Thursday, June 20, 2019

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል 3) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)



ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል 3)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)
ፎቶ አስቴር በዳኔ

እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ ሰንብተናል፤ በኣናርኮ ፋሺስቱ የኦሆዴድ መሪው ኣብይ አሕመድ “ስርዓተ-አልባ” አመራር ምክንያት ላልሰነበቱ ወገኖቻችን በጥልቅ ስሜት እናስታውሳቸዋለን።

“በነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ተሰላፊ ቡድኖች” ውስጥ ለዛሬ ልተነትን ተዘጋጅቼ ነበር ዛሬም እንዳለፈው ሳምንት ሊሆን አልቻለም። ሆኖም በዚህ ነጭ ባንዴራ ተሰላፊዎች ስር ሊካተቱ የሚችሉ ክስተቶች እና ግለሰቦች ቀልቤን ስላሰቡኝ በምትካቸው ለዛሬ የሳምንቱ ትኩስ መነጋጋርያ ሆኖ እስካሁን ድረስ እያነጋጋረ ያለው የግንቦት 7 ንብረት የሻዕቢያ ድምፅ ማጉያ እና የብርሃኑ ነጋ ጉሮሮ ማስተጋቢያ የነበረው ‘ኢሳት’ የተባለው አስገራሚ እና ሻጥረኛ የዜና ማሰራጫ ብትንትኑ መውጣቱን ያስገረማቸው ሰዎች በርካታ ስለሆኑ ‘ቀዳሚ ዜና’ ሆኖኛል። ኢሳት የግንቦት 7 የብርሃኑ ነጋ የፕሮፓጋንዳ ማስተጋቢያ ስለነበር በየአመቱ የዘመን መለወጫ መስከረም 1 ‘ቅዱስ ዮሃንስ’  በመጣ ቁጥር የብርሃኑ ነጋ ድምፅ ማስተጋቢያ እና የብርሃኑ ‘ተክለሰውነት’ መቅረጫ መኖሩን እናስታውሳለን።

በሚዲያው ቀርበው የታሪክ ትንተና ባካሄዱ የታሪክ ምሁራን እንደ እነ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ የመሳሰሉ የኦነግን ፖለቲካዊ ርካሽነት ስላጋለጡና በጥንታዊ ስሙ ‘የጋላ ማሕበረሰብ’ ሲኖርበት የነበረ አኗኗር “በከብት እረኛነት/ፓስቶራሊሰት” ሲተዳዳር ነበር በማለታቸው “ኢሳት በኦነግ ስም” ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦን “ይቅርታ እንዲጠይቁ” ሲጎተጉት ኢሳት ያለ ኣግባብ በስማቸው ኦነግን ይቅርታ ለመጠየቅ ሲቀላውጥ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው። ይግረም ብሎ በአደገኛው ሰውየ በሓጂ ነጂብ አማካይነት “የዝግ ስብሰባ ተደርጎ ”ጃዋር” ፕላኑን ሲናገር  እኛ በምንኖርበት አካባቢ (አርሲ) አብዛኛው ሙስሊም ማሕበረሰብ ስለሆነ አንድ ክርስቲያን አንገቱን ቀና ካደረገ አንገቱን በሜጫ ነው የምንለው ብሎ ለተከታዩ ሲናገር ተከታዩ በታላቅ ጭብጨባ ሃሳቡን ሲያጸድቅ  “እንዳንተ አይነቱን ያብዛልን!” የሚሉትን የመናዊ እና ኢትዮጵያዊ ትውልድ ናቸው የሚባሉት እንደ እነ ሓጂ ነጂብ እና ጃዋር  ‘ኢሳት ሚዲያ’ ነፃ ቃለ መጠይቅ እየሰጠ ሲቀልድብን ነበር። “በነ ጃዋር ስብከት ተከትሎ ክርስቲያኑ እና አብያት ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል ንብረት ወድሟል ዜጋ ተገድሏል። (ሰመረ  ዓለሙ)
(https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8)

ያንን በተነገረ ዕለት “የኢሳቱ ታማኝ በየነም” ተጨማሪ ዱላ በማቀል “አዎ እኛ ልጆች ሆነን ለኛ ለክርስትያኖች እንዲህ ሲደረግልን ለናንተ ሕዝበ ሙስሊሙ እንዲህ አልተደረገላችሁም ነበር! እያለ ነገር ሲያቀጣጥል እነ ሓጂ ነጂብና ከእነ ጃዋር ደስታቸው ቀልጦ ነበር። ኢሳቶች እየደጋጋሙ ‘የቃለ መጠይቅ’ ዕድል ከመስጠት ጀምሮ “አብረው” በእየ አገሩ ሲዞሩ የነበረውን ትዝታችን ዛሬም አልረሳነውም። 

ኢሳት ውስጥ የተሰባሰቡ አንዳንዶቹ የግንቦት 7 አባሎች የሚገርሙ ካድሬዎች ነበሩ።  “የግ7 አማራር” ጸረ አማራ የበዛበት ቡድን ነው ሲባሉ “በውሸት ይከንፉ ነበር”፡ የድርጅቱ ልሳን የሚጽፈው ዘረኛ ርዕሰ አንቀፅ እያነበቡትም ቢሆን ፤ (አስመራ ላይ ‘ከድምህት’ ጋር እፍ እፍ ፍቅር ይዞት ስለነበር ወልድያ ውስጥ ጥምቀት ቀን ስለደረሰው ክስተት የግንቦት 7 መሪዎች ምን እንዳሉ የምታስታውሱት ነው)። የገዛ ተጋዮቹን ለሻዕቢያ “ገራፊዎች” እያሳልፈ በመስጠት አስደብድቧል፤ አስረሽኗል፤ ብለው እያለቀሱ ላጋለጡት “ግንቦት 7 ለቀው ከኤርትራ የሸሹት ታጋዮችን” ሳይቀር  “ኢሳቶች የጋዜጠኛነት ሙያቸውን ጥለው” የግ7 ካድሬዎች በመሆን “ቅሬታ ላቀረቡ ታጋዮችን “የወያኔ ሰላዮች ናቸው” እያሉ እነ ሲሳይ እና መሳይ መኮንን ከግርፊያና ሞት ያመለጡ ታጋዮች “ስም ሲያጠለሹ ነበር።”
 
