Friday, June 9, 2023

እጉያው ውስጥ ሆነው በጣምራ ደምቀው እያበሩለት ያሉት ጤፍ የምታስለቅመዋ ጨረቃ እና የሰብአ ሰገል ኮዋክብቶችን ብርሃን ማየት ያቃተው የአማራ ወጣት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/9/23

 

እጉያው ውስጥ ሆነው በጣምራ ደምቀው እያበሩለት ያሉት ጤፍ የምታስለቅመዋ ጨረቃ እና የሰብአ ሰገል ኮዋክብቶችን ብርሃን ማየት ያቃተው የአማራ ወጣት 

                                            ጌታቸው ረዳ   

Ethiopian Semay

6/9/23

ከአውሮጳ ጉብኝቴ መልስ የታዘብኩት አዲስ ነገር ቢኖር በ ጋ*ቹ የ16ኛው ክ/ዘመን አረመኔዊ ጭንቅላት እየተመራ ያለው የ21ኛው ክ/ዘመን የኦሮሙማው ቡድን የጭካኔው እርከን ወደ ለየለት የሙሶለኒና የግራኝ አሕመድ ባህሪ ተሸጋግሮ የገዳም መነኮሳትን ወደ መጨፍጨፍ መሸጋገሩ ሲሆን የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ጎጃም ውስጥ በደብረኤሊያስ ወረዳ የሚገኘው የስላሴ ገዳም መነኮሳትና ካሕናት እንደነበሩ ከዳሰስኳቸው ዜናዎች አንዱ ሲሆን፡ ከዚህ በተመሳሳይ አዲስ አበባ ውስጥ ሸገር በሚባል የኦሮሙማ የቀድሞ ፋሺሰት ጣሊያን ያቀደው አዲስ አባባ የአማራ መናገሻ በሚል ሴራ የተሞላበት ዋና ከተማ የማጥፋት አገር ምስረታ ትልም ተንተርሶ ብዛት ያላቸው ቤተክርስትያናትና መስጊዶች መፍረሳቸውን በቪዲዮ ስመለከት መንግስትን መገልበጥ የሚያስችል አመጽ ሊያስነሳ ያለመቻሉ አስገርሞኛል።

ሌላው በወያኔ ፋሺሰቶች ትምህርት የተቃኙ የትግራይ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተብየ ካድሬዎች የትግራይ ሲኖዶስ መስርተዋል የሚል ዜና ስሰማ የአብይ  አሕመድና የአባ ማትያስ በውስጥ የቀጥሉበት ቡራኬ እንደተሰጣቸው ግልጽ ነው። ምክንያቱም የትግራይ ቀሳውስት የሚገበያዩት በአገሪቷ ገንዘብና ባንክ እንዲሁም መብራት ነዳጅና ስልክ አግልግሎት ሲሆን ተግንጥለናል ብለው ሲያውጁ አገር ሆነናል ማለት ነው። መጀመሪያ ወያኔ ተገንጥያለሁ ብሎ በወታደሩ ላይ ጥቃት እንደፈጸመበት እና መንግሥት ተብየው የእርምጃ አፀፋ እንደወሰደበት ሁሉ ነው። ቄሶቹተገንጥለናል ሲሉ የፖለቲካና አገር የማፍረስ ሴራ ውስጥ ስለገቡ የተጠቀሱት መንግስታዊና አገራዊ አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ በአዋጅ/በነጋሪት ጋዜጣ አሳውጆ ማገድ ይችል ነበር። እነዚህ አገልገሎቶች እንዲያገኙ በሚተባበሩት ላይም እርምጃና እገዳ ማድረግ በቻለ ነበር።  ሆኖም ሴራው ግልጽ የሆነ የውስጥ ስራ መሆኑን በሌላ ጊዜ የምምለስበት ቢሆንም  እንድታውቁት በእግረ መንገዴ ልጠቁማችሁ እፈልጋለሁ።

አብሮ የተያያዘው ትዝበቴ ደግሞ፡ይህ ሁሉ ጭካኔ እየተፈጸመ እያየ እጉያው ውስጥ ሆነው ከጭለማው እንዲወጣ እያበሩለት ያሉት ኮዋክብቶች ማየት ያቃተው የአማራው ወጣት ወደ ብርሃኑ ያለመጠጋቱ ሌለው ትዝብቴ ነው።

እንደምን ሰነበታችሁ!

