Thursday, October 2, 2008

ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ዕዉራን ንቦች


ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ዕዉራን ንቦች ጌታቸዉ ረዳ ዉሸት አገር ይፈታል ቅማል ሱሪ ያስፈታል የሚለዉ ምሳሌ ለዘመናት ሲደመጥ የኖረ ቢሆንም ለምሳሌዉ ተስማሚ ጊዜ ያገኘበት ጊዜ ቢኖር “ዉሸቱን ተቀብሎ በጭፍን የማመንን ባሕሪ፤ክህደትን፤አጭባሪነትንና፤ እየዋሹ ያለማፈርን፤በዛዉ ሐፍረተ-ቢስነት በሕሪ የመቀጠልን” አጠቃልሎ እነኚህ ነዉር የሆኑ ባህሪዎች እንደ ባሕል ተደርጎ የተወሰደ ዘመን እንደዛሬዉ ዘመን ከቶ የነበረ አይመስለኝም።
በ17 ዓመት ዉስጥ የታዘብኩት ባርኔጣቸዉን እያነሱ “ኖር” ብለዉ ቀጤማ ጎዝጉዘዉ ዉሸትን የሚቀበሉ ዜጎች ወየነ ወደ መንግሥትነት ከተለወጠ በሗላ ቁጥራቸዉ እያደገ መሄዱን ነዉ። የታሪክ ዘለፋ ብሎም ታላላቅ አዛዉንትን ሊቃዉንትን፤አርበኞችና ጀግኖችን የነገሥታትን እና የጀግኖች መታሰቢያ ሀዉልቶችን፤መቃብሮች እና በሀገር ዉስጥ የተፈጠሩ ፊደላትንና ቋንቋን የማጣጣል ባህል እና አረጋዊያንን የመዳፋር ባህሪ ባጠቃላይ-(“ዉሸት”-) የተጀመረዉ፤ በኤርትራ ነፃ አዉጪዎች ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ግምባሮች ወርዶ በወያኔ ተንከባካቢነት ነብስ ዘርቶ፤ የወጣላቸዉ የዉሸት ሰባኪያን በከፍተኛ ፍጥነት እየተራቡ/እያደጉ እንደመጡ አስተዉለናል።ዉሸት እንደ አዲስ ቅጂ/ሞዴል ሆነ እና “ስልጡን ፖለቲካ” ብለዉ ስመ-ክርስትና አወጡለት። ወያኔም፤ሻዕቢያም ሆነ በሕዝብ የጅምላ ግድያ እጁን በደም የነከረዉ እስካሁን ድረስ ከሳሽ አጥቶ የታሪክ ቀኑን እየጠበቀ ያለዉ “ኦነግ” እና የመሳሰሉት የፖለቲካ ተዉሳኮች፤ በኢትየጵያ ምድር ዉስጥ የታዩት የገዢ መደቦችን ሥልጣን ለማረጋገጥ ሲባል ወደ ሗላ ሩቅ ያለፉት ዘመናት በታዩት እርስ በረስ የተገፋፋንበትን እና የተፈጥሮ ሕግጋት ሆኖ ያገር ግንባታን/ታሪካዊ ክስተቶችን/ ለማፋጠን የተከናወኑበት ሂደቶችን በሕዝብ መሃል እንደተደረጉ ግጭቶች እያስመሰሉ በዘረኛ ስበከት ለሥልጣን ጥማቸዉ “በዉሸት” ሕዝቡን እያምታቱ ለስደት እና ለሞት ዳርገዉ በአዲሱ ትዉልድ- “በወጣቱ” ሕሊና ዉስጥም ይህንኑ ዉሸት አሰርገዉ በመመገብ ጥላቻዉ ብጥብጡ ስደቱ እና ሞቱ እንዲቀጥል ዉሸት መሳሪያቸዉ አድርገዉ ሕዘብ ከሕዝብ ሲያጋጩ ይገኛሉ።