 “ታጋዮቹም” ገርሞኣቸው ፤ የግንቦት አመራር ከነበሩት ከብርሃኑ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሁለታችንን ግምባር ለግምባር ጋብዛችሁ ሕዝቡ ሚዛን ወስዶ እንዲያደምጠን “ጋብዙን” ብለው ደብዳቤ ሁለት ሦስቴ የጻፉትን ጥያቄ “ሳይቀበል” ደምጻቸውን ያፈነ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ መጻፌን ታስታውሳላችሁ። ስለዚህ ኢሳት መፈረካከሱ የተጠናወታቸው ‘ካድሬኣዊ ባሕሪ’ ዛሬም “ለአብይ አሕመድ” በማጎንበሳቸው ‘ለኢሳት መፍረስ ምክንያት መሆኑን’ ባሕሪያቸው ለተከታልናቸው ብዙም አልገረመንም። ጠርቶ መውጣቱ ግን ጥሩ ነው!

ከብርሃኑ ጋር ያበረው የኢዜማው አባ ቄሱ “አንድአለም አራጌ” የተናገረው ስምታችሗል? እንዲህ ይላል፦

“ማሰር ማፈን እና ግድያ ስለቀረ “መንግሥት እንደሌለ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች አሉ፡ ታሪካችን ከግድያ እና ከአፈና ስለሚየያዝ ነው መንግሥት እንደሌለ የሚመሰላቸው።” ሲል አሳፋሪ መጎንበሱን አስደምጦናል። ለመሆኑ መንግሥት የሚባል በዚህ አገር አለ ወይ? ብለው እየጠየቁ ያሉት እኮ የአንዱአለም አራጌ መንግሥት “መንግሥት አልባው” አብይ አሕመድ የሚመራው “ቤት አፍራሽ እስላም ሴት አረመኔ ከንቲባዎች (ጉዲቶች)” ቤቶቻቸው የፈረሰባቸው እናቶች እና አረጋዊያን እያለቀሱ የሚጠይቁት ጥያቄ ነው፤ ለመሆኑ “ለኛስ ለመሆኑ መንግሥት አለን ወይ?!! እያሉ “አረንጓዴ፤ቢጫ ቀይ ቀለም እንባ እያቀረሩና እያለቀሱ (አዛውንት አባቶችና እናቶች!) “መንግሥት የለም እንዴ?!” እያለ ያውም ወንድ ልጅ ስያለቅስ? “አንዱአለም” ይህንን አሳዛኝ እምባ እና ጥያቄ እንዴት ማየት ተሳነው?

“ማሰር መግደል ማፈን” ቀርቷልና “መንግሥት መኖሩን እንድናውቅለህ” ያንን አፈና ቀጥልበት” ብለን ስንጮህና ስንተች ሰምተሃል አቶ አንድአለም አራጌ? ነብሰገዳይ ሽብርተኛ እና የባንክ ዘራፊው ሌቦቹ ተበራክቷል፤ አረመኔኣዊ ግድያ ቀጥሏል፡ ዘር አጥፊና ቤቶች እያፈረሱ ህጻናትና እርጉዞች ከመኖርያ  ቤቶቻቻው ወደ ጎዳና የሚጥሉ የአፓርታይዱ የስርዓት ስራ አስፈጻዎችን “ስርዓት ማስያዝ የማይችል “ስርዓተ አልባ” መንግሥት እንጂ “መንግሥት የሚባል የለም” ነው ያልነው። መንግሥት ነኝ ባዩ የኦሮሞዎቹ ‘አፓርታይድ’ ስርዓት በካድሬዎቹ፤በፖሊሶቹ እና በከንቲባዎቹ በኩል አድርጎ “ጋዜጠኞችን እያሰረ፤ እያስደበደበ ነው፤ አገሪቷ ወደ ዘመነ መሳፍንት ተለውጣለች፤ አቤት ለሚሉ ዜጎች ‘ጦርነት እከፍትባችለሁ” እያለ የሚዝት “መንግሥት አልባ” (አናርኪነትን ያስፋፋ) ነው አልን እንጂ “ግድያና አፋና ቀርቷል እና “መንግስት መኖሩን እንድናውቅ “ያንን አፈናና ግድያ አምጣ” ስንል ሰምተህ ታውቃለህ? ማስረጃ አለህ?

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው አንዱአለም አራጌ እያደረ የሚገርም ንግግር መናገር ጀምሯል፡ እንዲህ ይላል፦

 “አብይ አሕመድ እንደኛ ሰው ነው “በሆነ አጋጣሚ ወደ ሥልጣን የወጣ እንደ ማንኛውም ፍጡር ሰው የሆነ እንጂ የተለየ ክንፍ የለውምና እባክችሁ ታገሱት” ሲል እንደ ፖለቲከኛ ሳይሆን ሕዝብን በቄስነት ባሕሪው ተማጽኗል። ያውም ቤቶቻቸው በቡልዶዘር ለፈረሰባቸው እርጉዞች፤ እናቶች፤ ቤቶቻቻው ስለፈረሰባቸው ‘ትምህርታቸው የተጓጎለባቸው ህጻናትን” እና እምባ ለሚያቀርሩ አዛውንቶችን!! ነው ታገሱት እያለ የሚማጸናቸው። በዚህ ሰውየ ብዙ የምለው ነገር አለኝ! እሱን ለሌላ ቀን ላሳልፈው።

ስለ የብርሃኑ ነጋ የለመድናቸው አለቅላቂዎች ጉዳይ!

 “ኤዜማ” የተባለው የብርሃኑ ነጋ “ጋሪ” (ትሮጃን ሆርስ) ወደ ምድረ አሜሪካ ለመተዋወቅ ብቅ ብሏል። ጋሪውን ለማስተዋወቅ ብርሃኑ ነጋ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሕዝብ ስብሰባ ተገኝቶ “ሰብለወንጌል” የተባለች ጋዜጠኛ አዳራሹ ውስጥ የደረሰባትን ወከባ በዩቱብ ቪዲዮ ላይ በለቀቀቺው ዜና መሰረት ብዙ ሰው ዜናውን ሰምቶ ተገርሟል። “እንደ ዜጋ ምን እንደተባለ ለማድመጥ ሄዳ “ንግግሮቹን ለመቅዳት በሞከረቺበት ወቅት የስብሰባ ንግግሮች መቅዳት አይፈቀድም” ብለው ግራና ቀኝ ‘ብዙ እንዳዋከብዋት’ ገልጻለች። የብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 የቆዩ ሞገደኞች አባሎቹ (በዚህ ስራ የምናውቃቸው ‘ከሻዕቢያ ጋር ወግነው’ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለቡ ሰው ሲዘልፉ የነበሩ እጅግ ሲበዛ ሰውን የሚገላምጡና የሚያስፈራሩ ተከታዮች እንደነበሩት ዛሬም ወደ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ድርጅት” እንደተዛወሩ የሚያሳይ ፍንጭ ነው።)

ዛሬም በሰብለወንጌል ላይ አሜሪካ አገር እየኖሩ የፖለቲከኞችን የስብሰባ ንግግር በዘመናዊ መሳሪያ ለመቅዳት በሚሞክሩ ላይ “አትቀዱም” እያሉ ዜናን የማስተላለፍ ‘መብት’ ሲጥሱ “ኢዜማ’ የተባለው የብርሃኑ ነጋ “አዲሱ ጋሪ” በብርሃኑ ነጋ ባሕሪና በግንቦት 7 ተከታዮቹ ለወደፊቱ “እንከን ገጥሞት እንደሚኮላሽ” ታልሞ ሳይፈታ የተነበይነው ነገር ነበር። ይኼው ገና “እግር ሳይተክል” በሰብለ ላይ ደገሙት!

ዋሺንገቶን ‘ዲሲ’ ውስጥም ባደረገው ሕዝባዊ የኢዜማ ስብሰባ ከወለሉ (Floor-men) አስተናጋጆቹ አንዱ ‘ካንድ አመት በፊት’ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱን “ሲዘልፉና ሲያስፈራሩ” (ለተወሰኑ ደቂቃዎች “ሃይጃክ” አድርገው ከተቀመጠበት እንዳይንቀሳቀስ ሲያስጨንቁት ከነበሩት “የማስጨነቁ ዜና ሪፖርታጅ አቅራቢ” ዩቱብ ላይ ሲያጓራ የነበረ አንድ ሞገደኛው የዲሲ ግብረሃል አባል ነኝ የሚል ዛሬም “የኢዜማ ወለል አስተናጋጅ” ሆኖ በቪዲዮው ስመለከት ብርሃኑ በለፈለፈ ቁጥር ያደነቆረንን የሙሶሎኒ እና የሶቭየት መነሸቪኮች “ፉጨትና የጭብጨባ ሞዴል” አዳራሹ ውስጥ ሲስተጋባ “ምንጩ” ከየትኛው ቡድን እንደነበር ቀጥታ ገባኝ። ዲሲ ውስጥ በግብረሃይሉ የተለመደ ባሕሪ “ብርሃኑን በጥያቄና በተቃውሞ ያፋጠጡትን እንግዶች” ጉሮራቸው ያለመታነቃቸውና ያለመዘለፋቸው ግን እድለኞች ናቸው። ሌላ ቀርቶ እነኚህ የዲሲ ግበረሃይል ናቸው የሚባሉት ጎረምሶች አምና “ቴክሳስ እስፖርት በዓል” ላይ “የፌስ ቡኩ ዮኒ ማኛን” በቡድን ሊደበድቡት ሞክረው ‘ተደባድበው’ እንደነበር ዮኒ ማኛ ነግሮናል። የ“ኢ-ዜማ” ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋ!  እውነትም ኢ-ዜማ!

በመጨረሻም ለኔ ባይገርመኝም ‘ለብዙዎቹ’ ያስገረመው ዜና “ኢሳት የኔ የግ7 ንብረት ነው” ብሎ ብርሃኑ ይፋ የማድረጉ ዜና የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች እርስ በርሳቸው እያነታረካቸው ነው። ኢሳት ‘የኢሳያስ እና የብርሃኑ ነጋ ተክለሰውነት መቅረጫ’ የግ7 ሮፓጋንዳ ቱለቱላ ክፍል ስለነበር ‘እነ ኤርሚያስ፤ ሃብታሙ፤ ቶቦርነ፤ ርዕዮት ዓለሙ፤ ምናላቸው፤ እየሩ እና ….ወዘተ… ከግ7 እና ከአብይ ካድሬዎች መለየታቸው ጥሩ ነው።

 ማሳሰቢያ፦
ኢትዮ 360 በገንዘብ ልረዳችሁ ነኝ ብየ ፌስ ቡካቸው ብጽፍም መልስ አላገኘሁም። በዚህ አጋጣሚ ብታገኙኝ ደስ ይለኛል። “ጎ ፋንድ ሚ” የሚባለው ከኔ ካረድ ጋር አልሄድ ስላለኝ ሌላ መንገድ ጠቁሙኝ) getachre@aol.com  

