Friday, February 28, 2020

የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን ብሎናል የድሮው የኢንሳ የዛሬ የቴክ ሚኒስትር እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ሓላፊ! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) መልስ ለሚኒሰተር ለዶክተር አብርሃም በላይ (ክፍል 1) 2/28/2020 (በፈረንጅ አቆጣጠር)


የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን ብሎናል የድሮው የኢንሳ የዛሬ የቴክ ሚኒስትር እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ሓላፊ!
ከጌታቸው ረዳ  (ኢትዮ ሰማይ)
መልስ ለሚኒሰተር ለዶክተር አብርሃም በላይ
(ክፍል 1)
2/28/2020 (በፈረንጅ አቆጣጠር)

ዶ/ር አብርሃም በላይ ይባላል። ደናቁርት የወያኔ ተቃዋሚ ትግሬዎች ህ.ወ.ሓ፣ትን የሚጋፈጥ አንድ ሰው አገኘን እያሉ የሚቦርቁበት የትግራይ ሰው ነው። ከዚያም ተሻግረው አንዳንድ የፌስ ቡክ ደናቁርት ትግሬዎች መቀሌ ውስጥ ከሚኖሩት የዓረና ትግራይ ብሔረተኞች ደምረው “ቲም አብርሃም” በማለት እያቆለጳፐሱት የሚገኙ “ትኩስ” የትግሬዎች ታጋይ ነው።


ይህ ወጣት ከኮሎኔል አብይ አሕመድ ጋር የስለላ ማለትም “የደህንነት ስጋትና የፖለቲካዊ ምስጢሮች ጠለፋ ክንውን ክፍል” ሰራተኛ የነበረ የዛሬው የትግራይ ብልጽግና ተጠሪ እና በፋሺስቱ የአብይ አሕመድ መንግሥት “የሳይንስ እና ኢኖቬሽን” ሚኒስተር ባለሥልጣን ነው። ይህ ወጣት በዕድሜው ወጣት ነው። ቃለ መጠይቁን ያደመጥኩት  “ትግራይ ሃውስ ሚዲያ” በሚባል የወያኔ ድምፅ አስተጋቢ ቴ/ቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ስለተገረምኩ መጀመሪያ የማቀርበው (ጽሑፉ እንዳይረዝምብችሁ) ክፍል 1 የራሱን (የዶክተሩን) መከራከሪያዎቹን ብቻ አቀርባለሁ (ከራሴ ትንሽ ማብራሪያ ጋር)።

በክፍል ሁለት ደግሞ የሂትለር ናዚ ፓርቲ፤ የሙሶሎኒ የፋሺሰት ፓርቲ የጀርመን እና የጣሊያን ሕዝቦች እንደ ሕዝባዊ በዓል ካላከበሩዋቸው የትገሬዎቹ የህ.ወ.ሓ.ት ፋሺሰት ፓርቲ የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓል ሆኖ መከበር እንደሌለበት መከራከሪያየን በክፍል 2 አቀርባለሁ። አሁን ዶ/ር አብርሃም መከራከሪያ ነጥቦቹን እንመልከት፡=-እንዲህ ይላል በቀረበለት ጥያቄ ቃለ መጠይቅ

“በየአመቱ የምናከብረው የየካቲት 11 በዓል የሕዝብ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ በዓል አይደለም። የካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ በዓል ነው እናከብረዋለን፡ ይህንን የሚቃወሙ እንታገላቸዋለን።” በማለት ያደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ነው። ይህ አቋም የራሱ ብቻ ሳይሆን የብልጽግና (የብልግና ፓርቲ/ ‘ሩድ’ ፓረቴ ብየ የሰየምኩት) የፓርቲው አቋም እና በዓሉን አስመለክቶ ትግራይ ውስጥ ሲከበር ድርጅቱ በ ኢ ቲ ቪ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ያስተላለፈበት ልሳንም እንደሆነ ገልጿል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ በሰፊው ሲያብራራ በትግርኛ እንዲህ ይላል።

“ ከውጭም ሆነው አገር ውስጥ ይህንን ሕዝባዊ በዓል ጥላሸት ለመቀባት የጣሩ ሁሉ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ነው የኛ ፓርቲ  በተከበረው  የካቲት 11 አስመልክቶ ያስተላለፈው መልዕክት።አናቆምም ካሉ ለዚህ እንታገላቸዋለን። የካቲት 11 (ይህ በዓል) የሁሉም ሰላም ፈላጊ በዓል ስለሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ ፕሮቴክት (መንከባከብ) እንዳለበት የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፍነው።” ካለ በ

ሚኒሰተር ዶ/ር አብርሃም ይቀጥልና እንዲህ ይላል፦

“ሌላው ያስተላለፍነው መልዕክት የካቲት 11 የሕዝብ እንጂ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ታስቦ የተወሰነ ቡድን በባለቤትነት የሚመዘምዘው አዝማምያ ስህተት ስለሆነ ይህ ባህሪ መቆም አለበት ብለናል። የአንድ ቡድን ባለቤትንት ነው ማለት የጥፋት መንገድ ስለሆነ ያ መታረም አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈናል።