ሰሞኑን ስለ ደህንነቴ መልካም ምኞት የተመኛችሁልኝ ሁላችሁም አመሰግናለሁ።

ኦሮሞዎቹና ትግሬዎቹ (በጅምላ አትጥራ የሚሉ ብዙ የምሁራን ደናቁርትና ይህ አባባል የማይዋጥላቸው ብዙ ሰዎች አሉና ወደዳችሁም ጠላችሁም ሃቁ ያ ነውና እንደወረደ አንብቡኝ) እነዚህ ነገዶች ከሴረኞች ጋር በተባባሪነት ራሳቸውን እየጎዱ እና አገራችንንም ጭምር ከችግር ወደ ሌላ የባሰ ማጥ እየወሰድዋት ነው። ኢትዮጵያ ከብዙ ዘመናት መረጋጋት በሗላ አሁን ወዳለቺው የመፍረስ አደጋ የተጋረጠችበት ምክንያት ለምንድነው?  የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ሁላችን ሊረዳን ይገባል። መነሻው ምክንያት የሚከተለው ነው።

 

ቀዳሚ ተዋናዮች ዓድዋ ላይ የተሸነፈው የአውሮጳ የነጮች ጦር ፤ያሸነፈቻቸው ኢትዮጵያ የአማራውና የኦርዶክስ ስሪት ነች በለው አምነዋል። ስለሆነም መፍረስ አለባት ብለው ወስነዋል። ይህንን ለማከናወን “ባንዳ” የምንላቸው የውስጥ ተዋናያን ቅጥረኞቻቸው የትግራይ ወያኔ መሪዎችና የኦሮሙማው ቡድን (ኦነግ/ኦፒዲኦ/እስላማዊ ሃይሎች እና ጴንጤዎች) ለ35 አመት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየተካሄደው ባለው ትንቅንቅ ተዋናዮች ናቸው። ስለሆነም በዓድዋ የጣሊያን መሸነፍ ላይ በመሪነትና በሱታፌ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አማራ እና ኦርቶዶክስ ለመበቀል እንደሆነ በመጻሕፈቶቻቸው ነግረውናል። አዲሱ ትውልድ ይህንን ጠንቅቆ መገንዘብ አለበት።

ይህንን ለማከናወን ወጣቱ ምንም አይነት አገራዊነት እንዳይኖሮው በጥብቅ ለ27 አመት በብከላ (በሳብቨርዥን) ሰርተውበታል። አገራዊነት ስሜት እንዳይኖሮው የሚጠመድበት የሃይማኖት (ጴንጤ…ኢሉሙናቲ፤…ወዘተ)፤ የእፅ ሱሰኛነትና የግብረሰዶም የወሲብ ወጥመዶች አዘጋጅተው ያለ አላማ እና ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት እንዲኖሮው አንዲላሽቅ አድርገዋል። የተማረውም ካልተማረው በባሰ መልኩ እንዲደድብ የተለያዩ ወጥመዶች ገብተውበት ራሱን በማታለል በማያየው በሰንሰልት ታስሮ ሲንከላወት አይተናል (ያውም ለረዢም አመታት!!)

ያልነቃው ማሕበረሰብም ሃሳቦችን በሃሳብ ለመዋጋት እንዳይችል አድርገው “በ ዩቱብ” ብዙ የሕሊና ቀውሰኞችን እንዲፈሩ አድርገዋል። በሳል የነቁ አገራዊያን አርበኞችም በተለያዩ ሴራዎች እንዳይደመጡ በሴራ እንዲገለሉ  ተደርገዋል፣ እንኚህ  በተለይ ከወጣቱ ሕሊና ተሰርዘዋል፤ አያውቋቸውም፡ ባጭሩ የነቁ አገራዊያን  በጫጫታ እንዲሟሙ ሆኗል።

 በመጨረሻም በሕብረተሰቡ ተቀባይነት የነበራቸው የታወቁ አንቂዎች በሚያሳፍር ሁኔታ አገር በማፍረስ ላይ ላላው ቡድን ወግነው ብዙ ብልሽት ካደረጉ በሗላ መልሰው ተቃዋሚ ሆነው እያየናቸው ነው።