ቀጥሎ አብይ የደሴ አኩራፊነቱን እና ውሸቱን እንመለከታለን፡


 እንደተለመደው ውሸቱን ቀጥሎበታል፡ ማስፈራራቱንም እንደዚሁ። መለስ ዜናዊ ያስተማረው “አሉ! ብሎ መክዳት” ወይንም በውሸት መመለስ” አብይም ጭምር “ቁርጥ! የድሮ አለቃው መንትያ መስሏል። ሕዝብ ፊት ‘በመዋሸት’ “የመለስ ዜናዊ” ሞዴል ተከትሏል። ኦሮሞ ባንተ ዘመን ያላግባብ በብዛት ወደ ሥልጣን መጥቷል፡ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ “ኦሮሞ የተለየ ጥቅም አላገኘም ስላላገኘ ነው ይህ ሁሉ ዘመን የታገለው” ሲል ይዋሻል። 3/4ኛ ሰፊ ኢትዮጵያውያን መሬት በብቸኛ ባለቤትነት ይዞ እንዴት አልተጠቀም እንደሚል እንናንተው ፍረዱ። የተቀረቺዋን አገሪቷ ‘ሚጢጢ መሬት’ እና ‘አዲስ አበባም’ ጭምር ቀርታቻቸው ያችንም ለማጠቃለል ሕዝብ እያፈናቀሉ ባይናችን እያየን ‘አብይ ደግሞ’ “የኦሮሞ ጥቅም ለማስጠበቅ ሁላችን እናግዝ” እያለ ሲያሾፍ፤ አረመኔ ከንቲባዎች “ሕዝብ ሲያፈናቅሉ ደግሞ”፤ “አላየሁም አልሰማሁም ውሸታችሁ ነው” “ዓይናችሁ ላፈር” ይላል። ከሰማም በላ ምንም የማስቆም እርምጃ አልወሰደም። ምክንያቱም የራሱ ፓርቲ አጀንዳ ነውና!!
ሲአስፈራራን ደግሞ ‘በእኔው በኦሆዴድ አስተዳዳር ዘመን” ኦሮሞ ተጠቅሞ ከሆነ “ነገ ከሥልጣን እውርዳለሁ” ሲል ያሾፋል።


እኔ ደግሞ “ትግሬው እገነጠላለሁ እያለ ካስፈራራ ይኼው ዘመን” አልፎታል። እኔ ደግሞ እባክህ አታስፈረራን ክፉኛ አሳክኮሃል እና ‘ተሎ አድርገው’ “ሂድ ተገንጠል እና ቆፈኑን ቅመሰው” እያልኩኝ ስማጸናቸው አመት ሆኖኝ “ትግሬዎች” ቢገነጠሉ ምን እንደሚከተላቸው ስለሚያውቁ አላደረጉትም (ጉራቸው ግን ጣራ ነክቶ ቀጥሏል)። አብይም እውርዳለሁ እያለ ሲዝት ሲያስፈራራ “እኔ ደግሞ እባክህ አድርገው!” ካልኩት ‘አመት’ ሆኖኛል። አሁንም ሊያደርገው አልፈለገም። አሽከሮቹና ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ቡድኖቹም አብይ ከለቀቀ ማንን እንተካለን?” እያሉ በዜጎች የአዋቂ መሪ አፍላቂነት እና በፈጣሪ ታምር አውራጂነት ላይ ሲያጣጥሉና ሲያስፈራሩ ይኼው አሉ።፡ሁሉም እኛ ካልገዛናችሁ እያሉ ወዮላችሁ! እያሉ ያስፈራሩናል። ይህ ሰው በነጭ ባንዲራ አውለብላቢ ቡድነኖች ፕሮፓጋንዳ “ብቸኛ ፍጡር” ተደርጎ በማየት ወደ አምላክነት ለውጠውታል።እሱ ከሌለ “የኢትዮጵያ መጨረሻ ይሆናል ይሉናል!”

ደሴ ውስጥ “እንደዛሬ ግድያና መፈናቀል አልበዛም” ብለው ለጠየቁ ዜጎች፤ “ለምን አስተዳደሬን ወቀሳችሁት” ብሎ ለደቡብ ሕዝብ ለገዴኦ-ተፈናቃዮች የሰጠው የተለመደው “አኩራፊው” መልሱ፤ ዛሬም ደሴ ላይ ደግሞታል። ያንን እንመለከታለን።


አብይ አሕመድ “ወሎ ድረስ ለመጎብኘት” ሄዶ ከሕዝቡ የሰማው ቅሬታ አልጣመውም። “እስላም እና ክርስትያን እንደ ዱሮው አልሆነም፤ እናንተ እንደምታወሩት “አንድ አይደለም”  ወሎ ምድር ውስጥ “መስጊድ ቤተክርስትያን” እኔ ልስራ እኔ ልስራ “ፉክክር” ገብተዋል፡ የቤተክርስትያን አባቶች ተጨንቀዋል፤ ቤተክርስትያን እተቃጠለ ነው፡ የደሴ ሕዝብ የነበረው ባሕላዊ መከባባር የጫት ሱስ አንድነቱን አፍርሶታል፤በየዩኒቨርሲቲው ደጃፍ ጫት መቃም ጣራ ነክቷል፡ ከ6 ሰዓት በላ ወጣቱ ጫት እየቃመ ቅዱስ ወንጌልንም ሆነ ቅዱስ ቁርኣን የሚማር ወጣት የለም፡ ግብረ ገብ የለውም፡ ለጫቱ ሱስ ማስቆሚያ መፍትሄ አምጡልን! አጣየ ውስጥ “የወታደር ልብስ የለበሰ “አሸባሪ” ማን አለበሰው?” ደረጃው የጠበቀ የወታደር መኪና እየነዳ መጥቶ ሕዝብን የሚጨፈጭፍ አሸባሪ መኪናውን ከየትኛው ሰማይ ተላከለት?” ፤ የህጻናት ዝውውር እየታየ ነው (ምን አይነት ወሬ እና ትዕይንት ነው እየታየ ያለው?!) በማለት አንድ መነኩሴ አምርረው ጠይቀዋል። 

ሌለው አባት ደግሞ  “ባቡር ተዘርግቶ ‘ደሴ ከተማ እንዳይነካው’ ተብሎ ጫካ ለጫካ አልፎ ሰው በማይደርስበት አካባቢ ዞሮ ለኪደርስ ወደ ታቀደት ቦታ ተዘርግቶ (ወደ ትግራይ) እኛን ወሎን ከላዋ ረግጦ ወደ መዳረሻው ተዘርግቷል፡ ይህ ሴራ ትርጉሙ ምንድ ነው? ሲሉ አንድ አባት ቄስ  ይህ የትግራይ ፋሺሰቶች ዘረኛ የሴራ ፖለቲካ እንቆቁሉሹ “ትርጉሙ ምን እንደሆነ” እንዲፈታላቸው አብይን ጠይቀዋል።

