“የኢትዮጵያ
ሁቱዎች” እንኳን ተሳካላችሁ!
ጌታቸው
ረዳ
(Ethio
Semay)
11/2/2021
ለ4 ወር ማጎርያ እስር ቤት አስረው አሰቃይተው፤ ማስረጃ ሲያጡበት በ$20,000
ብር ዋስ አስይዞ ፈትተውት እንደነበር ባለፈው ከሁለት ሳምንት (ኦክተበር 14) ለወዳጆቼ ነግሬአችሁ እንደነበር ታስታውሳላችሁ።
ዛሬ ፤ አሁን በኢትዮጵያ ሰዓት ሌሊትኑ በሰላም ከሚኖርበት ቤቱ መጥተው በጸረ ትግሬው መሳይ መኮንን እና “ሦስት ጊዜ የመግደል
ሙካራ ተደርጎብኛል እና ደሴ ውስጥ “ለዘመናት እየቀለብናቸው” የኖሩ “30 ሺህ” የትግራይ ተወላጆች እየተለቀሙ በሙሉ ይያዙ በማለት
“ጸረ ትግሬው” እና “የፖለቲካ ማሃይሙ” የአብን አመራር አባል “የሱፍ ኢብራሂም” ባስተላለፈው “ጀነሳይ የማስፈጸም አዋጅ” ዛሬ
እንደገና ወንድሜን ወደ እማይታወቅ ማጎርያ ወስደውታል።
ዛሬ ወንድሜን ያለ ምንም ወንጀል እንደገና ማሰር፤ በእነ መሳይ መኮንን
እና የሱፍ ኢብራሂም የጸረ ትግሬ አዋጅ በመታሰሩ ማዘኔን ስገልጽላችሁ፤ በሙሉ ልቤ ለኢትዮጵያ አንድነት የታገልኩትን የዘመናት ትግል
ከንቱ መቅረቱን መረዳቴን ሳውቅ ከልቤ ሐዘን ተሰማኝ።
“በጅምላ
ማሰር” ኢትዮጵያን እንደ አገር የማቆየት ሳይሆን ይበልጥኑ እንደኔ
የመሳሰሉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎች ከአንድነቱ ጎራ እንዲርቁ ምክንያት እየሆነ ነው። ከዚቺው ደቂቃ በሗላ፤ ቁርጡ እስከሚታወቅ
ድረስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ “በኢትዮጵያ ሁቱ ጀነሳይደር ቀስቃሾች” ምክንያት ከናንተው ከማከብራችሁ እና ከምወዳችሁ ወንድሞች እና
እህቶች በፖለቲካው መስክ ለጊዜው እራሴን በማግለል እሰናበታች ለሁ። የመታገል ትርፉ እንደ የውጭ አገር ዜጎች “ተቀላቢዎች” እየተባልን
ውደ ማጎርያ ቤት የሚያስግዝ ከሆነ የኔ መታገል “ፋይዳው ምንድ ነው?
ለመሰናበቻ፡
ስለ ሁኔታው ያነጋገርኩት በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖር ወዳጄ ሰለ ወንድሜ
በድጋሚ አሁን መታሰሩን ሰምቻለሁ እና በናንተ በኩል ያለው ከተማ እንዴት ነው፤ ደህና ናችሁ ወይ ብየ ስጠይቀው እንዲህ ይላል፡
“የተኽላይ እንደገና መታሰሩን ስትነግረኝ በጣም አዘንኩ። በቃ ምንም መኖር አልተቻለም። የሰቀቀን ኑሮ እስከመቼ እንደሆነ ፤ እንጃ””
ብሎ ሲነግረኝ፡ እኔም “ድንጋጤየን አምቄ” አይዝዋችሁ አትረበሹ፤የምችለውን
እንደገና እጥራለሁ፡ ብየ ስለው፤ እሱም እንዲህ አለኝ፦
“አይ ጌታቸው፤
ጥቂት ሰዎች መጥፎ ስራ የሚሰሩ ሊኖሩ ይችላሉ፡ በሚሊዮን የምንቆጠር ትግሬዎች ግን በተወለድንበት ሃገር እንደ ሽብርተኛ እየታየን
መኖር ምን ያክል ከባድ እንደሆነ አይጠፋህም። እኛ እኮ በሕግ አልፈራንም፡ እያስፈራን ያለው የሕብረተሰቡ ዕይታ እና ማንገራገር
ነው። እኛን ለማጠፋት አመቺ ጊዜ ነው የሚጠብቁት የሚመስለው። የቅርብ ሰው የምንላቸው፤ያመናቸው እንኳ ነው የተቀየሩብን። እና አሁን
