Tuesday, November 1, 2022

አብይ አሕመድ ያደርገዋል ያልኩትን ክሕደት በቃሉ እነሆ አረጋጋጠልኝ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/1/2022


አብይ አሕመድ ያደርገዋል ያልኩትን ክሕደት በቃሉ እነሆ አረጋጋጠልኝ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 11/1/2022


ታስታውሳላችሁ  << በመቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው?  ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ >> የሚል በ 8/25/22 በ9/15/22 የጻፍኩዋቸው የአብይ አሕመድ የጦርነት አካሄድ ግምገማዎች? አንደኛው ፌስቡክ ሰርዞብኛል። በወቅቱ ብዙ ሰዎች ሳይገባቸው የቀረ ይመስለኛል። ግን አይመስለኝም። ምክንያቱም እነዚህ ትችቶቼን በግልጽ ነበር ያስቀመጥኩዋቸው።

እነሆ እንዲህ ነበር ያልኩት፡

አብይ የማይታመን ቀውሰኛ ፤ ከሃዲ እና እስስት ነው።አብይ በስቅላትየሚቀጣው ፍትሕ ባይገኝም አንደ በፊቱ መለስ ዜናዊን ለሞት እንደተመኘሁለት በሚገርም ትንቢትና እርግማን ምኞቴ ሰምሮ እግዚሃር እንደወሰደው አብይም በዚያ የመለስ ዕጣ እንዲሸኝ ዛሬም ጸሎቴ እና አቤቱታዬን ወደ እዚህ መሬት የላከው ዲያብሎስ መልሶ እንዲወስደው ምኞቴ ዛሬም ህያው ነው። “” ነበር ያልኩት ያኔ።

ለዚህም ምክንያቴን ሳቀርብ

አሁን በመካሄድ ላይ ላላው ሦስተኛው ዙር ጦርነት ከመካሄዱ በፊት ማለትም በሁለተኛው ዙር ጦርነት ወያኔ እስከ ደብረብርሃን አጠገብ ደርሶ ብዙ ችግር ፈጥሮ ልጃገረዶችን፤ መነኮሳትን እና ባለትዳሮችን ደፍሮ ፤ ንብረት ዘርፎ፤ ተቋማት አውድሞ ወደ አዲስ አባባ ሲገሰግስ፤አብይ አሕመድ ዓሊ ጦርነት ናፋቂዎች ናችሁ እያለ ሕዝቡን እየዘለፈ “ክላሽ አትሸከሙ” እያለ እየቀሰቀሰ፤ሲሻውም ፓርክ ውስጥ ኮማንዶዎችን አስከትሎ የልጆች መጫወቻ ብስክሌት ሲነዳና ችግኝ እየተከለ፤ፎቶ ሲነሳ “መታሰር የሚገባቸው የወያኔ መሪዎች ቸል ብሎ ሲዘባበትባቸው እነሱ መቀሌ መሽገው ሲዘጋጁ አስቀድሞ በለመዘጋጀቱ አገሪቷ ለጉዳት አጋለጣት።

ባጭሩ ባልተጠበቀ ቅጽበት የተደጋጋመው አይቀሬው የወያኔው ግስጋሴ ወደ አዲስ አባባ ቤተመንግሥት መሆኑን ሲያወቅ፤ የአማራን ሕዝብ በመማጸን “የኢትዮጵያ ወታደር ብቻውን ወያኔ መዋጋት አልቻለም እና በመሸነፉ እናንተ ገብታችሁ አድኑኝ” ብሎ ሲማጸን ሕዝቡ በውጭም በውስጥ አገርም ተረባርቦ ወያኔን ድባቅ መትቶ እንዲሸሽ አድርጎ ሲያበቃ በሸሽቱ ወቅት ተከታትሎ መቀሌ ገብቶ የመጨረሻ ምት ከመምታት ይልቅ ፤ ሆን ብሎ አብይ አሕመድ ግማሽ መንገድ አማራ መሬት ከተሞች ላይ እንዲመሽግ አድርጎ ጦርነቱን አስቁሞ “መለስ ኤርትራ ባድመ ጦርነት” ያደረገው ዓይነት ታሪክ ደገመው::

“አብይ አሕመድና ብርሃኑ ጁላ ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል ግማሽ መንገድ ስለተውት እንደ በፊቱ እነኚህን መነኮሳት እናቶች ያለተከላካይ በወያኔ ስር እንዲቆዩ ስላደረጉ ዳግም ያስደፍሯቸውና ያስለቅሳቸው ይሆን?>> ብየ ነበር፡ እንደፈራሁትም ፤ “ሆነ” ።  ከታች የምጠቅሰውን ማስረጃ  ለትውስታችሁ ያዙልኝ።