ጋዜጠኛው ንግግሩን በማስቆም እንዲህ ሲል ጠይቆታል፦

ህወሓቶች ምን አገባችሁ ድርጅቱ የኛ ነው የካቲት 11 ቀን ወደ ደደቢት ወርደን ፍትሕ ለማምጣት የመሰረትነው ስለሆነ 45ኛ የልደት በዓላችን የማክበር መብት ባለቤትነት እና የታገልንለት ድርጅታችን ስለሆነ መብት አለን ቢሉህሳ? (ለምሳሌ እንደ እነ ስብሓተ ናጋ የመሳሰሉ ቢለህስ?)?

መልስ፦    
“በዓሉ እንደ የትግራይ ሕዝብ በዓል ሆኖ እየተከበረ ስለሆነ እነሱም የሕዝቡ አካል ስለሆኑ የሁላችን ስለሆነ እነሱም የማክብር መብታቸው መነፈግ አለበት አላልንም። የሁላችን ባዓላችን እንጂ የፓርቲ/የድርጅት/ ብቻ በዓል ስላልሆነ አብረን እናክብረው ነው የምንለው። ድርጅቱ ማለትም ‘ህወሓት የትግራይ ሕዝብ አካል እንጂ ሕዝብ የድርጅት አካል አይደለም”። በዓሉ ሕዝባዊ ስለሆነ በኢትዮጵያውያኖች ጭምር “ሪኮግናይዝ” መደረግ አለበት። ይህ ሕዝባ በዓል የጠላት በዓል ነው እያሉ የሚያጠለሹት አካሎች አሉ። የኛም በዓል ስለሆነ ይህ መስተካከል አለበት በሚል መነሻ ነው መልዕክት ለሕዝብ ለማስተላለፈው የፈለግነው። ይላል።


ባጭሩ  ድርጅቱ ከሕዝብ የተገኘ እንጂ ሕዝቡ ከድርጅቱ የተገኘ አይደለም። የድርጅቱ ፈጣሪ ሕዝብ ነው፡ እያለን ነው። ህወሓት በሕዝቡ የተፈጠረና የተገነባ ከሆነ ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድም ሁለትም ሦስትም ናቸው ማለት ነው። ይሄ ብዙ የሚያነጋግረን ስለሆነ በሰፊው እንመለከተዋለን። ያም ሆነ ይህ በኒቶ ሙሶሎኒ በ1911 ዓ.ም (በእኛ ዘመን አቆጣጠር) ‘ፋሺዝሞ’ በሚል ስም ሰይሞ የመሰረተው ብሔረተኛ ድርጅት እና በ1967 ዓ.ም ደደቢት በረሃ መሽጎ የመሰረተው የትግራይ ህ.ወ.ሓ.ት በባሕሪያቸው አንድ ናቸው። የፋሺዝሞ ዓላማ የድሮ ጥንታዊቷ ሃያልዋን የሮም ገናናነትን መልሶ ለመፍጠር ሲያቅድ፤ የትግሬዎቹ ህ.ወ.ሓ.ት ድርጅትም የጥንት የአክሱም ገናናነት መልሶ በማደስ ሃያል ትግራይን መስርቶ በዙርያዋ ያሉ ጎሳዎች/ “ብሔሮች” የበላይነትዋን በማረጋገጥ የተመሰረቱ ሁለቱ የፋሽት ድርጅቶች ናቸው።


የትግራይ ፋሺስታዊነት በትግራዋይነት ጥምር ማፊያዊ ብሔራዊ (ሲንዲካሊዝም) ስሜት፤ በአብዮታዊ ብሔረተኝነትና በትግራይ ግዛት (ኢምፓየር) የበላይነትና ጥንካሬ በማረጋገጥ ቅኝት ነበር የተመሰረተው። ጣሊያን ሙሶሎኒ  የተጠቀመበት ምልክትም የጥንታዊትዋ (ሮም) ኃያልነት የሚወክል ተምሳሌነት ለመግለጽ  በአንድነት የተጠመሩ ጥቅል እንጨቶች የታሰረ መጥረቢያ ሲሆን የትግሬ የህ.ወ.ሓ.ት ምልክትም በጥንታዊትዋ ሃያልዋ ኣክሱም የቆመ ሃውልት እና የአክሱም ነገሥታት ገንዘብ ላይ ታትሞ የሚታየው የሰንዴና የዘምባባ ምስል በተምሳሌነት ወስዶ ምልክቱ አድርጎ ተጠቅሞበታል።

