/በየትያትር ተቋማቶች ዉስጥ የነበሩ ትግራይ ተወላጆች ወያኔ ሲገባ አግልግሎታቸዉ ሙሉ በሙሉ ለማን ነበር የለገሱት? ወያኔን በመረጃ ስምሪት እና ቅብብል ለ17 ዓመት ያገለገለዉ ማን ነበር? ሌላ ቀርቶ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ከ8 አዉራጃዎች ዉስጥ 7ቱ የደርግ የሕዝብ ድርጅት ጽ/ቤቶች የወያኔ አባሎች ያስተዳድሩት እንደነብር ራሳቸዉ ያመኑት ነዉ፣፣ አነኚህ ክፍሎች ይዞ ነበር ወያኔ ለዚህ ደረጃ የደረሰዉ፣፣ ብርሃኑ በርሀ እና ገበሩ አስራት ወያኔ ጉያ ዉስጥ አስከነበሩ ድረስ እና ገብሩ አስራትም የትግራይን ሕዝብ ለ10 ዐመት ሙሉ “ሲገዛ የሕዝብን ድምፅ እና ስሞታ ሲያፍን” እስከነበረበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ሕዝብ ከድርጅቱ ከወያኔ ጎን የቆመ ሕዝብ ነዉ እያለ ሲለፍፉ እንደነበር የሚዲያ ማስረጃዎች አሉን፣፣ ከዚያ ባሻገር ገበሩ አስራት እና ብርሃኑ በርሀ፣ አዉዓሎም ወልዱ አረጋሽ አዳነ …..ከወያኔዉ “ከመለስ ዜናዊ” ከተለዩ በሗላ የትግራይ ሕዘብ መለስን አዉግዞ ወደ “አንጃዉ ዞሯል፣ ሌላ አማራጭ እፈልጋለሁ ብሏል” ሲሉም ይደመጡ እነደነበር አሰራጯቸዉ መግለጫዎቻቸዉ ይመሰክሩባቸዋል፣፣ የትግራይ ሕዝብ የመለስን አስተዳደር በቃኝ ብሏል ካሉን በ1995 ግንቦት 7የተደረገዉ ምርጫ ገብሩ አስራት ለ6 ዓመት አንቀጽ 39ን እንዴት እዉን እንደሚሆን ዓረና ለመመስረት አድብቶ ከጓደኞቹ ጋር ማኒፌስቶ 39ን ሲያዋቅር ጊዜ ስለፈጀበት እና በ1995ዓ.ም ግንቦት ዉድድር ዉስጥ ገብቶ ለመወዳደር ስላልቻለ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች የመለስ አስተዳደር ጠልተዉ ለቅንጅት ድጋፍ በመስጠታቸዉ እና ይህ አዲስ ክስተት (“ሺፍት”) በቅንጅት መሪዎች እንደምሳሌ ተደርጎ ቢቀርብ የቅንጅት መሪዎች እነ እነጂነር ሃይሉ ሻዉል “ሌላዉ ኗረስ ይቅር - አዲስ አበባ ዉስጥ ለብዙ ዓመታት ወያኔን ሲደግፉ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች አንኳ ሳይቀር “ለቅንጅት ድምፅ ሰጥቷል” ብለዉ መናገራቸዉ “ጸረ የትግራይ ሕዝብ” የሚያስብለዉ ንግግር የቱ ላይ ነዉ?! “ትግሬ ወደ መቀሌ የተዘረፈ ንብረት ወደ ቀበሌ” ብሎ በዉስጥ በተንኮል ሰራዉን ቀምሞ ያሰራጨዉ ማን ነበር? በ እርግጠንነት ለመናገር “የቅንጀት አመራር እንደልለነበረ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ” ሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አድማም ሆነ በ50 የተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች ህዝባዊ አድማ ሲቀሰቀስ “ቅንጅት” የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለዉ በርግጠኝነት መናገር እንችላለን። እነ ብርሀኑ በርሀ እና እነ ገብሩ አስራት አለቆቻቸዉ እነ መለስ ዜናዊ ቅንጅት እንተርሀሙዌ ቅስቀሳ አደረገ ብለዉ ስለነገርዋቸዉ የወያኔ አለቆቻቸዉ ናቸዉና ከመለስ ከቅንጅት ይልቅ መለስ እና በረከት ማመን ነበረባቸዉ፤፤ ምንም ቢሆን በጎሰኞች ራዕይ “ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ” ነበርና። ስለነበርም ነዉ ገብሩ አስራት “ድሃይ ትግራይ” በተባለዉ ትግርኛ በሰጠዉ ቃለ መጠየቅቅ “ቅንጅት ትግራይ ጠላት እንደሆነ እና ከነ ቅንጀት ምንም የሚያገናኝ የፖለቲካ ትስስር ያኔም ሆነ ለወደፊቱ እንደማያደርግ የለፈፈዉ (የትግርና ትርጉም በማርኛ የተረጎምኩት በኢትዬጵያን ሰማይ አርካኢቭ “ይጎልጉሉ”/በማሰስ ይመልከቱ)፤፤ በዛዉ መጽሄትም አብሮ አዛዉንት ቤተሰቦቻችንን በእሳት እያቃጠለ ሲገርፋቸዉ ነበረዉ የድሮ የወያኔ የአየር ሃይል ኤታማዦር ሹም ነበረዉ የዛሬዉ ያዲስ አበባ ዩቨርሲቲ “የሕግ” (እባካችሁ አትገረሙ) መምህር የሆነዉ ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖትም (ጆቢ) ቅንጀት አዲስ አበባ ሲየሸንፍ “በኢንትርሃሙዌ ፕሮፖጋንዳ” ምክንያት ሽፋን ተጠቅመዉ “ከወያኔ የተባረሩት እና የለቀቁት የጦር ሹማምንት እና ወያኔ አንጃዎች ሁሉ ከመለስ ዜናዊ ቡድን ጋር በማበር ጊዜያዊ ኮሚቴ/ደርግ በማቋቋም በትጥቅ ማዕበሉን (መለስ ዜናዊ ከስልጣን/ወያኔ ከስልጣን እንዳይወርድ ማለት ነዉ) እንዲያቆሙት ምስጢራዊ ዝግጅት አድርገዉ እንደነበሩና መለስበቁጥጥር ሲያደርጋቸዉ እና ስልጠኑ መልሶ ካረጋገጡ በሗላ በምስጢር ተወቀረዉ ቡድን ለጊዜዉም ቢሆን እንደተበተነ (በይደር ዛሬም ሊኖር ይችላል) በሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ተዘግቧል።ስለዚህ የገብሩ እና የብርሀኑ በርሀ በማሃንዲሱ ሃይሉ ሻዉል መረባረብ አዲስ አይደለም እና ከስትራተጂ አንጻር የተጠና ከበባ ነዉ። ከዚህ በማያያዝም ልብ ልትሉት የሚገባዉ በወቅቱ በ1993 አካባቢ ወያኔ እንደ ብርጭቆ ሲሰነጠቅ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ዓባይ ፀሃየ ለስብሰባ ጠርቷቸዉ ካሰሙት ንግግር እና ዓባይ ጸሃየ እራሱ ለምን እምባ እንደተናነቀዉ በአንድ የትግራይ ተወላጅ ዘጋቢ የተላለፈዉን አስታዉሱት፣፣ ተሰብሳቢዎቹ ካሁን በፊት የማን ደጋፊዎች እንደነበሩ በሚቀጥለዉ እትም “ዘገባዉ እንዳለ” ለታሪክ ትዝብታችሁ እንዲዳብር በዝርዝር አቀርብላችሗለሁ፣፣ አሁን ብርሃኑ እየቀላመደ ያለዉን ዉንጀላዉ በምሳሌ እየተተቀሰዉ ያለዉ የከተማዉ የትግራይ ማሕበረሰብ ከቅንጅት በፊት በወያኔ ላይ የነበረዉን እምነቱ በትክክል ልትረዱት ትችላላችሁ፤፤ ስለዚህ ኢንጂነሩ ያዲስ አበባ የትግራይ ማሕበረሰብ ተወላጆች ሳይቀሩ ቅንጅትን መርጧል ማለታቸዉ አስመሰግናቸዋል እንጂ እንዴት ጸረ ትግራይ ሊያሰኛቸዉ ይችላል? የሰጡት ድምፅ ለኛዉ ለወያኔዎች ነዉ ብሎ መለስ ሲደሰኩር፤ በበኩላቸዉ ቅንጅትን የወከሉ መሃንዲስ ሃይሉ ሻዉል የለም ለኛ ለቅንጅት ነበር ድምፆቻቸዉ የሰጡት ብለዉ ቢሉ ምን ነዉር አለዉና ነዉ እነ ብርሃኑ እነ ገብሩ በመኢአድ መሪ ላይ ዓይናቸዉ ደም ለብሶ ለቁጣ እና ዉንጀላ ሊሰነዝሩ የበቁት? እኚህ ወንጀለኞች በጣም ቀለዱብን አይደል! ሆሆሆሆሆ! ዳሩ እነሱ ምን ያርጉ! ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች በዉጭም በዉስጥ አገርም እንደ አሸን እስከፈሉ ድረስ እዉነታቸዉ ነዉ፤ እነሱ ምን ያድርጉ? የ17 ዓመት ሙሉ የበረሃ ንገስታት ሆነዉ በሕዝብ ደም የነገዱ ወረበሎች፣ የስንቱን ሺህ ሕዝብ ደም አፍስሰዉ፣ ንብረት ሕይወት አፈናቅለዉ፣ አጣልተዉ፣ ኣባልተዉ አቀያይመዉ እና የሰዉ ልጅ በእሳትና በጋለ ሳንጃ ያቃጠሉ “ደናቁርት/beasts” ፍርድ ቤት የሚባል መቸም ቢሆን አለቅላቂዎች አስካሉ ድረስ ፍትህ አያዩ! በእስር ይልቅ ተደላድለዉ በሞቀ ትዳር እና ሕይወት ነጻ የዉጭ አገር የሽርሽር ሕይወት በመኖ ተደላድለዉ እየኖሩ ነዉ እነሱ ምን በደሉ? ይህ ለሰለባዎቻቸዉ የሚያበሳጭ እና የሚያቃጥል ሌላ ተጨማሪ ብትር እና ግፍ የሚየቀብሉዋቸዉ የኛዎቹ ናቸዉ “ከመሃላችን” ያሉት! ወገኖቼ፤- ገራፊዎቻቸዉ እና ጨቋኞቻቸዉ በነፃነት እንዲህ እየተዝናኑ ተንደላቀዉ ሲኖሩ የታዘቡ ሰለባዎቻቸዉ ዉስጣዊ ሕሊናቸዉ ምን እንደሚሰማቸዉ አስቡት! ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት መቅረብ እና መጠየቁስ ይቅር እኔን ሁሌ የደንቀኝ ግን “ዛሬም ኑ እና እንደ ግመል ጎትቱን” የሚሉ “አርጋጆች” እና “አለጥላጭ ወገቦች” ከማሃላችን ዉስጥ እንደ ሰንበሌጥ በቅለዉ እየተወዛወዙ የፍትህ መንገድ እንዳይታይ ሆን ብለዉ የነዚህ ወንጀለኞች ክብር እና ዝና እንዳይነካ የሚያራግቡትን ክፍሎችን ደጋግሜ ስታዘብ በቃላት ለመግለጸስ በሚከብድ ባገር እና በወገን ወንጀል የፈጸሙ እንኚህ ወንጀለኞች ዛሬ በኢትዬዖጵያዊያን እና በኢትዬያዊ የድርጅት መሪዎች ላይ የተካኑበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በድጋሚ ትግራይ ዉስጥ በትግራይ ሕብረተሰብ ተገኝተዉ ብርሃኑ እና ገብሩ አስራት ቀዳሚ አጀንዳቸዉ ያደረጉት የመወያያ አጀንዳ “መኢአድ/ሃይሉ ሻዉል” መሆኑን ዛሬም ያላንዳች ሃፍረት/ይሉኝታ ሲጠመዱ ዘገባዉን ማንበብ እዉነትም እነሱ ምን ያድርጉ ያሰኛል? በኔ ይሁንባችሁ “ለመጣዉ ሁሉ አርጋጆች እስካሉን ድረስ ወንጀለኞቹ ፍርድ ቤት የሚባል አያዩም!” በከበባ እና በወከባ አጠፋነዉ ብሉዉ የበተኑት እንዲሁም ግፍ ፈጽመዉበት የትም የተበታተነዉ ኢትዬጵያዊነቱ እና ሉአላዊ ክበሩ የተነካዉ ክፍል ዛሬም ባንድነት በመቆም እነዚህን ብሄራዊ ወንጀሎኞች ወደ ዓለም አቀፍም ይሁን አገር አቀፍ ፍርድ ቤት ጎትቶ ለማስቀጥት ሁሌም አትኩሮቱ በዛዉ ማድረግ አልቻለም፣፣ እነዚህ ወንጀለኞች ፖለቲካዉን እንደ ሽፋን ተጠቅመዉ የመተንኮስ ሱሳቸዉን ካላቆሙ እኛ የነዚህ ወንጀለኞች ሰለባ የሆንን ክፍሎች ሁሌም እየቀለዱብን እየተዘለፍን የምናርፍበት ምክንያት በፍጹም አይታየኝም፣፣ የነዚህ ክፍሎች በፖለቲካዉ መድረክ መልሰዉ ማንሰራራት የዘለፋ ዘመቻዉ ሰይፋቸዉ በድጋሚ በማን ላይ አዝምሞ እንዳለ ማጤን “ደመናዉ የዝናሙ መምጣት ይጠቁማል” እና ጠንቀቅ ማሉቱ አይጎዳም ሚል ምክር አለኝ። ሕዝቡን ለድጋሚ ማስጠንቀቅ አስፈላጊ ነዉ እላለሁ፣፣ መግቢያ በሮች ሁሉ ለነዚህ ወንጀለኞች ዝግ እንዲሆኑ በብርቱ መከላለከል ዛሬም ያስፈልጋል፣፣ በዓረና እና በስየ በኩል ጸረ ሃይሉ ሻዉልም ይሁን ጸረ ታየ ወልደሰማያት እና በሌሎች ኢትዬጵያዊያን ድርጅቶች እየተካሄደ የለዉ የጥላቻ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ የዋዛ ሳይሆን የተቀነባበረ የወያኔ ስልት መሆኑን ኢትዬጵያዊያን ካሁኑኑ ማወቅ ይገባል እላለሁ፣፣ ቅንጅት/(መ ኢ አ ድ) የመለስ ቡድ እና የገብሩ አስራት ቡድኖች እነዴት በማሃል አስገብተዉ የጥቃት እና የመከራከርያ ማአከላዊ “ኢላማቸዉ” እያደረጉት እንደሚገኙ በመረጃ ላስግፍ እና ቅንጀት/መ ኢአድን እንደ “አህያ” ቆጥረዉ ሁለቱም የወያኔ የጅቦች ቡድን በማሃል አስገብተዉ እንዴት ከበዉ እንደሚቀጠቅጡት አስደግፌ በመረጃ ልሰናበት። ከዚህ በታች የቀረበዉ ዘገባ በአሜርካ ድምፅ የትግር ክፍለ ጊዜ የቀረበ አብርሃም ገብረመድህን የተባለ የመለስ ተጠሪ እና አሁን እንጂነር ሃይሉን በጸረ ትግራይ ሕዝብ በሃሰት እየከሰሰ ያለዉ የዓረናዉ ምክትል ሊቀመንበር ብርሃኑ በርሔ ያደረጉት ክርክር ነዉ።ቃለ መጠይቁ ቀረበዉ በትረ ስልጣን በተባለዉ ያሜረካ ድምፅ የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ጋዜጠኛ ነዉ። ይሄዉና፦ By Betre Siltan Washington 04/03/2009 Ethiopians who represent the ideologies of the ruling Tigray People’s Liberation Front and the year-old Arena Tigray for Sovereignty and Democracy parties clashed in a heated radio debate on the Tigrigna service’s Crossfire show on Monday. Abraham Gebremedhin of the ruling TPLF and Berhanu Berhe, a leader of Arena Tigray for Sovereignty and Democracy, argued politics and purposes in a program moderated by Betre Siltan. Abraham says Arena is an agent of Kinijit, the 2005 coalition of political opposition to the EPRDF. Berhanu says the TPLF tries to dominate Ethiopia’s political discussion. “Arena Tigray is not an alternative party for the simple reason that all its programs are included in the EPRDF's policies," said Abraham. He called Arena-Tigray the mouth piece of Kinijit, the opposition coalition that was created during the 2005 Ethiopian election.” ሲል የመለስ ዜናዊ የወያኔዉ ቡድን ቅንጅትን/መ ኢአድን ማአከላዊ ጠላት ቆጥሮ ዓረና ከቅንጅት ጋር መጠጋቱ ሲወነጅለዉ፤- የዓረናዉ ብርሃኑ በርሄ ደግሞ ቅንጀት በ1995 በሊቀመንበርነት የመሩትን ማሃንዲስ ሃይሉ ሻዉልን (ቅንጅት/መ ኢአአድ)ን የትግራይ ጠላት ሲል በቅርቡ ወንጇሏቸዋል። ከዚህ የምንረዳዉ ቢኖር ቅንጅትን በጠንካራ ክንድ የገነባዉ የመኢአድ አመራር አባላት ዛሬም በሁለቱ ወያኔዎች እንደ ማካላዊ ጠላታቸዉ እንድተገነዘቡት ያስፈልጋል። አመሰግናለሁ። /-/ ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com