አብይ አሕመድ ሆን ብሎ ወያኔን ትግራይ ድረስ ገብቶ ላላማባረር ግማሽ መንገድ ስለተወው፤ ከዚያ ወያኔ በያዛቸው አማራዊና  ዓፋራዊ ቦታዎች ብዙ ስቃይ እያደረሰ እንድ አመት ሙሉ እራሱን አደራጅቶ ሕዝቡ በወያኔ ቅኝ ግዛት እጅ እንዲሰቃይ አደረገ። ‹‹ሲኦል እንኳን ብንገባ የማንቀጣዉን ያህል ቅጣት በወያኔ ተቀጥተናል››  የሚለውን የራያ አላማጣ ነዋሪዎች እሮሮ ትናንት የተለቀቀው ቪዲዮ በራሴ ፌስቡክ  “ለጥፌዋለሁ” እዩት።

አብይ አሕመድ ምርጥ የፋኖ መሪዎችን እየገደለና 20 ሺሕ ፋኖ ካሰረ በላ ወያኔ የልብ ልብ ተሰምቶት አሁን ለሦስተኛ ዙር በነሓሴ ወር ጦርነት ከፈተ። ክላሽ አትጣጠቁ፤ ወደ እርሻ ግቡ እያለ  አብይ አሕመድ ሲቀልድ ከርሞ ተጎትቶ እንደገና ወደ ጦርነት ገባ።

የመንግሥትም የሕዝብ ንብረትም ወድሞ፤ ዩሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት አመድ ሆኖ፤ የሺዎቹ እምባ ፈስሶ ፤በሺዎቹ ህይወት ገብሮ፤ መቀሌ ቢገባስ “ድል” ተብሎ ዳንኪራ ሊመታ በምን ሞራል ያስችላል? አብይ አሕመድ ተመልሶ መለስ ባድሜ እንዳደረገው አብይ ብያደረግስ መቀሌ መግባቱ ከኪሳራ በላይ ምን ይፈይዳል? ብየ ጠይቄ ነበር። (ያንን የጠረጠርኩትን እንደሚደግም ትናንት በስትያ የተናገረውን እንደ ማስረጃ ወደ መደምደሚያ በመጨረሻ አቀርባለሁ)

ያ ብቻ አልነበረም ያልኩት፡

አሁን በዚህ ሦስተኛው ዙር መቀሌ ቢገባስ እንደገና የትግራይ ገበሬ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ፤ ሰብሉ እስኪሰበስብ ድረስ ከትግራይ ወጥተናል ቢልስ” አብይ ማን ጠያቂ አለው? ብየም ነበር።

አሁን ጥርጣሬየን እውን እንዳደረገው አብይ አሕመድ በቃሉ ከሦስት ቀን በፊት በእንግሊዝኛ ተጠይቆ  “ሲ ቲ ጂ ኤን” ለተባለ የውጭ የዜና ወኪል የተናገረውን የባንዳነቱ ቃል በቃል  ልጥቀስ።ከዚያ እተረጉመዋለ ።

 “ሲ ቲ ጂ ኤን”

 << We are trying to convince TPLF to respect the law of the land to respect the law of the land, act as one state in Ethiopia, if they could understand our interest, they would believe their own constitution and work accordingly, I think, peace will be achieved >>

ትርጉም፤

<< << ህወሓትን ለማሳመን እየሞከርን ነው። የሀገሪቱን ሕግ አክብረው፣ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሆነው ከሰሩ እና የኛን ፍላጎት ከተረዱልን የራሳቸውን ሕገ መንግሥት አምነው በዚሁ መሰረት ከሰሩ ፣ሰላም የሚሰፍን ይመስለኛል።>>

በማለት እጅግ በጥርጣሬ የተነበይኩትን ክሕደት እንደሚፈጽም ይኼው በቃሉ አረጋገጠልኝ። ይኼው ከትናንት በስትያ ዳግም የባድሜው መለስ ዜናዊ በአካል ዞሮ መጣብን!

