Wednesday, January 8, 2020

ለዮኒ ማኛ ትችቴ- ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ለዮኒ ማኛ ትችቴ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

የመጀመሪያ ፎቶ በዮኒ ማኛ ሥልጡኖች የተባለላቸው ሥልጣኔን ሸሽተው ወደ አልሰለጠነቺው ኢትዮጵያ የሰተደዱ ሥልጡኖቹ ኤርትራውያን ስደተኞች ሲሆኑ። ቀጥሎም የኤርትራ ሥልጣኔ ማሳያ የሆነው “ምላሱ ተቆርጦ” በፎቶግራፍ የምታው ኤርትራዊው “ሃብቶም ተኪኤ” ይባላል። አሁን ወደ ዮኒ ማኛ ልውሰዳችሁ።

Indigenous/native ኢንዲጂነስ/ነቲቭ (ኦሪታዊ ተወላጆች) የሆኑ ኢትዮጵያውያንን “እራቁታቸው የሚሄዱ ባርዎች” እያልክ “ትምክሕት የተሞላበት vulgar” በሆነ ቃል እየዘለፍክ ጣሊያን በሰጣቸው በጣሊያን ቅኝ ተገዢነታቸውን የሚኮሩ “የዘመን መቁጠሪያና አገራዊ ስያሜን” ሥልጡን ለመባል የሚወጣጠሩት አጉልተኞቹ ኤርትራውያንን ሙትት እስክትልላቸው ድረስ ሰማይ የምትሰቅልበትን አስገራሚ “ ፍቅርህን” እንመልከት። እስኪ የዚህን ሥልጣኔአቸው በዚህ ፎቶግራፍ የሚታይ ከሆነ ፈልገህ ንገረኝ።

ከ30 አመቱ ውስጥ 12 አመት እርስበርሳቸው ‘ሻዕቢያና ጀብሃ” እየተባባሉ በዘግናኝ መተራረድ ገብተው ከፍተኛ እልቂትና ጦርነት ያካሄዱ የኤርትራ ሥልጡንነት በምን ትገልጸው ይሆን?

አንተ አቶ ዮኒ ማኛ “ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ስለ ኤርትራውያን ሕዝብና መንግሥት የሰጠው አስተያየት ከእውነት የራቀ ነው” በሚል ርዕስ በዩቱብ ያቀረብከው ትችትህን አድምጨዋለሁ። በዩቱብ የለጠፍከው ርዕስ ጨዋነት ያለው ርዕስ ቢሆንም ንግግር ላይ ስትገባ ግን “በአናትህ ተተከል” እያልከ በጨዋነት የሚነበበው አርዕስትህን አፈረስከው፤፡

ንግግርህ ስትጀምር “እኔ በፋክት” (እውነታውን) ተሞርክዤ ነው የምናገረው “ፋክት ሲሆን ፋክት”፤ “ስሕተት ሲሆን ስሕተት” ብየ ነው የምለው ስትል ‘ታምራት በኤርትራ ጉዳይ’ ስላለው “መስመር” ደጋግመህ ተናግረሃል። ኤርትራኖችን “ ኣይ ላቭ ዩ ቱ ዴዝ” በማለት ዑንቆች የምትላቸው ኤርትራውያኖችህን በወታደራዊ ሰላምታ “ፍቅርህን ገልጸህላቸዋል። በ1977 ዓ.ም የትግራይ ሕዝብ በርሃብ ተገርፎ እያለ “ወያኔ” ለራሱ ጥቅም ይሁን አይሁን ወደ ሱዳን ሲያሸጋግራቸው ያንተ ሥልጡኖቹና ሙትት ያልክላቸው ኤርትራኖችህ መንገድ ዘግተው አናሳልፍም ብለው በሺዎቹ ሕዝብ ማለቁን ተዘግቧል። አረጋውያን እርጉዞችና ደደካሞችን ጭካኔአቸው ያስመሰከሩ ያንተው “ሼራተኖችህ” ሥልጣኔ ያ ይሆን? ወይስ በጣሊያን መገዛትን የሚያሞግስ ትግሬው (ዛሬ ኤርትራዊ ነኝ የሚለን) ኢሳያስ አፈወርቂ የተነገረው ሥልጣኔ፦