ይህ ሁሉ ቅዠት መነሻዎች የየራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸውም በዚህ መሃል የጀርባ ተዋናዮች የእንግሊዝ ሰላዮች (ኤስ ኣይ ኤስ (ኤም 16) እና ሲ ኣይ ኤ የተባለው የአሜረካ የስለላ ድርጅት ከጀርባ ኣሉበት።

 እንግሊዝ አገር በቆየሁበት ወቅት “ኤስ ኣይ ኤስ” ወይንም “ኤም 16” የተባለው ድርጅት የቀጠራቸው ኢትዮጵያዊያን ከምድር በታች በታነጸ ክፍል ገብተው አገራቸውን ለማፍረስ በስለላ ሥራ ተቀጥረው በድርጅቱ ቃል ኪዳን መሃላ እንዲገቡ እንዴት እንደተመለሙሉ እና ኢትዮጵያ ለማፍረስ አማራውና ኦርቶዶክስን ማፍረስ ቀዳሚ ዓላማቸው አንደሆነ እና ወደ አዳራሹ “ውሰተ መርየት” ሲገቡ በልዩ ፍርሃት የተቀላቀለበት ስሜት ሆነው ጠረጴዛ ላይ ተደርድረው ያዩዋቸው በመላው ዓለም የተመሰረቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሽምቅ ተዋጊ ባነሮችና ሰንደቃላማዎች  ለወደፊቱ እንዲፈርሱ ኢላማ ውስጥ የገቡ አገሮች ምቹ መሳርያዎች እንዲሆኑ ተመልምለው ከነበሩት ውስጥ ትውስታቸው ሰያጫውቱኝ እንደ ታምር በህይወት የቆዩ ቢሆኑም በዚያ ሂደት ብዙ ሂደት ተራምደው ወደ ሕሊናቸው የተመለሱ ሸርተት ባሉ ተመልማዮችም ላይ በምስጢር የግድያ እርምጃ እንዴት እንደተወሰደባቸው  ሲያጨውቱኝ እጅግ ነበር በተመስጦ ያደመጥኩት።

ይህ ድርጅት  አንዲህ  ይላል፡

“SIS – የተባበሩት ኪንግዶም ሚስጥራዊ መረጃ አገልግሎት - MI6 በመባልም እንታወቃለን። ዩናይትድ ኪንግደም ደህንነቱ የተጠበቀ እና የበለጠ የበለፀገ ለማድረግ ህዝባችን በአለም ዙሪያ በሚስጥር ይሰራል። ከ100 ዓመታት በላይ SIS ዩናይትድ ኪንግደም እና አጋሮቻችን ከጠላቶቻችን አንድ እርምጃ እንዲቀድሙ አድርጓል።” ይላል። በመላው አለም በምስጢር ይሰራል ሲለን ከላይ የጫወትኳችሁ ሰላዮችን በማሰማራት ነው።

አጅግ የገረመኝ ከመልማዮች  ውስጥ  በዓለም ውስጥ በስም የታወቁ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች መስለው የምናያቸው ዛሬ ወያኔዎችን የሚደግፉ ብዙዎቹ እንግሊዞችና ኣይሪሾች የዚህ የስላላ መዋቅር አባሎች መሆናቸው ስማቸው እየጠሩ ሲያጫውቱኝ ብዙዎቹ የትግሬና የኦሮሞ ፖለቲከኞች ምንኛ አገራቸው ለጥቃት እንደጋረጥዋት ሳስበው አጅግ አዘንኩ።

ይህ ታሪክ ላካፍላችሁ የፈለግኩበት ምክንያት አገራችን በዚህ “በመፍረስና አለመፍረስ” ትግል ያለቺበት ምክንያት የውጭ ሃይሎች እጅ የገባበት መሆኑን እንደትረዱት በሚል ነው። ለማንኛውም እስኪ Martin Plaut የተባለው አደገኛ “ጣልቃ ገቢ” እና የብዙ ልበወለድ መጽሐፍ በመጻፍ የተካነቺው ቱራማታይዝ በሆነ ሕሊናዋ የምትዋዥቅ ጸረ-ኢትዮጵያ “መሰሪዋ” Sarah Vaughan የተባለቺው በጥምረት የጻፉት Undertsanding Ethiopia’s Tigray War” (Martin Plaut & Sarah Vaughan)  የሚል በቅርቡ ያሳተሙትን መጽሐፍ አንብቡ ።

