Friday, September 30, 2022

የሞት ፓስፖርት፡ የሩዋንዳ መታወቂያ ታሪክ እና የኢትዮጵያው የሞት ፓስፖትር የማንነት መታወቂያ ተመሳሳይነት ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 9/30/2022

 

የሞት ፓስፖርት፡ የሩዋንዳ መታወቂያ ታሪክ እና የኢትዮጵያው የሞት ፓስፖትር የማንነት መታወቂያ ተመሳሳይነት

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 9/30/2022

እዚህ የለጠፍኩት የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያ ተወላጅ ቅጽ ሞምያ ተመልከቱት፡ ተራ ቁጥር 6 “ስትመለከቱት ከዚህ ከውጭ ኤምባሲ ይህንን ቅጽ ሞልታችሁ ስትሄዱ እንደኔው በፖለቲካ ቂመኞች የተከበባችሁ ከሆናችሁ ኤምባሲው እና እዛው አገር ውስጥ በፀጥታ /ቤት ሰራ የተኮለኰሉ  ቀበኞች  (ልክ በኦሮሞ ክልል የሰብአዊ መብት /ቤት ቅርንጫፍ ሰሞኑን እንዳደረገው ለኦነግ የሰጠው ሽፋን ማለት ነው) በመነጋጋር ስማችሁ እና የጎሳ ማንነታችሁን በማረጋገጥ እና ማን መሆንክን ሲያረጋግጡ ታፍነህ ወይንም በመርዝ ትገደላለህ ማለት ነው። ብዙ ሰዎች በዚህ የተጠቁ አሉ። ለዚህ ነው አገሬን ማየት የማልችለው። ስርዓቱ ለግድያ የሚያመቻች ሰረኛ ሰርዓት ነው የምለው እና ይህንን ጽሑፍ የማቀርበው ለዚህ ነው።

ይህ የማቀርብላችሁየሞት ፓስፖርት የሚባለው የሩዋንዳ የማንነት መታወቂያ ታሪክ የቀረበው Jean de la Croix Tabaro በተባለ July 13, 2015 KT Press በእንግሊዝኛ የታተመ ለአማርኛ አንባቢዎች አንደሚመች ተርጉሜ የቀረበኩት ነው። ይህ ታሪክ ስታነብቡ በወያኔ እና አሁን ደግሞ በብልጽግና ኦሮሙማው ፓርቲ የሚመራው የኢትዮጵያ የማንነት መታወቂያ ለስንቶቹ ዜጎች የሞት ፓስፖርት ሆኖ በዕቅድ እንደተዘጋጀ ማወቅ ትችላላችሁ። መታወቂያቸው እየታየ ብዙ አማራዎች እንደተጨፈጨፉ ዛሬም ያላባራው የዘር ፍጅት ማንነታቸው እየታየ እየታደኑ ያሉት አማራዎች በዜና እየሰማችሁት ያለው ማስረጃ ነው።

የሞት ፓስፖርት፡ የሩዋንዳ የማንነት መታወቂያ ታሪክ

Jean de la Croix Tabaro July 13, 2015 KT Press

... 1929 የቤልጂየም ቅኝ ገዥ የሩዋንዳ ገዥ ሉዊስ ጆሴፍ ፖስትያ ሁሉንም ባህላዊ አለቆች እና የማህበረሰብ አባላትን 'ለድንገተኛ ስብሰባ' ጠራ። በምስጢር ለሶስት አመታት ሲሰራበት የነበረውፕሮጀክትእንደተጠናቀቀ  በዙርያው የነበሩ አለቆች  የዕቅዱ  ቅጂ እንዲይዙ ጋበዘቸው።

በኋላ 1930 ማህበረሰቡ፣ የመንደር አለቆችን ጨምሮ፣ በቤልጂየም የምስራቅ-መካከለኛው አፍሪካ ቅኝ ግዛቶች ጥቅም ላይ የሚውሉትን የአስተዳደር ቋንቋዎች በፈረንሳይ እና በፍሌሚሽ የተጻፈውንቡኩየተባለውን ባለ 8 ገጽ ቡክሌት እንዲሰጣቸው ተደረገ።ቡክሌቱ ብዙ ዝርዝሮችን ይዟል፣ ነገር ግን በጣም በአስፈላጊ ሁኔታ የማህበረሰቡን አባላት ጎሳዎች (ሁቱ፣ ቱትሲ ወይም ትዋ) አጉልቶ ያተኮረ ነው። ያልነበረው የጎሳ ሽንሸና በጎሳ ምደባ ተጀመረ።