ላይ Human Rights Commission እና የሕግ አካላት ምንም ሥልጣን ስለሌላቸው በትዕግስት መጠበቅ ነው የሚያዋጣን፡ እግዚአብሔር
ብቻ ይጠበቀን እንጂ የሩዋንዳ ድባብ እያንዣበበብን ነው።” በማለት ወዳጄ በተሰበረ የሐዘን ድባብ ነግሮኛል።
የነመሳይ መኮንን እና የነ የሱፍ ኢብራሂም በአንድ ከተማ ብቻ 30ሺህ
ሰላማዊ ትግሬዎች “መቀለብ ሰልችቶናል” የሚለው “አጉሮ የመጨፍጨፍ
አዋጅ” ውጤት ተሳክቶላቸዋል። “የኢትዮጵያ ሁቱ” ቡድኖች ነገድን ለይቶ የማጥቃት ድላቸው ለኢትዮጵያ ሰላም የሚሰጥ ከሆነ የምናየው
ይሆናል።፡ የጀነሳደሩ ካድሬ የ የሱፍ ኢብራሂም አዋጅና ተምክሕት ላልሰማችሁ ይህንን አንብቡ እና ልሰናበታችሁ፡-
እንዲህ ይላል፡
“ሕዝባችን
የማንም ደካማ መጫወቻ የሆነብትን እንቆቅልሽ “የግድ”፤”የግድ” እንፈታዋለን።ካሁን በሗላ የማንንም ተኳሽ እና አስተኳሽ
ታቅፈን “እየቀለብን” እና በይሉኝታ ተቀፍድደን የምንደበደብበት አንዳች ምክንያት አይኖርም።ጋሻው መርሻን እና እኔን ለመምታት ሦሰት
መድፍ ተተኪሿል። አንዱ መኪናችንን ሌላው የመኝታ ክፍላችንን አፍርሿል። ከተኳሹ አስተኳሹ፤ ከ30 ሺሕ በላይ የትህነግ አስተኳሽ
ታቅፎ የሚኖሮው የደሴ ከተማ ሕዝብ ከውስጥ ባይተኮስበት በውዥምብር ባይፈታ ኖሮ የሚገርመው። ደሴ ከተማ ለመግባት ከሞከረው ወራሪ
ሃይል “መቀሌ እንደምንገናኝ” ስነግራችሁ የማይሰበር፤ የማይነጥፍ ቃል መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ከዚህ በሗላ በትግላችን እቀልዳለሁ ወይንም እስላቃለሁ የሚል ካለ፤ “የብረት
ገላ ካለው ይሞክረው”። እጅግ መራር በሆነ ምዕራፍ እንገናኝ”
ካለ በሗላ
የዜናው አንባቢው ወደ እሚቀጥለው የመሳይ መኮንን ጀነሳይድ አዋጅ ከማንበቡ በፊት፤ “በአሁኗ ሰዓት የጁንታ ሰላይ ከየቤቱ እየታነቀ ይገኛል።” ሲል ጀነሳይዱ
በደሴ፤በባሕርዳር እና በየከተማ እና ገጠሩ መጀመሩ ነግሮናል።
መልካም ትግል፤ መልካም ድል ለ “ሁቱ” ኢትዮጵያዊያኖች ስመኝ
ለተቀራችሁ እስከዛሬ ድረስ አብሬአችሁ ለታገልኩኝ እህቶች እና ወንድሞች
ደግሞ ደህናውን እና ሰላሙን እመኝላችሗለሁ!
30ሺውን ትግሬ መቀለብ ችግሮናል ለሚሉ “ቀላቢዎች” 6 ሚሊዮን ትግሬ
በማጎር ኢትዮጵያ እንደ አገር ከቀጠለች አብረን እንገናኛለን።ካልቀጠለች ግን የሚቀልበን ሌላ “እንደ የአብኑ ካድሬ “ኢብራሂም የሱፍ”
እና መሳይ መኮንን የመሳሰሉ ሃብታም ቀላቢዎች” ስር ወድቀን እንጀራ እየለመንን በሩቅ እንተያያለን። ሁቱዎች የኢትዮጵያን መፍረስ
እያቀላጠፋችሁ መሆኑን አሁኑኑ ስነግራችሁ ላይረዳችሁ ይሆናል። በዚህ ከቀጠለ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ እንደምትፈርስ እርግጠኛ ሆኜ
እነግራችኋለሁ።
ላከበራችሁኝ፤ ለወደዳችሁኝና
ለተባበርችሁኝ ውድ የምወዳችሁ እህቶች እና ወንድሞች፤ ስለያችሁ እያዘንኩ ነው።
አመሰግናችለሁ።
ከቀላቢዎች ዓይን ያውጣችሁ!
ደህና ሁኑ!
ጌታቸው ረዳ