 ኢትዮጵያ እንዴት “ውዥምብር ውስጥ“ አስገብቶ ትግሬዎችና የኢትዮጵያ ታሪክ ፤ምኒሊክና ትግሬ፤ እንዲሁም የደቡብ ሕዝብና ኢትዮጵያ እያሉ “ኢትዮጵያ የ19ኛ ክ/ዘመን የኮሎኒ ቅርምት ውጤት” እያሉ አያታቸው ጣሊያን ያቀደው የመሸነፍ ፕሮፓጋንዳ በመጽሐፍ መልክ አዘጋጅተው አዲሰ ነገር ማፍራት ያልቻለ ለ50 አመት በጫካ ሕሊና እሳቤ የበሰበሰው የትግራይ የፋሺት ምሁራን ጨንቅላት እየስፈነደቁ ናቸው።

አሜሪካኖችም የወልቃይቱ ኮ/ል ደመቀ መኮንን እና ምጡቅ አማራዎችን ነጥሎ በዘር ማጥፋት ለመክሰስ “ሲ አይ ኤ” በሚመራው  “በሰብኣዊ መብት ተሟጋች” ተብየው ድርጅት በኩል ይፋ አድርገዋል። የጥንት ተቀጣሪ አባላቸው ጴንጤው አብይ አሕመድም አማራና ኦርቶዶክሰ በማፍረስ ከበባው ላይ የአንበሳ ድርሸው በመወጣት ላይ ነው።

ይህ ሁሉ ሲከናወን የኢትዮጵያ ወጣት ምን ነካው ብየ አልጠይቅም፡ ምክንያቱም ሁሉም በየጎጡ እንዲያስብ በባንዳዎች በኩል ለ35 አመት ልዩ “አዚም” ስለተሰራበት። ይልቁኑ የኢትዮጵያ ወጣት ምን ነካው ከማለት የአማራ ወጣት ምን ነካው? ልበል። አማራው በልዩ ከበባ ላይ ነው። አንድባንድ በየደረጃው ልውሰዳችሁ።

ጥር 24 ቀን 1994 ዓ.ም አዲስ አመን ጋዜጣ “ትግራይ እስክትለማ ሌለው ይድማ” ብሎ ወያኔ በተግባር ሲተረጉም  በባሰ መልኩ ያደማው አማራውን ማሕበረሰብ ነበር። አማራው ወጣት ያኔ በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ  የማደንዘዝ ዘመቻ በላዩ ላይ እየተከናወነበት ስለነበር ምን እየተደረገ እንዳለ አላወቀም ነበር። ያኔ ዝም ተባለ።

ደምቆ የታየው የመጀመሪያው ኮኮብ  አሳምነው ጽጌን አጨለሙት ወጣቱ ለመነሳት ትንሽ አንገራገ አንደገና አንቀላፋ።

የ16ኛው ክዘመን ጭካኔ በተላበሰው የኦሮሞ ነፃ አውጪና አብይ አሕመድ በጣምራ በሺዎቹ የአማራ ማሕበረሰብ እስላምና ክርስትያን “ከኦሮሞ አፓርታይዳዊው ክልል”  እየጨፈጨፈ ሲገድላቸው ግማሹም ንብረታቸው እየተነጠቁ ሲባረሩ ብዙዎቹ የአማራ ወጣቶች ከመንጫጫት የዘለለ የጣምራ አመጽ አላካሄደም።ያኔም  ከማንገራገረ ወዲያ ረዢም ዝላይ አልዘለለም።  

ወጣት አማራ ምሁራን እና የማሕበረሰብ አንቂዎች እየተለቀሙ ሲገደሉና ሲታሰሩ ወጣቱ ለአመጽ አልነሳ አለ። ቤቶች በዘር ዕቅድ ሲፈርሱ ምንም አልተሰማውም።

 

ኦርቶዶክስ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ከኣንገቱ ማተቡ ሲበጠስ ሰንደቃላማው ሲነጥቁት በመተባባር  “ሃይላችን እግዚአብሔር ነው! ፈጣሪ ሆይ መምጫህ መቼ ይሆን?” እያለ ወደ ሰማይ እያንጋጠጠ ማንነቱን በዝምታ አስደፈረ።  ያኔም ዝም!ዝም!