ዶ/ር አብርሃም በላይም ሆነ ህ.ወ.ሓ.ት የተመሰረተበት የካቲት 11 ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማክበር አለበት ብሎ የሚለን እና የሱን መስመር የሚከተሉ ሚሊዮኖች ትግሬዎች ልነግራቸው የምፈልገው፤ ህ.ወ.ሓ.ት ማለት ብሐረተኛ ማለት ነው። ለትግሬ ፋሺስቶችኢትዮጵያማለት በነገድ ተከፋፍላ በግንጣላ ታርጌት/ /ቀለበት/ የገባች እንደባዕድአገር ነች። በትግሬ ፋሺስቶች ዓይን፤ የአገሪቱ ታሪክ፤ አገር፤ ሃይማኖት፤ አማራ እና አማርኛ ቋንቋ፤ እግዚአብሔር እና ሉኣላዊነት  ሃገራዊ ሰንደቃላማችን እና አፄ ምኒሊክ በጥላቻ የተፈረጁ፤ በውጭ አገር ታዛቢዎች ፊት በፓርላማ የሚዘለፉ የሚብጠለጠሉ እሴቶችና ሊፈርሱ የተነደፉ ኢላማዎች ናቸው። ይህ ትዕይንት ብዙዎቻችን ያስገረመ፤ ብሔራዊ እሴቶቻችንን እንደ የባዕድ ዕቃ የሚንቋሸሹና የሚብጠለጠሉ ሆነው የተነጣተረባቸው ናቸው። ይህ ሊሆን የቻለው የካቲት 11 የተመሰረተው ህ ወ ሐ ት የትግሬዎች ፋሺዝም የሚመራው ቡድን እና ድርጅቱታሪክ በማይፈሩእኔ Intellectual Lampoons የምላቸውበዱርየነት ባሕሪ የሚመሩ፤ ማአከላዊነትን የሚያጠብቁ ምሁራንእና ከድርጅቱ ውጭ ላሉሆድ አደርምሁራንን ለመምራትየሚደፍሩነፍጥ ባነገቡባልተማሩ ዱርየዎችየተመራ ዘመናዊመስፍንቶችንያፈራ፤ በሲንዲካሊሰት የገንዘብ ማግበስበስ የተካነ፤ በነብሰገዳዮች የሚታዘዝ፤ ቀኝ አክራሪናበፓራኖይድ ፐርሶናሊቲ ዲስኦርደርየተጠቁ ሰዎች የሚንከባከቡት፤የድሮ ግሎሪ (ልዕልነት) የሚዘክርመስያኒክድርጅት ነው። የካቲት 11 ለኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር ወደቦችዋን ያስነጠቀ፤በተለይ ደግም የካቲት 11 ለአማራ ሕብረተሰብ የምጽኣት ዘመን ያመጣ በጣም አደገኛ የፋሺሰቶች ቀን በዓል ስለሆነ ዛሬ የአብይ አሕመድ ወኪል ሆኖ  በትግራይ የብልጽግና ፓርቲ ተጠሪ ነው የሚባልለት በብዙ ወያኔ በሚቃወሙ በብዙ ደናቁርት ትግሬዎች የሚወደስ አዲስ አብዮተኛ እየተባለ የሚወደሰው ዶ/ር አብርሃም በላይ ልነግረው የምፈልገው የካቲት 11 ቀን ማለት የትግሬዎች የግዛት ማስፋፋት እና በትግሬዎች የሥልጣን ጠቅላይነት እና ሃያልንት ስሜት የተቃኘ በዓል ነው።

 ወያኔ የተጠቀመው የጎሳ ፋሺዝም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊ ትግሬዎች አፍርቷል።  ተካተዮቹ በትግሬነታቸው እንደተጠቁ በማሳመን፤ ጠንካራ ድርጅት መስርቶ አማራን በጠላትነት መድቦ፤ ለትግራይ ድህነት አማራ ተጠያቂ በማድረግ፤ አማራን ጨፍጭፎ፤ አማራዎች የሚኖሩባቸው ብዙ ቦታዎች ወደ ትግሬ መሬት በመከለል፤ (የተቀሩትም በሉሎች ጎሳዎች ክልል ሥር እንዲጠቃለሉ በማድረግ) የፋሺዝም ዋናው የመሬት መስፋፋት መለኪያው በተግባር አሳይቶናል። የካቲት 11 ቀን የተመሰረተው ይህ ድርጅት የአካባቢውን የጥንትን ሥልጣኔ ባሕል ታሪክ ማንነት፤ጀግንነት (መስያኒክ) ተከታዮቹን እያስታወሰ፡ ሁሉ ኩራት በአማራዎች እንደተደመሰሰና እንደተነጠቀ በማስተማር፤ ያንን ተነጠቅን የሚለው ኩራት ፤ መሬትና ታሪክ ፤ መመለስቀዳሚ ትግላችን ነው” ብሎ በማስተማሩ ዘመቻ ውስጥ የትግሬ ምሁራን የትግራይን ሕዝብ በማሳሳት፤በተለይ ወጣቱን ትውልድ አክራሪ የተግራዋይነት የነገድ ፍቅር አንዲከተል በማስተማር ታሪክ የማይፍቀው ወንጀል ሠርተዋል።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል…………..
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)