Saturday, May 19, 2018

ስለጻፍኩት ደብዳቤ ለጠያቂዎቼ መልስ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ትኩስ ዜናየወያነው አምባሳደር ካሳ ተ/ማርያም ዲያስፖራዎች ‘ጮሃችሁ አልጮሃችሁ በጭሆት የምታመጡት ነገር የለም!” ሲል ዘለፋወን አስተጋባ!

የወያኔው አምባሳደር ካሳ ተክለማርያም “ውጭ አገር ያለነውን ኢትዮጵያውያን ዜጎች “ጮሃችሁም አልጮሃችሁም የምታመጡት ነገር የለም “ ሲል 45 አመት ወያኔ ያስተማረው የተጠናወተው ወያኔያዊ አሽከርነቱን እና ንቀቱን ዛሬም አትላንታ ውስጥ ደገመው። እንባቢዎቼ የወያኔው ደረገጽ ‘ዓይጋ” ድረገጽ ሄዳችሁ ጎብኙት እና ሰውየው ዛሬም በተጠመቀበት አሳፋሪ ፋሺስታዊ ርዕዮት ላይ እየተወራጨ እንደሆነ አድምጡልኝ። ከታላቁ መሪያችን ንግግር ልዋስ እና እየተባለ የመለስን ንግግር ሲዋስ የነበረው ካሳ ተክለማርያም፤ ዛሬ “ከደ/ር አብይ ንግግር ልዋስና“ የሚለው የሰሞኑ አዲስ የፋሺን ንግግር” እሱም ከዶ/ር አብይ ንግግር ልዋስና እያለ እዚህም እዚያም የሚዘላብደው የትውስት ንግግሮቹ መሸፈኛ ቢጠቀምባቸውም “የድሮ አለቆቹ ወያኔዎች ያስተማሩትን ትምክሕታዊ ንግግሮቹ (“ጮሃችሁም አልጮሃችሁም የምታመጡት ነገር የለም “) የሚለው ንግግሩ ስታደምጡ ዛሬም ዓለማዊ ወያኔነቱ እስከ የአለም ፍጻሜ የሚኖር መስሎታል። አገዋዊው ተክለብርሃን ካሳ በጎጃሜዎቹ አዊያዊያኖቹ ሙዚቃ የታጀበው ንግግሩ-ለማድመጥ

"የአምባሳደር ካሳ ተክለብርሀን አቅም እና የመንግስታቸዉ መልእክት ሁሉም ዳያስፖራ ዘንድ እንዲደርስ ተመኘዉ ።

የሚለውን አድመጡ እና ሰውየው ዛሬም በኖረበት የስድብ እና የንቀት ቅዠት ዛሬም እንዳልተላቀቀው  ትታዘባላችሁ። ይህ ሰው የሚመራው ኤምባሲ የአትዮጵያን ሰማይ “ለጽ/ቤቱ” የጻፈው ደብዳቤ መልስ ያገኛል ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ካሳ የሚመራው ኤምባሲ ለዜጎች ጥያቄና አስተያየት ዋጋ የማይሰጠው መሆኑን በታሪክ ለማስመዝገብ ነው። ካሳ ተክለብርሃን ማነው የሚለው ማሕደሩ ባለሥልጠኖችን የማጋለጥ በር ሲከፈት ለወደፊቱ ስለ ካሳ አብረን እየተከታታልን እናቀርባለን። ወያኔዎች እና አሽከሮቹ አምባሲዎች እስከተቆጣጠሩት ድረስ ዜጎች የሚጠይቁትን አስተያት መልስ ስለማያገኝ ‘እኛ ተቃዋሚዎች መጮሃችንን፤ መቃወማችንን፤ ማጋለጣችንን” የሚቀጥል መሆኑን ካሳ እና መሰል የወያኔ አምባሳደሮች እንዲያውቁት ዛሬም “አለን” እንላቸዋለን።

ራን አንባቢዎች ጉዳዩ በሚመለከት ለዛሬ የቀረበው ርዕስ በዘመነ ወያኔ ግብረሰዶም በኢትዮጵያ ምድር እንዴት እንደተስፋፋ ለማየት ይሄው አንብቡ። መልካም ንባብ።


ለጻፍኩት ደብዳቤ ለጠያቂዎቼ መልስ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

የኢትዮጵያ ሰማይ ዋሺንግተን ውስጥ ለሚገኘው ለወያኔው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት Ethiopia should close the Finland & Denmark Embassy in Addis Ababa for violation of Ethics!