ወያኔ አዲስ አባባ ለመድረስ ጥቂት ጉዞ ሲቀረው አብይ አሕመድ ሆን ብሎ ያልታጠቀው አማራን ለማስጨፍጨፍ ሲለቃቸው፤ወያኔዎች የጥፋት ተልዕኮአቸው ከፈጸሙ በላ፤ መጨረሻ ወያኔ ለመግፋት በማይቻልበት ደረጃ ሲደረስ በፍርሃት ቆፈን ተሸብቦ አብይ አሕመድ ወታደሮቼ ተሸንፈዋል እና የአማራ ፋኖዎች አድኑኝ ብሎ ተማጽኖ እሪታ ሲያሰሰማ ፋኖዎች ተነስተው ወያኔን አሯርጠው በማስወጣት አብይ አሕመድ ከመማረክ አዳኑት። አብይ ማተቢስ ነውና ፋኖዎችን ዘራፊዎች ሲል ዘለፋቸው፡ ወጣቱ ዝምብሎ አዳማጠው፡ ቀስ ብሎም በፋኖ ላይ የጦርነት አዋጅ አወጀ፤ ወጣቱ ወደ ፋኖ ከመጉረፍና ብረታዊው ገድል ከማጣነቀከር ይልቅ ከተማ ውስጥ ተቀምጦ ከመንጫጫት የዘለለ ስራ አልሰራም።

በሚገርም ድፍረት የአብይ አሕመድ ኦሮሙማ ወታደሮች ቄሶችን በጥፊ በመምታት የጀመሩት ድፍረት የንቀቱ ንቀት አብይ አሕመድ “አማራው ወደ አዲስ አባባ እንዳይገባ በይፋ አገደ” አማራው ወጣት የለየት አመጽ ከማስነሳትና ያ አልሆን ካለው ወደ ጫካ መሽጎ የሽምቅ ተዋጊ ከመመስረት ይልቅ፤ ወደ ሚዲያ ከመጮህ ባለፈ አመጽ አላነሳም አለ።  

በመጨረሻም ጦርነት የታወጀባቸው የፋኖ አርበኞች ራስን ለመካላከል የለየለት የጦርነት ፍልሚያ ሲያካሂዱ ወጣቱ ከተማ ውስጥ ሞባይል ሰልክ ይዞ ፎቶ ከመለጠፍ የዘለለ ስራ አልሰራ አለ።

 እስክንድር ነጋ እና ዘመነ ካሴ በወጣቱ የጠመንጃ ትግል እና የአልበገሬ አመጽ ሳይሆን በተአምር ከጅብ መንጋጋ ሲለቀቁ “ዕልልታ” አቅላጭ ሆኖ ከመታየት ያለፈ አፓርታይዱን ቡድን ማርበድብድ አልቻለም።

በመጨረሻ እስክንድር ነጋ የመሰለ አብሪ ኮከብ ከጉያቸው ውስጥ ሆኖ በጭለማ ውስጥ እየዳከሩ ያሉትን ወጣቶች ወዴት መራመድ እንደሚችሉ ቢያሳያቸውም፤ የአማራ ወጣቶች እንደ ትግሬ ወጣቶች በገፍ ወደ ጫካ ከመጉረፍ ይልቅ አሁንም በቀን ብርሃን እየተደናበሩ እያየሁ ነው።

 እጉያው ውስጥ በጣምራ ደምቀው እያበሩለት ያሉት ጤፍ የምታስለቅም የጨረቃና የሰብአ ሰገል ኮዋክብቶችን ብርሃን ማየት ካቃተው የአማራ ወጣት ምን ዓይነት መብራት ቢበራለት ማየት ይችላል?

 

ጌታቸው ረዳ