Sunday, September 13, 2015

የአመቱ ምርጥ ባለጌ ሰው!

የአመቱ ምርጥ ባለጌ ሰው!
መስከረም 1/2008 ዐ.ም አዲስ አመት የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ “የአመቱ ባለጌ ሰው” አፈላልጎ በብልግናው የመረጠው “የአመቱ ባለጌ ሰው” ባሕርዳር የሚኖረው ፎቶግራፉ ከላይ የሚታዬው “አለምነህ መኮንን” /ን ነው። አለምነህ መኮንን በጎሳው “አማራ” ነው። ወያኔ “አማራ ክልል” ብሎ ጸረ አማራ አጀንዳው ለማራመድ እንዲመቸው ባለ ሁለቱ ሕበረ ቀለም (ቢጫና ቀይ) ባንዴራውን በቅጅ አዘጋጅቶ፤ እንደ ግኡዝ ዕጭቃ አድቦልቡሎ ወያኔ ከሰራቸው፤ስብእናቸውን አውልቆ ጠርቦ በምስሉ የቀረጻቸው፤እራሳቸወን የማይመስሉ፤ ትንንሽ ሕሊና ያላቸውን ሰዎችን ትግራይ ሜዳ ውስጥ የሕሊና አጠባ አድርጎ ተሸክሞአቸው አማራውን ሕብረተሰብ  እንዲዘልፉለት ጎጃም ክ/ሐገር ባሕርዳር ውስጥ ከሾማቸው የወያኔ ብአዴን አማራዎች መካካል አለምነህ መኮንን ነው።

አለምነህ መኮንን ከነ ደመቀ እና ከነ ወንድወሰን የመሳሰሉ አማራዎች ሆኖ የወያኔ አሽከር ሆኖው ወያኔ ሲሞት ከወያኔ ጋር ለመሞት ከተዘጋጁ የአማራን ሕብረተሰብ ከሚያስሰድቡና ከሚሳደቡት ማፈሪያዎቹ  አንዱ ነው። ወያኔ እንደ አፓርታይድ በቋንቋ ክልሎ ካዘጋጃቸው አማራ ብሎ ከሚጠራቸው “ክፍለ አፓርታይድ” አካባቢዎች አንዱ ከሆነው “የአማራ ክልል” ምክትል ፕረዚዳንት እና የብአዴን ጽ/በት ሓለፊ ነው። አለቆቹ አማራን ስለዘለፈላቸው አሜሪካ ድረስ ልከው ሰሞኑን ካንሳስ ሲቲ አየር ማረፊያ ጣቢያ እንደታዬ  ዜናዎች እየዘገቡ ነው።

ይህ ሰው አባቱን እናቱን ዘመዶቹን በጠቅላላ አማራውን ሕብረተሰብ

“ስንፋጭ” ትምክህት የተጠናወተው፡፤ትምክሕትነቱን ያልተወው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር፤ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ መኖር የማይችል፤ የሸተተው እግሩ እንዳይሸት ከጫማው ስር ‘የባሕር ዛፍ ቅጠል ያደረግበታል”፤ /ዚስ ኢዝ ቴክኖሎጂ!………ባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ልሃጩን ማራገፍ አለበት! ይኼ ላሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ማንኛወም ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መነሻው አማራ ክልል ነው። ይላል። ምክንያቱንም ሲገልጽ  “ትምክህተኝነትን አንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብም እየተመገበ ያቅራራል።”  እያለ ተሰብሳቢ ካድሬዎቹን ሳቅ በሳቅ እያደረገ በሕዝብ ክብር ሲያላግጥ በድምፁ የተቀዳ ዋልጌ ግለሰብ ነው። 

ይህ ወላጆቹን እና ሕዝብን የሚሰድብ ስድ ግለሰብ፤ “አማራው ይህ ሰንፋጭ ትምክሕቱ በቤንሻንጉል እና በተቀሩት አካባቢዎች ለመሰደድ ምክንያት ሆኖታል።ሲል ተሳድቧል። ያውም እዛው በአማራዎች  አገር ፤ አማራዎች በሚኖሩበት በባሕርዳር ከተማ! ወይ ዘመን! አያሰማን ጉድ የለ!

ከትንሽም ትንሽ ሰው መሆኑን የሚያሳይ “ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ፤ የተቀዳው ድምፅ ይፋ ሲሆን ‘የሚመልሰው በማጣቱ ተደናግጦ ለካድሬዎቹ ጋዜጠኞቹን ሰብስቦ (አፋጥጠው ከነማስረጃው ሊወጥሩት አንደማይችሉ ስላወቀ)፤ ይህ እኔ አልተናገርኩም፤ የቴክኖሎጂ “የቆርጦ ቀጥል ስራ ነው” ሲል ንግግሩ ከሚያሳውቅበት ድንጋጤ ጋር ወዲያ ወዲህ ሲረግጥና ሲዘላብድ ተደምጧል። አለቆቹና ካድሬ ጸሐፊዎቹ በወያኔ ድረገፆች ላይ (አውራምባ ድረገጽ፤ትግራይ ኦን ላይን፤አይጋ… ላይ የተጻፈውን ተመልከቱት)፤ እሱን ለመከላከል ሲሉ ያልፈነቀሉት የሽፋን ጥረት አልነበረም። ሆኖም አገር ውስጥ የሚገኘው ‘ዩዲጀ’ የተባለው ፓርቲ የፔትሽን /የፌርማ የማሰባሰብን ስራ በመስራት ከሥራው እንዲባረር ቢጥርም፤ “ክቡር መሪያችን ከሞታቸው በፊት….” እያለ ጌታውን መለስ ዜናዊን ሲያሞካሽ ያደመጡት ጌቶቹ ከሥራው ሊያግዱት አልፈለጉም እና እዛው ሆኖ አማራውን ሕዝብ መዝለፉን እንዲቀጥል አድርገዋል። ሆኖም የባሕር ዳር ሕዝብ በነቂስ በመውጣት “ከባዶ ጭንቅላት፤ ባዶ እግር ይሻላል!” የሚል መፈከር ይዘው አዳባባይ ወጥተው፤ “ስድ አደግ”፤ “ሙጀሊያም አፍ” እና “የወያኔ መጸዳጃ የሚል ቅጥያ ስም  ተሰጥቶታል።      

ይህ ስድ አደግ’ ሙጀሊያም፤ጉርፉጥ አፍ (ግረፉጥ ማለት ትግርኛ ነው፤ ባለጌ ያልታረመ ፤ ማለት ነው” አማራውን ሕዝብ የዘለፈበትን ስድ አንደበቱን ለማድመጥ የሚከተለውን የአውዲዮ አድራሻ ይጫኑ። የአመቱ ባለጌ ሰው እንዴት እንደመረጥኩት መረጃው እራሱ ይናገራል። አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)፤ በዚህ ሦሰት ቀን የሚወጣ ሌላ ዝግጅት ስላለ፤ እሱንም እንዳያመልጣችሁ ይሁን። “የአመቱ ባለጌ ሰው” ሲናገር በአንደበቱ  ይኼውና አድምጡ። ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት የሕሊና ድኩማን ተሸክማ ትገኛለች።
Leaked audio:- Alemneh Mekonnen who is TPLF puppet Amhara region leader, insulting the Amhara people