አዲሱ ጠ/ሚኒስተር የዴንማርክ እና የፊንላንድ ኤምባሲ ጽ/ቤት ከአገሩ እንዲያባርር እንጠይቃለን!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)’ የሚል ደብዳቤ በ5/17/2018 (አውሮጳ ዘመን) መጻፌን ይታወሳል። ኤምባሲው የኢትዮጵያዊነት ባህል ያከብራል ብየ ሳይሆን ታሪክ እንዲዘግበው ነው የጻፍኩለት።ኤምባሲው እስካሁን ድረስ መልስ አልጻፈልኝም። የወያኔ ኤምባሲ የሚቆጣጠረው ኤምባሲ የኢትዮጵያ ዜጎች ለሚጽፉዋቸው ቅሬታዎች እና አስተያየቶች እንደ ሰለጠኑት አምባሲ አገሮች ለዜጎች ክብር ቃል እና ጥያቄ በማክበር ወዲያውኑ መልስ እንደሚጽፉት ሁሉ ይህ ኤምባሲ ተቃዋሚውን እንደ ዜጋ የማይመለከተውን ‘ጠያቂ’ ለጠየቀው መልስ አንጠብቅም። እስካሁን መልስ አላገኘሁም፤ ለወደፊቱ መልስ ከጻፈ አንባቢዎቼን አሳውቃችኋለሁ።

ይህ ካልኩኝ በኋላ በጻፍኩት ደብዳቤ ምክንያት ተቃዋሚ አስተያየቶች ደርሰውኛል። የቀረበው አስተያየትም “እንዲህ ያለ ስነ ምግባር ተፈጥሮ እንጂ ‘ባህሪ’ አይደልም ስለሆነም የጻፍከው ደብዳቤ የሰው ልጅ መብት መጋፋት ነው” በሚል ነው የደረሰኝ አስተያየት። እኔም ይህ የተፈጥሮ ሳይሆን በሽታው የሕሊና የባሕሪ ለውጥ ያመጣ ክስተት ስለሆነ መታከም ይቻላል፤ የሚል ክርክሬን አስሰምቻለሁ። ለዚህም በማስረጃ በቪዲዮ አስደግፌ ለአስተያየት ሰጪዎች ልኬላቸዋለሁ። በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው የባህል ጥቃት እየተካሄደ ያለው በ666 ማሕበሮች መሆኑን ተከራክሬአለሁ። በወያኔ እስር ቤቶችም ወንዶች እየተደፈሩ መሆኑን ሰምተናል። ይህ የተቀነባበረ ዘመቻ በሰፊው በሚመለከት በአዲሱ መጽሐፌ የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? (ደራሲ ጌታቸው ረዳ) በሚል መጽሐፌ ውስጥ “ሳብቨርዥን” (አፍራሽ የባህል ለውጥ በኢትዮጵያ) በሚል በገጽ 211 ላይ “ግብረሰዶማዊ የዝሙት ቱሪዝም በዘመነ ወያኔ!”  በሚል ሰፊ ማስረጃ እና መፍትሄው የገለጽኩበትን እንድታነብቡ እጋብዛለሁ። እነሆ፡


ምዕራፍ 8
ግብረሰዶማዊ
የዝሙት ቱሪዝም በዘመነ ወያኔ!
 በኢትዮጵያ ምድር የግበረሰዶም ህይወት በወያኔ ሥርዓት ለምን እንደ እሳት ሰደድ ተስፋፋ? የሚለው ጥያቄ መልሱን ‘ሳቨርዢን’ በሚለው ርዕስ የተመለሰ ስለሆነ ያንን አንቡቡ። ይህ ጉድ በሰይጣን አምላኪዎች 666 ኢሉሚናቲ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና በአረቦች ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። ወያኔም ለምዕራባዊያን እና ለዓረቦች ስለሚያጎበድድ፤ ለዝርፍያው ምንጭም የሚያገኘው የገንዘብ ብድር ከእነሱ ስለሆነ ይህ አስነዋሪ ባሕር እንዲስፋፋ በቸልተኛነት ለቅቆታል። አንዳንዱም ጫካ ውስጥ እያለ ያጋጠመ ባሕል እንደነበር የሚናገሩ ነባር ታጋዮች ሰምቻለሁ።