በማከታተልም አንዲት “ዓይነ ብርሃንዋ የተሰወረባት” እጅግ ብልህ የሆነች ወጣት “ዜጎች የሚኖሩባቸው ቤቶች በላያቸው ላይ በቡልዶዘር እየፈረሰባቸው ነው፤አማራው ዛሬም በየቦታው እየተጨፈጨፈ ነው፤ያማራ ልጆች በሚገደሉበት፤የአማራ ሕዝብ በሚፈናቀልበት እያየን ሳያመን ቀርቶ አይደለም (ክቡር ጠ/ሚኒሰቴር) ባንድ አመት ውስጥ ጤፍ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረስ? እንዴት እንኑር!? ዛሬም አገሪቱ በባሰ መልኩ ከድጡ ወደ ማጡ ዓይን ባወጣ በዘር ተበክላለች፤ እኛ ደሴዎች ኢትዮጵያን ብንዘምርም ውስጣችን ግን እያመመን ነው ያለነው፤አሮሞ መንበረ መንግሥቱን ተቆጣጥሮታል ……ወዘተ..ወዘተ.. ብላ አምርራ ለጠየቀቺው “የስርዓተ አልባው መንግስት መሪው አብይ አሕመድ በለመደው ሞላጫ ችሎታው እንዲህ ሲል ሁለት መልስ ሰጥቷል፡-

“አንድ አባት ቄስ ከምን ጊዜም ታይቶ በማይታውቅ ግድያ አሁን ተፈጽሟል’ ብለዋል።” ይህንን ስለታነገሩት ጉዳይ ልምልስ።…” በማለት የተለመደው አጭበርባሪ ፊቱን እንደ ኩራትም፤ ጠያቂውን እንደማናናቅም እያሰኘው “ተዋናይ የፊቱ ገጽታ እየለዋወጠ” እንዲህ ይላል፦

 “የሃይማኖት አባቶች ከናንተ በላይ የጥፋትን ጉልበት የሚያውቅ የለም። አባቴ! የበሩን ሜዳ ታሪክ የሚገልጸው እሱን አይደለም! (ይህንን ሲናገር የአብይ ቡቹላዎች አዳራሹን በጭብጫባ አጅበውታል! በደፈናው አንጨብቻቢዎቹ እና በማፏጨት ያጀቡት አጃቢዎቹ እነ ማን እንደሆኑ ለመረዳት የሚያቅታችሁ ኣይመስለኝም። ለምን ጭብጫባ እንዳስፈለገ “ምንጩ” ቢገባኝም ግን አልገባኝም።)…….. ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ባስተሳሰባቸው በሃይማኖታቸው ሲጮቆኑ ሲገረፉ ሲሰደዱ ነበር፤ አዲስ ታሪክ አይደለም። እኔ ደግሞ “ጅማ” ስለሆንኩ፤ ቡዙ የቦሩ ሜዳ ሰዎች ወደ ጅማ ተሰድደው እኛ ጋር ሰለኖሩ አውቀዋለሁ ታሪኩን (አሁንም ፉጮትና ጭብጫባ ተለግሶለታል፡ትርጉሙ እና እነማን መሆናቸውን ይገባችሗል ብየ እገምታለሁ)። “በእርግጥ የትናንት የዘሬን ያክል አይሰማም። እንደዛሬ “የፌስ ቡክ” ሚዲያ ስላልነበረ እንደዛሬ አይሰማም!” ….  በማለት ለተነገረው እውነታ መልስ ሲያጣ “ከጥላቻ ብዛት የተነሳ ‘ገድሎ የሰው ስጋ’ የሚበላበት የትግሬና የኦሮሞ አስተዳዳር ያስከተለው “ፋሺስቶች አረመኔ ዘመን” ያውም ‘የሰው ልጅ መሃል ከተማ በቀትር ጠራራ ‘ፓሎ ላይ ተዘቅዝቆ የሚጨፈርበት” የመለስ/ተሓህት/ እና የአብይ/ኦሆዴድ/ የእልቂት ዘመን” ከ ከቦሩ ሜዳ ፍርደገምድል ጋር አነጻጽሮ መልስ ነው ብሎ መልሶላቸዋል። ያውም “ኦሮሞ ከማይናገር ኢትዮጵያዊ ጋር ጋብቻ እንዳትጋቡ፤ንግድ እንዳትገበያዩ” እያሉ እነ በቀለ ገርባ ያለ ምንም ስጋት የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ቸል ብሎ ልቅ ሲለቃቸው ፤ “ዘረኞች” ልባችሁ ነፍታችሁ የፈለጋችሁን የጥላቻ ንግግር አሰራጩ ተብለው በሚፎልሉበት አገር፤ ከቦሩ ሜዳ ጋር እያነጻጻረ መልስ ሲሰጥ ስቅጥጥ አላለውም።

በእውነት አሁን ይህ ከአንድ መሪ የሚጠበቅ መልስ ነው? የካራማራ ጀግናው የወለጋ ኦሮሞው ተወላጅ “አሊ በርኬ” ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ ስለሚል ከእርሱ ጋር አብረን ግብዣ አንበላም” የሚሉ “የሰው እንሰሳዎች” የሚያሽሞነሙናቸው አናርኪስቱ አብይ አሕመድ ኦሮሞዎች ተገቢውን ነፃነትና ሥልጣን አልያዙም ይለናል።   

((በነገራችን ላይ እባካችሁ “የአሊ በርኬ” ስልኩ ካላችሁ ስጡኝ፡ አንድ ነገር ልልከለት አፈልጋለሁ፡ታማኝ ካነበብከኝ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል። ከኔ ጋር ‘ፖለቲካዊ ጸብ’ ቢኖርህም ለዚህ አርበኛ ስትል የግል ስልኩን ላክልኝ!!)
 