“እኛ ሥልጡን ስለሆንን በቪላ ቤቶች እንኖራለን ያልሰለጠኑት ኢትዮጵያውያን ደግሞ ጎጆ ውስጥ ይኖራሉ፤እኛ ፓስታ ስንመገብ እነሱ ከሳር የማይሻል “እንጀራ” የተባለ የከብቶች ሳር የሚመገቡ ያልሰለጠኑ ናቸው" ብሎ ያለውን ሥልጣኔ ነው አንተ የምታደንቀው? ሥልጡን ኤርትራኖች ከምጽዋ እስከ ባርካ እና ሱዳን ድምበር የተዘረጋው 3/4ኘኛው በሸርጥና በከናቲራ አልፎም ከወገቡ በላይ እራቁቱ የሚሄድ አሳን በማጥመድና ግመልና ከብት ጭራ እየተከተለ የሚኖር ሰፊ ዘላኑ የኤርትራ ማሕበረሰብን ነው ሥልጡን የምትለው? ከቦታ ቦታ እየዞረ ክግመሉና ከብቱ ጋር አብሮ የሚተኛውን ማንበብና መጻፍ የማይችለውን ነው ከኢትዮጵያውያን በልጠው ሥልጡን የምትላቸው? አንተ ከኛ የበለጡ ሥልጡኖች የምትላቸው በምናቸው ነው? ለመሆኑ ኤርትራ ታውቃታለህ?

ይህንን ከላይ እንድታነበው ያቀረብኩልህን የኢሳያስ ንግግር ያደመጡ ዜጎቻችን ምሁራን እንዲህ ብለውታል፦

To the Ethiopians, this remark was both foolish and nauseating. By it President Isayas distinguished himself as “the first man to praise colonialism, especially fascist Italy’s style”. (Getahun gebre-Amlak-Getahun gebre-Amlak “In Issayas Landl, Wonders never End, (Ethiopiafirst.com) Dec.30,-1999.) የቅርብ ትውቅ ያለን አብሮ አደጌ ዶ/ር ሃይለማርያም ኢሳያስም ሆነ ስለ ኡርትራኖችን ከንቱ መምበጣረቅ With reference to President Isayas’ remark editor of Ethiopian commentator Hailemariam Abebe:
Quote:

“When Isayas finishes eating his spaghetti to complete his metamorphoses into the likes of his Western masters and joins the club of high tech warriors (being facetious here) Ethiopia shall still whip Eritrea with only spear and arrows.”(M.Azene- May 2000)." በማለት አጣጥሎታል።
የኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ለማንበብ ከፈለግክ በራሴው “TFriday, June 5, 2009 ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ (ኢትጵያዊ)? Ethiopian Semay
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2009/06/blog-post.html
የሚለውን አንብብ።

“በፋክት” አምናለሁ ስላልከን “ፋክቱን” እንድታየው ነው ይህ ሁሉ ሰነድ የማቀርብልህ። በቪዲዮ ውርወራዎች’ ሱስ ያደረገ ማሕበረሰብ ረዣዥም የታሪክ ሰነዶችን የማንበብ ልምድ ያላዳበረ ሕዝብ ማጃጃል የዘመኑ ቀላል መንገድ ነው። ዕድሜ ለ“ዩ-ቱብ”።
ዮኒ ማኛ ሙትት እስክትል ድረስ ለነሱ ፍቅርህን መግለጽህ ችግር የለኝም። ካንተው ጋር ችግሬ ኢትዮጵያውያንን “እራቁታቸው የሚሄዱ ባርያዎች” እያልክ እየዘለፍክ ኤርትራውያንን ሰማይ የምትሰቅልብትን አስገራሚ “ ፍቅርህን” አስገርሞኛል።
እስኪ ከዘለፋ ውጭ ባለው እውነታ እንነጋገርና አንተ በምትለው በዛው “ፋክት” በምትለው እምነትህ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ስጥና ፋክትህን እንመልከተው።

በርካታ አስገራሚ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን የሚዘልፍ ንግግርህ እና የተሳሳቱ እይታዎችህንም ተደጋግመው የተዘበራረቁብህ እይታዎችህን ተመልከት
ኤርትራውያን ከኢትዮጵያውያን እጅግ በጣም የሰለጡኑ ናቸው “ሸራተን ናቸው” ኢትዮጵያያ ውስጥ እራቁቱ የሚሄድ “ባርያ” አለ። ስትል ባህላቸው የሆነውን ዜጎቻችንን “ባርያ” እያልክ Indigenous/native ኢንዲጂነስ/ነቲቭ (ኦሪታዊ ሕዝብ) ዜጎቻችንን ዘልፈሃል። 'የኤርትራን ሕዝብ አይዘለፍም' ትልና ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ስትደርስ ግን ኔቲቭ/ዜጎቻችንን የመዝለፍ መብትህ ማን ሰጠህ? በየትኛው የሞራል ሕግ ተሞርኩዘህ ነው አንተ ሕዝባችንን “ባርያ” ብለህ የምትሳደበው?

ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሆኖ “ኢትዮጵያውያንን በዚህ ዓይነት ነውረኛ ስድብ መስደብ እና ሰውን በሰውነቱ ክብር መጥራት ይገባዋል የሚሉት የጋምቤላው የሰው ልጅ መብት ተሟጋቾች እነ ኦባንግ ሜቶ እና የኦሞቲክ ኢትዮጵያውያን እነ ፊታውራሪ ዶሪ የመሳሰሉ ዜጎቻችን ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉህ ይሆን። ለመሆኑ እራቁታቸው የሚሄዱት የምትላቸው ሙርሲዎችም ኦሞቲኪና ጋምቤላና ወዘተ.. በወያኔ ዘመን ታስረዋል፤ ዛሬም በአብይ አሕመድ ዘመን በገመድ እየታሰሩ ሲሰቃዩ ዜናዎች እየተገቡ ባለበት ዘመን አንተ “ባርያዎች” ብለህ ስትዘልፋቸው ሰከን ብለህ ስታስበው “ምን ይሰማህ ይሆን”?

አንተ አንደ “አገዋዊ ነገድነትህ “ዘረኛነትን እቃወማለህ ትልና ጥንታውያን ዜጎቻችንን “ባሪያ” ቂጣቸውን ገልጠው የሚሄዱ የሰው መጨረሻ' ብለህ ስትዘልፋቸው መስማት ምን ይሰማሃል? ይህንን እውነት የምትለው ያንተን እውነት ታምራት ነገራን በተራ ዘለፋ “በኣናትህ ተተከል!” ትለዋለህ። ኢትዮጵያውያንን እራቁታቸው የሚሄዱ ወገኖቻችንን “ባርያዎች” ብሎ መዝለፍስ “እናትና ልጁ የምትላቸውን ማርያምና እየሱስ” ይወዱልሃል ብለህ ታምናለህ? “እናት እና ልጁ” በዚህ ዘለፋህ “ኩፍኛ” አይቀጡኝም ብለህ ትገምታለህ? ካላመንከስ ለምን? ባርያ ብለህ ባንተው “ፋክት” ለምታምናቸው “ለናትና ልጁ” ልታቀርብላቸው ትችላለህ?

እንዲህም ትላለህ፦ “በመንግሥት ደረጃ። ኤርትራውያን ናቸው ወይስ ኢትዮጵያውን ናቸው የፈለግናቸው?.... ኤርትራውያን ማንንም “ቧዘር” (ቸገርን ብለው ሳያስቸግሩ) መረረም ከፋም እራሳቸው ችለው እየኖሩ ነው፤”” ብለሃል።
ኢትዮጵያውያን ለራሳችን መቸ ደልቶን ተስማምቶንና ነው ኤርትራውያንን የምንጦሮው፤እንዴት ኤርትራውያን በኛ ነው የሚኖሩት እንላለን? ስላልከው ጉዳይ፤

እራሳቸው ስላልቻሉ እኮ ነው በየዓለማቱ 75% ኤርትራውያን በስደት የሚኖሩት። “የሰለጠ” ሕዝብ እራሱ የቻለ ሕዝብ፤ ቅኝ ገዛችን ብሎ ድንጋይ ለጣለላት ወደ ኢትዮጵያ መሬት ለምኖ አስገብኝ ብሎ ይመለሳል እንዴ? ያውም ወደ ጠሉት ወደ አማራ አገር? ብየ እጠይቃሃለሁ።
የኔ ወንድም በጉልበት በመንግሥት መንበር የተቀመጡት አብይም ሆኑ መለስ ዜናዊ የኤርትራን ጠቀሜታ ለማስጠበቅ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ብዙ ሚና ተጫውተዋል፡ አሁንም ቀጥሏል።ስለ ኢ-ሕጋውያኑ መሪዎች ለመኑ ተለማመኑ ፈለጉ ተፈላለጉ በመፈላለጋቸው “ሴራ” (በጀዳው አግሪመንት አንቀጽ 4 ኮንሰፒራሲ) ላይ እኛን ስለማይወክሉ እርስበርሳቸው ተገናኙ አልተገናኙ ለኛ ምንም እርባና ስለሌላው በዚህ ክርክር ለምን መተቸት እንደፈለግክ አልገባኝም። ደምበሩ ሲከፈት ጎርፈው የመምጣታቸው ምክንያት እንኳን ተከፍቶላቸው ምግብ፤ብርድልብስ፤ ከሰልና ላምባ (ነዳጅ) “ያጡትን” ሸቀጣ ሸቀጥ ለማግኘት ቀርቶ ሳይከፈትም “ጥይት እየተተኮሰባቸውም ድምበር እያጠሱ የሚሸሱባት መንደር ነች። ፍቅር ምናምን የምትለው ተውና “ፋክቱ” ይኼ ነው።
ታምራት የተናገረው ስለ “ማፎዮዚ “መሪዎች” አልነበርም። እሱ የተናገረው ኤርትራውያን ናቸው ወደ እኛ ለምነው እየመጡ ያሉት እንጂ እኛ ወደ እነሱ አልሄድንም ነው ብሎ የተናገረው። ይህ አባባሉ ደግሞ ከመንግሥት ግንኙነት ጋር አያይዘኸዋል። ያ እይታህን አስተካክል።