በኢትዮጵያ ምድር የግበረሰዶም ህይወት በወያኔ ሥርዓት ለምን እንደ እሳት ሰደድ ተስፋፋ? የሚለው ጥያቄ መልሱን ‘ሳቨርዢን’ በሚለው ርዕስ የተመለሰ ስለሆነ ያንን አንቡቡ። ይህ ጉድ በሰይጣን አምላኪዎች 666 ኢሉሚናቲ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና በአረቦች ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። ወያኔም ለምዕራባዊያን እና ለዓረቦች ስለሚያጎበድድ፤ ለዝርፍያው ምንጭም የሚያገኘው የገንዘብ ብድር ከእነሱ ስለሆነ ይህ አስነዋሪ ባሕር እንዲስፋፋ በቸልተኛነት ለቅቆታል። አንዳንዱም ጫካ ውስጥ እያለ ያጋጠመ ባሕል እንደነበር የሚናገሩ ነባር ታጋዮች ሰምቻለሁ።

ግብረሰዶማዊያኖቹ አርስ በርሳቸው ሲጠራሩ “ዜጋ” በሚል ሰም ይጠራሉ። ከግብረሰዶም ውጭ የሆኑትም “ቀጥ” በሚል ይጠርዋቸዋል። ቆንጆ ወንድ ይዛ የምትራመድ ሴትን ቆንጆውን ወንድ ነጠቀችን ለማለት “ዓይነጥላ” ይሏታል።በዚህ ህይወት ተዘፍቀው በሺዎች በምድረ ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ብዙዎቹ ራሳቸውን ገድለዋል። በጣም በቀልተኞች ስለሆኑ እነሱን የሚዘልፍ ሰው ክፉ ብቀላ እየተበቀሉ አገሪቷን ግበረሰዶም እንዲራባ አድርገዋል። ገብረሰዶማዊያኖቹ አንዳንዱ በተዋህዶ ቤተክርስትያን ጥረት ወደ ተፈጥሮአዊ ህይወታቸው ወደ ክርስትያን ህይወት ከተመሰሉ በኋላ “ግብደረሰዶማዊ ህይወት የዲያብሎስ ስራ ስለሆነ መንግሥት በሚዲያው የዚህ ህይወት መጥፎነት ከግበረሰዶማዊ ህይወት የወጡትን ቃለ መጠይቅ እያደረገ የዚህ ህይወት አስከፊነት ለሕዝብ እና ለወላጆች እንዲነግሩ ቢጠይቁም ፈቃደኛ እንዳልሆነ አንዳንድ መረጃዎች ይገልጻሉ። ያም ሆነ ይህ ግብረሰዶማዊ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሴቶቹም ወንዶቹም በዚህ ህይወት በሺዎቹ በየከተማው በጥንድ በጥንድ ሆነው ቤት እየተከራዩ፤ ትዳር እየመሰረቱ ፤ማታ ማታ የራሳቸው የዳንስ ምሽት ድግስ መስርተው ብዙ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በምስጢር ማታ ማታ ተሸሽገው እንደሚጋርዋቸው ተናግረዋል። ያም ሆነ ይህ የወያኔ መንግሥት ቸል ቢለውም  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ይህ ጉድ “የሴቶችና የወንዶች” ግበረሰዶማዊያን ባሕሪ  በየዩኒቨርሲቲውም ጭምር ሳይቀር ተስፋፍቶ በማየታቸው አሳሳቢ ሆኖ ስለተገኘ በዛው ወቅት የወያኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትረያሪክ የነበሩት ሟቹ አቡነ ጳውሎስ የሃይማኖት መሪዎችና የሚመለከታቸው ድርጅቶችን አፍሪካ አዳራሽ ላይ በመሰብሰብ፤ የሚመሰገን ታሪክ ሰርተዋል።