እድሜው 18 እና ከዚያ በላይ ላለውሩዋንዳዊ መታወቂያ’ (ኢንዳንጋሙንቱ) እንዲይዝ ግዴታ ነበር።"ይህን አለማድረግ ከቅኝ ገዥዎች የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ቅጣትን ያስከትላል። ይህንን ያላደረገ ሰው በተቀጠቀጠ የሸንኮራ አገዳ ስምንት ጅራፍ ይገረፋል።"

ነገር ግን 1962 የቅኝ ገዥው መንግስት ከወደቀ በኋላ የሪፐብሊኩ መንግስታት መታወቂያውን ጠብቀው ከቅኝ ገዢዎች ከወጡ በኋላም ሩዋንዳውያን በጎሳ እንዲከፋፈሉ በማድረግ በቱትሲ ላይ መለያየትን አመቻችቶ የተለያዩ አገልግሎቶችን እና መብቶችን እንዲነፈግ አድርጓል።

... 1981 ፕሬዘደንት ጁቬናል ሀቢያሪማና ሌላ መታወቂያ፣ ባለአራት ገፅ ትንሽ ካርድ አስተዋውቋል፣ ነገር ግን የያዛውን ጎሳ በመጠበቅ እናጮክ ብሎ የሚናገር መታወቂያነበር።ይህ በጎሳ ፖላራይዝድ (እርስ በርስ ውጥረት ውስጥ) ሆኖ እንዲቀጥል የተደረገ የሩዋንዳ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል፣ ይህም በኮታ ስርዓት የሁቱዎች የትምህርት እና የስራ እድል 90% እንዲመደብላቸው ሲደረግ፣ ቱትሲዎች ግን 10% ብቻ ተፈቅዶላቸዋል። ይህንን እውን ለማድረግ መታወቂያው ላይ የጎሳው ማንነቱ ይዞ እንዲቀጥል በማድረግ በዚያው እየታየ ቀጠለ።

ይህ መታወቂያ በስራ ቅጥር መድልዎ ብቻ ሳይሆን ወደ ግድያ ተሸጋጋረ። ... 1994 በተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል መታወቂያዎች  እየታዩ ቱትሲዎችን እያስቆሙ እንዳይተላለፉ መንገድ በመዝጋት ፣በስራ ቦታዎች በማስጨነቅ እና በመጨረሻም በጅምላ ገድለዋቸዋል። ማወቅ ያለብን የሩዋንዳ መላው ዜጎች የሚናገሩት ቋንቋ ሁለም አንድ ቋንቋ ነው። ስለዚህ ለይቶ ለመቅጠርና ለመፍጀት ማድረግ የነበረባቸው መታወቂያቸው ላይነገድ/ጎሳ/የሚለውን መመዝገብ ነበር (ለዚህ ነው ጮክ ብሎ የሚናገር መታወቂያ የሚል ከላይ ያስነበብኳችሁ) ይህንን መታወቂያ እያዩ ለይቶ መግደል በወሬ የሰማችቻንታል ሙክማናየተባለቺው የቱትሲ ነገድ እንዲህ ትላለች፦

ገዳዮቹ የእኔን ብሔር ለይተው እንዳያውቁና እንዳይገድሉኝ መንገድ ላይ ስደርስ መታወቂያዬን ለማኘክ ተገድጃለሁሲል ለኬቲ ፕሬስ ታሪኳን ተናገረች። ሙክማና በዚህ መደናገጥ የፈጠረቺው ዘዴየኢንተርሃምዌ ሚሊሻዎችንበማደናገር ከመገደል በማምለጥ፤ወዲያውኑ ጫካ ውስጥ ተደበቀች እና በሶስተኛው ምሽት ምግብ ሳትበላ እጇን ለመስጠት ወሰነች።

እንዲህም ትላለች፦

መጀመሪያ  ያገኘሁት ሰው ደበቀኝ፣ ነገር ግን ኢንተርሃምዌ ከአንድ ሳምንት በኋላ መደበቄን ሊያውቅ እንደሚችል ስላወቅኩአንዲት የሰው ርህራሄ ያላት ሀቱ ሴትዮ ያለሁበትን አደገኛ እና አሳዛኝ ሁኔታየን ስላሳዘናት በጎ አድራጊየ  ወደ ጫካ ወስዳ ከዛም እየመገበች እስከ ጁላይ 1994 ድረስ የዘር ማጥፋት ዘመቻው ተቋርጦ፤ የዘር ማጥፋት አገዛዝ እስከተገረሰሰ ድረስ ደብቃ አቆየቺኝ። ትላለች። ይህ መታወቂያ የማንንት ነጋሪ ባይኖር ኖሮ ብዙ ሰው ከጭፍጨፋ ይድን እንደነበረ ስትል ትናገራለች።