እውነታው የታምራት ነው።አዎ ወደ ቅኝ ገዢያችን ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ብለው “ድንጋይ ወርውረውላት ላለመመለስ ሄደዋል። በወቅቱ ነፃ ሲወጡ በዚያኑ ወቅት አዲስ አባባ ጋዜጦችና/ መጽሔቶች እንዲሁም በካናዳ አገር ሓዋርያ ጋዜጦች የጻፍኩትን ፈልግህ አንብብ። “ላለመመለስ ድንጋይ ወርውረውላት የሁዱ ኤርትራውያን በሳልስቱ ባይሮፕላን እንደሄዱ በእግራቸው አስገቢን ብለው ይመለሳሉ’ ብየ ነበር ያኔ። በራዲዮ ቃለመጠይቅም እዚሁ ባለሁበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥም የተደረገልኝ የየራዲዮ ቃለ ምልልስ ደግሜዋለሁ (ያኔ)።አዎ ይኼው አስገቢኝ ብለው በሺዎቹ በየቀኑ የሚጎርፉት ስደተኞች ኤርትራውያን በትግራይ መጠለያዎች እና አዲስ አበባ በገፍ የሚኖሩ ኤርትራውያንን ወደ እኛው ተመልሰው አስገቡን ብለው መጥዋል። አሁንም እየጎረፉ ነው።

ሕዝባችን ግን በሺዎች የሚቆጠር ኢትዮጵያዊን አስገቢን ብለን በስደት ወደ ኤርትራ አልሄድንም፤ አልጠየቅንም። ይህንን እውነታ እንዴት ማየት አቃተህ? ‘ፋክዩ’ ይኼ ነው። ማስረጃውን በለጠፍኩት የተባበሩት መንግሥታት ፎቶግራፍ ማስረጃ ተመልከት።

እምየ ኢትዮጵያ ሶርያ ሳይቀሩ አስገቢኝ እያልዋት ነው። እምየ ኢትዮጵያ ምንም ድሃ ብትሆንም አንተ "የባርያዎች አገር' የምትላትን “እምየ ኢትዮጵያ” መስህብዋ ሃያል ነው። ያንን ማመን ካልቻልክ በዓለም ውስጥ በብዛት ስደተኞችን የምተቀበል አገር ሆናለች? አደለም እንዴ?

ስለ ነፃነትና ባርነትታቸው ምርጫ (ሬፈረንደም) ስተናገር እንዲህ ብለሃል፡ “ኢሳያስ አውነቱን ነው ‘ከወያኔ ጋር ከመኖር ነጻነት ወይስ ባርነት” ብሎ ነው ኤርትራን ነፃ ያወጣው'' ብለሃል። ምርጫ ሲደረግ ከወያኔ ለመነጠል ነበር ሬፈረንደም የተደረገው እንዴ? ይህ ለመጀመሪያ ጀሮየ ነው እንዲህ ያለ አዲስ ነገር ያደመጥኩት።

በዘመን ቀደማዊ ሃይለስላሴ ጀምሮ በእነ ሳልሕ ሳቤና አብራሂም ሱልጣን የተጀመረው የመገንጠል ጥያቄ “ኤርትራ ከወያኔ ባርነት ለመላቀቅ” ነበር በዓረቦችና በሲኣይ ኤ ድጋፍ ተደርጎለት ነፃ የወጣቺው” የሚል የሬፈረንደሙ መግለጫ ለማንበብ እስኪ የት እንደምናገኘው ጠቁመን (ፋክት’ ፋክት ነው ስለምትለው ንግግርህን እስኪ ፋክቱን አሳያን)?

ወያኔና ሻዕቢያ እምየ ኢትዮጵያን ለመዝረፍ ሲሽቀዳደሙ አልነበረም ወይ ውግያ ውስጥ የገቡት? ኢትዮጵያውያኖች አመረሩ ብለህ "ከዘረፋየና ከኮንትሮባንዴ" ከከለከልከኝ እማ "ጦርነት እከፍታለሁ" ብሎ አይደለም እንዴ በግንቦት 1998 ከጥዋቱ ልክ 5፡30 በኤርትራ ብርጌዶች ጦርነቱን በባድሜና በመሳሰሉት ድምበሮች የጀመረው? የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬት ያኔ ሲያስጮኸው የነበረው እሮሮ አታውቅም”? የሰለጠነው ኤርትራኖች ዝርፍያ ነው እኮ ሕዝባችን ያስመረረው? ይህን አታወቅም ወይስ ልጅ ነበርክ?

የጥጋባቸው ብዛት “ደብረብርሃን ከተማ” ሰው በመኪና ገጭቶ ሲሄድ ፖሊስ ሲያቆማቸው እኛ’ኮ ኤርትራውያን ነን ፤ማንን ነው የምታቆመው ብለው በወታደሮች ሲያሾፉ ሽፍታው ወያኔ አገር በቁጥጥራቸው እንዲዘርፉና እንዲደነፉብን ማድረጋቸውን አታውቅም?