የፓትሪያሪኩ ንግግር ባጭር ልጥቀስ እነሆ፤

<< ሰለጠኑ በሚባሉ ሌሎች አገሮችና በመሳሰሉ የታየ ቢሆንም ይህ ባገራችን ያልተሰማ  የማይታወቅ  አዲስ ነገር ነው። ይሁንና በአካባቢያችን አዲስ ክስተት ሆኖ ዜናው በመሰማቱ በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን ሰው ያከበረውን እና የወደደውን የሰው ልጅ ክብረሕሊና የነካ ስለሆነ ይህ እንቅስቃሴ- ባስቸኳይ  ሊገታ የሚገባ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። መጀመሪያውኑ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ሴትና ወንድ አድርጎ የፈጠረው የሰው ዘር እንዲባዛ ነው። ሰው ብቻ አይደለም ‘እንጨቶችም ወንድ ሴት ናቸው”>> ሲሉ ድንቅ የሆነ ንግግር ማድረጋቸው የሚዘከር ነው። (ምንጭ አባ ጳውሎስ አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ) (104)
‘ደረጀ ነጋሽ ዘወይንዬ’ (104) የተባሉ የቤተክሕነት ሊቅ ይህንን ዘገባ በሚመለከት ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ተግባር መናሃርያ መሆን የለባትም በሚል ግብረሰዶማዊያን የነበሩትን ቃለ መጠይቅ በማድረግ EOTC "ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666”  በሚል የቪዲዮ ርዕስ እንዲሰማውና የሚመሰገን ዘገባ በቪዲዮ’ ዩ-ትዩብ ዘርግውታል።ሰይጣን የሚባለው 666 ምልክት ያለበት ሌላ ሳይሆን “ክፋት የተጠናወተው የሰው ዘር ነው”።ይህ ዓለምን የሚያስተው ክፉ መንፈስ ያደረበት ሰው። በገንዘባቸው፤ በጥበባቸው፤ በሃይላቸው በዓለም ተሰሚነት ያለቸው፤ ጫና መፍጠር የሚችሉ የአውሬ መንፈስ ጉዳይ አስገፈጻሚ አካላት ናቸው። እነዚህም በ666 ጥበብ ተማርከው ይከተሉታል።       (ሀ) የሰዶም ሃጢያት
ሐጢያተ ሰዶምን፤ከስድስት ስድሳ ስድስት ከ7ቶቹ ራሶች አንዱ የሰዶም ሐጢያት ሲሆን፤ ይህም ማለት ‘ግብረሰዶማዊነት’ ነው። በአራዊት ምስል የሚመሰለው  ከ7ቱ ወይም 10 ቀንዶቹ አንደኛው 666 ነው ‘ሲባል’ የ666ቱን ዓላማ ለማስፈጸም /የተለያዩ ክፉ ስራ ለመስራት የተሰማሩ ለባለ ገንዘቦቹ እና ተሰሚነት ላላቸው ሃያላት አጋንንቶቹ ድጋፍ ሰጪ/አቀነባባሪ ክፍሎች ማለት ነው። (እንሰሳ ማለት አይደለም፤ በተለያዩ ዘርፎች የተሰለፉ  የጫና ፈጠሪዎቹ አካላት ጉዳይ አስፈጻሚ ክፍሎች ማለት ነው። በዚህ መጽሐፍ “ሳብቨርዢን ብየ የተነተንኩትን የሚያካትት ነው) ።መጽሐፍ ቅዱስ በምሳሌ ነው “አራዊትና ሰይጣን” አስመስሎ እያስተማረን ያለው።

እንቀጥል!
ተመሳሳይ ጾታ ያለው ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስ ‘ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 19 ውስጥ ከቁጥር 1 ጀምሮ ታሪኩ ተገልጿል።እስራል ውስጥ 5ቱ አውራጃዎች ማለትም ‘ሰዶም፤ ገሞራ፤ አዳማ፤ ሲባማ፤ ሲባዩን”  ወንዶች ከወንዶች ጋር ባለቸው ጾታዊ ግንኙነት፤ እግዚአብሔር ተቆጥቶ በእሳት አጥፍቶአቸዋል ።ግብረ ሰዶም ማለት “የሰዶም’ ስራ ማለት ነው። ግብረሰዶማዊነት በዓለም ላይ ተስፋፍቷል። እንደ አሜሪካ ስዊድን፤ ኖርወይ፤ ፊንላንድ፤ ካናዳ ቤልጅም፤ አውስትራሊያ፤ ግብረሰዶማዊነት ሕጋዊ ሲሆን፤ ከአፍሪካ አገሮች ውስጥ ደግሞ “ደቡብ አፍሪቃ እና ሌሎች ሕጋዊ አውቅና ሰጥተው፤ ግብረሰዶማዊነትን እያስፋፉ ሲሆን ፤ በቅርቡ ደቡብ አፍሪቃ የግብረሰዶማዊያን የቁንጅና ውድድር አካሂዳ “ኢትዮጵያዊ ግበረሰዶማዊ” በውድድሩ ተካፍሏል። ይህ አሳፋሪ ተግባር ነው። 
(ለ) ግብረሰዶማዊነት በኢትዮጵያ