... 1996 የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር (RPF) ኢንኮታኒ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ካቆመ በኋላ ፣የያዙት የጎሳ ዝርዝሮች የሌሉበት አዲስ መታወቂያ ካርድ (አረንጓዴ ማኒላ ወረቀት) ተጀመረ። እና 2008, የወረቀት መታወቂያው አሁን ባለው የኤሌክትሮኒክ ካርድ ተተካ። ዛሬ ሩዋንዳውያን የሚይዙት መታወቂያ ማንንም በዘራቸው/በነገዳቸው/ መሰረት ያላነጣጠረ መታወቂያ ነው።

አዲሱስማርት መታወቂያያዢው፣ የተወለደበት ቀን፣ ጾታ እና የወጣበት ቦታ (የትውልድ ቦታ ሳይሆን) “ስም ብቻይዟል።አዲሱ መታወቂያ ($3) በውሃ መከላከያ ቁስ ላይ ታትሟል። የተያዥውን መረጃ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ለማግኘት ባር ኮድ አለው። ሩዋንዳውያን መታወቂያውን የሚያገኙት በድጎማ Rwf 500 ነው። ከስድስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ስማርት መታወቂያ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። የምስራቅ አፍሪካ ክልላዊ ውህደት እየጠነከረ ሲሄድ የሩዋንዳ ስማርት መታወቂያ ለክልላዊ አባል ሀገራት ትክክለኛ የጉዞ ሰነድ ነው። ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ብሩንዲ እና ደቡብ ሱዳን። ሆኖም የድሮ መታወቂያ ካርድ ከኮሚዩኒቲ ወደ ሌላ ለመጓዝ እንኳን በቂ አልነበረም። ለምሳሌ አንድ ሰው ከሩሱሞ (ምስራቅ) ወደ ዋና ከተማዋ ኪጋሊ ለመጓዝ ማለፊያ ሰነድ ያስፈልገዋል።

ከመቶ ዓመት ገደማ በኋላ፣ ዛሬ፣ኢቡኩ ከገባ በኋላ፣ማንም ሰው በነገዳችን/ጎሳችን/ በየትም ቦታ ተከታትሎ እንዲያጠቃን የማይፈቅድ መታወቂያ ካርድ ይዘናልትላላች ድሮ በክፉ ወቀት መታወቂያዋን አኝካ ከሞት የተረፈቺው መኩማን። ኢትዮጵያዊያንስ ከዚህ አፓርታይዳዊ መታወቂያ ለምን ይተቅማል ተብሎ ወያኔዎች ከሩዋንዳ ማሳለቂያው መሳሪያ የነበረው እኛ ላይ ለምን በአዋጅ ተገበሩት?

ለሕጋዊ  የብሄራዊ ማንነት መታወቂያም ሆነ ለሲቪል ምዝገባ ሥርዓት ማቋቋሚያ ሕጋዊ መሠረት በአዋጅ ቁጥር 760/2012 (በፈረንጅ)

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የዲጂታል ማንነት አዋጅ የሚጠይቀውን አሟልቶ መመዝገብ ግዴታ ነው። 

 አመልካቾች የሚከተለውን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡- ይላል። ጎሳ የሚለው ትመለከታላችሁ፡

. ሙሉ ስም አያትን ጨምሮ፤ 3

. ልዩ መታወቂያ, ካለ;

. የወላጆች ሙሉ ስም እና ዜግነት;

. የትውልድ ቀን እና ቦታ;

. ጾታ እና የጋብቻ ሁኔታ;

. ዋና መኖሪያ እና ሥራ;

. የትውልድ ጎሳ እና ሃይማኖት; (ethnic origin and religion)

. ፎቶግራፍ እና የጣት አሻራ;

እያለ ለኢትዮጵያዊያን የተከሸነልን የፍጅት ግብዣም ይህንን መታወቂያ በማዘጋጀት የተከናወነ ነበር።

ሰነዱን ብትቀባበሉት አስተማሪ ነው።

አመሰግናለሁ ትርጉም  ጌታቸው ረዳ