Thursday, February 29, 2024

በሻለቃ ዳዊትና በእስክንድር ላይ የሚዘምቱ የፖለቲካ ባለጌዎች ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 2/29/24

 

በሻለቃ ዳዊትና በእስክንድር ላይ የሚዘምቱ የፖለቲካ ባለጌዎች

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

2/29/24

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ  ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል።

ያንን በማድረጋቸው  “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ :- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል።

“ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>>

አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወየኔም ከኦነጎችም  እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው  የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበረው “ከጠ/ቅላይ ሚኒስትሩ በታች ያሉት እንጂ እሳቸው ተገቢው ሥራቸው እየሰሩ ነው…>> እያለ አየሩን ሲየቆሽሽ የነበረው (በቅርቡ ደግሞ ከኔ አልፎ  ዘመድኩን በቀለ (ነጭ ነጭዋን) ጋር የተጣመደው “ጎንደር ለጎንደሬዎች” ባዩ ዶ/ር አምሳሉ የተባለው በሻቃው ላይ አፉን የሚከፍተውና እና ሌለው ደግሞ እንዲሁ በወያኔ ዘመን “የኦነግ ባንዴራም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም እኩል አሸብርቁ” እያለ ሲያውከን የነበረው ዛሬ የአብይ አሕመድ ካድሬ ሆኖ “የሃቅና ሳቅ” ዩቱብ አዘጋጅ “አበበ ቶላ” (ቶኩቻው) የተባለው እንግሊዝ አገር የሚኖሮው  <<የፖለቲካ ባለጌ>> ፤ ባልተገራ ምላሱ በውትድርና እና በትምህርት እንዲሁም አገራቸውን ያገለገሉበት የውትድርና ማዕርጋቸውን በማንኳሰስ “ሹሉቃ” እያለ የመንደር ስድብ ሲዘልፋቸው መስማት እጅግ ከገረመኝ የሰሞኑ ክስተት አንዱ ነው።  ሌሎችም አሉ።

ሻለቃ ዳዊትን ብቻ ሳይሆን የተጠመዱት <<ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋንም>> ሳይቀር “እስክንድር ያለ ቦታው ነው የገባው፤ እዛ በረሃ ጠመንጃ ይዞ ከመታገል ይልቅ እዚህ መጥቶ ለተጋዮቹ የንዋይ (የገንዘብ) ድጋፍ ሰጪ ቢሆን የረባ አስተዋጽኦ ያደርግ ነበር>> ሲል ያደመጥኩት እጅግ የማከብረው ተመራማሪው ወጣት ምሁሩ የጥንቱ ወዳጄ <<አቻምየለህ ታምሩ>> እንዴት ወደ እዚህ ዓይነት የወረደ ግምገማ እንደገባ አስደግጦኛል። ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃብታሙም በበኩሉ “የእስክንድር ዓላማ ምንድነው?” ሲሉ አቻምየለህ ታምሩ ጋር አብረው ጠይቋል።  እስክንድር ለምን ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ እኛ እና ጠያቂዎቹ ያልተቀበልነው መከራ የተቀበለ አስገራሚ የዘመናችን አርበኛ እስክንድር “ኣላማው ምንድነው?” ትበሎ ሲጠየቅ እውነት እስክንድር ለምን ተገፍቶ እዛ ጫካ እንደገባ ዓላማው ለምን እና ለማን ተብሎ ፍዳውን እያየ እንዳለ “ሰሚ አጥቶ ለነበረው ለአማራው ተስፋ ፤መመኪያ ፤ የሞራልና የጉልበት አለኝታ እየሆነ እንደሆነ እውን ይጠፋቸዋል? ዓለማው ምንድነው!? ደጋግሞ እስክንድር ያዳመጠ ሰው እንዴት ዓላማው እስካሁን አልበራለትም? ከጥፋት ራስን መከላከል እንዴት የዓላማ ጥያቄ ያስነሳል? ወይ ከዚህ ከዲያስፖራ ምቾት ለቅቀን እዛው ጫካ እራሳችንን እናግኝ ካልሆነ “መከራቸውን እያዩ ላሉ ራሳቸውን ከመጥቃት ለማዳን የሚታገሉ ዜጎችን ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ነውር ነው። በዙርያቸው ለግንጠላ እየሄዱ ባሉ ታጣቂዎች የተከበው የአማራ ሕዝብና ሕዝባቸው በጥቃት ቀለበት የገባባቸው ታጋዮች፤ ዓላማቸው ምንም ይሁን ምን ለጥያቄ የሚቀርቡ አይደሉም።

እኛ በተደንደላቀቀ አልጋ ተኝተን ግማሹ እስር ቤት በካቲና ታስሮ ግማሹ በየጫካው በጥይት እየተቆላ እኛ ዩ ቱብ ላይ በጋለ ብረት በሚጠበሱ በታሰሩትና በጥይት በሚቆሉት ላይ ዓላማን ማስነሳት ዕብደት ወይስ ውቀት? እነ መስከረም አበራ እና በሺዎቹ እመጫቶች ልጆቻቸውን ጥለው በጭለማ ታስረዋል፤ እነዚህን ለማስለቀቅ በሚጥሩ አርበኞች ላይ መሳለቅና ዓላማቸውን መጠየቅ የተመቻቸው ሰዎች ጥያቄ ነው። እግዚአብሔርን እንፍራ እንጂ። እኔ ትግሬ ነኝ፤ ትግራይ ምድር ውስጥ በየአዳራሹ የሚነገረው ስለግንጠላ ነው፤ ብታደምጧቸው ትደነግጡና ዕብደት ወይስ ድንቁርና ትላላችሁ። ጉዟቸው ስለ ግንጠላና ዛቻ እንጂ ስለ አንድነት አይደለም። ኦሮሞዎቹም እንደዚያ፤ በነዚህ መሃል እንደ “ሳንድዊች” የታጠፈው ሕዝብ እንደሚዳቓ ያለ ተከላካይ ቆሞ በሁለም እጣጫ ይለቅ? የነዚህ ታጋዮች ዓላማ መጠየቅ ፈጣሪን የደፈርነው መስሎ አልታያችሁም?

መስክሩላቸው ብንባል <<አፋቸው ማይክሮፎን ላይ መትከል እንጂ “ተግዳሮትን” (ቻለንጅን) መቋቋም የማይችሉትን እንደ እነ ኤርምያስ ለገሰ እና የፖለቲካ ባለጌው “አበበ ተላ” (ቶኪቻው) በሻለቃውና በእስክንድር ትግል ላይ “ከስራ መልስ የድብርታቸው ማስወገጃ በማድረግ” በየዩቱቡ ተድጠው  የነዚህ ሰዎች ትግልና ማዕረጋቸውን ማብጠልጠል ስናደምጥ ‘ዩ ቱብ’ የሚባለው እጅግ ሲበዛ የፖለቲካ ባለጌወችን የልብ ልብ ሰጥቷቸው በታጋዮች ላይ ሲቀልዱ ማድመጥ እውነትም <<ኢትዮጵያ አገሬ  መኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ>> የሚባለው እውነት ነው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)