በአገራችን ግብረሰዶማዊነትን እያደገ    በምመጣቱ በተጨማሪ፤ እነዚህን እኩይ ተግባር የሚቃወሙትንና የማይፈልጉትን ‘መበቀል፤ መድፈር፤ ማታለል’ ተያይዘውበታል ።  ይህ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ወንጀል ነው። በ1997 ዓ.ም የወጣው የኢፌድሪ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 629 ላይ የተፈጥሮ ባሕሪ ተቃራኒ የሆኑ ወይንም፤ ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ከሌላ ሰው ተመሳሳይ ጾታ ካለው ሰው ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ወይንም ግብረሰዶም ቢፈጽም ያስቀጣል ይላል። <ግን እየተፈጸመ ነው!!>። ይህ የግብረሰዶማዊነት ተግባር በመጽሐፍ ቅዱስ፤ በእግዚአብሔር ፍጹም የተጠላ ነው። <ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋልና ይገደሉ። ደማቸው በላያቸው ነው።>> ይላል (ኦሪት ዘሌዋውያን
ምዕራፍ 20 ቁጥር 13) (105) በእስልምናም ተመሳሳይ ሕግ ይኖራል ብየ አገምታለሁ። እኚህ ቀሲስ <በመዲናችን አዲስ አበባ ወንድ ከወንድ፤ ሴት ከሴት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተጋብተው እየኖሩ ናቸው። የ666 ዋና አሰራሩ ግበረሰዶምን የሚያስፋፉበት፤ ህጻናትን በልጅነት ማጥቃት ነው። በርካታዎቻችን የምንጨነቀው ለሴት ልጆቻችን ነው። ነገር ግን በግብረሰዶማዊያኖቹ ቃለ መጠይቅ እና መረጃ መሰረት ወንድ ህጻናት ባሁኑ ሰዓት በአንዳንድ <ዘመድ፤ አስጠኚ፤ ጎረቤት፤ ጓደኛ’ በቅርብ ሰውና በተለያዩ ሰዎች ይጠቃሉ። ቢናገሩም ቤተሰብ ለማን ጉዴን እናገራለሁ ብሎ ያፍናል።ልጁ ሲያድግ ግበረሰዶማዊ ይሆናል።

ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈጸምና ለማስፈጸም፤ ዶላር በመያዝ፤ ከአውሮጳ፤ አሜሪካ፤ ከተለያዩ ዓረብ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ፤ በርካታ ደናግላን ወንዶች አሉ በማለት “ሴክስ ቱሪዝም’ ለዝሙት ቱሪዝም ጉብኝት የሚመጡ ቱሪስቶች ተበራክተዋል።
በቀጥታም ሆነ በደላላ ይገናኛሉ። ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱ ዘጋቢ ።  በመቀጠልም፡

ለምሳሌ በአዲሰ  አበባ ከተማ ፤ሚሰትና ልጆች’ ያሉት ሰው፤ 17 የወንድ ሚስቶች ነበሩት። እጅግ በጣም ያሳዝናል። እኛ በተለምዶ የምናውቀው ‘ሴተኛ አዳሪዎችን ነው” በጥናት እንደተደረሰው ብዙ ሺህ ወንድ አዳሪዎች አሉ። ይህ በዘመነ ወያኔ በሕግ የተከለከለ ነገር ግን ወያኔ በአበዳሪዎቹ (ከላይ የተጠቀሱት ማለት ነው) በኩል በተዘዋዋሪ ልቅ ሆኖ ይሄው አገራችን ለዚህ አሳፋሪ ተግባርና ለ666 ድርጅቶችና ኢሉሚናቲ አምላኪዎች ተጋልጣ ትገኛለች። የወያኔዎች ዲሞክራሲያዊት ፌደራላዊት አገር አየናት፤ ይህንን ትመስላለች።”)  ምንጭ  (የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? (ደራሲ ጌታቸው ረዳ) ገጽ 211 የተቀነጨ። የቪዲዮ ማስረጃ ለመመለክት       EOTC "ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ 666 አሰራር" በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ https://youtu.be/AkWgvYHgW6w

አመሰግናለሁ፦
Ethiopian Semay ጌታቸው ረዳ