ለምሳሌ፤- ባለፈዉ የቅንጅት መሪዎች ነን ብለዉ “እናንተን-አንድ ለማድረግ መጣን” በሚል ሽፋን/ዉሸት እኛኑን አጣልተዉ አራርቀዉ ከምንወዳቸዉ እና ከምናከብራቸዉ ወዳጆቻችን ሳይቀር በዉሸት ስበከታቸዉ አለያይተዉን በጋራ አንድ ሆነዉ መጥተዉ እነሱም ራሳቸዉ ተበጣብጠዉ ወደ መጡበት ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለሱ አንዳንድ አዉራዎቻቸዉም አሜሪካን አገር ጥገኝነት ጠይቀዉ በመቅረት ዉሸታቸዉን በረቀቀ/በአታለይ መንገድ ሳይሆን በግልጽ እየዋሹ፤ ዉሸታቸዉን እንደ ባሕል ተቀብለዉ የሚያስተናግዷቸዉ እዉቅ የዉሸት ኢነተርፕረነሮች አንደ አሸን ፈለተዋል።
ያለፈዉ ታሪካችነን ስንመለከት የአንድ ትዉልድ እልቂት ሊከናወን የቻለዉ በሁለት ዓመት ዉስጥ ነበር።የአንድ ትዉልድ እለቂት ለማከናወን ሚና የተጫወተዉ “ዉሸትና ማጭበርበርን” ተጠቅሞ ህዘቡን በማደንዘዝ የሥልጣን ጥምን” ለማርካት ነበር። ዋሾች መዋሸት ብቻ ሳይሆን መንግሥታዊ ሰገነት ከያዙ ግድያ ዉስጥም ይገባሉ።ይህም ማለት እንደሰዉ ትክክለኛዉ የፖለቲካ ጨዋታ ሊጫወቱ አይፈቅዱም።ሕጉን ተከትሎ ልጫወት የሚለዉን ከፊት ለፊት ደንቅሮ የሚቆምባቸዉን ሁሉ የወሽት ድሩ ተጠቅሞ ሌሎቹን ጥሎ ከጫዋታ ዉጭ ለማድረግ ይሞክራል።በሂደቱ ለፍትህ የሚደረጉ ትንቅንቆች ይበለሻሉ ፤ወይም ዋሾዉ ስልጣን ለይ ወጥተዉ ሌላ የመከራ ጊዜ ይቀጥላል ወይንም ህዝቡን በስቃይ እየገረፈ ያለዉን ስርዓት ዕድሜዉን እንዲረዝምለት አስተዋጽኦ ያደርጋል። በቅርብ የታዘብነዉ ትምህርት-እናንተን ለማስታረቅ እና አንድ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መጣን ያሉንን ዉሸተኞች እኛኑን ለጥገኝነት ሽፋን ተጠቅመዉ፤ አንድ ማድረግ ቀርቶ አብረዉ እንደ መጡ አብረዉ መመለስ ያቃታቸዉ ምክንያት ሲጠየቁም “እናተ ሁሉ ምንድናችሁ ማለት ነዉ? ለምን ተነጥላቸሁ ቀራችሁ ስትሉን እኮ አናነተን ራሰችሁን ሁሉ እኮ እየሰደባችሁ ነዉ?!” ብለዉ ሲመልሱ፤ እንደዚህ ዓይነት የዓለም--ምፅዓት ታይቶም ተሰምቶም አያቅም። ይህ አስገራሚ ክንዉን ሲፈጸም ቁጥሩ በጣም የማይናቅ ሕዝብ ዕቅፍ አበባ እያበረከተ ቀጤማ ይነሰንስላቸዉ ነበር። ደማቅ ዉሸት ሲዋሹም ደማቅ ጭብጨባ ይደረግላቸዉ ነበር።በዉሸት የታካኑ ቁንጮ የመድረክ ኢነተርፐሬኖሮችም አዟዟሪ/አስጎብኚ አድርገዉ ዉሸትን እንዲቀበል ህዘብን የማደንዘዙ ሥራ ተሰርቷል።አሁን ወደ ሗላ መለስ ብለችሁ ስታስተዉሉት እኮ፤ በዉነት አስገራሚ ትዕይንትና “ታላቁ ሽወዳ” የሚሰኝ መጸሃፍ የሚያስጽፍ የፖለቲካ ሸቀጥ ነበር።