አውነት ሲነገረው ‘የሚያኮርፍ’ አብይ አሕመድ ከወራት በፊት ወደ ደቡብ ክፍላችን በመሄድ በጠባብ ኦሮሞ ወረቦሎች የተፈናቀሉት በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ለማነጋገር ሄዶ “አንተ ስትመጣ ሞት በረከተ ፤ ስደት በረከተ፤ መፈናቀልና መከራ በዛብን..” ብለው አምርረው ቅሬታቸው ለተናገሩ ተፈናቃዮች “እኔ ከስልጣን ስወርድ ይቆማል’ ብሎ “ለምን የኔን ስልጣን ነቀፋችሁ፤ለምንስ አመረራችሁ” ብሎ ያለውን ይህ አስቀያሚ ንግግሩ በስደተኞች ላይ ማሾፉንና ቅሬታቸውን ማጣጣሉን ‘ክፉኛ እንደተተቸ’ የሚታወስ ነው።

ያ እንዳይበቃ፤ ዛሬ ደግሞ “ለምን አስተዳደሬን ተነቀፋችሁ” በሚል ቁጭት ተነሳስቶ “ሰለጠነ በተባለበት ዘመን ፤ ዲሞክራሲ አለ በተባለለት ዘመን” ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ በመንግስት የታገዘ መፈናቀል እና ግድያ ፤ በመንግሥት የታገዘ ትዕዛዝ የአዛውንት እና ነብሰ ጡሮች መኖርያ ቤቶች ሲፈርሱ “አላያሁ አልሰማሁ” እያለ የግፉ አስፈጻሚ መሆኑን ለመደበቅ ሲል  ፤ የዜጎችን ሰቆቃ ምንም ሳያሳስበው ‘ስንት እና ስንት አመት ያለፈበትን ዘመን’ ወደ ላ ሄዶ  በአፄ ዮሐንስ ትዕዛዝ ምላሳቸው የተቆረጡ ቱምቧሆ እየቃሙ ለተገኙ አፍንጫቸው ለተፎነኑ ጥቂት የወሎ ኗሪዎች (እስላሞች) እና ክርስትያኖች “ለጅማው ልጅ” ለአብይ አሕመድ፤ “የቦሩ ሜዳን” ኢፍትሃዊ  የነበረው “ንጉሳዊው” ፍርደገምድል ‘በዲሞክራሲ ያልታነጹትን ከነገሥታት’ እርምጃ ጋር እያነጻጸረ እዚህ ግባ የማይባለውን “የቦሩ” ፍርደገምድል ማወዳደሩን ሳደምጥ ይህ ሰው “ታሪክ የማያውቅ” (ልክ ባሮ ቱምሳ ኦነግ ገድሎት መንግስት ነው የገደለው ብሎ ያለውን ድንቁርናውን ያክል) የሚገርም “ደካማ” ሰው ነው።

 አብይ መስማት የሚፈልገው ነገር ካለ “አትውቀሱኝ” ፤ “ሰላም ነን በሉኝ” “አብይ! አብይ” በሉኝ” የሚል ሱስ ይዞት ናላው የሙገሳ ስካር ‘ፍላጎቱ’ ሕሊናው በጥብጦታል። አጨብጫቢዎች ጫማው ስር እየወደቁ አስክረውታል፤ ሱስ አስይዘውታል! በቃ! ወቀሳ የማይወድ ልክ “ሁለተኛ መለስ ዜናዊ” የሆነ አሳፋሪ መሪ እየሆነ መጥቷል? ቁርጥ መሪውን መለስ ዜናዊ የተካ!

ይህ ሰውየ ስለ አማራ እልቂት፤ ስለ ኦርቶዶክስ ሰቆቃ ተነስቶ ለሚጠይቅ መልሱ ሁሌም ማጣጣል ነው። ሕግን የጣሰ ትግሬዎች ለሁለት ጊዜ የተሾሙበት ቤተእምነት “ሁለት ጳጳሳትን መሾም” ሕጋዊ አድርጎት ቆጥሮት “አስታርቄአቸዋለሁ” እና አመስግኑኝ ሲል ተናግሯል። ባህርዳርንን ለመተዋወቅ መጀመሪያ ሲጎበኝ የአካባቢው ካሕናት ተነስተው ሲወጥሩት ስለ አማራ እና ክርስትያኖች መገፋት መቆም እንዳለበት አቤት ሲሉ “ተመሳሳይ መልስ ነበር እያጣጣለ ጎጃሜዎችን የመለሰላቸው”። ዛሬም ደሴ ውስጥ ማጣጣሉን ደገመው። ባለፉት ወራትም የገዴኦ ተፈናቃዮች’ ከአምና ይልቅ ”ባንተ ጊዜ መፈናቀልና ግድያ በረከተ” ብለው ለሚያማርሩ ተመሳሳይ የማጣጣል መልስ ነው የሚሰጠው “ገና ግድያውና መፈናቀሉ ይጥላል!” የሚል መልስ ነው ‘በቃ’ ይህ ነው መልሱ!

ግድያ እና መፈናቀሉ እንደሚቀጥል እያወቀ ለማስቆም ምንም ነገር አያደርግም። ለምን አታስቆመውም፤ ተብሎ ሲጠየቅ ወይንም ‘ሲፈናቀሉ’ ደግሞ “አልሰማሁም አላያሁም” የሚል መልስ ይሰጣል። አጭበርባሪ መሆኑን ለማወቅ ቀላል ነው።መጽሐፍ ላይ ያነበበው ፍልስፍና በሰው ህይወት ሊፈላስፍበት የሚሞክር “እንዝህላል” ጀነሳይዳል” መሪ ነው።

ኦሮሞ ስልጣን ላይ ነው ብላ ላመረች ይህች ወጣትም፤ “ኦሮሞ ስልጣን ላይ የለም” ሲል “ባይነ ደረቅነት” ይመልሳል። ስለ ኦሮሞዎች ወያኔ ትግሬዎችን የመተካት ማስረጃ በተመስገን ደሳለኝ የቀረበ ሰነድም ሆነ በተለያዩ ምሁራን እና ቅሬታ እቅራቢዎች የተለቀቁ መረጃዎች ስላሉ እነሱን ተመልከቱ። ያንን ማስረጃ አብይም ሆነ ኦሮሞዎች በማስረጃ እስካሁን ድረስ አልመከቱትም። የወያኔ ትግሬዎች ሥልጣን እንደተቀራመቱ እንዲያ ያለ ጥያቄ ሲቀርብባቸው ቀጣፊነታቸውን ስለሚያውቁ ‘ማስረጃውን መመከት አልቻሉም”። አብይም እንደዚሁ! ሁለቱም በቅርምት ስለተጠመዱ ‘ያንን ማስረጃ መጋፈጥ አይችሉም!”። ሌባ ዘርፎ ሲያበቃ “ዝርፌአለሁ ብሎ ራሱን ለቅጣት አያቀርብም!