ኢትዮጵያውያንን 27 አመት የወያኔ ባርያ አልነበርክም ወይ ስትል ኢትዮጵያውያን በባርነት ኤርትራውያን በነፃነት እንደሚኖሩ ስለተናገርከው ጉዳይ። ያም ባርነት ይህም ባርነት ከሆነ “ኢሳያስ እውነቱ ነው” ያልከው እውነታው ልትነግረን ትችላለህ”?

አንተ ‘ፋክት’ ነው የምናገረው ስላልክ “ፋክቱን እስቲ ንገረን? ኢትዮጵያ ልጆችዋን “ጥፍር መንቀል፤ ብልትን በሃይላንድ ማንጠልጠል ወዘተ ታሰቃያለች ስትል “ኢሳያስ ያለደረገውስ ምን ነበር? ሌላ ቀርቶ ሰው ግደል ተብሎ የታዘዙትን ሓኮሞች እነ “ዶ/ር ንስረዲን እና ደ/ር አብርሃም” እምቢ ስላሉ አይደለም እንዴ በግድ በካቴና ታስረው ዶክተሮቹ “በኤይድስ ቫይረስ” የተበከለ የደም መርፌ ተወግተው ወንጀል የተፈጸመባቸው? ዛሬም ንስረዲን እስከ ቅርብ ጊዜ ትግራይ ኤርትራን ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ገብቶ የሰጠው ቃለ መጠይቅ በራሴው ድረግጽ ተመዝግቦ ይገኛል። ይህ ወንጀል ኤርትራኖችን ሥልጣኔ ምልክት ምን ያህል እንደሆነ ማሳያ ነው?

ሙትት ብምትልላቸው ሥልጡኖቹ ኤርትራኖች “ምላሱ ተቆርጦ” በፎቶግራፍ የምታው ኤርትራዊው “ሃብቶም ተኪኤ” ይባላል። ይህንን ከ5 አመት በፊት የተቸሁበትን በራሴው ድረገጽ ይኼው ማስረጃው አንብብ፦

ዴምህት “ዓሰብ! ዓሰብ!” የአማራዎች መፈክር ነው አለ” ትችት በጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ) TUESDAY, NOVEMBER 18, 2014

ይህ ምላሱ የተቆረጠው ልጅ ኤርትራ ውስጥ በኢሳያስ ጽ/ቤት ልዩ የደህንነትና የጥበቃ አባል የነበረ ነው። አሁን በስደት ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቆ ትግራይ ውስጥ ለኤርትራኖች ከተዘጋጁት መጠለያዎች ውስጥ እየኖረ ነው። ይህ የሃብቶም ተኪኤ ፎቶግራፍ የሚያሳየን የኢሳያስ አሽከር በሆነው በጀነራል ተኽላይ ክፈለ (ተኽላይ ማንጁስ) እጅ በምላጭ ምላሱ ከተዘለዘለ በኋላ ነው።ይህ ታሪክ ታውቀለህ? ሥልጣኔ ማለት ይህ ነው?
ዓለም ያወገዘው በታሸገ “ኮንተይነር” የሰው ልጅ አሽጎ አፍኖ የመግደልና የገዛ ጓዶቹን ዓይነስውር ያደረገ፤ የሳባ እና የጴጥሮስ ሰለሞን ልጆች እናትና አባት በጨካኝ እስር ቤት አስገብቶ ያለ አባትና እናት የሚያስቀር ማን ነው? የሞተን ሬሳ (የናይዝጊ ክፍሉ ሬሳ) ወደ አገር እንዳይገባ የሚከለክል ነፃነት በምን ሞራልና ሕግ “ነጻነት” ብሎ ሕዝብ እንዲመርጥ ነፃነት ይሆናል? (በኤርትራኖች የሚነገረው አውድዮና መጽሐፍት የሚቀርቡ የወንጀል “ጉዶች’ ትግርኛን ማድመጥ ካችልክ አድምጠው የሥልጣኔአቸው ምጥቀት እግዚኦ ትላለህ። ኢሳያስ ነፃነት ወይስ ባርነት ሲል እውነቱ ነው የምትለው እውነቱ ምኑ ላይ ነው እውነቱ ነው በለህ ጥብቅና የቆምክለት?