ዋሾች ትልቁ እና ዋናዉ ሚናቸዉ ተከታይን ማደንዘዝ ነዉ።አድማጩን አስቀድሞ ከሰለበዉ፤ በሕሊና ስካር ዉስጥ የሚዋልል የደነዘዘ አድማጭ እዉነት ዉሸት ይደበላለቅበት እና ለዉሸትም ለእዉነትም እኩል ቦታ ይሰጣል።ሲዋሹ ያንጨበጭብላቸዋል - እወነቱን ሲናገሩም ያንጨበጭብላቸዋል።ለነሱ ሁሉም እኩል ነዉ። ሂትለር ደማቅ ዉሸቱን ሲዋሽ ደማቅ ጭብጨባና ጭሆት ሲለገስለት የነበረዉ አድማጩን አስቀድሞ በዉሸት በማደንዘዙ ነዉ። በዋሸ ቁጥር አድማጩ የዉሸት ሱሰኛ እየሆነ በመሄዱ፤ ሂትለር መድረክ በጠራ ቁጥር ድምጹን ለማዳመጥ ይቋምጡ ነበር።ጨካኙ የኛኑ ኮሎኔል በወታደራዊ ልበሱ የብዙዉ ሰዉ ዓይን ማርኳል።
እነዚህኞቹም እናንተን ለማስታረቅ ነዉ የመጣነዉ ብለዉ ሲሰብኳቸዉ፤ ተከታዮቻቸዉ የእዉነት መስሏቸዉ ጆሯቸዉ ተማርኮ የዉሸተኞቹ ስበከት ሱሰኞች በመሆን በቃላት ሊገለጥ የማይችል ካበድ የሕሊና እከክ አተርፈዉ፤ ዛሬ ዋሽዎቹ ስበሰባ ባዘጋጁ ቁጥር ሮጦ ለማዳመጥ ሲንጋጉ ይታያሉ። በስነ ሕሊና ሕግ በየዋህ አድማጭ ላይ ወንጀል ፈጸመዋል ማለት ይቻል እንደሆን አላቅም አንጂ -የሆነ ጉዳት እነዳደረሱባቸዉ አልጠራጠርም። የአገሪቱን ፖለቲካ አስተካክላለሁ ብለህ በግምበር ተሰልፌአለሁ ብለኸን እናንተን ለማስተረቅ ከ ኢትዮጵያ መጥቻለሁ(ለመምጣቴም ምክንያት የኸዉ ነዉ) ብለህ አንተ እና ጛደኛህ ለምን አዚህ ለመቅረት ወሰንክ ተብሎ ስለተጠየቀ “እናንተም ሁሉ እኮ ራሳችሁን እየሰደባችሁ ነዉ! ቀረሁ አልቀረሁ የራሴ ጉዳይ ነዉ፤ ምን ያገባችሗል?”ለምን ተጠየቅኩ ብሎ በድንፋታ ሲመልስ “ለምን በኛ ስም መጣህ? “ዋሻኸን”።ከዋሸህም፦ ከፖለቲካ መድረክ ራሰክን አስወግድ” ብሎ ከመመለስ ይልቅ ላከበረዉ ህዝብ እንደዚያ ዋሽቶ እነሱን አሳንሶ ሲያቀላቸዉ (ግርምቢጥስያ ማይ ንዓቐብ!) ደማቅ ጭብጨባ ለገሱለት። ይሄ በሽታ ነዉ። ስም ያልተሰጠዉ በሽታ።እንደዚህ ዓይነቱ ለዉሸት ራሱን የሚያስገዛ ምቹ ሕዝብ እየበረከተ ባለበት ወቅት ከቶ እንዴት ሕዘባችን ወዳጁ እና ጠላቱን ለይቶ አዉቋል እያልን እንሰብካለን? ብሎ ለሚጠይቅ መልስ የማገኝለት አይመስለኝም።
የምንቆጭለትን ከባዱን ኢትጵዊ ባሕላችን ያለ መዋሸትን ተረግጦ ዉሸትን ያክል ትልቁ አስነዋሪ ሸክም በጫንቃቸዉ ተሸክመዉ ወደ ባሕር ማዶ ሲመጡ ትከሻቸዉ በስፋት አለጥልጠዉ አመቻችተዉ የሚረከቧቸዉ የቁም ሙታን ብብዛት እንዳሉ አላጡትም ነበር’ና አገር ዉስጥ የ “የሙት -ከተማ” የትግሉን አድማ አንዳስወረዱት ሁሉ እዚህም መጥተዉ አንድነታችነን አደፈረሱት። ወያኔ ሲያቀብጠዉ በሳጥን ድምጽ ዕድሌን ልሞክር ብሎ ገብቶ አክ እንተፍ መባሉን መርዶዉን ሲሰማ፤- ርሸናዉን አጧጥፎ አሸነፍኩ በማለት “ነቨር-ኤገይን!” (አይደገምም!