   ሌላው ርዕስ ከያኒት አስቴር በዳኔ እና የአገው አዝማሪ እና ዳንኪረኛው መኳንንት መለሰን ከነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ቡድኖች’ ሥር መካተታቸው እንመለከታቸዋለን።

ሰሞኑን በርካታ አዝማሪዎች ወደ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ሰልፈኛው ቡድን” በመቀላቀላቸው እያስደመሙን ሄደዋል።ባለፈው ክፍል 2 ነ መስፍን በቀለን ተመልክተናል። ዛሬ ድገሞ ከነኚህዎቹ በከያኒነት (አርቲስት ይሉዋቸዋል መሰለኝ በወያኔ ዘመን አጠራራር ማዕረግ) የምትታወቀዋ ከአማራ እና ከኦሮሞ እወለዳለሁ የምትል ከያኒት “አስቴር በዳኔ” (ሰሞኑን) እና የአገውኛ አዝማሪና ዳንኪረኛው “መኳንንት መለሰ” (ብግንቦት ወር) ወደ ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ቡድን ተቀላቅለዋል።

የዘመኑ የዩቱብ ቱልቱላዎች “አስቴር በዳኔ ዛሬም የልቧን አፈረጠችው የምትገርም አርቲስትን ያለማድነቅ ከባድ ነው” እያሉ በዩቱቡ ሲዘረጉላት እያደምጥኩ ተገርሜኣለሁ። በዘንድሮ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ንቃት ሁሌም እገረማለሁ። በዚያ ‘የየዚያ-ትውልድ’ የ66 ቱ ‘ሴት ታጋዮችም’ ሀኑ  የ የዚያ ዘመን “ሴት ከያኒያን” ድፍረትና ቆራጥንት ያላየ የዘመናችን ወጣት “አስቴር በዳኔ” ወያኔዎች ጋብዘዋት “ደደቢት” በረሃ ሄዳ የተናገረቺው “ትርኪ ምርኪ” ሲያሞካሹላት እና ሰማይ ሲሰቅልዋት የመገረሜን ያህል ‘ዛሬም ልክ እንደ ታቻምናው “ትርኪ ምርኪዋን” እየሸጡላት ነው።

"ኢትዮጵያ የፈራረሰች የምትመስለው “ፌስ ቡክ” ላይ ነው” ትላለች አዲስ ዘመን ከተባለው የወያኔ ቱለቱላ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ ቀርባ የሰጠቺው ‘ትኩሲትዋ ፖለቲከኛ’። በላያቸው ላይ ተኝተው በቡልደዘር እየፈረሰባቸው ላሉት እና ለሚፈናቀሉት፤ለሚታረዱት፤ለታመጹት ልጃገረዶች እና ባለትዳር እመቤቶች “አገራቸው እየፈራራሰች እየሄደች መሆንዋን በፌስ ቡክ ላይ ያዩት የሕልማቸው ቅዠት ነው” ልትለን ነው ይህች ከያኒት። ፖለቲካ ገብቼ ልወዳደር ነው እያለች “አብይ አሕመድ “በአንድ አመት ውስጥ የሰራው ስራ የአሰር አመት ስራ ነው”  ስትል እያሞካሸቺው እንዴት ወደ ፖለቲካ ገብታ ይህንን ይዛ “እንደምትፎካከረው” አልገባኝም። ፖለቲከኛዋ በዚህ ብቻ አላበቃችም እንዲህም ትላለች፦

“ቆሻሻ ስለሚጠርግ ይሰደባል፤ ችግኝ ስለተከለ ይሰደባል፤ሰው ስለማያስር ይሰደባል፤ ሰው ስለማይገድል ይሰደባል፤ ሰው ስለማይሰደብ ይሰደባል፤ አንዳንድ ጊዜ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ግራ ይገባኛል!” ብላለች። “ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንድያ ነው የሚል ሕዝብ ነው”  እንዳሉት ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም ‘አስቴር በዳኔም’ የራሱን ዘረኞችን ከማጽዳትና ከማስቆም ይልቅ “ቆሻሻን” ማጽዳቱ “ቀዳሚ’ ቁም ነገር ተደርጎ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ግራ ይገባኛል ብላ “ወርቅ ላነጠፈለት ፋንድያ ነው ይላል ‘ የማሉትን አባዜ ደግመዋለች።

ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ሳታውቅ ወደ ‘ፖለቲካ ተፎካካረነት’ እገባለሁ ማለትዋ የሚገርም ነው። ለመሆኑ እስክንድር ነጋ ምን እንደሚፈልግ የማያውቅ ወይንም በፖለቲካው  ዐለም ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ አያውቅም ሆኖ ነው እንዲህ በአብይ ስርዓትም እየተንገላታ እና እየተዛተበት ያለው? ወይ ጉድ! “ፍቅር ያለሸነፈን ሕዝቦች ነን” ብላ ስትደመድም የሚገርም ነው። አብይ አሕመድ እስክንድር ነጋን ምን የሚሉት ፍቅር አሳይቶት ነው እንዲህ ስለ አብይ ፍቅር ሰባኪነት የምትነግረን? “የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይን የሰላም ስብከት ከይሁዳ ሰላምታ ለይተን አናየውም!” የሚሉ ተሰላፊዎች መፈክር አላነበብች ይሆን?