የመጀመሪያ ክሕደቱን እና ልፍስፍስነቱን በመጀመሪያዋ ቃሉ ከላይ የተናገረወን ላስምርበት።

ሽብርተኛ ተብሎ በራሱ ፓርላማ ያጸደቀው ሽብርተኛውን ቡድን “ህወሓት” እያለ መጥራት ጀምሯል። ህወሃት ማለት በሕገመንግሥቱ ተብየው አንድ ሕጋዊ አባል ነው። ስለዚህ ከሽብርተኛነት አስወጥቶ በሕጋዊ ስሙ አክብሮ እየጠራው ነው።

ከላይ ብትርጉሙ እንዳነበባችሁት አብይ እያለ ያለው የፈለገውን ወንጀል ብትፈጽሙም  <<እኔን እንደ መሪ አድርጋችሁ ከተቀበላችሁኝ እኔም እንድጠራችሁ በምትፈልጉኝ ስማችሁ “ህወሓት” እያልኩ አክብሬ ይኼው እየጠራሁዋችሁ ነው፡ ያወም እንደ የትግራይ ክልል ወኪል አድርጌ አከብራቸዋለሁ፤ ምን ወንጀል ቢኖራችሁም አልጠይቃችሁም፤አልከስሳችሁም፤ ክብራችሁ ወደ ነበረበረበት ተመልሶ ጥቅማ ጥቅማችሁን አከብራለሁ ፤ ደሞዝ እከፍላለሁ፤ እቀበላችኋለሁ። >>  ነው እያለ ያለው።   

ከሁን በፊት ግን ፓርላማ ተብየው ውስጥ ተገኝቶ ምን ሲል ነበር?

ይህንን ላስታውሳችሁ እና ልደምድም።

<< አሁን የትግራይ ወዳጆች የተከበረው ምክርቤት ለመግለጽ የምፈልገው፤ ‘ቲ. ፒ. ኤል. ኤፍ’ ማለት በነፋስ ላይ እንደተበተነ እንደ ዱቄት ማለት ነው! ከእንግዲህ በላ ሰብስበን ዱቄት ልናደርገው አንችልም። እርሱን ትተን (ወያኔን ትተን) አዲስ ሃይል፤ አዲስ የተማረ፤ አሁን ያለውን ዘመን የሚዋጅ አስተሳሰብ መምራት የሚችሉ ሰዎች መፍጠር ይቻላል፡ ትግራይ ውስጥ ብዙ አሉ። እንበልና የተከበረው ምክር ቤት “”እዛው የተሸሸጉ አንዳንድ ሰዎች  መጥተው መንግሥት ይሁኑ ቢባል እና መቀሌ ቢመለሱ፤ በምን ዓይናቸው ነው ሚዲያ ላይ ቀርበው ስለ ትናንትና መናገር የሚችሉት? መልካቸው ስለተበላሸ ብቻ ኣይደለም፤ ሞራልስ ደቋል እኮ በየት በኩል? ማንስ ነው የሚሰማቸው? ማንስ ነው ካሁን በኋላ የሚያምናቸው? ካሁን በኋላ እንዴት የክልል ፕረዚዳንት ይሆናሉ? አይኮንም! IT IS GONE!!  ይኼ ታሪክ ነው። ብንዋጋ ባንዋጋ አይደግምም። >>

ይህ ሰውየ የሐሊና ቀውስ አለው የምለው ለዚህ ነው። ያሸነፈ ሲመስለው ይህ ሁሉ ይቀባዥራል። ሲደንግጥ ደግሞ “ዱቄት የሆነውን አምጥቶ፤  << መለካቸው የተበላሸ ነው>> <<ሞራላቸው የደቀቀ ነው >>  << ፕረዚዳንት መሆን አይችሉም፤ እንዴት ተኩኖ? >> እያለ ሲሳለቅባቸው የነበሩት ዱቄቶች እንደገና ይቃዥና  <<የክልል ፕሬዚዳንት መሆን ትችላላችሁ>> እያለ የራሱን ምላስ ሲቆረጥም እያየን ነው።

ለዚህ ነበር  << በመቀሌ ቢገባስ ምን ትርጉም አለው? >> ብየ በመስከረም ወር እና በነሓሴ ወር የጻፍኩዋቸው ትቸችቶቼ በምክንያት ነበር።

ለዚህም ነበር;-

<< አብይ በስቅላትየሚቀጣው የፍትሕ ተቋም ባይገኝም በፊት መለስ ዜናዊን ለሞት እንደተመኘሁለት በሚገርም ትንቢትና እርግማን ምኞቴ ሰምሮ እግዚሃር እንደወሰደው አብይም በዚያ የመለስ ዕጣ አንዲሸኝ ዛሬም ጸሎቴ እና አቤቱታዬን ወደ እዚህ መሬት የላከው ዲያብሎስ መልሶ እንዲወስደው ምኞቴ ዛሬም ህያው ነው። “” ያልኩበት ምክንያትም ለዚህ ነበር።

ጽሑፉን አዳርሱት

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