አይታለምም!) ያለንን የጫካዉ ሰዉ ወያኔን ማዶ ሆኖችሁ መታገል “ነዉር” ነዉ እያለ ሲየዋግዘንና “ሲያንኳስሰን” የነበረዉ “ብርሃኑ ነጋ” -ትግሉን መምራት- ከማዶ ሆኖ ነዉ ብሎ እኔ የምመራዉ ድርጅት አለ እና ይህ ቅጽ/ፎረም ሞልታችሁ እኔን ተከተሉ እያለ በየ አሜሪካን ክፍለሀገሮች ተዟዙሮ ሲቦተልክባቸዉ አሰየዉ አሉት። ስለዋሾቹ ማንሳት ቢሰለቸኝም የዕምብርቱ ችግር እነሱ ስለሆኑ ብንወድም ብንጠላም የምንመለስበት ሐዲድ ሆኖ እናገኘዋለን።
አንድነት ይፈጠር ሲባል፤ለግብር ይዉጣ ተለጣጥፋችሁ ርገጉ ማለት መሆን የለበትም። ዋሾቹ ብዙ የዉሸት አድናቂና ተካታይ መቀፍቀፋቸዉን እሰካላቆሙ ድረስ እንቅፋት ለትግሉ ደንቃሮች ናቸዉና መታቀብ ካልቻሉ /ዉሸታቸዉን አስካላቆሙ/ ድረስ የብዕር ጦርነቱ የቀጥላል። አስቀድሞ ትግሉ የሚካሄደዉ በዉሸት መሆን አለበት። ወያኔም ሆነ በተቃዋሚ ስም የተደራጁት ዋሾች ሁሉ በቅደም ተከተል በአንድ እና በሁለተኛ ደረጃ አይመደቡም። ምደባቸዉ ሁለቱም በአንደኛ ደረጃ ጠላትነት ዉስጥ ነዉ። ጠላትን ለመግደል እንዲአመች ምሽግክን ለጠላት እያጋለጠ የሚያስመታህ አስቀድሞ መግደል አሾክሿኲዉን ነዉ፡ የተባለዉም ለይስሙላ አልነበረምና በዚህ ብዥታ መኖር የለበትም።
ለምንድ ነዉ ይህ ለማለት የተገደድኩት? የኢትዮጵያ ግምባር ቀደም አረጋዊ መሪዎችን፤ ምሁራንና የፖለቲካ ታጋዮችን ክብርና ስም ሲዘልፉና ከዋሾች አንደበት የሚወጣዉ የዉሸት ሰበካ ለማድመጥ ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ብዙ ዕዉራን ንቦች አሁንም አሉን። አንድ ቀን እግር ጥሎኝ በአንድ ሦስቱ ያከል የፓል-ቶክ መድረክ ገብቼ ያዳመጥኳቸዉ ረዢም ሰዓታት በጣም የሚያስገርም እና በስሜት የሚጋልብ ጭንቅላት መድረኩን ዉጦት የታዘብኩትን ልግለጽ። ለስሜታቸዉ ግፊት ዋነኛዉ መሳርያ የሚጠቀሙበት -እዛም- ቢሆን “ዉሸት” ነበር። አንዲት የዋህ በልቅሶ ስቅስቅ ብላ ስለ ኢትዮጵያ ችግር ስታለቅስ ሰምቻለሁ። ልጅቷ ሃገር ፍቅር ኖሯት ማልቀሷን የማከብራት ብሆንም፤ አሳዛኙ ክስተት ደግሞ የዋሾቹ ሰለባ ሆና እነሱን ስታሞግስ እና ለሚያስለቅሳት ያገሯ ተደጋጋሚ ችግር አነሱ አንደሚፈዉሱት አድርጋ ራሷን በእርግጠኝነት ስትሟገት መስማቴም አዘነኩላት።አነኚህ ንቦች ናቸዉ።ንቦቹ ንግሥቲቱ ወደ ጭስ ብትመራቸዉም አብረዉ ይቀቀላሉ።ዕዉራን ናቸዉና ወደ ዉሸት ቀፎ ይገባሉ።ለዚህም ነዉ በዉሸት ላይ መዝመት ለትግሉ ተቀዳሚ ፈዉስ ነዉ የምለዉ። ጽሁፌን በዚህ ስደመድም፡ለማስታወሻችሁ ይረዳ ዘንድ ታች የምታነቡት የዋሾቹን ማሕደር ጣል ላድርግና ልሰናበታችሁ።