ኤርትራ አንድ ናቸው እርስ በርስ አይጣሉም ብለሃል። ምናልበት ትግረኛውን ማደምጥ ስለማትችል ይሆናል እንጂ ባውራጃ የመነታረኩን ፖለቲካ መሪዎችና ተከታዮቻቸው ብታደምጥ ይህንን አትልም ነበር (የደቡብ ሱዳን እልቂት የሚያስንቀው በሰፊው የዘገብኩትን የ12 አመት እርስበርስ መተላለቃቸው እንዳለ ሆኖ)። ኢሳያስ በዘር አልከፋፈላቸውም ትላለህ። አንተ አንዲያ ብትልም ፡ጀበርቲዎችና ኩናማዎች” አንተ የምትለው አይቀበሉትም። ውሸታም ይሉሃል። አዋተ.ካም ድረግጽ ግባና ትንሽ ምርምር አድርግ፡ ጀበርቲ.ካም ወይንም ኩናማ.ካም ግባና ምርምሩን አካሂድ። የባርካ መሬቶች ለከበሳዎች “ክርስትያኖች” እየተሰጠ ነው፡ ቋንቃችንና ነገዳችን በትግርኛ ነገድ እየተረገጠ ነው፡ የሚሉ በርካታ የታወቁ ዘፋኞችንና የነገዶችን አባሎች ቀፍድዶ አስሮአቸዋል/አጥፍቶኣቸዋል። ኩናማዎች ከኢሳያስ (ኤርትራ) ይልቅ ኢትዮጵያን እንመርጣለን ብለው እነ ዑስማን መርቀሌዎስ (የኩናማ ግምባር መሪ) የተናገሩትን አጢን (አሁንም ባርካ ውስጥ በብርት ትግል ገጥመው ይገኛሉ)።


ኤርትራ እንደኛ በስም በቋንቋ አይጣሉም ስላልከው ምርምር አደርግ።በታጋዮች የሚጻፉ የትግርኛ ሕትመቶችን አስተርጉሙልኘ ብለህ አንብብ። ወይንም በኤርትራ ነፃነት "ድምፃችን አንሰጥም ያሉትን ንብረታቸው ነጥቆ እንዲሰደዱ ያደረጋቸው “የጆሆባ ዊትነስ” (የሁዋ ምስክር) ሃይማኖት ተከታዮችን ታሪክ አንብብ። ሃይማኖት ጣልቃ መግባት የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ገና ‘ሕዝባዊ ሓይሊታት’ ብሎ “ንሕናን ዕላማናን” (እኛ እና ዓላማችን) ብሎ በእጁ የጻፈውን ሰፊ ሰነድ ከጀብሃ ሲነጠል ደጋ ክርስትያኖች በቆላማ በእስላሞች እየታረዱ ናቸው ብሎ እራሱ የመሰከረበትን ኤርትራውያን በሃይማኖት አንደተጋደሉ መረጃውን ፈልገህ አንብብ።

በይበልጥ የገጽ ብዛት 622 የሆነ ረድኢ መሓሪ በተባለ ከእኔ ጋር ትውውቅ ያደረግን፤ መጽሐፉን ካነበብኩ በሗላ “ብላሽ ታሕሪር” (የተበላሸው ነጻነት) የሚል አጭር የመጽሐፍ ግምገማ አድርጌለት የጻፍኩት የረድኢ መሓሪ ፡ “ትልሚ ንዘርኢ ክርዳድ” (የእንክርዳድ ዘሩ ዒላማ) ወይንም (የእንክርዳድ ዘሩ ኢላማ ጽንሰ ሓሳብ) የሚለው በጣም እጅግ በጥልቀት የተጻፈ ከ “ሀ” እስከ “ጰ” ያለውን የኤርትራ ትግል ማንበብ ይጠቅምሃል። ብያነስ የኔው የመጽሐፉ ግምገማ ብታነብ ስለ ሥልጡኖቹህ (ሼራተኖችህ)” ኤርትራውያን እንዴት ተጠልፈው እንደተሞኙና የወደቁበት መጨረሻ ህይወታቸው ብታነበው ፋክቱ ይገልጥለሃል። ያ ሁሉ ደምና መስዋዕት ከፍለው የሥልጣኔአቸው ደረጃ የት ድረስ አንደዘቀጠ ታየዋለህ።
2) ያይናችሁ ቀለም አላማረኝም ውጡ ብሎ ኤርትራውያንን ያባረረ ኢሳያስ ነው ወይስ መልስ? ብለህ ጠይቀሃል።

የጥርስ ወርቅ ሳይቀር አስነቅሎ ንብረታቸው ነጥቆ ያባረራቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንስ ስለ ኢሳያስ ወንጀል፤እና “የሥልጡንነታቸው” ጭካኔነት የምታውቀው ነገር ፈልገህ እንዴት አጣህ? ሌላ ቀርቶ አህያን የወታደር ልብስ አስለብሰው “አማራ አህያ” እያሉ ኮምቢሽታቶ ሲጨፍሩ አላደምጥክም? ቪዲዮው ሲሰራጭ አይተህ አታውቅም ? (ያኔ ልጅ ልትችል ይሆናል) ያንን ካለወቅክ በራሴው መጽሐፍ የተዘገበውን ያንን ታሪክ አንብብ። ያንን ስታነብብ የፋክቱን ትርጉም ታውቀዋለህ ብየ እገምታለሁ።በቅርቡም ያንን እለጥፈዋለሁ።