የሚገርመው ደግሞ እንዲህ ያለቺውን መልሶ አስገርሞኛል፦

“50 አርቲስቶች (ከያኒያን) ወደ ቻይና ለሥልጠና ሲላኩ እኔ አልተላክሁም። እኔ ዶ/ር አብይን ስደግፍ በነበርኩበት ወቅት፤ ከተላኩት ውስጥ አብይን ሲቃወሙ እና ሲሳደቡ የነበሩ ወደ ቻይና ሄደዋል። ስለመደመር እየተወራ ተቀንሻለሁ።” ስትል እሮሮዋን ገልጻለች።

ሕዝቡ እንደሆነ ሊረዳሽ አይችልም፤ ምክንያቱም “ምን እንደሚፈልግ ለራሱንም ስለማያውቅ!” ብለሽ ደምድመሻል። ምን እንደሚፈልግ ለሚያውቀው የአስር አመት ስራ በአንድ አመት ያጠናቀቀው ‘ፈጣን መልስ ሰጪው ፤አብይ አሕመድሽን’ አደልዎና ዘረኛነት ለምን “ዓይን አውጥቶ እየባሰበት እንደሆነ” ብትጠይቂው መልስ ልታገኚ ትችይ ይሆናል። እኛ ግን ቅሬታሽን አንብበናል። ቆሻሻ ከመጥረግ “የአድለዎ ቆሻሻ” ከማሪዎችን “ከየመስራቤቱ አጥራ” ብለን ያልንበት ምክንያትም ይህ ነው። ለመሆኑ “በዕምባ የታጀበው” የኢትዮጵያ ምርጥ የልብና የውስጥ ሕመም የጥገና ባለሞያ ሓኪሞች “አቤቱታ” ምን እንደሚፈልጉ አያውቁም’ ብለሽ “ሕዝብ” ከምትይው “ሕዝብ” አስገብተሻቸው ይሆን? እባክሽን ረጋ በይ! ትወና እና እውተኛ ህይወት ይለያያሉ።

የአስር አመት ስራ በአንድ አመት ውስጥ ያከናወነው አብይ “የተሽመደመደ መንግሥት” ከተባሉት 25ኘው ተራ ተመዝገቧል። እንዲህ ተቀምጦልሻል።

This is a list of countries by order of appearance in the Fragile States Index (formerly the Failed States Index) of the United States think tank Fund for Peace.

A fragile state has several attributes. Common indicators include a state whose central government is so weak or ineffective that it has little practical control over much of its territory; non-provision of public services; widespread corruption and criminality; refugees and involuntary movement of populations; and sharp economic decline.[1] በቃ ይህ ነው።

 “መኳንንት መለሰ”

በመጨረሻም አዝማሪና ዳንኪረኛው “መኳንንት መለሰ” ምርጥ ኢትዮጵያዊ እየተባለ  አገር ውስጥም ዋሺንግቶን መጥቶ በነበረበት ወቅትም “ኢትዮጵያዊ ቀናኢነቱን” ሲወራለት የቆየው ይህ የአገውኛ አዝማሪና ዳንኪረኛ በግንቦት ወር ጉድ አይተንበታል።  የውርደት ዘመን ተብሎ በአገር ወዳድ ምሁራን የተሰየመው “በግንቦት ወር ውስጥ ፋሺስታዊ ስርዓት” ይዞልን የመጣውን ወያኔ ወደ አዲስ አባባ የገባበትን ወር ለመዘከር እንዲጨፍርለት ሲል ይህ አዝማሪ “ዘር ማጥፋት ወደሚካሄድበት” “ራያ” ወደ ተባለው ወያኔ በጉልበት ወደ ትግራይ ወደ አጠቃለለው ‘አጨቃጫቂ’ ቦታ በመሄድ ሲጨፍር በቪድዮ አይተናል።ከታች የምትመለከትዋቸው ‘ጊታሪስቶች’ የወያኔ ሙዚቀኞች ናቸው።
እንኳን ለግንቦት በዓል አደራሳችሁ! በማለት በአገውኛ መድረኩን በመክፈት ወያኔዎችን አስጨፍሯል። በአገውኛ ምን እንዳለ ባለውቀም ከወያኔ ‘ጨፋሪ ጀሌዎች’ ሽልማቱን በገፍ ጎርፎለታል። አብይ አሕመድም “እንኳን ለግንቦት በዓል አደረሳችሁ!” ሲል ነጭ ባንዴረ አውለብላቢ አዝማሪዎችም የአብይን ቃል በመድገም “እንኳን ለግንቦት በዓል አደረሳችሁ!” በማለት ቤት ንብረቱ እየፈረሰበት ለሚፈናቀለው ዜጋም ሆነ በግደድ ትግሬ ሁን ተብሎ የዘር ጽዳት ለሚፈጸምበት የራያ ሕዝብም ሆነ የወልቃይት ሕዝብ ላይ የሚያሾፉ ‘ነጭ ባንዴራ አውለብላቢ አዝማሪዎችና ዳንኬራ መቺዎች’ በታሪክ መወገዝ አለባቸው።

ድሮስ እሺ ይሁን የኪነት ሰዎች “ፈርተው” አድርጉ የተባሉት በግድ ሲያደርጉ ነበር እንበል ፤ ዛሬ የመሰላችሁ ነገር ‘እምቢ” የማለትም ሆነ “ያለ መሳተፍ” ነፃነት ሰጥቻችሗለሁ ብሎ የነገራቸውን አብይ አሕመድን ፈርተው ይሆን ይህ ሁሉ “ኢሳያስ አፈወርቂን ይቅርታ የመጠየቅ” ፤ “ወያኔ መንደር ጋር ሄዶ ዳንኪራ መምታት” ፤ “እንኳን ለግንቦት በዓላችን አደረሳቸሁ” የሚለው የደንቆሮዎች ጩኸት እንዲያስተጋቡ “ማን አስገደዳቸው”?  እነኚህ አድርባዮች “ከሰለሞን ተካልኝ” በምን ይለያሉ?
ነጭ ባንዴራ አውላቢዎች ቁጥር 4 ይቀጥላል፡…………………\
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (አትዮ ሰማይ አዘጋጅ)  (getachre@aol.com)