ጠያቂ_ ከሌላኛዉ የቅንጅት ግሩፖች…. ጋር ያላችሁ ልዩነት የሌላኛዉ ግሩፕ የጭቃ ሹም አስተዳደር የምስለኔ እንዲሁም ደግሞ የጭቃ ሹም አስተዳደር አራማጆች ናቸዉ። እኛ ግን ዲሞክራቶች ነን የሚል ነዉ። ይሄንን፡ ከዚህ በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በንግግርዎም በቪኦኤ ምልልስም እንደዚሁም ጓደኛዎ ክቡር አቶ አንዳረጋቸዉ ጽጌ በኢንተርኔት ባሰፈሩት ይህነን ባተኮረ አስፍረዋል። የኔ ጥያቄ በሕዝብ ዉስጥ የሚነገር አንድ ንግግር አለ።ከዚህ በፊት የተከበሩ ደ/ር ብርሃኑ ነጋ የተከበረች ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንና ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በቀስተ ዳመና ፕረዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በቀጭን ትዛዝ ለካዉንስል ምክር ቤት እንዲሁ ሳይመረጡ በእርስዎ ዉሳኔ ብቻ አሰመርጠዋቸዋል። የሚባል ነገር አለ እና ይህነን አድረገዋል ወይ? ይህስ ካደረጉ ሌሎችን ሳልነካ በእርስዎ ላትኩርና እራስዎን የዲሞክራሲ ጠበቃ አድርገዉ ለማቆም የሚየያስችል የሕሊና ንጽህና አለዎት-ወይ?
የብርሃኑ ነጋ መለስ፦ Really, በጣም ባጭሩ ነዉ የምመልሰዉ። መጀመሪያ የጠየቁት ብርቱካንና አንዳረጋቸዉን በቀጭን ትእዛዝ የካንስል አባላት አድረገሃል ነዉ። ያለኝም በጣም አጭር መልስ ነዉ። መልሱ- “ዉሸት ነዉ!” (ብርሃኑ ከካደ በሗላም- የዕዉራን ንቦች- ጭብጨባ ይደመጣል-ጨብ!!!! ጨብ!!!! ጨብ!!!!!!!!!!!) የአንዳረጋቸዉ ጽጌ መልስ ከታማኝ (ቲቪ ቃለ በጠይቅ) አድርጎ ለብረሃኑ ነጋ መለስ የሰጠዉ እዉነታዉ ቀጥሎ ያለዉን ያንብቡ።
ታማኝ- አቶ አንዳርጋቸዉ የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባል ነበሩ ወይ? “አዎ! ከዛ በፊት የማንም ድርጅቶች አባል አልነበርኩም።ልወጣ ስል ነዉ ብረሃኑ መጥቶ ይሄ ሁሉ ስራ ሰርተህ ሰዉስ ምን ይላል (አንዳረጋቸዉ ሁኔታዉ እያሳቀው መሰለኝ አግርሞት ሳቅ ሲስቅ ይደመጣል/ይታያል)…እዚች ላይ ፎርም ሙላ እና ሞልተህ ብትሄድ ይሻላሃል፤ ብሎ ብርሃኑ ነዉ የቀስተ ዳመና ፎርም አስሞልቶኝ ነበር። እና ቀስተ-ዳመና ሰዎች ወደ ላዕላይ ምክር ቤት በሚያስገባበት ሰዓት ላይ “ኦል-ሬዲ” እኔ ዉጭ ከወጣሁ በሗላ የስራ አስፈጻሚ ኮሞቴ አባል አድረገዉ አስመርጠዉኝ ነበር። እኔ በሌለሁበት ነዉ ምርጫዉ የተካሄደዉ። አቶ ዳኒኤልም ነበር። እኔ በሌለሁበት ነዉ ምርጫዉ የተካሄደዉ። አቶ ዳኒኤልም ሌሎችም በስልክ ነግረዉኛል፡ምን ዓይነት ምርጫ እንደነበረ። ይሄ በ “ኖሚነሽን” ከሌሎቹ ሰዎችም ጋር እንድወዳደር አይደለም የሆነዉ በቀጥታ በ“አክላሜሽን” ነዉ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያደረጉኝ።”