ልክ እንደ ወያኔዎቹ የኪነት ቡድኖች፤ አንተም የኤርትራውያን ጀግንነት ዕንቁነት ስትክብ “ጀግንነታቸውን እንድንቀበል” አስረግጠህ ‘ ተናገረሃል። ጀግንነት ስለምትለው ስለ ኤርትራ የጦርነቱ የቅርብ ምስክሮች ስላለን እሱን ለእማኞች ተወው (አንተ ገና ከኛ በዕድሜ ያነስክ ስለሆንክ ብዙ ይቀርሃል፤ቀስ ብሎ ግን ሁኔታው ይገባሃል)። እኛን ካላመንክ (book by Professor Tesfatsion Medhanie page 48- “Eritrea Dynamics of National Question) “Fred Halliday, “The fighting in Eritrea” New left Review. No.67 (May-June 1971 p.65 የሚለው ኤርትራኖች ያለ ኢትዮጵያውያን እገዛ እና ማእከለዊው መንግሥት እንዲዳከም ባያደርጉላቸው ኖሮ የኤርትራ ነፃነት የሚባለው “የማይተገበር ሕልም” ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር ሲል ተዘገበው እውነታ አንብብ።

ያ ካልሆነም በእኛው በጦር አዛዦችና ተራ ወታደሮች የተዘገቡ መጽሐፍቶችን ለምን ምሽጎቻቸውን እንዲለቁ እንደተገደዱ መረጃዎቹን ማንበብ ጀምር። ያኔ እውነታው ታገኘዋለህ። ኖቭል ሽልማት የተሸለመ ሁሉ እውነትነት አለው ማለት እንዳልሆነ ሁሉ የተገነጠለ ሁሉ በጀግነነቱ ነው ነፃነቱን ያገኘው የሚለው ውሸት መቀበል ትንሽ ምርምር ይጠይቃል።

ያም ሆነ ይህ ሕዝብን ባርያ እያልክ ኤርትራኖችን ዑንቅ ሕዝብ ማለት “እባትና ልጁ” አይወዱልህም። ቅጣትም እንዳያወርዱብህ በፀሎት ይቅርታ ጠይቃቸው።
በመጨረሻ ያልተዘጋው ዶሴ ለማወቅ ይህንን በራሴው ድረገጽ የተለጠፈውን በአክሊሉ ወንድ አፈራውና “የዩክሬይን ክራሚያ እና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ” የተለጠፈውን ምን እንደሚጠቁመን መመራመር አለብህ።
ሙትት ብለህ ወድደህ የሞትክላቸው “ሸራተን” ኤርትራውያኖችህ ጉዳይ በኛ በኩል ገና ያልተዘጋ አጀንዳ ነው። ቀኑ ሲመጣ በናንተው ሳይሆን ታሪክ ዕውቀት በታጠቁ በቁርጥ ቀን ልጆች ቀኑ ሲደርስ ሒሳቡ በቀኑ ይወራረዳል (ሉሁም ወቅት አለው ብሏል ጠቢቡ ሰለሞን)። ታምራት ነገራም ያለው ያ ነበር (የጊዜ ጉዳይ!!!)።

ስለ ኤርትራውያን ሙትት ማለት ባንተ አልተጀመረም፤ ወያኔዎች ሙትት ብለውላቸው ነበር፤ ኢሳቶቹ በነ መሳይ መኮነን ፋሲል የኔአለም፤በሲሳይ አገና ምትት ብለውላቸው ነበር (ዛሬም ያው ናቸው) ለኤርትራኖችና ለወያኔዎች “ሙትት” የሚልላቸው አያጡም በዚያ ታድለዋል (ጊዜአዊ ቢሆንም)። ያ ባንተ አልተጀመረም ። የኢሳቱ ባለቤት በሻዕቢያ ፍቅር ሙትት ያሉው ብርሃኑ ነጋም ሆነ እነ አንዳርጋቸው እና ኤፍሬም ማዴቦ (ነፍጠኖች ባዩ) እና እነ ብርሃኑ ነጋ ለኦነግና ሻዕቢያ ፖለቲካ ወግነው “ከዚህም ከዚያም የተከማቹትን ቆሻሾች እንጠርጋቸዋለን” ሲሉን ነበር። “ የጠየቀውን ሃያሲ “በንፍጥ የተሞላ አእምሮ” ብሎ የሚሳደቡ እነ ብርሃኑ ነጋ ስለ ሙትቻዋ ኤርትራ ፍቅር ማስተጋባት የለመድነው ነው። ባንተ በዮኒ ማኛ አልተጀመረምና ብዙም አልገረመንም።

ለመሁኑ ወቅት ተለዋዋጭ ሆኖ ነው እንጂ የባሕረ ነጋሽ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ መምጣት አዲስ ነገር አልነበረም፡ ከአክሱም ጀምሮ የቆየ ታሪካችን ነው። ነበረች ሄዳለች፤ ትናንት ሄዳለች፤ነገ ትመጣለች (ሙትት ላልክላት ኤርትራ ልትነግራት የምንፈልገው መልዕክት የኛን የጥንት ደም ሥራችን ባሕራችንን ዘግታ በሰላም አትኖርም። በውድ ወይንም በግድ የባሕር በራችንን እናስመልሰዋለን። ወድክም ጠላህም ያንን ፋክት እኛን በሚደግፉ በወላጆቻቸው ኮቴ የሚምሉና የሚለከተሉ ወጣት አርበኞች ዕውን ያደርጉታል (ታምራት ነገራ አንዱ ነው። የምፅዋው አንበሶቹ የነ ኮለኔል ተሻገር ይማም አንባሰነት ሻዕቢያኖች ሳይቀሩ የመሰከሩላቸውን አርበኞቻችን ኮቴ የተከተሉ ወጣቶች እነ ታምራት እውን ያደርጉታል)ኮቴው እየተወራረሰ ይቀጥላል።። አንተ ከነሱ ጋር ወግን፤ የኛ ወጣቶችም ከድሃዋ አገራቸው አብረው ይቆማሉ። ያንን ልንነግርህ እንፈልጋለን)።

ጋዜጠኛው ወንድወሰን እንዲህ ያለውን ልጥቀስልህና ልደምድም። ከ150 ዓመት በፊት) የአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ዜና መዋዕል ዘጋቢ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አለቃ ዘነብ “መፅሐፈ ሥጋዊ ወ መንፈሳዊ” በተሰኘው “…አስተካክሎ ከማይናገር መልዕክተኛ የማለዳ ወፍ ትሻላለች፤ ምነው ቢሉ መንጋቱን በትክክል ትናገራለች፡፡ ብለው ነበር።

ወጣቱ ዮኒ ማኛ “በኤርትራዊው/ትግሬው መለስ ዜናዊና በአይሁዱ ሲኣይኤው “ሄርምነ ካኸን’ ጥብቅና እና በግብጻዊው ቡጥሮስ ቡጥሮስና በዓረቦች ድጋፍ ተደግፈው ነጻ የወጡት ያንተ ጀግኖች ኤርትራውያኖቹ ነፃ ወጣን ብለው “ስለ ብላሽ ታሕሪራቸው” ሲበጠረቁ በነበሩበት ሰዓት “የኮሎኔል ጎሹ ወልዴ”ን ታሪካዊ ሙግት ከመቸው ረሳኸው? እስቲ እራቁታቸው የሚሄዱ ባርያዎች ብለህ ስለዘለፍካቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ስም እና ሙትት እል፤ላችሗለሁ በምትልላቸው ስም ልብ እንድትላት ይህችን የኔን “ትናንትም ዛሬም ነገም ለወደፊቱም የገዳያቻን የሻዕቢያ ባንዴራ ብንሞትም አናውለበልብም!” የሚለውን የቆየ የራሴ የጽሑፌን ጥቅስ ልሰናበትህ? እንዲህ ትላለች፦

“ዘመኑ የወገን ደም ረስቶና አንኳስሶ ገዳዮችንና ወረበሎችን የሚያወድስ ትውልድ እና ጥርሰ-ቢስ ተሸብራኪ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ዘመን ስለሆነ ብረዛው፤ክሕደቱ እና ንቀቱ ኢትዮጵያንን የሚያዋርድ ክስተት መሆኑን ታሪክ እንዲመዘግበው አብየቱታችንን ለታሪክ እናስመዘግባለን።” ብየ ነበር:: ብዙዎቹ ኤርትራዊያኖች ወደፊት የሃገራቸዉ ልማት መሰረት ኢትዮጵያ መሆኗን እያወቁ ኢትዮያን ለሰላሳ ኣመታት ተዋግተዉ ይባስ ብሎ ደግሞ ይልቁንም በ1991 እንደገና ለምን ዉግያ ዉስጥ በመካፈል ብዙ መስዋዕት ከፈሉ? ብየ ነበር።
በዚች ልደምድም።

ኤርትራንና የምስራቅ አፍሪቃ ቀጠና ጉዳይ በሚመለከት በጻፋቸው ጥልቅ የምርምር መጽሐፍቶቹ ዓለም አቀፍ ምሁራን የሚጠቅሱለትን በወዳጄ የሕግ መምህር የሆነው ኤርትራዊው ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃንየ አባባል ልደምድምና ልሰናበት።
“አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፋዊ ህግ መሰረት ዓሰብን ብቻ ሳይሆን ምፅዋንና ሌሎች ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችላት መብት አላት፡፡ ችግሩ ኤርትራ ውስጥ ይህንን መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ጨዋ ጤነኛና ለህግ ተገዢ የሆነ መንግስት የሌለ መሆኑ ነው።” ይላል።
አመሰግናለሁ
ድል ለኢትዮጵያ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)