(እንግዲህ ከላይ ብርሃኑ በሕዝብ ፊት የሰጠዉ መልስ እና ሌሎችን በምሰለኔነት ሗላቀርነት ሲከስስ- አወዳድሩትና ገምግሙት-)።
ብርሃኑ ነጋ፦ “ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካ ትግል ዉስጥ ከገባሁ አንድ 6 ወር 7 ወር ቢሆን ነዉ።ከዚያ በፊት ያሉት ነገሮች ብትጠይቁኝ “አላቅላችሁም!” ነዉ የምላቸወሁ። “ሶ” ኮንተይን/ (ኮንስንት..?) የምናደርገዉ በነዚህ ጊዜዎች ነዉ።”
ብረሃኑ ነጋ፦”ኢሰንሺያሊ-ሞር ዛን ኤኒቲንግ ኤልስ/ ወደ ትግሉ ልገባ የፈለግኩት በኢኮኖሚዉ ምክንያት ነዉ”:
{አንባቢ-ልብ በሉ።ሰዉየዉ የገባዉ ቅደሚያ ኮኖሚዉ አሳስቦት እንጂ ፖለቲካዉ አልነበረም። ኢኮኖሚዉ አድጎ በልጽጎ ቢሆን ወያኔ ያፈለገዉ “ግራዚያኒም ሆነ ፈራንኮ፤ሂተልርም ይሁን ፖልፔት” ፖለቲካ ዉስጥ ባልገባ ነበር ነበር ማለት ነዉ። ዓይኑ ትኩረቱ -ሞር ዛን ኤኒቲንግ ኤልስ- “ኢኮኖሚዉ” ላይ ነብርና ወደ ትግሉ ከ6 ወር በፊት ወደ ፖለቲካዉ ሊገባ የቻለዉና በዋናነትያሳሰበዉ)። ግምገማዉ ለናንተዉ ልተዉ።
ብረሃኑ ነጋ። ጦርነት ላይ አንገባም ስትሉ ኢሕአዴግ ጋር ተስማምታችሗል ወይ? የሚል ጥያቄ አለ። … የተስማማንበት ነገር የለም፡፤ አሱ ማለት ከሆነ። እኛ ከዚህ ፖለቲካ ዉስጥ የገባነዉ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ነዉ።ጦርነት ለማካሄድ የሚፈልግ ይችላል። ዕድሉ መሞከር ይችላል።ጦርነት የሚፈልግ ጦርነት ካለበት ቦታ ሄዶ ይዋጋ።እኔ አንድ አድቫይስ የማደርገዉ፤ ጦርነት ሚፈለግ ሰዉ አንተንም ልጆችህንም አሱም ለጆቹንም ጨምሮ የሚታገል መሆን አለበት ነዉ የምለዉ። ሌላ የድሃ ገበሬ ልጅ የሚያታገልበትና ከዉጭ ሆኖ አመራር የሚሰጥበት ዓይነት ጦርነት ካሁን በሗላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያቆመ መሰለኝ።
(እንግዲህ ዶክተሩ የራሱን ድርጅት መስርቶ በ አመራር ደረጃ ተቀምጦ እዉራን ንቦቹን እያደናበረ ዉጭ አገር ነዉ የለዉና- የሚቀጥለዉ ተዕይንት አበረን ለማየት ያብቃን።) ዉሸቱ የመጽሃፍ ክምር ሊሆንብን ነዉና በዚህ ላብቃ።አምላክ ኢትየጵያን ይጠብቅ//-// www.ethiopiansemay.blogspot.com